Hallelujah ACE

Hallelujah ACE ACT 2:-38-42

04/04/2024
11/03/2024

33ኛዉ ዋራ ቤቴል
ነፃ ወጣሁኝ እስራቴም ተበጣጠሰ
ኢየሱስ ስመጣ ነገር ሁሉ ተገለበጠ

11/03/2024
እንኳን ለ33ኛው ዓመት የዋራ ቤቴል አለም አቀፍ ጉባኤ በሰላም አደረሳችሁ!በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት መቋቋሙ ይታወሳል። የሚዲያ አገልግሎት ክፍሉ ስራውን ...
11/03/2024

እንኳን ለ33ኛው ዓመት የዋራ ቤቴል አለም አቀፍ ጉባኤ በሰላም አደረሳችሁ!

በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት መቋቋሙ ይታወሳል። የሚዲያ አገልግሎት ክፍሉ ስራውን በይፋ የጀመረ ሲሆን፣ ቤተክርስቲያንን በሚመጥን ደረጃ ዝግጅቱን ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው።

አገልግሎቱም እንደ መነሻ “አሜን-የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን መልቲ ሚዲያ አገልግሎት” የተሰኘ የቴሌግራም ቻናል የከፈተ ሲሆን በቅርቡ ለታሰቡት የማህበራዊና ዲጂታል ሚዲያ አማራጮች እንደ መደላድል የምንጠቀምበት አማራጭ ይሆናል። ከዚህም በተጨማሪ ከክፍሉ የሚተላለፉ የጅማሬ ማስታወቂያዎችና ዝግጅቶች ወደ ቅዱሳን የሚደርሱበት መንገድ ይሆናል።

ቻናሉን አሁኑኑ ለመቀላቀል ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ!👇🏽

https://t.me/AmenApostolicMedia

የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት ክፍል

በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሳችሁ፥ የሁላችን ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠራችሁ ሁሉ! ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ...
29/11/2023

በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሳችሁ፥ የሁላችን ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠራችሁ ሁሉ!

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን!

ዛሬም ለልጆቹ ለራሱ ክብርና ለአካሉ መታነጽ የሚሆነውን ልዩ ልዩ ጸጋ እንደ ፈቀደ የሚሰጠው አምላካችንን እየባረክን በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የኅብረ-ዝማሬ መዘምራን የተዘጋጀውንና "እግዚአብሔር አንድ ነው!" የተሰኘውን የዝማሬ ሰንዱቅ ስናቀርብላችሁ ለምስጋናና ለመታነጽ እንዲሆንላችሁ በማመን ነው።

በዚህ የዝማሬ ዝግጅት በሁሉም አቅጣጫ የተሳተፉትን ሁሉ እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ በወሰነው በረከቱ አትረፍርፎ እንዲባርካቸው እየጸለይን ጌታችን ቢፈቅድ ብንኖር አልበሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ እጃችሁ ባለው ስልክ ላይ በሚገኘው የአፖስቶሊክ ሶንግስ መተግበሪያ ላይ ዝግጁ ይሆናል።

የኦዲዮ ቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል

ኅዳር 2016 ዓ.ም

28/11/2023
🙏🙏🙏Wooowww❤❤❤👇👇👇👇
27/11/2023

🙏🙏🙏Wooowww❤❤❤

👇👇👇👇

25/11/2023

(13th)
13ኛው የሰሜን ወላይታ ቅ/ሰበካ አመታዊ ጉባኤ እነሆ ደረሰ!!

ያኔ የዛሬ 2000 ዓመታት በፊት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው እንድልክ የጠራቸው የበጉ ሐዋርያት ከሌሎች የጌታ ተከታዮች ጋር 120 ሰዎች ሆነው አብረው ሲጸልዩ በዓለ ሃምሳ የተባለው ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶ የተገለጠው እና "ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ" (ሐዋ 2፥38) የሚለው መዳን የሚገኝበት ቁልፍ ትምህርት ለኢትዮጵያም ደርሶ ነበር (ሐዋ 8፥26)።

ይህ ለሐዋርያት የተገለጠው የመዳን ትምህርት ሳይበረዝና ሳይከለስ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ (ሐዋ 1፥8) እንዳለ በአገራችን በዚህም ዘመን በሙላት ተገለጠ። በዚህም ሂደት እግዚአብሔር በዚህ በመጨረሻው ዘመን ያስነሳቸውን ባሪዎቹን በመላክ የእውነትን ወንጌል እንዲያደርሱ ተጠቅሞባቸዋል።

ዛሬ ላይ ቤተክርስቲያን ምእመናኖቿ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ፣ ከ50 በላይ ሰበካዎችና ቅርንጫፍ ሰበካዎች ተደራጅተው በሚንቀሳቀሱ በሺሆች የሚቆጠሩ አጥቢያዎች እና አገልጋዮች ያሉባት ደረጃ ላይ ደርሳለች። ለዚህ ሁሉ ያበቃንን አምላካችን የተመሰገነ ይሁን።

እንግዲህ ከእነዚህ ቅ/ሰበካዎች ውስጥ አንዱ ደግሞ የሰሜን ወላይታ ቅ/ሰበካ ነው። የሰሜን ወላይታ ቅ/ሰበካ ከኢትዮጵያ ሐ/ቤ/ያን ዋናው ጽ/ቤት መቀመጫ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በ299 ኪ.ሜ ርቀት ሆሳዕና-ወላይታ ሶዶ መስመር ላይ የሚገኝ ሲሆን ከወላይታ ሰበካ በሰሜናዊው ክፍል ከሶዶ ከተማ በ29 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።

ቀድሞ ወላይታ ሰበካ የሚባለው ግንቦት 2003 ዓ.ም በአራት ቅ/ሰበካዎች ከተከፋፈለ ቦኃላ የሰሜን ወላይታ ቅ/ሰበካ ራሱን የቻለ ቅርንጫፍ ሆኖ የወጣ ሲሆን በውስጡ 16 ንዑስ ሰበካዎችና 162 አጥቢያዎችን የያዘ ግዙፍ ቅ/ሰበካ ነው።

በየአመቱ በታህሳስ ወር የሚካሄደወው 13ኛው የቅ/ሰበካው አብይ ጉባኤ ልጀምር እነሆ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል። ከታህሳስ 04-07/2016 ዓ.ም ለአራት ቀናት ለሚካሄደው ለዚህ ጉባኤ የእግዚአብሔር ቅዱሳን በጾም እና በጸሎት በምልጃም እንዲሁም የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ የጌታ ኢየሱስን በርቱ ክንድና ከአራቱም አቅጣጫዎች የሚመጡ ቅዱሳንን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን አደረሰን!!

ኮንፍረንሱ በሚጀመርበት ሐሙስ እለት ልክ ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ በአረካ ከተማ በአራቱም አቅጣጫዎች የቅ/ሰበካው መዘምራን በአጠቃላይ ተሰልፈው ከአመት አመት ያደረሳቸውን አምላካቸውን በጣፋጭ ዝማሬ የዘንባባን ዝንጣፍ ይዘው ሲያወድሱ፣ ካህናት ከፊት ለፊት ወንጌልን ይዘው እየመሩ ወደ ከተማዋ ይገባሉ። በከተማይቱ መሃል አደባባይ ላይ ይህ የሐዋርያት ወንጌል በገሃድ ለሰው ሁሉ ይሰበካል።

ከዚያ በመቀጠል ከአራቱም አቅጣጫ የተሰበሰቡ ቅዱሳን ከዋናው አደባባይ ኮንፍረንስ ወደሚካሄድበት ቸርች አጥር ግቢ ያቀናሉ፣ የጉባኤውም ጅማሬ ይሆናል። በዚህም ጉባኤ ጌታ ኢየሱስ የወደደውን እንደፈቃዱ ያድርግ እያለን ለታመነው አምላካችን አደራን እንሰጣለን።

ሁላችሁም ከዚህ ከታላቁ ግብዣ እንድትካፈሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ተጋብዛችኋል!!

"የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል። በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ

የአባታችን የአምላካችንና የጌታችን ብሩካን ሁሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን!የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በይዲድያ መዘምራን ህብረት በኦሮምኛ ቋንቋ የተዘጋጀው...
25/11/2023

የአባታችን የአምላካችንና የጌታችን ብሩካን ሁሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን!

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በይዲድያ መዘምራን ህብረት በኦሮምኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን 2ኛ የዝማሬ ሰንዱቅ (Album) ለመታነጽና ለበረከት እንዲሆንላችሁ ወደ እናንተ በዚህ እሁድ ያቀርባል።

ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ 9፥12 “ደግሞ በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር ይበዛል፤” እንዳለ የዝማሬ ጸጋ ከላይ በተቀበሉ ወንድሞችና እህቶች የሚዘጋጁትን መዝሙሮች በትክክለኛው መንገድ በማግኘት ምስጋናችን ለእግዚአብሔር እንዲበዛ ምክንያት እንደሚሆኑልን እምነታችን ብሎም ጸሎታችን ነው።

በኢትዮጵያ ያላችሁ ተጠቃሚዎቻችን ዝማሬዎቹን ለማውረድ የምትጠቀሙበትን ኮድ በቴሌግራም ቦት ላይ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ከኢትዮጵያ ውጪ ያላችሁ ደግሞ ክሬዲት ካርድ በመጠቀም አልበሙን ማግኘት እንደምትችሉ እንገልፃለን።

የኦዲዮ ቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል

ህዳር 2016 ዓ.ም

Awikalehu🙏🙏
25/11/2023

Awikalehu🙏🙏

https://youtu.be/cPfq_SdRUJc?si=7D-b7yPG5vRBOnjEFaarsaa maxxansa 2ffaa Gurmuu Faarfattoota Yidiidiyaan qophaa`e ilaalchi...
25/11/2023

https://youtu.be/cPfq_SdRUJc?si=7D-b7yPG5vRBOnjE

Faarsaa maxxansa 2ffaa Gurmuu Faarfattoota Yidiidiyaan qophaa`e ilaalchisuun Kenname kan gadhiifamu sadaasa 16/2016 dha.
በይዲድያ መዘምራን ህብረት በተዘጋጀው 2ኛ አልበም አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ።
መዝሙሩ በApostolic Songs መተግበሪያ ለይ የሚለቀቀው ህዳር 16/2016 ነው ።
Koodii argachuuf/ኮዱን ለመገኘት:-
0921310201 Br. Abel
0942503619 Br. Robe
0935218592 Br. Zalalem
0917624079 Br. Amanti
0921745931 Br. Aboma
0969256069 Br. Bonsa

Faarsaan Gurmuu Faarfattoota Yidiidiyaa Album 2ffaan guyyaa gaafa sadaasa 16/2016 waan gadi lakkifamuuf ammuma irraa kaa...
22/11/2023

Faarsaan Gurmuu Faarfattoota Yidiidiyaa Album 2ffaan guyyaa gaafa sadaasa 16/2016 waan gadi lakkifamuuf ammuma irraa kaasun galmaa`un koodii faarsaa kanaa Gurmuu Faarfattoota Yidiidiyaa qunnamuun argachuu nii dandeessu.

https://youtu.be/ZUxqXqt1ZL4?si=CGL8pMSvQrLMEu3aComing soon 2nd Album  OROMIC SONGSby YIDIDIIYAA  CHOIRApostolic Church ...
21/11/2023

https://youtu.be/ZUxqXqt1ZL4?si=CGL8pMSvQrLMEu3a
Coming soon
2nd Album OROMIC SONGS
by YIDIDIIYAA CHOIR
Apostolic Church of Ethiopia
For More information
Facebook :YidiidiyaaWaldaaErgamootaa
Telegram :
Youtube :YidiidiyaaWaldaaErgamootaa
Tiktok :YidiidiyaaWaldaaErgamootaa

05/11/2023

“ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።”
— መዝሙር 92፥12

05/11/2023

“The righteous shall flourish like the palm tree: he shall grow like a cedar in Lebanon.”
— Psalms 92:12

05/11/2023

“Namni qajeelaan akka muka meexxii biqila in tola, akka gaattiraa Libaanosis ol in guddata.”
— Far. 92:12

02/11/2023

Degu Kebede part 1

02/11/2023

Bishop Degu Kebede

02/11/2023

Bishop Terefe Feka

31/10/2023

መዝሙር 91
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
² እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።
³ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።
⁴ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
⁵ ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥
⁶ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።
⁷ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
⁸ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።
⁹ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
¹⁰ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
¹¹ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
¹² እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
¹³ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።

Psalms 91 (KJV)¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹ He that dwelleth in the secret place of the most High shall abide under the shadow of the Alm...
31/10/2023

Psalms 91 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ He that dwelleth in the secret place of the most High shall abide under the shadow of the Almighty.
² I will say of the LORD, He is my refuge and my fortress: my God; in him will I trust.
³ Surely he shall deliver thee from the snare of the fowler, and from the noisome pestilence.
⁴ He shall cover thee with his feathers, and under his wings shalt thou trust: his truth shall be thy shield and buckler.
⁵ Thou shalt not be afraid for the terror by night; nor for the arrow that flieth by day;
⁶ Nor for the pestilence that walketh in darkness; nor for the destruction that wasteth at noonday.
⁷ A thousand shall fall at thy side, and ten thousand at thy right hand; but it shall not come nigh thee.
⁸ Only with thine eyes shalt thou behold and see the reward of the wicked.
⁹ Because thou hast made the LORD, which is my refuge, even the most High, thy habitation;
¹⁰ There shall no evil befall thee, neither shall any plague come nigh thy dwelling.
¹¹ For he shall give his angels charge over thee, to keep thee in all thy ways.
¹² They shall bear thee up in their hands, lest thou dash thy foot against a stone.
¹³ Thou shalt tread upon the lion and adder: the young lion and the dragon shalt thou trample under feet.
¹⁴ Because he hath set his love upon me, therefore will I deliver him: I will set him on high, because he hath known my name.
¹⁵ He shall call upon me, and I will answer him: I will be with him in trouble; I will deliver him, and honour him.
¹⁶ With long life will I satisfy him, and shew him my salvation.

Address

Addis Ababa

Telephone

+251928628410

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hallelujah ACE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hallelujah ACE:

Videos

Share

Category