FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/

FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/ Ethiopian Broadcasting Corporation is a 24 hour working public media.
(181)

Ethiopian Broadcasting Corporation is a national media which disseminates its news and programs world wide via Television,Radio and Website.

የፕሮግራም ጥቆማ ለሀገር ልጆችከጥበብ ማዕድ አዘጋጆች  የጋዜጠኛ፣ ሐያሲና ደራሲ   ዛሬ በወዳጆቹ አንደበት እያነሳሳን ስለአንባቢነቱ፣ ስለወዳጅነቱ፣ ስለአፃፃፍ ስልቱ እና ስለሕይወቱ ከብዙ ቀ...
20/04/2024

የፕሮግራም ጥቆማ ለሀገር ልጆች
ከጥበብ ማዕድ አዘጋጆች



የጋዜጠኛ፣ ሐያሲና ደራሲ ዛሬ በወዳጆቹ አንደበት እያነሳሳን ስለአንባቢነቱ፣ ስለወዳጅነቱ፣ ስለአፃፃፍ ስልቱ እና ስለሕይወቱ ከብዙ ቀጥቂቱ እናወጋለን።

አሰራርን የተመለከተ ከባለሙያዎች ጋር የተደረገን ቆይታ በሙዚቃ አጅበንእናስደምጣችኋለን።

ዝግጅታችን የንባብ ባህላችንን የተመለከተ ጥንቅር ታደምጣላችሁ።

መረጃዎችና የተመራረጡ የሙዚቃ ግብዣዎችም እንደተጠበቁ ናቸው።

#ቅዳሜ ከ10 --12 ሰዓት በቀጥታ ስርጭት በfm addis 97.1 (EBC) ላይ እንጠብቃችኅለን።

የፕሮግራም ጥቆማ ለሀገር ልጆችከአዲስ ስፖርት አዘጋጆች  #አዲስ ስፖርት ቅዳሜ ሚያዚያ 12/2016 ከጠዋቱ 12:40 እስከ 2:00 በልዩ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ቡፌ ቆይታ ያደርጋል።  #በሎን...
19/04/2024

የፕሮግራም ጥቆማ ለሀገር ልጆች
ከአዲስ ስፖርት አዘጋጆች

#አዲስ ስፖርት ቅዳሜ ሚያዚያ 12/2016 ከጠዋቱ 12:40 እስከ 2:00 በልዩ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ቡፌ ቆይታ ያደርጋል።

#በሎንዶን ማራቶን የሚሮጠው አንጋፋው አትሌት #ቀነኒሳ በቀለ ለ25 አመታት መሮጥ ቀላል አይደለም ብሏል። ቀነኒሳ በቀጣይ #ኦሊምፒክን ያስባል?

#የአለም የሴቶች ማራቶን ክብረወሰን ባለቤቷ #ትዕግሥት አሰፋ ለሎንዶን በጣም ጥሩ ልምምድ ሰርቻለሁ ብላለች። ከውድድሩ በፊት ምን ይሰማታል?



#ታምራት ቶላ እና #ልዑል ገብረስላሴ በታላቁ ውድድር ይጠበቃሉ። ከውድድሩ አስቀድመው ምን ተናገሩ?

#ጉዳፍ ፀጋዬ እና ለሜቻ ግርማ የአመቱን የዳይመንድ ሊግ ውድድር ቅዳሜ በቻይና ይጀምራሉ። ሌሎች እነማን ይጠበቃሉ?

#ፕሪሚየር ሊጉን መልሰው በተቀላቀሉበት አመት በአስደናቂ ብቃት ሊጉን እየመሩ ናቸው፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግርኳስ ክለብ። ወጣቱ አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ልዩ ቆይታ ከአዲስ ስፖርት ጋር አድርጓል። አሰልጣኙ ምን አለ?

#የቅዳሜ ማለዳ አዲስ ስፖርትን ማለዳ ከ12:40 እስከ 2:00 በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ይጠብቁን

19/04/2024
የአትሌቶቹ ውጤትና ሽልማት ተሰርዟል።በቤጂንግ ግማሽ ማራቶን መነጋግሪያ የነበሩት   ኢትዮጵያዊ   ደጀኔ ሀይሉና ሁለቱ ኬኒያውያን  ማናንጋትና ሮበርት ኬተር  ቻይናዊውን አትሌት እንዲያሸንፍ ...
19/04/2024

የአትሌቶቹ ውጤትና ሽልማት ተሰርዟል።

በቤጂንግ ግማሽ ማራቶን መነጋግሪያ የነበሩት ኢትዮጵያዊ ደጀኔ ሀይሉና ሁለቱ ኬኒያውያን ማናንጋትና ሮበርት ኬተር ቻይናዊውን አትሌት እንዲያሸንፍ አድርገዋል በሚል ምርመራ ተከፍቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

አትሌቶቹ በውድድሩ መጨረሻ ፍጥነታቸውን በመቀነስ የአሸናፊነት ክብራቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል ተብሏል።እነዚህ አትሌቶች የቀዳሚነት እድሉን ለቻይናዊው በመስጠት የውድድሩን ህግ መጣሳቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

በዚህም የአሸናፊውን ጨምሮ የአራቱንም አትሌቶች ውጤት በመሰረዝ ሜዳሊያቸውን ሲነጠቁ የሽልማት ገንዘብም እንደማይሰጣቸው በውሳኔው ተገልጿል።

ቻይናዊው አትሌት ሂ ጃይ በሀገሪቱ ስማቸው በትልቁ ከሚነሱ አትሌቶች አንዱ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የፕሮግራም ጥቆማ ለሀገር ልጆችከመሰንበቻ አዘጋጆች #መሰንበቻ ቅዳሜ ሚያዚያ 12/2016ዓ.ም ከረፋድ 4:00 እስከ 6:00 በተለያዩ ጉዳዮች ቆይታ እናደርጋለን:: #ጠረፍ ካሳሁን(ኪያ) ተወዳ...
19/04/2024

የፕሮግራም ጥቆማ ለሀገር ልጆች
ከመሰንበቻ አዘጋጆች

#መሰንበቻ ቅዳሜ ሚያዚያ 12/2016ዓ.ም ከረፋድ 4:00 እስከ 6:00 በተለያዩ ጉዳዮች ቆይታ እናደርጋለን::

#ጠረፍ ካሳሁን(ኪያ) ተወዳጇ ወጣቷ ድምፃዊት አብራን ትቆያለች::

ከሰሞኑ አዲስ በሰራችው ሙዚቃዋ እና መክሊቴ ለኢትዮጵያዬ በበጎ አድራጎት ተቋሟ ዙሪያ ብዙ ብላናለች::

"ነዋይ ደበበ ስለጅማ ሙዚቃ ሊፅፍልኝ ይገባል"

ከሙዚቃ የተሻገረው የድምፃዊቷ ስብዕና

"ለፋሲካ ኑ እና ከኔ ዶሮ ግዙ"

#ጥላሁንጉግሳ ተወዳጁ ተዋናይ በቤት ልማት ላይ ተሰማርቷል::

በመድረክ በድራማ እና በፊልም ስራዎቹ በርካታ አድናቂያን ያሉት ሰው “ስለምን ቤት ሰርቶ ለተጠቃሚ ላቅርብ አለ?”

"አዲስ በምሰራው ፊልም ላይ ልጄ የድምፅ ውድድሩን ካለፈች ትተውናለች"

#እሌኒ ገ/መድህን (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በቅርብ ባቋቋመችው የካፒታል ገበያ የቦርድ አባል የሆኑት ሰው የህይወት ታሪካቸውን እየፃፉ ነው::

"አባቴ ጎደኛዬ ልጆቼ መካሪዎቼ ናቸው"

ለሀገርዎ ያለዎት ምኞት ?

#መክሊት ሀደሮ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ድምፃዊት ከዝነኛዋ የጥበብ ሰው ጋር የተጣመሩበት አልበም ወጥቷል::

ከኢትዮጵያ ድምፃዊያን የማን አድናቂ ነሽ ?

#መሰንበቻን ቅዳሜ ረፋድ ከ4:00 እስከ 6:00 በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ይከታተሉን::

«የአርቴፊሻል መጫወቻ ሜዳ ለሴት ስፖርተኞች ፈታኝ ነው» ቤዛዊት ተስፋዬየ2016 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ውድድር ሲጠናቀቅ  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደረጃ ሰንጠረዡን ...
19/04/2024

«የአርቴፊሻል መጫወቻ ሜዳ ለሴት ስፖርተኞች ፈታኝ ነው» ቤዛዊት ተስፋዬ

የ2016 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ውድድር ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደረጃ ሰንጠረዡን በ32 ነጥብ እየመራ አጠናቋል። ሀዋሳ ከተማ በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ ተከታዩን ደረጃ ይዟል።

ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ ያደረገችው የሀዋሳ ከተማዋ ተጫዋች ቤዛዊት ተስፋዬ በአንደኛው ዙር ክለቧ ሀዋሳ ከተማ ውጤቱ ጥሩ መሆኑን ገልፃ በይበልጥ ለቀጣይ ጨዋታዎች ተሻሽለው እንደሚቀርቡ ተናግራለች።

በሀዋሳ ከተማ ሲደረግ በነበረው ውድድር ፉክክሩ ጥሩ እንደነበር ገልፃ የመጫወቻ ሜዳው አርቴፊሻል (ሰው ሰራሽ) መሆኑ በተለይ ለሴት ስፖርተኞች ፈታኝ ስለሚሆን ቢታሰብበት ብላለች። ከዚህ በተጨማሪም ክለቦች የተጫዋቾችን ደሞዝ በጊዜው ቢከፍሉ የተሻለ ይሆናል ስትል ተናግራለች።

ኑራ ኢማም

አርጀንቲናው ግብ ጠባቂ በኮንፍረንስ ሊግ ጨዋታ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ አግኝቶ ከሜዳ ያልወጣው ለምንድነው? ትናንት ምሽት ሊል ከ አስቶንቪላ በደረጉት የኮንፍረንስ ሊግ ወሳኝ ጨዋታ የቪላው ግብ ጠ...
19/04/2024

አርጀንቲናው ግብ ጠባቂ በኮንፍረንስ ሊግ ጨዋታ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ አግኝቶ ከሜዳ ያልወጣው ለምንድነው?

ትናንት ምሽት ሊል ከ አስቶንቪላ በደረጉት የኮንፍረንስ ሊግ ወሳኝ ጨዋታ የቪላው ግብ ጠባቂ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ሰዓት በማባከን የቢጫ ካርድ ሰለባ ሆነ፡ቀጥሎም ጨዋታው በድምር ውጤት አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት ቡድኖቹ ባመሩበት አጋጣሚ ያልተገባ ባህሪ በማሳየቱ ሁለተኛውን ቢጫ ካርድ ተመለከተ።

ነገር ግን መሀል ዳኛው ቀይ ካርድ ሳያስከትሉ ማርቲኔዝም ከሜዳ ሳይወጣ መለያ ምቱ ላይ ተሳትፎ ሁለት ምቶችን መክቶ ቪላን ለግማሽ ፍጻሜ አደረሰ።

ይህን አጋጣሚ ተከትሎ የፊፋ የጨዋታ ደንቦችን በማውጣት የሚታወቀው አለም ዓቀፉ እግርኳስ ማህበር ቦርድ(IFAb) የተሰኘው አካል በቅርቡ ያሻሻለው የቢጫ ካርድ ደንብ ልብ ይሏል።
'በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የተሰጡት የቢጫ ካርድ ማስጠንቀቂያዎች ወደ መለያ ምት ክፍለ ጊዜ አይተላለፉም'።
ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ የተሻሻለው ደንብ ትናንት ቢጠቅመውም የአንድ ጨዋታ ቅጣትን አላስቀረለትም።በቀጣይ በግማሽ ፍጻሜው የመጀሪያው ዙር መርሀግብር በቅጣት ያሚያመልጠው ይሆናል።

በ ፍቃዱ ተስፋዬ

አቶ ቢልልኝ መቆያ  የአፍሪካ የቦክስ ኮንፌዴሬሽን (AFBC) ዋና ፀሀፊ ሆነው ተመርጡ።በስፖርቱ ዘርፍ ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱት አቶ ቢልልኝ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ደርባን በተደረገ ...
19/04/2024

አቶ ቢልልኝ መቆያ የአፍሪካ የቦክስ ኮንፌዴሬሽን (AFBC) ዋና ፀሀፊ ሆነው ተመርጡ።

በስፖርቱ ዘርፍ ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱት አቶ ቢልልኝ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ደርባን በተደረገ ስብሰባ ነው የቦርድ አባላቱን ሙሉ ድምጽ በማግኘት የተመረጡት።

ያላቸው የብዙ አመታት የአመራርነት ልምድ ዘርፉን ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።

የከፍተኛ ሊግ የውድድር ፎርማት መቀያየር የሊጉን የፉክክር ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው አሰልጣኞች ተናገሩ።ባለፈው አመት ከነበረበት 3 ምድብ ዘንድሮ ወደ 2 ዝቅ ያለው ሊጉ መቀጣይ አመት ደግሞ...
19/04/2024

የከፍተኛ ሊግ የውድድር ፎርማት መቀያየር የሊጉን የፉክክር ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው አሰልጣኞች ተናገሩ።

ባለፈው አመት ከነበረበት 3 ምድብ ዘንድሮ ወደ 2 ዝቅ ያለው ሊጉ መቀጣይ አመት ደግሞ በአንድ ወጥ ሊግ ይከናወናል። ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የምድብ ለ ተፎካካሪዎቹ የአርባ ምንጩ በረከት ደሙ ጥራት ያለላቸውን ቡድኖች ወደ ቋት መሰብሰቡ የፉክክር መንፈሱን ከፍ አድርጎታል ።

የደሴ ከተማው ዳዊት ታደለ በበኩላቸው ብዙ ክለቦችን በማሳተፍ ውስጥ ጥራት ካልተገኘ ለሀገሪቱ እግር ኳስ እድገትም ችግር ነው ብለዋል።

በከፍተኛ ሊጉ በአመት ውስጥ 20 ጨዋታዎ ብቻ ይደረጉ እንደነበር ያነሱት አሰልጣኙ በዚህ የጨዋታ መጠን ሀገሪቱ ብቁ ተጫዎቾች ታገኛለች ብየ አላምንም ስለዚህ የፎርማት ለውጡ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ከፍተኛ ሊጉ በተመሳሳይ ሰው ሰራሽ ሳር ንጣፍ ሜዳዎች ላይ መደረጉ እኩል የፉክክር እድል ፈጥሯል ነገር ግን ውድድሩን በ2 ከተሞች ብቻ ከመጨረስ በ4 ከተሞች ቢደረግ ሌሎች ወጣቶችም ተደራሽ እንዲሆኑ ያግዛል የእግር ኳስ እንቅስቃሴውንም ማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የመለማመጃ ሜዳ እጥረቶችን መቅረፍ የሚያስችል የከተሞች ምርጫ ቢደረግም ሲሉ ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

ዓለማዬሁ ገላጋይ (ደራሲ) ‹‹ለንባብ ከተሰጡ፣ በንባብ ከተሠሩ፣ ንባባቸው በወርቅ እሳት ከሚፈተኑ ወርቅ ባሉትም የኪነት ስራዎቻቸውን ከሚያስጌጡ ጥቂቶች ደራሲዎች አንዱ ነው›› ይሉታል፡ ዓለማ...
19/04/2024

ዓለማዬሁ ገላጋይ (ደራሲ)

‹‹ለንባብ ከተሰጡ፣ በንባብ ከተሠሩ፣ ንባባቸው በወርቅ እሳት ከሚፈተኑ ወርቅ ባሉትም የኪነት ስራዎቻቸውን ከሚያስጌጡ ጥቂቶች ደራሲዎች አንዱ ነው›› ይሉታል፡ ዓለማዬሁ ገላጋይን፡፡ 56ኛ ዓመት ዕድሜው ላይ ያለው ዓለማዬሁ ገላጋይ የተወደለው አዲስ አበባ አራት ኪሎ ሠፈር ነው፡፡

ከክበባት እንቅስቃሴ ጀምሮ ዝንባሌው ወደ ንባብና ድርሰት የሆነው ዓለማዬሁ ገላጋይ አጫጭር እና ረጅም ልቦለዶችን ይጽፋል፡፡ በጋዜጦችና መጽሔቶችም ከአምደኝነት እስከ አዘጋጅነት ሠርቷል፡፡ ከሌሎች ደራስያን ጋር በስብስብ ያሳተማቸው ሥራዎቹ ሳይቆጠሩ አስራ ሠባት መጻሕፍትን ማሳተም የቻለው ዓለማዬሁ ገላጋይ የመጀመሪያ ሥራው ‹‹አጥቢያ›› በሚል ርእስ የተጻፈ ልቦለድ ሲሆን መቼቱም ተወልዶ ያደገበት አራት ኪሎ ሠፈር ነው፡፡

‹‹የፍልስፍና አጽናፍ›› በሚል ርእስ የተረጎመውን የአድለርን ፍልስፍናዊ ምልከታዎችን ጨምሮ በሥብሐት ገብረ እግዚአብሔር ሕይወትና ሥራዎች ላይ የሚያጠነጥኑ ሁለት መጻሕፍትን አሳትሟል፡፡ ዘጠኝ የልቦለድ ሥራዎችም አሉት፡፡ በዚህ አያበቃም በተለያዬ ጊዜ በጋዜጦችና መጽሔቶች ያስነበባቸውን መጣጥፎች በመጻሕፍት መልክም አሳትሟል፡፡

በአንድ ወቅት ‹‹በንባብ ወደ ውጭ ተሰድጄ ነበር፤ ከስደት የመለሰኝ የእጓለ ገ/ዮሐንስ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ ነው›› ሲል የተደመጠው ዓለማዬሁ ገላጋይ በቅርቡ ደግሞ በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ አንኳር ደራስያንን ሥራዎች እና ማንነት የፈተሸበትን ሥራውን ‹‹ማዕበል ጠሪ ወፍ›› በሚል ርእስ አሳትሟል፡፡

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ‹‹ለተሻለ ነገ እናንብብ›› የንባብ ዘመቻ የምጊዜም ሦስት ምርጥ መጽሐፉን እንዲያስተዋውቅ ጋብዞታል፡፡

1-የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ፡ እጓለ ገ/ዮሐንስ
2-የባሲሊቆስ እንባ፡ ትዕግስት ታፈረ ሞላ
3- ያ ደግ ሰው ግርባብ፡ ፈቃዱ አየልኝ

19/04/2024

ወቅታዊ ውይይት-

በአዲስ አበባ ከተማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዙሪያ የሚደረግ ውይይት

👉 አታላንታ ከ ሊቨርፑል ከደቂቃዎች በኋላ በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ በዩሮፓ  ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ መርሐግብር ቤርጋሞ ላይ አታላንታ ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ  ከምሽ...
18/04/2024

👉 አታላንታ ከ ሊቨርፑል

ከደቂቃዎች በኋላ በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ በዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ መርሐግብር ቤርጋሞ ላይ አታላንታ ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በአገር አቀፍ ስርጭት ቅኝት በኳስ ሜዳዎች ወደ እርስዎ እናደርሳለን።

ማን ያሸንፋል? የጨዋታ ግምትዎን ያስቀምጡ!!

ፕሮግራሙን አፍሩ ፊልም ፕሮሞሽንና ኢንተርቴይመንት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬሽን ጋር በመተባበር በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ያቀርቡታል።

ቅኝት በኳስ ሜዳ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የቀድሞ ክለቡን ጁቬንቱስ በክስ ረትቷል ጁቬንቱስ ለ ሮናል ከ 9.7 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ያልተከፈለ ደመወዙን እንዲከፍል ተወስኖበታል። የ39 አመቱ ሮናልዶ ከ2018 እስከ 2...
18/04/2024

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የቀድሞ ክለቡን ጁቬንቱስ በክስ ረትቷል

ጁቬንቱስ ለ ሮናል ከ 9.7 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ያልተከፈለ ደመወዙን እንዲከፍል ተወስኖበታል።

የ39 አመቱ ሮናልዶ ከ2018 እስከ 2021 ለጣሊያኑ ክለብ ጁቬንቱስ መጫወቱ ይታወሳል። ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር በነበረበት ጊዜ በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ደመወዙን በከፊል ለማዘግየት ተስማምቶ ቆይቷል። ይህን ያልተከፈለ ከ9.7 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ደመወዙን (10.35 ሚሊዮን ዶላር ) ከነወለዱ ጁቬንቱስ ለቀድሞ ተጫዋቻቸው እንዲከፍሉት የጣልያን እግርኳስ ፌደሬሽን ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ጁቬንቱስ ረቡዕ ዕለት ባወጠው መግለጫ “በፌደሬሽኑ የግልግል ቦርድ የተወሰነውን ውሳኔ እንገመግማለን” ብሏል። የፌደሬሽኑ ውሳኔ በክለቡ “ማጭበርበር አለመፈጠሩን” እውቅና መስጠቱን ገልፆ ሮናልዶ እንዲህ ዓይነቱ የቅነሳ ስምምነት ውል ለማድረግ በራሱ ፈቃደኛነት ላይ የተመሰረተ እንደነበረም አስታውሷል።

አንዳንድ የጁቬንቱስ ተጫዋቾች ክለቡ የፋይናንስ ችግር በገጠመው ወቅት የአራት ወር ደሞዛቸውን ለማዘግየት ተስማምተው ነበር። ሮናልዶ ከጁቬንቱስ ጋር ባደረገው ስምምነት የደመወዙን የተወሰነ ክፍል ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ተስማምቷል ነገርግን የተስማማውን ገንዘብ እስካሁን አልተቀበለም።

የሮናልዶ የመጀመሪያ ጥያቄ 19.5 ሚሊዮን ዩሮ ተመላሽ ክፍያ ነበር። ፌደሬሽኑ ባደረገው ማጣራት በሁለቱም ወገኖች መካከል ቸልተኝነት እንደተፈጠረ በማመኑ 9,774,166.66 ዩሮ ደመወዝ እና ወለዱን ከነ ህጋዊ ወጪዎች ጁቬንቱስ እንዲከፍል ውሳኔ አስተላልፏል ሲል ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ሮናልዶ በ2018 ነበር ከሪያል ማድሪድ ለቅቆ ጁቬንቱስን የተቀላቀለው። ለአሮጊቶቹ በ134 ጨዋታዎች 101 ጎሎችን አስቆጥሯል። ሁለት የሴሪ ኤ ዋንጫዎችን ጨምሮ አምስት የሀገር ውስጥ ዋንጫዎችን ከክለቡ ጋር አንስቷል።

በአሁኑ ሰአት ለሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር እየተጫወተ ያለው ፖርቱጋላዊ ከጁቬንቱስ ከወጣ በኋላ ማንቸስተር ዩናይትድን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

በሐዋርያው ጴጥሮስ

አርቲስት ተስፋዬ አበበከበርካታ ወጣትና አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎች ጀርባ ተደጋግመው የሚጠቀሱ "የከያኒያን አባት" ናቸው። ለዛም ነው አንጋፋውን አርቲስት ተስፋዬ አበበን የሙያ ልጆቻቸው "ፋዘር...
18/04/2024

አርቲስት ተስፋዬ አበበ

ከበርካታ ወጣትና አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎች ጀርባ ተደጋግመው የሚጠቀሱ "የከያኒያን አባት" ናቸው። ለዛም ነው አንጋፋውን አርቲስት ተስፋዬ አበበን የሙያ ልጆቻቸው "ፋዘር" በማለት የሚጠሯቸው።

በቴአትር፣ በሙዚቃ ፣ በዝግጅት፣ በውዝዋዜ እንዲሁም በግጥምና ዜማ ደራሲነታቸው አሁን ድረስ በኪነ ጥበቡ አለም አበርክቷቸው የላቀ እንደሆነ የሚነገርላቸው አርቲስት ተስፋዬ አበበ፤ በ1933 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተወልደዋል። ትምህርታቸውንም በሊሴ ገ/ማሪያም መከታተላቸውን ታሪካቸው ይመሰክራል።

ገና በለጋ ዕድሜያቸው ልዩ የጥበብ ፍቅር የነበራቸው ሲሆን፤ በሀገር ፍቅርና በማዘጋጃ ቤት ይዘጋጁ የነበሩ ዝግጅቶችን በአንክሮ ይከታተሉ ነበር። የቀዳማዊ ሃ/ሥላሴ ቴአትር ቤት የአሁኑ ብሔራዊ ቴአትር ከመመረቁ በፊት ኦስትሪያዊው ፍራንስ ዙልዌከር ወደኦስትሪያ በመውሰድ በቴአትር ካሰለጠናቸው 51 ወጣቶች መካከል አንዱ ነበሩ።

በ1948 ዓም የቀዳማዊ ሃ/ሥላሴ ቴአትር ቤት ሲመረቅ የቀረበውን "ዳዊትና ኦርዮን" የተሰኘውን ቴአትር ጨምሮ ስነ-ስቅለት፣ ሐኒባል እና ቴዎድሮስ በመሳሰሉት የመድረክ ስራዎች ላይ ብቃታቸውን አሳይተዋል።

አርቲስቱ ከ40 በላይ ቴአትሮችን ፅፈው አዘጋጅተዋል። ከ500 በላይ የግጥምና ዜማ ስራዎችን በመፍጠር ለሒሩት በቀለ፣ ለጥላሁን ገሰሰ፣ ለሙሉቀን መለሰና ለሌሎችም አንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ተደማጭ ሙዚቃዎችን አበርክተዋል። አሁን ላይ የራሳቸውን የኪነጥበብ ማሰልጠኛ በመክፈት የበዙ ወጣቶችን በማፍራት ላይ ይገኛሉ።

በአገራችን የኪነጥበብ ታሪክ ውስጥ ስለነበራቸው ጉልህ አስተዋፅኦ ዕውቅና ለመስጠትም የአአዩ ሐምሌ 5/2006 ዓም የክብር ዶክትሬት ማዕረግን ተሰጥቷቸዋል።

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 "ለተሻለ ነገ እናንብብ" በሚል በጀመረው የ100 ቀናት የንባብ ዘመቻ መሰረት፤ አንጋፋው አርቲስት ተስፋዬ አበበ ተከታዬቹን ሶስት መፅሐፍቶች መርጠዋል።

1- ኦሮማይ =በበዓሉ ግርማ

2- የእስራት ዘመን- በሀበሻ ሀገር = በዶ/ር ሔነሪ ብላንክ

3- አጤ ምኒልክ = በጳውሎስ ኞኞ

18/04/2024

አዲስ ፎረም -የአዲስ አበባ ፅዳት፣የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ

17/04/2024

የሲዳማ ክልል ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ያለውን የቆየ አጋርነት እንደሚያጠናክር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለፁ፡፡በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ...

"የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን ለገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው" የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ሰብሳቢ ከፍተኛ ሊጉን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የውድድር ሰብሳቢው አቶ ሙራድ አብዲ ገል...
17/04/2024

"የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን ለገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው"
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ሰብሳቢ

ከፍተኛ ሊጉን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የውድድር ሰብሳቢው አቶ ሙራድ አብዲ ገልጹ። አምና ከነበረው ሶስት ምድብ ዘንድሮ ወደ ሁለት መውረዱ የሊጉን የፉክክር መጠን እና የወራጅ ቀጠናውን ትግል እጅግ አድምቆታል ሱሉ ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግረዋል።

ከሁለቱም ምድቦች አምስት አምስት ክለቦች ወደ አንደኛ ሊግ መውረዳቸው የውድድሩን ድምቀት ጨምሮታልም ብለዋል።

የከፍተኛ ሊጉን ፎርማት ወደ አንድ ወጥ ሊግ የመቀየር እና እንደ ፕሪሚየር ሊጉ ለገበያ ለማቅረብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የውድድሩ ሰብሳቢ ጠቁመዋል።

ፌደሬሽኑ ወጣት ተጫዋቾችን ለማበረታታት የአምስት ተጫዋቾች ቅያሬን በከፍተኛ ሊጉ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን ከአምስቱ ተቀያሪ ተጫዋቾች ውስጥ ሁለቱ የግድ ከክለቦቹ ታዳጊ ቡድኖች የመጡ (ከ 18-22 አመት በታች) መሆን እንዳለባቸውም ገልፀዋል። በዚህም የኢትዮጵያን እግር ኳስ መረከብ የሚችሉ ወጣቶች እድሉን እያገኙ ነው ብለዋል።

የከፍተኛ ሊግ ውድድር ምድብ ሀ በሀዋሳ ከተማ ምድብ ለ ደግሞ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተደረገ ይገኛል።

ሐዋርያው ጴጥሮስ

የከፍተኛ ሊግ ውድድር ሊጠናቀቅ የ6 ጨዋታ እድሜ ብቻ ቀርቶታል።ከሁለቱም ምድቦች ወደ ሊጉ የሚያድጉትን ክለቦች ቀድሞ የጠቆመ በሚመስለው ፉክክር ባለፈው አመት የወረዱትን አርባ ምንጭና ኢትዮ ...
17/04/2024

የከፍተኛ ሊግ ውድድር ሊጠናቀቅ የ6 ጨዋታ እድሜ ብቻ ቀርቶታል።

ከሁለቱም ምድቦች ወደ ሊጉ የሚያድጉትን ክለቦች ቀድሞ የጠቆመ በሚመስለው ፉክክር ባለፈው አመት የወረዱትን አርባ ምንጭና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚመልስ ይመስላል።

ነገ በአዲስ ስፖርት እንግዳ የምድብ ሀ ተፎካካሪ ወጣት አሰልጣኞች ጋር ቆይታ ያደርጋል።

የአርባ ምንጭ ከተማው በረከት ደሙየ እና የደሴ ከተማው ዳዊት ታደለ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ነገ ሀሙስ ከ5:00 - 6:00 ይጠብቁን።

ሀያ አንደኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና አስራ ሰባተኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በ አዲስ አበባ ከተማ እንደሚከናውን የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አሳወቀ።የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን...
17/04/2024

ሀያ አንደኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና አስራ ሰባተኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በ አዲስ አበባ ከተማ እንደሚከናውን የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አሳወቀ።

የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ህይወት መሀመድ እንዳሉት ከትግራይ ክልል በስተቀር ሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳድሮች በአስራ አንድ የባህል ስፖርቶች ይሳተፋሉ።

ውድድሩም ከሚያዝያ12 እስከ ሚያዝያ 20 2016 ዓ፡ም በ አዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል።

የባህል ስፖርት ውድድሮችና ፌስቲቫል ከውድድር ባለፈ ብሄርና ብሄረሰቦችን የማቀራርብ ወንድማማችነትን የማጠናከር ዓላማ እንዳለው የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ናቸው።

የውድድሩ መክፈቻ ውድድር በአዲስ አባባ ስታዲዬም ሲከናወን የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚና ጃን ሜዳ ስፖርት ማዕከል ውድድሮቹን የሚያስተናግዱ ይሆናል።

በውድድሩ ከአንድ ሺ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉም ተነግሯል።

ፍቃድ ተስፋዬ

ዶክተር  እሌኒ ገ/መድህን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ሥራ እንዲገባ በማድረግ ይታወቃሉ፣ አዳዲስ የኢኮኖሚ ፈጠራ ሐሳቦች አፍላቂ  ናቸው ይባልላቸዋል፡ ፡ታዋቂዋ ኢኮኖሚስት ኢሌኒ ገብረ መድኅ...
17/04/2024

ዶክተር እሌኒ ገ/መድህን

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ሥራ እንዲገባ በማድረግ ይታወቃሉ፣ አዳዲስ የኢኮኖሚ ፈጠራ ሐሳቦች አፍላቂ ናቸው ይባልላቸዋል፡ ፡ታዋቂዋ ኢኮኖሚስት ኢሌኒ ገብረ መድኅን (ዶ/ር)፡፡ ስለ አስተዳደጋቸው ሲናገሩ ‹‹ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ ትምህርቴን እስካጠናቅቅ የማንበብ ጥማት ነበረብኝ፤ በጣም በጣም ነበር የማነበው፡፡ እህቴ እና እኔ የተለያዬ ትምህርት ቤት እንማር ስለነበር ከየትምህርት ቤታችን ቤተ መጻሕፍት ስምንት ስምንት መጻሕፍትን በውሰት ማውጣት እንችል ነበር፤ ስለዚህ ሁለታችንም በሳምንት አስራ ስድስት መጻሕፍትን እናነብ ነበር›› ይላሉ፡፡

ዶ/ር ኢሌኒ አሜሪካን ሀገር በሚገኘው ኮርኔል ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከሚችንጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ ከስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢኮኖሚስት ሆነው እንዲሁም የምርት ልውውጥ ኤክስፐርት በመሆን ሠርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዓለም አቀፉ የምግብ ፓሊሲዎች ምርምር ተቋም ውስጥ አገልግለዋል፡፡ ‹‹ካደግሁ ዩኒቨርሲቲ ከገባሁ በኋላም የማንበብ ልምዴ ቀጥሏል፤ ነገር ግን እንደልጅነት ዘመኔ በሳምንት አሥራ ስድስት መጻሕፍት የማነብበት ጊዜ አልነበረም›› የሚሉት ዶ/ር ኢሌኒ ‹‹አሁንም ቢሆን ግን ሳላነብ አልተኛም፤ ትራሴ ላይ የመጻሕፍት ቁልል አለ›› ይላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው አገልግለዋል፡፡ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የእርሻ ሰብል ግብይት አሠራሮችንም በመፍጠር ከ15 ሚሊየን በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርገዋል፡፡ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ በኃላፊነት የሠሩት ዶ/ር እሌኒ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት / UNDP/ የፈጠራ ሥራዎች ዋና ዳይሬክተር ነበሩ፡፡ ብሉ ሙን ኢትዮጵያ የተሰኘ በግብርና ዘርፍ አዋጪ የንግድ ኃሳብ ይዘው ብቅ ለሚሉ ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች ስልጠና እና መነሻ ፋይናንስ የሚሰጥ ድርጅት መስርተው ይመራሉ፡፡

የዚህን ዘመን የንባብ ትዝብት ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ ‹‹በአሁኑ ዘመን ትኩረታችንን የሚስቡ ብዙ ጉዳዮች አሉ፤ ሕይወታችን ውጥረት ይበዛዋል፤ ስለዚህ እንደቀደመው ዘመን ለማንበብ የሚሆን ጊዜ እየጠበበ ነው››

ከኤፍ.ኤም.አዲስ 97.1 ‹‹ለተሻለ ነገ እናንብብ›› ዘመቻ የምንጊዜም ሦስት ምርጥ መጽሐፎቻቸውን ይግለጹ ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምርጫቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

1-Long walk to freedom: Nelson Mandela
2-The Prophet: Kahlil Gibran
3-Becoming: Michelle Obama

የስፔኑ ባርሴሎና ከፈረንሳዩ ፒኤስዤ ጋር ዛሬ ምሽት 4:00 በኤፍ አዲስ 97.1የጨዋታ ግምትዎን ያስቀምጡ!!በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ2023/24 የውድድር ዓመት የሩብ ፍጻሜ የመልስ መርሐግ...
16/04/2024

የስፔኑ ባርሴሎና ከፈረንሳዩ ፒኤስዤ ጋር ዛሬ ምሽት 4:00 በኤፍ አዲስ 97.1

የጨዋታ ግምትዎን ያስቀምጡ!!

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ2023/24 የውድድር ዓመት የሩብ ፍጻሜ የመልስ መርሐግብር በኢስታዲዮ ኦሊምፒኮ ደ ሞንዡክ የስፔኑ ባርሴሎና ከፈረንሳዩ ፒኤስዤ ጋር ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ የሚያደርጉትን አጓጊ ጨዋታ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በአገር አቀፍ ስርጭት በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ በቀጥታ ቅኝት በኳስ ሜዳዎች ወደ እርስዎ ያደርሳሉ።

ፕሮግራሙን አፍሩ ፊልም ፕሮሞሽንና ኢንተርቴይመንት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬሽን ጋር በመተባበር በኤፍኤም አዲስ 97.1 ላይ ያቀርቡታል።

ቅኝት በኳስ ሜዳ

አወዛጋቢው የእንግሊዝ ጠቅላይ ምኒስትር ሪሺ ሱናክ የሲጋራ ክልከላ ደንብየዩናይትድ ኪንግደሙ ጠ/ሚኒስትር ሱናክ አዲስ ነው የተባለ የሲጋራ ክልከላ ደንብ ዛሬ ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበ...
16/04/2024

አወዛጋቢው የእንግሊዝ ጠቅላይ ምኒስትር ሪሺ ሱናክ የሲጋራ ክልከላ ደንብ

የዩናይትድ ኪንግደሙ ጠ/ሚኒስትር ሱናክ አዲስ ነው የተባለ የሲጋራ ክልከላ ደንብ ዛሬ ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአገሪቱ በአመት ሰማንያ ሺ ዜጎች በሲጋራ ምክንያት ብቻ ለሞት እንደሚዳረጉና ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚመጡ በሽታዎችን ለማከም አገሪቱ በዓመት አስራ ሰባት ቢሊዮን ፓውንድ ወጪ እንደምታደርግ ይነገራል።

ታዲያ ይህንን ጉዳት በመቀነስ ለዜጎች ጤና ለአገር ኢኮኖሚ የተሻለ ያደርጋል የተባለ አዲስ የሲጋራ ክልከላ ረቂቅ ደንብ ዛሬ በጠ/ሚነስትር ሪሺ ሱናክ ለም/ቤት ቀርቦ ድምጽ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲሱ ዕቅድ እ.አ.አ ከጥር 2009 በኋላ የተወለደ ማንኛውም ዜጋ ሲጋራን መግዛትም ሆነ መሸጥን የሚከለክል ነው። ይሁን እንጂ አዲሱ ዕቅድ ከወዲሁ ተቃውሞ አያስተናገደ ይገኛል። ክልከላው ለህገ ወጥ የሲጋራ ንግድ ዜጎችን የሚጋብዝ የተጠቃሚውን ቁጥር ከፍ ያደርጋል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰሙ ነው።

የቀድሞ ጠሚኒስትር ሊዝ ትሩስም ተመሳሳይ አስተያየት አላቸው።እንደ ነጻ አገር ውሳኔ የመስጠት አቅምን ያዳበሩ ዜጎችን ሲጋራ አታጪሱ ማለት አግባብ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል። የዚህ መረጃ ምንጭ ዘሚረር ባለፈው ወር አሰባስብኩት ባለው የህዝብ ቃለ መጠይቅ 53በመቶዎቹ አዲሱን የጠ/ሚኒስትር ሪሺ ሱናክን ዕቅድ አይደግፉም ብሏል።

በፍቃዱ ተስፋዬ

ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ በሻህለረጅም ዓመታት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህርነት እና ተመራማሪነት የሠሩት ፕሮፌሰር ብሩክ ከመምህነትም በተጨማሪ ሀገራቸውን በዲፕሎማትነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ...
16/04/2024

ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ በሻህ

ለረጅም ዓመታት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህርነት እና ተመራማሪነት የሠሩት ፕሮፌሰር ብሩክ ከመምህነትም በተጨማሪ ሀገራቸውን በዲፕሎማትነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ በልዩ ልዩ ሀገራት ማለትም በሩዋንዳ፣ በጀርመንና በአሜሪካ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አስተምረዋል።

ስለ ትምህርት የኋላ ታሪካቸው ሲናገሩም ‹‹የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪዬን በፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት የሠራሁ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪዬንም በፖለቲካና ሚዲያ ሳይንስ ሠርቻለሁ›› ይላሉ፡፡ ስለሥራ ልምዳቸው እንዲህ ይላሉ
‹‹በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከማስተማር በተጨማሪ የውጭ ግንኙነት ቢሮ ኀላፊ በመሆን 3 ዓመት አገልግያለሁ ፣ በኃላፊነት ዘመኔ ከየውጭ ሀገር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በርካታ ስምምነቶች ተደርጓል።

ለ20 ዓመት ተቋርጦ የነበረውን 'የክብር ዶክተሬት' ማዕረግ በማንቀሳቀስ ለከበደ ሚካኤልና ለሀዲስ ዓለማየሁ እንዲሰጥ አስተዋጽኦ አድርጊያለሁ፡፡ የኢትዮጵያ የፓለቲካል ሳይንስ ሙያ ማኅበር መሥራችና የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዘዳንት በመሆን (ከ1990 እስከ 1993) ድረስ አገልግያለሁ›› ይላሉ፡፡

ፕሮፌሰር ብሩክ ከዚህም በተጨማሪ አሜሪካ በሚገኘው በኦሀዮ (Ohio) ዩኒቨርስቲ Global Leadership Center ዳይሬክተር የነበሩ ሲሆን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል። በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ፣ እንዲሁም ተጠባባቂ አምባሳደር ፣ በፓሪስ የዩኔስኮ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ሆኖ ማገልገል ለሀገራቸው ካደረጓቸው በርካታ ጉልህ አስተዋፅኦዎች ይጠቀስላቸዋል።

ከፓሪስ UNESCO የገንዘብና ባለሙያዎችን experts በማስተባበር የአክሱም ሀውልት እንዲመለስና እንዲተከል፣ የሐረር ከተማ የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ለማስቻል በተደረጉ ጥረቶች ውስጥ ሰፊ ተሳትፎ አድርገዋል።

ከሀገራቸው ቋንቋ በተጨማሪ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛና ጀርመንኛን የሚችሉት ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ከለውጡ ወዲህም ቢሆን በUSA የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል እንዲሁም በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው 'የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ሙያ ማህበር' ፕሬዚዳንት ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

‹‹ለተሻለ ነገ እናንብብ ዘመቻ የምንጊዜም ምርጥ ሦስት መጽሐፎቻቸውን እንዲያሳውቁ ጋብዟቸዋል፡፡

1-አርአያ፡ ግርማቸው ተ/ሐዋርያት
2-እሳት ወይ አበባ፡ ጸጋዬ ገ/መድኅን
3-ከአድማስ ባሻገር፡ በዓሉ ግርማ

"የሙዚቃ ስራዎቼን ለማበላለጥ አቅም አጣለሁ"!  ዝነኛው የሙዚቃ ሰው ሙላቱ  አስታጥቄ     የኢትዮጵያን  ሙዚቃ ተራቆበታል፥ በማሲንቆና ዋሽንት  የተከሸኑ  ባህላዊ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ ያዘወ...
15/04/2024

"የሙዚቃ ስራዎቼን ለማበላለጥ አቅም አጣለሁ"!

ዝነኛው የሙዚቃ ሰው ሙላቱ አስታጥቄ

የኢትዮጵያን ሙዚቃ ተራቆበታል፥ በማሲንቆና ዋሽንት የተከሸኑ ባህላዊ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ ያዘወትራል፥
ለጥላሁን ገሰሰ እና ሙሉቀን መለሰ አድናቆቱን ይቸራል፤
አራቱንም የሀገር ቤት ቅኝቶች በፍቅር ያደምጣል።
በኮንሶ፣ በወላይታ፣ በከፋ፣ በደራሼ፣ ጋሞ፣ አኙዋክ፣ በሱርማና በሌሎችም ብሔረሰቦች ሙዚቃ ላይ የሱሩትን ሙያተኞች ደግሞ ደጋግሞ ያወድሳል።

በጥበብ ውስጥ ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ የዘለቀው አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ የኢትዮጵያን ጃዝ ሙዚቃ ለማስተዋወቅ ዓለምን ዞሯል። ከታዋቂ ሰዎች ጋርም ኮንሰርቶችን ሰርቷል

በመጀመሪያው አልበም “አይፈራም ጋሜ አይፈራም”፣ “አልማዝ” እና “አክሱም” የተሰኙትን ኢትዮጵያዊ ሙዚቃዎችን ሲያካትት በሁለተኛው “ቆንጂት” እና “ከረዩ” የተሰኙትን አክሎበታል።

በዚ አጋጣሚ ነበር ኢትኖግራፈሩ ሙዚቀኛ ሙላቱ አስታጥቄ “ኢትዮ ጃዝ” የተሰኘውን የሙያ ልጁን ለመጠንሰስ የበቃው። አክብሮቱና ትህትናው ወደር አይገኝለትም። ተሞክሮውን ለማካፈል ደስ እያለው ጊዜውን ይሰጣል ።

በቀዳሚው ጣብያችን ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ከምስረታው ጀምሮ የአፍሪካ ጃዝ መንደርን ጠንስሶ በማቅረብ ላይ ይገኛል። ከአንጋፋው ባልደረባችን ጋር ''በእኔ ምርጥ'' መሰናዶዋችን ላይ ቆይታ አደረግን። ስራዎቹን ጠንቅቆ እንደሰራቸውና ለማበላለጥ እንደሚቸገር አጫወተን!!!

ነጥሎ ሶስት ተመራጭ ሙዚቀኞችን እንዲጠራ ጫን ብለን ጠየቅነው። የተወዳጁ ሙዚቀኛ ጥላሁንን ገሰሰ 'ያላንቺ አልኖርም' የተባለውን ሙዚቃ ጠራ። ከሙሉቀን ጋር የሰራቸውን ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችና በጥቅሉ ሁሉንም የሙዚቃ ቅንብሮቼን እወዳቸዋለው ሲል አከለ። የሰይፉ ዩሐንስን የከርሞ ሰውን ጨምሮ የሰራቸው በርካታ ስራዎቹ አይጠገቤነታቸው አያጠያይቅም።

ከዘመናችን መዚቃ የማንን ትሰማለህ? ብለን ጠየቅነው። ''ወጣት የባህል ሙዚቀኞች አጥብቄ አከብራለሁ እነሱን አመሰግኑልኝ" ።

በዳዊት አበበ

15/04/2024
15/04/2024

ኢትዮጵያዊው አትሌት ሲሳይ ለማ የ128ኛው የቦስተን ማራቶን አሸናፊ ሆነ::

ከዓለማችን ስድስቱ ሜጀር ማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የቦስተን ማራቶን ዛሬ ሲከናወን ከተጠባቂ አትሌቶች መካከል ኢትዮጵያዊው አትሌት ሲሳይ ለማ ሲያሸንፍ ሌለኛው ኢትዮጵያዊ ሞሀመድ ኢሳ ተከትሎት ውድድሩን አጠናቋል።

ሲሳይ ውድድሩን ለመጨረስ 2 ሰዓት ከ06 ከ 17 ሴኮንድ ወስዶበታል።

ኬኒያዊው አትሌት ኢቫንስ ቺቤት ኢትዮጵያዊያኑን ተከትሎ ሶስተኛ ሆኖ ገብቷል።

የሴቶቹ ውድድር በኬንያዊያን የበላይነት ተቋጭቷል። የአምና የቦታው አሸናፊ ሄለን ኦቢሪ በ2:22:37 አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሌላኛዎቹ ኬንያዊያን ሻሮን ሎኬዲ በ2:22:45 ሁለተኛ እና ኤድና ኪፕላጋት በ2:23:21 ሶስተኛ ሆነዋል። ኢትዮጵያዊያኑ ቡዜ ድሪባ እና ሰንበሬ ተፈሪ ተከታትለው በመግባት አራተኛ እና አምስተኛ ሆነው ውድድራቸውን ቋጭተዋል።

ውድድሩን 1ኛ ሆነው ያጠናቀቁ አሸናፊ አትሌትሌቶች 150,000 ዶላር የሚያፍሱ ሲሆን ሁለተኛ እና ሶስተኛ ለሚወጡት ሯጮች 75,000 እና 40,000 ዶላር ተዘጋጅቷል። የቦታውን ክብረወሰን ለሚያሻሽሉ የሁለቱም ፆታ ሯጮች 50,000 ዶላር የጉርሻ ሽልማትም መዘጋጀቱ ታውቋል።

የወንዶች ውጤት

🥇 ሲሳይ ለማ 🇪🇹 2:06:17
🥈 መሃመድ ኢሳ 🇪🇹 2:06:58
🥉 ኢቫንስ ቼቤት 🇰🇪 2:07:22

የሴቶች ውጤት

🥇 ሄለን ኦቢሪ 🇰🇪 2:22:37
🥈 ሻሮን ሎኬዲ 🇰🇪 2:22:45
🥉 ኤድና ኪፕላጋት 🇰🇪 2:23:21

በ ፍቃዱ ተስፋዬ እና ሐዋርያው ጴጥሮስ

(የኤትሌት ሲሳይ ለማ ድልን በቪዲዮ ይመልከቱ)

ኦቦ ሌንጮ ለታበበርካቶች ዘንድ በፖለቲካ ሰውነታቸው በጉልህ ይታወሳሉ። ገና በለጋ ዕድሜያቸው የጀመሩት በትጥቅ የተደገፈው የፖለቲካ ትግላቸው በበርካታ ውጣ ውረዶች የተሞላ እንደሆነ ታሪካቸው ...
15/04/2024

ኦቦ ሌንጮ ለታ

በበርካቶች ዘንድ በፖለቲካ ሰውነታቸው በጉልህ ይታወሳሉ። ገና በለጋ ዕድሜያቸው የጀመሩት በትጥቅ የተደገፈው የፖለቲካ ትግላቸው በበርካታ ውጣ ውረዶች የተሞላ እንደሆነ ታሪካቸው ይመሰክራል።

ትውልዳቸውና እድገታቸው ወለጋ ደምቢዶሎ ነው።ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የተከታተሉት ደግሞ አዳማ።ወደአሜሪካ አቅንተው ከፍተኛ ትምህርታቸውን በኬሚካል ኢኒጂነሪንግ ተመርቀዋል። በቅርብ የሚውቋቸው ሁሉ አንባቢ እና ፈጣን አእምሮ ያላቸው ናቸው ይሏቸዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን (ኦነግ) ከመሰረቱት ቀዳሚ አመራሮች አንዱ ናቸው። በትጥቅ የታገዘው የትግል ታሪካቸው ከሀገር ውስጥ እስከውጪ የሚታወቁበትም ሆኖ አልፏል። አብዛኛውን እድሜያቸው በትግል ነው ያሳለፉት።«ሶስት ልጆች ወልጃለው።ልጆቼን ወለድኳቸው እንጂ አላሳደኳቸውም።እኔ ዘመኔን ሁሉ ታጋይ ሆኜ ተለይቻቸው ነው የኖርኩት።ባለቤቴም በደርግ ለ10 ዓመት ታስራ ስለነበር ልጆቻችን ተገቢውን የወላጅ ክብካቤ አላገኙም ነበር »ሲሉ ይናገራሉ።

በወጣትነት ስህተት መስራታቸውን በትጥቅ ትግል እና በአብዮት መንግስት መጣል ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መፍጠር እንደማያስችል ዘግይተው መረዳታቸውን በዚህ ምክንያት የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴን መደገፍ ማቆማቸውን ይገልጻሉ።በምትኩ ወደዲሞክራሲ የሚወስዱ የሲቪልና የፖለቲካ ጥረቶችን መደገፍ ምርጫቸው መሆኑን ያወሳሉ።

አሁን ድረስ የዴሞክራሲ አቀንቃኝ በመሆን ለሀገር ይጠቅማል ያሉትን ሀሳብ በማዋጣት የሚታወቁት ኦቦ ሌንጮ፤ በሚሰጧቸው አስተያየቶች በአንዳንዶች ዘንድ አወዛጋቢ ቢባሉም ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ከማዋጣት ወደሗላ እንደማይሉ ይናገራሉ።

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ "ለተሻለ ነገ እናንብብ" በሚል በጀመረው የመቶ ቀናት ግድድር፤ ኦቦ ሌንጮ ለታም የምንጊዜም ምርጦቼ ናቸው ያሏቸውን መፅሐፍት እንደሚከተለው አሳውቀውናል።

1- War and Peace በሊዮ ቶሎስቶይ

2- Nineteen Eighty - Four በጆርጅ ኦርዌል

3- The Wretched of the Earth በፍራንቴዝ ፋኖን

ኢትዮጵያዊያን በሚጠበቁበት የቦስተን ማራቶን አንደኛ ለሚወጡ 150ሺ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።እድሜ ጠገቡ የቦስተን ማራቶን ለ128ኛ ጊዜ ሊደረግ ዝግጅቱን ጨርሷል። ከ100 በላይ ከሆኑ ...
14/04/2024

ኢትዮጵያዊያን በሚጠበቁበት የቦስተን ማራቶን አንደኛ ለሚወጡ 150ሺ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።

እድሜ ጠገቡ የቦስተን ማራቶን ለ128ኛ ጊዜ ሊደረግ ዝግጅቱን ጨርሷል። ከ100 በላይ ከሆኑ ሀገራት የተውጣጡ ከ30ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በውድድሩ ለመካፈል በቦስተን ተሰይመዋል። ሰኞ መጋቢት 7/2016 የሚደረገውን ማራቶን ለሚያሸንፉ አትሌቶችም የውድድሩ አዘጋጆች ዳጎስ ያለ የሽልማት ገንዘብ አሰናድተዋል።

አዘጋጆቹ በአጠቃላይ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ለውድድሩ አሸናፊዎች እንሸልማለን ሲሉ ተናግረዋል። በሁለቱም ፆታ ያሉ ባለ ድሎች እኩል የገንዘብ መጠን እንደሚያገኙ ታውቋል። ውድድሩን 1ኛ ሆነው ያጠናቀቁ አሸናፊ አትሌትሌቶች 150,000 ዶላር የሚያፍሱ ሲሆን ሁለተኛ እና ሶስተኛ ለሚወጡት ሯጮች 75,000 እና 40,000 ዶላር ተዘጋጅቷሉ። ሽልማቱ እስከ አስረኛ ደረጃ ድረስ ለሚያጠናቅቁ አትሌቶችም እንደየ ድርሻቸው ተከፋፍሏል።

የቦታውን ክብረወሰን ለሚያሻሽሉ የሁለቱም ፆታ ሯጮች 50,000 ዶላር የጉርሻ ሽልማትም መዘጋጀቱ ታውቋል። የቦስተን ማራቶን የቦታውን ክብረወሰን በሴቶች በ2014 ብዙነሽ ዳባ 2:19:59 እና በወንዶቹ ደግሞ 2011 ጄኦፍሪ ሙታይ 2:03:02 ይዘውታል። ከዚህም ባለፈ የዊልቼር እና የአካል ጉዳት ምድብ አሸናፊዎችም ከፍተኛ የሽልማት ገንዘብ ያገኛሉ።

በዚህ ውድድር ላይ ከ15 በላይ ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ፆታ ለአሸናፊነት ይሮጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሃዋርያ ጴጥሮስ

Address

Churchil Road
Addis Ababa

Telephone

+2515172516

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/:

Videos

Share

Our Story

FM Addis 97.1 is the First FM radio station in Ethiopia . On air since 2000. You can listen our station for 24 hours throughout the country and outside Ethiopia.

በ1992 ዓ.ም የተመሰረተውና በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ በተለያዩ የማሰራጫ አማራጮች በመላ ሀገሪቱና በባህርማዶ ለሚገኙ አድማጮቹ ለ24 ሰአታት የተለያዩ ዝግጅቶች ይቀርቡበታል፡፡ የፌስ ቡክ ትስስራችን ቤተሰብ በመሆንዎም እናመሰግናለን፡፡

Nearby media companies


Other Media/News Companies in Addis Ababa

Show All

You may also like