
17/01/2025
#ፍትህ በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደለው ለአቶ አርጋው ሽኩር !!
#የሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ የልብ ደጋፊ የነበሩት አቶ አርጋው ሽኩር በድንገተኛ አደጋ በተወለዱበት ሀገር ሀዲያ ሆሳዕና ከተማ ባልታወቁ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ።
#አቶ አርጋው ሽኩር ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ፕሪምየርሊጉ ባደገበት አመት የድሬዳዋ ሀዲያ ተወላጆችን በማስተባበር ለክለባችን የዋሉት ውለታ እና በሀዲያ ጉዳይ ላይ ግንባር ቀደመ ሰው መሆናቸው አይዘነጋም ።
#አቶ አርጋው ሽኩር ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ ከድሬዳዋ ሆሳዕና መጥተው ጉዳያቸውን ጨርሰው ወደ መኖሪያ ድሬዳዋ ለማቃናት በሌሊት ሀገር ሰላም ብለው ከሆሳዕና አዲስአበባ ለመሳፈር ስያቀኑ ሆሳዕና ከተማ በኮለኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ አከባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ተወግተው ተገድለዋል !!
#ህግ ባለበት ሀገር በከተማችን ጭካኔ በተሞላ መንገድ የሰው ህይወት የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መጥቷል ።
#ይድረስ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፤ የሀዲያ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ፤ ሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንድማችንን ህይወት የቀጠፉ ሰዎች የማያዳግም ፍርድ እንድሰጥ ፍትህ እንጠይቃለን !!
#ፍትህ በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደለው ለአቶ አርጋው ሽኩር !!
ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን ነብስ ይማር !!
Hossana Entertainment
Hossana City Administration Communication affairs Office Media
Hadiya.TV
Hadiya= ሀዲያ
Hadiya zone Government Communication Affairs Department
Hadiya Legga
Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau