Gize Media

Gize Media Gize is one of the best Ethiopian infotainment media. We provide with multidimensional access to the

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋ...
06/01/2025

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።

ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ። ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ፡ አሉ።” #ሉቃ ፪:፲፩_፲፬

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ🙏

በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የጤና እንዲሆን ልባዊ ምኞታችንን እየገለፅን በዓሉን ስናከብር በየአካባቢያችን የሚገኙ አቅመ ደካሞችን፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸውና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስታወስ፤ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉም ካለን በማካፈል፣ የቻልነውን በማድረግና በመደገፍ ሁላችንም አብሮነታችንን እንድናሳይ እንጠይቃለን። 🙏

መልካም በዓል ይሁንልን!

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

ትልቁ ህልሜ ኢትዮጵያ በራስዋ ፊደልና አኃዝ የራስዋን ቴክኖሎጂ መፃፍ መጀመር ነው። ይህ ለትውልድ የሚሻገር አሁንም ያለው ትውልድ እሴቱን አብዝቶ እንዲጠቀም የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥረት ያስፈል...
12/12/2024

ትልቁ ህልሜ ኢትዮጵያ በራስዋ ፊደልና አኃዝ የራስዋን ቴክኖሎጂ መፃፍ መጀመር ነው።

ይህ ለትውልድ የሚሻገር አሁንም ያለው ትውልድ እሴቱን አብዝቶ እንዲጠቀም የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥረት ያስፈልጋል።

እንደ ራሺያ፣ ቻይና፣ ጃፓን፣ ጀርመን የመሳሰሉት ሀገሮች በራሳቸው ቋንቋ ቴክኖሎጂ እንዳላቸው ሁሉ እኛም ከእኛ አልፎ ለአፍሪካውያን በሙሉ የሚሆን ተቋም እንገነባለን።

ኤልያስ የሳይንስ ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ ምስረታ ቅድመ ኮሌጅ ምክክር በሁሉም የአሜሪካን ስቴቶች ባሉ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር አደራጅነት ከካሪክለም ቀረፃ እስከ ግንባታ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ርብርብ እውን እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም!

Lij Elias Science University Addis Ababa, Ethiopia

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

እስረኞችን በአንበሳ የሚያስበላው ሜጀር ጄኔራል ቴላል አል-ዳካክ። ይህ ሰው የአምባገነኑ የአሳድ መንግስት ቀኝ እጅ የነበረ ነው። በተለይ በአሳድ መንግስት ላይ አምፀዋል ወይም ሊያምጹ አስበዋ...
10/12/2024

እስረኞችን በአንበሳ የሚያስበላው ሜጀር ጄኔራል ቴላል አል-ዳካክ።

ይህ ሰው የአምባገነኑ የአሳድ መንግስት ቀኝ እጅ የነበረ ነው። በተለይ በአሳድ መንግስት ላይ አምፀዋል ወይም ሊያምጹ አስበዋል እየተባሉ በየጊዜው የሚያዙትን ሰወች በማሰቃየትና በመግደል እንዲሁም እስረኞችን በአንበሶች እንዲበሉ ሲያደርግ ለአመታት የቆየ ሰው ነበር።

እሁድ እለት የአሳድ ስርአት መወገዱን ተከትሎ ይህ የሺህዎች ደም ያለበት ሰው ተያዘ። እና ዛሬ በሀማ በሚገኘው ኦሮንቴስ አደባባይ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ይህ ብዙዎችን ያሰቃየ ሰው በተራው በሞት ይቀጣል።

ያ መልአከ ሞት እጅግ ደፋርና ጨካኝ መስሎ ይታይ የነበረ ሰው በተያዘበት ወቅት በፊቱ ላይ ይታይ የነበረው ፍርሀት አስገራሚ ነበር።

በዛሬው እለት በዚህ ጄኔራል ላይ የሚፈፀመውን ቅጣት ለመመልከት በአደባባዩ ብዙ ሰው እየተጠባበቀ ነው።

:- Wasihune Tesfaye

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

አትሙት ያለው ነብስ!የአምባገነኑ ሃፌዝ አል አሳድ አገዛዝ መገርሰሱን ተከትሎ ከተሞችን የተቆጣጥረው ሀይል የመንግስት እስር ቤቶችን ሰብሮ የፖለቲካ እስረኞች የነበሩ ሰወችን ነጻ አድርጓል።ከነ...
08/12/2024

አትሙት ያለው ነብስ!

የአምባገነኑ ሃፌዝ አል አሳድ አገዛዝ መገርሰሱን ተከትሎ ከተሞችን የተቆጣጥረው ሀይል የመንግስት እስር ቤቶችን ሰብሮ የፖለቲካ እስረኞች የነበሩ ሰወችን ነጻ አድርጓል።

ከነዚህ መሀከል ደግሞ እዛው እስር ቤት ተወልዶ ያደገ ህጻን ልጅ እና ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ሰው ይገኝበታል።

በዋና ከተማዋ ደማስቆ ውስጥ በሚገኘውና አሰቃቂ በሆነ አያያዙ የሞት ፋብሪካ በሚል ቅፅል ስም በሚታወቀው ሲድናያ እስር ቤት የተገኘው ይህ እስረኛ በተደረገበት ከፍተኛ ድብደባ ምክንያት ከመጎዳቱ የተነሳ ስሙን እንኳን በደንብ መናገር አይችልም።

እና በጣም አስገራሚ የሆነው ነገር ይህ የግፍ እስረኛ ከረዥም ጊዜ እስራት በኋላ በዛሬው እለት እንደሚገደል ተነግሮት የነበረ ሲሆን ግድያው ከመፈፀሙ በፊት የአሳድ ተቃዋሚዎች በማሸነፋቸው ዛሬ ሊገደል ቀጠሮ የተያዘለት ይህ ሰው በታጣቂ ሀይሎቹ ከነበረበት እስር ቤት ነጻ መውጣት ችሏል።

:- Wasihune Tesfaye

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

የዌስትሃም አጥቂ ሚሼል አንቶኒዮ ከባድ የመኪና  አደጋ አጋጥሞታል። አደጋው ሲደርስ ቤተሰቦቹ መኪና ውስጥ ነበሩ። ተጫዋቹ እና ቤተሰቦቹ ያሉበት ሁኔታ ከባድ በመሆኑ ሁሉም ፀሎት እንዲያደርግለ...
07/12/2024

የዌስትሃም አጥቂ ሚሼል አንቶኒዮ ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥሞታል። አደጋው ሲደርስ ቤተሰቦቹ መኪና ውስጥ ነበሩ።

ተጫዋቹ እና ቤተሰቦቹ ያሉበት ሁኔታ ከባድ በመሆኑ ሁሉም ፀሎት እንዲያደርግለት ክለቡ ዌስትሀም ጥሪውን አቅርቧል።

:- እጅግ አስተማሪ ታሪኮችና ጽዕሁፎች ፔጅ

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

በዜግነት ኤማራቲ በትውልድ ሩሲያዊ የሆነው  Khamzat Chimaev እና ሩሲያዊው Ikram Aliskerov ወሳኝ የተባለ የቦክስ ( Mixed Martial Art ) ግጥሚያ ባደረጉበት ወቅት...
22/11/2024

በዜግነት ኤማራቲ በትውልድ ሩሲያዊ የሆነው Khamzat Chimaev እና ሩሲያዊው Ikram Aliskerov ወሳኝ የተባለ የቦክስ ( Mixed Martial Art ) ግጥሚያ ባደረጉበት ወቅት ነው።

በዚህ ጨዋታ ካማዛት ተቀናቃኙ የሆነውን ኢክራምን ደጋግሞ በመምታትና በመዘረር ካሸነፈ በኋላ ሁልጊዜ እንደሚያደርገው ለእናቱ ደወለ።

ሁለቱ ተፋላሚዎች ያደረጉትን ግጥሚያ በቴሌቪዥን ሲመለከቱ የቆዩት የካማዛት እናት አሸንፎ የደወለላቸውን የልጃቸው ድምፅ ሲሰሙ እያለቀሱ ያናግሩት ጀመር።

ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው አሸንፌያለሁኮ "አዎ ማሸነፍህንማ አይቻለሁ" እና ለምን ታለቅሻለሽ?

"እንደዛ አድርገህ ስትመታው ሳይ እናቱን አሰብኳት እሱምኮ እናት አለው። አንተ ልጁን በመታህበት ሁኔታ አንተን ሲመቱብኝ ባይ ምን አይነት ስሜት እንደሚሰማኝ አሰብከው? እኔ ግን ብትችል ይህን ስፖርት ብትተው ነበር ደስ የሚለኝ"

ካማዛት ይህን የእናቱን ንግግር ሲሰማ ያረጋጋቸው ጀመር ምንም እኮ አልሆነም እናቴ ከሪንጉ በእግሩ እየተራመደ ነው የሄደው ያሰብሽው ያህል አልተጎዳም።
የካማዛት እናት ይህን እንደሰሙ እኔ አላምንህም በርግጥ እንደምትለው ደህና ሆኗል? እያሉ ደጋግመው ጠየቁት።

ለኚህ ደግ እናት ከልጃቸው ማሸነፍ ይልቅ የኔ ልጅ ቢሆንስ የሚለውን አስበው የተጋጣሚው ጉዳት ነበር ያሳሰባቸው።

ሰው ስትሆን !

:- Wasihune Tesfaye



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

በኢትዮጲያ የሙዚቃ ታሪክ ላለፉት 47 ዓመታት ለበርካታ ድምፃዊያን ግጥምና ዜማ በመስጠት የሚታወቀዉ አሳየ ዘገየ ከ37 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ሲመጣ ደማቅ አቀባበል በሙያ ባልደረቦ...
21/11/2024

በኢትዮጲያ የሙዚቃ ታሪክ ላለፉት 47 ዓመታት ለበርካታ ድምፃዊያን ግጥምና ዜማ በመስጠት የሚታወቀዉ አሳየ ዘገየ ከ37 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ሲመጣ ደማቅ አቀባበል በሙያ ባልደረቦቹ ተደረገለት።

:- አብርሐም ግዛዉ ኢንተርቴይመንትና ፎቶ ፎከስ ስቲዲዮ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

በቴ ኡርጌሳ በግፍ መገደሉን በሰማሁ ጊዜ ቢያንስ ቤተሰቡን እናስታውሰው የሚል ይዘት ያለውን ፅሑፍ ገፄ ላይ ለጥፌ ነበር። ላለፉት ሰባት ወራትም "pinned" ተደርጎ ቆይተዋል።  ከሰሞኑም አ...
17/11/2024

በቴ ኡርጌሳ በግፍ መገደሉን በሰማሁ ጊዜ ቢያንስ ቤተሰቡን እናስታውሰው የሚል ይዘት ያለውን ፅሑፍ ገፄ ላይ ለጥፌ ነበር። ላለፉት ሰባት ወራትም "pinned" ተደርጎ ቆይተዋል። ከሰሞኑም አዲስ ነገር ሰምተናል።

የበቴ ኡርጌሳ ነፍስ ፍትህን ባታገኝም ቢያንስ ቤተሰቡ ከዚህ አገር ወጥቶ በአሜሪካ ማረፊያ አግኝቷል። ይህን በማሳካት ሂደት ውስጥ የተሳተፉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል🙏

ያኔ ያልኩትን አሁንም እደግመዋለሁ...

ዛሬ ሁላችንም ስለ ጃል በቴ ኡርጌሳ መገደል ሀዘናችንን እየገለፅን ይሆናል። ሁለት ሶስት ቀን ቢበዛ ደግሞ ለአንድ ሰምንት ተጯጩኸን ዝም እንላለን። ነገሩ በዛው ይዳፈናል። የተለመደው የሕይወት ኡደት ይቀጥላል።

ምናልባት ዛሬ እንኳን እኛ ኳስ ስለማየት እናስብ ይሆናል። ግን ይህን ቤተሰብ ተመልከት... ያለ አባት የቀሩ እነኚህን አሳዛኝ ህፃናትን... ዋርካዋ የወደቀባት እናትን... ዳግም ላይጠገን ልቧ የተሰበረን ሚስት... በለቅሶ ብዛት ጉንጮቿ የጅረት መውረጃ ቦይ የሰሩባትን "እመቤት"... የማይሽር ቁስል ተሸክሞ ለዘለዓለሙ በቁጭት ረመጥ እንዲቃጠል የተፈረደበትን ይህን ቤተሰብ አስበው።

:- ጥላዬ ያሚ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

ሚሊየነሯ እየተፈለገች ነው!ዘምዘም መሀመድ አሊ እባክሽ የማታ ሲሳይሽን ዱባይ ፈርመሽ ውሰጅ እስከ ታህሳስ 20 , 2017 ድረስ።እባካችሁ ሼር አድርጉት🙏‼️ይችን በፎቶ የምታዮዋትን ልጅ እምታ...
13/11/2024

ሚሊየነሯ እየተፈለገች ነው!

ዘምዘም መሀመድ አሊ እባክሽ የማታ ሲሳይሽን ዱባይ ፈርመሽ ውሰጅ እስከ ታህሳስ 20 , 2017 ድረስ።

እባካችሁ ሼር አድርጉት🙏‼️

ይችን በፎቶ የምታዮዋትን ልጅ እምታውቁ እባካችሁ ተባበሩ በተለይ ወሎ ያላችሁ ፓሥፖርቷን ያወጣችው ደሤ ነው ተብሏል።

ጉዳዩ ምንድን ነው ላላችሁ ህይወቷን የሚቀይር ገንዘብ ዱባይ ላይ እየጠበቃት ነው ነገሩ እንዲህ ነው ዱባይ ቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ትሠራ ነበር 2004 አካባቢ ይመሥለኛል ከዛ ከሰዎቹ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ጉዳት ያደርሡባታል የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት ጋር ጉዳዩ ይደርሣል።

ጽ/ቤቱም ጠበቃ ቀጥሮ ይከራከራል በዚህ መሀል ልጅቱ አገር ቤት ገብታለች ከዛ አሰሪወቿ ከከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ጋር ሸንፈትን ተኮናነቡ ልጅቱ አድራሻዋ ጠፋ እሥከ ጥር ድረሥ እየተጠበቀች ነው።

በነገራችን ላይ ወላጆቿ ቤተሠቧቿ ካሉም የ DNA ምርመራ ተደርጎ ይሠጣቸዋል ተብሏል ሥሟ ዘምዘም መሀመድ አሊ ትባላለች እና እባካችሁ ይሄኔ ምን ላይ እንደሆነች አናውቅም እና መረጃውን በማጋራት ይህችን እህት እናገናኛት።

:- ጉራማይሌ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

የደጋ ሰው በተሰኘ ስራዋ የምትታወቀውን ድምጻዊ የሚን ጨምሮ 35 የሀገራችን ስመ ጥር የሰርከስ ቡድን አባላት ዓለምን ሊዞሩ ነውኢትዮጵያዊያን የያዘው አፍሪካን ድሪም አርትስ በተለያዩ የአውሮፓ...
08/11/2024

የደጋ ሰው በተሰኘ ስራዋ የምትታወቀውን ድምጻዊ የሚን ጨምሮ 35 የሀገራችን ስመ ጥር የሰርከስ ቡድን አባላት ዓለምን ሊዞሩ ነው

ኢትዮጵያዊያን የያዘው አፍሪካን ድሪም አርትስ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሰርከስ ትርኢት ሊያቀርብ ነው።

አፍሪካን ድሪም አርትስና አፍሪካን ድሪም ሠርከስ ከህዳር 04 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ሠላሳ አምስት አባላት ያሉት ኢትዮጵያውያን ብቻ ያሉበት የሠርከስ ቡድን አባላት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች እየተዟዟሩ ስራቸውን የሚያሳዩ ሲሆን የሀገራችንን ውብ ባህሎችም ያስተዋውቃሉ ተብሏል።

በእዚህ ፕሮግራም ላይ የውዝዋዜ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾችን እና ድምፃዊያንን ከተለያዩ ክልሎች ካሉ የሰርከስ ማእከላት የያዘ ልዩ ቡድንን ይዞ ፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኘው ሰርከስ ካምፓኒ በሰርክ ፊኔክስ "ሰርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮኮቦች" ሾው በፊኔክስ መድረክ እንዲሁም በቤልጅዬም፤ በሞናኮ ሞንቴካርሎ፣ በስዊዘርላንድ፤ በአንዶራና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የኢትዮጵያን ባህል፣ አለባበስ፣ ሙዚቃና ጭፈራ ያካተተ ሙሉ የስርክስ ትርኢት ይዞ እንደሚጓዝ አስታወቀ።

አፍሪካን ድሪም አርትስና አፍሪካን ድሪም ሠርከስ በታዋቂው የሠርከስ አርቲስት፣ አሰልጣኝ፣ ዳይሬክተርና ማናጀር የኔነህ ተስፋዬ የተቋቋመ ሲሆን ለበርካታ ዓመታት ኢትዮጵያዊያን የሠርክስ አርቲስቶችን በሀገራችን ፣ በአህጉራችን ብሎም በዓለምአቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የሠርከስ ፌስቲቫሎች፤ የቲቪ ሾዎች፣ የጎት ታለንቶች፣ የጊነስ ወርልድ ሪከርድ ወዘተ ላይ ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካውያንን ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና በተለያዩ የሰርከስ ካምፓኒዎችና ማናጀሮች ስራዎቻቸው ተፈላጊና ተወዳጅ እንዲሆኑ ከፍተኛ አድናቆት እንዲያገኙ ብሎም እንዲሸለሙና ስራዎችን እንዲያገኙ ሲያደርግ የቆየ ነው ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ ለዓለም አቀፍ የሠርከስ ካምፓኒዎች ትርኢቶች በማቅረብ ለብዙ ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካውያን የስራ እድል ማመቻቸት መቻሉን የአፍሪካ ድሪምስ መስራች የኔነህ ሲሳይ ተናግሯል።



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

ኢንጂነር ቢጃይ በቡርኪናፋሶ ቤተመንግስት።ይህ ሰው በ36 አመቱ የሀገር መሪ የሆነ በምድራችን በእድሜ ትንሹ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ትራኦሬ ነው።ወደስልጣን ከመጣበት ከባለፉት ሁለት ...
29/10/2024

ኢንጂነር ቢጃይ በቡርኪናፋሶ ቤተመንግስት።

ይህ ሰው በ36 አመቱ የሀገር መሪ የሆነ በምድራችን በእድሜ ትንሹ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ትራኦሬ ነው።

ወደስልጣን ከመጣበት ከባለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ ሀገሪቱን ወደተሻለ ደረጃ ለመለወጥ እየጣረ የሚገኝ እንደፈረንሳይ ባሉ የአፍሪካን ጥሪት ከሚበዘብዙ ምእራባውያን ውጭ በሀገሩ ህዝብና በአካባቢው ሀገራት ተደማጭና ተወዳጅ እየሆነ የመጣ ባለ ራእይ ወጣት መሪ ነው።

ካፒቴን ኢብራሂም ትራዎሬ ወደስልጣን ከመጣ በኋላ የሀገሩን ህዝብ ህይወት ሊያሻሽሉ የሚችሉ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

የዚህ ቡርኪናፎሶን ለማሳደግ የስራ እድሎችን ለመክፈትና የህዝቡን ህይወት ለማሻሻል የተቀረፀው ፖሊሲ አንዱ አካል በሆነው ዛሬ በኮሉባ ቤተመንግስት በተካሄደው ስነስርአትም የቡርኪናፋሶው ወጣት ፕሬዝደንት በቡርኪናፋሶ የተለያዩ ቦታዎች ለኢንደስትሪና ግብርና የሚያገለግሉ ማሽኖችን ለማምረትና ወጣቶችን ለማሰልጠን ከኢትዮጵያዊው ኢንደስትሪያሊስትና በጎ አድራጊ ከኢንጂነር Bejai Nerash Naiker ጋር ተፈራርመዋል።

ይህ ለኢንጂነር ቢጃይ ብቻ ሳይሆን እንደሀገርም የሚያኮራ ነገር ነው።

:- Wasihune Tesfaye



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

የሀዘን ዜና !የኢትዮጵያ እግር ኳስ ምልክት ከሆኑት ታላላቅ ሰዎች ውስጥ የሚጠቀሰው አሰልጣኝ አስራት ሀይሌ (ጎራዴው) ማረፉ ተሰማ።ባደረት ህመም በቱርክ እና በኢትዮጵያ ህክምና ሲከታተል ቆይ...
25/10/2024

የሀዘን ዜና !

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ምልክት ከሆኑት ታላላቅ ሰዎች ውስጥ የሚጠቀሰው አሰልጣኝ አስራት ሀይሌ (ጎራዴው) ማረፉ ተሰማ።

ባደረት ህመም በቱርክ እና በኢትዮጵያ ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ዛሬ ዋርካው ማረፉን ጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ ፅፏል።

ባላገሩ ቴሌቪዥን ለቤተሰብ ወዳጅ ዘመድና፣ ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

:- ባላገሩ ስፖርት

#ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

የቡርኪናፋሶዋ ገበሬ! ይህች ልጅ ስዋሚድዋ ሀቢዳዲ ትባላለች ሀገሯ የቶማስ ሳንካራዋ ቡርኪናፋሶ 🇧🇫🇧🇫።ገበሬ ነች! ወላጆቿ ከሞቱ በኋላ በ16 ዓመቷ ግብርና ጀመረች።ከትምህርት ይልቅ እርሻን ...
22/10/2024

የቡርኪናፋሶዋ ገበሬ! ይህች ልጅ ስዋሚድዋ ሀቢዳዲ ትባላለች ሀገሯ የቶማስ ሳንካራዋ ቡርኪናፋሶ 🇧🇫🇧🇫።

ገበሬ ነች! ወላጆቿ ከሞቱ በኋላ በ16 ዓመቷ ግብርና ጀመረች።

ከትምህርት ይልቅ እርሻን መረጠች ፤ ከቤተሰቧ በውርስ ያገኘችውን 6 ሄክታር መሬት ''አሸሼ ገዳሜ ብላ አላጠፋችውም''። 6 ሄክታር መሬቷን ለተለያዩ አዝርዕት እና ፍራፍሬ ከፋፍላ አሳረሰች። ሩዝ ፣ በቆሎ ፣ ባቄላ ፣ አኩሪ አተር እና ፍራፍሬ እና ሌሎችንም ዘራች።

ከወላጆቿ የተረከበችውን 6 ሄክታር መሬት ለእርሻ ብቻ አዋለችው። መሬቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ዋና የገቢ ምንጭዋ ሆነ።

ስዋሚድዋ በዚህ አመት 10,000 ከረጢት በቆሎ ፣ 8,000 ከረጢት ሩዝ እና 5,000 ከረጢት የተፈጨ ለውዝ ሰበሰበች።

ከ900 በላይ ከብቶች ፣ 500 ፍየሎች አልዋት። 20 ወንድ እና 20 ሴቶች ቀጥራ ታሰራለች። በቀላሉ ለማልማት የሚያስችል ትራክተርም አላት።

ከጋዜጠኛው ጋር ቆም ብላ ስታወራ Vx hilux መኪናዋን ተደግፋ ነው። ከዚህ ተሽከርካሪ ሌላ እንደ 4 BMW ፣ 2 Mercedes Benz Wagon እና 3 Range Rover መኪኖች አሏት። ለእያንዳንዱ ሰራተኛ 40 ሞተር ሳይክል ገዝታለች።

በአሁኑ ጊዜ በአካባቢዋ የበጎ አድራጎት በስፋት ትሳተፋለች። መብራት ቧንቧ ውሃ ለአካባቢዋ አስገብታለች። ለበርካቶች እንጀራ እንዲወጣላቸው ምክንያት ሆናለች።

:- እጅግ አስተማሪ ታሪኮችና ጽዕሁፎች ፔጅ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

ይህ ከጀርመን ጎዳናዎች አንዱ ነው! ሰዎች ለድሆች እና በልተው ማደር ላቃታቸው ችግረኞች ምግብ በፌስታል አምጥተው ያንጠለጥላሉ።ቦታው ላይ ምንም አይነት ይህንን የሚገልጽ ማስታወቂያ የለም ፤ ...
17/10/2024

ይህ ከጀርመን ጎዳናዎች አንዱ ነው!

ሰዎች ለድሆች እና በልተው ማደር ላቃታቸው ችግረኞች ምግብ በፌስታል አምጥተው ያንጠለጥላሉ።

ቦታው ላይ ምንም አይነት ይህንን የሚገልጽ ማስታወቂያ የለም ፤ ካሜራም አልተገጠመም ፤ ምግቡን ሲያስቀምጡ እና ችግረኞችም ምግቡን ሲወስዱ አብረን ፎቶ ካልተነሳን የሚላቸው የለም ፤ ሲመገቡ ቪዲዮ እየቀረፀ የሚያጎርሳቸው የለም!

ምግቡ ፌስታሉ እና ችግረኞቹ ብቻ ነው የሚተዋወቁት።

ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው!!
አገር ቢሆንስ?

:- እጅግ አስተማሪ ታሪኮችና ጽዕሁፎች ፔጅ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

የአለልኝ ሞት የፖሊስ ምርመራ እና የፍርድ ሂደት 😭እንግዲህ ትላንትና ፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበረ ሲሆን ክሱን እንዲህ በማለት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ ተነቧል።የገዛ ሚስቱ እና የእህቱ ባል ...
16/10/2024

የአለልኝ ሞት የፖሊስ ምርመራ እና የፍርድ ሂደት 😭

እንግዲህ ትላንትና ፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበረ ሲሆን ክሱን እንዲህ በማለት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ ተነቧል።

የገዛ ሚስቱ እና የእህቱ ባል (የቀድሞ የአርባምንጭ ከንቲባ ጋርድ የነበረው) በራሱ መኖሪያ ቤት አቅደውና ተዘጋጅተው እንዳስገደለችው እንዳይታወቅባቸው እዛው ስፈረ ባለው ስልክ እንጨት ላይ በስልክ ገመድ ሰቅለው እንዳስቀመጡ በትላንትናው ቀጠሮ ለፍርድ ቤቱ ተነቧል።

አቃቢ ህጉም ከበቂ በላይ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ አቀርባለው በማለት ዳኛውም ለጥቅምት 21 2017 ተቀጥሯል።

የአለልኝ እናት ግን ልጃቸው ከሞተ በኃላ ለ6ወር ሙሉ ከቤት ያልወጡ ሲሆን፤ ለሊት እና ቀን አይናቸው እስኪጠፋ ድረስ እያለቀሱ ይገኛል። 😭

የሚስቱም ቤተሰቦች እጃቸው በጣም እረጅም ስለሆነ እንዲሁም ወደዚህ እና ወደዛ እያሉ ፍትህን ሊያጎድሉ እንዳይሆን ተፈርቷል።

ጥቅምት 21,2017 ፍትህ የምታገኝበት ቀን ሊሆን ይችላል ተብሏል።

እናት ግን እስካሁን ማቅ ለብሳ ና ሀዘን ለብሳ ልጄን እያለች ትገኛለች። 😭

:- እጅግ አስተማሪ ታሪኮችና ጽዕሁፎች ፔጅ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

በስንታየሁ ሲሳይ ጉዳይ የሚገባውን ያህል ያልተመሰገነ አንድ ሰው አለ። ድምፁን አጥፍቶ መልካም የዋለ። እሱም ነፃነት ወርቅነህ ነው። ዛሬ ለሁላችንም መረባረብ ፣ ለስንቴ ፈገግታ መመለስም ዋነ...
12/10/2024

በስንታየሁ ሲሳይ ጉዳይ የሚገባውን ያህል ያልተመሰገነ አንድ ሰው አለ። ድምፁን አጥፍቶ መልካም የዋለ። እሱም ነፃነት ወርቅነህ ነው።

ዛሬ ለሁላችንም መረባረብ ፣ ለስንቴ ፈገግታ መመለስም ዋነኛ ምክንያት የሆነ ሰው ነው ነፃነት ወርቅነህ !♥️

ስንቴ EBS ቅዳሜ ከሰዓት ላይ ከመቅረቡ በፊት ሀገሪቷ ላይ አሉ የተባሉ የቴሌቭዥን አዘጋጆችን ፣ ጋዜጠኞችን ፣ ሌላም አርቱ አከባቢ ያሉ ሰዎችን የሚያደርጉለት እገዛ ካለ አናግሯቸዋል። ግን ብዙዎች ስልክ አላነሱም። ብዙዎች ለጠየቃቸው ነገር መልስ አልሰጡትም!

ምክንያቱም የማህበራዊ ጉዳዬች አጀንዳ አልነበረምና!

በመጨረሻም ነፃነት ወርቅነህ ግን ተስፋ ሆነው። 'አይዞህ...' ብሎህ ሚዲያ ላይ እንዲወጣ አበረታው። 'የምችለውን አደርጋለሁ...' ብሎ ኮኔክሽኑን ተጠቀመ። የቅዳሜ ከሰዓት አዘጋጆችን አናገረለት።

ብዙ ሚሊየን በሚያየው የቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ እንግዳ ሆኖ ቀርቦ የሚያሰማውን እንዲናገር ፣ ከኢትዮጲያ ህዝብ ጋርም እንዲገናኝ በር ከፈተለት። የችግር ጊዜው መሸጋገሪያ ድልድይ ሆነለት!

በስንቴ ጉዳይ ከአጀቡ በፊት ፣ ይሄ ሁሉ ለመሆኑ ነፃነት ወርቅነህ የመጀመሪያው 'አለንልህ...' ባይ ሰው ነው'ና ምስጋና ይገባዋል።♥️🙏

:- ሙስተጃብ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

የፈጣሪ ተአምርይህ ወጣት የሱማሌ ወታደር ነበረ። በቦንብ አደጋ የጭንቅላቱ ግማሽ አካል በዚህ መልኩ ሲጎዳ የቀኝ አይኑ ጠፍቶ የቀኝ እግሩ ላይም ጉዳት ደርሶበታል። ሆኖም በግራ አይኑ ያያል በ...
11/10/2024

የፈጣሪ ተአምር

ይህ ወጣት የሱማሌ ወታደር ነበረ። በቦንብ አደጋ የጭንቅላቱ ግማሽ አካል በዚህ መልኩ ሲጎዳ የቀኝ አይኑ ጠፍቶ የቀኝ እግሩ ላይም ጉዳት ደርሶበታል።

ሆኖም በግራ አይኑ ያያል በግራ ጆሮ ይሰማል መናገርም ይችላል። ይህ ታዓምር እንጂ ሌላ ምን ይባላል!

እናቴ ስለ ውትድርና ስናወራት "በጦርነት ይከሰራል እንጂ አይተረፍም" ትላለች።

እኛ አፍሪካዊያን የፈረንጅ የጦር መሳሪያ መሞከሪያ መሆን የምናበቃው መቼ ይሆን!!? ስንት ሰውስ ከጎናችን በሞት ስናጣ ፣ አካል ሲጎድል ፣ ሀገር ሲወድም ይሆን?

የአምላክ ተዓምር መቼ ተቆጥሮ ያልቃል!!

:- ታሪኩ ዘውዱ ከካናዳ 🇨🇦



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

በወር ወይንም በሁለት ወር አንዴ... በእረፍት ቀንህ... ቁምሳጥንህ ውስጥ ለአመታት ከተቀመጡ ልብሶች ውስጥ ንፁህና አዳዲሶቹን ይዘህ ውጣ።አንድ ድህነትና ችግር ያጎሳቆለውን ሰው ፈልግና ገላ...
10/10/2024

በወር ወይንም በሁለት ወር አንዴ... በእረፍት ቀንህ... ቁምሳጥንህ ውስጥ ለአመታት ከተቀመጡ ልብሶች ውስጥ ንፁህና አዳዲሶቹን ይዘህ ውጣ።

አንድ ድህነትና ችግር ያጎሳቆለውን ሰው ፈልግና ገላውን ታጥቦ ያመጣህለትን አዲስ ልብስ ለብሶ ፀጉሩን ተስተካክሎ ልክ ምስሉ ላይ እንዳለው ሰው እንዲቀየር አድርገው።

ከቻልክ ትንሽ ብር ሸጎጥ አርግለት ይበልጥ ከቻልክ ደግሞ ስራ እንዲያገኝ አግዘው ካልሆነም እንዲህ ስለቀየርከው እንኳን ሞራሉ ይነቃቃል አዲሱ ገፅታው ስራ ለማግኘትም ይረዳዋል።

ይህን ለማድረግ የሚያስፈልገው ብዙ አቅም ሳይሆን ሩህሩህ ልብ ብቻ ነው። በዚህ ምስል ላይ ያለውን ሰው ከሜዳ አንስተው ወደሚገርም የቀየሩት ሰወችም መልካም ልብ እንጂ ብዙ ብር ያላቸው አይደሉምና እናንተም ሞክሩት ደስታን ታገኙበታላችሁ።

:- Wasihune Tesfaye



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gize Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share