Kidus media

Kidus media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kidus media, Media/News Company, Addis Ababa.

17/06/2024
15/06/2024
ችግሮችን በራስ አቅም መፍታት!የከተማችን ህዝብ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የተረጂነት ስሜት እንዳይኖር ለማድረግ እየሰራ ነው! ችግሮቻችንን በዘላቂነት መፍታት እንጂ ሁሌ በዕርዳታ ማስታገስን...
09/06/2024

ችግሮችን በራስ አቅም መፍታት!

የከተማችን ህዝብ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የተረጂነት ስሜት እንዳይኖር ለማድረግ እየሰራ ነው! ችግሮቻችንን በዘላቂነት መፍታት እንጂ ሁሌ በዕርዳታ ማስታገስን ከዚህ በኋላ በቃ ብለን መንቀሳቀስ አለብን።

መንግስት በተለይ ከተማ አስተዳደራችን ችግርንና አደጋን በራስ አቅም ብቻ ለመፍታት እየሰራ ይገኛል። ችግርን በራስ አቅም በመፍታት ከዘላቂ ጥገኝነትና ተረጂነት መላቀቅ የሚቻለው ልመናን የሚፀየፍ ትውልድ በመፍጠር ነው!

በዚህ እሳቤ በመጓዝ አዲስ አበባ የራሷን ችግር በራሷ አቅም ለመፍታት የምትሻ ከተማ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ይገኛል። የትኛውንም የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት እና ለህዝቦቿች አለኝታ ለመሆን ከተማ አስተዳደሩ እየተጋ ይገኛል።

ከፒያሳ-ሜክሲኮ፣ ከሜክሲኮ- ቄራ-ወሎሰፈር- ቦሌ የኮሪደሩ ትሩፋት ያሸበረቀው መንገድ!አይን ዘግቶ የመክፈት ያክል ፍጥነት ያለው የኮሪደሩ ልማት ስራ ከፒያሳንና አራት ኪሎ ሌላ የማናቀው አዲስ...
05/06/2024

ከፒያሳ-ሜክሲኮ፣ ከሜክሲኮ- ቄራ-ወሎሰፈር- ቦሌ የኮሪደሩ ትሩፋት ያሸበረቀው መንገድ!

አይን ዘግቶ የመክፈት ያክል ፍጥነት ያለው የኮሪደሩ ልማት ስራ ከፒያሳንና አራት ኪሎ ሌላ የማናቀው አዲስ ሰፈር አስመስሎ ማራኪ መዝናኛ አድርጎ አይተናል። የሚገርመው ብዙዎች ልብ ያላሉት የኮሪደሩ ልማት ከተማዋን አቆራርጦ እንዴት በዘመናዊ መልኩ እያገናኘ እንደሆነ አለማየታችን ነው። ፒያሳ ፒያሳ ሲባል ሜክሲኮን ረሳናት እንጅ ያ ሁሉ የህዝብ ጋጋታ፣ ህገወጥ ነጋዴዎች ግርግር እና የሌቦች አስቸጋሪነት ሲበረክት የነበረበት ሜክሲኮም ልዩ ሆኗል!

ከፒያሳ በብሄራዊ አድርጎ ሜክሲኮ የሚሄደው መንገድ በታክሲ መሄድ ነውር መስሏል። የተሰራውን እያደነቁ ሲፈልጉ እያረፉ የሚሄዱበት ልዩ መንገድ ሆኗል። ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በአፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት ያለው የኮሪደሩ ድምቀት ተራምዶበት የሚጠገብ ነውን? ያረቢ! ሂዱና እዩ ብቻ! ወርቅ በተፈጥሮ ነው ይላሉ እንጂ የሰው ልጅም እጆቹን ካሰራ ወርቅ የመሰሉ ስራዎችን መስራት እንደሚችል አይተናል።

ከሜክሲኮ ቄራ አድርጎ በጎተራ አልፎ ወሎ ሰፈር ደረሶ ወደ ቦሌ መንገዶ የሚገባው መንገድ እየተሰራ ያለው ስራ፣ የተሰራበት ፍጥነት፣ አሁን የሚታየው ገፅታ አጃዒብ ነው። ምን አለፋችሁ አዲስ አበባ ሌላ ሁናለች! መንገድ ዳር መሽናት ልማድ በነበረበት ከተማ አሁን መዝናኛው ሁሉ መንገድ ዳር ሆኖ አገኘነው። የት የተገኘ ልምድ ነው ግን በአንዴ እንዲህ በአዲስ አበባ የበራው ፀሃይ?

ወዳጄ! ለሙሽራ መሞሸርያ ፎቶ ቦታ በፍለጋ የምታገኝ የአዲስ አበባ ህዝብ አሁን በየመንገዱ ከፒያሳ እስከ ሜክሲኮ፣ ስትፈልግ ከሜክሲኮ ቄራ አይ ካልክ ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ ሰፊ ቦታ በአማራ ተፈጥሮ ይጠብቀሃል። ለቲክታክ መስሪያ ቦታ ሲመርጥ የነበረ ሁላ አሁን ሁሉ ቦታዎች የተመረጡ ሆነዋል። እንግዳም ከመጣ ከከተማ ወጣ ማለት አይጠበቅባችሁም እዚው ዞራችሁ የማትጨርሱ መዝናኛ አለላችሁ፣ በምሽት ሲሆን ደግሞ ልዩ ነው!

30/05/2024

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kidus media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share