ቅዱስ ገብርኤል
ታህሳስ 19 ቀን በዚህ ቀን ሰለስቱ ደቂቅ "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል" ያሉበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሣት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው።
ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ነገሩ እንዲህ ነው። ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔር ሰዎች የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩት ወጣቶች ሥም አናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) ነበሩ።
ት/ዳንኤል 3፡1-30 ታሪኩ እንደሚግረን ንጉስ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሣት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ። በዚህ መካከል ሰልስቱ ደቂቅ ነበሩ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር።
የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻል?" ባላቸው ጊዜ የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም እንኳን አንተ ለምታመልከው ጣኦት አንሰግድም አሉት ።
በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሣት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው
እንኳንን ለኅዳር( 21) ፅዮን ማሪያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን 🙏
እመቤታችን ድንግን ማሪያም ፀሎት ምልጃ እና ልመናዋ አይለየን ከክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን 🙏
አሜን አሜን አሜን
እንኳንን ለኅዳር( 21) ፅዮን ማሪያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን 🙏
እመቤታችን ድንግን ማሪያም ፀሎት ምልጃ እና ልመናዋ አይለየን ከክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን 🙏
አሜን አሜን አሜን
#አክሱም_ጽዮን #Ethiopian_Orthodox
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
በዓለ ሢመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
እንኳን ለሊቀ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!
በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች
የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል
ዳን12÷1(፲፪፣፩)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ህዳር 12
እንኳን ለሊቀ መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመቱ ታላቅ ዓመታዊ ክብር በዓል በሰላም አደርሳችሁ አደርሰን አሜን 🙏
በዚህች ቀን የሰማይ ሰራዊት ሁሉ አለቃቸው መልአከ ምክሩ የምክሩ አበጋዝ ይለዋል የቅድስት ስላሴ መንጦላእትን የሚከፍትና የሚዘጋ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ የገናናው ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ቀን ነው። በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡
እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)
የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር
ሰው አያልቅስብህ እንዳታለቅስ!
" ሰው አያልቅስብህ እንዳታለቅስ!
🙏 🙏 🙏. 🙏 🙏 🙏. 🙏🙏🙏
. ✞ ✨ጥቅምት ፳፯ (27) ✨✞
✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ መታሰቢያ በዓል ነው ። ✞✞✞
መድኃኔዓለም ክርስቶስ
ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::
በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::.
በዛሬዋ ቀን ቤተክርስቲያናችን የመድኃኔዓለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች ይኽም የለውጥ በዓል ነው ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ሥጋውን የቆረሰው መጋቢት ፳፯ ቀን ነው ይኽ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ደግሞ ሐዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ እና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰ
ቃለ ሕይወት ያሰማልን 🙏 🙏 🙏
@Followers