19/04/2024
#የአንድ አመት ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት ተያዘ ‼
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ኮሶል ቀጭን መንደር ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ ፀብ እናት የአንድ ዓመት ሴት ህፃን ልጅ ጥላ በመጥፋቷ ወላጅ አባት ቲቲዮስ ኪያግላስ የተባለው ተጠርጣሪ የአንድ ዓመት ህፃን ልጁ እያለቀሰች ስታስቸግረዉ በሁኔታው ተበሳጭቶ የአንድ አመት ልጁን በህይወት ለመቅበር ጉድጓድ ሲያዘጋጅ የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠታቸው ሊያዝ ችሏል።
ፖሊስ የህፃኗን ወላጅ እናት እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗ በአሁን ሰዓት ሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ እንክብካቤ እያደረገላት እንደሚገኝ የሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፒክተር አለማየሁ አማረ ገልፀዋል።
ዘገባው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነው።