Firtuna

Firtuna Firtuna is an Ethiopian-based entertainment news company
(2)

Firtuna is a media and production company that provides Art Related news Daily which has a vision of Transforming the Ethiopian art industry to the next level.

አንጋፋው ድምጻዊ ነበር፤ የአሁኑ ዘማሪ - ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያለው የቀድሞው ድምፃዊና ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ለረጅም ጊዜ በህክምና ሲ...
09/04/2024

አንጋፋው ድምጻዊ ነበር፤ የአሁኑ ዘማሪ - ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያለው የቀድሞው ድምፃዊና ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ለረጅም ጊዜ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ70 ዓመቱ ዛሬ ማለዳ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል::

እግዚአብሔር ነፍስህን ይማር!
ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥ!!

Prestige Tv
23/03/2024

Prestige Tv

23/03/2024
20/03/2024

- Beyond the Screen -

Join us for a captivating event with the renowned Selam Tesfaye, one of Ethiopia's most esteemed brand ambassadors and actresses!

Thursday - March 21 at 2pm (8:00 PM Ethiopian time)

Location: at US Embassy Addis Ababa

Make sure to bring your 🪪 ID and arrive on time as seats are limited and reserved.

Secure your spot now by registering at the link below to be a part of this incredible event! Don't miss out on this one-of-a-kind opportunity.

📋 Register here ➡️ https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

Access to the Satchmo Center is by membership only, please sign up: https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

U.S. Embassy Addis Ababa BBC News Amharic VOA Amharic DW Amharic Prestige Tv Selam romantesfaye EBS



U.S. Embassy Addis Ababa Selam romantesfaye

Don't miss  the event
18/03/2024

Don't miss the event

ሰላም እንደምን አላችሁ !

በየሁለት ሳምንቱ ተወዳጅ ዝግጅቱን ይዞላችሁ የሚቀርበዉ ፕርስቲጅ አዲስ ፤ ዛሬም እጅግ ተወዳጅ እና አንጋፋ የፊልም ተዋናይት እንዲሁም ብራንድ አምባሳዳር የሆነችውን አርቲስት ስላም ተስፋዬን ጋብዟል::

ሰላም የሥራ እና የህይወት ተሞክሮዋን የምታካፍለን ሲሆን ከወዳጅ እና ድናቂዎቿ ለሚቀርቡላት ጥያቄዎችም የፊታችን ሀሙስ መጋቢት 12 ,2016 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል።

በዕለቱ የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃ-ግብር ይኖራል::

ፕርስቲጅ አዲስ ከ ሰላም ተስፋዬ ጋር አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ እንድታደርጉ ይጋብዛል።

አድራሻ ፡ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 ( ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

ሰዓት- 8:00 🕘

⌚️ 🎯 ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ። ⏰

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ 🪪

📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱️

https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

U.S. Embassy Addis Ababa BBC News Amharic Selam romantesfaye VOA Amharic DW Amharic Etv English Language World EBS Firtuna LinkUp Addis Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) Nebyou Indris Seifemichael tesfaye LinkUp Addis

17/03/2024

ሰላም ተስፋዬን ስለምን መጠየቅ ይፈልጋሉ?

በመጪው ዝግጅታችን ተወዳጇ ሰላም ተስፋዬ በእንግድነት ስለምትጋበዝ የዝግጅቱ አንድ አካል ይሆኑ ዘንድ የማይገኝ ዕድል አመቻችተንልዎታል። ስለ ትወናዋ ፣ስለ ብራንድ አምባሳደርነቷ እንዲሁም የግል ፍልስፍናዋ ሙያዊ የሆኑ ጥያቄዎችን መጠየቅ የምትፈልጉ ከዚህ በታች ኮሜንት /ሀሳብ/ መስጫው ላይ በማስፈር የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ!

ይህንን ዝግጅት በጥሩ ቤተሰባዊ ጭውውት የማይረሳ እናድርገው። ለአዳዲስ መረጃዎች አብራችሁን ቆዩ



U.S. Embassy Addis Ababa VOA Amharic Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) Prestige Selam romantesfaye Seifemichael tesfaye Nebyou Indris Etv English Language World Firtuna Nabet Ok EBS LinkUp Addis LinkUp AddisBBC News AmharicBBC News AmharicDW Amharic

ሰላም እንደምን አላችሁ!ዛሬም እንደወትሮው ተወዳጅ እና አንጋፋ  የፊልምና የቴያትር ባለሙያ የሆነውን አርቲስት አለማየሁ ታደሰን የሥራ እና የህይወት ተሞክሮውን እንዲያካፍለን የፊታችን ማክሰኞ...
23/02/2024

ሰላም እንደምን አላችሁ!

ዛሬም እንደወትሮው ተወዳጅ እና አንጋፋ የፊልምና የቴያትር ባለሙያ የሆነውን አርቲስት አለማየሁ ታደሰን የሥራ እና የህይወት ተሞክሮውን እንዲያካፍለን የፊታችን ማክሰኞ በ ቀን 19-06-2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዘናል።

ከተወዳጁ የፊልም እና የቴያትር ባለሙያ አለማየሁ ታደሰ ጋር አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ እንድታደርጉ እንጋብዛለን።

አድራሻ ፡ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸 ( ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

ሰዓት- 8:00 🕘

⌚️ 🎯 ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ።

⏰ መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ 🪪

📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ፡፡👇🖱️
https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

Prestige Tv U.S. Embassy Addis Ababa BBC News Amharic DW Amharic VOA Amharic

- Coming Soon-     with Alemayehu Tadesse                                                                               ...
21/02/2024

- Coming Soon-

with Alemayehu Tadesse
Actor /Director/ writer

DON'T MISS THE OPPORTUNITY

AFFINI                                                                                                                  ...
25/01/2024

AFFINI
"አፊኒ ፊልም " ተመርቆ ለእይታ የሚበቃበት ቀን ይፋ ሆነ

| አፊኒ ፊልም የፊታችን የካቲት 2/6/20 በሲዳማ ባህል አዳራሽ እንደሚመረቅ የሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ::

የቢሮው ሀላፊ በመግለጫቸው "አፊኒ" የተለያዩ ኩነቶችን የያዘ ድንቅ የሲዳማ ባህል እንደሆነ ገልጸው ፊልሙ የሚዳስሳቸው አጠቃላይ የህዝቡን አኗናር አመጋገብ እንዲሁም የክልሉን መልከአ ምድር የዳሰሰ ሲሆን ትኩረቱ በሲዳማ የግጭት አፈታት መርሆች ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ገልጸዋል::

የቢሮው ሀላፊ አክለውም የፊልሙ ወጪ በመንግስት የተሸፈነ መሆኑን ገልጸው ተሰርቶ መጠናቀቁን ተከትሎ የፊታችን የካቲት 2/6/2016 በሲዳማ ባህል አዳራሽ በይፋ እንደሚመረቅ ገልጸዋል::

አቶ ጃጎ አገኘሁ በመግለጫቸው በስነ ስርአቱ ላይ የሲዳማ ክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሚኒስቴሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚገኙ ገልጸዋል::

የፊልሙ አሰሪ ኮሚቴ በበኩሉ የተሰራው ፊልም አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው ከምርቃት ሥነ ስርአቱ በኃላ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር ለእይታ እንደሚበቃ በመርሀ ግብር መያዙን ገልጸዋል::



Telegram: https://t.me/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/

Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

ሮፍናን ሁለት አልበሞችን በአንድ ጊዜ ሊለቅ ነውየኤሌክሮኒክ ዳንስ ሚዩዚክ እንዲሁም የሙዚቃ ባለሙያ የሆነዉ ድምጻዊ ሮፍናን ኑሪ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዲስትሪ ውስጥ የመጀመሪያው እንደሆነ የተ...
25/01/2024

ሮፍናን ሁለት አልበሞችን በአንድ ጊዜ ሊለቅ ነው

የኤሌክሮኒክ ዳንስ ሚዩዚክ እንዲሁም የሙዚቃ ባለሙያ የሆነዉ ድምጻዊ ሮፍናን ኑሪ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዲስትሪ ውስጥ የመጀመሪያው እንደሆነ የተነገረለት ሁለት አልበሞችን በአንድ ጊዜ አሰናድቶ ማጠናቁን እና ከሦስት ሳምንት በኋላ ለአድማጭ ተመልካች እንደሚደርስ ድምጻዊው በዛሬው እለት በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቋል።

ሙዚቀኛዉ ሦስት እና ስድስት ከተሰኙ "የኔ ትዉልድ" እና "ነፀብራቅ" ሁለት አልበሞቹ በኋላ ዘጠኝ በተሰኘዉ አልበም ዉስጥ "ሀራምቤ" እና "ኖር "የሚል ርዕስ ተሰጥቷቸዋል።

ከተሰራው ሁለት አልበም መካከል ሁለት ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራ ሲሆን አንደኛው ቪድዮ ክሊፕ ዛሬ ማታ ይለቀቃል ተብሏል።

የድምፃዊው ሦስተኛ እና አራተኛ አልበም የሆኑት አልበሞቹ 10 እና 11 ሙዚቃዎችን የያዙ ሲሆን በግጥም እና ዜማ አብዛኛውን ድምፃዊው እንደሰራቸው ገልጾ አልበሞቹ በሁሉም የዲጅታል የሙዚቃ ማሰራጫ አማራጮች እንደሚለቀቅ ተናግሯል።



Telegram: https://t.me/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/

Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

ገነነ መኩሪያ  ( ሊብሮ )1978 ዓ.ም ለነበረ የኢትዮጵያ ሻምፒዎና፣ የእርስ በእርስ ግጥሚያ የነበራቸው ቅዱስ ጊዮርጊስና ሜታ ቢራ በአንድነት ካረፉበት ገነት ሆቴል ሃይሌ ካሴ የተባለ የጊዮ...
23/01/2024

ገነነ መኩሪያ ( ሊብሮ )

1978 ዓ.ም ለነበረ የኢትዮጵያ ሻምፒዎና፣ የእርስ በእርስ ግጥሚያ የነበራቸው ቅዱስ ጊዮርጊስና ሜታ ቢራ በአንድነት ካረፉበት ገነት ሆቴል ሃይሌ ካሴ የተባለ የጊዮርጊስ ተጫዋች ከአንድ የሜታ ቢራ ተከላካይ ጋር አፍ ላፍ ገጥሞ ያወራል። የሜታው ተጫዋች እነ ቤከም ባወርን እየጠቀሰ "ሊብሮ" ስለሚባለው የአጨዋወት መንገድ ለሃይሌ ካሴ በስሜት አስረድቶታል።

በማግስቱ...ለሃይሌ ገለፃ ሲያደርግ የነበረው የሜታ ቢራው ተከላካይ ከኋላ ተነስቶ፣ ግብ ጠባቂውን ጨምሮ አራት የጊዮርጊስ ተጫዋቾችን አልፎ ግብ ያስቆጥራል። ደስታውን ከቡድን አጋሮቹ ጋር ገልፆ ወደ ሜዳው ሲመለስ ሃይሌ ጠጋ ብሎ ጠየቀው "ሊብሮ ያልከኝ ይሄ ነው?" የሜታው ተጫዋች በፈገግታ ሁኖ መለሰለት "አዎ"። ከደስታው ሳይመለስ፣ ፈገግታውንም ሳይጨርስ አዲስ ስም ወጣለት፦ "ሊብሮ"። ይህ ስሙ የአያቱን ስም ተክቶ ባሳለፋቸው የሜዳም የሚዲያም ታሪኩ ውስጥ ከፍ ብሎ ተጠርቶበታል፦ ገነነ መኩሪያ ሊብሮ።
የታሪክ ፍቅሩ ከስቴዲየም ጫማ አሰቅሎ ስቲዲዮ ውስጥ ብዕር ሙጥኝ እንዲል ያደረገውን... ገናና የታሪክና የስፖርት ሰው ታሪክ መሰነድ ኩራትም ፍርሃትም አለው።

➻ ህፃኑ ገነነ

"ብዙም ትውስታ የለኝም" በሚላት ይርጋለም ነው ውልደቱ፤ መጋቢት 5 1957 ዓ.ም። የውልደት አመቱ ከሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪ ዥን ጣቢያ የምስረታ ዓመት ጋር መግጠሙን አስተውሎ 'ይህ ልጅ የሚዲያ ሰው ይሆናል' ያለ ባይኖርም፤ እርሱ ግን በኋለኛው ዘመኑ በህትመቱም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው ላይ ስፖርትና ታሪክን ይዞ መግነን ችሏል።
ከማያስታውሳት ይርጋለም ከተማ የበዛ የልጅነት ጊዜውን ወዳሳለፈባት ሻሸመኔ አቀና። በዚያ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትሏል፤ የእግር ኳስና የጽሑፍ ችሎታውን ፈልጎ አግኝቷል። በአፄ ናዖድ ተማሪ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን እየተከታተለ የቡና ነጋዴ አባቱ ገቢ ወጫቸውን ሲፅፉበት ከርመው የሞላ መዝገባቸውን ይሰጡታል፤ ህፃኑ ገነነ ተቀብሎ ከጋዜጦች የሚያገኘውን የስፖርተኞችን ፎቶ እየለጠፈ ለጓደኞቹ ያከራያል። ግማሹን የሚያዩ የቁልፍ (አዝራር) ፣ ሙሉውን የሚኮመኩሙ 5 ሳንቲም እንዲከፍሉ ግድ ይላቸው ነበር።
እዚያው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ አዲስ ዘመንንና ሰለሞን ተሰማ ያዘጋጅ የነበረው "ስፖርት ፋና" ጋዜጦችን ያዞራል። 10 ጋዜጣ ለማዞሩ የሚከፈለውን 10 ሳንቲም ከመቀበል ይልቅ አንድ ጋዜጣ ተቀብሎ ይሄዳል። ከጋዜጦቹ ላይ የሚያገኛቸውን ስዕሎች ከአባቱ የሞላ መዝገብ ላይ እየለጠፈ፤ ዜናዎቹን በራሱ መንገድ ድጋሜ እየፃፈ ገቢውንም የጽሑፍ ችሎታውንም እኩል አሳደገ። ጋዜጣ ከማሳደድ ጎን ለጎን ኳስ ሊያድን "አረንቻታ" ለተባለ የሰፈሩ ቡድን በግብ ጠባቂነት ተሰለፈ። "ጎል ውስጥ መቀመጥ ስለማልወድ እየወጣሁ ብዙ ጎል ይገባብኝ ነበር" የሚለው ገነነ ከአረንቻታ ቀጥሎ "ነበልባል" ለተባለ ቡድንም በግብ ጠባቂነት ተጫውቷል።
7ኛ ክፍል ሲደርስ የወቅቱ መንግስት ከቀይ ሽብር በኋላ ወጣቱን በስፖርት ለመያዝ አልሞ በርካታ ውድድሮችን ያደርጋል። በቴኒስና በዝላይ ተሳትፎ ሳይቀናው የማታ ማታ አስር ሺ ሜትር ተወዳድሮ በወንድሙ እገዛ አንደኛ ወጥቶ ባልዲ እንደተሸለመ ያስታውሳል።
ይህ በሆነ በዓመቱ ከሰፈር ጓደኞቹ ጋር በመሆን "ቀዩ እምቡጥ" በሚባል የውትድርና ምልመላ ፕሮግራም ሰልጥሎ ለምደባ በዝግጅት ላይ እያለ የሻሸመኔ ቡድን የግብ ጠባቂ እጥረት ስላለበት የካምፑ ኃላፊና የወረዳው የስፖርት ሊቀመንበር "ገነነ ጥርሱ ቦንብ መንከስ አይችልም" ብሎ ሲያስቀረው ያለቀሰውን ለቅሶ ዛሬም አይረሳ።
እርሱ ብቻ ሳይሆን 5ቱም ወንድሞቹ እግር ኳስ ይጫወታሉ። አንድ ቡድን ውስጥ በዝተው ስላሉ የቀበሌያቸው ቡድን 09 ከመባል ይልቅ ‹የአቶ መኩሪያ ቡድን› ነበር የሚባለው። ገነነ ከሁሉም ወንድሞቹ በልዩነት ለሲ ቡድን አጥቂ፣ ለቢ ቡድን አማካኝ፣ ለኤ ቡድን ግብ ጠባቂ ሁኖ በመጫወቱ ሁለገብ ተጫዋች ተብሎ ብርሌ ተሸልሟል።
➻ የሸገር መንታ መንገዶች
1974 ዓ.ም ከግብ ጠባቂነቱ በመውጣት የሜዳ ተጫዋች በመሆን አውራ ጎዳና ለተባለ ቡድን ከፍተኛ ተከፋይ ሁኖ በ50 ብር ተቀጠረ። በአውራጃዎች ውድድር የሻሸመኔን መለያ ለብሷል፤ የሸዋ ውድድር ላይ ደግሞ ሃይቆችና ቡታጅራን ወክሎ ድንቅ ብቃቱን ናዝሬት ላይ አሳይቷል። ይህ ድንቅ ብቃቱ በ1975 ዓ.ም ገና የ12ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ለሜታ ቢራ እንዲፈርም አድርጎት ወደ ሸገር እንዲዘልቅ ሁኗል። ከሚከፈለው 183 ብር ላይ ቤት ተከራይቶ፣ የምግብ ኮንትራት ይዞ፣ ተግባረ- ዕድ ለትምህርት ከፍሎ የተረፈውን ቆጥቧል። 125 ብር በቆጠበበት ዓመት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ "ምርጥ ቆጣቢ" ብሎ እንደሸለመው እያስታወሰ በቅርቡ መንገድ ላይ ያገኘው የባንኩ ወጣት ሰራተኛ "አካውንት ክፈት" ሲለው "አንተ ሳትወለድ የባንኩ ደንበኛ ነበርኩ" እንዳለው ይናገራል።
እግር ኳሱን እየተጫወተ፣ ከተግባረ ዕድ በጄነራል መካኒክነት ተመርቆ ለሜታ ቢራ እየሰራ ለአዲስ ዘመን ፅሑፍ መፃፍ ጀመረ። በእጁም በእግሩም የሚታትር ትጉህ ሆነ። በ1978 የነበረ ዓለም ዋንጫ ላይ ማራዶና በእጁ ጎል ሲያገባ የገነነ ጽሑፍ ደሞ ከእድሜ እኩያው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በፀጋ ቁምላቸው በኩል ገባ። ስሙ በቴሌቭዥን ሲጠራ የሰሙት አለቃው ስራውን አመቻችተውለት ቤተ መጽሐፍት እየገባ መፃፉን አበረታ። ለተለያዩ ጋዜጦችና ሚዲያዎች ቢፅፍም ከየካቲት መጽሔት በስተቀር አይከፍሉትም ነበር። እርሱ ግን ሁለት የሚወዳቸው ነገሮች ስለከፈሉት ደስተኛ ነው፦ እግር ኳስና የጽሑፍ ስራው።
የሜታ ቢራ ተጫዋች ሁኖ 3 ጊዜ የኢትዮጵያ ሻምፒዮን የነበረ ቢሆንም በ1978 ዓ.ም የብር ሜዳልያ ተሸላሚ የሆነበትን የፍፃሜ ጨዋታ ግን አይረሳም። ከህንፃ ኮንስትራክሽን ጋር በነበረ የፍፃሜ ግጥሚያ ገነነ ለአጋሩ ግብ ጠባቂ አቀብላለሁ ያላት ኳስ ራሱ መረብ ላይ አርፋ አንድ ለዜሮ በሆነ ውጤት ተሸንፈው ዋንጫውን አጥተዋል። ታሪክ ወዳጁ ገነነ ይሄን የራሱን ገጠመኝ እያሰበ "በታሪክ ብቸኛው ሰው ነኝ... አሸናፊው ቡድን የተጋጣሚው ተጫዋች አግብቶለት ዋንጫ ሲበላ የመጀመሪያው ነው" ይላል። ይሄኛውን ጎል ጨምሮ በዓመቱ ውስጥ አምስት ጊዜ ራሱ ላይ ማግባቱን በማስታወስ "ራሴ ላይ የማገባው የጎል ድርቅ ሲኖር ነው... እዚያ ማግባት ካልቻልክ እዚህ ታገባለህ" ይላል በቀልድ መልክ።
1980 ዓ.ም ላይ የገነነን ብቃት ያየ የወቅቱ የመብራት ሃይል አሰልጣን መንግስቱ ወርቁ ወደ መብራት ያዛውረዋል። ብዙም ሳይቆይ መንግስቱ ከክለቡ ለቆ አዲስ አሰልጣኝ ሲመጣ በአዲሱ አሰልጣኝ እቅድ ውስጥ ያልነበረው ገነነ ሳይመዘገብ ይቀርና ከልምምድና ከወዳጅነት ጨዋታዎች በዘለለ መሰለፍ ሳይችል ይቀራል። ለዋና ጨዋታ ካለመሰለፉ አጠገብ እየጣፈጠው ያለ የጽሑፍ ስራው አለ። እዚህች ጋ ወሰነ፤ ጫማውን ሰቅሎ እግሩን አሳረፈው። ያረፈው እግሩ ላይ የነበረ ብርታትን ከእጁ ላይ አክሎ በትጋት መፃፉን ቀጠለ።
➻ የእግሩን ብርታት ለእጁ ሰጠ
ገነነ አንድ ቢሮ ተገኝቶ እየፃፈ ሳለ እስኪርቢቶው አልፅፍ ይላል። ከቢሮው ኃላፊ ጋር ከምታወራ አንዲት የቢሮው ባልደረባ እስኪርቢቶ ተበድሮ ያሰበውን ፅፎ ካጠናቀቀ በኋላ የተበደረውን ሊመልስ ቀና ሲል አበዳሪውን ያጣታል። በቀጣዮቹም ቀናት አልተመለሰች። ቢሮው የመርሃ ስፖርት ጋዜጣ ቢሮ ነበር፤ እስኪርቢቶ አበዳሪዋ ደግሞ መዓዛ ብሩ። መዓዛ ይዛው የነበረ የጋዜጣውን የስፖርት ክፍል ከእርሷ መውጣት በኋላ እንዲረከብ ሲጠየቅ ያልታሰበ የእስኪርቢቶ ውሰቱን እንደ ስልጣን ርክክብ ቆጥሮ በግርምት ፈገግ ብሏል። "በጣም ያሳወቀኝ" ያለውን መርሃ ስፖርት ጋዜጣ እንዲህ ነበር የጀመረው።
ከመርሃ ስፖርት እኩል ገነነ መኩሪያ ሊብሮ የሚለው ስም እንዲታወቅ ያደረገው ብስራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ እንደነበር ያስታውሳል። በተለይ በ1981 ዓ.ም ተፈጥሮ የነበረውን መፈንቅለ- መንግስት ለመስማት 2 ሰዓት ላይ የሚጀምሩ ብሄራዊ የሬዲዮና የቴሌቭዥን ስርጭቶችን በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩ ታዳሚዎች፤ በአንድ ሰዓት ብስራተ ወንጌል ላይ በወርቁ አለማየሁ ድምፅ የሚንቆረቆር የገነነን ፅሑፍ ልቅም አድርገው በመስማት አጣጥመዋል።
ከመንግስት ለውጥ በኋላ የግል ጋዜጣ ሲጀመር ገነነ ከአበበ ወልደ ጻድቅ፣ ወንደሰን ደምሴና ሁሴን አብዱልቀኒ ጋር በመሆን ሻምፒዮን የሚል ጋዜጣ ጀመረ። ተወዳጅ በነበረው ጋዜጣ ላይ ለወራት የሰራው የታሪክ ሰው "የምትሰጠኝ አንድ ከግማሽ ገፅ አነሰችኝ" በማለት ሌሎች አማራጮችን ማማተር ያዘ። ማማተሩ ሰምሮ በ1985 ዓ.ም ጥቅምት 23 ቀን ሊብሮ የተሰኘች የራሱን ጋዜጣ አሳተመ። ለዚህችኛዋ ጋዜጣ ህትመት የቦሌ ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ የነበረው አሰፋ ከበደ አስተዋፅኦ ከፍ ያለ መሆኑን ዛሬም ድረስ አልረሳም። የበዛ ትኩረቷን የሃገር ውስጥ ስፖርት ላይ ያደረገችው ሊብሮ ጋዜጣ ከዜና ይልቅ ለታሪክ ያደላች ነበረች። በ1973 ዓ.ም በጊኒ አድርገው ጠፍተው የነበሩ ተጨዋቾች ወደ ሃገር ቤት በተመለሱና ሞሮኮ የሄዱ ተጫዋጮች በጠፉ ሰሞን የመጀመሪያ ህትመቷ የሆነው ሊብሮ የፊት ገጿ ላይ ይዛው የወጣችው ርዕስ "ሞሮኮ ጠፉ፣ ጊኒ መጡ" የሚል ነበር። በወቅቱ አስር ሺ ቅጁ ተሽጦ ሁለተኛ እትም መታተሙን ያስታውሳል፡፡
➻ በድምፅ ሲገለጥ
ከጽሑፍ ስራው ሻገር ብሎ በራሱ ድምፅ በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጠው 2000 ዓ.ም ላይ በዛሚ ኤፍ ኤም ነበር። ስፖርትና የቀድሞ ሙዚቃዎችን ታሪክ ለአድማጮች አሻግሯል። ከ2001 እስከ 2006 ዓ.ም በኤፍ ኤም አዲስ ከአዲስ ዜማዎች ጋር ሰርቷል። 2007 ዓ.ም ደግሞ በብስራት ኤፍ ኤም "መሴ ሪዞርት" እና ሌሎች ዝግጅቶች ላይ ታሪክና ስፖርትን አዋዶ ተገልጧል። የሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ መበርታቱን ያየ ካፍ በ2009 ዓ.ም የ60 ዓመት ጎንደል ኦፍ ሜሪት ሸልሞታል። 6 ጋዜጠኞች ብቻ ያገኙትን ሽልማት በመውሰድ ገነነ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው። ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ከግሩም ዘነበ ጋር የቀረፀውን ዝግጅት በአሻም ቴሌቭዥን ላይ እያቀረበ ይገኛል፤ እስከ አሁን ከ150 በላይ የዚህ ተወዳጅ ዝግጅት ክፍሎች አየር ላይ ውለዋል። ከተመልካችም ጥሩ ምላሽ እንዳገኘ ይገልፃል።
➻ በመጽሐፍ ገነነ
ገነነ የሚዲያ ሰውነቱ፣ ዓለም ‹ዘመን የማይሽረው ሚዲያ› የሚለው መጽሐፍ ላይ ሲደርስ ይበረታ እንደሁ እንጂ ዝንፍ አይልም። ይህ ታሪኩ እስከተሰነደበት ጊዜ ድረስ ስምንት መጽሐፍትን ለንባብ አብቅቷል። ኢትዮጵያዊ ሥልጠና፣ የአሸናፊ ግርማ የህይወት ታሪክ፣ ኢሃፓና ስፖርት 1፣ 2፣ 3፣ የእግር ኳስ ወጎች፣ ፍትሃዊ የጠጅ ክፍፍል እና መኩሪያ። በ1994 ዓ.ም ለህትመት ያበቃው የመጀመሪያ መጽሐፉ ኢትዮጵያዊ የሆነ የእግር ኳስ አሰለጣጠንን በመፃፍ ቀዳሚም ብቼኛም እንደሚያደርገው ይናገራል።
አያይዞም ከተወዳጁ የስፖርት ጋዜጠኛ ሰዒድ ኪያር ጋር በመሆን GS and GK በሚል የስልጠና መንገድ ቡድን እንዳቋቋሙና በድረ ገፅም ተደራሽ እያደረጉት እንደሆነ ይናገራል። እንዳለ ጌታ ከበደ ጋር አንድ መድረክ ላይ ቆይታ ያደረገው ገነነ ኢሃፓና ስፖርት የሚል መጽሐፉ በአብርሃም ገዛኸኝ አማካኝነት "የነገን አልወልድም" በሚል ርዕስ ወደ ፊልም ቢቀየርም እስከአሁን አለማየቱን ሲናገር የዚህ ታሪክ ሰናጅ ተገርሟል።
➻ ሰነፉ ገነነ
‹‹በማህበራዊ ህይወቴ ደካማ ነኝ›› የሚለው ገነነ ጠንካራ ከሚላት ሚስቱ ጋር ሮማርዮ እንዳገናኘው ይናገራል። በአንድ አጋጣሚ የሮማርዮ ፎቶ በትልቁ የተለጠፈበት ምግብ ቤት ይገባና ምስሉን ወዶት ኖሮ ለጋዜጣ ይፈልገዋል። ወስዶ ኮፒ አድርጎ ለመመለስ ሲጠይቅ የምግብ ቤቱ አስተዳዳሪ ብር እንዲያሲዝ ትጠይቀዋለች። እንዳለችው አድርጎ ምስሉን ከመለሰ በኋላ ያዝያዘውን ብር ሳይቀበል ደጋግሞ ይመላለሳል። በመጨረሻም ምልልሱ ፍሬ አፍርቶ ብር አስይዝ ያለችው አስቴር አየለን አግብቶ የሁለት ልጆች አባት ሁኗል። ቃል በቃል "ከፈጣሪ በታች እርሷ ናት ያለች" ያለችኝ የሚላት ባለቤቱ ለእያንዳንዱ እርምጃው ድጋፍ እንደምታደርግለት በኩራት ይናገራል።
ሜዳም ሚዲያም ላይ እንደስሙ የገነነው ታሪክና ኳስ ወዳዱ ገነነ ተወዳጅ ሚዲያ የግለሰቦችን ታሪክ ለመሰነድ መነሳቱን ያደንቃል። በስራ አጋጣሚ የጊዮርጊስ፣ የመቻልና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መስራቾችን አግኝቶ ቃለመጠይቅ ማድረጉን እንደ እንድለኝነት የሚያየው ገነነ ዛሬ ታሪካቸው እንዲሰነድ ተጠይቀው ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች በኋላ እንደሚቆጫቸው ይናገራል። የማይደክመው የታሪክ ሰው አሻም ላይ ካለው ዝግጅቱ ጎን ለጎን በቅርቡ ኢሃፓና ስፖርት 4ን ጨምሮ በሌሎች ስራዎቹ ለመገለጥ ዱብ ዱብ እያለ መሆኑን ነግሮናል። የዚህ ታሪክ ሰናጅ ኩራት አንድ ነው... "የታሪክ ወዳዱን ሰው ታሪክ የሰነደ" መባል፤ ፍርሃቱም አንድ ነው "የታሪክ ወዳዱን ሰው ታሪክ ሲሰንደድ እንደመሻቱ ሰርቼለት ይሆን?" የሚል።
የመዝጊያ ሀሳብ ፤ ይህ መዝጊያ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የኢንሳይክሎፒዲያ ቦርድ አባላት አቋም የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
ገነነ መኩሪያ፣ ተንቀሳቃሽ ኢንሳይክሎፒዲያ ቢባል ይገባዋል፡፡ ስፖርትና ታሪክ አጣምሮ ይወዳል፡፡ ገነነ ለሚናገራቸውም ወይም ለሚያቀርባቸው የጽሁፍ ስራዎች በቂ ማስረጃ እና ሰነድ ይዞ ነው፡፡ በታላላቅ ቤተ-መጽሀፍቶች ጎራ ያለ ገነነን ሊያጣው አይችልም፡፡
ገነነ ሲያነብም ሆነ ሲመራመር አይደክመውም-ቢደክመው እንኳን ድካሙን ይረሳል፡፡ ገነነ ታሪክን ሲያቀርብ ማጣፈጡን ያውቅበታል፡፡ ለ45 ደቂቃ በዩኒቨርሲቲ የታሪክ ክፍለ ጊዜ ላይ ከመታደም የ12 ደቂቃዋ የገነነ ምጥን የታሪክ ጨዋታ ወደ አእምሮ ኩልል ብላ ትገባለች፡፡ ይህንን ለማድረግ ትልቅ ጥረትን ይጠይቃል፡፡ ማንበብን ይጠይቃል፡፡ ጥልቅ ምርምር ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ነገሮችን ወይም ያለፉ ታሪኮችን በሚገባ አዋዝቶ ማቅረብን ይጠይቃል፡፡ ማዋዛት የገነነ ልዩ ክህሎት በአድማጭ ፤ አንባቢ በተመልካች የተመሰከረለት ነው፡፡ገነነ ይጽፋል ያነባል የእግር ኳስ ቴክኒክን ያስተዋውቃል፡፡ ገነነ መጽሀፎቹን ሲጽፍ ከበቂ ጥናት ጋር ነው፡፡ ደግሞም መጽሀፎች ጥሩ የሽያጭ ሰንጠረዥ ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ ገነነ መኩሪያ በ 1970ዎቹ መጨረሻና በ 1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ በሀገራችን ብቅ ካሉ በሳል የሚድያ ሰዎች አንዱ ነው፡፡

©️ ተወዳጅ ሚዲያ (በእዝራ እጅጉ)

ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሀፍት ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በሞት መለየት አስደንጋጭ መረጃ ነው። ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን!

የአስፋው መሸሻ የሽኝትና የጸሎት መርሃግብር
17/01/2024

የአስፋው መሸሻ የሽኝትና የጸሎት መርሃግብር

የአስፋው መሸሻ ሥንብትና ሽኝት በእሁድን በኢቢኤስ ፕሮግራም አዘጋጅነትና አቅራቢነት ተወዳጅነትን ያተረፈው አንጋፋው የራዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ አስከሬን ረቡዕ...
16/01/2024

የአስፋው መሸሻ ሥንብትና ሽኝት

በእሁድን በኢቢኤስ ፕሮግራም አዘጋጅነትና አቅራቢነት ተወዳጅነትን ያተረፈው አንጋፋው የራዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ አስከሬን ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ቤተሰቦቹ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት የሥንብት ሥነስርዓት ይካሄዳል፡፡

በዚሁ ዙሪያ ከአሜሪካ መረጃዎችን ያደረሰን ባልደረባችን ጋዜጠኛ አበበ ፈለቀ የፊታችን ሃሙስ ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሜሪላንድ በሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን የፍትሃት ሥርዓት እንደሚከናወንለትና ቅዳሜ ጥር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የአስከሬን ሽኝት ይደረግለታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጾልናል።

በአዲስ አበባም በቀብር ሥነስርዓቱ አፈጻጸም ዙሪያ በአገር ውስጥ ኮሚቴ ተዋቅሮ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የቀብሩን ቀንና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በይፋ በሚሰጥ መግለጫ እንደሚነገር ኮሚቴው አሳውቋል።

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በህክምና ሲታገዝ ቆይቶ ለህክምና በሄደበት በአሜሪካ ዋሽንግተን ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ለሊት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

የተወዳጁ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ  የህይወት ጉዞአስፋው መሸሻ ከእናቱ ከወይዘሮ ዘነበወርቅ አሻግሬና ከአባቱ አምባሳደር መሸሻ አስፋው በሀምሌ 19 ቀን1959 ዓ.ም ለቤተሰቡ ...
15/01/2024

የተወዳጁ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ የህይወት ጉዞ

አስፋው መሸሻ ከእናቱ ከወይዘሮ ዘነበወርቅ አሻግሬና ከአባቱ አምባሳደር መሸሻ አስፋው በሀምሌ 19 ቀን1959 ዓ.ም ለቤተሰቡ አምስተኛ ልጅ በመሆን ይቺን ምድር ተቀላቀለ።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በሀረር ከተማ በሚገኘው ቤቴልሄም ወይም ማልቴዝ በተሰኘ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲከታተል ቆይቶ ወላጆቹ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ሀረር የጀመረውን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ አበባ በሚገኘው በቤተልሄም ትምህርት ቤት ተከታተለ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንና የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን በታንዛኒያ እና ኬኒያ ናይሮቢ በመከታተል የመጀመሪያ ዲግሪውን በኮምፒዩተር ሳይንስ ተቀብሏል።

አባቱ አምባሳደር መሸሻ አስፋው ዲፕሎማት በመሆናቸው በስራ ምክንያት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ይጓዙ ስለነበር አስፋውም አብሯቸው የመንቀሳቀስ እድል እንደነበረው ይናገራል፡፡
አስፋው መሸሻ በሀገራችን የመጀመሪያ በሆነው የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ላይ በ1992 ዓ.ም በሰኔ ወር በወቅቱ በርካታ አድማጮች በነበረው “አይሬ” በተሰኘ የሙዚቃ ፕሮግራም ላይ ከዳናኤል ግዛው ጋር በማዘጋጀት እና በማቅረብ ለስድስት ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል።

አስፋው መሸሻ በአይሬ” የሙዚቃ ፕርግራም ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር ከቀኑ በ8 ሰዓት ጀምሮ ያቀርብ በነበረው ፕሮግራም ላይ የነበረው አቀራርብና አድማጭን እንዳያሰለች የሚጠቀማቸው አቀራረቦች ልዩ እንደነበሩ የቀድሞ የአይሬ የሙዚቃ ፕሮግራም አዘጋጅና የቅርብ ጓደኛው ዳንኤል ግዛው ይመሰክራል።
አስፋው መሸሻ ከሬዲዮ የሙዚቃ ፕሮግራሙ ባሻገር የተለያዩ ማስታወቂያዎችንም ይሰራ ነበር።

ከዚያም ወደ አሜሪካ ያቀና ሲሆን እዛው አሜሪካ እያለም 2001 አመተ ምህረት ወደ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በመቀላቀል “ኑሮ በአሜሪካ” የተሰኘውን የኢቢኤስ ፕሮግራም በማዘጋጀትና በማቅረብ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

ለአመታት በዘለቀው ኑሮ በአሜሪካ በተሰኘው ፕሮግራም በአትላንታ፣ ኮሎራዶ፣ ሲያትል፣ ዴንቨር፣ ቨርጂኒያ፣ ዲሲ፣ ሜሪላንድና በሌሎችም የአሜሪካ ግዛቶች በመዘዋወር ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ሲያስተላልፍ ቆይቷል ።

አስፋው ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ኑሮውን ሙሉ ለሙሉ አዲስ አበባ ካደረገ በኋላ እሁድን በኢቢኤስ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ አቅራቢ በመሆን ሲሰራ ነበር ። ታድያ በእነዚህ ሁሉ የሚዲያ ስራ ጊዜያቱ ተመልካቾችን የሚያዝናኑና ቁምነገር አዘል መልዕክቶችን በማስተላለፍ ታዋቂነትን አትርፏል።

በእሁድን በኢቢኤስ ፕሮግራም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከማገልገሉም ባሻገር ፕሮግራሙ በተመልካች ዘንድ ተናፋቂ እንዲሆን ካደረጉት መካከልም አስፋው በዋነኝነት የሚጠቀስ ነበር፡፡

ተወዳጁ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በህክምና ሲታገዝ ቆይቶ ለተሻለ ህክምና በሄደበት በአሜሪካ ዋሽንግተን ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ለሊት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
አስፋው መሸሻ የአንድ ልጅ አባት ነበር ፡፡

ተወዳጁ የEBS የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈ!ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ከ...
14/01/2024

ተወዳጁ የEBS የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈ!

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ከሀገር ውጭ ከወጣም በኃላ ኑሮ በአሜሪካ የተሰኘ አስተማሪ ፕሮግራም ለኢትዮጵያን ሲያቀርብ የነበረ ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነበር

ከውጭ ሀገር ተመልሶም በEbs የእሁድ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ዝግጅቶችን በማቅረብ እጅግ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻለ የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር በአግባቡ የተላበሰ በሳል ጋዜጠኛ ነበር!

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ በዛሬው እለት ማረፏ ተስምቷል!

ነፍስ ይማር!

15/12/2023
ሰላም እንደምን  አላችሁ !Prestige Tvዛሬም እንደወትሮው ተወዳጁን እና አንጋፋ  የፊልም ፣ የቴያትር ብሎም የህግ ባለሙያ የሆነው አርቲስት አበበ ባልቻን የሥራ እና የህይወትተሞክሮ እን...
04/12/2023

ሰላም እንደምን አላችሁ !
Prestige Tv

ዛሬም እንደወትሮው ተወዳጁን እና አንጋፋ የፊልም ፣ የቴያትር ብሎም የህግ ባለሙያ የሆነው አርቲስት አበበ ባልቻን የሥራ እና የህይወት
ተሞክሮ እንዲያካፍለን የፊታችን ማክሰኞ በ ቀን 25-03-2016 ዓ.ም
ቀጠሮ ይዘናል።

ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ በመምጣት ከተወዳጁ የፊልም እና የቴያትር እንዲሁም የህግ ባለሙያ አበበ ባልቻ ጋር አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ እንድታደርጉ እንጋብዛለን።

መግቢያ -በነጻ
አድራሻ ፡ አሜሪካን ኢምባሲ ( ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )
ቦታ- አሜሪካ ኢምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸
ሰዓት- 9:00 🕘

⌚️ 🎯 ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ። ⏰

በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡??🖱️

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdkEyvXoSIGO30XQ8USUm6yCiK1_JVyD84QTYkNRbFAObm4pA/viewform?pli=1

ሰላም እንደምን  አላችሁ !ዛሬም እንደወትሮው ተወዳጁን እና አንጋፋ  የፊልም ፣ የቴያትር ብሎም የህግ ባለሙያ የሆነው አርቲስት አበበ ባልቻን የሥራ እና የህይወትተሞክሮ እንዲያካፍለን የፊታች...
01/12/2023

ሰላም እንደምን አላችሁ !

ዛሬም እንደወትሮው ተወዳጁን እና አንጋፋ የፊልም ፣ የቴያትር ብሎም የህግ ባለሙያ የሆነው አርቲስት አበበ ባልቻን የሥራ እና የህይወት
ተሞክሮ እንዲያካፍለን የፊታችን ማክሰኞ በ ቀን 25-03-2016 ዓ.ም
ቀጠሮ ይዘናል።

ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ በመምጣት ከተወዳጁ የፊልም እና የቴያትር እንዲሁም የህግ ባለሙያ አበበ ባልቻ ጋር አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ እንድታደርጉ እንጋብዛለን።

መግቢያ -በነጻ

አድራሻ ፡ አሜሪካን ኢምባሲ ( ከ ስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ )

ቦታ- አሜሪካ ኢምባሲ ቅጥር ግቢ🇺🇸

ሰዓት- 9:00 🕘

⌚️ 🎯 ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ⏰

📎 በ ዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ ፡፡👇🖱️

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdkEyvXoSIGO30XQ8USUm6yCiK1_JVyD84QTYkNRbFAObm4pA/viewform?pli=1

A Little Form His Journey Location: USA embassy  🇺🇸
30/11/2023

A Little Form His Journey

Location: USA embassy 🇺🇸

ተዋናይ ማቲው ፔሪ በድንገተኛ አደጋ አረፈ    | ‘ፍሬንድስ’ የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ‘ሲትኮም’ ተዋናይ ማቲው ፔሪ በ54 ዓመቱ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፖሊስ አ...
29/10/2023

ተዋናይ ማቲው ፔሪ በድንገተኛ አደጋ አረፈ

| ‘ፍሬንድስ’ የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ‘ሲትኮም’ ተዋናይ ማቲው ፔሪ በ54 ዓመቱ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፖሊስ አስታወቀ።

ተዋናዩ ሎስ አንጀለስ በሚገኝ ቤቱ ውስጥ ቅዳሜ ዕለት ሞቶ መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን ምናልባት በድንገት ባጋጠመው የመስጠም አደጋ ሕይወቱ ሳያልፍ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ፎክስ ኒውስ ቲኤምዜድን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የድንገተኛ አደጋ ሠራተኞች መጀመሪያ ከቤቱ የደረሳቸው ሪፖርት አንድ ሰው በልብ ድካም መያዙን የሚያመላክት ነበር።

እንደ ቲኤምዜድ መረጃ ከሆነ፣ በቦታው ላይ ምንም ዓይነት መድኃኒት (እፅ) አልተገኘም፤ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሟል የሚል ጥርጣሬም የለም።

‘ፍሬንድስ’ የተሰኘው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ‘ሲትኮም’ በዴቪድ ክሬን እና ማርታ ካውፍማን የተዘጋጀ ሲሆን መጀመሪያ አየር ላይ የዋለው እ.አ.አ ከመስከረም 22 ቀን 1994 እስከ ግንቦት 6 ቀን 2004 ነበር።

ለ10 ሲዝን የዘለቀው አስቂኝ ድራማው ዋና ተዋናዮች ዛሬ በድንገት ሕይወቱ ያለውፈው ማቲው ፔሪን ጨምሮ ጄኒፈር አኒሽተን፣ ኮርትኒ ኮክስ፣ ሊሳ ኩድሮው፣ ማት ለብላንክ እና ዴቪድ ሽዊመር ነበሩ

ከስክሪኑ ባሻገር 🔈ሁላችሁም ተጋብዛችኋል በጣም በጉጉት የምንጠብቀው አዝናኝ እና ብዙ ልምድ እና ተሞክሮ የምንካፈልበት ዝግጅታችን ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።በአሁኑም ዝግጅት ሁለት...
08/09/2023

ከስክሪኑ ባሻገር

🔈ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

በጣም በጉጉት የምንጠብቀው አዝናኝ እና ብዙ ልምድ እና ተሞክሮ የምንካፈልበት ዝግጅታችን ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

በአሁኑም ዝግጅት ሁለት ተፅእኖ ፈጣሪ ወጣት እንግዶችን የጋበዝን ሲሆን ያላቸውን ልምድ እና ተሞክሮ ያካፍሉናል።
እንግዶቻችን ቪዲዮ ክሬተር መቅዲ እና ቤኪ 4 ኪሎ የፊታችን ቅዳሜ ሜክሲኮ ቅድስት ማርያም ዮኒቨርስቲ ውስጥ ባለው አሜሪካ ሴንተር የሚገኙ ይሆናል ።

ሁላችሁም በመምጣት የዚህ የማይረሳ እና አዝናኝ ዝግጅት አካል እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል ።

🗓ቀን- ቅዳሜ ጷግሜ 4

⌚ሰዓት - 10:30 ሎካል

መግቢያ- በነፃ

📍ቦታ- ሜክሲኮ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አሜሪካ ሴንተር



Telegram: https://t.me/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/

Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

ድምጻዊ ሬማ ጋር የነበረንን ውል አቋርጠናል!ሸራተን አዲስ ሆቴል ለአዲስ ዓመት ዋዜማ ያዘጋጀው ኮንሰርት በተያዘለት መርሃግብር እንደሚቀጥል ምንጮቻችን አስታውቀዋል።አዘጋጆቹ ከናጄሪያዊው ድምጻ...
07/09/2023

ድምጻዊ ሬማ ጋር የነበረንን ውል አቋርጠናል!

ሸራተን አዲስ ሆቴል ለአዲስ ዓመት ዋዜማ ያዘጋጀው ኮንሰርት በተያዘለት መርሃግብር እንደሚቀጥል ምንጮቻችን አስታውቀዋል።

አዘጋጆቹ ከናጄሪያዊው ድምጻዊ ሬማ ጋር የነበራቸውን ውል በማቋረጥ በምትኩ ሌሎች አለማቀፍ አርቲሰቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የመ‍ዚቃ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡም ተሰምቷል።

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ በርካታ ወገኖች ድምፃዊ ሬማ በኮንሰርቱ ላይ መገኘት የለበትም ሲሉ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው የሚታወስ ነው።

አዘጋጆቹ የህዝብን ድምፅ ለማክበር ሲሉ ድምፃዊው ከሙዚቃ ድግሱ እንዲሰረዝ አድርገዋል። ይሁን እንጂ ከውጭ ሀገር የሚመጡ በርካታ ታዳሚዎች፣ አስቀድመው ትኬቱን የገዙ ተመልካቾች እና ለኮንሰርቱ በተደረገው ከፍተኛ ቅድመዝግጅት ምክንያት ዝግጅቱን ለመቀጠል መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል።

ለቅድመ ዝግጅት ከተከፈለው የገንዘብ ወጪ ባሻገር በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ታዳሚዎችን ስሜትና ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ሲባል ዝግጅቱ ይቀጥላል።

ሸራተን አዲስ በየአመቱ የአዲስ አመት ዋዜማ የሙዚቃ ድግስ ያዘጋጃል። የዘንድሮ ዝግጅትም ከወትሮ የተለየ አይደለም።



Telegram: https://t.me/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/

Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

ኢቢሲ እያሳደጋቸው ለሚገኙ ህፃናት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያሳደጋቸው ለሚገኙ ህፃናት አዲሱን ዓመት ምክንያት...
05/09/2023

ኢቢሲ እያሳደጋቸው ለሚገኙ ህፃናት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያሳደጋቸው ለሚገኙ ህፃናት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ በዛሬው እለት አድርጓል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ዲፓርትመንት ኃላፊ ወ/ሮ ዘላለም ቱሉ፤ ለህፃናት የተደረገው ድጋፍ አስፈላጊ ነገሮች እንዲሟላላቸው እና ደስተኛ ሆነው ትምህርታቸውን አንዲከታተሉ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢቢሲ ሰራተኞች ከወርሃዊ ደሞዛቸው ተቆራጭ በማድረግ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህፃናት የተለያዩ እገዛዎችን እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

ኢቢሲ ከቂርቆስ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተሞች ጋር በመሆን የአቅም ውስንነት ያለባቸውን እና ድጋፍ የሚስፈልጋቸውን ህፃናት የመለየት ስራ መጀመሩን ያወሱት ወ/ሮ ዘላለም ቱሉ፤ ተቋሙ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማስፋት የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚንቀሳቀስም ተናግረዋል።

ለህፃናቱ በዛሬው ዕለት የተደረገው ድጋፍ የዘይት፣ የፉርኖ ዱቄት እንዲሁም የልብስ እና የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍን ያካትታል።

ማህበረሰቡ በየአካባቢው የተቸገሩትን በመደገፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣም የህፃናቱ አሳዳጊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በላሉ ኢታላ



Telegram: https://t.me/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/

Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

ኮካኮላ የሸራተን የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት ስፖንሰር መሰረዙን ገለፀስፓንሰርሺፕ አጋርነት መሰረዛችንን ስለማሳወቅበአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሸራተን አዲስ ሊከናወን የተሰናዳውን የሙዚቃ ድግስ ድ...
05/09/2023

ኮካኮላ የሸራተን የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት ስፖንሰር መሰረዙን ገለፀ

ስፓንሰርሺፕ አጋርነት መሰረዛችንን ስለማሳወቅ
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሸራተን አዲስ ሊከናወን የተሰናዳውን የሙዚቃ ድግስ ድርጅታችን ኮካ-ኮላ ቤቭሬጅስ አፍሪካ ኢትዮጵያ ስፖንሰር አጋር የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የስፓንሰርሺፕ አጋርነታችንን የሰረዝን መሆኑንና የፕሮግራሙ አጋር አለመሆናችንን እናሳውቃለን።

ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አማ

(ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ~ኢትዮጵያ)



Telegram: https://t.me/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/

Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ ! እኔ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ጳጉሜ 6 በሸራተን አዲስ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ስራዬን ለማቅረብ ተፈራርሜ የተዘጋጀሁ ቢሆንም ይህን ስራ በመሰረዜ የሚ...
05/09/2023

የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ !

እኔ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ጳጉሜ 6 በሸራተን አዲስ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ስራዬን ለማቅረብ ተፈራርሜ የተዘጋጀሁ ቢሆንም ይህን ስራ በመሰረዜ የሚያስከፍለኝ ዋጋ ቢኖርም ከሁሉም በላይ በቃሏ የምመራላት ቤትክርስትያን ሀይማኖት አባቶቼን ትዕዛዝ በመቀበል የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ !

ለውድ አድናቂዎቼ እንዲሁም የፕሮግራሙ አዘጋጆች ይቅርታ እየጠየኩ በሌላ ዝግጅት እንደማስደስታችሁ እና እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ በታላቅ አክብሮት እና ምስጋና ነው!

ኩኩ ሰብስቤ



Telegram: https://t.me/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/

Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከለከለ!የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ መከልከሉን ድምፃዊው ገለፀ። አርቲስቱ ባስተላለፈው መልዕክት «በትናትናው እለት እንደ ...
29/08/2023

የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከለከለ!

የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ መከልከሉን ድምፃዊው ገለፀ። አርቲስቱ ባስተላለፈው መልዕክት «በትናትናው እለት እንደ አባቴ እወድሻለሁ የተሰኜው አዲሱ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከልክሏል እንዲህ ስለሆነ ለሀገሬ እና ለህዝቦቿ ያለኝ ፍቅር አይቀንስም እንደ አባቴ እወድሻለሁ» ብሏል።



Telegram: https://t.me/FirtunaMedia
Facebook: https://www.facebook.com/firtunamedia/
Instagram: https://www.instagram.com/firtunamedia/
Tiktok : https://www.tiktok.com/

Stay with us.
አብራችሁን ቆዩ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Firtuna posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Firtuna:

Videos

Share