Kalkidan wondimu -ቃል

Kalkidan wondimu -ቃል Started

07/03/2024

ADILA HOTEL HOSSANA

04/03/2024
03/12/2023
አርሰናል ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበነሐሴ 16/2015 (አዲስ ዋልታ) በሳምንቱ የመጨረሻ  የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ክሪስታል ፖላስን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ  የፕሪምየር ሊ...
22/08/2023

አርሰናል ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ

ነሐሴ 16/2015 (አዲስ ዋልታ) በሳምንቱ የመጨረሻ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ክሪስታል ፖላስን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የፕሪምየር ሊግ ጉዞውን አስቀጥሏል::

የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፍያ ግብ ማርቲን ኦዲጋርድ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል::

በአርሰናል በኩል ቶሚያሱ በ68ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል::

ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ተመረቁአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት ...
12/08/2023

ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ዛሬ ተመርቀዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤልን ጨምሮ የፌደራል እንዲሁም የክልሉ የጸጥታ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ነው የምረቃ ሥነ- ሥርዓቱ የተካሄደው፡፡

አቶ ሙስጠፌ ባደረጉት ንግግር÷ ተመራቂዎቹ በስልጠናው ባገኙት ክህሎት በመታገዝ የተረከቡትን ኃላፊነት በሀገር ወዳድና በፖሊሳዊው ሥነ-ምግባር ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

በስልጠና ወቅት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት እውቅና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የትግራይ ክልል ወጣቶች ለዘላቂ ሰላም የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመነሐሴ 6/2015 የክልሉ ወጣቶች የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግና የልማት ግንባታን ለማፋጠን የድርሻቸውን ሊወጡ እ...
12/08/2023

የትግራይ ክልል ወጣቶች ለዘላቂ ሰላም የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ

ነሐሴ 6/2015 የክልሉ ወጣቶች የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግና የልማት ግንባታን ለማፋጠን የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

የወጣቶች ቀን ዛሬ በመቀሌ ከተማ በፓናል ውይይት በተከበረበት ወቅት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳደር ጌታቸው ረዳ ባስተላለፉት መልዕክት የተገኘውን ሰላም ጠብቆ ልማትና እድገት እንዲረጋገጥ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ ይገባል ብለዋል።

ወጣቶች ያላቸውን እውቀትና ጉልበት አሟጠው በመጠቀም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ወጣቶች ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ በመሳተፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የወጣቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ፕሮጀክቶች በመቅረጽ በስራ ላይ ሊውሉ እንደሚገባ አመልክተዋል።

በዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን አከባበር ላይ የመቀሌና አካባቢው ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

የተመረቁት ኮማንዶዎች ሁለት ዓላማ አላቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)   | የተለያዩ አስቸጋሪ መሰናክሎችን ማለፍን እንዲሁም ፈጥኖ መድረስን ለሚጠይቁ ተልዕኮዎች ጠንካራ ስል...
12/08/2023

የተመረቁት ኮማንዶዎች ሁለት ዓላማ አላቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

| የተለያዩ አስቸጋሪ መሰናክሎችን ማለፍን እንዲሁም ፈጥኖ መድረስን ለሚጠይቁ ተልዕኮዎች ጠንካራ ስልጠና ወስደው የተመረቁ ኮማንዶዎች ሁለት ዓላማ እንዳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ ትልቁ ኤሊት ኃይል የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል” ብለዋል።

በመልዕክታቸውም ይህ ኃይል ሁለት ዓላማዎች አሉት በማለት ገልጸው፤ ውጊያ ማስቀረት እና ገፍቶ ከመጣ ደግሞ ውጊያን የመጨረስ ተልዕኮ ያለው ነው ሲሉ ዓላማውን አስረድተዋል።

እንዲህ ያለው ኃይል ይህቺን ትልቅ ሀገር አጽንቶ ለትውልድ ያሻግራል ብለዋል።

የብላቴ ኮማንዶና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ኮማንዶዎችን ዛሬ ማስመረቁ ይታወቃል።

"ነገን ዛሬ እንትከል"    | « ነገን ዛሬ እንትከል »  የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኪነ-ጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በሲዳማ ክልል በሐ...
12/08/2023

"ነገን ዛሬ እንትከል"

| « ነገን ዛሬ እንትከል » የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኪነ-ጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ ታቦር ተራራ ላይ ተካሄደ።

የትራንስፎርሜሽን ሙዚቃና ማስታወቂያ ድርጅት ከተባባሪ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ያዘጋጁት የችግኝ ተከላ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መርሀ ግብሮችን በአርባምንጭ ፣ በቢሾፍቱ እና በዱከም ከተሞች እንዲሁም ዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ የመገናኛ ብዙሃን ፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አትሌቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት ተከናውኗል።

ሐዋሳን ፍጹም ሰላማዊ፣ ለኑሮ ተስማሚ፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ከተማ ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን ያሉት በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከተማዋን ስማርት ከሚያደርጉ ኘሮጀክቶች መካከል የታቦር ተራራ፣ የሐዋሳ መግቢያ በር እና ሌሎችም እንደሚጠቀሱ ገልጸው ከተማዋን ለአለም የሰላም ተምሳሌት በሚያደርግ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የኘሮግራሙ አጋር አካል በመወከል የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ስራ አስፈጻሚ ተወካይ የሆኑት አቶ ፍጹም ከተማ በ8 ዓመታት ውስጥ ከ13 በላይ ፓርኮችን በተለያዩ ቦታዎች መገንባት እንደተቻለ የገለጹ ሲሆን በዚህ አረንጓዴ አሻራ መርሀግብሩ በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ ፓርኮችና ከተማዎች ጋር በመተባበር ከ15 ሚሊዬን በላይ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ገልጸዋል።

"ኑ ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መነሻ ሀሳብ የተሰናዳው የችግኝ ተከላ መርሐግብሩ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማት ፣ ግለሰቦች ፣ የኪነጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷል።

የችግኝ ተከላው መርሐግብር የትራንስፎርሜሽን ሚዲያና አድቨርታይዝንግ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እና ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመቀናጀት መዘጋጀቱን
ገልጸዋል።

የመካከለኛው የምግብ እጥረት ህክምናን ወደ ጤና ኤክስቴንሽን ስርዓት ለማስገባት የመግባቢያ ስምምነት ተደረገ____________ከባለፉት ዓመታት ወዲህ በተሰሩ መጠነ ሰፊ የምግብና የስርዓተ ምግ...
11/08/2023

የመካከለኛው የምግብ እጥረት ህክምናን ወደ ጤና ኤክስቴንሽን ስርዓት ለማስገባት የመግባቢያ ስምምነት ተደረገ
____________

ከባለፉት ዓመታት ወዲህ በተሰሩ መጠነ ሰፊ የምግብና የስርዓተ ምግብ ፖሊሲና ስትራቴጂ ትግበራዎች፣ የሰቆጣ ቃልኪዳን ስምምነት ትግበራ፣ የስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መቋቋምን ጨምሮ በተከናወኑ አንኳር ስራዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በጨቅላ ህፃናት ላይ በስፋት እየተስተዋሉ ያሉትን የመቀንጨር (stunting) እና የመቀጨጭ (wasting) ችግሮች መሻሻል ይታይባቸዋል ያሉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በዓለም እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ያጋጠሙ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የምግብ ዋጋ ንረት፣ የእረስ በእርስ ግጭት፣ ድርቅ እና ረሃብ መከሰታቸው እንደ ሀገር እተሰሩ ባሉ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ስራዎች ላይ ትልቅ ትጽዕኖ መፍጠሩን የጠቀሱ ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ይህም በተለይ በልጃገረዶች፣ በአጥቢ እናቶች፣ በጨቅላ ህፃናትና፣ በነፍሰጡር እናቶች ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የምግብና የስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት ዳርስኔ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የያዘችውን የምግብና የስርዓተ ምግብ ተግበራን በ2030 ለማሳካት የተለያዩ የአሰራር ስልቶችን በመከተል እና የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው የሚደረገው የመግባቢያ ስምምነት ተቋማት የሚያከናውኑትን የምግብና የስርዓተ ምግብ ትግበራ በቅንጅት ለመስራት የሚያግዝ ነው ያሉ ሲሆን በተለይ የመካከለኛው የምግብ እጥረት ህክምናን ወደ ጤና ኤክስቴንሽን ስርዓት በማስገባት ተገቢውን ክትትል እና ድጋፍ እንዲሁም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ት ጄኔፈር ቢቶንድ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት የምግብ እጥረትን ለመከላከልና በምግብ እጥረት ምክንያት ለሚፈጠሩ የጤናና ተያያዥ እክሎች እየሰጠ ያለውን አፋጣኝ ምላሽ ያደነቁ ሲሆን በዚህም የመቀንጨር (stunting) ምጣኔን ከ58% ወደ 37% በመቶ መቀነስ መቻሉን እንዲሁም መቀጨጭ (wasting) 10% ወደ 7% መቀነስ መቻሉ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ ገልጸው የምግብ እጥረት ችግርን ለመቅረፍ እና የተያዘውን ግብ ለማሳካት በዘርፉ የተገኘውን ሀብት በአግባቡ መያዝ እና በጥቅም ላይ ማዋል እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እና በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ከመከላከልና አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት ረገድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እጅግ አበረታች እንደሆኑ የገለጹት በኢትዮጵያ የዩ.ኒ.ሲ.ኤፍ ምክትል ዳይሬክተር ማሪኮ ካጎቺማ ሲሆኑ በምግብና በስርዓተ ምግብ ረገድ እየተሰሩ ያሉ ዘረፈ ብዙ ስራዎችን በማጠናከር መስራት እንደሚገባና በምግብ እጥረት የሚጠቁ ህፃናት ተገቢውን ህክምና የሚያገኙበት ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

በመድረኩም የሚመለከታቸው የመንግስትና አጋር ድርጅት ኃላፊዎች የመካከለኛው የምግብ እጥረት ህክምናን በተሻለ መልኩ ለመፈጸም የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሱ ናቸው *ባህር ዳር *ጎንደር *ደብረ ብርሃን * ሸዋሮቢት *ላሊበላ   | በግጭት ውስጥ የሰነበቱት አንዳንድ የአማራ ክልል ከተሞች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እ...
10/08/2023

ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሱ ናቸው

*ባህር ዳር *ጎንደር *ደብረ ብርሃን * ሸዋሮቢት *ላሊበላ

| በግጭት ውስጥ የሰነበቱት አንዳንድ የአማራ ክልል ከተሞች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሱ መሆኑን የየከተሞቹ ነዋሪዎች ገልጸዋል

*የክልሉ ርዕስ ከተማ ባህር ዳር የተኩስ ድምፅ የማይሰማባት ከተማ ሆና እንደዋለች የገለጹት ነዋሪዎቹ በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች ሱቆች እንደተከፈቱም ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አሁንም የትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎት እንዳልተጀመረ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች ግን እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመራቸውን ነው ያነሱት።

*በጎንደር ከተማ የባንክ አገልግሎትን በስፋት ስራ የጀመረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የመንግስት ሰራተኞችም ወደ ስራ መግባት እንደጀመሩ ተገልጿል።

በከተማዋ ከትናንት በተሻለ የሰዎች እንቅስቃሴ እንዳለ የገለጹት ነዋሪዎቹ የተኩስ ድምጽም እንደማይሰማም ተናግረዋል። የንግድ መደብሮች በከተማዋ ስራ ስለመጀመራቸውም ያረጋገጡት ነዋሪዎቹ በከተማዋ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ግን አሁንም የለም ብለዋል።

*ደብርብርሃን ከተማ ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርትን ጨምሮ በከተማዋም ከባጃጅ ና ሞተር ሳይከል ውጭ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መጀመሩን የገለጹት የከተማዋ ነዋሪዎች የተኩስ ልውውጥም ሆነ የተለየ እንቅስቃሴ እንደማይሰተዋልም ገለጸዋል።

በደብረ ብርሃን የባንክ አገልግሎት እንዲሁም ሱቆችም ወደ ስራ መግባታቸውንም ነዋሪዎች ተናግረዋል።

*ሌላዋ የግጭት ማዕከል የነበረችው ደብረማርቆስ ከተማ በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የተኩስ ድምጽ እንዳልተሰማባት የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ጉሊት እና ትናንሽ ሱቆች ስራ መጀመራቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ የባንክ አገልግሎት ወደ ስራ እንዳልገባ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ባንኮች ነዋሪዎችን በኤቲኤም እንዲጠቀሙ ማመቻቸታቸውን ገልጸዋል።

*በሸዋሮቢት ከተማ ደግሞ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እስከረፋድ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ መቋረጡን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ በሸዋ ሮቢት ከተማ የሰዎች መደበኛ እንቅስቃሴ ግን እየተመለሰ መሆኑን አንዳንድ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም በከተማዋ የቅርብ እርቀት አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ለኢትቪ ገልጸዋል።

*ላሊበላ ከተማ ሰሞኑን የከባድ መሳሪያ ደምጽን ጨምሮ ተኩስ በስፋት ሲሰማ እነደነበር የገለጹት የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ አሁን ላይ ምንም አይነት የተኩስ ድምጽ እንደማይሰማ ገልጸዋል፡፡ ይህም በመሆኑ ባንኮች እና መደበኛ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ነዋሪዎቹ ለኢትቪ ገልጸዋል።

በከተሞች የሚገኙ የንግድ ቤቶችም ወደ ስራ መመለሳቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

10/08/2023
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ለማሳለጥ የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ አጠናክሮ ይቀጥላል - የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው    |  የኢትዮጵያ አየር ...
10/08/2023

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ለማሳለጥ የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ አጠናክሮ ይቀጥላል

- የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው

| የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬታማ እንዲሆን የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ለመደገፍ በቅርቡ የ10 በመቶ የካርጎ (የዕቃ ጭነት) ዋጋ ቅናሽ አድርጓል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገና ከጅምሩ የፓን አፍሪካን እሳቤ በመያዝ አፍሪካውያንን ሲያስተሳስር የኖረ ተቋም ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መጀመሩን ለአፍሪካ አገራት ምጣኔ ኃብታዊ ትስስር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ጠቁመው፤ ይህንንም ሂደት አየር መንገዱ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ አየር መንገዱ አፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ለመደገፍ በቅርቡ የ10 በመቶ የካርጎ ዋጋ ቅናሽ ማድረጉን ጠቅሰው፤ ይህም በአህጉሪቱ በንግዱ ዘርፍ የሚካሄደውን የጭነት እንቅስቃሴ በእጅጉ እንደሚያሳልጠው ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

በቀጣይም አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናውን ስኬታማ ለማድረግና የአህጉሪቷን እድገት ለማስቀጠል አየር መንገዱ አገራትን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ አየር መንገዶች ከሌላው ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ጋር ሲወዳደር በመንገደኞች አገልግሎትም ይሁን በዕቃ ጭነት አገልግሎት ወደ ኋላ የቀረ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ሊያድግ ይገባል ነው ያሉት።

ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሁለቱም የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎቱን እያጠናከረ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም የሚጠበቅበትን አህጉራዊ ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ነፃ የንግድ ቀጣናው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከርና በአህጉሪቷ አገራት መካከል ሸቀጦች እንዲዘዋወሩ ከማድረግ ባሻገር ለአየር መንገዶች እድገትም ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

ነፃ የንግድ ቀጣናው የአህጉሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስቀጠልም ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ገልጸው፤ ይህ አህጉራዊ የነፃ የንግድ ቀጣና ተጨባጭ ውጤት እንደሚያመጣ አገራት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2019 ወደ ሥራ የገባው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አሁን ላይ በጅምር ደረጃ በተለያዩ አገራት ገቢራዊ እየተደረገ ነው።

ነፃ የንግድ ቀጣና በአግባቡ ገቢራዊ ከተደረገ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2035 የአፍሪካውያንን ገቢ 9 በመቶ ከፍ እንደሚያደርገው ዓለም ባንክ ገልጿል።

ይህም ብቻ ሳይሆን በነፃ የንግድ ቀጣናው በሚፈጠረው የሥራ ዕድል 50 ሚሊየን አፍሪካውያን ከድኅነት እንደሚወጡ የባንኩ ትንበያ ያመላክታል።

በተለያዩ ተቋማት ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ ሰነዶች እና ማህተሞች በቁጥጥር ስር ዋለ  | በአዲስ ከተማ እና በየካ ክፍለ ከተሞች በተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ስም የተዘጋጁ በርካታ ሃሰ...
10/08/2023

በተለያዩ ተቋማት ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ ሰነዶች እና ማህተሞች በቁጥጥር ስር ዋለ

| በአዲስ ከተማ እና በየካ ክፍለ ከተሞች በተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ስም የተዘጋጁ በርካታ ሃሰተኛ ሰነዶች እና ማህተሞች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ምዕራብ ሆቴል አካባቢ አንድ ግለሰብ በተለያዩ ተቋማት ስም በተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነዶች እየተገለገለ ገንዘብ በመቀበል ለተለያዩ ግለሰቦች ዋስ ሆኖ የጥበቃ ስራ ሲያስቀጥራቸው መቆየቱ በቀረበ ጥቆማ እና በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ይህንን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ባከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ ተመሳሳይ ተግባር የሚፈፅሙ ሌሎች ሶስት ግብራበሮቹን መያዝ ተችሏል፡፡

በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት፣ የገቢዎች ቢሮ፣ የተለያዩ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም በወረዳ አስተዳደር ስም የተቀረጹ ሃሰተኛ ክብ ማህተሞችን ጨምሮ ሌሎች ልዩ ልዩ ሃሰተኛ ሰነዶች ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው በግ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ የተለያዩ ሃሰተኛ ማህተሞች እና ሰነዶች በብርበራ ተይዘዋል፡፡

ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መነሻነት በህግ አግባብ በተከናወነው ብርበራ ከተያዙት መካከል በተለያዩ ተቋማት በሚሰሩ ሃላፊዎች ስም የተዘጋጁ ቲተር እና ክብ ማህተሞች፣ የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 14 ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ እና ማስረጃ አገልግሎት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ማህተሞች እና ልዩ ልዩ ሃሰተኛ የትምህርት ተቋማት ሰነዶች ይጠቀሳሉ፡፡

በአጠቃላይ እነዚህን ሃሰተኛ ሰነዶች በማዘጋጀትና በሰነዶቹ በመገልገል የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡

ሃሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም የሚፈፀሙ ወንጀሎች እንደሃገር የሚያስከትሉት ጉዳት ዘርፈ ብዙ በመሆኑ እነዚህን ጉዳቶች አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ መረጃና ጥቆማ የመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ለስራ ቅጥርም ሆነ ለተለያዩ ጉዳዮች ሰነዶችን የሚጠይቁ ተቋማት አገልግሎቱን ከመስጠታቸው አስቀድመው የቀረቡላቸውን ሰነዶች በማረጋገጥ ሃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

  👉https://www.facebook.com/profile.php?id=100063892ከሮበርት ኪዮሳኪ ምርጥ መጽሐፍት   እና   የተቀመሙ 10 ሀብት የመገንባት ጥበቦች፡- ! ብዙ ሰዎች ገንዘብ...
09/08/2023



👉https://www.facebook.com/profile.php?id=100063892

ከሮበርት ኪዮሳኪ ምርጥ መጽሐፍት እና የተቀመሙ 10 ሀብት የመገንባት ጥበቦች፡-

!

ብዙ ሰዎች ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው እንዴት በትክክል ማስተዳደር እንዳለበት አይማርም።

የፋይናንስ ብልህነት (Financial intelligence) የሚጀምረው በገቢና ወጭህ መካከል ያለውን ልዩነት ከመረዳት ነው። ከምታወጣው የበለጠ ገቢ እንዳለህ አረጋግጥ፤ ይህም የበለጠ ሀብታም ያደርግሃል።

!

ብዙ ሰዎች የሚያገኙትን ገንዘብ የሚያውሉት እዳቸውን ለመክፈል ነው።

ብልህ ሰው ግን ሁልጊዜ ከሚያገኘው ገቢ ውስጥ:-

- ኮርሶችን ለመውሰድ
- መጽሐፍት ለመግዛትና
- ልምድ ለመውሰድ ያውላል።

!

መቆጠብ ግዴታ እና ጥሩ ልማድ ተደርጎ ይቆጠራል። ነገር ግን ገንዘብህን ከዋጋ ግሽበቱ በበለጠ በሚያድግበት ነገር ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያስፈልግሀል።

መቆጠብ የገንዘብን የመግዛት አቅም ሲያዳክም፣ ኢንቨስትመንት ግን የገንዘብን ዋጋ ይጨምራል።

!

ብዙ ሰዎች በአንድ የገቢ ምንጭ ላይ ብቻ ጥገኛ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ከሆንክ በፍፁም ሀብታም መሆንና የገንዘብ ነፃነት ላይ መድረስ አትችልም።

ተጨማሪ ገንዘብ የምታገኝበት ሌላ አማራጭ ሊኖርህ ይገባል።

!

በህይወትህ ሪስክ እስካልወሰድክ ድረስ ማደግ አትችልም።

በህይወት ውስጥ አንዳንድ እድሎች የህይወትህን አቅጣጫ የመቀየር አቅም ስላላቸው ሪስክ መውሰድ አለብህ።

!

በዓለም ዙሪያ ያለው የትምህርት ሥርዓት የሚያሳዝነው ነገሩ ለገንዘብ መሥራትን የሚያስተምር መሆኑ ነው። የትምህርት ስርዓቱ ገንዘቡን እንዴት ማግኘት፣ ማስተዳደር እና ጠብቆ ማቆየት እንደሚቻል በጭራሽ አያስተምርም።

ማንኛውም ሰው ሀብትን እንዴት መፍጠር እንደሚቻል መማርና የፋይናንስ ነፃነትን ለማግኘት እቅድ ማውጣት አለበት።

!

ድሃ አባቴ ሁልጊዜ እንዲህ ይለኝ ነበር "ይህን ለመግዛት አንችልም" ሀብታም አባቴ ግን "እንዴት መግዛት እንደምችል" ያስተምረኛል።

በዚህ መንገድ አፍራሽ አስተሳሰብህን ወደ አወንታዊ አስተሳሰብ ቀይረው። ይህን ስታደርግ በእርግጠኝነት ግብህን ለማሳካት መንገዶችን ታገኛለህ።

የአንተ አመለካከት እና አስተሳሰብ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ነው።

ማንኛውንም ነገር ለማድረግ የመጀመሪያው እና ዋናው ነገር በራስህ ማመን ነው።

!

ሀብታም ሆነህ የፋይናንስ እውቀት ከሌለህ ብዙ ግብሮችን ትከፍላለህ። ሀብታሞች ብዙ ጊዜ ኢንቨስትመንታቸው በመማር ላይ ስለሆነ መክፈል ያለባቸው ቀረጥ ትንሽ ነው።

በመሆኑም እንደ የሂሳብ አያያዝ፣ ኢንቨስትመንት፣ የገበያ ሃይሎች እና ህግ ባሉ የተለያዩ ዘርፎች የፋይናንስ እውቀት ሊኖርህ ይገባል።

!

‘በክፍሉ ውስጥ በጣም ብልህ ሰው ከሆንክ፣ የተሳሳተ ክፍል ውስጥ ነህ።’ የሚል በጣም ታዋቂ አባባል አለ።

ብልህ መሆን ከፈለግክ ከአንተ የበለጠ ብልህ በሆኑ ሰዎች እራስህን ከበብ።

!

ስሜትህን መቆጣጠር በማትችልበት ወቅት ሁኔታው በጣም የከፋ

በድሬዳዋ ሊሰርቅ የሰው ቤት ገብቶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ውስኪ ሲጠጣ የተገኘው ሌባ በ3 አመት እስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ! ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን የማይገባ...
09/08/2023

በድሬዳዋ ሊሰርቅ የሰው ቤት ገብቶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ውስኪ ሲጠጣ የተገኘው ሌባ በ3 አመት እስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ!

ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት በማሰብ ሀምሌ 9 ቀን 2015ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰአት ገደማ በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ጎሮ 32 መንገድ ከሚገኘው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በር ሰብሮ በመግባት ነበር አስገራሚ የሆነውን ተግባር የፈፀመው።

ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ የግል ተበዳዮችን ቤት በር ሰብሮ ከገባ በኋላ ጤረጵዛ ላይ ታብሌት ስልክ ተቀምጦ ይመለከታል እሱን ይዞ ለመውጣት ያስብና ቀና ሲል ውስኪ ብፌ ውስጥ ያያል ልቡ ሸፈተ ቆይ በዚህ ውስኪ ለምን ትንሽ ዘና አልልም ይልና ብርጭቆ አቅርቦ ሶፋ ላይ ፈልሰስ ብሎ ተቀምጦ ልክ እንደራሱ ቤት እየተዝናና እያለ ነበር ከተወሰነ ሰአት በኋላ የግል ተበዳዮች መምጣታቸውን ይሰማና ጠረጴዛ ላይ የነበረውንና የዋጋ ግምቱ 12ሺ ብር የሚያወጣ ታብሌት ስልክ ብድግ አድርጎ በድንጋጤ ሽንት ቤት ይደበቃል የግል ተበዳዮችም ወደ ቤታቸው ሲገቡ ውስኪውን እና ብርጭቆ ጤረጴዛ ላይ ይመለከታሉ ታዲያ በዚህ ሰአት ማነው እዚህ ቤት የገባው ብለው በድንጋጤ ቤታቸውን ሲፈትሹ ተከሳሹን ግለሰብ ከነሰረቀው ንብረት ሽንት ቤት ውስጥ እጅ ከፍንጅ በመያዝ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይደውላሉ።

በዚህም መሰረት ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ ወደ ጣቢያ ይወሰዳል ለፈፀመው ከባድ የስርቆት ወንጀልም በአቃቤ ህግ ክስ ይመሰረትበታል።

በፖሊስ ተጣርቶ በአቃቤ ህግ የተመሰረተበትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሀምሌ 21 ቀን 2015ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰን ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው በሶስት አመት ከሶስት ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

ውስኪ ያዘናጋው ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ እንዳሻው መሆን ሳይችል ወደማረሚያ ወርዷል ሲል የድሬዳዋ ፖሊስ ነው የዘገበው።

የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ተመዛኞች በሙሉ_________በMedicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Scienc...
09/08/2023

የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ተመዛኞች በሙሉ
_________

በMedicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በሰኔ 30/2015 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን የመውጫ እና ብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች በሙሉ

▫የዳግም ተመዛኞች hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና በጤና ሚ/ር የተሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን ከነሃሴ 4/2015 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

▫አዲስ ተመዛኞች (በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ምዝገባ ያካሄዳችሁ በሙሉ) በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ መያዝና የጤና ሚኒስቴርን የማለፊያ ነጥብ ማሟላት የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ሁለቱንም መስፈርቶች አሟልታችሁ ያለፋችሁ ተመዛኞች ስም ዝርዝራችሁን ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ መሆኑን እየገለጽን የተለያዩ ጥያቄዎች ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በአካል የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ሙያ ፣ የፈተና መለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን ተቋም በማስቀደም ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ከዚህ ዓለም ድካም አረፈ   | አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ለረዥም ጊዜ በህመም ላይ የቆየው አርቲስት አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ አርቲስት አብ...
09/08/2023

ከዚህ ዓለም ድካም አረፈ

| አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ለረዥም ጊዜ በህመም ላይ የቆየው አርቲስት አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ነበር።

ከዚህ ውስጥ አሉላ አባነጋ፣ የቼዝ ዓለም፣ ዳኛው፣ እስረኛው ንጉስ እና ነቅዕ ቴአትሮች ላይ ተውኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አያስቅም፣ አንድ እድል፣ ላምባዲና፣ ሰበበኛ፣ ባንቺ የመጣ፣ ቁልፉን ስጭኝ፣ የነገርኩሽ እለት፣ ፍቅር እስከ መቃብር እና አትሸኟትም ወይ በተሰኙ ፊልሞች ላይ በመተወን አድናቆትን አግኝቷል።

ስንቅ ፣መለከት፣ ትርታ እና ለወደዱት ደግሞ የተሳተፈባቸው ቲቪ ድራማዎች ሲሆኑ፥ በግሉም የቅብብሎሽ ድራማን ደርሷል።

Address

Addis Ababa
HEY,I'MUSINGTELEGRAMTOCHAT.JOINME!DOWNLOADITHERE:HTTPS://TELEGRAM.ORG/DL

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251916459146

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kalkidan wondimu -ቃል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kalkidan wondimu -ቃል:

Videos

Share


Other Social Media Agencies in Addis Ababa

Show All