ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!
በተቋማት የተነቃቃ እና መልካም የስራ ግንኙነትን በመገንባት የአመራር እና ሰራተኛውን የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም እናጎልብት!
አዲስ አበባ ታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም
መልካም የአገልጋይነት ቀን!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) ለ ሶስተኛ ወገን በሚተላለፉ አገልግሎቶች ዙሪያ ከ ፋና ቴሌቭዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ!
አዲስ አበባ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም
***************
ከ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!
አዲስ አበባ ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም
*************
የአገልግሎት አሰጣጥ ለአንድ ተቋም ህልዉና መሰረታዊ ነዉ ሊባል ይችላል።
መግባባት ማለት መልእክት በሚያስተላልፈዉ ባለሙያ ወይንም ሰራተኛ እና መልእክትን በሚቀበል ሌላ ሰራተኛ አልያም ባለሙያ፤ተገልጋይ መካከል ያለዉን አመቺ የሆነዉን የግንኙነት መስመር በመጠቀም ሀሳብን መለዋወጥ፤እቅድ ወይንም ግብን ማሳወቅ ፖሊስ እና ደንቦችን እንዲሁም መሰል ጉዳዮችን ማስተላለፍ እና የተላለፈዉንም መልእክት በትክክል በተቀባዩ በኩል ግልፅ ግንዛቤ መኖሩን ማወቅ ማለት ነው፡፡
ጥራት ያለዉ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የተገልጋዮች አያያዝ የአንድ ወቅት ስራ ብቻ ሳይሆን ራእይ፣አላማ፣ግብ ያለዉ በአገልግሎት ስራ አመራር የሚመራ እና እየተሻሻለ የሚሄድ ቀጣይነት ያለዉ ተግባር ነው።
የአገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋዩን ማህበረሰብ ጥያቄ እና ፍላጎት ለማርካት ያለመ በተገልጋዩ ተቀባይነት ያለዉ እና ስርአት ባለዉ መንገድ የሚመራ እንቅስቃሴ ነው።
እያንዳንዱ አገልግሎት ሰጪ ተቋም አገልግሎት አሰጣጥን የማሻሻል፣ብቃት ያለዉ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የማስቻል ኃላፊነት ይኖርበታል።
ስለሆነም የመንግስት ሰራተኛዉ እና አመራሩ በቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር እንደ መስራቱ መጠን ዘወትር የተግባቦት አቅሙን ማጎልበት እና ማዳበር
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!
************
አዲስ አበባ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም
ቅንጅታዊ አሰራር ለተቋም ግንባታ!
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!
**********************
አዲስ አበባ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም
ዝቅ ብለን አገልግለን ፤ታላቅ ሃገር እንገነባለን!!
እኔ የቱ ጋር ነኝ?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!
መልካም የአገልጋይነት ሳምንት ይሁንልን!!
ፐብሊክ ሰርቪስ ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም
*****************
አገልግሎት አሰጣጥ ምንድ ነዉ?
የአገልግሎት አይነቶች
የአገልግሎት አይነቶች ቁሳዊ(ማቴሪያል) እና ሰብአዊ(ፐርሰናል) ተብለዉ በሁለት የሚከፈሉ ሲሆን ቁሳዊ(ማቴሪያል) የምንለዉ የአገልግሎት አሰጣጠ ተጨባጭ የሆነዉን ወይንም የሚዳሰሰዉን የአገልግሎት አሰጣጥ የሚያሳይ ይሆናል ለምሳሌ ለአገልግሎት የሚከፈል የገንዘብ ክፍያ፤አገልግሎቱ የሚወስደዉ ሰዓት፤የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እና መሰል ተግባራትን የሚያካትት ይሆናል።
የሰብአዊ አገልግሎት የምንለው ደግሞ የማይጨበጠዉን (የማይዳሰሰዉን የአገልግሎት ሂደት ይሆናል ለአብነትም የሰዉነት እንቅስቃሴ ፈገግታ፤በጥሞና መናገር እና ማዳመጥ፤ ለተገልጋዩ ትኩረት እና ክብር መስጠት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
ይህንንም ተከትሎ አገልግሎት ሰጪዉ የላቀ እና የተዋጣለት አገልግሎት ለመስጠት ለሁለቱም አይነት አገልግሎቶች ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ማለት ነዉ።
ስለሆነም በአንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማረጋገጥ የተቋሙን፤የተቋሙን ሰራተኛ እና የተገልጋዩን ጥረት ይፈልጋል።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለተገልጋይ የሚሰጡትን አገልግሎት በጥራት በብቃት እና ቀጣይነት ባለዉ መልኩ ለማ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከአዘርባጃን መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስ ልኡክ ቡድን ጋር መከረ፡፡
አዲስ አበባ ህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም
**********
ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የከተማችን አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ በሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በቀጣይም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማረጋገጥ የተያዘውን እቅድ ከግብ ለማድረስ መወሰድ ስላለባቸው ተሞክሮዎች ከልእኩ ጠይቋል፡፡
የአዘርባጃን ልኡክ በበኩሉ በአዲስ አበባ ከተማ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር አበረታች ጅምሮች መመልከቱን ገልፆ በተለይም ሰፊ ቁጥር ያለው የከተማዋ የመንግስት ሰራተኛ አምራች በሚባለው የእድሜ ክልል ላይ መሆኑ በራሱ ትልቅ ሀብት እንደሆነ ጠቁሟል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ልኡኩ በአዘርባጃን ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ተግባራዊ የተደረጉ እና መወረስ የሚገባቸውን ተሞክሮዎች እንደሚከተላዉ አካፍሏል፡፡
አዘርባጃን አጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሲሆን ወደ ግማሽ ሚሊዮን ወይንም 500ሺህ ገደማ የሚጠጋ የመንግስት ሰራተኛ አላት፡፡
አዘርባጃን የፈጠራ ሽግግር ሀገር (the land of innovation) በሚል ቅፅል ስም ትታወቃለች፡፡
ይህንንም ተከትሎ የአዘርባጃን ልእክ እንዳስታ
በዓለም 44ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ የቱሪዝም ሳምንት በማስመልከት የጎዳና ላይ ትርዒት ተካሄደ
ከ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ!
******
ጥቅምት 18/2016 ዓ. ም(ባ.ኪ.ቱ ቢሮ)
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በዓለም ለ44ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ የሚከብረዉን የቱሪዝም ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ‹‹ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት - አረንጓዴ ልማት ለቱሪዝም›› በሚል መሪ ቃል የአለም የቱሪዝምን ቀን በተለያዩ ፕሮግራሞች እያከበረ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ማክሰኞ ጥቅምት 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በተለየ መልኩ ከሁለት ሚሊየን በላይ ታዳሚ በሚገኙበት ለማክበር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ በመሆኑ ኑ አብረን ስለከተማችን ቱሪዝም እንወቅ፤ እንመካከር ይልዎታል።
#ቱሪዝም#ለአረንጓዴ_ልማት!!!
ከ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!
እንኳን ለ 116ኛው ዓመት የሠራዊት ቀን አደረሳችሁ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ!