አንተነህ አብርሃም

አንተነህ አብርሃም free speech, free spirit.

አትክልት ፣ ናትናኤል እና አንተነህ  የአብርሃም ልጆች
01/12/2024

አትክልት ፣ ናትናኤል እና አንተነህ የአብርሃም ልጆች

የቀድሞ ትምህርት ቤታችን ቦሌ ከፍተኛ ጀርባ ከአዲሱ ስታዲዬም ፊትለፊት "ሶቦስ" የተሰኘ ድንቅ የቁርጥ ስጋ ከጎዲን ጥብስ ጋር ተገባበዝን። ከስጋው ጣፋጭ ጣዕም በላይ የቀረቡልን የበርበሬ ዳታ...
26/11/2024

የቀድሞ ትምህርት ቤታችን ቦሌ ከፍተኛ ጀርባ ከአዲሱ ስታዲዬም ፊትለፊት "ሶቦስ" የተሰኘ ድንቅ የቁርጥ ስጋ ከጎዲን ጥብስ ጋር ተገባበዝን። ከስጋው ጣፋጭ ጣዕም በላይ የቀረቡልን የበርበሬ ዳታ ቫራይቲ የትም ቁርጥ ቤት ያላየሁት ነው። ሶቦስ ከVIP እንግዶቼ ጋር የተለየ እንክብካቤ ተደርጎልኛል።
ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እውቅ ዲፕሎማቶች ጋር የሆድ የሆዳችንን ስናወጋ የሰማብን የለም።
ደግሜም ከአንጋፋው ጋዜጠኛና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ መኮንን ተሾመ ቶሌራ ጋር ስለሀገራችን ተስፋና እድሎች ገለጻ ተደርጎልኛል።
እውቋ አርቲስት አስቴር በዳኔ በምሽት የአዲስ አበባን አዲስ ገጽታ ስታስጎበኘኝ ለውድ የመኪናዋ ነዳጅ አንዳች አልተጨነቀችም። በባለአምስት ኮከቡ ስካይላይት ሆቴል ስትጋብዘኝ ለብሯ አልሳሳችም። እስከ እኩለ ሌሊት የአዲስ አበባን ኮሪደር ልማት ከምርጥ ዝርዝር ማብራሪያ ጋር ስታስረዳኝ የከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤት የፕሬስ ሰክሬታሪያት ሀላፊ ትመስል ነበር። ከቦሌ መንገድ አንስታ በስጢፋኖስ አራት ኪሎ የድል አደባባይን ስታስጎበኘኝ "አየሄው? ያንንስ አየሄው ?" ትለኝ ነበር። ሰባ ደረጃ ጸድቶ በርቷል። በምሽቱ ከከዋክብት ጋር ይነጋገራል። ይህንን አሳምረው የሰሩ ይባረኩ። ብዙ ያሳለፍንበት ራስ መኮንን ድልድይ አሸብርቋል። የተለጠፉ የተኮለኮሉት የወርቅ መሸጫ ሱቆች ተጠርገዋል። የማውቃትን የቦረቅኩባትን ፒያሳን ግን ባይኔ አጣሁዋት። በጣም የምንወዳቸው አንጋፋ ጋዜጠኞች አርቲስቶች በሞት አልፈዋል። ፒያሳም አርጅታ ሞታ ተቀብራ በአዳዲስ ዘመናዊነት ተተክታ ጠበቀችኝ። አስቴር በዳኔ የአድዋ መታሰቢያ በውጭ በኩል ከመኪና ሳንወርድ ስታብራራልኝ በድሮው ጊዜ በቲያትር መድረክ ላይ ተውኔት ከምትሰራበት ወርቃማ እድሜዋ ጋር ሳነጻጽራት ምንም ለውጥ የላትም። የምር ተዋናይ ነች። የግትርነት እና አይቻልም የምትለው ነገር እና እኔ ያልኩት ካልሆነ የምትልበት የልጅነት ጸባዩዋ እስካሁን አብሯት እንዳለ ምስክር ነኝ። በርካታ ታሪክ የተሰራበት የቀድሞ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ቢሮ እየሩሳሌም ህንጻን ሳጣው በድንጋጤ ክው ብዬ ደርቄ ቀረሁ። የማውቀው ሰው የሞተ ያህል ስሜት በውስጤ አጫረ። የኢትዮጵያ ሚኒሊዬም ብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ አባል ሆኜ ድፍን ሁለት ዓመት የሰራሁበት ቢሮዬም ነበር። በቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ዊኒስተን ቸርችል የተሰየመው "ቸርችል" አውራ ጎዳና ቁልቁል ስንመለከት ቀን እንጂ ከምሽቱ ሦስት ሠዐት ያለፈ አይመስልም። የመብራት ፈረቃና መቆራረጥ ታሪክ ሆኖ ቀርቷል። አሁን የመብራት መቆራረጥ ስጋት አይደለም። የሰሩ እጆች ይባረኩ። እስቴርም እንዳለችኝ ይሄንን ልማት ማንም ይዞት አይሄድም። የእኛው ነው።
ወዳጄ የቁምነገሩ ቁምነገረኛ ጋዜጠኛ ታምራት ኃይሉ በበኩሉ እስካለሁበት መጥቶ ከእኔ ጋር ጊዜውን ለማሳለፍ ያለሁበት ለመድረስ አስር ደቂቃ አልፈጀበትም። ታሜም በበኩሉ የክት ሙሉ ልብሱንና ቆዳ ጫማውን እንኳን ሳይቀይር እጅግ በምወደው የቦሌ ጎዳና ማምሻውን በእግር ጉዞ ሽር ብትን ስንል ስለሃገሬ የነበረኝ የመረጃ ጥማት እያሟላ ነበር። ከታሜ ባህሪ ደስ የሚለኝ በየወሬው መሃል "ምን ቢሆን ጥሩ ነው? " የሚላት ነገር ነች።
እውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳና አበጋዝም ጥቂት ካወጋን በኋላ የመታሰቢያ ፎቶ አብሬ የተነሳሁዋቸው ናቸው። የማስታወቂያና ማተሚያ ባለሙያ ለታሪክ አለማየሁ የክብር እስፖንሰሬ ነበር። በወካችን መካከል ያጋጠሙን ጋዜጠኛ ሃብቴ ታደሰና ኦአድ አንዱአለም ጋርም ስለጥንቱ ትዝታችን ስናወጋ ጥርሳችን በደስታ ፈገግታ ያበራ ነበር። አዲስ አበባ ላይ ምሽቱ ሲገፋ ብርዱ ይከፋል። የጀርባ አጥንት ህብለሰረሰር ላይ በረዶ የሰራ ያህል ያንሰፈስፋል። አዲሳባ ወድሻለሁ። ወዳጆች ክብረት ይስጥልኝ።

አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡአዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት በመሆን መመረጣቸው ተ...
19/11/2024

አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት በመሆን መመረጣቸው ተሰምቷል፡፡

የሶማሊላንድ ምርጫ ኮሚሽን የዋዳኒ ፓርቲ እጩ አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።

አብዲራህማን በምርጫው 63 ነጥብ 92 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፉት ሲሆን፥ የወቅቱ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ 34 ነጥብ 81 በመቶ ድምጽ በማግኘት ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

በምርጫው ሂደት ውስጥ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ዋዳኒ፣ ኩልሚዬ እና ካህ ቁልፍ ተዋናዮች ሆነው መታየታቸው ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በሶማሊላንድ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን በመግለጽ ህዝቡ ላሳየው ተሳትፎ አመስግኗል።

አዲስ የተመረጡት ፕሬዚዳንት በሚቀጥሉት ቀናት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ያሳውቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሙስታክባል ሚዲያ ነው የዘገበው፡፡

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባለፈው ሳምንት ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም መካሄዱ ይታወቃል።

12/11/2024

I love USA.

ሰው ነገሮችን የሚያይበት አቅጣጣጫ ይገርማል። የህይወት ዘመን ፕረዝደንት ሆኖ ተቸንክሮ የቀረውን ሰውዬ እነዚህ ሁሉ ሲቀየሩ ያልተቀየረ ጀግና ነው ይሉናል። ምን ብለን መከራከር እንችላለን ?
09/11/2024

ሰው ነገሮችን የሚያይበት አቅጣጣጫ ይገርማል። የህይወት ዘመን ፕረዝደንት ሆኖ ተቸንክሮ የቀረውን ሰውዬ እነዚህ ሁሉ ሲቀየሩ ያልተቀየረ ጀግና ነው ይሉናል። ምን ብለን መከራከር እንችላለን ?

ይሁና እንግዲህ ምን ይደረጋል። ፈጣሪ ከእኛ ጋር ይሁን!!
06/11/2024

ይሁና እንግዲህ ምን ይደረጋል። ፈጣሪ ከእኛ ጋር ይሁን!!

05/11/2024
የካፒቶል ፖሊስ ዛሬ ኖቨምበር 5 በጎብኚዎች መግቢያ በኩል ሰውነቱ ነዳጅ (ቤንዚን/ጋዝ) የሚሽት ሰው ለመግባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትና በፍተሻም እሳት ማቀጣጠያ ቁሶች እንደተገኙበት...
05/11/2024

የካፒቶል ፖሊስ ዛሬ ኖቨምበር 5 በጎብኚዎች መግቢያ በኩል ሰውነቱ ነዳጅ (ቤንዚን/ጋዝ) የሚሽት ሰው ለመግባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትና በፍተሻም እሳት ማቀጣጠያ ቁሶች እንደተገኙበት ተነግሯል:: ይህን ተከትሎም የካፒቶል ጎብኚዎች ማዕከል ለጊዜው ተዘግቷል::

05/11/2024

ይሄው ነው!! አራት ነጥብ።

02/11/2024

በደቦ የሚደረግ የደሞዝ ጭማሪ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። ኑሮ በተወደደ ቁጥር ያንን እየተከተሉ እግር በእግር ደሞዝ መጨመር የዋጋ ግሽበቱን በማባባስ የብሩን የመግዛት አቅም ይጎዳል። መንግሥት ደሞዝ የሚጨምረው ለሰራተኛው ሲሆን ለመንግሥት የማይሰሩት ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ በሚመጣ ግሽበት ጉዳይ ይደርስባቸዋል።

ስለሆነም መንግስት የሚጨምረውን ደሞዝ አዘግይቶ ረጅም ዘመንን ያስቆጠረውን የወር ደሞዝ አከፋፈል ቢቻል ሳምንታዊ ባይቻል ደግሞ በየ15 ቀኑ ማድረግ ይኖርበታል ። ደሞዝ አኑስተኛም ሆኖ በየሳምንቱ አርብ አርብ የሚወጣ ቢሆን ኑሮን ለማረጋጋት አስተዋጽኦ ይጫወታል። ጭማሪው ደግሞ በወር ደሞዝ ላይ ከሚደረግ ይልቅ ለሰዓት ተካፍሎ በአንድ ሰዓት በሚከፈለው ደሞዝ ላይ የሚጨመር ቢሆን የተጋነነ ጭማሪ ሳይታይ ሰራተኛው እጅ ብር ይገባል ማለት ነው። ደሞዝ በእጥፍ የሚጨመር ከሆነ ብሩን መጨመር ማሳወቅ ሳያስፈልግ በቀጥታ በየአስራ አምስት ቀኑ ያንኑ የወር ደሞዝ እንዲያገኝ ቢደረግ ጠቃሚና ግርግር የሚቀንስ ይሆናል። ሃሳቤን በቪዲዩ ላይ መመልከት ይቻላል።

ኢትዮጵያ ለኤርትራ የሰጠችውን የሀገርነት እውቅና ስለመንሳት !ኤርትራ  ሀገር አይደለችም ፣ ሀገር ሆናም አታቅም ። ቀደሞም ሀገር ያልነበረች፣ የደርግ መንግስት መውደቁን ተከትሎ  "ሀገር ሁኚ...
01/11/2024

ኢትዮጵያ ለኤርትራ የሰጠችውን የሀገርነት እውቅና ስለመንሳት !

ኤርትራ ሀገር አይደለችም ፣ ሀገር ሆናም አታቅም ።
ቀደሞም ሀገር ያልነበረች፣ የደርግ መንግስት መውደቁን ተከትሎ "ሀገር ሁኚ" ተብሎ በሴራ እንድትገነጠል ተፈቅዶላት የተገነጠለች ቢሆንም 34 ዓመት ሙሉ ሀገር መሆን ያቃታት ኢትዮጵያ ወደ ባህር እንዳትወጣ የተፈጠረች በኢትዮጵያና ቀይባህር መሀል የተሰነቀረች ምድረበዳ አጥር ነች።

ኤርትራ በነግብፅ የዓመታት ሴራ ስትገነጠል ሻዕቢያ ህልም አርጋ የተነሳችው ኤርትራን ሲንጋፖር ኢትዮጵያን የኤርትራ የምትታለብ ላም አርጎ የመኖር ሞኛሞኝ ህልም ይዛ ነበር ።

ነገር ግን አልሆነም ኤርትራ በሻዕቢያ ስር የምድራችን ሲኦል ሆና ላለፉት 34 ዓመታት ኖራለች። በህዝብ ቁጥር ትንሽ ሆና በስደተኝነት ግን ከአለም ቀዳሚ ወጣት አልባ፣ ትምህርት አልባ ህግ አልባ ፣ የሽማግሌዎችና ጥቂት ሴት ወታደሮች ትልቅ እስር ቤት ናት ኤርትራል ።

የኤርትራ ህዝብ በተገኘው እድል ሁሉ ድምበር ላይ ጥይት እየተተኮሰበት ከኤርትራ ሾልኮ ኢትዮጵያ መግባት ነው ትልቁ ህልሙ ተግባሩ ነው፤ ለዚህም ማሳያው በአሁን ሰዓት ኤርትራ ካሉ ወጣቶች በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ኤርትራዊያን ፈልሰው አሉ(በተለይ በአለፉት 5ዓመታት ) በኤርትራ ከሚኖር 3.5 ሚሊየን ህዝብ ከ 1 ሚሊየን ወጣት በላይ ኢትዮጵያ ገብቷል። በሰሜኑ ጦርነት በርካታ በ10ሺዎች ሚቆጠሩ የሻዕቢያ ወታደሮች ወደ አስመራ ሳይሆን ወደ አዲስ አበባ ነው ዩኒፎርም አውልቀው ክላሽ ሽጠው ያቀኑት።

ይህን ተከትሎም ኢሳያስ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም መፈጠሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ በማየሉ ቀድሞውኑ ድንበር የዘጋ ቢሆንም ወደ ተለመደው የተፈጥሮው ጠላትነት መግባቱን መርጧል፤ ከወላጁ ግብፅ ጋርም ሴራ መሸረብ ከጀመረ ሰነባብቷል ።

ኢትዮጵያ ከሻዕቢያ የሽፍታ ቡድን ጋር ሊዋደድ ሚችል ፖሊሲም ሆነ ስርዓት መቼም ሊኖራት አይችልም ፤ ምክንያቱም ኤርትራ ያረጁ ወታደሮች ካምፕ እንጂ ሀገር አይደለችምና ።

በመሆኑም 2.9ሚሊየን የአመታት እስረኛ የኤርትራ ህዝብ ያለ ታላቋ የ129 ሚሊየን ህዝብ ግዙፍ ሀገር ኢትዮጵያ እውቅና ሀገር መሆንም መምሰልም አይችልምና ኢትዮጵያ ለኤርትራ የሰጠችውን የሀገርነት እውቅና ስለማንሳት ማጤን አለባት ። ኤርትራ ያለ ኢትዮጵያ ፍቃድ አለም ሁሉ ቢፈልግ ሀገር መሆን አትችልምና ።

ኤርትራን እውቅና መንሳት ትንሽ ግርግር ብዙ ድል ለኢትዮጵያ ያስገኛል ። የኤርትራ መንግስት ሀገር መመስረት ያቃተው እጅግ በሚባል ደረጃ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ያለ ትልቅ ለመምሰል እዚም እዛም የጦር ጉሰማ ሚጎስም አንድ ጥይት ተተኩሶ ድንበር ቢከፈት እንደ ተሰበረ ቅል ፈንድቶ ወታደሩም ህዝቡም ምድሩን ጥሎለት እንደሚጎርፍ የተረዳ ፈሪ መንግስት ነው።

ኢትዮጵያን ባህር አልባ አርጎ ህዝቦቿን እያባሉ ለዘመናት ሲደክም የኖረውን የሻዕቢያዋን ኤርትራ እውቅና በመንፈግ ፣ ቀጥሎም ሻዕቢያን አስወግዶ ልክ እኛ ላይ በ1983 እንዳረጉት ሁሉ የተወሰደብንን ቀይ ባህር ፈርሞ ሚመልስ መንግስት መመስረት ከወዲሁ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያ ልክ እንደ ግዙፍ ግን ሞኝ የትናንሽ ህፃን ሀገር መሳይ ቡድኖች መጫወቻ መሆኗ አብቅቶ ኤርትራን ወደ ሚገባት ወደ ሚመጥናት ቅርፅ መቀየርና ለአከባቢው ሰላምና ብልፅግና ማምጣት ግድ ሆኗል።
የዚህን የቀጠናው ደነቀራ አጥር መነሳት ከግብፅ ውጪ መካከለኛው ምስራቅ እነ ሳኡዲ የመንን ጨምሮ እስከ አሜሪካ ከተሰራበት በሚገባ ይደግፉታል ። ባይደግፉትም ግድ የለን ...ለኢትዮጵያ ግን እሾህን በእሾህ ተጠቅማ ባህሯን ማስመለስ ለቀጣይ ትውልድ የማይባል ነው !

ለቀይ ባህር በራችን የሚደረግ ማነኛውም ነገር በሙሉ ቅዱስ ነው !

ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet

"እኔ ከተመረጥኩ ከምሰራው ዝርዝር ጋር ትራምፕ ከተመረጠ ከጠላቶቹ ዝርዝር ጋር ለበቀል ወደ ፕሬዚዳንት ቢሮ ይገባል" ካማላ ሃሪስ እጩ ፕሬዚዳንትየዓለማችን ልእለ ኃያሏ አሜሪካ እጩ ተወዳዳሪ ...
30/10/2024

"እኔ ከተመረጥኩ ከምሰራው ዝርዝር ጋር ትራምፕ ከተመረጠ ከጠላቶቹ ዝርዝር ጋር ለበቀል ወደ ፕሬዚዳንት ቢሮ ይገባል" ካማላ ሃሪስ እጩ ፕሬዚዳንት

የዓለማችን ልእለ ኃያሏ አሜሪካ እጩ ተወዳዳሪ ም/ፕሬዚዳንት ካሚላ ሀሪስ በቀጣዩ ሳምንት በሚጠናቀቀውና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በመከናወን ላይ በሚገኘው ምርጫ ቅስቀሳ ላይ ሰንብተዋል።

ይህ ምርጫ በሁለት ፓርቲዎች ወይም በሁለት እጩዎች መካከል የሚካሄድ አይደለም። ምርጫው በአንድነትና ነጻነት እንዲሁም በመከፋፈልና በቀውስ መካከል የሚደረግ ነው ሲሉ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ዛሬ የምርጫ ቅስቀሳ የመዝጊያ ንግግር በዋሽንግተን ዲሲ ፕሬዚዴንሻል ጋርደን ከነጩ ቤተመንግስት ጀርባ አድርገዋል።

ከ40 ሺ በላይ ደጋፊዎች በተገኙበት አደባባይ ባሰሙት የቅስቀሳ ንግግር በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ከፍተኛ ትችት የሰነዘሩት እጩ ፕሬዝዳንቷ ፤ ትራምፕ ከፋፋይና ህዝቦች እርስ በርሳቸው አንዱ ሌላውን እንዲጠራጠር ቀስቅሷል ሲሉ ከሰዋቸዋል።

ትራምፕ በርካታ ክሶች የተከፈቱበትና በፍርድ ቤት በመታየት ሂደት ላይ የሚገኙ ናቸው ያሉት ካሚላ ሃሪስ፤ የፈጸሟቸው ወንጀሎችን ያጣሩ፣ የመረመሩና ለህግ ያቀረቡትን ለመበቀል "ጠላቶች " ያሏቸውን ስም ዝርዝር በእጃቸው መያዛቸውንና ገልጸው ፤ የፕሬዳንቱን ቢሮ አሸንፈው ከወሰዱ ከፍተኛ በቀል ሊያደርሱ እንደሚችሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል ።

እኔ ህገወጥነትን ስከላከልና ለተጎዱት ጥብቅና ስቆም ነበር ያሉት ሀሪስ፤ ከመረጣችሁኝ እዳምጣችኋላሁ፤ መግባባትንም ለመፍጠር በቁርጠኝነት እሰራለሁ። እናንተ ብቻ እድሉን ስጡኝ ሲሉ መራጮችን ተማጽነዋል።

ትራምፕ ቢመረጥ ለሃብታሞቹ ጓደኞቹ ታክስ በመቀነስ በመካከለኛ ገቢ በሚኖሩ ላይ ጫና ያበረታል፤ ካሉ በኋላ በአነሰተኛ ገቢ ለሚተዳደሩት ኑሮን ለመደጎምና የጤናን መድህን ዋስትና ለማረጋገጥ ከልብ እሰራለሁ ብለዋል።

ጽንስ ማቋረጥን ትራምፕ ማገዱ በግለሰብ የገላ ነጻነት ላይ መወሰን በመሆኑ ሴቶች ነጻነታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል እኔም ይሄንኑ መብታቸውን በህግ እንዲከበር ህግ አወጣለሁ፤ ፊሪማዬንም አኖርበታለሁ ነው ያሉት።

የድንበር ማስከበርና የስደተኞች ጉዳይን በሚመለከትም የተጠናከረ የድንበር ጥበቃ ስርዓት እንደሚዘረጉና ህገወጦች ሲያጥሙም ወዲያ እንደሚያባርሩ አረጋግጠዋል። ይሁንና በህጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ ስደተኞች መብታቸውን እንደሚያስከብሩና አሜሪካንን በመገንባት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ንግግራቸውን በመቀጠል ለወጣት አዲስ ቤት ገዥዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤቶች እንዲገነቡ እንደሚደርጉና የቅድሚያ ክፍያ ድጋፍም እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል።

ትራምፕ በቅስቀሳው አሜሪካውያንን ለመከፋፈል እየጣረ ነው በማለት የከሰሱት እጩ ፕሬዚዳንቷ ፤ ህዝቡ ሳይከፋፈል ድምጹን ለሀሪስ እንዲሰጣቸውና እርሳቸውን ለሁሉም አሜሪካውያን ያለ ልዩነት እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል ።

የድምጽ መስጠት ሂደቱ እየቀጠለ የሚገኘው የዘንድሮው ምርጫ በቀጣዩ ሳምንት የሚጠናቀቅ ሲሆን ቀጣይ የሃያሏ ሃገር መሪም ተለይቶ ይታወቃል።
በአንተነህ አብርሃም
ከዋሽንግተን ዲሲ

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሃገሩን በህልሙ ሲመለከት።
27/10/2024

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሃገሩን በህልሙ ሲመለከት።

የኤርትራ ጦር ሰራዊት አባላት የባህር ሃይል አባላትን ጨምሮ ሶማሊያ መግባታቸውን ራዲዮ ኤርና ዘግቧል። በሶማሊያ ከ300 በላይ የኤርትራ ወታደሮች ተሰማርተዋል። በአሁኑ ወቅት ከ3,000 በላይ...
23/10/2024

የኤርትራ ጦር ሰራዊት አባላት የባህር ሃይል አባላትን ጨምሮ ሶማሊያ መግባታቸውን ራዲዮ ኤርና ዘግቧል።

በሶማሊያ ከ300 በላይ የኤርትራ ወታደሮች ተሰማርተዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ3,000 በላይ የሶማሊያ ወታደሮች ኤርትራ ውስጥ ስልጠና እየወሰዱ ነው።

ፎቶ፡ ራድዮ ኤርና

22/10/2024

በአዲስ አበባ የአዲስ ከተማ (መርካቶ ሸማ ተራ) ቃጠሎን ተከትሎ ልንወስዳቸው የሚገቡ የጥንቃቄ መልዕክት አለኝ።
ሼር ሼር!! አርጉት

ዋው የአይኔ ቀለም ጥቁር ቢሆን ኖሮ ምን እመስል እንደነበር በአንድ አፕ ቀይሬ አየሁት። የቱ ያምራል?
22/10/2024

ዋው የአይኔ ቀለም ጥቁር ቢሆን ኖሮ ምን እመስል እንደነበር በአንድ አፕ ቀይሬ አየሁት። የቱ ያምራል?

13/10/2024

የናይል ስምምነት ወደ ትግበራ መግባቱ አስደሳች ነው።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911403407

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አንተነህ አብርሃም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share