18/11/2024
የአየር መንገዳችን ስም ሲነሳ አብረው የሚነሱት ካ ፕ ቴ ን መ ሐ መ ድ አ ህ መ ድ
¤ ¤ ¤
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለአሁኑ ስምና ዝናው ካበቁት ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ካፕቴን መሐመድ አህመድ ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቋቋመው በ1946 ዓም ነበር። አየር መንገዱ በተቋቋመት ዘመን የበረራ መስመሮቹ ውስን የነበሩ ሲሆን ይኸውም ከአአ - ካይሮ እና ደርሶ መልስ ነበር።
በ1963 ዓም ካፒቴን መሐመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ካፕቴኑ በሁለቱም ስርዓት ማለትም በንጉሳዊውና በደርግ ስርዓት አየር መንገዱን በዋና ስራ አስኪያጅነት አስተዳድረዋል። በዚህም ወቅት አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ተፎካካሪ እንዲሆንና ዘመናዊነቱ እንደተጠቀ እንዲቀጥል በማድረግ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።...
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን / የኢትዮጵያን አየር መንገድ ወደ ዘመናዊና ተወዳዳሪ አየር መንገድ እንዲሸጋገር መሰረት ከጣሉት የመጀመሪያዎቹ CEO ዎች ውስጥ ካፕቴን መሐመድ አህመድ አንዱና በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው። ከ1963 ዓም ወዲህ አየር መንገዱ ዘመናዊና ግዙፍ የመጓጓዣ አይሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ በመግዛት የበረራ አድማሱን ወደ የተለያዩ አፍሪካ አገራት፣ መካለኛው ምስራቅ እንዲሁም እስከ ቻይናና አውሮፖ ድረስ እንዲያስፋፋ አድርጓል።....
ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ የአየር መንገዱ ህልውና አደጋ ላይ ወድቆ እንደነበር የሚታወስ ነው። ያ ዘመን ለአየር መንገዳችን ወሳኝ ጊዜ ነበር። ደርግ ስልጣን ላይ በወጣ ማግስት የሚከተለው መርህ የሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለምን እንደሆነ አወጀ። ይህ አየር መንገዱ የአውሮፕላን አቅራቢው ከሆነው የቦይንግ ኩባንያ ጋር ያለውን ግንኙነት ፈተና ውስጥ የሚጥል ሆነ። በዚህ ጊዜ ስራ አስኪያጁ በደርጉ ሊቀመንበር መንግስቱ ኃ/ ማሪያም መመሪያ መሰረት አየር መንገዱ የሚገለገልበት የአሜሪካን ሰራሽ ቦይንግ አይሮፕላን በሶቭየቶቹ አንቶኖቭ እንዲተካ የሚያስገድድ ትእዛዝ ደረሳቸው። ሆኖም ግን ካፕቴን መሐመድ እምቢ አሻፈረኝ አሉ።
በድርጅቱ አስራር ውስጥ ጣልቃ መግባት ድርጅቱን ለኪሳራ እንደሚዳርግና ከገበያ ውጪ እንደሚያደርግ ለሊቀመንበሩ አሳሰቡ። በመጨረሺያም ምክረ ሀሳቡ አሳማኝ ሆኖ በመገኘቱ ስራቸውን ያለምንም ተጽዕኖ እንዲሰሩ ተፈቀደላቸው። በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ ጥራት ያለውና ዘመናዊ አገልግሎት መስጠቱን ቀጠለ።
ካፕቴን መሐመድ አህመድ አትራፊ ሆኖ በቀጠለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በስራ አስኪያጅነት እስከ 1990 ድረስ በመስራት ከዚያም በስራ ዕድገት ወደ አፍሪካ አቪዬሽን ወደ ናይሮቢ ተዛውረው በመስራትም አገልግለው በአሁኑ ወቅት በጡረታ ላይ የሚገኙ ሰው ናቸው ::
_____
የእኚህን ሰው ታሪክ በደንብ ለማወቅ የፍሰሀ ደስታን መፅሀፍ ማንበብ ጠቃሚ ነው። አየር መንገዱን በዚያ ዘመን እንዴት ከኪሳራ ወደ ትርፍማና ዘመናዊ ድርጅት እደቀየሩት መረዳት ይቻላል።