ኢትዮ SPORT

ኢትዮ SPORT የተለያዩ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ እግር ኳሳዊ መረጃዎች
?

♨ ሩበን አሞሪም ኦልትራፎርድ ላይ የመጀመሪያ ሽንፈት ቀምሷል!- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታ ኖቲንግሀም ፎረስትን ኦልትራፎርድ ላይ ያስተናገዱት ማንችስተር ዩናይትዶች 3ለ2 ...
07/12/2024

♨ ሩበን አሞሪም ኦልትራፎርድ ላይ የመጀመሪያ ሽንፈት ቀምሷል!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታ ኖቲንግሀም ፎረስትን ኦልትራፎርድ ላይ ያስተናገዱት ማንችስተር ዩናይትዶች 3ለ2 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

- ለ ኖቲንግሀም ሶስቱን ጎሎች ሚሌንኮቪች፣ ጊብስ ዋይት እና ዉድ ሲያስቆጥሩ ለዩናይትድ ሆይሉንድ እና ፈርናንዴዝ አስቆጥሯል።

- አሞሪም በማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነቱ በ 4 ቀናት ውስጥ በተከታታይ ሁለት የሊግ ጨዋታዎችን ተሸንፏል።

"ፔፕ ጋርዲዮላ ትላንት ስለ እኔ የሆነ ነገር ብሎ ነበር.... እሱ ስድስት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል እኔ ደግሞ ለሶሰት ጊዜ ዋንጫውን አሸንፌያለሁ ነገር ግን እኔ እነዛን ዋንጫዎች ፍትሀዊ...
06/12/2024

"ፔፕ ጋርዲዮላ ትላንት ስለ እኔ የሆነ ነገር ብሎ ነበር.... እሱ ስድስት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል እኔ ደግሞ ለሶሰት ጊዜ ዋንጫውን አሸንፌያለሁ ነገር ግን እኔ እነዛን ዋንጫዎች ፍትሀዊ በሆነ እና በግልፅ ሁኔታ ነው ዋንጫዎቹን ያሸነፍኩት።

እኔ ከ 150 ክሶችን እያስተናገድኩ ዋንጫ ማሸነፍ አልፈልግም

ከተሸነፍኩ ተጋጣሚዬን ለድልህ እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለሁ።" - ጆዜ ሞሪንሆ

ፔፕ ጋርዲዮላ በሊቨርፑሉ ጨዋታ በእጃቸው 6 ጊዜ ያህል የሊጉን ዋንጫ ማሸነፋቸውን ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ማሳየታቸውን ተከትሎ በጋዜጣዊ መግለጫ ስማቸው ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር ተመሳሳይነት እንደዳለው ጥያቄ ተነስቶ ፔፕ ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል። በዚህም አወዛጋቢው ጆዜ ለፔፕ ንግግር አስገራሚ አስተያየት ሰጥተዋል። [Via: Mail Sport]

♨ አርሰናል ዩናይትድን ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ነጥብ ጥሏል!- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን አስተናግዶ በቲምበር እና ሳሊባ ጎሎች 2ለ0 አሸንፎ ወጥቷል።...
04/12/2024

♨ አርሰናል ዩናይትድን ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ነጥብ ጥሏል!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን አስተናግዶ በቲምበር እና ሳሊባ ጎሎች 2ለ0 አሸንፎ ወጥቷል።

- ሊቨርፑልን ከኒውካስትል ጋር ሶስት አቻ ሲለያይ ለሊቬ ግቦቹን መሐመድ ሳላህ 2x እና ጆንስ ሲያስቆጥር ለኒውካስል አይሳክ ፣ ሻር እና ጎርደን ከመረብ አሳርፈዋል።

- ማንችስተር ሲቲ ኖቲንግሃምን አስተናግዶ በዴብሮይን ፣ ዶኩ እና ሲልቫ ግቦች 3ለ0 አሸንፏል።

- ቼልሲ በ ዲሳሲ ፣ ንኩንኩ ፣ ማዱኬ ፣ ፓልመር እና ሳንቾ ጎሎች ሳውዝሀምፕተንን 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

በሌላ ጨዋታ ኤቨርተን ከዎልቭስ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 4ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

- ሊቨርፑል ሊጉን 35 ነጥብ ሲመራ አርሰናል እና ቼልሲ በ 28 ነጥብ ይከተላሉ።

" ኮል ፓልመር እና ጆዋኦ ፌሊክስ ሰዎች የትኬት ክፍያ ከፍለው እግር ኳስን እንዲመለከቱ የሚያደርጉ አይነት ተጫዋቾች ናቸው። ይሄንን ስል ሌሎች ጥሩ ተጫዋቾች አይደሉም እያልኩ አይደለም ነገር...
02/12/2024

" ኮል ፓልመር እና ጆዋኦ ፌሊክስ ሰዎች የትኬት ክፍያ ከፍለው እግር ኳስን እንዲመለከቱ የሚያደርጉ አይነት ተጫዋቾች ናቸው። ይሄንን ስል ሌሎች ጥሩ ተጫዋቾች አይደሉም እያልኩ አይደለም ነገር ግን ሁለቱ ተጫዋቾች የተለዩ ናቸው። ይህ ግልፅ ነው።" - ኤንዞ ማሬስካ

♨ አርኔ ስሎት በዚህ ሲዝን ፔፕ ጋርዲዮላን፣ ካርሎ አንቼሎቲን፣ ዣቢ አሎንሶን እና ኤሪክ ቴንሃግን አሸንፏል። እነዚህን አሰልጣኞች እያንዳንዱ ሲያሸንፍ አንድም ጎል አልተቆጠረበትም! 😳እነሆ ...
01/12/2024

♨ አርኔ ስሎት በዚህ ሲዝን ፔፕ ጋርዲዮላን፣ ካርሎ አንቼሎቲን፣ ዣቢ አሎንሶን እና ኤሪክ ቴንሃግን አሸንፏል። እነዚህን አሰልጣኞች እያንዳንዱ ሲያሸንፍ አንድም ጎል አልተቆጠረበትም! 😳

እነሆ እውነተኛው መላጣ ወደ መድረኩ መጥቷል! 🫡

♨ አርኔ ስሎት በእውነቱ ክብር ይገባዋል! 🫡 - በአለማችን ትልቁ ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ገና በመጣበት የመጀመሪያ ሲዝኑ ይህንን አይነት ክስተታዊ ቡድን አደራጅቶ ሊጉን በሰፊ የነጥብ ...
01/12/2024

♨ አርኔ ስሎት በእውነቱ ክብር ይገባዋል! 🫡

- በአለማችን ትልቁ ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ገና በመጣበት የመጀመሪያ ሲዝኑ ይህንን አይነት ክስተታዊ ቡድን አደራጅቶ ሊጉን በሰፊ የነጥብ እርቀት እየመራ ይገኛል። ይሄንን የውድድር ሲዝን ጨምሮ ባየናቸው ተከታታይ ሶስት ሲዝኖች የፔፕ ጋርዲዮላውን ማንችስተር ሲቲ በሊጉ በቅርበት ሲፎካከር የነበረው አርሰናል የነበረ ቢሆንም አሁን ምን እንደተፈጠረ ተመልከቱ። በቻምፒዮንስ ሊጉም ሪያል ማድሪድን ጨምሮ ከ 5 ጨዋታ 5 በማሸነፍ ብቸኛው ቡድን ነው! አስቡት ለዛውም በመጀመሪያ ሲዝኑ! 😳

Just a WOW 😳👌👏

♨ ሊቨርፑል ሲቲን በማሸነፍ ብቻውን እየተጓዘ ነው!- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ሊቨርፑል አንፊልድ ላይ ማንችስተር ሲቲን አስተናግዶ በጋክፖ እና ሞሀመድ ሳ...
01/12/2024

♨ ሊቨርፑል ሲቲን በማሸነፍ ብቻውን እየተጓዘ ነው!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ሊቨርፑል አንፊልድ ላይ ማንችስተር ሲቲን አስተናግዶ በጋክፖ እና ሞሀመድ ሳላህ ጎሎች 2ለ0 በሆነ ውጤት አሽንፏል።

- የ ፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ 4ኛ ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

- አስደናቂው አርኔ ስሎት በሊቨርፑል አስደማሚ ጉዞ እያደረገ ሲገኝ የፕርሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ከሁለተኛ ደረጃ ካለው ክለብ በ9 ነጥብ ርቆ በ34 ነጥብ ብቻውን እየገሰገሰ ይገኛል። ሲቲ ወደ 5ኛ ደረጃ ተንሸራቷል።

♨ ከረጅም አመታት በኋላ ማንችስተር ዩናይትድ እንደ ቡድን አሳማኝ ብቃት አሳይቶ አሸንፏል! - በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን ኦልትራፎርድ ስቴዲ...
01/12/2024

♨ ከረጅም አመታት በኋላ ማንችስተር ዩናይትድ እንደ ቡድን አሳማኝ ብቃት አሳይቶ አሸንፏል!

- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን ኦልትራፎርድ ስቴዲየም ላይ አስተናግዶ በማርከስ ራሽፎርድ እና ዚርክዚ ሁለት ሁለት ግቦች 4ለ0 አሸንፎ ወጥቷል።

- አስደናቂው ሩበን አሞሪም ከዘመናት በኋላ በኦልትራፎርድ ደጋፊዎችን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ አስደስቶ እና አይደንቲቲ ያለው ቡድን አሳይቶ በአሳማኝ የቡድን ብቃት በሰፊ ጎል አሸንፎ ወጥቷል።

- በብዙ የክለቡ ደጋፊዎች የሚወቀሰው ማርከስ ራሽፎርድ እስከነ ድክመቶቹ ወደ ግብ አስቆጣሪነቱ ተመልሷል።

- በአሞሪም ዘመን በዩናይትድ ቦታ አይኖረውም፣ ቀርፋፋ ነው ምናምን እየተባለ ሲወቀስ የኖረው ዚርክዚ ብቃቱን አውጥቶ ማሳየት ችሏል።

- አማድ ዲያሎ በሩበን አሞሪም ዘመን ታላቅ ተጫዋች ለመሆን ነገሮች የሰመሩለት ይመስላል።

- ቀጣዩ ጨዋታ ከአስደናቂው የሚኬል አርቴታው አርሰናል ጋር ነው። አሞሪም ትልቁን ፈተና በብቃት የሚወጣው ይሆናል? ወይስ?

♨ አማድ ዲያሎ ምን አይነት ድንቅ ተጫዋች ነው!? አንቶኒን በዛ ሁሉ ገንዘብ መጥቶ የአማድን ግማሽ ያህል ብቃት ማሳየት አልቻለም!
01/12/2024

♨ አማድ ዲያሎ ምን አይነት ድንቅ ተጫዋች ነው!? አንቶኒን በዛ ሁሉ ገንዘብ መጥቶ የአማድን ግማሽ ያህል ብቃት ማሳየት አልቻለም!

♨ አሞሪም በኦልትራፎርድ የመጀመሪያ ጨዋታውን አሸንፏል!- በኢሮፕ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ቦዶ ን ኦልትራፎርድ ላይ ያስተናገዱት ማንችስተር ዩናይትዶች በሆይሉንድ ሁለት እና ጋራናቾ ግብ 3ለ2 በሆ...
28/11/2024

♨ አሞሪም በኦልትራፎርድ የመጀመሪያ ጨዋታውን አሸንፏል!

- በኢሮፕ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ቦዶ ን ኦልትራፎርድ ላይ ያስተናገዱት ማንችስተር ዩናይትዶች በሆይሉንድ ሁለት እና ጋራናቾ ግብ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፈው ወጥተዋል።

- ሩበን አሞሪም በኦልትራፎርድ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ሲያሸንፉ ለክለቡ ደጋፊዎች ቃል በገቡት መሰረት ማንችስተር ዩናይትድ እስከነ ድክመቶቹ በትክክል የጨዋታ ሀሳብ አይደንቲቲ ያለው ቡድን አሳይተውናል።

- በምሽቱ ጨዋታ አስደናቂ ብቃቱን ያሳየው ማኑኤል ኡጋርቴ በእርግጥም የሩበን አሞሪም ቁልፋ ተጫዋች እንደሆነ አረጋግጧል! ማዝራዊም ምርጥ ብቃቱ ደጋግሞ እያሳየን ይገኛል።

- የሆይሉንድ በአሞሪም ቀጣዩ ጊዜው ብሩህ ሆኖ ሲታይ ጋራናቾ ግን በርካታ ግልፅ የግብ እድሎችን እየሳተ እስከመቼ በቡድኑ ቋሚ አሰላለፍ እንደሚቀጥል ጥያቄ ያጭራል።

♨ ኑሳይር ማዝራዊ ምን አይነት አስደናቂ ተጫዋች ነው?!  ማንችስተር ዩናይትድ በአያክስ የአንቶኒ ግዢ ላይ ቢከስርም በእርግጠኝነት ግን ኑሳይር ማዝራዊ ን ግን ከባየር ሙኒክ ዘርፏል!
28/11/2024

♨ ኑሳይር ማዝራዊ ምን አይነት አስደናቂ ተጫዋች ነው?! ማንችስተር ዩናይትድ በአያክስ የአንቶኒ ግዢ ላይ ቢከስርም በእርግጠኝነት ግን ኑሳይር ማዝራዊ ን ግን ከባየር ሙኒክ ዘርፏል!

♨ በ ዩጋንዳ የሚገኙ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ለክለቡ አዲሱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ለመፀለይ ከያሉበት ተሰባስበዋል 😆🙏
28/11/2024

♨ በ ዩጋንዳ የሚገኙ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ለክለቡ አዲሱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ለመፀለይ ከያሉበት ተሰባስበዋል 😆🙏

♨ ሊቨርፑል ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ በቻምፒዮንስ ሊግ ድንቅ ጉዞውን አስቀጥሏል!- በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ አንፊልድ ላይ ሪያል ማድሪድን ያስተናገዱት ሊቨርፑሎች በማክ አሊስተ...
27/11/2024

♨ ሊቨርፑል ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ በቻምፒዮንስ ሊግ ድንቅ ጉዞውን አስቀጥሏል!

- በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ አንፊልድ ላይ ሪያል ማድሪድን ያስተናገዱት ሊቨርፑሎች በማክ አሊስተር እና ጋክፖ ግቦች 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈው ወጥተዋል።

- በጨዋታው በከንቱ ሲባክን ያመሸው ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት ሲሰት ሞሀመድ ሳላህም በተመሳሳይ ሊቨርፑል ያስገኛትን ፍፁም ቅጣት ምት ስቶታል።

- ሊቨርፑሎች አስደናቂውን ወጣት የመስመር ተከላካይ ብራድሊ ሲያስመለክቱን ኪሊያን ምባፔ በዚህ ወጣት ቁጥጥር ውስጥ ገብቶ ምንም ማድረግ ሳይችል ወጥቷል።

- አዲሱ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ሊቨርፑል የሊጉንም የቻምፒዮንስ ሊጉንም በአስደናቂ ብቃት የደረጃ ሰንጠረዥ በአንደኝነት እየመሩ ይገኛል።

- የምሽቱ አውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ውጤት፦

አስቶን ቪላ 0-0 ጁቬንቱስ
ቦሎኛ 1-2 ሊል
ሴልቲክ 1-1 ክለብ ብሩጅ
ዳይናሞ ዛግሬብ 0-3 ዶርቱመንድ
ሊቨርፑል 2-0 ሪያል ማድሪድ
ሞናኮ 2-3 ቤንፊካ
ፒኤስቪ 3-2 ሻካታር ዶኔስክ

♨ የፔፕ ጋርዲዮላ ሲቲ ያለ ሮድሪ ምንም ነው! - ይሄንን ያውቃሉ? በወርሀ ሴፕቴምበር ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር አድርጎት በነበረው ጨዋታ የባሎንዶር አሸናፊው ሮድሪ ከባድ ጉዳት አስተና...
27/11/2024

♨ የፔፕ ጋርዲዮላ ሲቲ ያለ ሮድሪ ምንም ነው!

- ይሄንን ያውቃሉ? በወርሀ ሴፕቴምበር ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር አድርጎት በነበረው ጨዋታ የባሎንዶር አሸናፊው ሮድሪ ከባድ ጉዳት አስተናግዶ ለመሉ ሲዝኑ ከጨዋታ ከወጣ በኋላ እንደ ማንችስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ በርካታ አደገኛ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት አንድም ክለብ የለም። ሲቲም ባደረጋቸው ያለፉት 6 ጨዋታዎች አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም በ 5ቱ ተከታታይ ጨዋታዎች ሲሸነፍ በ 1 ጨዋታ አቻ መውጣት ችሏል።

ታዲያ የወቅቱ የፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ካለ ሮድሪ ምንም ነው ብንል ማጋነን ይሆናል? ፔፕ የሮድሪ እውነተኛ ተተኪ ካላገኘ በሲዝኑ ቶፕ 4 ማጠናቅ የሚችል ይመስላችኋል?

♨ የፔፕ ጋርዲዮላው ሲቲ ሲፍረከረክ አርሰናል ጣፋጭ ድል ተጎናፅፏል!- የፔፕ ጋዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ፊኖርድን በገዛ ሜዳው አስተናግዶ በ ሀላንድ ×2 እና ጉንዶጋን ጎሎች እስከ 75ኛው ደቂ...
26/11/2024

♨ የፔፕ ጋርዲዮላው ሲቲ ሲፍረከረክ አርሰናል ጣፋጭ ድል ተጎናፅፏል!

- የፔፕ ጋዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ፊኖርድን በገዛ ሜዳው አስተናግዶ በ ሀላንድ ×2 እና ጉንዶጋን ጎሎች እስከ 75ኛው ደቂቃ 3ለ0 ሲመራ መቆየት ቢችልም በአስገራሚ ሁኔታ ሶስት ጎሎች ተቆጥሮበት ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

- መድፈኞቹ ከሜዳቸው ውጪ በማርቲኔሊ፣ ሀቨርትዝ፣ ጋብሬል፣ ሳካ እና ትሮሳርድ ጎሎች የቀድሞውን የሩበን አሞሪም ቡድን አፈራርሰዋል።

- የምሽቱ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ውጤት፦

ስፖርቲንግ ሊስበን 1-5 አርሰናል
ማንችስተር ሲቲ 3-3 ፊኖርድ
ባርሴሎና 3-0 ብረሴት
ባየር ሙኒክ 1-0 ፒኤስጂ
ባየር ሌቨርኩሰን 5-0 ሳልዝበርግ
ኢንተር ሚላን 1-0 ሌፕዚግ

" አሞሪም በጨዋታው እለት ከፊትለፊቴ ነበር በእውነቱ እሱ በጣም ተበሳጭቶ ነበር፤ ይሄንን መዋሸት አልፈልግም። " በመጀመሪያው አጋማሽ በዳሎት የቦታ አያያዝ ደስተኛ አልነበረም እንዲሁ በሁለተ...
26/11/2024

" አሞሪም በጨዋታው እለት ከፊትለፊቴ ነበር በእውነቱ እሱ በጣም ተበሳጭቶ ነበር፤ ይሄንን መዋሸት አልፈልግም።

" በመጀመሪያው አጋማሽ በዳሎት የቦታ አያያዝ ደስተኛ አልነበረም እንዲሁ በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይሮ በገባው የዚርክዚ ነቦታ አያያዝ ትንሽ ብስጭት ውስጥ ከቶታል።

"እነዚህን መሰል አብዛኞቹ ተጫዋቾች በቀጣይ ሶስት ወይም አራት ሳምንታት በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብተው የሚጫወቱ አይመስለኝም።" - ኦዌን ሀርግሬቭሰ

♨ ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማሸነፍ አልቻሉም!- የማንችስተር ዩናይትድ አዲሱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን  ከሜዳቸው ውጪ ከኢፕሲች ታውን ጋር አድርገው በአንድ አ...
24/11/2024

♨ ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማሸነፍ አልቻሉም!

- የማንችስተር ዩናይትድ አዲሱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ከኢፕሲች ታውን ጋር አድርገው በአንድ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የአሞሪም ዩናይትድ ገና በ 85ኛው ሰከንድ በማርከስ ራሽፎርድ ግብ ጨዋታውን መምራት ችሎ የነበረ ቢሆንም ለኢፕሲች ባስቆጠራት ድንቅ ግብ ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

- አሞሪም በርካታ የቡድኑን ቋሚ ተጫዋቾች በበቂ የጊዜ ሁኔታ በማሰራት ለጨዋታው የዝግጅት ጊዜ ባያገኝም እንደ መጀመሪያ ጨዋታው እስከነ ድክመቱ በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ ቡድኑ ቅርፅ የያዘ እና በከፍተኛ ኢንቴንሲቲ የሚጫወት ቡድን አሳይቷል። ነገር ግን የቡድኑ የፈጠራ ብቃት በደካማነቱ ቀጥሎ ተስተውሏል።

- በዛሬው የአሞሪም የመጀመሪያ ጨዋታ ድንቅ ሆኖ መታየት የቻለው የከሰለቡ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ነበር።

♨ ብዙ ያልተባለለት የፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ ኮኮብ! - ሞሀመድ ሳላህ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሊቨርፑል ማሊያ መጫወት ከጀመረበት የውድድር አመት አንስቶ በፕሪሚየር ሊጉ በተካፈለባቸው 8 ሲዝ...
24/11/2024

♨ ብዙ ያልተባለለት የፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ ኮኮብ!

- ሞሀመድ ሳላህ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሊቨርፑል ማሊያ መጫወት ከጀመረበት የውድድር አመት አንስቶ በፕሪሚየር ሊጉ በተካፈለባቸው 8 ሲዝኖች በሁሉም ሲዝኖች ቢያንስ በእያንዳንዱ ሲዝን 10 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

- ሳላህ በሊቨርፑል ማሊያ በፕሪሚየር ሊጉ ከሜዳው ውጪ ለክለቡ 100 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

- አስደናቂው ግብፃዊው በውድድር አመቱ በሊጉ 16 የግብ ተሳትፎዎችን በማድረግ ቀዳሚው ተጨዋች ሆኗል። 10 ጎሎችን ማስቆጠር ሲችል በተጨማሪም 6 አሲስቶችን ማድረግ ችሏል።

ባለፋት 8 ዓመታት በፕሪሚየር ሊጉ እንደ ሞሀመድ ሳላህ በወጥነት አስደናቂ ብቃቱን ማሳየቴ የቻለ ተጫዋች አለ?

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ SPORT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share