Sami model cast

Sami model cast Arts and entertainment

sisters sweet  catering ሆሳዕና 🍥🥟🎂ለልደት ፣ለምርቃት ፣ለሽምግልና ፣ለbraid to be ፣ለmom to be እንዲሁም ለአራስ መውጫ እና ለማንኛውም ፕሮግራሞች ደውለው ይዘዙንበ...
07/06/2024

sisters sweet catering ሆሳዕና 🍥🥟🎂

ለልደት ፣ለምርቃት ፣ለሽምግልና ፣ለbraid to be ፣ለmom to be እንዲሁም ለአራስ መውጫ እና ለማንኛውም ፕሮግራሞች ደውለው ይዘዙን

በስልክ ቁጥር 0934798835 . . .0906983335
0913123827 ....0912615261 ይደውሉልን 📞

የሁልጊዜ ምርጫችን ሎራዶበ0930077913/16 ላይ ይደውሉ።https://www.tiktok.com/.ethiopiaSemu N Kedir መልካም ስራ እህትነት 👊
02/06/2024

የሁልጊዜ ምርጫችን ሎራዶ
በ0930077913/16 ላይ ይደውሉ።
https://www.tiktok.com/.ethiopia

Semu N Kedir መልካም ስራ እህትነት 👊

"  #የሚስቶቼ  #ባሎች " የተሰኘውን ቴአትር  ነገ አብረን ብናየውስ ? #ደራሲ አበባየሁ ታደሰ  #አዘጋጆች ተስፋዬ ገ/ማርያም እና ይገረም ደጀኔ አስቴር                  #ተዋን...
28/05/2024

" #የሚስቶቼ #ባሎች " የተሰኘውን ቴአትር ነገ አብረን ብናየውስ ?

#ደራሲ
አበባየሁ ታደሰ

#አዘጋጆች
ተስፋዬ ገ/ማርያም እና
ይገረም ደጀኔ አስቴር

#ተዋንያን

ይገረም ደጀኔ ( አስቴር )
ሸዊት ከበደ
ሔኖክ ብርሃኑ
የምሥራች ግርማ
ብሩክ ምናሴ ( ቡቡ )

#ዘውግ ኮሜዲ #መቼት አሜሪካ

ዘወትር ረቡዕ 11:30 ሰዓት
በዓለም ሲኒማ

ሳሚ ኢቨንትና የማስታወቂያ ስራሳሚ ኤቨንትና ፕሮሞሽን ድርጅታችን ከሚሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ....👇🏼👉የተለያዩ መድረክ ማስተዋወቅ 👉የተለያዩ ዝግጅቶች ማስተባበር ( Event )👉 የቴሌቪዥንና...
14/05/2024

ሳሚ ኢቨንትና የማስታወቂያ ስራ
ሳሚ ኤቨንትና ፕሮሞሽን ድርጅታችን ከሚሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ....👇🏼

👉የተለያዩ መድረክ ማስተዋወቅ
👉የተለያዩ ዝግጅቶች ማስተባበር ( Event )
👉 የቴሌቪዥንና ሬዲዮ ማስታወቂያ ማዘጋጀት
👉 የሞዴሊንግ አጫጭር ስልጠናውን መስጠት....

እንግዲ ከፈለጉን በስልክ ቁጥር 0911018540 ይደውሉልን !

04/05/2024

በዋቸሞ ዩንቨርስቲ በተከናወኑ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ዘጋቢ ፊልም!!! - https://www.facebook.com/EBCzenaየመዝናኛ...

 # የጤንነቶ ጉዳይ ያሳስቦታል ? አዎ ለራሶና ለቤተሰቦ ጤንነት ማሰብና ቅድሚያ መስጠት ብልህነት እና አርቆ አሳቢነት ነው ~ እንግዲያውስ አያሳስቦት አስተማማኝ እና ዘመኑን የዋጀ  የህክምና...
04/05/2024

# የጤንነቶ ጉዳይ ያሳስቦታል ?
አዎ ለራሶና ለቤተሰቦ ጤንነት ማሰብና ቅድሚያ መስጠት ብልህነት እና አርቆ አሳቢነት ነው
~ እንግዲያውስ አያሳስቦት አስተማማኝ እና ዘመኑን የዋጀ የህክምና አገልግሎት በብቃት ወደምንሰጥበት ዶ/ር ይድነቃቸው መካከለኛ ክሊንክ ጎራ ይበሉ ።
~ በቅርቡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና በሆነችው ሆሳዕና በከፈትነው የህክምና መስጫ ተቋማችን የካበተ ልምድና እውቀት ባላቸው ስፔሻሊስት ሀኪሞች የታገዘ የ24 ሰዓት አገልግሎት በብቃትና በጥራት መስጠት
ጀምረናል ።
~ ብቃትና ጥራት ደግሞ መለያችን ስለሆነ እርሶም ወደ ዶ/ር ይድነቃቸው መካከለኛ ክሊንክ ጎራ ካሉ በአገልግሎታችን በሚገባ እረክተው ይመለሳሉ ።
በዶ/ር ይድነቃቸው መካከለኛ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች
👉 ማንኛውም የድንገተኛ ህክምና
👉 የውስጥ ደዌ ህክምና
👉 የህጻናት ህክምና
👉 የቆዳ ህክምና
👉 ከ አንገት በላይ ህክምና
👉 የነርቭ ህክምና
👉 የመለስተኛ ቀዶ ህክምና
👉 እጅግ የዘመነ የህፃናት ግርዛት ( ከ7 ቀን ጀምሮ
👉 በተሟላ ላብራቶሪ የኢሲጂ(የልብ ምርመራ) አልትራሳውንድ የ24 ሰዓት አገልግሎት እንሰጣለን ።
"ዕልፍ ህይወት ማዳን አላማችን ነው"
ዶ/ር ይድነቃቸው መካከለኛ ክሊኒክ ሆሳዕና #አድራሻችን ከቪዥን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 100 ሜትር ከፍ ብሎ ያገኙናል።
ስልክ 0913822574\0916674431 ይደውሉ መረጃ ይውሰዱ ።
🙏🙏 መልካም በዓል ይሁንላቹ ...🙏🙏

የመጨረሻዉ ዙር ድምፅ መስጠት ከ 2 ቀናት በኋላ ያበቃል! 13ኛው የለዛ ሽልማት የመጨረሻ ዙር እጩዎች ድምፅ መስጠት ከ 4ቀናት በኋላ ያበቃል! ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to...
29/04/2024

የመጨረሻዉ ዙር ድምፅ መስጠት ከ 2 ቀናት በኋላ ያበቃል!

13ኛው የለዛ ሽልማት የመጨረሻ ዙር እጩዎች ድምፅ መስጠት ከ 4ቀናት በኋላ ያበቃል!

ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ላይ የለዛ ሞባይል መተግበሪያን ወይም https://Vote.leza.show ተጠቅመው ለ Hana Fekadu Cru ድምጽዎን ይስጡ፤ ኪነ ጥበብን ያበረታቱ!

ለዛ ሽልማት
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር

1 ሺህ 206 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ*********(አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14/ 2016 ዓ.ም)  በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነ...
22/04/2024

1 ሺህ 206 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
*********

(አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14/ 2016 ዓ.ም) በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 206 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 1 ሺህ 206 ዜጎች ውስጥ 994 ወንዶች፣ 172 ሴቶች፣ 6 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እና 40 ጨቅላ ህፃናት ናቸው።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የኢፌዴሪ መንግስት በሰራው ዜጋ ተኮር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ7800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

የጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ "ሉዱንዳ" የተሰኘ  አዲስ የጠቅላላ እውቀት መጽሐፍ የፊታችን አርብ ለንባብ ይበቃል። መጽሐፉ ጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እስከ ፋና 98.1...
21/04/2024

የጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ "ሉዱንዳ" የተሰኘ አዲስ የጠቅላላ እውቀት መጽሐፍ የፊታችን አርብ ለንባብ ይበቃል። መጽሐፉ ጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እስከ ፋና 98.1 በሰራባቸው ከ6 ለበለጡ ዓመታት ያዘጋጀው ለነበረው የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ መርሐግብር ይሰበስባቸው የነበሩ የጠቅላላ እውቀት መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ በአንድ የያዘ ነው።

"ሉዱንዳ" መጽሐፍ በ17 ምዕራፎች ከ190 በላይ አስገራሚ መረጃዎች፣ አስደማሚ ክስተቶችንና ጠቃሚ መረጃዎችን ይዞ በ159 ገፅ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል።

በተለይ የንባብ ፍላጎት በተቀዛቀዘበትና ስለአንድ ነገር ለማወቅ ሰፋ ያለ ፅሁፍ አገላብጦ መረዳት የተራራ ያህል በከበደበት በዚህ ሰዓት፣ በርካታ የእውቀት ዘርፎችን የተመለከቱ መረጃዎችን በአንድ የያዘው ሉዱንዳ የመረጃ ብፌ ሆኖ ያገለግላል።

የመጽሐፉ ርዕስ ''ሉዱንዳ'' የቃሉን ትርጓሜ የሀድይሳ ቃል ሆኖ የሁለት ቃላት ጥምር ነው።''ሉዱ" እና "ሁንዳ''ፍቺውም ጠቅላላ ዕውቀት የሚል አቻ ትርጉም ያለው ወይንም (ከሁሉም የተቀነጫጨበ ዕውቀት) እንደማለት ነው ።

"ሉዱንዳ" አርብ ሚያዚያ 18 በ10:00 በወ መዘክር አዳራሽ፣ አንጋፋና ወጣት ደራሲያን የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

መፅሀፉ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቅርቡ ሆሳዕና ከተማም ይመረቃል ።

የሐረር ሰው ለፀብ አይመችም!Shuwalid in Harar -    የሐረር ሰው እጅግ ሲበዛ ሰላም ወዳድ ነው።  የሳቅና ጨዋታ ሙዳችንን የሚከንፍ ሰው ከመጣ አንሰማውም። "በቃ እንደፈለክ! አቦ...
17/04/2024

የሐረር ሰው ለፀብ አይመችም!
Shuwalid in Harar -



የሐረር ሰው እጅግ ሲበዛ ሰላም ወዳድ ነው። የሳቅና ጨዋታ ሙዳችንን የሚከንፍ ሰው ከመጣ አንሰማውም። "በቃ እንደፈለክ! አቦ በቃ ፥ለደንታቹ ነው፥የመሰላቹሁን አድርጉ፤ኡፍፍ በቃ ተውን፥ደስ እንደአለህ እንዳአለሽ፥የተመችህን ደስ ያለህን አርግ ኻላስ! አብሽራ " ነው የምንለው።በቃ ንዝንዝ ንትርክ፥ጥላቻን አጥብቀን እንጠላለን።
#በንትርክና ንዝንዝ ላይ ደፍረህ ከዚህ በላይ የመሄድ አቅም የለህም። ምክንያቱም አንተ የፈለከውንና ደስ ያለህን እንድታደርግና ከቻልክም ከፊታቸው ዞር እንድትል ነው ፍላጎታችን። በቃ ለመነዛነዝ አፒታይዘራቻን ዝግ ነው። በቃ አንፈልግማ።ለሐረር ሰው ነገሮችን ለማስረዳትና ለመረዳት ሐረር ለመሔድ ከአዲስ አበባ ተነስቼ፥ደቡብ ሱዳን ሄጄ ግብፅ ምሳ በልቼ ማለት አይጠበቅብህም ፥በአጭሩ አጭርና ግልፅ አማረኛ እንጂ ዙሪያ ጥምጥም አካሄድ አይገባውም።ይሄን ከአደረክ በቆምክበት ጥሎህ ላሽ ነው።

ሐረር መወለድ በራሱ ነው ሰላም ፥እረፍት፥ቅንነት፥ደግነት፥ፍቅር፥አንድነትና ግልፀኝነት እንድውም ጭንቅ አለመውደድን ተጎናፅፈህ ስለምታድግ መታደል ነው ብል ማጋነን አይሆንም።ብቻ ለፀብ የማንመች፤ግልፅና ማኛ የሆንን ህዝብ ነን። ብቻ ከፈለክ ይሄን አርግ ካልፈለክ ይሄንንም እንደአማራጭ ውሰድ ይልሀል፥ሁሉም ካልተመቸህ ስራህ ያውጣህ ብሎ ያቀጥነዋልና።

የፋቅር ሀገር ሀረር !

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱርዝም ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የመግቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።የጉረግኛ የቀቤንኛ  እና የማረቆኛ ቋንቋዎችን በሞባይል መተግበሪያ የ...
16/04/2024

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱርዝም ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የመግቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የጉረግኛ የቀቤንኛ እና የማረቆኛ ቋንቋዎችን በሞባይል መተግበሪያ የመሰነድ እና የመጠቀም ስራ ለመስራት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱርዝም ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የመግቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የህብረተሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከነዝህም ለአብነት የየም ብሄረሰብ ባህላዊ መድሃኒት ቅመመን ለማዘመን ተመራማሪዎችን መድቦ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣

በሀገር ደረጃ የማህበረሰብ ቋንቋ ድጂታላይዝድ እንዲሆንና እንዲሰነድ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በርካታ ስራዎች መሰራቱን ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ብሮ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ በክልሉ ያሉ ቋንቋዎች ለሁለገብ ስልጣኔ እንዲሆኑ በተደራጀ መንገድ ድጅታላይዝድ ሆነው እንዲሰነዱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የሀገር በቀል እውቀት ጥናት ዳይሬክተር አቶ እያሱ ጥላሁን የኢትዮጵያን ቋንቋዎች በአንድ ቋት መሰነድ ፕሮጀክት ላይ እስካሁን ከ14 በላይ ቋንዎችን መሰነድ መቻሉን ጠቁመው፣

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሉ ውስጥ ካሉ ቋንቋዎች ጉራግኛ ቀቤንኛና ማረቆኛ ቋንዎች ብቻ ድጂታላይዝድ ያልተደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው እነሱንም ለመሰነድ እና ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚያዝያ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነት እና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

‘አስተውሎት’ - ፊልም ተመረቀ   |  በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ‘አስተውሎት’ የተሰኘ ፊልም በዛሬው እለት ተመርቋል።በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር...
16/04/2024

‘አስተውሎት’ - ፊልም ተመረቀ

| በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ‘አስተውሎት’ የተሰኘ ፊልም በዛሬው እለት ተመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ሰውኛ ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይመንት አማካኝነት የተዘጋጀው ‘አስተውሎት’ ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የተሰሩ ሮቦቶችንና ሰዎች በጥምረት የሰሩት ፊልም ነው ተብሏል፡፡

ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) ፊልሙ የተሻለ ነገን እንድናይ ዛሬን ከትናንት በተሻለ እንድንኖር የሚያግዝ ነው ብለዋል።

We are excited to share that the launching ceremony of CARE ALL PLC was successfully held today at AG Hotel, Hossana, wi...
15/04/2024

We are excited to share that the launching ceremony of CARE ALL PLC was successfully held today at AG Hotel, Hossana, with the participation of 30 founding members. This event marked a significant milestone for the establishment of CARE ALL HOSPITAL.

CONTACT US HERE :-
Email- [email protected]
Telegram - https://t.me/careallhospitallphone
Instagram - https://www.instagram.com/care_allhospital
linkdin - https://www.linkedin.com/groups/13002746
Facebook - https://www.facebook.com/profile.php?id=61557805269569
phone number - +251945333697

Eid Mubarak !
10/04/2024

Eid Mubarak !

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ -አልፈጥር ረመዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! Eid Mubarak !
10/04/2024

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ -አልፈጥር ረመዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

Eid Mubarak !

ሁለተኛው ዙር ተጀምራል ! የአዋሳ ከተማ አምባሳደር ለሆነችው አርቲስት ሀና ፈቃዱን በለዛ አዋርድ ላይ ድምፅ እንስጣት ✋️መረጃውን ሼር በማድረግ ይተባበሩን !የመጨረሻው ዙር ድምፅ የመስጠት ...
01/04/2024

ሁለተኛው ዙር ተጀምራል !

የአዋሳ ከተማ አምባሳደር ለሆነችው አርቲስት ሀና ፈቃዱን በለዛ አዋርድ ላይ ድምፅ እንስጣት ✋️

መረጃውን ሼር በማድረግ ይተባበሩን !

የመጨረሻው ዙር ድምፅ የመስጠት ሂደት ተጀምሯል
ውድ የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች እነሆ 13ኛ የለዛ ሽልማት ሒደት ቀጥሏል፡ ሁለተኛው እና የመጨረሻው ዙር ላይ ደርሰናል፡፡

የዳኞችና የህዝብ ድምፅ ተሰብስቦ በተገኘው ውጤት መሰረት ለዚህ ለመጨረሻው ዙር የደረሱት የኪነ ጥበብ ስራዎች እና ጥበበኞች ከየ ዘርፍ ዘርፉ ተለይተው ታውቀዋል አሁንም ሁለተኛው እና የመጨረሻው ዙር እነሆ ተጀምሯል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የነበረው ኪነ ጥበብን ማበርታትና የመደገፍ ተሳትፏችሁ በሁለተኛውም ዙር ይቀጥል ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ለምትወዷቸው የኪነ ጥበብ ስራዎች ጥበበኞች ከየ ምድብ ምድቡ ላለፉት አምስት አምስት እጩዎች ድምፃችሁን በVote.leza.show ትሰጡ ዘንድ ኪነጥበብና ጥበበኞችን በማበርታት ተሳትፏውም ትገፉበት ዘንድ ይሁን !

በመሪ ተዋናይነት እንዲሁም በድርሰት በዳይሬክቲንግ ፕሮዲዩስ በማድረግ ድንቅ ብቃቷን ያሳየችንን እጩ የአመቱ ምርጥ ሴት ተዋናይት Hana Fekadu Cru ን በ #7ጊዜ7 ፊልም ከታች ባለው ሊንክ ላይ እየገባን እንምረጣት 👇🏼✋️

https://vote.leza.show/

የማስታወቂያ ሰዓት !ሪች family ዲዛይን 👗🛍ለሰርግ ለመልስ ለልደት ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሆን አልባሳት ክራይ እና ሽያጭ ጨምሮ ሪች family ዲዛይን ከመጡ ያገኛሉ !አድራሻ፦ ሆሳዕና ...
31/03/2024

የማስታወቂያ ሰዓት !

ሪች family ዲዛይን 👗🛍

ለሰርግ ለመልስ ለልደት ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሆን አልባሳት ክራይ እና ሽያጭ ጨምሮ ሪች family ዲዛይን ከመጡ ያገኛሉ !

አድራሻ፦ ሆሳዕና በረከት ሆቴል ግራውንድ ስር እንገኛለን !

ለበለጠ መረጃ ፦ 0916696816 ቢደውሉ ያገኙናል !

ለመልካም ነገር መቼም ቢሆን ረፍዶ አያውቅም !"ዕብደት በህብረት" ቲያትር በአዋሳ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ።በቅርቡ ከአርባምንጭ ሲመለሱ ላጣናቸው ወንድምቻችን ቤተሰብ የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ የ...
28/03/2024

ለመልካም ነገር መቼም ቢሆን ረፍዶ አያውቅም !

"ዕብደት በህብረት" ቲያትር በአዋሳ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ።

በቅርቡ ከአርባምንጭ ሲመለሱ ላጣናቸው ወንድምቻችን ቤተሰብ የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ የኪነ-ጥበብ ምሽት በአዋሳ ከተማ በነገው እለት ይካሄዳል !

በነገ እለት በአዋሳ ከተማ በመሀል ፒያሳ በሲዳማ የባህል አዳራሽ ከ 11 ሰዓት ጀምሮ የተወዳጁ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ "እብደት በህብረት" የተሰኘ የመድረክ ቲያትር በድምቀት ይታያል...ይመረቃል !

ታዲያ...አንድ ቲያትሩን መታደም አንድም በሞት ያጣናቸው ቤተሰብ ማገዝ ነውና ቲያትሩን እንድታደሙ በአክብሮት እንጋብዛለን !

መግቢያ ትኬቶች አዋሳ ከተማ በአራቱም አቅጣጫ እየተሸጠ ይገኛል...

መግቢያ ትኬቱን ለማግኘት 0912885682 ይደውሉልን !

ዞዊ የቤት ለቤት  ህክምና  አገልግሎት ZOWIE HOME HEALTH CARE SERVICE 🛖የምንሰጣቸው አገልግሎቶች🏘 የቤት ለቤት ህክምና ክትትል እና የምክር አገልግሎት (በሐኪሞች እና በስፔ...
28/03/2024

ዞዊ የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት

ZOWIE HOME HEALTH CARE SERVICE

🛖የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🏘 የቤት ለቤት ህክምና ክትትል እና የምክር አገልግሎት (በሐኪሞች እና በስፔሻሊስቶች )
🏘የ24 ሰአት የነርስ ክትትል

🏘 ቁስልን በኬሚካል አጥቦ የማሸግ አገልግሎት (dressing)

🏘 በሀኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን መስጠት (Medication)

🏘የሽንት ቱቦ ማስገባትና መቀየር (Catheterization)

🏘 ለደም ግፊት ፣ ስኳር እና ካንሰር ህመምተኞች ክትትልና የማስታመም አገልግሎት መስጠት

🏠 መመገብ ለማይችሉ ህመምተኞች የመመገቢያ ቱቦ ማስገባት (NG tube)

🏠🩺የቤት ለቤት የአረጋውያን እንክብካቤ አገልግሎት

🏠🩺በጤና ባለሙያ የ ህመምተኞች የውጭ ሀገር የህክምና ጉዞ ማመቻቸት እና እጀባ
🏠🩺የነርሶች የሞግዚትነት አገልግሎት

🏠🩺የቤት ለቤት የፊዝዮቴራፒ (Physiotherapy) አገልግሎት

🏠🩺በሐኪሞች እና በስፔሻሊስቶች የቤት ለቤት እይታ (Home Based patient round)

🩺ሆስፒታል ውስጥ አስተማሚን ተክቶ የማስተማም አገልግሎት
🩺ለድርጅቶች የዱቤ የቤት ለቤት የማስታመም እና እንክብካቤ አገልግሎት

🏠👉 አጠቃላይ የጤና ምርመራ በቤትዎ
🏠👉የሆስፒታል ሪፈራል አገልግሎት
🏠👉 የስነ አእምሮ ህክምና ክትትልና ማማከር
🏠👉 የላቦራቶሪ አገልግሎት
🏠 ኦክስጂን ኮንሰንትሬተር (oxygen concentratet ),; የአክታ ማውጫ ማሽን( suction machine) , የህሙማን አልጋ (patient Bed),ዊልቸር በተመጣጣኝ ዋጋ እናክራያለን

🩺👩‍⚕ ሁሉንም አገልግሎቶች ብቃት ባላቸው ሐኪሞች እና ነርሶች እንዲሁም በተለያዩ የጥቅል አማራጮች ያሉበት ድረስ መጥተን አገልግሎት እንሰጣለን።

🏡 ☎️ 0924064146../ 0993552295_0906375554
https://t.me/zaLAZ034z6wyZDU0
አድራሻ
አዲስ አበባ ; ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለ ፊት

4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.34

Email፡[email protected]

Phone no.
0924064146
0906375554
0993552295

የማስታወቂያ ሰዓት !Je's online shopping 👠👗🛍ለበለጠ መረጃ 0948934186 📞እንዲሁም ከታች ባስቀመጥነው የቴሌግራም አድራሻችን ሊያገኙንና ሊጎበኙን ይችላሉ !https://t.m...
28/03/2024

የማስታወቂያ ሰዓት !

Je's online shopping 👠👗🛍

ለበለጠ መረጃ 0948934186 📞

እንዲሁም ከታች ባስቀመጥነው የቴሌግራም አድራሻችን ሊያገኙንና ሊጎበኙን ይችላሉ !
https://t.me/Jerrytesfayee

  የህዝብ ድምጽ አሰጣጥዛሬ ከምሽቱ 6 ሰአት ይጠናቀቃል በምርጥ ተዋናይት ዘርፍ አርቲስት ሀና ፍቃዱ በአንደኝነት እየመራች ትገኛለች። አንድ ሰው እስከ ሶስት ግዜ ድምጽ መስጠት የሚችል በመሆ...
20/03/2024

የህዝብ ድምጽ አሰጣጥ
ዛሬ ከምሽቱ 6 ሰአት ይጠናቀቃል በምርጥ ተዋናይት ዘርፍ አርቲስት ሀና ፍቃዱ በአንደኝነት እየመራች ትገኛለች።

አንድ ሰው እስከ ሶስት ግዜ ድምጽ መስጠት የሚችል በመሆኑ በመጨረሻዎቹ ሰአታት ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ...

የአመቱ ምርጥ ፊልም 7 ጊዜ 70
የአመቱ ምርጥ ተዋናይት ሀና ፍቃዱ
የአመቱ ምርጥ ተዋናይ ሄኖክ ዘርአብሩክን በመምረጥ በከተማችን አዳዲስ እና ወጣት ባለሙያዎች የተሰራው "ሰባት ግዜ ሰባ" ፊልም እንዲያሸንፍ የራሳችንን ጠጠር እናስቀምጥ :- ሊንክ 👇👇

https://vote.leza.show/

ሼር በማድረግ ለሁሉም ያድርሱ 🙏🙏

ዶ/ር በየነ መካከለኛ ክሊኒክ ሆሳዕና 🩺ዶ/ር በየነ አበራ መካከለኛ ክሊኒክ እነሆ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች በተጨማሪ ለታካሚዎቹ ማስገባቱን ምክንያት በማድረግ የቦታ ጥበት ስላጋጠው የስራ ...
18/03/2024

ዶ/ር በየነ መካከለኛ ክሊኒክ ሆሳዕና 🩺

ዶ/ር በየነ አበራ መካከለኛ ክሊኒክ እነሆ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች በተጨማሪ ለታካሚዎቹ ማስገባቱን ምክንያት በማድረግ የቦታ ጥበት ስላጋጠው የስራ ቦታውን ሁሉንም መስተንግዶ አንድ ቦታ ወደሚያገኙበት ለታካሚዎቹ ምቹና አስተማማኝ ወደሆነ ቦታ የአድራሻ ለውጥ ማድረጋችንን ስነግሮ በደስታ ነው !

ይምጡና ይጎብኙን ለጤናዎ ሁሌም እንተጋለን 🩺

አዲሱ አድራሻችን ፦ ሆሳዕና አዲሱ መናኸሪያ አጠገብ ወደ እስታዲየም በሚመስደው መንገድ በቀኝ በኩል ያገኙናል !

ለበለጠ መረጃ ፦ በስልክ 0925745969
ወይም 0952423232 ይደውሉልን 📞

የማዕፀንና ፅንስ እስፔሻሊስት
Dr. በየነ አበራ መካከለኛ ክሊኒክ ሆሳዕና 🩺

ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ፦ጉዳዩ:- በሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያዎች (Facebook Fake Account) ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ስለማሳሰብ ይሆናል፡፡ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞ...
06/03/2024

ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ፦

ጉዳዩ:- በሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያዎች (Facebook Fake Account) ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ስለማሳሰብ ይሆናል፡፡

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመንግሥት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በብቃትና በቁርጠኝነት እየተወጣ የሚገኝ ተቋም ነው።

በዚህም ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ተቋሙ በሁሉም ዘርፎች የዩኒቨርሲቲና የአካባቢ ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት፣ በቁጭት እና በቁርጠኝነት መንፈስ ተግቶ በመስራት በሀገር ደረጃ እውቅና ያገኘ ጠንካራ ተቋም ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተቋሙ ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን የሚገልጹ ሰነዶችን በአሉታዊ ጎን በመተርጎም እና የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲስተጓጎል ሙከራ ማድረግ፣ የተረጋጋ ተቋም እንዳይሆን ሁከትና ትርምስ ለመፍጠር መሞከር፣ ህዝብንና ሀገርን በሙያቸው በማገልገል ላይ የሚገኙና ለተቋሙ በጎ እይታ ያላቸውን ሰዎች እና የተቋሙን የስራ ኃላፊዎች ማሸማቀቅ እና ስም ማጥፋት፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አካላት እርስ በርሳቸው እንዳይተማመኑ ለማድረግ አቅዶ በመስራት እንዲሁም አፍራሽ ዓላማ በማንገብ የሚሠሩ ጥቂት ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ባለቤቶችና ግብረ-አበሮች በሀሰት በሚለቁትና በሚያሰራጩት መረጃ የተቋሙን ማህበረሰብ ለማሳሳትና ለማደናገር የሚደረግ ከመሆኑም በላይ የውስጥ አሠራር ሂደት ያልተከተሉና ያልተገመገሙ መረጃዎች ስለሆኑ፣

መላው ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እያሳሰብን ተቋሙ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ያልተገባ መረጃዎችን በሚያሰራጩ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ እና ተከታትሎ ለህግ የሚያቀርብ መሆኑን ጭምር ያሳስባል።

በዚሁ አጋጣሚ ከሰሞኑ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት በኩል በወጣው ልዩ ኦዲት እና የግለሰቦችን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ለሁለት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ተከፈለ የተባለዉን ክፊያንና የግለሰቦችን አቤቱታ በማየት የተቋሙ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት መልሶ በሰነድ በማስደገፍ እንዲያቀርብ በማለት የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን ውጤቱ ተጠናቆ ስመጣ ለግቢው ማህበረሰብ የምናሳውቅ መሆኑን ከወዲው እንገልፃለን።

Let Your Light Shine in the Society!

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር

የካቲት 27/2016 ዓ.ም

በአፍሪካ 9ኛው በኢትዮጰያ አምስተኛው  የትምህርት ቤት ምገባ ቀን  በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተከበረ፡፡=============================የካቲት 22/2016ዓም (ትሚ) በአፍሪካ...
02/03/2024

በአፍሪካ 9ኛው በኢትዮጰያ አምስተኛው የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተከበረ፡፡
=============================

የካቲት 22/2016ዓም (ትሚ) በአፍሪካ 9ኛው በኢትዮጰያ አምስተኛው የትምህርት ቤት ምገባ ቀን " ለሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ ለተሻለ ትውልድ ግንባታ!!" በሚል መሪ ቃል በሀገር ደረጃ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ተከበረ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበዓሉ ላይ ተገኝተው የትምህርት ቤት ምገባ ወጪ ሳይሆን በመጪው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ የሚደረግ አዋጭና ዘላቂ የሰብዓዊ ልማት ኢንቨስትመንት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መርሃ-ግብሩ በአግባቡ ከተተገበረ የልጆችን አካላዊና አዕምሮኣዊ ዕድገት በማፋጠንና ጤንነታቸውን በመጠበቅ የተማሪዎችን የትምህርት ውጤታማነት እንዲሻሻል በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የትምህርት ቤት ምገባ እንደሃገር በመንግሰት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ያለና ከ6.2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ተጠቃሚ ያደረገ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የመንግስት አካላት፣የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶችና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ታዳጊዎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ለመገንባት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍ እያበረከቱ ላሉት አስተዋጽኦ አመስግነው በቀጣይም ድጋፋቸውን ይበልጥ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሃር በበኩላቸው ከተማ መስተዳድሩ ለትምህርት ቤት ምገባ ከፍተኛ ትኩረት ስጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአለም ምግብ ፕሮግራም ተወካይ ሚስተር ኤልቪስ ኦድኬ ኢትዮጵያ በዚህ አመት በትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ተጠቃሚ በማድረግ በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ መሆኑዋን ጠቅሰው በቀጣይም እ.አ.አ. በ2030 ሁሉንም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብር ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራች ያለችው ስራ ስኬታማ እንዲሆን ተቋማቸውም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጽዋል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልልና ከተማ መስተዳደር ትምህርት ቢሮ፥ የሴክተር መ/ቤቶች ተወካዮችና አመራሮች፥ ሌሎችም ባለድርሻና አጋር አካላት እንዲሁም የዴሬደዋ ከተማ መስተዳደር አመራሮች፥ የአከባቢው ማህበረስብ ተወካዮች የተሳተፋ ሲሆን ስኬታማ የትምህርት ቤት ምገባ ስራዎች ተጎብኝተዋል ።

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

ጌጃ ገሪቦ (የሀዲያው ፊታውራሪ)በሀዲያ ዞን በቀድሞ አጠራር ኮንቶም ወረዳ፤ በአሁኑ ሌሞ ወረዳ ዱባንቾ ቀበሌ ልዩ ስሙ ለምሰላ በሚባልበት አከባቢ 1860 ዓ/ም ተወለዱ።ፊታውራሪ ጌጃ የአጤ ም...
02/03/2024

ጌጃ ገሪቦ (የሀዲያው ፊታውራሪ)

በሀዲያ ዞን በቀድሞ አጠራር ኮንቶም ወረዳ፤ በአሁኑ ሌሞ ወረዳ ዱባንቾ ቀበሌ ልዩ ስሙ ለምሰላ በሚባልበት አከባቢ 1860 ዓ/ም ተወለዱ።

ፊታውራሪ ጌጃ የአጤ ምንሊክን የክተት አዋጅ በመቀበል የጣሊያንን ጦር ለመመከት በ28 ዓመታቸው ወደ አድዋ ዘምተዋል።

አድዋ በነበረው የአንድ ቀን ጦርነት ኢትዮጵያ ድል ከተጎናፀፈች በኋላ ጣሊያን ዳግም ወረራ ባካሄደበት በማይጨው ጦርነት ለሁለተኛ ጊዜ ከሀዲያና ከምባታ 5000 እግረኞችንና 1000 ፈረሰኞችን በማስከተል ለሀገር ግንባታ የተዋደቁ ፊታውራሪ ናቸው።

ውድ ህይወታቸውንም በተንቤን ግንባር አጥተዋል።

የተለያዩ ተቋማትና የቦታ ስያሜዎች በስማቸው የተሰየሙ ሲሆን አዲስ አበባ መግቢያ አካባቢ በተለምዶ ሬዲዮ ጣቢያ ተብሎ በሚጠራበት "ጌጃ ጀዌ" እና የአዲስ አበባው "ጌጃ ሰፈር" የሚጠቀሱ ናቸው።

እንኳን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ድል አደረሳችሁ!

የፊንላንድ መንግስት በትምህርት ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::የካቲት 12/2016 ...
20/02/2024

የፊንላንድ መንግስት በትምህርት ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የካቲት 12/2016 ዓ.ም (ትሚ) የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የሁለቱ ወገኖች ውይይት ያተኮረው በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የትኩረት መስኮች ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን በዋነኝነትም በአካቶ እና የልዩ ፍለጎት ትምህርት ላይ ያሉ ጉድለቶችን ለመሙላት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በውይይቱ ወቅት ባደረጉት ገለጻ ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረት ውስጥ የፊንላንድ መንግሰትና ህዝብ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ እያይዘው በኢትዮጵያና ፊንላንድ መንግሰት መካከል ያለው ዘላቂ የትምህርት ትብብር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ትብብር ማሳያ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ፡፡

በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ክብርት አምባሳደሯ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባደረጉት ገለጻ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በትምህርቱ ዘርፍ በተለይም በአካቶና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

The Government of Finland pledged to strengthen its support in the education sector.
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
Her Excellency Ayelech Eshete,State Minister of the Ministry of Education, hosted the Finland Ambassador to Ethiopia,today.

During their meeting the two parties held disscussion inline with their education partnership and cooperation particularly in areas of their prior interest in the General Education sector.

At the meantime, the State Minister,recognized the existing strong and strategic partnership of the Government of Ethiopia and Finland,and urges to strength it in the year to comes.

Her excellency Sinikka Antila,Finland Ambassador to Ethiopia, in her part pledged her government's unwavering commitment to support the Ethiopian Education Sector.

Inline with that the Ambassador noted her Government's readiness to operate new projects in its various forms of Cooperation and Partnership Programs.

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -http

http://vote.leza.showሐምሌ 1 2013 - ሰኔ 30 2015      ፲፫ ተኛው አብረን ተጉዘናል ሁሉም ጥሩ ይሆናል ! ከ16 ዓመት በፊት ሸገር ራዲዮ ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን ሲጀም...
19/02/2024

http://vote.leza.show
ሐምሌ 1 2013 - ሰኔ 30 2015

፲፫ ተኛው

አብረን ተጉዘናል ሁሉም ጥሩ ይሆናል ! ከ16 ዓመት በፊት ሸገር ራዲዮ ጣቢያ መደበኛ ስርጭቱን ሲጀምር የተከፈተ ዘፈን ነበር። ያኔ ዕወቁ የሙዚቃ ሠው ደረጃ መኰንን ፀደኒያ ገ/ማርቆስንና ሌቨንን አሳትፎ የሠራው ይሄንን ሙዚቃ ለዛሬው የላዛ ፕሮግራም አዘጋጅ ከሌሎች አራትና አምስት ሙዚቃዎች ጋር አዳብሎ ሠጥቶት ነበርና ነው ይሄ ዘፈን ለመክፈቻነት የዋለው .: በስተኋላ ሚካኤል በላይነህ የተጫወተው መሆኑ ነው። እናም ውድ የኪነጥበብ አፍቃሪያን አብረን መጓዝ ከጀመርን ኪነጥበብንና ጥበበኞችን ማወደስ፣ ማክበር፣ መዘከረ ከጀመርን 13 ዓመታት ። አሁንም አብረን ተጉዘናል ሁሉም ጥሩ ይሆናል !
ያለፉት 12 ዓመታት እንዲህ እንደዋዛ የታለፉ አይደሉምና አብረን እናንተን ይዘን መጓዛችን ሽክማችን እንዲቀል ሆኗል። ዘንድሮም ለ13ኛ ጊዜ የሚከናወነው የለዛ የሽልማት ስነ-ስርዓት እንደተለመደው በ12 ዘርፎች ይሠጣል። የዓመቱ ምርጥ ዘፈን እና የህይወት ዘመን ዘርፎች 100 ፐርሰንት በዳኞችና ሙያተችን ድምፅ የሚወሰን ሲሆን የሙዚቃ ቪዲዮ እና ነጠላ ዜማ ዘርፎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ በአድማጭ ተመልካች ድምፅ የሚወሠኑ ናቸው። የሙዚቃ ቪዲዮ ምድብ አልበም አውጥተው የሙዚቃ ቪዲዮ የቀረበላችው ስራዎች ብቻ ናቸው በዕጩነት የሚቀርቡት :: ሌሎች ዘርፎች 50 ፐርሰንት አድማጭ ተመልካች 50 ፐርሰንት ሙያተኛ ዳኞች በሚሠጡት ድምፅ ይወሰናል። . ለ1 ወር የመጀመሪያው ዙር ከተከናወነ በኋላ ለሁለተኛው ዙር ከየምድቡ የተመረጡ አምስት አምስት ስራዎች በሁለተኛው ዙር ድምፅ ተሰቶባቸው ተሸላሚ ይሆናሉ፡
ያለፉት 2 ዓመታት እንደሃገር የገጠሙን ሳንካዎች ሊያስጉዙን ባይችሉም the Show must go on ትርዒቱ ይቀጥላል! በችግርና ፈተናም ውስጥ ቢኮንም ኪነጥበባዊ ስራዎች መታያት መሠራታቸው ግድነው ቢልም ስርዓቱ ይህንን ግን መከወን ተስኖን ሁለት ዓመታት ተቆጥረዋል። እኛ እንኳን the Show must go on ሂደቱ መቀጠል አለበት ብንል እና ዝግጅቱን ለመከወን ብናስብ በቂ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ለመታየት ለመደመጥ ለመሠራት ባለመቻላችው የግድ ሁሉም ጥሩ እስኪሆን ሁሉም ጥሩ ይሆናል እያልን መጠበቅ ነበረብንና በአመቱ ሳናሳካው ለመቅረታችን ምክንያት ሆኗል። 12 ተኛውንና 13 ተኛውን በአንድ ደብለንም 13 ተኛው የለዛ የሽልማት ስነስርዓት በሚልም ከ ሀምሌ 1 - 20 13- ሰኔ 30 - 2015 ዓ.ም ድረስ ለወጡ የኪነጥበብ ስራዎች ተገቢውን ክብር ለመስጠት እየተጋን ነው :: እነም እናንት የኪነጥበብ ወዳጅ ፣ ደጋፊ ፣ አበርቺዎች አሁንም በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ለወጡ ስራዎች ኪነ ጥበባዊ ፋይዳቸው ከፍ ላሉባችሁ ሙያተኞች እና ስራ ቸውhttp://vote.leza.show ወይንም ከቴሌ ብር ሱፐር አፕ ላይ Leza Award የሚለውን መተግበሪያ በማውረድ ድምፃችሁን በመሥጠት ሁሌም እንደምንለው መፈከሪያችንም እንደሆነው " ሁላችንም ሚና አለን" ሚናችሁን እንድታወጡ ኪነጥበብና ሙያተኞቿን እንድታ ክበሩ በአክብሮት እንጠይቃለን።
የ13 ተኛው የለዛ ሽልማት ሂደት በይፋ ተጀምሯል ና የ ሃሳቡን ፅኑነት የወደፊት ተስፋውንም በኪነ ጥበብ ቤተሰብ ዘንድ የማስረጽ ሃሳባችን፦ የድምፅ ሰጡ ሂደቱንም በተለለያዩ መንገዶች በማህበራዊ ትስስር ገጾቻችሁ በአየር ሞገዶቻችን ታስተጋቡልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን ። አብርን ተጉዞን እዚህ ደርሰናል! ወደ ፊትም እንጓዛለን ! አብረን ተጉዘናል ሁሉም ጥሩ ይሆናል እንዲል ታላቁ ሙዚቀኛ ደረጀ መኮንን :: ድምፆችሁን በመስጠት የኪነጥበብ ቤተሰብን አበርቱ

ጋዜጠኛዋ የተሰኘ ፊልማችን 🎬 🎬የአመቱ ምርጥ ፊልም በመሆን በለዛ አዋርድ ላይ በእጩነት ቀርቧል 🙏🥇🙏 ሴቶች ፣ ጋዜጠኞችና አካል ጉዳተኞች ላይ ትኩረት ያደረገው ጋዜጠኛዋ የተሰኘ ፊልማችን ለ...
19/02/2024

ጋዜጠኛዋ የተሰኘ ፊልማችን 🎬 🎬
የአመቱ ምርጥ ፊልም በመሆን በለዛ አዋርድ ላይ በእጩነት ቀርቧል 🙏🥇🙏

ሴቶች ፣ ጋዜጠኞችና አካል ጉዳተኞች ላይ ትኩረት ያደረገው ጋዜጠኛዋ የተሰኘ ፊልማችን ለዛ አዋርድ ላይ በመታጨቱ የተሰማንን ልባዊ ደስታ ለመግለፅ እንወዳለን !

ለኪነ-ጥበብ አፋቃሪያንና ለጋዜጠኛዋ ፊልም ወዳጆች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ / አለን ለማለት እንወዳለን...

ጋዜጠኛዋ ፊልም ከታች 👇🏼 በተዘረዘሩት በሶስቱም ዘርፍ እጩ መሆን ችሏል !

1. Best Movie of the year
( የአመቱ ምርጥ ፊልም ) 👇🏻
👉 Gazetegnawa ጋዜጠኛዋ ✔️

2. Best Actress of the year
የአመቱ ምርጥ ተዋናይት 👇🏻
Elianna Birhanu ( Gazetegnawa )
👉ኤልያና ብርሃኑ ( ጋዜጠኛዋ ) ✔️

3. Best Actor of the year
የአመቱ ምርጥ ተዋናይ 👇🏼
Fares Biru ( Gazetegnwa )
👉ፋሪስ ብሩ ( ጋዜጠኛዋ ) ✔️

ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ፊልማችን በለዛ አዋርድ ላይ እጩ መሆን ይታወቃል...

በመሆኑም 👉 ( Leza award voting website ) ውስጥ እየገባችሁ ድምፅ እንድትሆኑኑን በአብሮት እንጠይቃለን 🙏

መረጃው ሼር በማድረግ የምንም ጊዜ ትብብሮ እና እገዛዎ አይለየን 🙌

ስለምታደርጉ ሁሉ እገዛና መልካምነት ከልብ ለማመስገን እንወዳለን 🙏🙏🙏

ዝክረ አድዋ!!ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ይቀርባል፡፡አብርሃም  ግዛው  ኢንተርቴመንት  ‹‹ኢ...
17/02/2024

ዝክረ አድዋ!!

ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ይቀርባል፡፡አብርሃም ግዛው ኢንተርቴመንት ‹‹ኢትዮጵያዊነት ዝክረ አድዋ› › የተሰኘ ትልቅ የኪነ-ጥበብ እና የማነቃቂያ ዝግጅቶች ስለ ሰላምና አንድነት ዙሪያ ላይ ታዋቂ ፖለቲከኞች ንግግር ያቀርባሉ፡፡ በእለቱ ከጥንታዊ ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ጀግኖች አርበኞች ሽለላን ፉከራ በሻሎም የባህል ባንድ ታጅበዉ ያቀርባሉ።

ተጋባዥ ሰርፕራይዝ እንግዶች በእለቱ በመገኘት መልክቶቻቸውን ያስተላልፋሉ፡፡ የዚህ የኢትዮጵያውያን የአፍሪካም ብሎም የጥቁር ህዝቦች የአሸናፊነት ምልክት በሆነው የአድዋ ድል ዋዜማ በሚካሄው ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ታዋቂ ግለሰቦች ፣አርቲስቶች፣ጋዜጠኞች እና የስነ-ጽሁፍ አፍቃሪዎችና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በሚገኙበት ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰአት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይካሄዳል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911018540

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sami model cast posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sami model cast:

Videos

Share


Other Modeling Agencies in Addis Ababa

Show All