Ethio Jobs Ads and Online Market

Ethio Jobs Ads and Online Market Online Jobs and vacancy. Give information on jobs and opportunities, fun and educ content.

"ቆንጆ አግብቼ  ላትጠቅመኝ ባለ መኪና ነጠቀኝ" ይላቅ ሀይለ ማርያም። ጥቅምት 1/1954 ዓ.ም
30/12/2024

"ቆንጆ አግብቼ ላትጠቅመኝ ባለ መኪና ነጠቀኝ" ይላቅ ሀይለ ማርያም።

ጥቅምት 1/1954 ዓ.ም

30/12/2024

የተሻለ ማደግ ሲገባቸው በየጊዜው እየቀጨጩ ያሉ የሀገራችን ኢትዮጵያ ከተሞች : Mojo Axum Fiche Alem-Ketema Gimbi Hosanna Shambu Bichena Bedele Ambo Debre-Markos Dila Gimbi Gubba Gura-Ferda Jinka Adwa Durame Kibre-Mengist Kombolcha Konso Maji Ziway Mekane-Selam Mettu Negele Borena Nekemte Robe Woldiia Shashemene Shire Axum Yirgalem

30/12/2024

Messi ነው ወይስ Ronaldo ነውየዘመናችን GOAT???
( ሳሞኑን የፈረንሳዩ League 1 ክርክሩን ተቀላቅሏል)
በርግጥ Messi ፈጣሪ ባርኮታል በዋንጫ !!!)

29/12/2024

ማደግ ሲገባቸው በየጊዜው እየቀጨጩ ያሉ ከተሞች :-

Alem Ketema Hosanna Fiche Bichena Bedele Debre Markos Dila Gimbi Gubba Gura Ferda Jinka Kibre Mengist Kombolcha Konso Lafto Maji Mekane Selam
Mettu Modjo Negele Borena
Nekemte Robe Shashemene
Shire Weldiya Yirgalem Zway

29/12/2024

አንድ ሰው የቤቱ ቁልፍ ይጠፋበታል። ይህ ሰው የጠፋበትን ቁልፍ በቀላሉ ለማግኘት በመመኘት ብርሃን ወዳለበት ሄዶ መፈለግ ይጀምራል።

ይህንን ያየ በመንገድ ተላላፊ ሰው፥ "ምን እያደረግህ ነው?" ሲል ይጠይቀዋል።

መልስ፤ "ቁልፌ ጠፍቶ እየፈለግሁኝ ነው።"

ጠያቂው፤ "የት ነው የጠፋብህ?"

መልስ፤ " እዚያ ቦታ ነው የጠፋብኝ።"

ጠያቂው፤ "ታዲያ ለምን እዚያው የጠፋብህ ቦታ አትፈልግም?"

መልስ፤ " እዚያ ጨለማ ስለሆነ ለማግኘት ይከብዳል። እዚህ ብርሃን ስላለ ።"

29/12/2024

ለአውሮፓ አስደንጋጭ ዜና !!
ሩሲያ Albania Andorra Armenia Austria Belarus Cyprus Estonia Bosnia-and-Herzegovina
Bulgaria Croatia Finland Georgia Iceland Ireland Kosovo Latvia Liechtenstein Lithuania Monaco Luxembourg Malta Moldova Montenegro North-Macedonia
Slovakia Slovenia

የተባሉ የአውሮፓ ሀገራትን ልትወር ነው። ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ፓናማን ግሪንላንድንና ካናዳን ወርረው ወደ አሜሪካ ሊጠቀልሏቸው ተዘጋጅተዋል።

የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ትሩፋቶችብላቴን ጌታ ኅሩይ በተለይ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጀመርያ ሩብ በሥነ ጽሑፍና በሌሎች የአስተዳደር ጉዳዮች ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ነበሩ...
29/12/2024

የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ትሩፋቶች

ብላቴን ጌታ ኅሩይ በተለይ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጀመርያ ሩብ በሥነ ጽሑፍና በሌሎች የአስተዳደር ጉዳዮች ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ነበሩ፡፡ ከአዲስ አበባ ከንቲባነት እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት በብቃት እንዳገለገሉ ይነገርላቸዋል፡፡

በሸዋ መርሐ ቤቴ ጊቦ ገዳም በተባለ ሥፍራ በ1871 ዓ.ም. የተወለዱት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ከሃያ ያላነሱ መጻሕፍትን በመጻፍ ለአገራቸው አበርክተዋል፡፡ ከሥራዎቻቸው መካከል ‹‹ኢትዮጵያና መተማ (የአፄ ዮሐንስ ታሪክ ባጭሩ)፣ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የዓድዋ ድል፣ ‹‹ወዳጄ ልቤ፤ የሰውን ጠባይና ኑሮ በምሳሌ የሚገልጽ፣ ‹‹የልዕልት ወይዘሮ መነን መንገድ በኢየሩሳሌምና በምስር፣ ‹‹በኢትዮጵያ የሚገኙ በግዕዝና በአማርኛ ቋንቋ የተጻፉ የመጻሕፍት ካታሎግ፣ ‹‹ማኅደረ ብርሃን ሀገረ ጃፓን፣ ‹‹ለልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ፣ ‹‹የልብ አሳብ፤ የብርሃኔና የጽዮን ሞገስ ጋብቻ፣ ‹‹ጎሀ ጽባሕ፣ ‹‹አዲስ ዓለም፤ የቅኖችና የደግ አድራጊዎች መኖሪያ ይገኙበታል፡፡

ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ዕውቀትን ለመሸመት አዳዲስ ነገሮችን ለማወቅ ያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ ሰዎች የተለያዩ ፍረጃዎችንና ትችቶችን ይሰጧቸው ነበር፡፡ ለአብነትም ዓረብኛ ቋንቋን ለመማር ሲሞክሩ ‹‹ይኼ ሰው ሊሰልምነው እንዴ››፣
‹‹ፈረንሣይኛና እንግሊዝኛ ለመማር ሲጥሩ ደግሞ ካቶሊክ ሊሆኑ ነው›› በማለት ያሟቸው ነበር፡፡

ሌላው የጉዞ ማስታወሻ በሚጽፉበት ወቅት ጃፓን፣ ኢየሩሳሌም፣ ግሪክ፣ ፈረንሣይና ለንደን ሲሄዱ ያጋጠማቸውን ልክ እንደ መዕዋለ ዜና ዘጋቢ የገጠማቸውን ገጠመኝ፣ የተደረገላቸውን አቀባበል፣ ያዩትንና የሰሙትን ይከትቡ ነበር።

የጠቅላላ ዕውቀት መጻሕፍትን በሚያዘጋጁበት ወቅት ደግሞ ኢትዮጵያውያን ወደ ውጭ አገር በሚሄዱበት ወቅት በዕውቀት ጉድለት ምክንያት አገርን እንዳያሰድቡ አስቀድመው ምን ማድረግ እንዳለባቸው አሳይተዋል፣ በዚህም አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ ውጭ አገር በሚሄድበት ወቅት ከዚህ ቀድሞ ያላየውን አዲስ ነገር ሲመለከት ትልልቅ ሕንፃዎችን፣ ትልልቅ የምግብ ገበታዎችን በሚመለከትበት ወቅት አንድ ጊዜ ካየ በኋላ ዝም ማለት ወይም ደግሞ ደጋግሞ አለማፍጠጥ እንዳለበት ምክር ይሰጡ ነበር፡፡
ይህም ወደ ውጭ አገር የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ስህተት ሠርተው የአገርን ክብር እንዳያበላሹ በማሰብ የፃፉት ምክር አዘል ጽሑፍ ነው፡፡

ኅሩይ ወደ አገር ቤት የሚመጡ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር የሚቀድማቸው አልነበረም፡፡ ስልክ አዲስ አበባ በገባበት ወቅት በግላቸው (በቤታቸው) አስገብተው ሲጠቀሙ ከነበሩ አራት ሰዎች መካከል እሳቸው አንዱ ነበሩ፡፡ በሌላ በኩል ሴት ልጆቻቸውን ወደ ውጭ አገር ልከው ማስተማር ከቻሉ የመጀመርያዎቹ ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ፡፡ በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ሴት ልጅ አግብታ መውለድ፣ ሙያም መማር እንጂ እንዴት ለትምህርት ተብሎ ወደ ውጭ አገር ይልካሉ በማለት ሲተቿቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡

በፋሺስት ጣሊያን የወረራ ዘመን (1928-1933) ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር በእንግሊዝ በስደት ሳሉ በ1931 ዓ.ም. ያረፉት ብላቴን ጌታ ኅሩይ፣ ቀብራቸው በባዝ ከተማ ሉግዘምበርግ ሲፈጸም፣ በሥርዓተ ቀብር ላይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባሰሙት ዲስኩር እንዲህ ብለው ነበር፦

‹‹ታላቅ ነህ ሳልልህ ብቀር ሥራዎችህ ቀድመውኝ ይናገራሉ፡፡ ይህ የአዳም ልጆችን ወግ ሲቀበል የምታዩት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በሀገራችን ሥርዓት በመልካም አያያዝ ያደገ፣ ከኢትዮጵያም ከፍ ከአሉት ሊቃውንት የሚቆጠር ነው፡፡ ብልኃቱንና ትጋቱንም ለመልካም ሥራ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ስላደረጋቸው በመንግሥታችን ሥራ ለመመረጥና ወደ ታላቁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ለመድረስ ችሏል፡፡ በጊዜውም የጻፋቸው መጻሕፍት ከፍተኛ ባህሪውን የሚገልጹ ይልቁንም በቤተ ክህነትና በታሪክ ዕውቀት በዓለም ሊቃውንት ዘንድ የታወቀና የተከበረ አደረጉት፡፡ ለምታውቁት ሰው ከታሪኩ ከዚህ የበለጠ ልነግራችሁ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡››
በኋላም ጣሊያን ሲወገድ በ1940 ዓ.ም. አፅማቸው ፈልሶ በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል፡፡

ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባነት፣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት፣ በቀይ መስቀል፣ የውጭ ዜጎችን በሚዳኝ ልዩ ፍርድ ቤት፣ በኢትዮጵያ ባንክ አስተዳደር ምክር ቤት ውስጥ በፕሬዚዳንትነት፣ ከሃያ በላይ መጻሕፍትንም በማሳተም ለአገር ልማት አገልግለዋል፡፡
ኅሩይ ኢትዮጵያ ወደ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ስትቀላቀል ልዑክ በመሆን፣ በመጨረሻም በጣሊያን ስትወረር አቤቱታዋን ለማሰማት ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር ሰፊ ጥረት ያደረጉ የአገር ባለውለታና በጥንታዊ የአገር በቀል ዕውቀቶችና በዓለም አቀፋዊ ጉዞና ንባብ የተቀረጹ ነበር።

የኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የሚገኘውን የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ስመጥር ጸሐፊ፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ መኖሪያ ቤትና ግቢን ተረክቦ የቀድሞው ይዞታውን ሳይለቅ እያለማ እየተገለገለበት እንዳለና በዚህ ታሪካዊ ሕንፃ ውስጥም በስማቸው የሥነ ጥበባት ማዕከልን በማቋቋም የተለያዩ የሥነ ጥበባት ዘርፎችን በሳይንሳዊ መንገድ የማዘመን ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል።

The former residence of the late Blaten Geta Hiruy Woldeselassie (BGHWS) is an adequately fenced large compound covering over 13,500 square meters of land and buildings consisting of: -The main house that was formerly the residence of BGHWS,
-A Birds zoo, a miniature castle built of bricks,
-A modern lion zoo, built of bricks, and
-Two deep wells and a large water reservoir.

The residence was built between the 1920s and 1930s. It was one of the modern architectural structures in that period for Addis Ababa. The building is partially connected to the mound, so the front side view has the graceful look of the G+1 building, and when turning at the back side of the building it looks like a modest wide villa. The building is made from bricks, strong rock pieces, and oak wood. It has more than 17 rooms of different sizes and shapes.

Since 2012, the building has been serving as the headquarters of the Ethiopian Academy of Sciences, with the Academy as the custodian of its heritage. As a result, the Academy has established a Center for Creative Arts named after BGHWS in the residence. This center has a mini-museum in one of the rooms of the building to commemorate Hiruy. The building also houses exhibition space, library, residence space for artists, offices, and more.
______________
የምስል መግለጫ፦
• ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ

29/12/2024

ትልቅ የነበሩ አሁን እየከሠሙ ያሉ ከተሞችን ምድብ አዋሣ ተቀላቅላለች። ልጆቿም ሸገር መጥተው የኮዬ ፈጩ ጫኝ አውራጅ ወጣቶች ንቀው የተውአቸውን የሸክም የጋሪ እና የጽዳት ሥራዎች እየሞካከሩ ነው። ክልል ይገባናል በሚል "ትግል" ብዙ ሺህ ወላይታ አማራ ጉራጌ ስልጤ ሀዲያ ከምባታ ጌድኦና ጋሞ ተገድሎበታል። በማይመለከታቸው ጉዳይ !!

29/12/2024

አልጸጸትም!! የጃዋርን መጽሃፍ ወደ አማርኛ የተረጎመው ሰው ለአማራውና ለሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያስተላልፍ የፈለገው መልዕክት ያለ ይመስላል።
Geleta Gammo

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የነዳጅ ዘይት የቁፋሮ ሳይት እየጎበኙ ነው።በግራ ዳር እጃቸውን ወኋላ አጣምረው የቆሙት ራስ አበበ አረጋይ ሲሆኑ በቀኝ በኩል ጠርዝ ላይ የቆሙት ደግሞ ራስ መስፍን ስለሺ ...
29/12/2024

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የነዳጅ ዘይት የቁፋሮ ሳይት እየጎበኙ ነው።

በግራ ዳር እጃቸውን ወኋላ አጣምረው የቆሙት ራስ አበበ አረጋይ ሲሆኑ በቀኝ በኩል ጠርዝ ላይ የቆሙት ደግሞ ራስ መስፍን ስለሺ ናቸው። መሐከል ላይ ከጃንሆይ አጠገብ የቆሙት ደግሞ ጸሐፌ ትዕዛዝ ተፈራ ወርቅ ኪዳነ ወልድ ናቸው።

ኢትዮጵያ ነዳጅ አውጥታ እንዳትበለፅግ አለም ተባብሮ ደቆሳት። ደሃ ለማኝ እንድትሆን ተፈረደባት። ያሳዝናል 😢

1947/48 ዓ.ም
ፎቶ ምንጭ: ታሪካችን

ሲስተም ይኑርህ!ትልልቅ ነገሮች በስርዓት የሚመሩ ናቸው። ስርዓት የስኬት መሠረት ነው። ስርዓት የረብሻ ጠላት ነው። የመሬትና የፀሓይ ግንኙነት ስርዓት አለው። የወቅቶች መፈራረቅ ስርዓት አለው...
29/12/2024

ሲስተም ይኑርህ!

ትልልቅ ነገሮች በስርዓት የሚመሩ ናቸው። ስርዓት የስኬት መሠረት ነው። ስርዓት የረብሻ ጠላት ነው።

የመሬትና የፀሓይ ግንኙነት ስርዓት አለው። የወቅቶች መፈራረቅ ስርዓት አለው። መሽቶ የመንጋት ጉዳይ ስርዓት አለው።

ሰውነትህም ስርዓት አለው። የአተነፋፈስ ስርዓት አለህ፣ የደም ዝውውር ስርዓት አለህ፣ የነርቭ ስርዓት አለህ፣ የምግብ አፈጫጭና አሰለቃቀጥ ስርዓት አለህ።

መንግስትም፣ ቤተሰብም፣ ዓለምም ሁሉም የሚተዳደሩት በስርዓት ነው።

ሲስተም (ስርዓት) የሌለው ጉዳይ ለችግር የተጋለጠ ነው። ለዚህ ነው ባንኮች ስርዓት ለሌለው ንግድ ለማበደር ዳተኛ የሚሆኑት።

ስርዓት ካለህ ሠራተኞች ይታዘዙሃል፣ አለቆች ያከብሩሃል፣ ባንክ ያበድርሃል፣ ደንበኞች ይጎርፉልሃል።

ስርዓት ግን ምንድን ነው?

ስርዓት አንድ የታወቀን ዓላማ ለመፈጸም በታወቀ መልኩ በተከታታይነት የሚከወን የተለያዩ አካላት ተናብበውና ተጣጥመው በተቀናበረ መልኩ የሚከውኑት ተግባር ነው።

የተለያዩ አካላት ካልተጣጣሙ፣ ካልተናበቡ የስርዓት ችግር አለ። የታወቀ ዓላማ ከሌለ ስርዓት አለ ለማለት አይቻልም። የተለያዩ አካላት ተግባራቸውን የሚፈጽሙበት መንገድ የታወቀ ካልሆነ፣ ተከታታይነት ከሌለው የስርዓት ችግር አለ።

አሁን የመንግስታችን አሠራር ከዚህ አንጻር ሲቃኝ ምን ይመስላል? ስርዓት አለው ወይ? ውሃ ክፍሉ እና የመንገድ ባለስልጣኑ አይናበቡም። የታክስ ቢሮው ባልተገመተና በማይታወቅ መልኩ የታክስ ተመኑን እንዳሻው ይቀያይራል። የትራፊክ ፖሊሶቹ መንገድ ማስተናበር ትተው ከአቅጣጫህ ውጪ ጠርተው ያጋጩህና መንገድ ያስዘጉሃል። ጉድ እኮ ነው!

በ4:00 ሰዓት በረራ ዱባይ ሂድልኝና ጉድ ተመልከትልኛ! በዱባይ ፖሊሶቹን ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር አታያቸውም። በየቦታው "ና ተፈተሽ!" የሚልህ የለም። ያለስጋት ከተማውን ስትዞር ብትውል ጫፍህ ላይ የሚደርስ የለም። ዕቃ ርካሽ ነው፣ ሀገር ሰላም ነው። ያ ሁሉ ደግሞ ታክስ ሳትከፍል እየኖርህ ነው።

በዱባይ "ታክስ መክፈል የዜግነት ግዴታ ነው" የሚል የቀልድ መፈክር የለም። በዱባይ ከደሞዝህ ላይ ታክስ አይቆረጥም። እንዲያውም በዜግነትህ የሚሰጡህ ብዙ ጥቅሞች አሉ።

ዱባይ ከተባበሩት ዐረብ ኤመሬቶች አንዷ ነች።

በቅርቡ የዱባይ እና የአቡዳቢ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ የሚል ወሬ ሽው እያለ ነው። ከእነ ሲስተማቸው ከመጡልን እሰየው ነው። በመጀመሪያ ግን የገቢዎች ቢሮ ሲስተምን ቢለውጡልን ጥሩ ነው።

እንዲያውም ለምን የእኛ የገቢዎች ቢሮ በዱባይ ሰዎች ለምን አይመራም? እስኪ ከምርጫው በፊት ለ1 ዓመት ቢሞከር ጥሩ አይመስላችሁም?

አጼ ቴዎድሮስ ጆን ቤል እና ፕላውዴን የሚባሉ አማካሪዎች ነበራቸው። አጼ ዮሓንስ እንኳ ምክር የሚሰሙ አይመስሉም። አጼ ምንሊክ አልፍሬድ ኢልግ የተባለ የስዊዝ አማካሪ ሰው ነበራቸው። ጃ ምክር በምክር ናቸው። በደርግ ዘመንስ የጦር አማካሪ ከውጭ ሀገር ስናስመጣ ከርመን የለ?

እናም የገቢዎች፣ የኢንዱስትሪ፣ የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የሰላም፣ የትራንስፖርት ሚ/ር መ/ቤቶች ከዱባይ አማካሪ ቢያስመጡ ጠቃሚና ዜጋውን የሚያሳርፍ ስርዓት ይዘረጉልናል ብዬ አምናለሁ።

እኔ ራሴ ለዚህ ሀሳቤ ሊከፈለኝ አይገባም? 🤔

ግዴለም እንዲህ ዝብርቅርቅ ባለ አካሄድ ሩቅ አንጓዝም። የሚሻለው አማካሪ መያዝ ነው።

አማካሪ ይዘን እድገት በሚያመጣ ስርዓት በሰላም ታክስ ሳንከፍል መኖር ይሻለናል። ይህ ደግሞ ቀልድ አይደለም። ይቻላል!

ይህን የመሰለ መሬት፣ ውሃና አየር ይዘን ስንራብ ያሳፍራል።

ችግራችን የሁነኛ ስርዓት እጦት ነው።

ስርዓት የሌለው ህዝብ ምግብ ሳያጣ እርስ በርሱ ይባላል። ስርዓት የሌለው ህዝብ በመሬት ይጣላል። ስርዓት የሌለው ህዝብ በወንዝ ይጣላል። እኛ አሁን የቀረን በአየር፣ በፀሓይ እና በጨረቃ መጣላት ነው።

ግዴለም የዓለም ህዝብን በሰላም የሚያኖሩትን ዱባዮች ጥሩልንና አማካሪ አድርጋችሁ ያዙልን። ታድያ ስሟቸው።

ታክስ ዜሮ ሲሆን ያኔ ዱባዮቹ እንደመጡ እናውቃለን። የቱሪዝም ገቢ ሲጨምር ያኔ ዱባዮቹ እንደመጡ እናውቃለን። የውጭ ሀገር ነጋዴ ሲበዛ ያኔ ዱባዮቹ እንደመጡ እናውቃለን። ፋብሪካ ሲበዛ እና የዕቃ ዋጋ ሲረክስ እና የሥራ ዕድል ሲጨምር ኬንያውያን ለሥራ በሀገራችን ሲርመሰመሱ ያኔ ዱባዮቹ እንደመጡ እናውቃለን።

ዱባዮቹ በምን ይበልጡናል? ዱባዮቹ ስርዓት ያውቃሉ። ከምንም ተነስተው ትልቅ ነገር ይፈጥራሉ። ወደ ውጤት የሚያምዘገዝግ ሀሳብ አላቸው!

እነርሱ ባይሆኑ ኖሮ ፀሓይ፣ አሸዋ እና ባህርን ማን ሀብት አድርጎ በንግድ፣ ትራንስፖርት እና ቱሪዝም ከፍ ያለ ገቢ ያገኝ ነበር?

በነገራችን ላይ የኤመሬትስ አየር መንገድ ከእኛ አየር መንገድ በ5 እጥፍ የላቀ ዓመታዊ ገቢ አለው።

ዝ! ዱባዮቹን ጥሩልንማ።

አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ውጤት ያመጣል!

የት ነው ?
29/12/2024

የት ነው ?

"ጀዋር ማለት የመጨረሻ ፈሪ፣ ውሸታም፣ጉረኛ ፣ ተለዋዋጭ እና ይሉኝታ ቢስ የሆነ የሥልጣን ሱሰኛ ነው፣ጃዋር የሚያደንቀው እንጂ የሚያዘው ቄሮ የለውም " ጋዜጠኛ ቤተልሔም ታፈሰ።=========...
29/12/2024

"ጀዋር ማለት የመጨረሻ ፈሪ፣ ውሸታም፣
ጉረኛ ፣ ተለዋዋጭ እና ይሉኝታ ቢስ የሆነ የሥልጣን ሱሰኛ ነው፣ጃዋር የሚያደንቀው እንጂ የሚያዘው ቄሮ የለውም " ጋዜጠኛ ቤተልሔም ታፈሰ።
======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ምንጭ : Ayuzehabesha

15 ቀን ቀረው❗❗Crypto ወደፊት ትልቅ ተስፋ አለው፣ዛሬም አንድ ጥሩ ፕሮጀክት እንጠቁማችሁ። የፕሮጀክቱ ስም seed ይሰኛል፣አንድ seed 1.1$ ነው። እንዳትቆጩ፣አሁኑኑ ከስር የተቀመጠ...
28/12/2024

15 ቀን ቀረው❗❗
Crypto ወደፊት ትልቅ ተስፋ አለው፣ዛሬም አንድ ጥሩ ፕሮጀክት እንጠቁማችሁ።

የፕሮጀክቱ ስም seed ይሰኛል፣አንድ seed 1.1$ ነው። እንዳትቆጩ፣
አሁኑኑ ከስር የተቀመጠውን ሊንክ ክሊክ አድርጋችሁ start በሉ👇👇

t.me/seed_coin_bot/app?startapp=473382500

ያገለገለ pick up መኪና መግዛት ለምትፈልጉ🌷Bank 1.800.000 ሺህ ብር አዋጭ አለበት 🌷ለባለቤቱ ካሽ 1.600.000 ሞዴል 2008 D4D✍️Make:Toyota✍️Model:Hilux ✍...
28/12/2024

ያገለገለ pick up መኪና መግዛት ለምትፈልጉ

🌷Bank 1.800.000 ሺህ ብር አዋጭ አለበት
🌷ለባለቤቱ ካሽ 1.600.000 ሞዴል 2008 D4D

✍️Make:Toyota
✍️Model:Hilux
✍️Year:2008
✍️Engine: D4D
✍️Fuel:Diesel
✍️Plate no.:Code 3
✍️Transmission-Manual
✍️Mileage : KM
✍️Perfect body
✍️Perfect Engine
✍️Accident free.
✍️Condition:Super Excellent

🌷Bank 1.800.000 አዋጭ አለበት
🌷ለባለቤቱ ካሽ 1.600.000
🌷በወር ለባንኩ የሚከፈለው 35ሺህ

🌷Commissio 2%
🌷Tel 0973973838

28/12/2024

እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶች ላይ ተወያይተናል።

28/12/2024

ፈጣሪ ሆይ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ሌት ተቀን በሚሰሩ እባቦች መቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን ሳላስቀምጥ 🌹 የኢትዮጵያን ትንሳኤ ሳታሳየኝ

🙏 እንዳትገድለኝ.🙏

ኢትዮጵያ አትፈርስም✊

አሜን.🙏

28/12/2024

Colonel Goshu Wolde !!!
የጎሬ ፍሬ፣ የየል ምሩቅ፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ አንድነት ጠበቃ ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በአሜሪካ ም/ቤት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ፊት ምስክርነት እየሰጡ ነው - ሰኔ 1983 ዓ.ም

ኮሎኔሉ አሜሪካ በጎሳ ለተደራጁ፣ ለታጠቁ፣ ጠባብ፣ ገንጣይ እና ስታሊናዊ ቡድኖች ኢትዮጵያን ማስረከቧን በመኮነን በለንደን የፈጸመችውን ስህተት በማረም ለኢትዮጵያ አንድነትና ዲሞክራሲ እንድትቆም ጠይቀዋል።

ምንጭ፡
Historic Ethiopia Through The Camera Lens: 1860s - 1990s

Address

Bole Road
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Jobs Ads and Online Market posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Jobs for everybody.

Educated people are expected to be better than others.