DJ SIKU

DJ SIKU DJ SIKU the best DJ in town

26/01/2024

ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቀው ዘውትር ቢጠጡ እነዚህን 10 የጤና ጥቅሞች ያገኛሉ

1. ጉበቶን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳሉ፡፡ለብ ባለ ውሃ ውስጥ የሎሚውን ጭማቂ (ፈሳሽ) ብቻ ሳይሆን የሎሚው ልጣጭ ጭምር ከተን የምንጠጣ ከሆነ ደረጃ 2 የጉበት ፀረ- መርዝ ማስወገድ ተግባራን ያከናውናል፡፡

2. ጉበቶ ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባታማ ምግቦችን ሰውነቶ እንዲፈጭ ይረዳል፡፡

3. ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳታችን(cells) እንዳይወድሙ ይጠብቃቸዋል፡፡

4. በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- ኦክሲደንት እና ፌቶኬሚካልስ የጉበት ሕዋሳት እንዲታደሱ ይረዳል፡፡

5. በሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የምግብ ስርዓተ ልመትን ያፋጥናል እንዲሁም የኩላሊት ጠጠርን (kidney stone) ያሟሟል፡፡

6. ሎሚ ከሰውነት ውጭ አሲድ ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ አልካላይን ነው ስለሆነም በሰውነት ውሰጥ ያለውን የፒ ኤች ደረጃ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳል በተጨማሪም በሽታን ይከላከላል፡፡

7. በሎሚ ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ጠንካራ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከል አቅም እንዲኖረን ያስችላል፡፡

8. ሎሚ የደም ቅባትን በመሰባበር በዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሀሞት ድንጋይዎች(gall stones) በሰውነታችን ውስጥ እንዳይፈጥር ያግዛል፡፡

9. ሎሚ ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ስላላው የዩሪክ አሲድ መጠንን በመቀነስ ሰዎች በሪህ (Gout) እና የአጥንት አንጓ

10. ብግነት (Arthritis) እንዳይጠቁ ይጠብቃቸዋል፡፡

11. ሎሚ ከአንደንድ የካንስር በሽታዎችም ይከላከላል፡፡
መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ!

Hakim-bet.com

07/01/2024
እንኳን ለጌታችን ለመዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ
07/01/2024

እንኳን ለጌታችን ለመዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ

02/12/2023
26/11/2023

ሙሴና ሚካኤልን ፍለጋ

| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው

እስራኤል በፈርዖን አገዛዝ እጅግ ተጨንቀዋል:: "በግብፅም ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነሣ" (ዘጸ. 1:8) ከተባለበት ዘመን ጀምሮ የእስራኤል እናቶች የዕንባ ጅረት ፤ የእስራኤል ሕፃናት የደም ጎርፍ አልቆመም:: ዮሴፍን የማያውቁ ፈርዖኖች አይነሡ እንጂ የተነሡ እንደሆነ "ግብፅን ያቀናነው እኛ ነን" ብትል ስለ ዮሴፍ ውለታ ብትተርክ የሚሰማህ የለም:: ሕፃናት አለቁ ብትል "ለግብፅ ፒራሚድ ሥራ ይጠቅማል" ትባላለህ እንጂ የሚሰማህ የለም:: ፈርዖን ነፃነት ሲጠይቁት "ጠግባችሁ ነው" ብሎ ምግብ የሚቀንስና ሥራ የሚጨምር ጨካኝ መሪ ነበር:: (ዘጸ. 5:18)
+++

እንደምንም አለፈ:: ይህንን የጨለማ ዘመን አሳልፎ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ ባርነት ነፃ ባወጣበት በዚያ ታላቅ ዕለት ግን ይህ ሆነ::

፳ኤል ከባርነት ተላቅቀው ከግብፅ ከወጡና ጉዞ ከጀመሩ በኋላ ንጉሥ ፈርዖን ሒድ ብሎ የለቀቀው ሕዝብ ጉልበት ቆጨው:: በቁጣ ነድዶ ሠራዊቱን አስከትቶ በፈጣን ሠረገላ እየጋለበ መጣባቸው:: ከፊታቸው ደግሞ የሚያስፈራ ባሕር ተደቅኖአል:: ሕዝቡ ግን የፈረደበት ሙሴ ላይ በቁጣ ጮኹበት::

መጽሐፈ መቃብያን "ያንን ሁሉ ሕዝብ ሲጠብቅ ያልተበሳጨ ሙሴን አስበው" እንደሚል እንደ ሙሴ ትሑትና ታጋሽ መሪ መቼም ታይቶ አይታወቅም:: (2 መቃብያን 11:1) መቼም ሙሴ ለእስራኤል ያልሆነው ነገር አልነበረም:: "ሕዝቤን ከምታጠፋ እኔን አጥፋኝ" የሚል መሪ ከሙሴ በቀር የት ይገኛል? "የአንተ ሥልጣን ሳይነካ ሕዝቡን ልደምስሰው" ሲባል ሥልጣኑ ይቅርብኝ ሕዝቡን ከምትደመስስ ከሕይወት መጽሐፍ ስሜን ደምስስልኝ ሲል የሚገኝ መሪ ከወዴት ይገኛል? (ዘጸ. 32:32) "ሥልጣኔን ለማቆየት ምንም ያህል ሕዝብ ቢያልቅ ይሻላል" ብለው የሚያስቡ መሪዎች ዓለምን በሞሉባት ዘመን ፣ ሕዝቦች ስለ መሪዎች ሥልጣን ሲባል ደማቸው እንደ ጎርፍ በሚፈስስበት ዘመን ሆነን ስናስብ "ሕዝቤ ከሚጠፋ እኔ ልጥፋ" የሚል መሪ በነበራቸው እስራኤል እንቀናለን::

እስራኤል ግን የሙሴ መሪነት አልታያቸውም:: ከፈርኦን ነፃ መውጣት ቢፈልጉም ለሙሴም መታዘዝ አይፈልጉም:: እሱን መቃወም የጀመሩት ገና ግብፃዊውን ገድሎ እስራኤላዊውን ባዳነባት ማግሥት ነበር::

ሁለት እስራኤላውያን ሲጣሉ ያየው ሙሴ "ለምን ወንድምህን ተመታዋለህ?" ብሎ ሊሸመግል ሲሞክር
"በእኛ መካከል ዳኛ አድርጎ ማን ሾመህ?" ብለው አፈጠጡበት:: (ዘጸ. 2:14) ለካስ የወንድማማችን ጸብ እዳኛለሁ ብለህ መነሣት ራሱ አደገኛ ነገር ነው!? "ወንድማማቾች ናችሁ አትጣሉ" ማለት ለካ ዋጋ ያስከፍላል:: እናም ይህ ሙከራው ሙሴን ለስደት ዳረገው:: ሕዝቤን አድናለሁ ብሎ ራሱ ስደተኛ ሆነ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "እስራኤል ለምን ቁስሌን አከምክልኝ ብሎ ሐኪሙን የሚቆጣ በሽተኛ ይመስላሉ" እንዳለው ሙሴ ለወገኔ ልቁም ባለበት ዕለት ስደተኛ ሆነ::

እስራኤል ከዚያ ወዲያ ሙሴ ላይ ምን ያላደረጉት አለ? ሆኖም ልክ በዚያች ባያት ዛፍ ላይ እሳት ሲነድባት እንዳልተቃጠለች እስራኤላውያንም ሙሴ ላይ ለዓመታት ቢነድዱም አላቃጠሉትም:: የተቀደሰውን ጽላት እስኪሰብር ድረስ ቢያማርሩትም ተስፋ አልቆረጠባቸውም::

በዚህ የመሻገር ቀንም "በግብፅ መቃብር ጠፍቶ ልታስፈጀን ነው?" "ከሞት ባርነት በስንት ጣዕሙ?" እያሉ እስራኤል በኤርትራ ባሕር ዳርቻ ሙሴን በቁጣ እየጮኹ አስጨነቁት::

መሪነት ከባድ ነው:: ያንን ሁሉ ድንቅ ነገር አድርጎ እግዚአብሔር ነፃ ሲያወጣቸው ሙሴ ለእነርሱ ቤዛ ሆኖ ተሹሞ ብዙ ዋጋ ከፍሎአል:: ውለታውን ረስተው አፋጠጡት::

"ሙሴም ለሕዝቡ፦ አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ፡ አላቸው"

ሙሴ ሕዝቡን ከጩኸታቸው ሲያረጋጋ ሳለ የእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ሙሴ መጣ
"ሙሴ ሆይ ለምን ትጮኽብኛለህ?" አለው::

ልብ አድርጉ የጮኸው ሕዝቡ ነው ሙሴ አረጋጋ እንጂ ቃል አልተናገረም:: ሆኖም ሙሴ አፉ ዝም ቢል ልቡ ይጮኽ ነበር:: ከእስራኤል ጩኸት ይልቅ የሙሴ ዝምታ እግዚአብሔር ጆሮ ደረሰ:: እግዚአብሔር ኤልያስ እንዳላገጠባቸው የአሕዛብ አማልክት በጩኸት ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለም:: በትዕቢትና አመፅ ከሞላበት ጩኸት ይልቅ በተሰበረ ልብ የሚቀርብ ዝምታ እግዚአብሔር ጋር ይጮኻል::

የእስራኤል ጩኸት ፍርሃት ይነዛል:: ልናልቅ ነው የሚል ሽብር ይፈጥራል:: የሙሴ ዝምታ ግን ባሕር ይከፍላል::

ጌታ ሆይ ጩኸታችን አልሆነልንም:: ዝምታችንን ሰምተህ ሀገራችንን ከከበባት ጥፋት ታደግልን:: የሚጮኹብን ሳይሆን የሚጮኹልን ሙሴዎችን አብዛልን:: የእኛ መጨቃጨቅና ጠብ ባሕር አይከፍልም:: የእኛ ጩኸት ከመነካከስ በቀር አያሻግርም:: በአርምሞ የሚለምኑህን በእኛ ፊት ዝም አሉ የምንላቸው በአንተ ፊት ግን የሚጮኹትን ሰምተህ ታደገን::

ሙሴ ባሕሩን መታው:: የኤርትራ ባሕር በዝምታ ተከፈለ:: የመሪዎች ሥራ ባሕሩን መምታት እንጂ ሕዝቡን መምታት አይደለም:: በትር የተሠጣቸውም ባሕር ከፍለው ሕዝቡን እንዲያሻግሩ እንጂ ሕዝቡን እንዲያስቸግሩ አይደለም:: ይህ የገባው ሙሴ ሕዝቡን ትቶ ባሕሩን መታው:: ራሔል ስለ ልጆችዋ ያለቀሰችው ዕንባ እስከ ራማ ደርሶ የኤርትራን ባሕር ከፈለ::

[የራሔል ዕንባ እስከ ራማ ተሰማ ሲባል ስሰማ የድንግል ማርያም ዕንባ የት ድረስ ይሰማ ይሆን? እላለሁ:: "እመቤታችን ሆይ ስለ እኛ ስለልጆችሽ እባክሽን አልቅሺ:: የራሔል ዕንባ ራማ ከደረሰ የአንቺ ዕንባ የት ሊደርስ ነው? በየበረሃ እየወደቀ ስላለው ልጅሽ ስለሞተለት ወንድም እባክሽን ለምኚ:: ሙሴ በወንድሙ አሮን በትር ባሕርን ከፈለ:: ሳይተክሏት የለመለመችው የአሮን በትር ድንግል ሆይ የኃጢአታችን ባሕርስ የተከፈለው ባንቺ አይደለምን? አሁንም የመከራችን ባሕር የማትከፍይልን ለምንድን ነው? ያሰኘኛል]

በሙሴ በትር ባሕሩ ተከፈለ:: የኤርትራ ባሕር (ቀይ ባሕር [በግሪኩ erythos ማለት ቀይ ነው]) እጅግ ባለ ታሪክ ባሕር ነው:: ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደረቅ ሆኖ ፀሐይ ያየውና ግማሽ ሚልየን የሚሆን ሕዝብ በመካከሉ ተራምዶ ያለፈበት ይህ ባሕር እንንደ ግድግዳ የቆመ ብቸኛው የዓለማችን ባሕር ነው::

በዚህ ባሕር እስራኤል ሲሻገሩ ፈርኦን ከነሠራዊቱ ሰጠመ:: በእግር የሔዱት የተሻገሩትን ባሕር በሠረገላ የሔዱት አቃታቸው:: የኤርትራ ባሕር ለእስራኤል ትንሣኤ ሲሆን ለፈርኦን ግን መቃብር ሆነ:: ፈርኦን ደንግጦ መመለስ የነበረበት ባሕሩ ሲከፈል ሲያይ ነበር:: ፈርኦንን ያደቆነ ሰይጣን ግን ባሕር መካከል ሳያቀስስ አልለቀቀውም:: እግዚአብሔር ሲቀጣ በፍትሐዊነት ነው:: ሕፃናት እያረደ ወደ ባሕር የጨመረው ፈርኦን የእርሱም ሞት ውኃ ውስጥ ሆነ:: ጎልያድ ብዙዎችን በገደለባት በገዛ ሰይፉ እንደሞተ ፈርኦንም ብዙዎችን በገደለበት ውኃ ሞተ::

በትዕቢቱ "እግዚአብሔር ማን ነው?" ብሎ ነበርና እግዚአብሔርን በዚያ ባሕር ተዋወቀው:: እሱ ሲሰጥም እስራኤል በኩራት "እግዚአብሔር ማን ነው? " ለሚለው የፈርኦን ጥያቄ ከባሕር ማዶ ሆነው መልስ ሠጡ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው" አሉ:: እስራኤል በኤርትራ ባሕር መሻገራቸው የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ "በባሕርና ደመና ተጠመቁ" ተብሎላቸዋል:: ፈርኦን ግን እስራኤል በተጠመቁበት ጠበል ውስጥ ሰጠመ::
የኤርትራ ባሕር እንደ ባቢሎን እሳት ለአንዱ መዳኛ ለሌላው መሞቻ ሆነ:: እስራኤልም በእሳቱ እንደዳኑት እንደ ሠለስቱ ደቂቅ በባሕሩ ዳኑ ግብፃውያንም በእሳቱ እንደሞቱት እንደ ባቢሎናውያን በባሕሩ ሞቱ:: በሁለቱ ታሪኮች ላይ ነገሩን ያስፈጸሙት ደግሞ ብርሃናውያኑ ሚካኤልና ገብርኤል ነበሩ::

የኤርትራን ባሕር ሲሻገሩ ከሙሴ ሌላ እስራኤልን ሲመራ የነበረ አንድ ሰማያዊ ጠባቂም ነበረ:: እርሱም የእስራኤል ጠባቂ (advocate of Israel) በመባል የሚታወቀው ቅዱስ ሚካኤል ነበር::

"በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ" ዘጸ 14:19 እንዲል ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን ዐምድ እየተመሰለ በመንገድ መራቸው::

እኛም ያጣነው ሙሴንም ሚካኤልንም ነው:: እኔን ከሕዝቤ ያስቀድመኝ የሚል ሙሴ እና እኔ ላብራላችሁ የሚል ሚካኤል እንሻለን:: በእርግጥ የቀን ደመና የሌሊት ብርሃን ሆኖ የሚቆም ጠባቂ ከሚካኤል በቀር ወዴት ይገኛል? "ከሚካኤል በቀር የሚያጸናኝ የለም" ያለው ገብርኤል ያለ ምክንያት አልነበረም:: እውነትም ሁሉ ነገር በጨለመበት በዚህ ዘመን የሚያበራ መንገድ መሪ ያስፈልገናል::

ቅዱስ ሚካኤል ሲጨልም ከማብራት ፀሐይ ሲከርር ከማጥላት በቀር አንዳች ያልተናገረ ሲጠብቅ የማይታይ ውለታ ቁጠሩልኝ የማይል ቅዱስ ጠባቂ ነው:: ይህንን ከእስራኤልም ታሪክ የመልአኩን ጥበቃ ከቀመስን ልጆቹም ታሪክ መረዳት ይቻላል:: ሊቁ ቢቸግረው የመልአኩን በዝምታ የተሞላ ጠባቂነት ቢያይ "አንተኑ ሚካኤል መና ዘአውረድከ" "ሚካኤል ሆይ መናን ያወረድኸው አንተ ነህን?" ብሎ እየጠየቀ ያደንቃል:: እያበሩልህ አበራንልህ የማይሉ እየመገቡ አበላንህ የማይሉ ሚካኤላውያን ከወዴት ይገኙ ይሆን?

እኛ ዛሬም ድረስ ያለነው ከባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው:: ሁሉም መሻገር ይፈልጋል:: ከእኛ መካከል እንደ ፈርኦን ሰጥሞ የሚቀር ይኖራል:: እንደ እስራኤል የሚሻገር ይኖራል: : ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ለእኛም ድረስልን:: ይህንን ክፉ ዘመን በክንፎችህ አሻግረን:: መናው ይቅርብን መና ሆኖ ከመቅረት ግን ታደገን::

https://janderebaw.org/ሙሴና-ሚካኤልን-ፍለጋ/




ማስታወሻ :- ዘወትር ረቡዕ የሚቀርበው የቀሲስ ታምራት ውቤ ዐምድ በቅዱስ ሚካኤል በዓል የክብረ በዓል ጽሑፍ ምክንያት ለነገ የተሻገረ መሆኑን እንገልጻለን::

ክፍል 2በአካል የልጁን መጎዳት ያዩት Easter እና Erick በተመስገን ብርቱ ጥረት እና ትግል ህክምናውን ለማስጀመር መስማማታቸውን ገለጹለት ይህን ዜናም ተመስገን ለኡሪና ቤተሰቦች አበሰራ...
31/10/2022

ክፍል 2
በአካል የልጁን መጎዳት ያዩት Easter እና Erick በተመስገን ብርቱ ጥረት እና ትግል ህክምናውን ለማስጀመር መስማማታቸውን ገለጹለት ይህን ዜናም ተመስገን ለኡሪና ቤተሰቦች አበሰራቸው።

ጭንቀት ውስጥ የነበሩት ትንሽ ቀለል አላቸው የልጃቸውን ፊት ፊት እያዩ አሁን ይድንልን ይሁን በሚመስል መልኩ ፈዘው ይመለከቱትም ነበር ተመስገንም የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ለራሱ ቃል ገባ ፕሮሰሱ ተጀመረ ለአባት መታወቂያ ማውጣት ለህክምና የሚሆን የድጋፍ ደብዳቤዎች በማስጻፍ ሙሉ ሀላፊነትን በመረከብ አሳክሞ እስከመመለስ ድረስ ሁሉም በሰላም ተጠናቀቀ አሁን የሚቀራቸው መጓዝ ብቻ ነው መጓዝዝዝዝዝዝዝ

ጉ...ዞ.....ተጀመረ

በርግጥ በጉዞው ወቅት ለተመስገን ሁሉ ነገር ቀላል አልነበረም ፈተናዎች ብዙ ነበሩ ሰዎቹ የልጁን ፊት በማየት ብቻ አልጋ ለማከራየት አለመፍቀድ፣ምግብ ቤት ለማስገባት ፍቃደኛ አለመሆን ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ግን ከጓደኛው ጋር በመመካከር በተጠቀሙት ዘዴ በስተመጨረሻም ለአዳር የሚሆን መኝታ ቤት አግኝተው የሚበላውን ገዝተው ተመግበው አዳራቸውን አርባ ምንጭ በማድረግ በለሊት ጉዞ ወደ ሸገር አደረጉ

ሸገር እንደደረሱ ለኡሪና ለአባቱ ሁሉ ነገር አዲስ ነበር ያው ህክምናው ረዥም ጊዜ ስለሚወስድ ቀን በቀን ለመኝታ ቤት ከመክፈል እና ከወጪው አንጻር ያለው አማራጭ ቤት ተከራይቶ ከለመዱት ማህበረሰብ ውጪ አዲስ ማህበረሰብ ጋር ተቀላቅለው ሁሉን ባህል እንዲላመዱ ማድረግ ነበር እና ይህንንም አድርጎታል ህክምና የሚያደርግበት ሆስፒታልም አቀኑ የተከሰተውን በሙሉ ተመስገን ለዶክተሮቹ አስረዳቸው የፊት ሰርጀሪ እንዲሰራለት ዶክተሮቹ ይነግሯቸዋል በዚህም ተመስገን እና የኡሪ ቤተሰቦች በመነጋገር የፊት ሰርጀሪው እንዲሰራለት ተስማሙ... እንደታሰበው ሰርጀሪው ግን ቀላል አልነበረም ማለትም የፊት ሰርጀሪውን ከአንድም ሶስት ጊዜ አድርጓል በዛን መሃል በየአንዳንዱ ሰርጀሪ ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር የሚፈጅ ጊዜ ቀጠሮ የነበረው ሲሆን ይሄን ሁሉ ጊዜ ያለመታከት ከጎናቸው ላለፉት ከባድ ጊዜያት አንድ ብርቱ ወጣት ነበር ተ...መ....ስ....ገ...ን

በቀነ ገደብ ቀጠሮው ሰርጀሪው ለሶስት ዙር የተሰራለት ሲሆን የመጨረሻው ሰርጀሪ እንደተሰራለት ከትንሽ ቆይታ በኋላ ኡሪ ከልጅነት ጓዶቹ ጋር ለመቦረቅ ለመጫወት ተስፋን ሰንቆ ቤተሰቦቹ ልጃቸው ወደ ቀድሞው የፊቱ ገጽታ እንደሚመለስ አምነው ከህክምናው በኋላ ወደ አከባቢያቸው በዚህ ብርቱ ወጣት አማካኝነት ተመለሱ።

በዚህ ላለፉት ሶስት ዓመታት ያለ መታከት እና ያለ መሰልቸት ከኡሪና ቤተሰቦቹ ጎን የነበረው ተመስገን እንዲህ እያለ ያስታውሳል ከህክምና ጀምሮ የ አውሮፕላን ትኬት ወጪ ፣ የመኪና ትራንስፖርት ወጭ ፣ አልጋ ፣ የምግብ ፣ ታክሲ ከተማ በምሄዱበት ግዜ ለአባትና ልጅ ሙሉ ልብስ እስከነ መቀየሪያቸው ... ወዘተ ወጭዎችን በመቻል ይህ ነው የማይባል እስከ 3000,000 ብር የሚገመት ገንዘብ Easter እና Erick ፈሰስ እንዳደረጉ ይገልጻል።

ነገር ግን በዚህም አላበቃም ኡሪ ከህክምና መልስ ቁስሉ እስኪሽርለት በባክቴሪያ ኢንፌክሽን እንዳይጠቃበት በዞን የሚገኘው ሆስፒታል በማመላለስ የእጥበት ሂደቱን እንዲከታተል ያደረገ ሲሆን ያ ሁሉ ጉዳይ ተጠናቆ ኡሪ ቁስሉ ከሻረለት በኋላ ወደ ትውልድ መንደሩ በመመለስ ከጓደኞቹ እኩል እየቦረቀ ይማር ዘንድ የትምህርት ቁሳቁሱን በሟሟላት ከትምህርት ጽ/ቤት ኋላፊ አቶ አንተነህ ጌታቸው ጋር መንደራቸው ድረስ በመሄድ ለኡሪና ቤተሰቦቹ ቁሶችን አበርክተዋል።

ጽናት፣ትጋት፣ ሰብዓዊነት፣የአንድን ወጣትን ህይወት ከማዳን አልፎ እንደ አዲስ ተስፋን እስከመዝራት የተከፈለ መስዕዋትነት❤❤❤❤...

ኡሪና ቤተሰቦቹ አሁን ላይ ያመሰግኑታል እንደ ቤተሰባቸውም ይቆጥሩታል አሁን ላይ በደስታ እየኖሩ ነው ዕድሜ ለዚህ ብሩህ ታጋይ ወጣት እና ሰብዓዊነት ተሰምቷቸው ከባህር ማዶ ሆነው ለረዱት Easter እና Erick❤❤❤

ጽሁፌን በዚሁ አበቃው ቸር ሰንብቱ

አንዲት ያልታሰበች አጋጣሚ***********************ክስተቱ የተፈጠረው ከሶስት ዓመት በፊት  ከዚሁ ከዲመካ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ስንበሌ ቀበሌ ዞገላ መንደር ውስጥ ነ...
31/10/2022

አንዲት ያልታሰበች አጋጣሚ
***********************

ክስተቱ የተፈጠረው ከሶስት ዓመት በፊት ከዚሁ ከዲመካ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ስንበሌ ቀበሌ ዞገላ መንደር ውስጥ ነው አንድ የ12 ዓመት ልጅ ቤት ውስጥ ብቻውን ተቀምጧል ነገር ግን መቼስ የሆድ ነገር ልጁን የረሃብ አለንጋ ይገርፈው ጀመር ይህንን ለማስታገስ ልጁ ምግብ መፈለገ ጀመረ የሚላስ የሚቀመስ ቢያጣ አንድ ሀሳብ መጣለት ረሃቡን ለማስታገስ በቆሎ ጠብሶ መብላት🌽🌽 የፊም እሳቱ ሙቀት እንደ ጅራፍ የሚጋረፍ ነው ልጅ የረሃብ ጉዳይ ሆኖበት በቆሎውን ይጠብስ ጀመር.......

የረሃብ አለንጋ ግርፊያውን ለማስታገስ እሳቱን እየቆሰቆሰ በቆሎውን መጥበሱን ተያይዞታል ነገር ግን ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ሁሉን ነገር የሚቀይር ክስተት ተከሰተ ልጅ ተስፋ ያደረገውን ረሃብ ለማስታገስ በቆሎ ጠብሶ የመብላት ፍላጎቱ ወደ ማይሻር ጠባሳ ተለወጠበት😭😭 ከልጅነቱ ጀምሮ ያመው የነበረው የሚጥል በሽታ ልጁን አዙሮ ያ የፊም እሳት ላይ ይጥለዋል ነገር ግን በሰዓቱ በቤት ውስጥ ማንም ባለመኖሩ ልጅ በወደቀበት ፊቱ ይቃጠል ጀመር😭 እሳቱ ሙሉ በሙሉ ፊቱን አቃጠለው ከዛም አልፎ ተርፎ አንድ ዓይኑን አፈሰሰው😭 ረሃብ ለማስታገስ አሳዛኝ ክስተት

እንደ ድንገት ከማሳ ስራቸውን ጨርሰው ቤተሰቦቹ ሲመለሱ ቤት ትተውት የሄዱት ልጅ እሳት ላይ ወድቆ ያዩትና እየተጯጯሁ ቀርበው ቢያነሱትም አስቀምጠው እንደሄዱት ነገሮች ሁሉ በቦታቸው አልጠበቋቸውም የልጃቸው ፊት ተቃጥሎ ዓይኑ ፈሶ ነበር ያገኙት ብቻ አዲስ ክስተት😭 ድንጋጤ ዋጣቸው።

ቤተሰቦቹ ባላቸው አቅም እዚሁ ዲመካ ጤና ጣቢያ አሳክመውት ከዚህ በላይ የሆነ ጉዳይ ስለነበር ርፌር ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል በተጻፈላቸው መሰረት ጂንካ ቢወስዱትም በተመሳሳይ ከዛም በላይ ጉዳይ ነበር እና ልጃቸውን ወደተሻለ ህክምና ቦታ እንዲወስዱት ይነገራቸዋል ወይ ጣጣ😭 መቼስ ልጅ አይደለ የማሳከሙ ፍላጎት ቢኖራቸውም ማሳከሚያ ገንዘብ ስለሌላቸው ብቻ ተስፋ በመቁረጥ ልጃቸውን ይዘው ወደ ቀበሌያቸው ስንበሌ ዞጎላ መንደር ተመለሱ።

የልጁ ተስፋ ጨለመ እንደለመደው ከጓደኞቹ ጋር መቦረቅ እና መጫወት እየናፈቀው አንድ ዓመት ቆየ ቤት ወዋል እዛው መተኛት ብቸኝነት፣ህመም፣ለየት ያለ ስሜት ብቻ ከባድ ነበር ፊቱን ያዩ ጓደኞቹ ሁሉ ይሸሹት ጀመር ነገር ግን ቀስ በቀስ እየተለማመዱ ሲሄዱ ልጅ ለጨዋታ ፊቱን በጨርቅ በመሸፈን ጓደኞቹ ጋ ለጨዋታ ይሄድ ጀመር።

ነገር ግን ከቆይታ በኋላ አንዲት ቅጽበት የልጁን ህይወት የልጁን ተስፋ የሚያለመልም ክስተት ይፈጠራል ነገሩ እንዲህ ነው በዕለቱ በቀበሌያቸው ስንበሌ ዞጎላ መንደር ዝላይ ነበር(ዝላይ ማለት አንድ የሐመር ወንድ ሚስት ከማግባቱ በፊት ቅድሚያ የሚከውነው ተግባር ሲሆን ይህም በተደረደሩ ከብቶች ላይ መዝለል ነው)

ይህን ዝላይ ለመታደም ከውጪ የመጡ ዜግነታቸውም ሆላንዳዊ የሆኑ Easter እና Erick እንደ ድንገት ዘወር ዘወር እያሉ በሚቀርጹበት ወቅት አንድ የ12 ዓመት ልጅ ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ከርቀት ያዩታል ይህም ልጅ በእሳት አደጋው የፊቱ ገጽታ የተበላሸበት አንድ ዓይኑ የፈሰሰበት ኡሪ ቃላ ነው እንግዶቹ ጠጋ በማለት ምን ሆኖ እንደሆነ ታሪኩን መጠየቅ ፈልገው አብሯቸው የተጓዘውን አስተርጓሚ ጠሩት ስሙም ተመስገን ከበደ( Tommy Hamer) ይባላል የልጁን ፊት የተመለከተችው Easter የጥያቄ ናዳ ታወርድ ጀመር ተመስገንም የማስተርጎም ስራውን እያቀላጠፈ እየጠየቀ እየተረጎመ ያግባባ ጀመር ልጅም የሆነውን ሁሉ ማስረዳቱን ቀጠለ......

በስተመጨረሻም ያዩት እና የሰሙት ነገር ያሳዘናቸው Easter እና Erick በውስጣቸው ሀሳብ ይመላለስ ጀመር የልጁን ቤተሰብ መተዋወቅም ፈለጉ እንደፈለጉትም ተዋወቁ አባት አቶ ኡሪ ቃላ እናት ወ/ሮ ኬሪ አሳዳጊ ወላጆቹ ናቸው።

የጀመሩትን የሄዱበት የዝላይ ፕሮግራም ጨርሰው ወደ ጂንካ ይጓዛሉ በዚህ መሀል ስለ ልጁ ማሰብ አላቆሙም መፍትሄ ለማፈላለግ በሀሳብ ያብሰለስሉ ጀመር ነገር ግን በተመስገን ብርቱ ትግል እና ጥረት በስተመጨረሻም ለልጁ የሚከፈለውን ሁሉ በመክፈል ለማሳከም ፍቃደኛ ሆኑ። ከመሄዳቸው በፊትም አድራሻቸውን ከአስተርጓሚው ተመስገን ጋር በመቀያየር ወደ ሀገራቸው ሄደውም መጻጻፍ ጀመሩ ያኔ ነው ሁሉ ነገር መቀየር የጀመረው ለኡሪም የተስፋ ብርሃን ጭላንጭል ይታይ ጀመር ለዓመት ይናፍቀው የነበረው ህ..ክ...ም..ና

ወጣት ሙዚቀኛ ነው ጥበቡ አሰግደው ይባላልበራሱ ግጥምና ዜማ የሰራውን ሙዚቃ ጀባ ብሏልአዳምጡት ትወዱታላችሁ ሙዚቃው ሰኞ ይለቀቃል መልካም ቀን
30/04/2022

ወጣት ሙዚቀኛ ነው ጥበቡ አሰግደው ይባላል
በራሱ ግጥምና ዜማ የሰራውን ሙዚቃ ጀባ ብሏል
አዳምጡት ትወዱታላችሁ
ሙዚቃው ሰኞ ይለቀቃል መልካም ቀን

ለ126ኛ የጥቁር ሰው ድል እንኳን አደረሳችሁ
02/03/2022

ለ126ኛ የጥቁር ሰው ድል እንኳን አደረሳችሁ

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድሀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ ተወልዶላችኋልና ሉቃ 2፣11እንኳን ለልደት/ገና/በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
07/01/2022

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድሀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ ተወልዶላችኋልና ሉቃ 2፣11
እንኳን ለልደት/ገና/በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።

Address

Minilik Avenue
Addis Ababa
ADDISABABA

Telephone

+251910069378

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DJ SIKU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to DJ SIKU:

Share

Category


Other DJs in Addis Ababa

Show All