ልቦና ቲዩብ Libona Tube

ልቦና ቲዩብ Libona Tube የልቦና ቲዩብ ትክክለኛ የፌስቡክ ፔጅ ይሄ ነው።
(2)

20/10/2023

በቦሌ አራብሳ ለሚ ጃርሶ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እየተደረገ ያለው ተዓምር

#ቃጥላ ⛪️ #ቤተክርስቲያን #ኦርቶዶክስ #መዝሙር #ኢትዮጵያ

ቪዲዮ ኤዲተር እፈልጋለው !
13/09/2023

ቪዲዮ ኤዲተር እፈልጋለው !

ውድ ቤተሰቦቼ እንኳን ከዘመነ ሉቃስ  ወደ ዘመነ ዮሀንስ በሰላም አሸገገራችሁ ።ከምርቃቴ በኋላ ራሴን ላሳርፍና ጥሞና ለመውሰድ ያስቀመጥኳቸው ቀናቶች እያለቁ ስለሆነ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ...
12/09/2023

ውድ ቤተሰቦቼ እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሀንስ በሰላም አሸገገራችሁ ።

ከምርቃቴ በኋላ ራሴን ላሳርፍና ጥሞና ለመውሰድ ያስቀመጥኳቸው ቀናቶች እያለቁ ስለሆነ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በቅርቡ በሰፊው እንደምንገናኝ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ ። በአዲሱ ዓመት ከምንም በላይ ሀገራችን ሰላም የምታገኝበት ሰዎች ማይገደሉበት የእምነት ተቆማት ማይነዱበት ማይፈርሱበት ምዕመናን ማይፈናቀሉበት ቸሩን ሁሉ የምንሰማበት ያድርግልን ለሁላችሁም መልካም በዓል እመኝላቹሀለው ቸር ያገናኘን ።

ትንሹ ወንድማችሁ ያብስራ ማቴዎስ
መስከረም 1 / 2016 ዓ.ም

ክብር ምስጋና ለእናትና ልጁ ! አሜን ፫
21/08/2023

ክብር ምስጋና ለእናትና ልጁ ! አሜን ፫

አባቴ ተመርቄልካለው 🎓የፈለገ ቃላት ባስረዝም ስሜቴን ይገልፀዋል ብዬ አላስብም በአጭሩ ''ሁሉ በርሱ ሆነ፥ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለርሱ አልሆነም። ''የዮሀንስ ወንጌል 1:3ምስጋና ገንዘቡ ...
05/08/2023

አባቴ ተመርቄልካለው 🎓

የፈለገ ቃላት ባስረዝም ስሜቴን ይገልፀዋል ብዬ አላስብም በአጭሩ ''ሁሉ በርሱ ሆነ፥ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለርሱ አልሆነም። ''የዮሀንስ ወንጌል 1:3
ምስጋና ገንዘቡ ላደረገ ከልጅነቴ ጀምሮ በቤትክ ያሳደከኝ እኔ ሳላውቅ አንተ አውቀኸኝ ለዚህ ያደረስከኝ መድኀኔዓለም ክብር ምስጋና ሁሌም ለአንተ ይገባል በመቀጠል ከፈጣሪ ቀጥሎ እናትና አባቴን እጅግ በፈጣሪ ስም አመሰግናቸዋለሁ ።ይችን ቀን በአካል ያላኘከው አባቴ እጅግ ለኔ ብዙ ብዙ ዋጋ ከፍለክልኛል መድኀኔዓለም ከደጋጎቹ ጎን እንዲያሳርፍ ሁሌም ፀሎትና ልመናዬ ነው አባቴ እጅግ እወድሀለው ነፍስ በሰላም ትረፍ ።

ሐምሌ 29
ያብስራ ማቴዎስ ወንድምአገኘሁ

ሰኔ 30ለቅዱሳን ቤተሰቦቹ የጸሎት መልስ የሆነው፣ ለዚህች ዓለም የሚነድና የሚያበራ መብራት የነበረው፣ የሥጋን ጣዕም ያልቀመሰው ፍጹም ተሐራሚ፣ ተፈጥሮው የሰው ኑሮው የመልአክ የነበረው፣ ዕረ...
07/07/2023

ሰኔ 30

ለቅዱሳን ቤተሰቦቹ የጸሎት መልስ የሆነው፣ ለዚህች ዓለም የሚነድና የሚያበራ መብራት የነበረው፣ የሥጋን ጣዕም ያልቀመሰው ፍጹም ተሐራሚ፣ ተፈጥሮው የሰው ኑሮው የመልአክ የነበረው፣ ዕረፍትን የማያውቅ የበረሃው ሰው የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ልደቱ ዛሬ (ሰኔ 30) ይታሰባል።

ቅዱሱ ሰማዕት እንደ ኖኅ ጻድቅ የነበረ፣ እንደ አብርሃም በእግዚአብሔር የተወደደ፣ እንደ ዮሴፍ የታሰረ፣ እንደ አቤል በአመጻ የተገደለ፣ እንደ ሄኖክ አካሄዱን ከአምላኩ ጋር ያደረገ ነው።

በመንፈስ ቅዱስ አሳዳጊነት በመላእክት አገልግሎት በበረሃ ያደገው ዮሐንስ ክብሩ እንዴት ያለ ነው? እርሱ እንደ ሕፃናት ባለቀሰ ጊዜ የሚያባብለው ሰው አልነበረም። "አይዞህ ልጄ" እያለች የምታጽናናው እናቱም ገና በልጅነቱ ተለይታዋለች። ነገር ግን እግዚአብሔር ብቻውን በበረሃ አልተወውም። አጥንት በሚያለመልም የመላእክት ምስጋና አረጋጋው። በልዩ ጥበቡም አሳድጎ በመንፈስ እንዲጠነክር አደረገው። የእግዚአብሔር አብን ልጅ ዮሴፍ በናዝሬት (የሰው ልጅ) እንዳሳደገ፣ የዘካርያስን (ለሰውን) ልጅ ዮሐንስን እግዚአብሔር በበረሃ አሳደገ።

ዮሐንስ ነቢይ ነው። ግን ከነቢያትም ይበልጣል። እርሱ እንደ ሌሎቹ ነቢያት የመሲሑን መምጣት በመንፈስ ዓይቶ "ይመጣል" ብቻ አላለም። "እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" ብሎ ወደ እርሱ በመጠቆም ሲጠበቅ የኖረው ለመምጣቱም አብሣሪ ሆኗል። እርሱ ነቢያቱ ሊያዩ የወደዱትን ግን ያላዩትን፣ሊሰሙ የፈለጉትን ግን ያልሰሙትን አይቷል፤ ሰምቷልም። ወልድን የዳሰሰ፣ አብን የሰማ፣ መንፈስ ቅዱስን ያየ እንደ ዮሐንስ ያለ ነቢይ ማን አለ?

ዛሬ የተወለደው ቅዱስ ዮሐንስ አምላኩን ማገልገል የጀመረው ገና በእናቱ ማኅጸን ሳለ ነው። ነቢዩ ለፈጣሪው በደስታ የሰገደው ገና ከተፈጠረ በ180ኛው ቀኑ ነው። ታዲያ እኛ እግዚአብሔርን ለማገልገል ለምን ቀጠሮ እናረዝማለን? ገና ነን እንደርስበታለን እንዴት እንላለን? ከዛሬው ባለ ልደት አንጻር ለአገልግሎትና ለምስጋና በጣም የዘገየን አይመስላችሁም? የታደለው ቅዱስ ዮሐንስ በስድስት ወሩ ሰገደ። የእኛስ ይህ አፈርና ትቢያ የሚሆን ሰውነታችን ሳይወድቅ በፊት ፈጣሪውን የሚያገለግለው መቼ ነው?

"በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል"
ሉቃ 1፥14

©ልቦና ቲዩብ

https://t.me/libonatube

21/06/2023
   እመቤታችን ማርያም /እመቤታችን በድብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ነው።ይህም በዓል ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚህ ቀን ግ...
29/05/2023





እመቤታችን ማርያም /እመቤታችን በድብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ነው።

ይህም በዓል ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር።

እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ ፤ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተ...ከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር።

ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ግማሹ ነብዩ ዳዊትን ግማሹ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል፤እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር።

አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው።የእመቤታችን ረድአት እና በርከቱ በሁላችን ላይ ይድርብን አሜን፡፡

©ልቦና ቲዩብ

27/05/2023

ምንድን ነው የሚሻለን ?

የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው !እንኳን አደረሳችሁ
09/05/2023

የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው !
እንኳን አደረሳችሁ

ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም በሶስተኛውም ቀንም ሊነሳ ግድ ነው። (ሉቃ .24÷5) እንኳን ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ...
16/04/2023

ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም በሶስተኛውም ቀንም ሊነሳ ግድ ነው። (ሉቃ .24÷5)

እንኳን ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በውጭም በሀገር ውስጥም ያላችሁ ቤተሰቦቼ መልካም የትንሳኤ በዓል እመኝላቹሀለው ።

ቅዳሜ ስዑር ማለት የተሻረች ቅዳሜ ማለት አይደለም !!!ስለ ቀዳሜ ስዑር ቅዳሜ ስዑር የሚለውን ቅዳሜ ሹር ይሉታል መፅሀፍ የሚለው ሌላ እነሱ የሚሉት ሌላ ማለትም ቅዳሜ ስዑር ማለት ስዕረ ለመ...
15/04/2023

ቅዳሜ ስዑር ማለት የተሻረች ቅዳሜ ማለት አይደለም !!!

ስለ ቀዳሜ ስዑር

ቅዳሜ ስዑር የሚለውን ቅዳሜ ሹር ይሉታል መፅሀፍ የሚለው ሌላ እነሱ የሚሉት ሌላ ማለትም ቅዳሜ ስዑር ማለት ስዕረ ለመለመ ከሚለው ግዕዝ የተገኘ ቃል ነው ።አንድም የሳር ቀን ለማለት ነው።ቅዳሜ ስዑር አለ እንጂ ሹር የተሻረ አላለም ስዑር ማለት ሉሙልሙ ማለትም የለመለመ ሳር የተባለውም በገነት የበቀለውን የገነት ሳር ነው ። ቅዱሳን አበው እነ አብርሃም ዳዊት እነ ሰለሞን የሚያርፉበት የገነት ሳር ነው እንጂ የበረሀ ሳር አይደለም....የበረሀ ሳር አራዊት አጋንንት ዛር ልዩ ልዩ መናፍስት የሚተነፍሱበት የሚተኙበት የሚንከባለሉበት ሳር ነው ። ቅዳሜ ስዑር የተባለበት ሚስጥር ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን በመስቀሉ አድኖ አጋንንትን አሳምኖ ሞትን በሞቱ ኮንኖ በመስቀል ተሰቅሎ ሳለ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ በሲኦል ያሉ ነፍሳትን በብርሀን ሸፍኖ ወንጌለ መለኮቱን በሲኦል ሰብኮ ነፍሳተ ፃድቃንን ነፍሳትን ሁሉ ከዲያቢሎስ እጅ ማርኮ ዲያቢሎስን አንበርክኮ መኮንንተ ፅልመትን እፍረክርኮ ሀይለ መስቀሉን ነገረ መለኮቱን ለወዳጆቹ ሰብኮ አርብ 11 ነፍሳተ ፃድቃንን ነፍሳትን ሁሉ እየመራ ወደ ለመለመ ሳር ወደ ገነነው ሀመልማሎ አፀደ ገነት መካካል ወደ ተሾሞለሞለው ሀመልማለ ገነት ነፍሳተ ፃድቃንን ነፍሳትን በመሉ ይዞአቸው ገባ ። በለመለመ ሳርም አሳረፋቸው አሰነበታቸው አርብ ቅዳሜ እሁድ በለመለመ ሳር አቆያቸው ።
ሶስት ቀን ለምን አሰነበታቸው ቢሉ ከሞተላቸው ከተሰቀለላቸው ከሲኦል ካወጣቸው በሲኦል ካስተማራቸው ለጊዜው ለምን ወደ መንበረ መንግስቱ ወደ መንግስተ ሰማያት ለምን አልወሰዳቸውም ቢሉ ሞቱ በአባቱ ፍቃድ በራሱ ፍቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ መሆኑኑ ሊያስተምራቸው ነው ። ሰው የሆነው በአባቱ ፍቃድ በራሱ ፍቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ነው ይህም የፍቅር ምልዕክት ነው ።

ምስክሩም መዝመር ዳዊት 22
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል።

ስብሀት ለእግዚአብሔር !

©ልቦና ቲዩብ

በሕማማት ወቅት ግድ ልናደምጠው የሚገባ አንዴ ጀምሩት አታቆርጠትም 👇👇👇👇
10/04/2023

በሕማማት ወቅት ግድ ልናደምጠው የሚገባ አንዴ ጀምሩት አታቆርጠትም 👇👇👇👇

ሕማማትመደኃኔ ዓለም ክርሰቶስ ከተያዘበት እስከ ተቀበረበት ያለውንን መከራ የሚቃኝ በዓብይ ፆም ሊደመጥ የሚገባ።ፀሀፊ : ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ ንባብ : ዲያቆን ፍቅረ ሚካኤል ዘየደምንም .....

🌿 ሆሳዕና በአርያም 🌿እንኳን አደረሳችሁ
09/04/2023

🌿 ሆሳዕና በአርያም 🌿
እንኳን አደረሳችሁ

08/04/2023
30/03/2023
ቸሩ መድኃኔ ዓለም በቀኙ ያቁምዎ!አዕርፍ እግዚኦ ነፍሰ አቡነ አረጋዊ!
21/03/2023

ቸሩ መድኃኔ ዓለም በቀኙ ያቁምዎ!

አዕርፍ እግዚኦ ነፍሰ አቡነ አረጋዊ!

05/03/2023

የዓብይ ፆምን ሕማማትን የተሰኘው እጅግ ድንቅ መፅሀፍ ገዝታችሁ ማንበብ ላልቻላችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ በፀሀፊው ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ መልካም ፍቃድ በግሩም አተራረክ በ6 ምዕራፎች ያዘጋጀንላችሁን ሲሆን መደኃኔ ዓለም ክርሰቶስ ከተያዘበት እስከ ተቀበረበት ያለውንን መከራ የሚቃኝውን በልቦና ቲዩብ ታገኙታላችሁ ወይም ከታች ባለው ሊንክ መሉውን የምታገኙት ይሆናል ።
-ፀሀፊ : ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ
-ንባብ : ዲያቆን ፍቅረ ሚካኤል ዘየደ
ምንም ሳይጨመር ሳይቀነስ ሙሉ መፅሀፉ በፀሀፊው መልካም ፍቃድ
በልቦና ቲዩብ የቀረበ ፡፡
https://youtube.com/playlist?list=PLaHOIicdErt-jI8Zl26bj7Ib0wrLM_d7a

"ውሏችን!እንደተለመደው የዓድዋን በዓል ለማክበር ጠዋት ላይ ነጭ ልብሳችንን ለብሰን በላዩ ነጠላ ጥለንበት ከወንድሜ ከተመስገን ጋር ነበር ከቤት የወጣነው።ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ መንገድ ላ...
02/03/2023

"ውሏችን!

እንደተለመደው የዓድዋን በዓል ለማክበር ጠዋት ላይ ነጭ ልብሳችንን ለብሰን በላዩ ነጠላ ጥለንበት ከወንድሜ ከተመስገን ጋር ነበር ከቤት የወጣነው።

ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ መንገድ ላይ ያገኘን ከጊዮርጊስ አቅጣጫ የሚመጣው ሰው ሁሉ አፍንጮ በር ጋር ዘግተውታል አትልፉ ተመለሱ እያለ ይነግረን ነበር።

እኛም ግድ የለም አይተን እንመለሳለን ትንሽ ቆይተው ይከፍቱታል በማለት ተስፋ አድርገን መንገዳችንን ቀጠልን።

እንደተባለው በአፍንጮ በር በኩል ፤ በሰሜን ሆቴል በኩል ወደ ጊዮርጊስ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው። በዮሐንስ በኩል እንይና እንመለሳለን ብለን ስንሔድ በዚያም በኩል በፖሊሶች ተዘግቷል።

እንሳለም ብለን ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ገብተን ለደቂቃዎች ከቆየን በኋላ ከቤተ ክርስቲያኑ በአፍኣ መጮህ ሲጀምር ከግቢው ስንወጣ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ሕዝቡ እንዳይሄድ አግደውት የነበሩ ፖሊሶች ሕዝቡ እንዲሔድ በመፈቀዱ እንደሆነ ተረዳን።

እኛም ከሌሎች ጋር ተሰብስበን እየዘመርን መሔድ ጀመርን። በግምት ከመቶ ሜትር በኋላ ሌሎች ፖሊሶች ከዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፒያሳ የሚወስደው መንገድ ላይ ዘግተው ቆመዋል።

ሕዝቡ እየዘመረ አጠገባቸው ሲደርስ በዱላ መማታት ጀመሩ። ሕዝቡ ሲበታተን ግማሹ ሲወድቅ አንዱ በአንዱ ላይ እየወደቀ ብዙ ሰው ተጎድቷል።

መሐል ላይ ጥይት መተኮስ ተጀመረ። [እኔ የሰማሁት ሁለት ጊዜ] በዚህ ጊዜ ወንድሜ ተመስገን ወድቆ ተነሳ። እኔ አደናቅፎት መስሎኝ ነበር ላካንስ በጥይት ተመትቶ ነበር። ደሙ በነጩ ሱሪው ላይ መውረድ ጀመረ።

ይዘነው ወደ አናንያ ሆስፒታል በመቀጠልም በሪፈራል ወደ አቤት ሆስፒታል ወሰድነው።

አቤት ሆስፒታል ባጣራነው መሠረት 16 ሰው ተጎድቶ የገባ ሲሆን አንዱ ሕይወቱ አልፏል።

በጥይት የተመታ፣ በሰደፍ ጀርባው ተመትቶ አጥንቱ የወለቀ፣ እጁ በዱላ ተመትቶ አጥንቱ የተሰበረ ..... ሌላም ሌላም ሞልቷል።

እንግዲህ ምን እንላለን?
ሀገር አለን'ን?

ትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነኝ


~ ዮሐንስ ዘኆኅተ

ከዮሀንስ ሞላ ፌስቡክ ገፅ

02/03/2023

ዛሬ በአራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይቺ ብላቴና '' እምነታችሁ ያድናችኋል አትሩጡ ፈረሰኛው ይመጣል '' ምን ማለት ይቻላል ?

ነፃነት የማያዉቁ በዛሬው ዕለት የአደዋ ድል በዓልና የሰማዕቱን ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር በወጣው ህዝብ ላይ በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ሳይቀር ፀረ ኢትዮጲያ...
02/03/2023

ነፃነት የማያዉቁ

በዛሬው ዕለት የአደዋ ድል በዓልና የሰማዕቱን ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር በወጣው ህዝብ ላይ በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ሳይቀር ፀረ ኢትዮጲያና ፀረ ኦርቶዶክስ በሆነዉ ወታደራዊና ፋሽስታዊ ስርዓተ መንግስት ዛሬ በህዝብ ላይ የፈፀመው ወንጀል፡ ግፍና ነዉር ለትዉልድ ሲነገር ይኖራል። አሁን የገጠመን መከራ ከዮዲት ጉንዲትና ከአህመድ ግራኝም ይበልጣል።

በምድሯ የበቀሉ ነፃነት በማያዉቁ የጣልያን የልጅ ልጆች በኢትዮጲያዉያን ላይ የፈፀሙትን የባንዳነትና የክህደት ተግባር በታሪክ ማህደር በቆሻሻነት ተመዝግቦዋል።

ወዳጄ ፋሽታዊና ዘረኛ መንግስት ስትሆን የበታችነት መንፈስ ትታመማለህ። በህዝብ ላይ ጦርነት አዉጀህ እንዲህ አይነት ወንጀል በግልፅ ትፈፅማለህ። መጥፊያህ ግን ቅርብ ነዉ። ከነትርክትህ ላትመለስ ትቀበራለህ። ኢትዮጲያና ኦርቶዶክሳዊነት ዳግም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣሉ።

የካቲት  23 / ፳፫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታትየካቲት ሀያ ሦስት በዚህች ቀን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት አባቶቻችንን አድዋ ላይ የረዳበት ነው፡፡ አንድ አምላክ በኾነው በአብ በወልድ ...
02/03/2023

የካቲት 23 / ፳፫
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት

የካቲት ሀያ ሦስት በዚህች ቀን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት አባቶቻችንን አድዋ ላይ የረዳበት ነው፡፡

አንድ አምላክ በኾነው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

በዚያን ወራት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ አራት ዓመት በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በነገሡ በሃያ ስድስት ዓመት የምኒልክ የጦር አለቃ ገበየሁ ድል ከአደረጋቸው በኋላ እንደገና ምኒልክም ወግተው ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሊገዙ የሮም ሰዎች መጡ።

ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት፡ ዳግማዊ አጤ (ዓፄ) ምኒልክ መስከረም ፯ ቀን ፲፰፻፹፰ (1888፡ዓ.ም ) ላይ "እግዚአብሔር በቸርነቱ፡ እስከ አሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስከ አሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፡፡ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት፤ እግዚአብሔር የወሰነልንን የባህር በር አልፎ መጥቷልና እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስከ አሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ የአገሬ ሰው፤ ከአሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም አንተም እስከ አሁን አላስቀየምኸኝም፡፡ ስለዚህ ስንቅህን በአህያ አመልህን በጉያህ ይዘህ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ፡፡ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፤ለሚስትህ፤ ለሃይማኖትህ ስትል በኀዘን እርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን በኋላ ትጣላኛለህ አልተውህም፡፡ ማርያምን! በዚህ አማላጅ የለኝም"፡፡ ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ" ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ ዳግኛም በፈረሶታቸው መጣብር ላይ በጦራቸው አንደበት ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ጭፍሮችን አዘዛቸው መስቀል ጠላትን ድል አድራጊ እንደሆነ አስቀድሞ ያውቅ ነበርና።

አዋጁን ካስነገሩ በኋላ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ትግራይ ክፍለ አገር ዘመቱና ከትግራይ አውራጃ አንዷ የምትሆን አድዋ የምትባል አገር ደረሱ፡፡ የሣህለ ማርያም (ዳግማዊ ምኒልክ) ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) በንጉሡ ትዕዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስን አስይዘው ከሊቀ ጳጳሱ ከአባ ማቴዎስ እንዲሁም ከቀሳውስቱና ከመነኰሳቱ ጭምር ከንጉሡ ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዘች፡፡በዚያም ጊዜ የአክሱም ጽዮን መነኰሳትና ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ወደ ምኒልክ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ ከነአቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ጸሎት ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ።

ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ የካቲት ሃያ ሁለት ቀን ነው ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) የጦር ልብሱን ለብሰው ከሠራዊቱ ጋር ወደ ጦር ግንባር ሄደ፡፡ ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝቶ ከሌሊቱ ዐሥራ አንድ ሰዓት ጦርነቱን ጀመረ፡፡ የንጉሡ የሣህለ ማርያም (የምኒልክ) ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት እያደረች ሲነጋ ወደጦርነቱ ቦታ በመሄድ እጅግ ለሚያስደንቅ የአነጋገሯ ኃይል ቃል በጦርነቱ መካከል እየተገኘች ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ትሰጣቸው ነበር። በእውነትም ለተመለከታት ሁሉ እንደ ኃይለኛ ተጋዳይ አርበኛ ትመስል ነበር እንጂ የሴቶች የተፈጥሮ ባሕርይ በእርሷ ላይ አይታይባትም ነበር። የንጉሡም ወታደሮች የንግሥቲቱን የጀግንነት አነጋገር በሰሙ ጊዜ በእሳት ላይ እንደተጣደ የብረት ምጣድ ልባቸው ጋለ ይልቁንም ላም እንዳየ አንበሳና የፍየል መንጋ እንዳየ ነብር እየተወረወሩ በጦርነቱ መካከል በመግባት የጠላትን ጦር በሰይፍ ይጨፈጭፋት ነበር። መጽሐፍ ሹመትን ሽልማትን ያየ አርበኛ ከጦርነት ከሰልፍ ወደኋላ አያፈገፍግም ብሎ ተናግሯልና፡፡ በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) በጦርነቱ መካከል ሳለ ሊቀ ጳጳሱ አባ ማቴዎስ እንዲሁም የአክሱም መነኰሳትና ሌሎቹ ካህናት በሙሉ ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኋላ በደጀንነት ቆመው ጸሎተ ምህላ ያደርሱ ነበር። ንግሥቲቱ ወለተ ሚካኤል (እቴጌ፡ጣይቱም) በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ አትለይም ነበር። የጽዮን አገልጋዮችም በእግዚአብሔር የሕጉ ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር።

በዚህም ዕለት ይኸውም የካቲት ሃያ ሦስት ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ሆነ በዚህም ጊዜ በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ። ማለትም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ ከዚያም ከቀስተ ደመናው ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የመሰለ ጢስ ይወጣ ነበር፡፡ ከዚህም ጢስ ውስጥ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ያለ ድምጽ ተሰማ፡፡ ከዚህም የነጐድጓድ ድምጽ የተነሳ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር ሆነ ለመዋጋት አልቻሉም፡፡ ይልቁኑ ኃያሉ ገባሬ ተአምር ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ላይ ፈረሱ ተቀምጦ ከነፋስ ሩጫ ይልቅ እየተፋጠነ በአየር ላይ በተገለጸ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ፡፡ "የኢትዮጵያ ህዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ እንግዲህ ማን ያድኅነናል" አሉ ምድርም ጠበበቻቸው በዚህን ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን የጦር ሠራዊት ፈጁዋቸው የተረፉትንም ማረኳቸው ፈጽመውም እስኪያጠፏቸው ድረስ በሮማውያን ላይ በእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያውያን እጅ እየበረታ ሄደ፡፡ ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) በእግዚአብሔር ኃይልና በተአምራት አድራጊው በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳይነት የሮማውያንን የጦር ሠራዊት ድል አድርገው የድል አክሊል ተቀዳጅተው ተመለሱ፡፡

ስለዚህም በዳዊት የምስጋና ቃል የድል ዘውድ ያቀዳጀኝን እግዚአብሔር "ባለ ዘመኔ ሁሉ አመሰግነዋለሁ ለፈጣሪዬ እዘምራለሁ" አለ ሕዝቡም ሁሉ "በክብር ከፍ ከፍ ያለ እግዚአብሔርን በፍጹም ምስጋና እናመስግነውለን የሮማውያንን ኃይል ቀጥቅጦ አጥፍቷልና ሠረገሎቻቸውንም ሠባብሯልና ሠራዊቱንም ሁሉ በምድር ላይ በትኗልና" እያሉ አመሰገኑ። በፈጣሪው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በጦርነቱ መካከል የረዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስንም በፍጹም ማድነቅ አደነቁ። የሮማም የጦር ሠራዊት በኢትዮጵያውያን ፊት ተዋረዱ ዳግመኛም በኢትዮጵያ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። በምኒልክም ዘመነ መንግሥት ኢትዮጽያ ከጦርነት ለዓርባ ዓመት ያህል አረፈች።

የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ከአደዋ ጦርነት ከተመለሱ በኋላ በአዲስ አበባ በምትበል ከተማው መካከል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተክርስቲያን አሠራ። ስሟንም ገነተ ጽጌ ብለው ሰየሟት። ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ቦታ ሁሉ ይረዳው ነበርና። ልመና ክብሩ በኛ ለዘላለሙ በዕውነት ይደረግል። በረከቱ ከእኛ ጋር ትሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነት ይማረን ለዘለዓለሙ አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፨

(ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተአምር 17)

ቦረናን እንታደግ
24/02/2023

ቦረናን እንታደግ

https://www.facebook.com/100044640840128/posts/727661958731826/?flite=scwspnss
24/02/2023

https://www.facebook.com/100044640840128/posts/727661958731826/?flite=scwspnss

+ ረሀብ ስንት ቀን ይፈጃል? +

"ከረሃብ ሰይፍ ይሻላል" የሚል የአበው ብሂል ቢኖርም አሁን ሁለቱም እሳቶች ወገናችንን እየፈጁ ነው:: ከጦርነት እሳት ያመለጠውን የረሃብ እሳት ይቀበለዋል:: ረሃብን በምን ቃል እንግለጸው? በዚህች ደቂቃ ውስጥ አንተ ይሄን ጽሑፍ ስታነብ በረሃብ አለንጋ ክፉኛ ተገርፎ እያሸለበ ያለ ብዙ ወገን አለ::

ረሃብን ለመግለጽ ምን ቃል አለ?? ነፍሳቸውን ይማርና ሁለቱ ዕንቁ ደራስያን ጋሽ ጸጋዬ እና ጋሽ ስብሐት እንዲህ ብለው ነበር :-

ረሃብ ቀጠሮ ይሰጣል?
ወይስ ቀን ቆጥሮ ይፈጃል?
“የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል”
ይባላል፣ ድሮም ይባላል
ይዘለዝላል ይከትፋል
ብቻ እስከሚጨርስ ድረስ ሆድ ለሆድ ጊዜ ይሰጣል?

ወተት አንጀት ነጥፎ ሲላብ
ሆድ ዕቃ ደርቆ ሆድ ሲራብ
ተሟጦ አንጀት በአንጀት ሲሳብ …

የጣር ቀጠሮው ስንት ነው?
ለሰው ልጅ ሰው ለምንለው?
ላይችል ሰጥቶ ለሚያስችለው?
ስንት ቀን ነው? ስንት ሌት ነው?
(ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

"የተራቡ ልጆች አባት ምሬት :-

አበላቸው እህል ከልክለህ አምስት ልጆች የሠጠኸኝ ምነው?

አምስት ልጅ ተሰብስቦ አንድ ላይ ሲውል አንዲት ሳቅ ብቅ ሳትል መምሸቱ ምነው?

ልጆቼ አንዲት ቀን እንኳን አኩኩሉ ሳይጫወቱ ማለቃቸው ምነው?

ልጆቼን በአንድ ቀን ስቀብር ዝም ብለህ ማየትህ ምነው?"

(ጋሽ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር)

በያለንበት ለምግብ በተቀመጥን ጊዜ እያንዳንዱ ጉርሻ የሆነን ሰው ዕድሜ ሊያራዝም ይችል እንደነበረ እናስብ::
ጠጥተን የምንታጠብበትን ውኃ አጥቶ በዚህች ቅጽበት የሚያሸልብ ወገናችንን አንርሳ:: ደግመን እንላለን ጦርነት ክፉ ነው:: ረሃብ ደግሞ የባሰ ነው:: ሀገራችንን ከሁለቱም ዕረፍት ትፈልጋለች:: እስከዚያው ግን ለወገኖቻችን በየአቅጣጫው እንረባረብ!

በቦረና በረሃብ ወገኖቻችን እያለቁ ነው:: ከሰኞ ጀምሮ የእርዳታ ዘመቻ ይጀመራል::




Check this page 👇👇👇
Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

መምህራችን እና ልጅ ቢኒ እንዲሁም ሌሎች የታሰሩት አህት ወነሰድሞቻችን ተፈተዋል እንኳን ደስ ያለን !
21/02/2023

መምህራችን እና ልጅ ቢኒ እንዲሁም ሌሎች የታሰሩት አህት ወነሰድሞቻችን ተፈተዋል እንኳን ደስ ያለን !

+ በጾም ጥገቡ + አጽዋማት በመጡ ጊዜ እየደጋገምን ከምንሰማቸው ነገሮች ውስጥ "ጾም መከልከል ነው" የሚል ነው። ከምን ቢሉ በአእምሮ ከክፉ አሳብ፣ በዓይን ከመጥፎ እይታ፣ በጆሮ ከከንቱ ወሬ...
19/02/2023

+ በጾም ጥገቡ +

አጽዋማት በመጡ ጊዜ እየደጋገምን ከምንሰማቸው ነገሮች ውስጥ "ጾም መከልከል ነው" የሚል ነው። ከምን ቢሉ በአእምሮ ከክፉ አሳብ፣ በዓይን ከመጥፎ እይታ፣ በጆሮ ከከንቱ ወሬ፣ በእጅና በእግር ከክፉ ተግባር መከልከል ነው። ጾም ከክፉ ሥራ መከልከል እንደሆነ ሁሉ ለበጎ ሥራ ደግሞ መሰማራት ነው። በጾም ለከፉ ሥራ ብንዘገይም ለበጎ ሥራ ግን መፋጠን አለብን። በጾም ውስጥ በርካታ መንፈሳዊ ድርጊቶች ይከወኑበታል። ጸሎት፣ ምጽዋትና ስግደት ዋነኞቹ ቢሆኑም አርምሞና ሌሎችም ሰናይ ምግባራት የምንማርባት ጾም የሕይወት ሰሌዳ ናት። ሊቃውንት አባቶቻችን ጾምን ሲገልጿት "ጾም እማ ለጸሎት፣ ወእኅታ ለአርምሞ፣ ወነቅዓ ለአንብዕ፣ ወጥንተ ኩሉ ገድለ ሰናይት" ይሏታል።

አዎ እንደሚባለው ጾም የረሀብ አድማ አይደለም። ቁርስና ምሳ የዘለልነውንም ማምሻውን የምናካክስበትም አይደለም። ይልቁንስ ቀን የባሳቸውና ወረት ያነሳቸውን ወገኖች የምናይበት መንፈሳዊ ጉብኝት ነው። በጾም ወቅት ቁርስና ምሳን ስንዘል ለቁርስና ለምሳ የምንጠቀመውን ለወገኖቻችን የምናጋራበትም የቸርነት እጅ ነው። ጾም የኃጢአት ማስተሥርያ፣ የምሕረት መቀበያ መንፈሳዊ መሣሪያ ነው። በሌላ በኩልም ለተወሰኑ ጊዜያት በጾም የምንራበው እድሜ ዘመናቸውን በረሃብ የሚያሳልፉ ሰዎችን ለማሰብም ጭምር ነው። ስቃያቸው ይገባን ዘንድ፣ ረሃባቸውንም እንረዳው ዘንድ እንጾማለን። ጾም የምግባርና የትሩፋት ማዕድ ናት። በምግብ ስንራብ በጽድቅ የምንጠግብባት፣ የታረዙትን ስናለብስ ጸጋ እግዚአብሔርን የምንለብስባት፣ በውኃ ስንጠማ በምሕረት ጠል የምንረካባት ድንቅ የጽድቅ መንገድ ናት።

የዓቢይ/የሁዳዴ ጾምን ደግሞ ልዮ የሚያደርጋት ጹሙ ያለን የጾመባት፣ ጸልዮ ያለን የጸለየባት፣ በኋላም የሰዎችን እንባ የሚያብስ እርሱ ያነባባት ስለሆነች ነው። ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተም እንዲሁ አድርጉ ሲለን ወደ አገልግሎቱ ከመሄዱ በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ጾሟል። እኛም መጪ ጊዜዎቻችን ይባረኩልን ዘንድ፣ መንፈሳዊ ረሃባችንም ይጠግብ ዘንድ እነሆ የጌታችን ጾም ከፊታችን ናት። ጅማሬውን ፍጻሜ፣ እፍኙን ኩንታል የሚያደርግ አምላካችን በጾሙ ብዙ የምናተርፍበት ያድርግልን።

መልካም የዓቢይ/የሁዳዴ ጾም ይሁንልን።

ታምራት ለገሰ

18/02/2023

ሴራው ካልገባህ ላስረዳክ

ሴራው ካልገባህ በቀላል አማርኛ ላስረዳህምንድነው እየሆነ ያለው ብለሀል አይደል??እየሆነ ያለው ጵጵስናን የማራከስና የማቃለል ስራ በሰፊ እየተሰራ ነው ያለው! ለምን አትልም?፩- ጳጳሳት ልክ ...
18/02/2023

ሴራው ካልገባህ በቀላል አማርኛ ላስረዳህ

ምንድነው እየሆነ ያለው ብለሀል አይደል??
እየሆነ ያለው ጵጵስናን የማራከስና የማቃለል ስራ በሰፊ እየተሰራ ነው ያለው! ለምን አትልም?

፩- ጳጳሳት ልክ እንዳንተ ውሸታምና ቀጣፊ እንደሆኑ አድርገህ እንድታስብ ትላንት ተስማምተው ዛሬ ይሽራሉ እንድትል ነው ለምን እንደዛ እንድታስብ ተፈለገ???

መንፈስ ቅዱስ የሚመራውን የአባቶችህን ጉባኤና ትዕዛዝ ሰምተህ አንገትህን ለሰይፍ ግንባርህንም ለጥይት ሰጥተሀል። ነገ ላይ ቤተክርስቲያን እና አባቶች ድረስልን ሲሉህ ደሞ ነገ ዞረው ለሚስማሙት ለምን ብዬ ከፊት ልሰለፍ እንድትል ይህ ሴራ እየተጎነጎነ ነው::

፪-ጡረታ ልውጣ ያሉትም አባት ያውቁታል ስርዓቱን መኖራቸው ለስጋቸው እንዳልሆነ ታዲያ ለምን አሉ አትልም?

ሲኖዶስን እንደ መስሪያ ቤት አባቶችን እንደ ሰራተኛ አድርገህ እንድታስብ እና መንፈስ ቅዱስ የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከልብህ ላይ አስክዶ እንደመዘጋጃ አንድ ተቋም መሆኑን እንድታስብ ይህ ሴራ በእቅድ እየተሰራ ነው።

የመጨረሻው ይሄን ሁሉ ለምን አትልም?

የበቀደመ ሴራ ለምን ከሸፈ? ሕዝቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ሚለውን ብቻ ስለሰማ እና የአባቶችን ቃል እንደ እግዚአብሔር ቃል ቆጥሮ ከፊት ስለቆመ ሊሰሩት ያሰቡት ሁሉ ከሽፏል።

ስለዚህ የመንጋውን መሪ ክብርና መደመጥ የቅዱስ ሲኖዶስንም ክብር ከልብህ ካወጣ በቀላሉ መንጋው ተበተነ ማለት አይደል?

ይሄ ደግሞ ቤተክርስቲያኗን ለማፍረስ ከግማሽ በላይ መንገድ ያስጉዛቸዋል።

ወንድሜ እየሆነ ያለው ይኸው ነው ታዲያ መፍትሔው ምንድነው አትልም?

ዛሬም ከትናንቱ በላይ ዐይንህን ከቤተክርስቲያን ጆሮህንም ከቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ላይ አታንሳ!!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ልቦና ቲዩብ Libona Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category