Ethio Jobs Ads and Online Market

Ethio Jobs Ads and Online Market Online Jobs and vacancy. Give information on jobs and opportunities, fun and educ content.

02/02/2025
02/02/2025

ሰበር ዜና ...
የብል**ና ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።
comment
1. ዜናውን ማን ሰባበረው ?
2. በጣም ነው እንዴ የተሰበረው ?
3. ፉክክሩ ከባድ ነበር

02/02/2025

የወንዶች ጉዳይ ...
ጀርመን በፍቅር አጋሮቻቸው ጥቃት ለሚፈጽምባቸው ወንዶች መጠለያ ማዘጋጀት ጀመረች።

በ"ወንዶች መጠለያዎቹ" በሴቶች አካላዊ፣ ወሲባዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወንዶች ብሶታቸውን የሚተነፍሱበት እድል ተመቻችቶላቸዋል።

በትዳር እና የፍቅር አጋራችን ወሲባዊ ትንኮሳና ጥቃት ተፈጽሞብናል፤ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት ደርሶብናል የሚሉ ወንዶች እየተበራከቱ ነው።

የጀርመን ግዛቶችም ይህ በወንዶች ላይ የሚፈጸም የቤት ውስጥ ጥቃት እየጨመረ መሄድ አሳሳቢ ነው በሚል ለመፍትሄው እየተንቀሳቀሱ ነው ተብሏል።
© Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

መህቡባ/ቢሊሌ - የጀርመናዊውን ልዑል ልብ አሸፍታ ከባርነት ለልዕልትነት የታጨች ውድ የኦሮሞ ልጅ ጉማ በምትባል መንደር እ.ኤ.አ. በ1820 ስትወለድ ቤተሰቦቿ "ቢሊሌ" የሚል ስም አውጥተውላ...
02/02/2025

መህቡባ/ቢሊሌ - የጀርመናዊውን ልዑል ልብ አሸፍታ ከባርነት ለልዕልትነት የታጨች ውድ የኦሮሞ ልጅ

ጉማ በምትባል መንደር እ.ኤ.አ. በ1820 ስትወለድ ቤተሰቦቿ "ቢሊሌ" የሚል ስም አውጥተውላት ነበር። ትርጉሙም "ቆንጆ" "የምታምር" እንደማለት ነው። መህቡባ ማለት ደግሞ በአረብኛ "ተወዳጇ" ማለት ነው።

መህቡባ እድሜዋ 15 ዓመት ሲሞላት እ.ኤ.አ. በ1835/36 በተነሳ የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት አባቷንና ስድስት ወንድሞቿን አጣች። በ1837 በለጋነት እድሜዋ በእሳት ቃጠሎ ከወደመው የትውልድ መንደሯ በባሪያ ፈንጋዮች ተፈንግላ ከእህቷ ጋር ተቆራኝታ ወደ ጎንደር ከተወሰደች በኋላ ለሽያጭ ልትቀርብ በሱዳን ካርቱም አድርጋ ወደ ካይሮ አቀናች።

በ1837 የጀርመኑ ልዑል ኸርማን ፉርስት ቮን ፐክለር-ሙስካው ወደ ሰሜን አፍሪካ ጉዞ አድርጎ ነበር። በካይሮ ቆይታው የቱሪስቶች ተወዳጅ ስፍራ ወደሆነው የካይሮ የባሪያ ገበያ ቦታ ይሄዳል። በእዛም በባርነት ለሽያጭ በቀረበች አንዲት ጉብል የኦሮሞ ልጅ ውበት ይማረካል። ወዲያው ተደራድሮ ከገዛት በኋላ አገልጋዬ ናት በማለት ዋሽቶ ከእራሱ ጋር አብራው እንድትጓዝ አደረገ።

ልዑሉ በመህቡባ ፍቅር ተንበረከከ። ልዑሉና መህቡባ ወደ ፍልስጥኤም፣ ሶርያ እና ኢስታንቡል አብረው ተጉዘዋል። ልዑሉ ተፈጥሮ ለመህቡባ በለገሰቻት ሞገስና የአውሮፓውያንን ባህል ለመልመድ በምታሳየው ፍላጎት ተደምሞ ነበር። እሷም ባልጠበቀችው አዲስና ያልታሰበ ሁኔታ ደስተኛ ሆና ነበር።

አውሮፓ እንደደረሱ ለተወሰነ ጊዜ በቡዳፔስት ቆይታ አድርገው ነበር። በእዛም መህቡባ የቅዱስ ጥምቀት ስነስርዓት እከናውናለች። ልዑሉም መህቡባን ለተወሰነ ጊዜ በቪየና ወደሚገኝ ጥሩ ትምህርት ቤት አስገብቷት የትምህርት ቤቱን መነኩሴዎች አውሮፓዊ አኗኗርን እንዲያስተምሯት ነገራቸው። እሷም ተፈጥሮ በሰጠቻት ፀጋና ንቃት በትምህርቷ በመጎበዝ ሁሉንም አስደስታለች። የገባችበት ሁሉ አካባቢውን በፈገግታዋ ታደምቅ ነበር። ለቋንቋ የተሰጠች ስለነበረች ጣሊያንኛ በቶሎ ለመደች። አብረዋት ሊሆኑ የሚወዷትና በተፈጥሮ ገርና ደግ ነበረች።

ማህበረሰቡም የልዑሉንና የልዕልቷን ግንኙነት በቅንነት ተቀብሎ የመህቡባ አስደናቂ ውበት ያደንቅ ጀመረ። የቪየና ጣእም ሆነች፣ ጋዜጦችም ስለሷ አድንቀው ይፅፉ ነበር። የወሬ ሁሉ ማድመቂያም ሆነች። ወደ ንጉሱ ዙፋን በተወሰደች ጊዜም ይሁንታንና ግርማ ሞገስን አገኘች። ሁሉም ሰው ወደዳት።

ይሁን እንጂ መህቡባ ምግቡንና ቀዝቃዛውን የአውሮፓ አየር መልመድ አቃታት። በጊዜ ሂደትም በሳንባ ምች ተይዛ በፅኑ ታመመች።

ልዑሉ መህቡባን ለሚንከባከበው ሃኪም ጥብቅ ክትትል እንዲያደርግላትና ስለ እርሷም እንዲያሳውቀው አዝዞት ለሥራ ወደ በርሊን ተጓዘ። ከሁለት ቀናት ቆይታ በኋላ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 27 ቀን 1840 የመህቡባ አገልጋይ የመህቡባን መኝታ ክፍል መጋረጃ ስትገልጥ መህቡባን ሞታ አገኘቻት። ብቻዋን ሞታ ተገኘች። በትልቁ አልጋ ላይ እንደ ትንሽ ምስል ትታይ ነበር። በአቅራቢያው በሚገኝ መካነ መቃብርም ተቀበረች። በመቃብሯም ላይ "መህቡባ" ብቻ የሚል ፅሁፍ ያለው ምልክት ተደረገላት። መካነ መቃብሯን በየአመቱ ሺህዎች ይጎበኙታል።

ልዑሉ ስለ መህቡባ ሞት ለጓደኛው በፃፈው ደብዳቤ "ሰው መውደድ እችላለሁ ብዬ ከማስበው በላይ ወድጃት ነበር። ሞቷም ጥልቅ ስቃይ ውስጥ ከትቶኛል። እርሷ ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች" በማለት መሪር ሃዘኑን ገልጿል።

ፀሐፊው : - Tilahun Girma Ango ነው
-------------------------------------------------------------

02/02/2025

Il governo Etiope è un bugiardo inaffidabile.

02/02/2025

Le gouvernement Éthiopien détruit l'Éthiopie.
02/02/2025

02/02/2025

የጅቡቲው ድሮን አፋር ክልልን የደበደበው በኢትዮጵያ መንግስት ይሁንታ ነው ።
ጃዋር መሐመድ
( from Zehabesha )

ይህ ቤት ምን ተብሎ ይጠራል ?
02/02/2025

ይህ ቤት ምን ተብሎ ይጠራል ?

An Ethiopian hero Oballa Nyigwo, from the Anuak, Gambela. ኢትዮጵያዊው ጀግና የጋምቤላ ተወላጅ ሰይፉን እንደያዘ
02/02/2025

An Ethiopian hero Oballa Nyigwo, from the Anuak, Gambela.
ኢትዮጵያዊው ጀግና የጋምቤላ ተወላጅ ሰይፉን እንደያዘ

ይህ እንግሊዛዊ ጦሩን እየመራ መጥቶ ትእቢተኛውን የኢትዮጵያ ንጉሥ ገጠመ።
02/02/2025

ይህ እንግሊዛዊ ጦሩን እየመራ መጥቶ ትእቢተኛውን የኢትዮጵያ ንጉሥ ገጠመ።

የቲክቶክ ባለቤት ቻይናዊው Shou Zi Chew
02/02/2025

የቲክቶክ ባለቤት ቻይናዊው Shou Zi Chew

01/02/2025

መንግስት ግን ታታሪ ነው። ከኮሪደር ልማቱ በተረፈችው ትንሽ ሠአት ታዋቂ ሰዎችን ወደ እስር ቤት ያግዛል።

በሔድክበት ሁሉ:እየተከተሉአፍህን ለጉመው:አትናገር ካሉ።እና?...እጅና እግርህን በካቴና አሥረው:እሥር ቤት ከጣሉህጠላቶችህ ናቸውበገዛ ሕሊናቸው አላማ አቋምህን  እውነትክን እያዩታሥረው የሚገ...
01/02/2025

በሔድክበት ሁሉ:እየተከተሉ
አፍህን ለጉመው:አትናገር ካሉ።
እና?...
እጅና እግርህን
በካቴና አሥረው:እሥር ቤት ከጣሉህ
ጠላቶችህ ናቸው
በገዛ ሕሊናቸው አላማ አቋምህን እውነትክን እያዩ
ታሥረው የሚገኙት:እየመሰላቸው አንተን ያሰቃዩ።
እናም እንዳታምን
ፍጹም እንዳይመሥልህ
አልታሠርክም አንተ:አንተ ነጻ ሰው ነህ።

Ephraim soliana

01/02/2025

የኢትዮጵያ ህዝብ ሦስት አይነት ነው ይባላል።
ታስሮ የተፈታ
አሁን እስር ቤት ያለ እና
ወደፊት የሚታሠር !!!
ምሥራቅ ተረፈ ታሠረች።
" ሰመረ ባሪያው " ታሠረ።

የአርሴናል እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ዲክላን ራይስ የተባለው ኮከባቸው ሸንቃጣና መልከ-መልካም ሴት እንዲያገባ ሁሌም አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ።.....እሱስ ምን አለ❓❓የሱ ምላ...
01/02/2025

የአርሴናል እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ዲክላን ራይስ የተባለው ኮከባቸው ሸንቃጣና መልከ-መልካም ሴት እንዲያገባ ሁሌም አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ።.....እሱስ ምን አለ❓❓
የሱ ምላሽ የሚከተለው ነው። 👇

"እኔ እና Lauren Fryer ከሃይስኩል ጀምሮ ብዙ ጣፋጭ የፍቅር ጊዜያትን በጋራ አሳልፈናል። ያኔ እኔ በነበረኝ አስቀያሚ የሰውነት አቋም የተለያዩ ትችቶች ሲሰነዘሩብኝ እሷ ግን ማራኪ የልጅነት ውበቷን ይዛ ከኔ ዘወር አላለችም...ይልቁንም ከኔ ጋር በፍቅር ፀንታ ቆመች።"

"አሁን ላይ በወሊድና በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች የ Lauren Fryer ተክለ-ሰውነት እንደ ፊልም አክተሪሶች እና ሞዴሊስቶች ሳቢና ማራኪ ላይሆን ይችላል። ግን እሷ ማለት ታማኝ ሃቀኛ እና ከውስጥም ከውጭም ውብ የሆነ ስብዕናን የተላበሰች ሴት ነች።"

"....በርግጥ ደጋፊዎች የተለያዬ አስተያዬት ይሰነዝራሉ....እኔ ልነግራቸው የምፈልገው Lauren Fryer ለኔ ምቹ፣ አስፈላጊና ህይወቴን የተድላና የፍሰሃ ያደረገች የረጅም ጊዜ የህይወት አጋሬ መሆኗን እወቁልኝ እላለሁ።"

👉አንዳንድ በስፖርቱ ዓለም ዝናቸው ጫፍ የደረሱ ተጨዋቾች የቅንጦት ህይወት እየመሰላቸው ሞዴሊስቶች፣ አርቲስቶች...እያሉ ሴት ሲያማርጡ የዲክላን ራይስ ታማኝነትና የፍቅር ጽናት ለወጣቶች ያስተምራል ብዬ አቀረብኩላችሁ።

👉 ወዳጄ ልቤ የዛሬ ገጠመኝህ ትናንትህን አስረስቶ የነገ ውድቀትህን እንዳያፋጥን...ታማኝና ቅን ሁን እልሃለሁ!!

✍️ @አለበል ንጋቱ

01/02/2025

Tewodros Teklearegay የኮንዶሚኒየም ቤት እንዲሰጠው የ አ አ ከንቲባን ጠይቋል።

እናታችንን አፋልጉን************************ "እኚህ የ80 ዓመት እድሜ ባለፀጋ እናታችን  #ሌንሴ ኦርዶፋ ይባላሉ! አርብ ጥር 23 ከመካኒሳ ቆሬ አካባቢ ጠፍተውብናል!እባካችሁን...
01/02/2025

እናታችንን አፋልጉን
************************
"እኚህ የ80 ዓመት እድሜ ባለፀጋ እናታችን #ሌንሴ ኦርዶፋ ይባላሉ! አርብ ጥር 23 ከመካኒሳ ቆሬ አካባቢ ጠፍተውብናል!እባካችሁን ከጭንቅ አውጡን🙏 "
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

😭😭😭

0913267738 ታደሉ
+251914454243 ኤደን



በማድረግ እናታችንን አፋልጉን ።

የ 2005 የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ ነኝ። በቂ ቁጠባ አድርጌያለሁ። ከንቲባዋ ቤት እንዲሰጡኝ መልእክቴን አድርሱልኝ።
01/02/2025

የ 2005 የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ ነኝ። በቂ ቁጠባ አድርጌያለሁ። ከንቲባዋ ቤት እንዲሰጡኝ መልእክቴን አድርሱልኝ።

Address

Bole Road
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Jobs Ads and Online Market posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Jobs for everybody.

Educated people are expected to be better than others.