ከደራሲያን አለም ፔጅ

ከደራሲያን አለም ፔጅ ማንበብ "ሙሉ" ሰው ያደርጋል

~ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው  #ህልሙ ነው!~ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው  #ፀሎቱ ነው!~ምን አልባት እኛ ያለፈን  #የማይጠቅመን ነው!~ምን አልባት ያሳመመን  #ሊያስተምረን ነ...
18/02/2025

~ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው #ህልሙ ነው!
~ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው #ፀሎቱ ነው!
~ምን አልባት እኛ ያለፈን #የማይጠቅመን ነው!
~ምን አልባት ያሳመመን #ሊያስተምረን ነው!
~ምን አልባት የሆንነው የሆኑትን እንድንረዳ ነው!
~ ምን አልባት የተበለሻሸውን እንድንቀያይረው ነው!
~ምን አልባት አማራጭ ያጣነው አማራጭ #እንድናመጣ ነው!

ብቻ #ትእግስት ይኑረን #ሁሉም ነገር ለበጎ ነው !!

መጋቢ አዲስ እሸቱ አለማየሁ
ከደራሲያን አለም ፔጅ

 #እንቆቅልሽ 👉 " "    #ተሳተፉ "ከንጉስ ፊት ቁማ ሽንቷን የምትሸና " ?  word's  ! ከደራሲያን አለም ፔጅ       👇👇👇https://www.facebook.com/share/1DeR...
18/02/2025

#እንቆቅልሽ 👉 " " #ተሳተፉ
"ከንጉስ ፊት ቁማ ሽንቷን የምትሸና " ?
word's
!
ከደራሲያን አለም ፔጅ



👇👇👇
https://www.facebook.com/share/1DeRHsQqA4/


ተወዳጁ ድምፃዊ ABD ከከባድ አደጋ ተረፈ ድምፃዊ አብዱ ኪያር ከከባድ ጉዳት ተረፈ። የሊፍት ገመድ ተበጥሶ ወድቆ ነው ተብሏል። ድምፃዊው በፌስቡክ የሚከተለውን ፅፏል 👇"ከባድ አደጋ ነበር።ት...
16/02/2025

ተወዳጁ ድምፃዊ ABD ከከባድ አደጋ ተረፈ

ድምፃዊ አብዱ ኪያር ከከባድ ጉዳት ተረፈ። የሊፍት ገመድ ተበጥሶ ወድቆ ነው ተብሏል። ድምፃዊው በፌስቡክ የሚከተለውን ፅፏል 👇

"ከባድ አደጋ ነበር።
ትንሽ የአጥንት መሰንጠቅ ከጉልበቴ በታች አጋጠመኝ። ዳኑ orthopedics ዶክተር ኤልያስ በአስገራሚ ብቃት አክሞኝ አሁን በጣም ጥሩ ነው ያለሁት። አልሓምዱሊላህ። Thank you so much Dr Elias, Dr Aida and all the Danu orthopedics team. .girma "

ብሏል።
እንኳን አተረፈህ የሀገር እንቁው ኤቢዲ 🙏 አላህ ጨርሶ ይማርህ 🙏

ከደራሲያን አለም ፔጅ

iQ Comments Answer ?
15/02/2025

iQ
Comments Answer ?

  !"1↱ፈጣሪ ካልፈታው ገንዘብ ችግርህን       አይፈታውም   ↱ፈጣሪ ካልሞላው ሰው ጎንህን አይሞላውም.     ↱ፈጣሪ ካልገለጸ እውቀት ጥበብ አይሆንም፡2⚂ይቺ ዓለም ለሁሉም እኩል ናት፡...
15/02/2025

!"

1↱ፈጣሪ ካልፈታው ገንዘብ ችግርህን
አይፈታውም
↱ፈጣሪ ካልሞላው ሰው ጎንህን አይሞላውም.
↱ፈጣሪ ካልገለጸ እውቀት ጥበብ አይሆንም

2⚂ይቺ ዓለም ለሁሉም እኩል ናት፡፡
⚂ ዛሬ ብታገኝ ነገ ታጣለህ ✔
⚂ዛሬ ብታሸንፍ ነገ ትሸነፋለህ✔
⚂ለሁሉም ጊዜ አለው የሚባል መዶሻ አለ፡፡
⚂መልካምነት ዋጋ ያስከፍልሃልና ሁሌም ፍጹም
መልካም ሰው ሁን✔

3↩ህይወትህ ትርጉም እንዲኖራት ዓላማ ይኑርህ፡፡

4↩የአንተነትህ ትልቁ ምዕራፍ ከእውቀትህ በላይ ስራህ መሆኑን አትርሳ፡፡

5↩ንጹህ ልብ ልክ እንደ አበባ ናት! ፍሬ ባናገኝባትም ውበቷ ግን እጅግ ማራኪ ነው፡፡
:
6↩የውድቀት መጀመሪያ ራስህን አዋቂና ብቸኛ አድርጎ ማሰብ ነው

6↩ፍጻሜህ እንዲያምር ራስህን አታመጻድቅ.
↩ሁሌም ከስህተትህ ለመታረም ፈቃደኛ ሁን
↩ጥፋትህን አሜን ብለህ መቀበልህ ክብርህን
የሚጎዳብህ አይምሰልህ፡፡

7↩ጠቢብ ሰው እንኳን ከራሱ ከሰው ስህተት ተምሮ ራሱን ይጠብቃል ይመለሳልና፡፡

8↩በህይወት ውስጥ አንዱ ሲታወር አንዱ መሪ መሆን አለበት

9↩እውነትነ የሚናገር ሰው አፉ ክፉ ይመስላል ልቡ ግን ንጹህ ነው

10↩ህይወት በመደጋገፍ የተሞላች ናትና ወንድምህን ለመርዳት ወደሗላ አትበል!

11 ↩ዝምታ ሞኝነት ሳይሆን ፣
ከሰው ጋር የመኖሪያ አንዱ ዘዴ ነው✔


ልብ ♥ይበሉ አዳዲስ መጣጥፎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርስወ
ፔጁን ሼር፣፣ላይክ follow,,invite ያድርጉ

ዩኒቨርሲቲ አብረን የተማርን አንድ ወዳጅ ነበረኝ። ከሃይስኩል ጀምሮ በጣም ለትምህርት እሩቅ ከሆነ ቦታ አቅራቢያ ያለው ትንሽዬ ከተማ እየተመላለሰ ይማር የነበረ ነው። ቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን እ...
14/02/2025

ዩኒቨርሲቲ አብረን የተማርን አንድ ወዳጅ ነበረኝ። ከሃይስኩል ጀምሮ በጣም ለትምህርት እሩቅ ከሆነ ቦታ አቅራቢያ ያለው ትንሽዬ ከተማ እየተመላለሰ ይማር የነበረ ነው። ቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን እንደ መንደር አርሶአደሩ አዋጥቶ መርቆ ሸኝቶ ያስተማረው ነው። ካምፓስ እያለን ታሪኩንም ስስማ እሱን ላስተማረው ያ ህብረተሰብ የነበረኝ የክብር ስሜት ልገልፅላቸው አልችልም። ጊዜው ደርሶ ሁላችንም ተመርቀን ህይወት ወደየ አቅጣጫው በተነችን። ከ6 ዓመት ቡሃላ በሆነ አጋጣሚ እሱን ያስተማረው ማህበረሰብ ያለበት አከባቢ ለሆነ ጉዳይ እንደሚሄድ ሳውቅ አፈላልጌ በሰው ሰው ስልክ ቁጥሩን አግኝቼ ሄድኩ። ቁጭ ብለንም ትዝታችንን አንስተን ስንጫወት ቆየን።

በወረዳ የመንግስት ስራ ገብቶ እንደነበረና ቡሃላም ቢሮክራሲው ሰልችቶት ስራውን ትቶ እዛ ያስተማረው ህብረተሰብ መንደሩ ተመልሶ በሰው ፍቃድ አውጥቶ Pharmacy እንደከፈተ ነገረኝ። እኔም ደስ ብሎኝ በአዕምሮየ የአንተ ንግድ ብቻም ሳይሆን ህብረተሰብህንም የምትክስበት እድል ነው እያልኩ... ስራ እንዴት ነው? ያዋጣል ወይ? ምናምን ብዬ ሲጠይቀው: "እስካሁን በመንግሥት ስራ ያሳለፍኩት ይቆጨኛል: መድሃኒት አየር አለው እንዲህ ከታች በኩል የሚገባ... Expired ያደረገ ካርቶኑን ቀይረህ እንዲህ ታረጋለህ.. ምርመራ ላይ እንዲህ ታደርጋለህ... " ምናምን እያለ በMoral ሲያወራ ውስጤ እንዴት እንደደነገጥኩ!!!

አሰብኩት: ልጃችን አለ ፋርማሲው ሄደን መድሃኒት እናገኛለን ብለው እሱን ተማምኖ (ያሳደጉት ያስተማሩት ናቸውና) ካርቶኑ የቀየረ Expired ያደረገ መድሃኒት ሲሰጣቸው!!! ብቻ ከዛ ቡሃላ ያወራነውን በደንብ አላውቅም ከላይ ላዩ ብቻ እወራው እንደነበረ ትዝ ይለኛል። ከዛም በአቅራቢያው ባለው ከተማ ቤት እንደገነባ ልጆችም እንደወለደ ሰምቼያለሁ። ሁሌም የሚቆጨኝ ውስጤን የሚበላኝ!!!
~ የመንግስት ጤና ጣቢያም: ፍርድ ቤቶችም የመንግስት መ/ቤቶችም በቀበሌም በወረዳም ይሀ አይነት ወጣቶች በብዛት ታገኛለህ። የመንግስት ሆስፒታልም እንዲሁ። ከተማ ገብተውም የተወለዱበትን ማህበረሰብ: ሳይማር ያስተማራቸውን ሳይጎርስ ያጎረሳቸው አርሶአደር የሚበዘብዙ ሳይ ጭካኔው ይገርመኛል። ምክንያቱ ብቻ ነው እስካሁን የማይገባኝ።
ጉልበት አላጣህ: ጤና አላጣህ!!! ተሸክሞ መኖር በስንት ጠዓሙ!!!

በከተማችን እንደዚህ ትዉልድ ገዳይ ቆሻሻ ስራ የሚሰሩ ስግብግብ ሰወች አሉና በዉስጥ መስመር መረጃ ላኩ ተባብረን እናጋልጣለን ።

ከደራሲያን አለም ፔጅ

 #መስፈርት ህልምና መጽሐፍን የሰጠኝ እግዚያር ግን ደግ ነው። ልጅ እያለሁ አብረን መርካቶ ያደግን ታየች የምትባል የልብ ጓደኛ ነበረችኝ። የሆነ ጊዜ ላይ ራጉኤል ጋር የነበረው የአባቷ ጨርቃ...
14/02/2025

#መስፈርት
ህልምና መጽሐፍን የሰጠኝ እግዚያር ግን ደግ ነው።

ልጅ እያለሁ አብረን መርካቶ ያደግን ታየች የምትባል የልብ ጓደኛ ነበረችኝ። የሆነ ጊዜ ላይ ራጉኤል ጋር የነበረው የአባቷ ጨርቃ ጨርቅ ሱቅ በጣም ታዋቂ ሆነ። ከዛ ብዙም ሳይቆይ አለፈላቸውና መርካቶን ለቀው ኦልድ ኤርፖርት የሚባል ሰፈር ቤት ሰርተው ገቡ። እኔ እዛው መርካቶ ጭቃ ላይ እየተራገጥኩ አንበጣ ሳባርር ታየች ቢኪኒ የሚባል ጡት ማስያዣ ተገዝቶላት መዋኝት ተማረች። አልፎ አልፎ ቤታቸው ስጋበዝ ምቾቷ ይጋባል። የእማማ ራድያ የሽንት ቤት ፍሳሽ በግቢዬ የሚያልፈው እኔ፣ የእነ ታየች ግቢ ውስጥ ያለው ጋርደን ላይ ተንጋልዬ መጽሐፍ እያነበብኩ ስታይ፣ አይ ውበት። አመሻሽ ላይ ወደ መርኬ ለመመለስ ገብሬል ጋር ያለው ታክሲ ውስጥ ስገባ፣ መጽሐፌን ጭብጥ እድርጌ ይዤ ከስፊው ህዝብ ጋር ስገፋፋ፣ ጎበዝ ለካስ ምቾት ይተንናል!።

ጥቂት አመታት አልፈው እኔ በ"ክልክል" አጥር ውስጥ፣ ፍቅርኛ መያዝ በማይፈቀድልኝ አስተዳደግ ውስጥ ስዳክር ታየች ሳምሶን የሚባል እንደሷ
በምቾት የሚንሳፈፍ የከንፈር ወዳጅ ያዘች። ህልምና መጽሐፍን የሰጠኝ እግዚያር ግን ደግ ነው። አሁን ደሞ ቸርነቱ በዝቶ የእኔ ከንፈር እንኳ በእውን ባይሳም የጓደዬ የታየች ከንፍር ሲሳም ሊያሳየኝ! እሱ ምን ይሳነዋል!

አንድ ቅዳሜ ታየች ደወልችልኝና ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ሰነዘርች። "ቲጂዬ ዋና ትችያለሽ?".. ከሳምሶን ጋር ጊዮን ሆቴል ሊዋኙ ተቀጣጥረው ኖሮ አብሬያቸው እንድዝናና መጋበዝዋ ነበር። ምቾቷ አሳውሯት ነው እንጂ የት ነው እኔ መርካቶ ውስጥ ዋና የምማረው? ታደለች የምትቸረችረው የከሰል ሐይቅ ውስጥ? ወይስ ወ/ሮ የሻረግ ጠላ ቤት ያለው ማሰሮ ውስጥ? ታየች ፌዝ ተማረች። ታየች ዋና ተማረች። ከመርካቶ ቦይ በኮንጎ ጫማ ተንደርድራ በቢኪኒ ጊዮን ሆቴል የውሃ ገንዳ ውስጥ ተጠመቀች።

እሁድ ጠዋት የከንፈር ወዳጆቹን አጅቤ እነሱ ሊዋኙ እኔ ፎጣ ልጠብቅ ጊዮን ሆቴል ደረስን። ጁስና ኬክ ታዞልኝ እነሱ ውሃ ውስጥ ሲንሳፈፉ እኔ በእነሱ አለም ውስጥ ስንሳፈፍ፣ እንሱ በአራት ነጥብ የታጠሩ ደማቅ አርፍተ ነገሮች። እኔ ገና ያልተብራራው ተከፍቶ ያልተዘጋ ቅንፍ። ውሃ ሲረጫጩ ደስ ሲሉ። ይጎነታተላሉ። ኦ ቢኪኒዋ! አረንጓዴ ባለአበባ። ሳምሶን ከጀርባዋ ቆሞ እሷ ጸጉሯን ወደ ላይ ሰብስባ የላላውን የብኪኒዋን ገመድ እያሰረላት ሲጠጋት እሷ እየሳቀች ከወሲብ እንፋሎቱ ስትሸሽ። ሲያስቀኑ። በቀረብልኝ በጥቂት ደቂቃዎች ነው ኬኩንም ጁሱንም የሰለቀጥኩት። እንዲህ ያለው ምግብ በነጻ ሲገኝ ሰጪው ሃሳቡን ሳይቀይር ቶሎ ማውደሙ ከልምድ የመጣ ነው። የመርካቶ ቅደም ተከተሉ መጀመርያ ረሃብ ማስታገስ ከዛ ስለ ታየች የከንፈር ዕጣ ፈንታ ማሰላሰል።

በጨረፍታ እያየኋቸው ደስታቸው ተጋባብኝ። ያሽካካሉ። ፊታቸው ያብረቀርቃል። ሳምሶን ብዙ ሳምሶኖች ቢሆን፣ እኔን ጎትቶ ውሃ ውስጥ የሚያጠልቀኝ ሌላ ሳምሶን ከዚህኛው ላይ ተቆርሶ ቢመጣ። ሮዝ ቢኪኒ ቢኖረኝ። የብኪኒዬ ገመድ ቢላላ፣ ሳምሶን ሊያስርልኝ ቢጠጋኝ፣ በወሲብ እንፋሎቱ እጠመቅ ነበር። መጣበቅ፣ መጠመቅ፣ አንድ መሆን። ታየች ለምን ሸሸች?

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያላሰብኩት ክስተት ተፈጠረ። ታየች እየተጣደፈች ከገንዳው ስትወጣ አየኋት። ፊቷ ላይ ብስጭቷ ይነበባል። ዞር ብዬ ሳምሶንን ቃኝሁት። ግራ ገብቶት ፈዞ ያያታል። አጠገቤ ስትደርስ በፍጥነት ፎጣዋን አንስታ ገላዋን እያደራረቀች "ቲጂ ቶሎ መሄድ አለብን ተነሽ" ብላኝ ሳትጠብቀኝ ወደ ልብስ መቀየሪያው ክፍል አመራች። "ይህ ቀዥቃዣ ወሲባም ምን አድርጓት ይሆን?" ብዬ እያሰላሰልኩ ተከተልኳት። ለባብሳ ወደ ታክሲ ስናመራ የሳምሶን አብሮን አለመሆን ግራ እንደገባኝ ስታውቅ "የኔ እና የእርሱ ነገር አብቅቷል" ብላ በረጅሙ ተነፈሰች።

እንዴ? ይህ የተመቸው ቦንቦሊኖ የመሰለ ልጅ፣ ለመላው የመርካቶ ኮረዳ ኬክና ጁስ የመግዛት አቅም ያለው ሳቂታው የሃብታም ልጅ፣ ቢኪኒዋን ወሲብ በተሞላበት ርህራሔ ያሰረላት ስሱ ሳምሶን ምን አድርጓት ይሆን? ልምድ ያካበቱ የሚመስሉ ከንፈሮች እንዲሁ በዋዛ ሊቀሩ?
"ምን እንዳደረገ ታውቂያለሽ?" አለች እየተብከነከነች። "የውሃው ገንዳ ውስጥ፣ እዛ የምንዋኝበት ገንዳ ውስጥ፣ አፍንጫውን ጨምቆ፣ በሃይል እንፍፍፍፍፍ ብሎ ንፍጡን ስቦ ካወጣ በኋላ እዛው ውሃ ውስጥ አይወረውረው መሰለሽ? ከዛ ደሞ እጁን መለቃለቁ! አይኑን ማየት አልፈልግም" ብላ አስረግጣ ነገረችኝ።

ወንድሜ ሆይ፣ የታየች መስፈርት ግልጽ ነው። መርሴዲስ ቢኖርህ፣ ተጫዋች፣ አማላይ፣ ሳቂታ አፍቃሪ ብትሆን፣ ነገር ግን ንፍጥህን በየቦታው የምታዝረከርክ ከሆነ፣ ከታየች ጋር እድል አይኖርህም። የህዋ ተመርማሪ ብትሆን፣ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ብትሆን፣ ምን አለፋህ የሮም ከተማን የቆረቆርከው መሃንዲስ አንተ ብትሆን፣ ግን ህዝብ የሚዋኝበትን የውሃ ገንዳ በንፍጥህ የምትበክል ዝርክርክ ከሆንክ የታየች አጸያየፍ ከእግዚያር ፍጥረት ሁሉ የረቀቀ ነው።

በትግስት ሳሙኤል

ከደራሲያን አለም ፔጅ

  እወቋቸው፣ እራቋቸውም.........👉 ስንፍና ትዳርን ይገድላል ።👉 አጉል ጥርጣሬ ትዳርን ይገድላል።👉 እምነት ማጣት ትዳርን ይገድላል።   👉 አለመከባበር ትዳርን ይገድላል። 👉ይቅር አለማ...
13/02/2025

እወቋቸው፣ እራቋቸውም.........

👉 ስንፍና ትዳርን ይገድላል ።

👉 አጉል ጥርጣሬ ትዳርን ይገድላል።

👉 እምነት ማጣት ትዳርን ይገድላል።

👉 አለመከባበር ትዳርን ይገድላል።

👉ይቅር አለማለት፣ አብዝቶ መኮሳተር፣
ጥላቻና ንዴት ትዳርን ይገድላሉ።

👉 አላስፈላጊ ክርክርና ጭቅጭቅ ትዳርን
ይገድላል።

👉 ሚስጥር መደባበቅ ትዳርን ይገድላል።

👉በገንዘብ፣ በስሜት፣ በስነ-ልቦና፣ በቁሳቁስ የሚደረግ ጭቆና ትዳርን ይገድላል።

👉ደካማ የሆነ ተግባቦት ትዳርን ይገድላል።

👉ውሸት ትዳርን ይገድላል።

👉 ከትዳር አጋር ይልቅ ከቤተሰብ ከጓደኛና ከዘመድ አዝማድ ጋር ጊዜን ማሳለፍ ትዳርን ይገድላል።

👉 በቂ፣ ተገቢና ጤናማ ወሲባዊ ግንኙነት አለማድረግ ትዳርን ይገድላል።

👉 የትዳር አጋርን ማንጓጠጥ፣ ማዋረድና መዝለፍ ትዳርን ይገድላል።

👉 ወሬ ማብዛትና ጥንቃቄ የጎደለው ንግግር ትዳርን ይገድላል።

👉 ለትዳር አጋርና ለትዳሩም ጭምር በቂ ጊዜ አለመስጠት ትዳርን ይገድላል።

👉 የጋራ ጥረትና የጋራ ትብብር በሚጠይቀው የጋራ ትዳር ውስጥ አብዝቶ በራስ መወሰን እና በራስ ብቻ መቆም /independent/ ትዳርን ይገድላል።

👉ወጪ ማብዛት፣ ድግስ ቸበርቻቻ፣ ከአቅም በላይ ወጪ የሚያስወጡ መኀበራዊ ግንኙነቶች ትዳርን ይገድላሉ።

👉 ለቤተሰብና ለዘመድ የትዳር አጋርን ድክመት መናገር ትዳርን ይገድላል።

👉 ፈጣሪን አለመፍራት፣ ከሃይማኖትም ከዕምነትም ህግጋት ውጭ መሆን ትዳርን ይገድላል።

👉 ከስህተት አለመማርና ጥፋትን ለማረም አለመሞከር ትዳርን ይገድላል።

👉 ጋባዥ ያልሆነ፣ ደባሪ ሙድና ፈገግታ የተለየው ፊትን ለትዳር አጋር አዘውትሮ ማሳዬት ትዳርን ይገድላል።

👉በትዳር ውስጥ ያለንን ኃላፊነትና ድርሻ አለመወጣት ትዳርን ይገድላል።

👉ቁጣንና ብስጭትን መቆጣጠር አለመቻል ትዳርን ይገድላል።
🤔🤔ምን ቀረኝ? አዎ 'a problem well stated is a problem half solved' እንዲሉ እነዚህንና መሰል ትዳር ገዳይ ስንክሳሮችን አስወግዱ...............ከዛም በሱ ፈቃድ🖕ጣፋጭ ትዳር ይኖራችኋል።
________________//________________
በሰላም አምሹ አዳዲስ አስተማሪ ታሪኮች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ፔጁን ሼር ፣፣፣ላይክ ያድርጉ
ከደራሲያን አለም ፔጅ

የድብርት ምልክቶች ከሰው ሰው ሊለያዩ ይችላሉ...ግን በብዙ ሰዎች ሊታዩ የሚችሉ የተለመዱ  ምልክቶች አሉ፡፡1.ሀዘን፣ጭንቀት ፣ ወይም የባዶነት ስሜት መሰማት2. ተስፋ መቁረጥ ወይም ጨለምተኛ...
13/02/2025

የድብርት ምልክቶች ከሰው ሰው ሊለያዩ ይችላሉ...ግን በብዙ ሰዎች ሊታዩ የሚችሉ የተለመዱ ምልክቶች አሉ፡፡

1.ሀዘን፣ጭንቀት ፣ ወይም የባዶነት ስሜት መሰማት

2. ተስፋ መቁረጥ ወይም ጨለምተኛ መሆን

3. ያልተገባ የጥፋተኝነት ስሜት ፣ጥቅም አልባነት ፣ረዳት አልባነት

4 በፊት የሚወዱት እና የሚያስደስት ነገር ላይ ፍቅር መቀነስ ወይም መጥላት

5 ድካምና የኃይል ማነስ

6 የትኩረት ማነስ ወይም አለማስተዋል

7 የእንቅልፍ ዕጦት ወይም ከልክ በላይ ማንቀላፋት

8.የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና የክብደት ለውጥ

10. ስለ ሞት ወይም እራስን ስለ ማጥፋት ማሰብ ወይም ራስን ለማጥፋት መሞከር

11.ራስምታት ፣ ሕመም ፣ ድካም ወይም ትክክለኛ የሆነ አካላዊ ምክንያት የሌለው ወይም በሕክምና የማይድን የሕመም ስሜት መሰማት

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ቢያንስ ለሁለት ሳምንት ያክል እራስዎት ላይ ወይም ሌላ ሰው ላይ ካስተዋሉ እርዳታ ማግኘት የግድ ያስፈልጎታል።

(የጤና ወግ)
ከድብርት ጋር ተያይዞ የገጠሞት ነገር ካለ ቢያጋሩን!

ETC 61.9 ቢልዮን ብር አተረፈ 🙏🙏
12/02/2025

ETC 61.9 ቢልዮን ብር አተረፈ 🙏🙏

 #እናመስግንዳናውብ Mለሜቄዶኒያ 700 ሽ ብር  ብር ሰጠችበጣም አመግኑልን           #ሜቄዶኒያ
12/02/2025

#እናመስግን
ዳናውብ M
ለሜቄዶኒያ 700 ሽ ብር ብር ሰጠች

በጣም አመግኑልን

#ሜቄዶኒያ

በእምነት ሙሉጌታ /አደይ ለሜቄዶኒያ 1.4 ሚሊዮን ብር ሰጠችበጣም አመግኑልን           #ሜቄዶኒያ
12/02/2025

በእምነት ሙሉጌታ /አደይ
ለሜቄዶኒያ 1.4 ሚሊዮን ብር ሰጠች

በጣም አመግኑልን

#ሜቄዶኒያ

ልደቷን ያከበረች ፈቃድ አግኝታ ነው 😎🙄በአየር መንገድ ግቢ ውስጥ ከአመራሮች እውቅና ውጪ ተነሳ የተባለው ፎቶ በእውቅና መደረጉን የሚያሳይ ደብዳቤ ወጣ ከቀናት በፊት ሲያነጋግር የነበረው የአ...
12/02/2025

ልደቷን ያከበረች ፈቃድ አግኝታ ነው 😎🙄

በአየር መንገድ ግቢ ውስጥ ከአመራሮች እውቅና ውጪ ተነሳ የተባለው ፎቶ በእውቅና መደረጉን የሚያሳይ ደብዳቤ ወጣ

ከቀናት በፊት ሲያነጋግር የነበረው የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የተነሳው ፎቶ እንደተባለው "ከተቋሙ አመራሮች እውቅና ውጪ" ሳይሆን በእውቅና መደረጉን የሚያሳይ ደብዳቤ ለመሠረት ሚድያ ደርሷል።

የአየር መንገዱ የአዲስ አበባ ሽያጭ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ግሩም አበበ ለሲቪል አቪዬሽን ደህንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተር ታህሳስ 25/2017 ዓ/ም በፃፉት ደብዳቤ አርቲስት ምህረት ታደሰ በአየር መንገድ የአየር ክልል ውስጥ የፎቶ ፕሮግራም እንድታደርግ መጠየቋን ያሳያል።

ደብዳቤው አክሎም የፎቶ ፕሮግራሙ ለአየር መንገዱ ማስታወቂያነት ስለሚጠቅም ታህሳስ 27/2017 ዓ/ም ቅጥር ግቢ ውስጥ ገብተው ፎቶ እንዲነሱ ይጠይቃል።

የፎቶ ፕሮግራሙ በዚህ ሁኔታ በተቋሙ እውቅና ቢካሄድም ተቋሙ ከትናንት በስቲያ በፌስቡክ ገፁ "የግለሰቧ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የልደት ምስል ቀረጻ ከተቋሙ አመራሮች እውቅና ውጭ የተደረገ ነው" ማለቱ ግርታን ፈጥሯል።

በተጨማሪም የፎቶ ፕሮርግራሙ የግል የልደት ፕሮግራም መሆኑን አርቲስቷ በሶሻል ሚድያ ገጿ ላይ የገለፀች ቢሆንም ይህ በምን መልኩ ለአየር መንገዱ በማስታወቂያነት እንደሚጠቅም ግልፅ አልሆነም።

ተቋሙ ለፎቶ ፕሮግራሙ ከአርቲስቷ ገንዘብ አለመቀበሉን እና ምንም አይነት ውል እንደሌለው በመግለጫው ላይ ገልፆ ነበር።

በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ድርጊቱን ከአየር የበረራ ክልል ደህንነት ጋር በማንሳት ጥያቄ ሲያቀርቡ ሌሎች ደግሞ በምን መስፈርት አንድ ግለሰብ የግል ልደት ከፍ ያለ ደህንነት በሚያስፈልገው አውሮፕላን ላይ ዲኮር በመስራት ተከበረ የሚል ጥያቄ አንስተዋል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ክስተቱ ለአየር መንገዱ ጥሩ ማስታወቂያነት ውሏል ብለው ሀሳብ የሰጡም አልጠፉም።

Via መረጃን ከመሠረት!

ከባድ  #የመኪና አደጋ ተከሰተ 27 ሰው የሞት😭43 ሰው ከባድ አደጋ 🙄በምስራቅ ወለጋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ27 ሰዎች ሕይወት አለፈ*********በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን...
11/02/2025

ከባድ #የመኪና አደጋ ተከሰተ
27 ሰው የሞት😭
43 ሰው ከባድ አደጋ 🙄

በምስራቅ ወለጋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ27 ሰዎች ሕይወት አለፈ
*********

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ጉዳያ ቢላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ27 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ የደረሰ አደጋ ነው ተብሏል።

በአደጋው የ27 ሰዎች ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 43 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የሻምቡ ወረዳ አስተዳዳሪ ምሬሳ ፌጤ ለኢቲቪ ገልፀዋል።

በዘአማኑኤል መንግሥቱ

ነፍስ ይማር ሳትሉ አትውጡ
Rip

 !  ጊዜህን የምታሳልፍበት መንገድ ማንነትህን ይገልጻል፡፡ እንዴት እና መቼ እንደምትሞት አትመርጥም፤ ነገር ግን አሁን እንዴት እንደምትኖር መወሰን ትችላለህ፡፡ እመነኝ ከዛሬ አንድ ዓመት በ...
11/02/2025

!


ጊዜህን የምታሳልፍበት መንገድ ማንነትህን ይገልጻል፡፡ እንዴት እና መቼ እንደምትሞት አትመርጥም፤ ነገር ግን አሁን እንዴት እንደምትኖር መወሰን ትችላለህ፡፡ እመነኝ ከዛሬ አንድ ዓመት በኋላ ምናለ ዛሬ ጀምሬ በነበረ ስትል ትመኛለህ፡፡


ቆየም ዘገየ፣ የሚቆጠረው በመንገድህ ላይ የምታጣው ነገር ሳይሆን፣ አሁንም በእጅህ ላይ ባለህ ነገር የምታደርገው ነገር መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡ ስትተወው፣ ይቅር ስትል እና ወደፊት ሕይወትህን ስትቀጥል በምንም መንገድ ያለፈውን አትለውጠውም፤ የወደፊቱን ግን ትለውጠዋለህ፡፡

የእያንዳንዳችን ውበት ያለው በድክመቶቻችን፣ በፍቅሮቻችን፣ በውስብስብ ስሜቶቻችን እና በእውነተኛው ፍጹም አለመሆናችን ውስጥ ነው፡፡ ማንነታችንን ስንቀበል እና ፍጹም ከመሆን ይልቅ እውነተኛ ለመሆን ስንወስን ራሳችንን ለእውነተኛው ግንኙነት፣ ለእውነተኛው ደስታ እና ለእውነተኛው ስኬት ክፍት እናደርጋለን፡፡ ጭምብል ማድረግ አያስፈልግም፡፡ ያልሆኑትን ሰው ለመሆን ማስመሰል ፋይዳ የለውም፡፡ አሁን ባለህበት መንገድ ፍጹም ባለ እንከን ነህ፡፡


ስህተት እንደሆነ ያመንከውን ነገር እንደማድረግ ጎጂ የሆነ ነገር ምንም የለም፡፡ እምነትህ ብቻ እንድታድግ እና እንድትመነደግ አይረዳህም፤ ባህሪህ እና ድርጊቶችህ ናቸው የሚረዱህ፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜም በልብህ ትክክል መሆኑን የምታውቀውን ነገር አድርግ፡፡


ላለህ ነገር አመስጋኝ ስትሆን እና አዎንታዊ ነገሮችን እንደ መብት ባለቤትነት ከማየት ይልቅ እንደ ነጻ ስጦታ ማየት ስትጀምር ቀስ በቀስ እያደግክ በመሄድ ታላቅ ስኬትን ትቀናጃለህ፡፡


ከደራሲያን አለም ፔጅ

Check yours 😎Just fun የናተን ኮሜንት ??🖐  follower coming soon
10/02/2025

Check yours 😎
Just fun የናተን ኮሜንት ??🖐

follower coming soon

ወደ ደም የተቀየረው ወንዝ     የአለም መነጋገሪያ ሁኑዋል ነገሩ እንዲህ ነው አርጀንቲና ዋና ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፍ ወንዝ ከትናንት በስቲያ እንዲህ ወደ ደምነት ተወይሮ አድሯል። እስካሁ...
10/02/2025

ወደ ደም የተቀየረው ወንዝ
የአለም መነጋገሪያ ሁኑዋል
ነገሩ እንዲህ ነው አርጀንቲና ዋና ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፍ ወንዝ ከትናንት በስቲያ እንዲህ ወደ ደምነት ተወይሮ አድሯል።
እስካሁንም ወደ ቀድሞ መልኩ ይቀየራል ቢባልም አልሆነም።

ናሙናው ተወስዶ መንስኤው ቢጣራ ምንም መልስ ያልተገኘለት የወንዙ ወደ ቀይነት መቀየር የአለም መገናኛ ብዙሃን ትኩረት ስቧል።

በተመሳሳይ መልኩ በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ /የደም ምንጭ ተብሎ የሚጠራ ቀይ የዉሃ ምንጭ እንዳለ ይታወቃል ።

Address

Adis Abeba Ring Road
Addis Ababa
BOLE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከደራሲያን አለም ፔጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share