Tofa arada

Tofa arada Digital army and propaganda for prosperity party

07/08/2024

ነባራዊ ሁኔታውን በጥልቀት በመመርመር ፣ ዘላቂ ዕድገታችንን ለማረጋገጥ የተደረገው ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ግቡን እንዲመታ የድርሻችንን እንወጣ !

ፓርቲያችን በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ባለብዙ ወገን የኢኮኖሚ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ በተለይም ምርትና ምርታማነት በእጅጉ እንዲጨምር ታሪካዊ ውሳኔዎችን እያሳለፈ መጥቷል።

በተደራራቢ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች የማይበገር ፣ ስንዴን ኤክስፖርት ወደ ማድረግ ጭምር መሸጋገር የተቻለው ዘመኑን በዋጁ የፓርቲያችን ፖሊሲዎች ጥራት እና በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመጣው የመንግስት የመፈፀም አቅም ነው፡፡

ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋጥ በምናደርገው ርብርብ የዜጎቻችን ህይወት እየተሻሻለ ሲሄድ መንግስት በኢኮኖሚው ላይ እጁን እያሳጠረ እንደሚሄድና በአንፃሩ ደግሞ የግሉ ዘርፍ የአንበሳውን ሚና እንዲጫዎት ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠሩ ፓርቲያችን በኢኮኖሚ ፕሮግራሙ አመላክቷል።

ተራማጅ የሆኑ እሳቤዎች ባለቤት የሆነው ፓርቲያችን ተለዋዋጭ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ሁኔታዎችን ቀድሞ በመረዳት ትናንትን ከዛሬ ፣ ዛሬን ደግሞ ከነገ እያስተሳሰረ ጠንካራ ሀገር ለመፍጠር ይተጋል እንጅ በጅምር ስኬቶች አይረካም ፤ በጊዜያዊ ተግዳሮቶችም ያነገበውን ራዕይ ዕውን ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም።

በየዘርፉ ውስብስብ ዕዳዎችን የተረከብን ትውልዶች እንደመሆናችን ያለፈውን በማከም የሚገጥመንን ችግር ቀድመን በመከላከል እንዲሁም ለስኬታችን መስፈንጠሪያ በማድረግ ከድል ላይ ድል ማስመዝገብ የህልውናችን ዋስትና ነው።

አንዳንዶች በቅርቡ በሀገራችን የተደረገው ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ሳይታሰብበት ድንገት የተደረገ አድርገው ተረድተውታል ወይም ተርጉመውታል።

ትርፍና ኪሳራው ተለይቶ ከዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ግባችን አንፃር በዘርፉ ምሁራን በጥልቀት ተጠንቶ ፣ የተለያዩ ሂደቶች አልፎ የመጣ እንጅ ድንገተኛ አለመሆኑን የፓርቲያችን አቅጣጣዎች እና ከውሳኔው ቀደም ብለው የነበሩ ምክክሮችን ማስታወስ ይበጃል።

ሰው ተኮር ፕሮግራሞችን በስፋትና በጥራት እየተገበረ የሚገኘው መንግስታችን የህዝባችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርስን የኑሮ ጫና ለማቃለል አበረታች ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል ፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ለአብነትም በከተማችን ዘርፈ ብዙ ትርጉም ያለው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ተቋማዊ ለማድረግ የተከናወኑ አበረታች ስራዎች ፣ የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላትን በማስፋፋት ፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራምን በዘላቂነት ህይወትን በሚያሻሽል አሰራር እንዲደገፍ እየተደረገ ያለው ጥረት ፣ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ፣ በትራንስፖርት እና በመሳሰሉት የሚደረጉ በቢሊዮን ብር የሚቆጠሩ ድጎማዎች ዋነኛ ዓላማ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዟችን ሂደቱም ጭምር ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ እንዲሄድ ፓርቲያችን እና መንግስታችን ያላቸውን ፅኑ አቋም አመላካች ነው::

ሰሞኑን የተደረገውን ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ተከትሎም በህዝባችን ላይ ሊፈጠር የሚችልን የኑሮ ጫና ለማቃለል መንግስት ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይጠበቃል።

አጋጣሚዎችን ሁሉ በህዝብ ላይ ተረማምደው ያልተገባ ጥቅም ለማጋበስ የሚሞክሩ ስግብግብ ግለሰቦችን ደግሞ በህግ እና በአሰራር ተጠያቂ የማድረጉ ተግባር እንደሚጠናከር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሰሞኑን መግለፃቸው አይዘነጋም ።

ዘላቂ ዕድገታችንን ለማረጋገጥ የተደረገው ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ በታለመለት መልኩ ግቡን እንዲመታ በተለይም የንግድ ስርዓታችንን በማዘመን ፣ ብልሹ አሰራሮችን ፈጥኖ የማረም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በህገ -ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ህዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ ለዘላቂ ጥቅሙ እና ለመብቱ መረጋገጥ የድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግም በትኩረት ይሰራል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ /ቤት


07/08/2024

መስፈንጠር ለፈጣን ሀገራዊ የብልጽግና ስኬት!!

በኢትዮጵያ በቅርቡ የተጀመረዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገሪቱን የብልጽግና ጉዞ ፍጥነት የሚጨምር እና የተጀመረዉን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ከሚፈለገዉ ከፍታ የሚያደርስ ትልቅ አስተዋፅዖ የሚኖረዉ ነው። የፊስካል ስርዓትን በማስተካከል የዋጋ ንረትን በመቀነስ ፣ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የሰጠው ትኩረት ለዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት አስተማማኝ መሰረት የሚጥል ይሆናል።

ከእነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ በጣም ተስፋ ሰጪ ከሆኑት መካከል አንዱ መሠረተ ልማትን እና የህዝብ አገልግሎቶችን ማሻሻል ላይ ትኩረት መስጠቱ ለንግድ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የበለጠ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።

እንደ ቴሌኮሙኒኬሽን እና ፋይናንሺያል ያሉ ቁልፍ ሴክተሮችን በከፊል ነፃ ለማድረግ የታቀዱ ማሻሻያዎች ከወዲሁ ከፍተኛ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ጀምሯል። ይህ የካፒታል ፍሰት የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ ለዳበረ ኢኮኖሚ አስፈላጊ የሆኑትን ፈጠራ እና ውድድርን እያጎለበተ ነው።

በተጨማሪም የቁጥጥር ሂደቶችን ለማቀላጠፍ እና ግልጽነትን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት መዳረሻነት ከዚህ ቀደም ከነበረዉ ማራኪነት የሚያጎለብት ይሆናል።

ኢትዮጵያ በዚህ ጎዳና ላይ ስትቀጥል የተጠናከረው የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት እና የባለሀብቶች መተማመን መጨመር ለዜጎቿ የረዥም ጊዜ ብልጽግና እና መሻሻል አስተዋጽኦ ያደርጋል። አሁን በኢትዮጵያ እየታየ ያለዉ የመልማት ፍላጎት እና የተገኘው ስኬት የሪፎርም ስትራቴጂው ውጤታማነት ማሳያ እና የወደፊቷ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ተስፋ ሰጪ ማሳያ ነው።

ይህንንም ቀጣይነት ባለዉ መልኩ ለመተግበር እና ሀገራችን ተከታታይ የባለሁለት አሃዝ እድገት በማስመዝገብ በሚቀትሉት አመታት ለመድረስ ያሰበችዉን ራዕይም ለማሳካት ከእርምጃ መስፈንጠር እና ሁለንተናዊ የብልጽግና ስኬትን እዉን ለማደርግ አዳዲስ ማሻሻያዎችን መተግበር አለምአቀፍ ተወዳዳሪነታችንን ማረጋገጥ አስፈላጊ ይሆናል።

07/08/2024
07/08/2024
07/08/2024

ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት እንዲሁም ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የትኩረት አቅጣጫችን ነው!

የብልጽግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ፕሮግራም የፓርቲያችን የኢኮኖሚ ፕሮግራም ዋነኛ ዓላማ ልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት ነው፡ ፡

በዚህም የህዝባችን ሰፊ ክፍል የሆነውን አርሶ አደር፣ አርብቶ አደር፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማ ነዋሪዎች ማዕከል ያደረገ አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት በመገንባት የህዝባችንን የጋራ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ የፓርቲያችን የትኩረት አቅጣጫ ነው፡ ፡


ፓርቲያችን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንግስት የራሱ የሆነ ሚና ቢኖረውም በተለይም የግሉ ዘርፍ ወሳኝ ሚናውን እንዲወጣ ምቹ ሁኔታ የመፍጠሩን ጉዳይም ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶታል።

መንግስት በኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ያለው ተሳትፎ የገበያ መርህን በመከተል ስትራቴጂካዊ በሆነ ሁኔታ ሀብት የሚፈጥር፣ በተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ማእቀፍ ውስጥ የግሉን ዘርፍና ሌሎች የኢኮኖሚ ተዋናዮችን ተሳትፎ በማጎልበት ምርታማነትን በላቀ ደረጃና ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲያሳድግ ይደረጋል ።

ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት እንዲሁም ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ደግሞ የማይበገረ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታው ላይ በጋራ እንረባረብ።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

16/06/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል አደሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አቶ ጸሀዬ ብረሃኑ

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የብልጽግና ,ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

16/06/2024

እንኳን ለ1ሺህ 445ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን"

አራዳ ሰኔ 07/ 2016
ከሁሉ አስቀድሜ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እና ለወረዳ 02 የእምነቱ ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል አድሃ/አረፋ/ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።

በዓሉን ስናከብር ባህላችን የሆነውን የመረዳዳትና አብሮነትን በተግባር በመተግበር የተቸገሩ ወገኖችን፣ አቅመ ደካሞችን በመጋዝ እንድሆን አደራ እላለው።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!! አደረሰን!! ኢድ ሙባራክ !!

አቶ ከዲር ጀርሶ ፦ በአራዳ ክ/ክከተማ የወረዳ 02 ዋና ስራ አስፈፃሚ

30/04/2024

"በህብር ወደ ብልጽግና"

የብልፅግና ፓርቲ ዋና አላማ ህብረ ብሄራዊነቱን የጠበቀ እና የጋራ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያለው ማህበረሰብ መገንባት ነው።

ስለ ህብረ ብሄራዊነት ስናወራ ሁሉንም ብሔረሰቦችን፣ ኃይማኖቶችን ወይም ማንነቶችን ያካተተ ነገር ግን የትኛውንም ብሔር የማያገለል ማለታችን ነው።

የብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሄራዊነት በአሳታፊነት፣ ብዙሃነት እና አቃፊነት መገለጽ አለበት ብሎ ያምናል።

ህብረ ብሄራዊ አንድነት ብዘኃነትን እንደ ልዩ ሥጦታ ይመለከተዋል። ህብረ ብሄራዊ አንድነት የእርስ በርስ መተሳሰራችን መገለጫ እና የጠንካራ አንድነታችን ምልክት ነው። ህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያሳየው እጣ ፈንታችን በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ መቆም፣ መረባረብ እና ለጋራ አላማ መቆም እና መደጋገፍ እንዳለብን ነው።

ህብረ ብሄራዊ አንድነት የጋራ የማንነታችን መገለጫ፣ የአንድነታችን እና የጠንካራ ትስስራችን ምልክት ነው። የህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያሳየው እጣ ፈንታችን በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ መቆም፣ መረባረብ እና ለጋራ አላማ መቆም እና መደጋገፍ እንዳለብን ነው።

ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ብዙ ሆነን አንድ አንድ ሆነን ብዙ በመሆን ለጋራ ዓላማና ተልዕኮ የተሰባሰብንበት አንድነት ነው።

በብዝሃነታችን ውስጥ እየበራን፣ በአንድነታችን ጠንክረን መገስገስ የውበታችንና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው።

ፍትህ ከተረጋገጠ ሰብአዊ ክብር ከሰፈነ ብልፅግና ከመጣ እንደ ሀገር ቀጣይነታችን ይለመልማል። ነገር ግን የጋራ ህብረ ብሄራዊነት እነዚህ ምሰሶዎች ከተሳኩ ብቻ ሳይሆን ለዓላማው መሳካት የበኩላችንን ሚና እንድንጫወት ስለሚያስችሉን "በጋራ ወደ ብልፅግና እንሄዳለን" በሚለው መመሪያ መሰረት ፓርቲያችን ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።

30/04/2024

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ9 ወራት ስራ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ምሽት ከስር በተጠቀሱ ሚዲያዎች ላይ ይተላለፋል።

ይጠብቁን!

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tofa arada posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share