The Christian News - የክርስቲያን ዜና

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ቻናል ተዓማኒነት ያላቸው የክርስቲያን ዜናዎች እና መልዕክቶች ከመላው አለም ይደርሶታል። the Christian news በተጨማሪም 32ሺህ ቤተሰቦች በyoutube ስላሉን አዳዲስ የሆናቹ ቤተሰብ እንድትሆኑ እንጋብዛችኋለን።

01/06/2024

#ወንጌል አይታሰርም ... አልሰማንም እንዳትሉ

#ወደ #ዓለም #ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀ #ይድናል ያላመነ #ግን ይፈረድበታል። ስለሚል ቢያንስ የ #አንድ #ሰው ነብስ ከዘላለም ቅጣት በክርስቶስ #ኢየሱስ በኩል ይድን ዘንድ ባገኘውን አጋጣሚ #ሁሉ ከመናገር ወደ ኋላ አንልም።

አሁንም እንላለን አልሰማንም እንዳትሉ። ያመነ የተጠመቀ ይድናል። ያላመነ ግን ይፈረድበታል።

ከዘላለም ፍርድ ለማምለጠ የተሰጠንን #ውድ ሰጦታ እንድንቀበል ጥሪያችንን እናቀርባለን!!!

#ወንጌል #ለዓለም #ሁሉ

መንፈሳዊ ትምህርቶች #እና መልዕክቶችን ለመካፈል የቴሌግራም ገፁን ይቀላቀሉ 🙏🙏🙏 https://t.me/TCNEW

 #እናመሰግናለን 🙏🙏🙏 The Christian News - የክርስቲያን ዜና በYoutube ቻናላችን   ሺህ ቤተስቦች ደርሰናል።ታማኝ እና ፈጣን  #የክርስቲያን መረጃዎች ምንጭ አድርጋችሁ አብራ...
01/06/2024

#እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በYoutube ቻናላችን ሺህ ቤተስቦች ደርሰናል።

ታማኝ እና ፈጣን #የክርስቲያን መረጃዎች ምንጭ አድርጋችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።

በቀጣይ እጅግ በርካታ ስራዎች በጋራ እንደምንሰራ በማመን አሁንም አብሮነታችሁ ይቀጥል እንላለን።

በቅርብ ጊዜ ለምስጋና በድጋሜ እንደምንገናኝ እናምናለን።

https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A

የ  #ኤርትራ ባለሥልጣናት የወንጌል አማኞችን እያሰሩ መሆናቸው ተነገረ።የኤርትራ  #መንግሥት የፀጥታ ባለሥልጣናት በአገሪቱ ያሉ ወንጌላውያንን ከመኖሪያ ቤታቸው እየወሰዱ በማሰር ላይ መሆናቸው...
01/06/2024

የ #ኤርትራ ባለሥልጣናት የወንጌል አማኞችን እያሰሩ መሆናቸው ተነገረ።

የኤርትራ #መንግሥት የፀጥታ ባለሥልጣናት በአገሪቱ ያሉ ወንጌላውያንን ከመኖሪያ ቤታቸው እየወሰዱ በማሰር ላይ መሆናቸው ተነገረ።

በተለይ ባለፉት ሳምንታት በሰሜናዊ #ቀይ ባሕር፣ በአንሰባ #እና በጋሽ ባርካ ዞኖች #ውስጥ በርካታ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው መወሰዳቸው ቤተሰቦች እና የዕምነት መብት ተሟጋች ቡድን ገልጸዋል።

አዲሱ የእስር ዘመቻ በተለይ በዞኖቹ ምዕመናንን #ላይ #ብቻ ሳይሆን በአገልጋዮች ላይ ጭምር ያነጣጠረ ስለመሆኑ በቁጥጥር ስር ለሚገኙ ምዕመናን መብት የሚሟገተው ሪሊዝ ኤሪትሪያ የተባለው ቡድን ለቢቢሲ ገልጿል።

ባለፈው #ወር በተለይ በተሰነይ፣ በአቁርደት እና በባረንቱ ከተሞች በርካታ ወንጌላውያን በአገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።

በጋሽ ባርካ #ዞን ከታሰሩት መካከል ከ60 በላይ የሚሆኑት ቢንቢና ተብላ በምትጠራ #ከተማ በተከፈተ #አዲስ የማቆያ እስር #ቤት እንደሚገኙ የመብት ተቆርቋሪዎች ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲ-ተከለዛን፣ ከረን እና ጋህተላይ ከተሞች ጭምር ብዙ ምዕመናን እንደታሰሩም ተገልጿል።

በኤርትራ መንግሥት ዕውቅና ከተሰጣቸው እምነቶች ውጪ የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በእስር ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ወር በርካታ ሰዎች በእምነታቸው ምክንያት መታሰራቸው ለቢቢሲ ያረጋገጡት ‘ሪሊዝ ኤሪትሪያ’ የተባለውን የወንጌላውያን መብት ተሟጋች ድርጅት ዳይሬክተር፤ በአገሪቱ ያሉ መደበኛ ያልሆኑ እስር ቤቶች ብዛት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል።

የሪሊዝ ኤሪቲሪያ ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሃነ አስመለሽ ከሳምንታት በፊት ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ “የወንጌላውያን ሁኔታ ባለፉት 20 ዓመታት መሻሻል አላሳየም። ቀደም ሲል የታሰሩት መሪዎች አሁን 20 ዓመት ሞልቷቸዋል።”

“ማንም የተከሰሰ ወይም ሕጋዊ የክስ ሂደት ተከትሎ የታሰረ ሰው የለም” ብለዋል።

የኤርትራ ባለሥልጣናት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ስለሚያዟቸው ዜጎች ይፋዊ መግለጫም ሆነ መረጃ አይሰጡም። ብዙውን ጊዜ በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ አይፈቅዱም።

የተባበሩት መንግሥታት #ድርጅት ባለፈው የካቲት ወር ባደረገው ጥሪ የኤርትራ ባለሥልጣናት በሕገ ወጥ መንገድ ያሰሩዋቸውን በሙሉ እንዲፈቱ እና ያሉበት ቦታ እና የጤና ሁኔታቸው ላይ መረጃ እንዲሰጡ ጠይቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክትል ዋና ኃላፊ ኢልሴ ብራንድስ ኬህሪስ ባለፈው የካቲት ወር በጄኔቫ ስዊትዘርላንድ ባደረጉት ስብሰባ በኤርትራ “ሰቃይ እና ሕገ-ወጥ እስር” ቀጥሏል ብለዋል።

“በሺህ የሚቆጠሩ የሃይማኖት ቡድኖች መሪዎች እና አባላት፣ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች ከገደብ የለሹ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት አምልጠው ይሰደዳሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

የኤርትራ ባለሥልጣናት ግን ክሱን የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ “ፖለቲካዊ እና ኃላፊነት የጎደላቸው ውንጀላዎች” ሲሉ ያጣጥሉታል።

በአገሪቱ ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ የመንግሥት ፍቃድ የተሰጣቸው የእምነት ተቋማት እንኳ ከመንግሥት ጣልቃገብነት ነፃ አይደሉም።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኤርትራ ባለሥልጣናት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚተዳደሩትን የጤና እና የትምህርት ተቋማትን በመዝጋት ጳጳስን እስከ ማሰር ደርሰው ነበር።

የኤርትራ መንግሥት በአገሪቱ ትልቁ በሆነውና ብዙ አማኞች እንዳሉበት በሚነገረው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የውስጥ ጉዳዩ ጣልቃ በመግባት ፓትርያርኩን ከመሪነት በማንሳት ለዓመታት በቁም እስራት እንዲቆይ አድርጓል የሚል ክስ ይቀርብበታል።

በመሪዋ ሞት ምክንያት ፓትርያርክ አጥታ የቆየችው ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ወቅት በውጭ አገር በሚገኙ ተከታዮች ተከፋፍላለች።

ከነጻነት ጀምሮ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ መምህራን እና ሼሆች ታስረዋል፣ ከታሰሩትም በርካቶች ደብዛቸው ጠፍተዋል ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይገልጻሉ።

BBC News Amharic

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

በሥነ መለኮት ዙሪያ ውይይት ለማድረግ የተቋቋመው አለም ዓቀፉ የሉተራን-ኦርቶዶክስ የጋራ ኮምሽን 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጥንታዊ በሆነችው የግብጿ ካይሮ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፓትርያርክ ገዳ...
01/06/2024

በሥነ መለኮት ዙሪያ ውይይት ለማድረግ የተቋቋመው አለም ዓቀፉ የሉተራን-ኦርቶዶክስ የጋራ ኮምሽን 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጥንታዊ በሆነችው የግብጿ ካይሮ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፓትርያርክ ገዳም አካሂዷል።

የውይይቱም ተካፋዮች በሁለት የጋራ አቋም መግለጫዎች እና በመጪው ዓመት በሚከበረው የኒቅያ ጉባኤ 1,700ኛ ዓመት ክብረ በዓል ዝግጅት ዙሪያ በጋራ ሰርተዋል።

በእስክንድሪያው ፓትሪያሪክ አስተናጋጅነት በተዘጋጀው ስብሰባ ከኢትዮጲያ የወንጌላዊት ሉተራዊት ቤተክርስቲያን (የኢት/ወ/ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ)፣ ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል ተካፍለዋል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

አመታዊው የባለትዳሮች ቃል ኪዳን የማደስ ፕሮገራም ተደረጋ።የተቀባ  #የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክረስቲያን አመታዊ የባለትዳሮች ቃል ኪዳን የማደስ ቀንን አክብራለች ፡፡በዕለቱ በሦስትም...
30/05/2024

አመታዊው የባለትዳሮች ቃል ኪዳን የማደስ ፕሮገራም ተደረጋ።

የተቀባ #የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክረስቲያን አመታዊ የባለትዳሮች ቃል ኪዳን የማደስ ቀንን አክብራለች ፡፡

በዕለቱ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም መክ፤4-12 በሚል ቃል ባለትዳሮች የጋብቻ ቃልኪዳናቸውን እንዲያጠብቁ አፅኖኦት በመስጠት የእግዚያብሔርን ቃል ታምረዋል፡፡

#ይህ ፕሮገራም ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን ባለትዳሮች በአንድት እግዚያብሄርን ያመለኩባት፣ስላለፋው ድካማቸው ንስሃ የገቡበት፤ እና ስለ ባላቸውና ሚሰታቸው መልካምነት የተደናነቁበት #ድንቅ ምሽት ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ አገልጋዮች በጋብቻ ውሰጥ በአንድነት ስለመገመድ፣ ስለ ጋብቻ እና ቤተክርሰቲያን እነዲሁም ጋብቻችን በማህበረሰቡ ውሰጥ ስላሚኖርው ሚና ትምህርተ ተሰጥትዋል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

27/05/2024

የ #ኢየሱስ ፊልም በምልክት #ቋንቋ ተሰራ።

መስማት የተሳናቸውን ሰዎች ለማገልገል የተቋቋመው መስማት የተሳናቸው የወንጌል አገልግሎት፣ በአሜሪካ የምልክት ቋንቋ (ASL) የተዘጋጀውን ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ ሊያቀርብ እንደሆነ ተሰማ።

ሰኔ 20/2024 ይለቀቃል የተባለው #ይህ #ፊልም በጆሴፍ ዲ ጆሴሊን ዳይሬክተርነት እንዲሁም በጌዲዮን ፊርል ዋና ተዋናይነት የተሰራ ሲሆን ሁለቱም መስማት የተሳናቸው ናቸው።

"በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ እንደማደጌ ስለ ኢየሱስ ብዙ ፊልሞችን እመለከት ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ ፊልሞች በምልክት ቋንቋ ቢሆንስ ብዬ ሁልጊዜም አስብ ነበር,?" በማለት የፊልሙ ዳይሬክተር ጆሴሊን ለክርስቲያን ፖስት በአስተርጓሚ ተናግሯል።

"እ.ኤ.አ. በ 2006 መስማት የተሳነው የሚሲዮን አገልግሎትን ከተቀላቀልኩ በኋላ ሀሳቡ ቅርፅ መያዝ ጀመረ ፣ ምንም #እንኳን በወቅቱ ይህንን ለመስራት የሚፈለገው የቴክኖሎጂ እና የገንዘብ መጠን በጣም ከባድ ይመስል ነበር በማለት ተናግሯል ።"በመጀመሪያም የኢዮብ መጽሐፍ ላይ ተመስረተን ፊልም ሰራን ፤ ይህም የምንፈልገውን ልምድ ሰጠን።

ይህም ልምድ የ 'ኢየሱስ' ፊልም ትልቅ ፕሮጀክት ለመቀጠል እንደተዘጋጀን እንዲሰማን አድርጓል" ሲል አክሏል። “መስማት የተሳናቸው አግልግሎት የተሰራው የኢየሱስ ፊልም በሮማውያን የይሁዳ አገዛዝ ሥር ከፍተኛ ውጥረት በነገሠበት ዘመን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ፣ ተአምራቱን፣ ኃይሉንና በወቅቱ ለነበሩት የሃይማኖት መሪዎች ጋር ያደረጋቸውን ፈታኝ ሁኔታዎች ጨምሮ በኢየሱስ ክርስቶስ በአገልግሎቱ ያሳለፋቸውንና ያከናወናቸውን ቁልፍ ጊዜያትና ተግባራት ፊለሙ ጎላ አድርጎ ያሳያል ተብሏል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

ተለቀቀ የዝሙት ሕይወቴን ማንም አያወቅም ነበር ሰዎች መማር ካለባቸው ከእኔ ይማሩ  #ድንቅ  #ምስክርነት ከዚህ ልምምድ መውጣት ሲያቅተኝ ከጌታ ቤት ባክ አደረኩኝ https://youtu.be/...
25/05/2024

ተለቀቀ

የዝሙት ሕይወቴን ማንም አያወቅም ነበር ሰዎች መማር ካለባቸው ከእኔ ይማሩ #ድንቅ #ምስክርነት ከዚህ ልምምድ መውጣት ሲያቅተኝ ከጌታ ቤት ባክ አደረኩኝ

https://youtu.be/ugkLCiXAYII

25/05/2024

#ሰዎች መማር ካለባቸው ከእኔ ይማሩ #እኔ አገልጋይ ነኝ ግን አልቻልኩም #ድንቅ #ምስክርነት ከዚህ ልምምድ መውጣት ሲያቅተኝ ከጌታ ቤት ባክ አደረኩኝ #ምሽት ላይ በዩቲዩብ ቻናላችን ይጠብቁን!!!

ተለቀቀ የዝሙት ሕይወቴን ማንም አያወቅም ነበር ሰዎች መማር ካለባቸው ከእኔ ይማሩ #ድንቅ #ምስክርነት ከዚህ ልምምድ መውጣት ሲያቅተኝ ከጌታ ቤት ባክ አደረኩኝ https://youtu.be/ugkLCiXAYII

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

24/05/2024

የማይቀርበት #ቀጠሮ #ወደ #ቤተ #ምህረት

በዚህች አጥቢያ አተኩረን የምንሰራዉ ተተኪ ትዉልድ #ላይ ነዉ። ዘማሪ #እና መጋቢ እንዳለወልደ ጊዮርጊስ

የቤተ ክርስቲያን ተከላና- የመክፈቻ ፕሮግራም ከግንቦት 21-25 / ከእሮብ እስከ ቅዳሜ ከ 10:00 ጀምሮ እሁድ ጠዋት ይከናወናል።

አድራሻ፦ ከቡልጋሪያ ወደ ቄራ ሲወርዱ ስካኒያ አካባቢ የቤተ ምህረት ማስታወቂያ ባለበት 100 ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል።

ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካሎት Comment
በፍጥነት ለወዳጆ ለማካፈል ያድረጉ

ተዓማኒነት እና ፈጣን የሆኑ መረጃዎች እንዲደርሶት በቴሌግራም የክርስቲያን ዜና ቤተሰብ ይሁኑ።

https://t.me/TCNEW

ማህበራዊ ሚዲያዎችን ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊ መልዕክቶችን በሚያስተላልፉት ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ።  #የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ...
24/05/2024

ማህበራዊ ሚዲያዎችን ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊ መልዕክቶችን በሚያስተላልፉት ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ።

#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

በጉባኤዉ የካዉንስሉ አባል ቤተ እምነቶች እና ከፍተኛ የአብያተክርስቲያናት መሪዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤው የካዉንስሉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዉ ጉባኤዉን አስጀምረዋል።

በጉባኤዉ የሰላም ሚንስቴር ተወካይ ዶ/ር አወቀ አጥናፋ መልእክት ያስተላለፋ ሲሆን በመልእክታቸዉም የወንጌል አማኞች ሰላምን ጠንቅቃችሁ ታዉቃላችሁ ከዚህ በበለጠ ለሰላም ስሩ ሲሉ ተናግረዋል። እንዲሁም የመፅሃፍ ቅዱስ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ይልማ ጌታሁን ለጉባኤዉ ሰላምታ አቅርበዋል።

በእለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ከአገር ውስጥና ከመላው አለም ስብሰባውን የተካፈሉና ለጠቅላላ ጉባኤው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በአባላት መካከል ሊኖር ስለሚገባ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ፍቅር የእግዚአብሔር ቃል መልዕክትም ቀርቧል።

ጠቅላላ ጉባኤው በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች አጀንዳ አድርጎ ከመወያየት ባሻገር ያለፈውን አመት የስራ ክንውን ሪፖርት እና የቀጣይ አመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት የጸደቀ ሲሆን በካውንስሉ አባላት መካከል ተከስቶ የነበረውን ክፍተት በውይይት እንዲፈታ ላደረጉ መሪዎችም ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷል ።

በቀረበዉ እቅድ ከጉባኤዉ ለተነሱ ጥያቄዎች የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰተዋል። የአስተምህሮና የልምምድ ችግር ባለባቸው አራት ተቋማትና የተቋማቱ መሪዎች ላይም እግድ ተደርጓል።

በቀጣይም ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊ መልዕክቶችን በሚያስተላልፉና ሆን ብለው የወንጌል አማኞችን ገጽታ በሚያጠፉ ግለሰቦች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር አስተማሪ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን የካውንስሉ ጽ/ቤት የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን አግባብነት ባላቸው መመሪያዎች መሰረት እያከናወነ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በመጨረሻም የካዉንስሉ ፅ/ቤ ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ ቃለ ጉባኤ አቅርበዉ የቀረበዉ ቃለ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ ፀድቆ ጉባኤዉ በፀሎት ተጠናቋል።

ዘገባው Evangelical MEDIA/Council ነው።

ዜናውን ከወደዱት Like
ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካሎት Comment
በፍጥነት ለወዳጆ ለማካፈል ያድረጉ
ተዓማኒነት እና ፈጣን የሆኑ መረጃዎች እንዲደርሶት በቴሌግራም የክርስቲያን ዜና ቤተሰብ ይሁኑ።
https://t.me/TCNEW

 #ይፈቱ በኤርትራ ከ 20 አመታት በላይ የታሰሩ የፕሮቴስታንት እምነት ፓስተሮች እንዲፈቱ አሜሪካ ጠየቀች።የአሜሪካው ዓለማቀፍ የኃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን፣ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ...
24/05/2024

#ይፈቱ

በኤርትራ ከ 20 አመታት በላይ የታሰሩ የፕሮቴስታንት እምነት ፓስተሮች እንዲፈቱ አሜሪካ ጠየቀች።

የአሜሪካው ዓለማቀፍ የኃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን፣ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኤርትራ ላለው የኃይማኖት ነጻነት ጥሰት ትልቅ ትኩረት እንዲሰጥ መጠየቁ ዳጉ ጆርናል ከዘገባዎች ተመልክቷል።

ኮሚሽኑ፣ ፓስተር ኃይሌ ናይዝጊ እና ፓስተር ክፍሉ ገብረመስቀል የተባሉ የፕሮቴስታንት ኃይማኖት ሰባኪዎች ከታሠሩ ከ20 ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል ሲል ለአብነት ጠቅሷል።

#ኤርትራ ፣ ከኃይማኖት ነጻነት ጋር በተያያዘ 5 መቶ ያህል ሰዎችን ክስ ሳይመሠረትባቸው እንዳሠረች ኮሚሽኑ አመልክቷል።

የኤርትራ መንግሥት ባለፈው ዓመት ከኃይማኖት ጋር በተያያዘ የታሠሩ ዘጠኝ እስረኞችን #ብቻ መፍታቱን ያስታወሰው ኮሚሽኑ፣ ጅምሩ #ግን ሳይቀጥል ቀርቷል በማለት ወቅሷል። ሲል ዋዜማ ሬድዬ ዘግቧል።

ዜናውን ከወደዱት Like
ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካሎት Comment
በፍጥነት ለወዳጆ ለማካፈል ያድረጉ

ተዓማኒነት እና ፈጣን የሆኑ መረጃዎች እንዲደርሶት በቴሌግራም የክርስቲያን ዜና ቤተሰብ ይሁኑ።

https://t.me/TCNEW

 #መቀሌ  #ታላቁ ተልዕኮ ኢትዮጵያ 10ኛ ቢሮውን በትግራይ መቀሌ ከፈተ።ግሬት ኮሚሽን ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ  #በኢትዮጵያ የወንጌል ስራን ሲሰራ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት በአዳማ፣ ባህርዳር፣...
23/05/2024

#መቀሌ

#ታላቁ ተልዕኮ ኢትዮጵያ 10ኛ ቢሮውን በትግራይ መቀሌ ከፈተ።

ግሬት ኮሚሽን ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ #በኢትዮጵያ የወንጌል ስራን ሲሰራ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት በአዳማ፣ ባህርዳር፣ ሃረር፣ ሃዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምቴ፣ አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕና እና አምቦ የአካባቢ ቢሮዎችን አቋቁሞ በየአካባቢው ከሚገኙ ሚኒስትሪዎችና አብያተ ክርስቲያናት ጋር ወንጌልን እየሰራ ይገኛል።

ግሬት ኮሚሽን #ኢትዮጵያ ሚኒስትሪ፣ የጂሰስ ፊልምን በ74 የሃገር ውስጥ ቋንቋዎች በማስተርጎምና በ10 ሃገራት ውስጥ ኢንዲጂተስ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ማህበረሰብን በመፍጠር በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጪም ወንጌልን እየሰራ ይገኛል።

ከጦርነት መልስ የወንጌል ስርጭት ማዕከል በትግራይ የተከፈተውን ይሄንን ቢሮ ያስተባበረው ወንድም ሲሆን በመድረኩ እውቅና ተሰጥቶታል።

ወንድም ካሳሁን መቀሌ እና መላውን ትግራይ ላለፉት 10 ዓመታት በወንጌል ለመድረስ ሲያገለግል ቆይቷል።

ምንጭ፣ GCMEthiopia

ዜናውን ከወደዱት Like
ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካሎት Comment
በፍጥነት ለወዳጆ ለማካፈል ያድረጉ

ተዓማኒነት እና ፈጣን የሆኑ መረጃዎች እንዲደርሶት በቴሌግራም የክርስቲያን ዜና ቤተሰብ ይሁኑ።

https://t.me/TCNEW

 #አዲስ  #ዜና የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለመንግሥት እንዲያቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር...
22/05/2024

#አዲስ #ዜና

የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለመንግሥት እንዲያቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡

" የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጅ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውንም ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

የሃይማኖት ተቋማቱ የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን እንደሚኖርበትና የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን እንዳለባቸውም ይገልጻል።

አንድ የሃይማኖት ተቋም በራሱ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ፣ ለዚሁ ሥራ የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ እንዳለበትም ተደንግጓል፡፡

በተጨማሪም ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ ይኖርበታል ተብሏል።

በተጨማሪም የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስምና አድራሻ፣ የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነትና መጠን፣ እንዲሁም ስጦታው ወይም ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ የሃይማኖት ተቋማቱ ጨምርው ማሳወቅ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባን Ethio tube እንዳጋራዉ

" #የአፍሪካ  #መንፈሳዊ ቀን" በአፍሪካ ሕብረት ተካሄደ።በInter religious Association for Peace And Development (IAPD Africa) አዘጋጅነት  "Educa...
22/05/2024

" #የአፍሪካ #መንፈሳዊ ቀን" በአፍሪካ ሕብረት ተካሄደ።

በInter religious Association for Peace And Development (IAPD Africa) አዘጋጅነት "Educating the African person to be Spiritually fit in the 21st Century" በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ መሪዎች በተገኙበት በአፍሪካ ሕብረት ተከናውኗል።

የሃይማኖት ተቋማት እና መሪዎች በሰላም እና በልማት ስራዎች ላይ በቅንጅት ለአፍሪካ መስራት እንደሚገባቸው በመድረኩ ተጠቅሷል።

በመድረኩ የInter religious Association for Peace And Development (IAPD Africa) የአፍሪካ ሊቀመንበር ዶ/ር ኡዙዊን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እና የእስልምና እምነት በሀገራችን የትምህርት ስረዓት ያበረከቱትን አስተዋጽዖ በተመለከተ የተለያዩ ጽሑፎች ቀርበዋል።

በጉባኤው በቅርብ ጊዜ የምስረታ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን ያከበሩት አንጋፋዎቹ የመሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ (ቢጫ ኳይር) ዝማሬ አቅርበዋል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

 #ቤተ  #በአዲስ አበባበሆሳዕና ለረጅም አመት እያገለገለች የምትገኘዉ ቤተምህረት  #አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ የቤተ ክርስቲያን ተከላና- የመክፈቻ ፕሮግራም ከግንቦት 21-25 / ከእሮብ እ...
20/05/2024

#ቤተ #በአዲስ አበባ

በሆሳዕና ለረጅም አመት እያገለገለች የምትገኘዉ ቤተምህረት #አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ የቤተ ክርስቲያን ተከላና- የመክፈቻ ፕሮግራም ከግንቦት 21-25 / ከእሮብ እስከ ቅዳሜ ከ 10:00 ጀምሮ እሁድ ጠዋት ይከናወናል።

#አድራሻ ፦ ከቡልጋሪያ #ወደ ቄራ ሲወርዱ ስካኒያ አካባቢ የቤተ ምህረት ማስታወቂያ ባለበት 100 ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል።

#ቤተ ምህረት እንገናኝ 🙏🙏

 #የአርሰናል ደጋፊዎች በቤተክርስቲያን ምስጋና አቀረቡ።በኬንያ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ከድል በኋላ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ምስጋና አቀረቡበኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ የሚገኙት የአርሰናል ...
20/05/2024

#የአርሰናል ደጋፊዎች በቤተክርስቲያን ምስጋና አቀረቡ።

በኬንያ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ከድል በኋላ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ምስጋና አቀረቡ

በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ የሚገኙት የአርሰናል ደጋፊዎች ቅዳሜ እለት ባደረጉት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቡድናቸው ክሪስታል ፓላስን 5 ለ 0 በመርታቱ አድናቆትን ከማትረፍ ባለፈ በአንድ አጥቢያ ቤተክርስትያን በመሰባሰብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ደጋፊዎቹ የመድፈኞቹን ማሊያ ለብሰው በእሁድ ጠዋት አገልግሎት ላይ ቡድናቸው ላሳየው አስደናቂ ብቃት በደስታ ውዳሴ እና ምስጋና አቅርበዋል።በመጪው የውድድር ዘመን ለአርሰናል ቀጣይ ስኬት ተስፋ በማድረግ ጸሎት አቅርበዋል።

ከታዳሚዎቹ መካከል ጋዜጠኛ ኬኔዲ ሙሪቲ በፀሎት ስነ ስርዓቱ ላይ የተነሱትን ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራቱን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።የሰሜን ለንደኑ አርሰናል አንድ ጨዋታ ከሚቀረው ማንቸስተር ሲቲ እኩል እና ከሊቨርፑል በአምስት ነጥብ ዝቅ ብሎ ተቀምጧል።

ፎቶዎቹ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን የፈጠሩ ሲሆን አንዳንዶቹ በደጋፊዎች ላይ አፌዜዋለሁ፡፡

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

 #በሃኪም እገዛ ራስን ማጥፋት  #እና  #ቤተክርስቲያን የስኮትላንድ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ Assisted Su***de  #ወይም በእገዛ ራስን ማጥፋትን እየተቃወሙ ይገኛሉ።ይሄንን ያው...
14/05/2024

#በሃኪም እገዛ ራስን ማጥፋት #እና #ቤተክርስቲያን

የስኮትላንድ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ Assisted Su***de #ወይም በእገዛ ራስን ማጥፋትን እየተቃወሙ ይገኛሉ።

ይሄንን ያውቁ ነበረ። በአለማችን 15 ሃገራት በሃኪም የታገዘ ራስን ማጥፋት ይፈቅዳሉ። Assisted Su***de ወይም በሃኪም የታገዘ ራስን ማጥፋት ማለት፣ #አንድ #ሰው ራሱን ሲያጠፋ በሃኪም እገዛ ህጋዊ በሆነ መንገድ የህይወት ጉዞውን ማብቃት ማለት ነው።

የስኮትላንድ አብያተ ክርስቲያናት ይሄንኑ ድርጊት በሃገሪቱ ህጋዊ እንዲሆን መጠየቁን ተከትሎ ነው ድምጻቸውን ያሰሙት።

ለ129 የምክር ቤት አባላት በተላከው ደብዳቤ መሰረት፣ በአንድ የምክር ቤቱ አባል የቀረበውን ይሄንኑ አጸያፊ ተግባር ህጋዊ እንዳይደረግ ጠይቀዋል።

በደብዳቤያቸው፣ ይሄ ህግ የሰው ልጅን ሞራላዊነት አሽቀንጥሮ መጣል ነው፣ እንደ ሃገር አለን የምንለውን የሰው ልጆች ዋጋ የሚያሳጣን ነው ብለዋል።

ህጉ የሚጸድቅ ከሆነ ስኮትላንድ ስነምግባር የሌለባት፣ ምክር ቤታችንም ለሰው ልጆች ዋጋ የሌለው አዳራሽ መሆኑ ነው ሲሉ አሳስበዋል።

በእገዛ ራስን ማጥፋት ማለት የሰው ልጅ ህይወት ዋጋ የሌለው መሆኑን ማሳያ ነው። ዘፍጥረት ላይ #እግዚአብሔር በአምሳያው የሰውን ልጆች መፍጠሩ፣ ሁሉም የሰው #ልጆች በእግዚአብሔር እንደሚወደድ ማሳያ ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ ህይወት ዋጋ አለው ብለዋል።

ይሄንን ደብዳቤ የላኩት ቄስ አንድሪው ዶውኒ እና ቄስ ቦብ አክሮይድ የዩናይትድ ፍሪ ቸርች ኦፍ ስኮትላንድ አገልጋዮች ናቸው።

ሃገራችን ስኮትላንድ ሰዎች ራሳቸውን ማጥፋት የማያስቡባት መሆን አለባት ብለዋል። ምናልባት በመሰል ስሜት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ማህበረሰባችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቅርና እንክብካቤ ማሳየት አለበት ብለዋል።

ስኮትላንድ የ1517ቱ ተሃድሶ እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ያገዙት ጆን ኖክስ ትውልድ ሃገር መሆኗ ይታወሳል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

የአፍሪካ ወንጌላዊያን ማህበር በአዲስ አበባ ስብሰባውን አካሄደ።ማህበሩ ባካሄደው ስብሰባው የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ተጽኖ የሚያደርሱ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል። በስብሰባው ከአፍሪካ ...
14/05/2024

የአፍሪካ ወንጌላዊያን ማህበር በአዲስ አበባ ስብሰባውን አካሄደ።

ማህበሩ ባካሄደው ስብሰባው የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ተጽኖ የሚያደርሱ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል።

በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት፣ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ማህበሩ በአፍሪካ የሚገኙ ከ250 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናትን ያቀፈ ነው።

በስብሰባው የአፍሪካ ህብረት በ2063 ሊያሳካ ካቀዳቸው ግቦች መካከል ጤናማ ዜጋ መፍጠር እና ተሸጋጋሪ ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ማድረግን እንደሚያግዝ በመድረኩ ተነስቷል።

አፍሪካን የበለጸገችና ሰላማዊ ለማድረግ እንደሚሰራም የአፍሪካ ወንጌላዊያን ማህበር ገልጿል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

 #እንኳን  #ደስ አለህ  #ወጣቱ ወንድማገኝ የመላዉ አፍሪካ አብያተክርስቲያናት ጉባኤ የጠቅላላ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጧል። የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ የልጆች እና ወ...
13/05/2024

#እንኳን #ደስ አለህ

#ወጣቱ ወንድማገኝ የመላዉ አፍሪካ አብያተክርስቲያናት ጉባኤ የጠቅላላ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጧል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ
ናይጄሪያ አቡጃ እየተካሄደ በሚገኘዉ በ12ኛው የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ወጣቶችን በመወከል የጠቅላላ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጧል::

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የተሰማንን ደስታ እየገለፅን #መልካም የአገልግሎት #ጊዜ እንዲሆንልህ እንመኛለን። Wondmagegn Udessa Bidire 🙏🙏🙏

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

 #ኑ አብረን እናመስንግን  #እግዚአብሔር ድል ሰጥቶናልና  #50 የድል ዓመታትየመሠረተ ክርስቶስ  #ቤተክርስቲያን የመዘምራን ቡድን "ቢጫ ለባሾቹ" የምስረታ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል በድምቀ...
11/05/2024

#ኑ አብረን እናመስንግን #እግዚአብሔር ድል ሰጥቶናልና #50 የድል ዓመታት

የመሠረተ ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን የመዘምራን ቡድን "ቢጫ ለባሾቹ" የምስረታ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል በድምቀት እያከበሩ ነው።

በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እየተከናወነ በሚገኘው የምስጋና ፕሮግራም የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።

የመዘምራን ኳየሩ ዝማሬዎቹን ለእግዚአብሔር ክብር ፤ ለህዝቡም በረከት እንዲያቀርብ ከተመሠረተበት ከ1966ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱ ውስጥ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያዎች ፤ በባህር ማዶ በየኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አጥቢያዎች ሲያገለግሉ እንደቆዩ መድርረኩ ተጠቅሷል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለዘጋባ በስፍራው በመገኘት እየተከታተለን ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

"...  #ማን ያውራ ? የነበረ ...."የባሊ አቦው  #ልጅ ወደ ጌታ  #ሄዱ 😥😥..የሐረር መምህራን ማሰልጠኛ ተማሪው የመጀመሪያ የጰንጠቆስጠ ቤተ ክርስቲያን አጀማመር በኢትዮጵያ ከፍተኛ አ...
10/05/2024

"... #ማን ያውራ ? የነበረ ...."
የባሊ አቦው #ልጅ ወደ ጌታ #ሄዱ 😥😥..
የሐረር መምህራን ማሰልጠኛ ተማሪው

የመጀመሪያ የጰንጠቆስጠ ቤተ ክርስቲያን አጀማመር በኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ የሙሉ #ወንጌል ቤተክርስቲያን ምስረታ ውስጥ የነበሩ ባህር ተሻግረው ቤተክርስቲያን በመትከል እና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ላይ በትጋት የሰሩ የኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ከ60 ዓመት በላይ በማገልገል ባለውለታ የሆኑት ፓስተር ዶክተር ዘለቀ አለሙ ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል።

በትዳር ከ46 ዓመታት በላይ ተሻግረዋል በምዕራቡ አለም ያላቸው ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ሊገዙ እየተሰናዱ እና "ግሬስ" በተሰኘ ሴንተር የሰው ልጆች በሙሉ በክርስቶስ የተደረገልን ምንድነው የሚለውን እንዲረዱ ለመስራት እና ለመስበክ እና ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እቅድ እንደነበራቸው በአንድው ወቅት The Christian News - የክርስቲያን ዜና ጋር #የክርስቲያን እንግዳ ሆነው ድንቅ ቆይታ ባደረግንበት ጊዜ አጫውተውን ነበር።

በተለይ በወጣቱ እና በአንጋፋዎች መካከል ያለውን የትውልድ ክፍተት ለመድፈን ቤተክርስቲያን ደቀ መዝሙር የማድረግ ስራ ላይ ትኩረት አድርጋ ሰርታ ተተኪ ትውልድ የማስነሳት ስራ ልትሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸው አስተላልፈዋ ነበር።

"... ማን ያውራ ? የነበረ ..." እንዲሉ የኢትዮጵያ ጰንጠቆስጤአዊ እንቅስቃሴ አጀማመር መተረክ ከሚችሉት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ መጋቢ ዘለቀ አለሙ (ዶ/ር) ነው።

"ሕይወቴ እና ጰንጠቆስጤአዊ እንቅስቃሴ አጀማመር በኢትዮጵያ" በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ቀድመው አስተያየት ከሰጡ ሰዎች መካከል መጋቢ በቀለ ወልደ ኪዳን አስተያየታቸው ሰጥተዋ ነበር።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና እጅግ ለተወደዱት የቤተክርስቲያን አባት ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸን ወዳገለገሉት #ጌታ በመሄዳቸው እንጽናናለን።

ለቤተሰቦቻቸው በሙሉ መጽናናትን እየተመኘን አዝናኝ እና አስተማሪ የአገልግሎት ጊዜያቸውን በተመለከተ በቻናላችን ከ2 ዓመት በፊት ያደረግንላቸውን ቃለ መጠይቅ ሊንኩን በመጫን እንድትመለከቱ ግንዣችን ነው።

https://youtu.be/1FHp-jLOZJI?si=Fn1MqoGRvgaFq30H

 #ታላቁ  #የወንጌል አርበኛ  #ወደ  #ጌታ ተሰበሰቡ 😥መጋቢ ሰለሞን ጂኖሎ የሻሸመኔ አጥቢያ የሕይወት ብርሃን  #ቤተክርስቲያን መሪ መጋቢ ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል።በወንጌል ላልተደረሱ ...
09/05/2024

#ታላቁ #የወንጌል አርበኛ #ወደ #ጌታ ተሰበሰቡ 😥

መጋቢ ሰለሞን ጂኖሎ የሻሸመኔ አጥቢያ የሕይወት ብርሃን #ቤተክርስቲያን መሪ መጋቢ ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል።

በወንጌል ላልተደረሱ አካባቢዎች ወንጌል የማድረስ ሸክም ሲሰሩ ቆይተዋል።

በእንዲህ ሁኔታ በመሰጠት የሚያገለግሉ አባት ማጣት እጅግ ልብን የሚሰብር ዜና ቢሆንም ወዳገለገለው ጌታ ተሰብስቦአልና እንጽናናለን።

መጋቢ ሰለሞም #የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ዋና ጸሐፊ በመሆንም ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል።

የቀድሞ የስራ ባልደረቦቹ እና አብረዉት ያገለገሉ መሪዎች የተሰማቸዉን ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸዉ መፅናናትን ተመኝተዋል።

ጌታ ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንዲሰጥ The Christian News - የክርስቲያን ዜና እንመኛለን።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

 #ጅማ ክርስቲያንበጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖ ካምፓስ የቀድሞ  የ #ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት (ኪቶ ፋሚሉ) አባል የነበሩ ተማሪዎች መልካም ግንኙነት ሊያስቀጥል የሚችል ክርስቲያን ኔትወርኪንግ ...
07/05/2024

#ጅማ ክርስቲያን

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖ ካምፓስ የቀድሞ የ #ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት (ኪቶ ፋሚሉ) አባል የነበሩ ተማሪዎች መልካም ግንኙነት ሊያስቀጥል የሚችል ክርስቲያን ኔትወርኪንግ ኢቨንት ተካሄደ።

#ይህ ለሁለተኛ #ጊዜ የተዘጋጀው ፕሮግራም በዋናነት ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ወጥተው በተለያዩ የግል የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ተማሪዎችን ግንኙነት ማስቀጠል #እና የተሰማሩበትን የቢዝነስ ዘርፍ አስተዋውቀው #መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪ ወንድም አቤኔዜር ማቴዎስ ለክርስቲያን ዜና ተናግሯል።

አቤኒዘር አክሎ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ ግንኙነቱ ሲቀጥል አይታይም ይህን ክፍተት ለመቀነስ ያሰበ መልካም ግንኙነት እንደሆነ ተናግሯል።

ይህ ሕብረት በቀጣይ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ውጪ የሚገኙ ሕብረትን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ወጣት አቤኔዜር አክሎ ለክርስቲያን ዜና ተናግሯል።

ክርስቲያን #ዜና ያናገራቸው በፕሮግራሙ #ላይ የሚሰሩትን የተለያዩ ስራዎችን ይዘው የቀረቡ የቀድሞ ተማሪዎች ይህ የህብረት ፕሮግራም ከሌሎች ጋር የመተዋወቅን እና የቢዝነስ ስራ በጋራ ለማሳደግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ነግረውናል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዘገባውን አዘጋጀን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በክርስቲያን ዜና የዮቲዩብ ቻናል ይዘን እንመለሳለን።

የመሠረተ  #ክርስቶስ  #ቤተክርስቲያን  #ለ389 ወገኖች ማዕድ አጋራች። በመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን  #በኮተቤ አጥቢያ አስተባባሪነት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአከባቢው የ...
06/05/2024

የመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን #ለ389 ወገኖች ማዕድ አጋራች።

በመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን #በኮተቤ አጥቢያ አስተባባሪነት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአከባቢው የሚገኙ አቅመ ደካሞች የሆኑ ወገኖችን ከአከባቢው የወረዳ አስተዳደር ተመልምሎ ለተሰጣቸውን 389 ወገኖችን ዛሬ የምሳ ግብዣ ተደርጓል።

በማዕድ ማጋራት ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት ፓስተር ደሣለኝ አበበ #የሐገር ዕድገት መለኪያው በብዙ ድሆች መካከል በተገኙ ጥቂት ባለሃብቶች ሳይሆን በዜጎች መሠረታዊ ፍላጎት መሟላት ነው ብለዋል።

ስለሆነም ቤተክርስቲያን እንደዚህ ዓይነት ተግባራትን ለማድረግ በዓላትን ሣትጠብቅ የዘወትር ተግባሯ እንዲታደርግ ብሔራዊ ሥርዓት ተበጅቷል ካሉ በኃላ የኮተቤ አጥቢያ ላደረገችው ግንባር ቀደም ተግባር ምስጋና አቅርቧል።

የኮተቤ አጥቢያ ካለፈው ሰኔ 2015 ዓም ጀምሮ " " በሚል መረሃ ግብር #እሁድ ለአምልኮ የሚመጣ ማንኛውም አባል ለምግብ የሚሆን ይዞ እንዲመጣ በማድረግ በሣምንት 5ቀናት 200 ሰዎችን በመመገብ ላይ ትገኛለች።

#ወደ ፊት ሌሎች በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቸገሩ ወገኖችን ለመድረስ አቅም የፈቀደው #ሁሉ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

 #አስደሳች  #ዜና የቦሌ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ለ500 አረጋውያን የበዓል ቅርጫ አከፋፈሉ።የ2016ዓ.ም የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ ላለፉት 11 ዓመታት ሲከነውን ...
06/05/2024

#አስደሳች #ዜና

የቦሌ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ለ500 አረጋውያን የበዓል ቅርጫ አከፋፈሉ።

የ2016ዓ.ም የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ ላለፉት 11 ዓመታት ሲከነውን እንደነብረው የአረጋዊያን ቅርጫ ሥጋ ክፍፍልን በዛሬው ዕለት አከናውናለች።

ለዚህም ተግባር በቤተክርስቲያንቱና በተለያዩ ሀገራት ያሉትን አጋሮቸዋን በማስተባበር ለአረጋዊያን ቅርጫ ሥጋ 26 በሬ እንዲሁም ለጎዳና ተዳዳሪዎች ምሳ ግብዣ ለወጥ 1 በሬ በጠቅላላ 27 በሬ ከአቃቂ ገበያ ተገዝቶ ቄራ ድርጅት በማሳረድ ከቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ለተወጣጡ 530 ለሚሆኑ አረጋዊያን የቅርጫ ሥጋ ክፍፍል ተደርጓል።

በመረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙባረክ ከማል በጎነት አብሮነት እና ወንድማማችነትን ያጠናከረ እና በክ/ከተማው ባህል እየሆነ የመጣ ነው ብለዋል።

የአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት መጋቢ ጌታሁን ታደሰ የትንሳኤ በዓል የክርስቶስ መታሰቢያ እንደመሆኑ ከምግብ ባለፈ የክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ለምን እንደሆነ ማሰብ ይጠይቃል ያሉ ሲሆን በዚህ ሰዓት ሌሎች እየበሉ አቅመ ደካማ አረጋውያን ሳይበሉ መመልከት ተገቢ አይደለም ስለዚህ አረጋውያንን የምናግዝበት ሃይማኖታዊ ግዴታችን ነው ብለዋል።

የቦሌ አማኑኤል ሕብረት ቤተክርስቲያን ላለፉት 11 ዓመታት ይህንን በጎ ተግባር ስታከናውን የቆየች እንደሆነች የጠቀሱት የቤተክርስቲያኒቱ ዋና መሪ መጋቢ አመሉ ጌታ በዚህ ታላቅ በጎ ተግባር በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው፣ በማስተባበር በሁሉም መንገድ የተሳተፉትን አመስግነዋል።

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

የትንሳዔ በዓልን የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በድሬዳዋ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም በተለያየ የአምልኮ ስርዓት አከበሩ። በዛሬው የትንሳዔ በአል በድሬዳዋ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም...
05/05/2024

የትንሳዔ በዓልን የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በድሬዳዋ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም በተለያየ የአምልኮ ስርዓት አከበሩ።

በዛሬው የትንሳዔ በአል በድሬዳዋ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም ሲከበር የድሬዳዋ አስተዳደር #ከንቲባ ክቡር ከዲር ጁሀርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ በርካታ የወንጌላዉያን ዕምነት ተከታዮችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በተዘጋጀው የትንሳኤ በዓል አከባበር ላይ የክብር እንግዳ የነበሩት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሀር በዓሉን ስናከብር ትላንት የነበሩ ዛሬ ያልነበሩ ወገኖቻችን ቤተ ዘመዶችን ከጎናቸው በመቆምና የተቸገሩትን ደግሞ በመደገፍ መሆን እንዳለበት አስገንዝበው ለመላው ክርስትና ዕምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በፕሮግራሙ #ላይ የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዋና ሰብሳቢ መጋቢ ሚኪያስ ታዬ የዛሬው የትንሳዔ በዓል አከባበር ዝግጅት መሳካት የድሬዳዋ አስተዳደር ላደገላቸዉ ትብብር ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቀርበዋል።

የድሬዳዋ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ ሊቀ ብርሀናት ቀለመ ወርቅ ቢምረው በዛሬው የትንሳኤ በዓል ዲያቢሎስ የታሠረበት፣ ሀጢያት የተሻረበት እንዲሁም ብዙዎች ነጻ የወጡበት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

የዛሬው #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት የትንሣኤ በዓል ዝግጅት ለስኬት እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ጁሌት ተድላ ለድሬ ቲቪ እንደዘገበዉ
ካሜራ:- ምንተስኖት ደረጀ
https://youtu.be/tOWD7qwfcDo

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

የወልቂጤ  #ከተማ ወንጌላውያን አማኞች የትንሳኤ በአልን በህብረት አደባባይ ላይ አከበሩ።ምዕመኑ በአብሮነት ለሰላምና ለአንድነት መስራት ይጠበቅበታልም ተብሏል።የወልቂጤ ከተማ ወንጌላዉያን አብ...
05/05/2024

የወልቂጤ #ከተማ ወንጌላውያን አማኞች የትንሳኤ በአልን በህብረት አደባባይ ላይ አከበሩ።

ምዕመኑ በአብሮነት ለሰላምና ለአንድነት መስራት ይጠበቅበታልም ተብሏል።

የወልቂጤ ከተማ ወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ሰብሳቢ መጋቤ ብርሃኑ አቅነዳ የበአሉ አከባበርን አስመልክተው እንዳሉት የእምነቱ ተከታዮች በአንድነት እንዲያከብሩ መንግስት ማመቻቸቱ የሚያስደስትና እምነቱም ምእመን በጋራ እንዲያከብር የሚያዝ ነው ብለዋል።

#ህብረቱ በበአል ወቅትም ይሁን ከበአል ውጪ የተቸገሩ ወገኖችን ማገዝ ልምዱ ነው ያሉት መጋቤ ብርሃኑ የትንሳኤ በአል አክባሪዎች ይህን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው በዚህ ወቅት እንዳሉት ትንሳኤ ለህዝበ ክርስቲያኑ ታላቅ በአል ነው ብለዋል።

በዋናነት እምነቱ በሚያዘው መሰረት አብሮነትን በማጠናከር ለተቸገሩ ወገኖችን ከመርዳት ባለፈ እርስ በርስ ከሚሸረሽሩ ተግባሮች ከመታቀብ ባለፈ የ #ሰላም መጠበቅ በሚያጸና መልኩ ሊሆን እንደሚገባም ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን #ዋና አስተዳዳሪ ተወካይና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ኃላፊ #አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል ፈጣሪ ሁሉን በእኩል የሚያይና በእኩል የሚዳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የትንሳኤ በአል የደስታ በአል ነው ያሉት አቶ አለማየሁ የይሁዳ ፀፀት ቢዘጋም እርስ በርስ ዛሬም በሀገራችን አንዳንዶች በሰው #ደም የመነገድ ተግባር የሚፈፅሙ አሉ ብለው #ይህም ወንጀል መሆኑን መረዳትና ለሰላም መስራት ከምእመኑ ይጠበቃል ነው ያሉት።

በአል አከባበሩ ላይ የተገኙት አካላትም በአሉን በአደባባይ በህብረት በማክበራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው ላመቻቹ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

በአሉ ሲከበር የተቸገሩትን በመርዳት መሆን እንዳለበትም ገልፀዋል።

አማን ቢካ ለወልቂጤ ሬድዬ እንደዘገበዉ ...

https://youtu.be/tOWD7qwfcDo

 #ተነስቷል .. በሐረር የሐረር ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ  #ልዩ የምስጋና ፕሮግራም አካሂደዋል።ምስጋና 📷 KAL Pictures h...
05/05/2024

#ተነስቷል .. በሐረር

የሐረር ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ #ልዩ የምስጋና ፕሮግራም አካሂደዋል።

ምስጋና 📷 KAL Pictures

https://youtu.be/tOWD7qwfcDo

ዝርዝር መረጃዎችን ለመመልከት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW

 #ተለቀቀ !!! #እኔ አገልጋይ ነኝ እያየሽ ግቢበት ነው ያልኳት ያልተሰሙ  #አስገራሚ እና  #አዝናኝ የተወዳጁ አገልጋይ  #ዘማሪ እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ እና ቤተሰቡ የበዓል ቆይታ
05/05/2024

#ተለቀቀ !!!

#እኔ አገልጋይ ነኝ እያየሽ ግቢበት ነው ያልኳት ያልተሰሙ #አስገራሚ እና #አዝናኝ የተወዳጁ አገልጋይ #ዘማሪ እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ እና ቤተሰቡ የበዓል ቆይታ

#እኔ አገልጋይ ነኝ እያየሽ ግቢበት ነው ያልኳት ያልተሰሙ #አስገራሚ እና #አዝናኝ ከተወዳጁ አገልጋይ #ዘማሪ እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ እና ቤተሰቡ ጋር ልዩ የትንሳኤ በዓል ቆይታ ...

 #ክህደት ፍቅርን አያጠፋም  #የተከፈለው መሰዋዕትነት ለሌሎች ምህረት እንድናደርግ ነው የፓስተር ጻዲቁ አብዶ  #ድንቅ መልዕክት  #እንኳን አደረሳችሁ!!
04/05/2024

#ክህደት ፍቅርን አያጠፋም #የተከፈለው መሰዋዕትነት ለሌሎች ምህረት እንድናደርግ ነው የፓስተር ጻዲቁ አብዶ #ድንቅ መልዕክት #እንኳን አደረሳችሁ!!

#ክህደት ፍቅርን አያጠፋም #የተከፈለው መሰዋዕትነት ለሌሎች ምህረት እንድናደርግ ነው የፓስተር ጻዲቁ አብዶ #ድንቅ መልዕክት #እንኳን አደረሳችሁ!! #....

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Christian News - የክርስቲያን ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to The Christian News - የክርስቲያን ዜና:

Videos

Share

Nearby media companies


Other Media/News Companies in Addis Ababa

Show All