EBC-መዝናኛ

EBC-መዝናኛ Ethiopian Broadcasting Corporation is a 24 hour working public media.

16 ቀናት ብቻ ቀሩ!!! 📢ዝግጁ ናችሁ!? በአንድነት ድምቅ የምንልበት ቀን 16 ቀናት ብቻ ይቀሩታል ሀገር በ10ኪ.ሜ 2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ      ...
07/11/2025

16 ቀናት ብቻ ቀሩ!!! 📢

ዝግጁ ናችሁ!?

በአንድነት ድምቅ የምንልበት ቀን 16 ቀናት ብቻ ይቀሩታል

ሀገር በ10ኪ.ሜ

2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ

ማስታወቂያ 17 ቀናት ብቻ ቀሩ!!! 📢ዝግጁ ናችሁ!? በአንድነት ድምቅ የምንልበት ቀን 17 ቀናት ብቻ ይቀሩታል ሀገር በ10ኪ.ሜ. 2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ...
06/11/2025

ማስታወቂያ

17 ቀናት ብቻ ቀሩ!!! 📢

ዝግጁ ናችሁ!?

በአንድነት ድምቅ የምንልበት ቀን 17 ቀናት ብቻ ይቀሩታል

ሀገር በ10ኪ.ሜ.

2018 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ

በሰርጉ ቀን ኮቱ ላይ ማስታወቂያ ሰርቶ የሰርግ ወጪውን የሸፈነው ሙሽራ*******ፈረንሳዊው ግለሰብ እጮኛውን ለማግባት ይፈልግና ለሰርጉ ወጪ የሚሆን ገንዘብ ያጥረዋል።እጮኛው ደግሞ ሰርጉ በአ...
06/11/2025

በሰርጉ ቀን ኮቱ ላይ ማስታወቂያ ሰርቶ የሰርግ ወጪውን የሸፈነው ሙሽራ
*******

ፈረንሳዊው ግለሰብ እጮኛውን ለማግባት ይፈልግና ለሰርጉ ወጪ የሚሆን ገንዘብ ያጥረዋል።

እጮኛው ደግሞ ሰርጉ በአደባባይ ተደግሶ እንዲጋቡ ትፈልጋለች።

ታድያ ይህ ሰው አንድ መላ መጣለት፤ ወዲያውም በኤክስ ገፁ ላይ ለሠርግ ቀኑ በሚለብሰው ኮት ላይ ለድርጅቶች የሚሆን የማስታወቂያ ቦታ እንደሚኖረው አስታወቀ።

ሀሳቡ በፍጥነት ይሰራጭና 26 ኩባንያዎች ማስታወቂያውን እንዲሰራላቸው ጠይቀውት በአጠቃላይም 10 ሺ ዶላር አገኘ።

በቅርቡም የጥንዶቹ ጋብቻ እንግዶች ፊት ሲፈፀም ግለሰቡ በቃሉ መሰረት የ26 የድርጅቶች አርማ የያዘውን ኮቱን ለብሶ የደስታውን ቀን አሳለፈ።

ታዲያ የሰርግ ወጪውን እንዲሸፍን ያስቻለው ይህ የሙሽራው እቅድ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አስገኝቶለታል።

አንድ የሥራ ፈጣሪ ድርጅትም የግለሰቡን ጠንክራ የሥራ አቅም ተመልክቶ በኒውዮርክ በሚገኝ ኩባንያ ውስጥ የሥራ ዕድል ሰጥቶታል።

ግለሰቡም ከሚወዳት ሴት ጋር ጋብቻ ለመፈፀም በአመጣው ሃሳብ ዘላቂ ገቢ የሚያገኝበትን እንጀራውንም ማብሰል ችሏል።

በሴራን ታደሰ

06/11/2025

መሳፍንት አዳነ
”አልተለየሽኝም ”
የኢትዮጵያ አይዶል ጉዞ ጥብበን ፍለጋ ባሕር ዳር ክፍል 3
Full Program on: https://youtu.be/rWcP4l5TFXs

ሩሲያ ወላጆች የልጆቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል የሚችሉበትን ሲም ካርድ ይፋ አደረገች*******ወላጆች የልጆቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል የሚችሉበት ሲም ካርድ ይፋ መደረጉን የሩሲያ ዲጂታል ል...
06/11/2025

ሩሲያ ወላጆች የልጆቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል የሚችሉበትን ሲም ካርድ ይፋ አደረገች
*******

ወላጆች የልጆቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል የሚችሉበት ሲም ካርድ ይፋ መደረጉን የሩሲያ ዲጂታል ልማት፣ ኮሙኒኬሽን እና መገናኛ ብዙኃን ሚኒስትር ማክሱት ሻዳዬቭ አስታውቀዋል።

ሲም ካርዱ የሕፃናት ደኅንነትን ለመጠበቅ ታስቦ የተዘጋጀው ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ሲም ካርዱ ከ14 ዓመት በታች የሆኑ አዳጊዎች ተገቢ ያልሆኑ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ይዘቶችን እና የማይመከሩ ድረ-ገጾችን ማየት እንዳይችሉ የሚገድብ እንደሆነም ተገልጿል።

ወላጆች ሲም ካርዱ የሚልክላቸውን መረጃ ተጠቅመው ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ልጆቻቸው ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንደሚችሉም ተመላክቷል።

ሲም ካርዱ የሚሰጠው በወላጆች ፈቃድ ብቻ መሆኑን የዘገበው ቻይና ኒውስ ነው።

ይሁንና ወላጆች የልጆቻቸውን የእንቅስቃሴ መረጃ የሚከታተል ሌላ አካል ከፈለጉ በራሳቸው ፈቃድ ኃላፊነቱን መስጠት ይችላሉ ተብሏል።

በሔለን ተስፋዬ

ስኬተሩ አሳማ 10 ሜትር በመጓዝ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበ*******ኖርበርት የተሰኘ አሳማ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ በጊነስ ዎርልድ መዝገብ ላይ መስፈሩ ተሰምቷል።አ...
06/11/2025

ስኬተሩ አሳማ 10 ሜትር በመጓዝ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበ
*******

ኖርበርት የተሰኘ አሳማ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ በጊነስ ዎርልድ መዝገብ ላይ መስፈሩ ተሰምቷል።

አሳማው በመንሸራተቻ ስኬት ቦርድ ላይ በ11.3 ሰከንድ ውስጥ 10 ሜትር ርቀት በመጓዝ ነው የጊነስ ወርልድ ሪከርድን ያስመዘገበው።

ከ79 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝነው አሳማው በአሜሪካ የተወሰኑ የልምምድ ጊዜዎች ከተሰጠው በኋላ በስኬት ቦርድ ላይ መጓዝ እንደጀመረ ተገልጿል።

አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበው ኖርበርት በታዋቂው የስኬትቦርድ ተጫዋች ቶኒ ሃውክ ክብር ለመግለፅ ሲባል “ቶኒ ፖርክ” የሚል ቅፅል ስም እንደተሰጠው ተገልጿል።

በሴራን ታደሰ

06/11/2025

ታምራት ተሻገር
የኢትዮጵያ አይዶል ጉዞ ጥብበን ፍለጋ ባሕር ዳር ክፍል 3
Full Program on: https://youtu.be/rWcP4l5TFXs

1 ሜትር ከ80 ሣ.ሜ የሚረዝመው ትራፊኩ ሮቦት ሥራውን ጀምሯል***************በቻይና ዤጂያንግ ግዛት፣ ቶንግሺያንግ ከተማ አንድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል።የ1 ሜ...
06/11/2025

1 ሜትር ከ80 ሣ.ሜ የሚረዝመው ትራፊኩ ሮቦት ሥራውን ጀምሯል
***************

በቻይና ዤጂያንግ ግዛት፣ ቶንግሺያንግ ከተማ አንድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል።

የ1 ሜትር ከ80 ሣ.ሜ ቁመት ያለው ትራፊኩ ሮቦት ዛሬ በይፋ ሥራውን መጀመሩን ተከትሎ የቶንግሺያንግ ከተማን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማሳለጥ ላይ ይገኛል።

አቅጣጫዎችን እና የተለያዩ የመንገድ ትራፊክ ምልክቶችን እንዲረዳ ተደርጎ የተፈበረከው ሮቦቱ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት በተገቢው መንገድ በመረዳት ሥራውን በአግባቡ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

05/11/2025

ኤደን አበባየሁ - "ይሉኝታም የሌለህ"

በ3 ወራት ውስጥ 50 ኪሎ ለቀነሰ ሰው መኪና የሚሸልመው ጂም ቤት*******አንድ የቻይና ጂም ቤት በ3 ወራት ውስጥ 50 ኪሎ ግራም ለቀነሰ የመጀመሪያው ሰው ዘመናዊ የስፖርት መኪና እንደሚሸ...
04/11/2025

በ3 ወራት ውስጥ 50 ኪሎ ለቀነሰ ሰው መኪና የሚሸልመው ጂም ቤት
*******

አንድ የቻይና ጂም ቤት በ3 ወራት ውስጥ 50 ኪሎ ግራም ለቀነሰ የመጀመሪያው ሰው ዘመናዊ የስፖርት መኪና እንደሚሸልም አስታውቋል።

ፈቃደኛ የሆኑ ተሳታፊዎች የክብደት መቀነስ ሒደቱን ከመጀመራቸው በፊት 1 ሺህ 400 ዶላር መክፈል እንዳለባቸውም ጂም ቤቱ ገልጿል።

መመዝገቢያ ክፍያው የተወዳዳሪዎችን የስልጠና፣ የምግብ እና የ3 ወራት ቆይታ ወጪን የሚሸፍን መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ታዲያ ተወዳዳሪዎቹ ባያሸንፉም እንኳን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ድጋፍ በቀጣይነት እንደሚያገኙም ጂም ቤቱ አስታውቋል።

ተወዳዳሪዎችን በመመዝገብ ላይ የሚገኘው ጂም ቤቱ የተወዳዳሪዎች ቁጥር 30 ሲደርስ ምዝገባውን የሚያቆም መሆኑን ገልጿል።

በሴራን ታደሰ

Address

Churchil Road
Addis Ababa

Telephone

+251115172539

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EBC-መዝናኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EBC-መዝናኛ:

Share

Our Story

Ethiopian Broadcasting Corporation is a national media which disseminates its news and programs world wide via Television,Radio and Website.