15/01/2025
ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመስኖ ልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ- ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2017(ኢዜአ)፡- ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመስኖ ልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ ገለጹ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶይስሃቅ አብዱልቃድር በመተከል ዞን ፓዊ ወረዳ የመስኖ ልማት ስራዎችን ጎብኝቷል።
አቶ ጌታሁን በመተከል ዞን ፓዊ ወረዳ በመስኖ እየለሙ የሚገኙ የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰብሎችን በክላስተር የማልማት ስራም ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባም ገልጸዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድር፤ እንደ ሀገር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ የተጀመረውን የኢኮኖሚ አቅም ለመገንባት የመስኖ ልማት ስራዎችን ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
የፓዊ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ አሰፋ በወረዳው የተገኘውን ሰላም በመጠቀም የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ አበረታች የልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።