Nahoo Television

Nahoo Television Nahoo TV Nahoo TV is a private Infotainment TV station with a motto of promoting Ethiopian Culture.

Nahoo Tv is a privately held media company established in 2016 in Ethipia with a motto of promoting Ethiopian Culture, History & general well being of the society. Main Office
Rosetta Bldg. 2nd Floor # 14/2010, Addis Ababa, Ethiopia

በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት ያለ እድሜ ጋብቻ በደቡብና ሰሜን ወሎ ሆን እየጨመረ መሆኑ ተገለፀ። የትምህርት ተቋማት በጦርነቱ ምክንያ...
27/12/2024

በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት ያለ እድሜ ጋብቻ በደቡብና ሰሜን ወሎ ሆን እየጨመረ መሆኑ ተገለፀ።
የትምህርት ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት የተዘጉባቸዉ አካባቢዎች ላይ ያሉ ህፃናት በቤተሰቦቻቸዉ አስገዳጂነት እድሜያቸዉ ሳይደርስ እየተዳሩ መሆኑን የገለፁት የደቡብ ወሎ ዞን ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ቤተልሄም ሰሎሞን መምሪያዉ ከተቀበላቸዉ 100 ያለእድሜ ጋብቻ ሊፈፀም ነዉ ጥቆማ ዉስጥ ማስቆም የቻለዉ ስምንቱን ብቻ ነዉ ብለዋል፡፡
በሰሜን ወሎ ዞንም አሁን ላይ ጦርነት እየተካሄደባቸዉ ባሉ አካባቢዎች ባለሙያዎች ገብተዉ ሰራ መስራት ካለመቻል ባለፈ ያለእድሜ ጋብቻን ለመቆጣጠር የህግ አስከባሪ አካላት በቀበሌዎች ባለመኖራቸዉ ችግሩን ለመከላከል አስቸጋሪ አድርጎታልም ብለዋል፡፡ በመምሪያዉ የህፃናት መብት ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ በበኩላቸው ያለ እድሜ ጋብቻ ጎልቶ የሚታይበት የደቡብ ወሎ ከላላ ወረዳ በርካታ ትምህርት ቤቶች ዝግ ከመሆናቸዉ ጋር በተያያዘ ከአመት አመት ህፃናትን ያለ እድሜያቸዉ መዳር አየጨመረ እንደሆነ መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ አስነብቧል።
ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡ ሴት ተማሪዎች ቁጥር መቀነስ ያሳሰበዉ የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ለሁለተኛ ዙር ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ምዝገባ እያደረገ ቢሆንም ያለእድሜ ጋብቻ ፈተና መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ገልፀዋል።
አሁን ላይ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን ያለእድሜ ጋብቻን በድብቅ መፈፀም እየተበራከተ በመምጣቱ ባለድርሻ አካላት ችግሩን ለመቅረፍ ርብርብ እንዲያደርጉም ተጠይቋል።

የህዝብን እና የመንግስትን መሬት የወረረን ግለሰብ ተጠያቂ ማድረጉን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀየአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ...
27/12/2024

የህዝብን እና የመንግስትን መሬት የወረረን ግለሰብ ተጠያቂ ማድረጉን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ቶልቻ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሬት ባንክ የገባን የህዝብና የመንግስትን መሬት በህገወጥ መንገድ ለግል ጥቅም ለማዋል የተወረረን መሬት ማስመለሱ አስታውቋል።
ግለሰቡ በሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ 477.61ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ በማጠር የወረረ መሆኑን በባለስልጣኑ የለሚኩራ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር አባላቱ በተደረገው ክትትል የተደረሰበት መሆኑ ተጠቁሟል።
ባለስልጣኑ መረጃውን በማጣራት ከፖሊስ አባላት ጋር በመሆን ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል በሊዝ አዋጅ ተጠያቂ እንዲሆን እና እንዲቀጣ ክስ እንዲመሰረት በማድረግ የታጠረውን ቦታ በማፍረስ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ማድረጉን ገልጿል።
ባለስልጣኑ በህገ ወጦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ደንብ የሚተላለፉ አንዳንድ ግድ የሌሽና ስግብግብ ግለሠቦችን ነዋሪዎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመርን በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረቡን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢሰመጉ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል መታገዳቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ላለፉት 33 ዓመት ስራ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ...
27/12/2024

ኢሰመጉ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል መታገዳቸውን ይፋ አደረጉ፡፡
ላለፉት 33 ዓመት ስራ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስሥልጣን መታገዳቸውን በይፋ አስታውቀዋል።
ሁለቱም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በተቆጣጣሪ ባለሥልጣኑ በተጻፈ ደብዳቤ "ከማንኛውም እንቅስቃሴዎች" መታገዳቸውን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ሐሙስ ታህሳስ 17 ባሰራጨው መግለጫ፤ "በታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በደረሰን ደብዳቤ ድርጅታችን ከማንኛውም እንቅስቃሴዎች እገዳ እንደተጣለበት ተገልጾልናል" ብሏል።
ኢሰመጉም እገዳው የተላለፈበት በተመሳሳይ ቀን በተላከ ደብዳቤ መሆኑን በመግለጫው ጠቁሟል። ነገር ግን ሁለቱም ድርጅቶች የታገዱበት ደብዳቤ የተጻፈው በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን አስታውቀዋል።
ባለስልጣኑ በጻፈው ደብዳቤ "ድርጅቶቹ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ መንቀሳቀሳቸው፣ ገለልተኛ አለመሆናቸው፣ ግልጽ የሆነ የአደረጃጀት መዋቅር የሌለው መሆኑ" ለእገዳው በምክንያትነት የተጠቀሱ ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪም "ድርጅቱ ሃላፊነት በጎደለው መልኩ የተንቀሳቀሰ መሆኑ በተደረገ ክትትልና ግምገማ ለማረጋገጥ ተችሏል" ሲል ባለሥልጣኑ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ለተቋማቱ በጻፈው ደብዳቤ ላይ አትቷል። ነገር ግን ሁለቱም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በባለሥልጣኑ የቀረበባቸውን ክስ አስተባብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በመግለጫው "ድርጅታችን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ በየትኛውም ያልተገባ ወይም ከህግ የሚጻረር እንቅስቃሴ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የማያውቅ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን" ብሏል።

ኢሠማኮ ሠራተኛውን የሚወክል ፓርቲ እንዲያቋቁም ተጠየቀ፡፡ሠራተኞች እየገጠማቸው ያለውን ችግር ለማቃለልና መብቶቻቸውንም ለማስጠበቅ የሚያስችል የሠራተኞች ፓርቲ ማቋቋም እንዲቻል እንዲያደርግ የ...
26/12/2024

ኢሠማኮ ሠራተኛውን የሚወክል ፓርቲ እንዲያቋቁም ተጠየቀ፡፡
ሠራተኞች እየገጠማቸው ያለውን ችግር ለማቃለልና መብቶቻቸውንም ለማስጠበቅ የሚያስችል የሠራተኞች ፓርቲ ማቋቋም እንዲቻል እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሽን (ኢሠማኮ) ተጠይቋል፡፡
‹‹እኛ እንደ ሠራተኛ በሚኒስቴር ደረጃ የተወከለ የለንም፡፡ ሁልጊዜ የሥራና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ እየተባለ የሚጠቀሰው ቀርቶ ቢያንስ ሠራተኛውን የሚወክል ሚኒስቴር ይኑረን›› ተብሏል፡፡
የሌበር ፓርቲ ጉዳይ “እኔ በቀላሉ የምመልሰው ጉዳይ አይደለም” ያሉት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ “በሕገ ደንባችን መሠረት ፓርቲ ማቋቋም አንችልም” ብለዋል፡፡
ነገር ግን በሥራ ላይ ያሉና የተቋቋሙ ፓርቲዎችን ማገዝ እንደሚቻል ጠቅሰዋል፡፡ ለጊዜው የአገራችን ፖለቲካ “አይዶሎጂ ላይ የተመሠረተ አይደለም” ያሉት አቶ ካሳሁን አይዶሎጂ ላይ ያልተመሠረተ ደግሞ፣ ለእኛ አይጠቅመንም ሲሉ አክለዋል፡፡
እኛ የራሳችንን ፓርቲ እናቋቁም ከተባለ ደግሞ ይህንን ለማድረግ “ጥናት ማድረግን ይጠይቃል”ማለታቸውን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ኢሰማኮ ግን በቀጥታ ፓርቲ ማቋቋም እንደማይችል በመግለጽ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አንጋፋውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን ማገዱ ተሰማ፡፡ኢሰመጉ የታገደው ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አድር...
26/12/2024

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አንጋፋውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን ማገዱ ተሰማ፡፡
ኢሰመጉ የታገደው ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አድርጓል በማለት ሲሆን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹና ሠራተኞቹ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
የኢሰመጉ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚሁ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ መግለጹ ማስታወሱን እና በትናንትናው እለት መታገዱን የተለያዩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበውታል፡፡
ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ “ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል” በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው አይዘነጋም።
በተመሳሳይ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ጨምሮ ሶስት የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ላይ እገዳ ተጥሎ እንደነበር እና ቆይቶም እገዳው የተነሳ ቢሆንም በድጋሚ እገዳው ተጥሏል የሚል መረጃዎች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ትኩረት ያልተሰጠው ጉዳይ መሆኑ ተገለፀ።ይህ የተገለፀው የሴቶች እና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍሪደም ፈንድ ጋር በመተባበር የሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ...
23/12/2024

በኢትዮጵያ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ትኩረት ያልተሰጠው ጉዳይ መሆኑ ተገለፀ።
ይህ የተገለፀው የሴቶች እና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍሪደም ፈንድ ጋር በመተባበር የሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ጥረት ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።
ከኢትዮጵያ ወደተለያዩ ሀገራት የሚፈልሱ አብዛኞቹ ፍልሰተኞች የኢኮኖሚ ፍልሰተኞች መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ በሕገወጥ የሚደረጉ ፍልሰቶች ዜጎችን ለከፍተኛ ችግር እያጋለጠ እንደሆነም ተመላክቷል።
በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ከ200 ሚሊዮን በላይ ፍልሰተኞች እንደሚገኙ እና ከ180 ሚሊዮን በላዩ የከፋ የጉልበት ብዝበዛ እንደሚደርሳቸው ነው የአለም አቀፍ ፍልሰተኞች መረጃ የሚያመላክተው።
በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዩ አቶ ደረጀ ጥግ ይበሉ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አሳሳቢነትን በመረዳት ፖሊሲ እሰከማሻሻል ደርሶ ድርጊቱን ለመከላከል እና አጥፍዎችን በሕግ ለመጠየቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከ2014 ወዲህ ከ280 ሺህ በላይ በችግር ውስጥ የነበሩ ስደተኞችን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉንም ተናግረዋል።
ስደተኞችን ወደ ሀገር ውስጥ በመመለስ ሂደት ውስጥ የሴቶች እና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍሪደም ፈንድ ጋር በመተባበር ከስደት ተመላሾችን መልሶ የማቋቋም ስራው እየተከናወነ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
ፍትህ ሚኒስቴርን ወክለው የተገኙት አቶ አብርሀም በበኩላቸው በኢትዮጵያ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተገቢ ትኩረት ያልተሰጠው መሆኑን ገልጸው፣ ከኢትዮጵያ ወደተለያዩ ሀገራት የሚፈልሱ አብዛኞቹ ፍልሰተኞች የኢኮኖሚ ፍልሰተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘገባው የባልደረባችን ኢሳያስ አሸናፊ ነው፡፡

በገበያ ላይ የሚገኙ ጥራታቸው ያልተረጋገጠ የፀረ-ወባ መድሀኒትቶች ማህበረሰቡ ከመጠቀም እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በገበያ ላይ የሚገኙ አን...
23/12/2024

በገበያ ላይ የሚገኙ ጥራታቸው ያልተረጋገጠ የፀረ-ወባ መድሀኒትቶች ማህበረሰቡ ከመጠቀም እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በገበያ ላይ የሚገኙ አንዳንድ የፀረ -ወባ መድሀኒቶች ጥራታቸው ያልተረጋገጠ እና ለጤና ጎጂ በመሆናቸው ማህበረሰቡ ከመጠቀም አዲቆጠብ አሳስቧል፡፡
ደህንነት እና ጥራታቸው በባለስልጣኑ ያልተረጋገጡ መድሀኒቶች ለጤና ጎጂ እና የከፋ ችግር የሚያስከትሉ በመሆናቸው በምስሉ ላይ የተዘረዘሩትን መለያ ቁጥር የያዙ መድሀኒቶች ከመግዛት እንዲቆጠቡ እንዲሁም በቤት ውስጥ የሚገኝ ከሆነም ማህበረሰቡ በአፋጣኝ እንዲያሶግዱ ባለስልጣኑ መመሪያን አስተላልፏል፡፡
መድሀኒቶቹም ማላሪያ ቤንን ጨምሮ ስምንት ያህል ሲሆኑ ማህበረሰቡ ከመግዛትም ሆነ ከመጠቀም እንዲቆጠብ እንዲሁም የመድሀኒት መደብሮች ለገበያ እንዳይቀርቡ ነው ባለስልጣኑ የጠቆመው፡፡

በክልሎች የሚገኙ አየር ማረፊያ ተርሚናሎች ለአካል ጉዳተኛ ደንበኞች ምቹ አገልግሎት የመስጠት አቅም እንደሌላቸው ተገለፀ፡፡የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አደረኩት ባለው ጥናት እና ሪፖርት...
23/12/2024

በክልሎች የሚገኙ አየር ማረፊያ ተርሚናሎች ለአካል ጉዳተኛ ደንበኞች ምቹ አገልግሎት የመስጠት አቅም እንደሌላቸው ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አደረኩት ባለው ጥናት እና ሪፖርት የአካል ጉዳተኞች በአየር መንገድ አገልግሎቶች ላይ ምቹ መገልገያዎችን ለመስጠት ክፍተት እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡
ይህን ተከትሎም በተለይም በክልሎች ላይ የሚገኙ የአየር ማረፊያ ተርሚናሎች ውስጥ ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጥ አገልግሎት ምቹ እንዳልሆነ እና ተጠቃሚዎቹም ለተጨማሪ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሪፖርቱም በክልል በሚገኙ አየር ማረፊያ ተርሚናሎች ወደ አውሮፕላን ለመግባትም ሆነ ከአውሮፕላን ወጥቶ ለመሄድ የመጓጓዣ አገልግሎት የማይሰጥ በመሆኑ በተለይ በዝናብ ወቅት እና በረሃማ በሆኑ አካባቢዎች አካል ጉዳተኞች ለተጨማሪ እንግልት መዳረጋቸው ማወቅ መቻሉን አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም የዐይነ ስውራን አቅጣጫ መጠቆሚያ ነጭ በትር እና የእግር ጉዳተኞች የሚጠቀሙባቸው ክራንቾች ካርጎ እንዲገቡ የሚጠየቅበት ሁኔታ መኖሩ፤ መስማት ለተሳናቸው እና ለዐይነ ስውራን መንገደኞች በአየር መንገዱ ውስጥ ሲስተናገዱም ሆነ በረራ ላይ ሳሉ መረጃ በተገቢው እና በተሟላ መልኩ እንደማይደርስ ኢሰመኮ ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡
በአጠቃላይ ከዓለም አቀፍ በረራዎች አንጻር ሲታይ የሀገር ውስጥ በረራ የአካል ጉዳተኞችን መብቶች በማክበር ረገድ ክፍተት መኖሩ በክትትሉ ከተለዩ አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከሠራዊት አባልነት ኮብልለው የነበሩ ከ1 ሺህ 300 በላይ የፖሊስ አባላትን አፈላልጎ ወደ ሥልጠና ማስገባቱን አስታወቀ፡፡ዩኒቨርሲቲው በተለያየ ምክንያት ከአባልነት...
23/12/2024

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከሠራዊት አባልነት ኮብልለው የነበሩ ከ1 ሺህ 300 በላይ የፖሊስ አባላትን አፈላልጎ ወደ ሥልጠና ማስገባቱን አስታወቀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በተለያየ ምክንያት ከአባልነት ጠፍተው የነበሩ አባላት በወንጀል ድርጊት እንዳይጠለፉ በሚል ሥጋት፣ የተጠረጠሩ የቀድሞው ሠራዊት አባላት፣ በአስቸኳይ ሥልጠና እንዲያገኙ የሚል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ወደ ሥልጠና መግባታቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሸነር መስፈን አበበ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህን ያስታወቁት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲን የ2015 በጀት ዓመት የሒሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ታኅሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ሲገመግም ነው፡፡
ኮሚሽነሩ የፖሊስ አባላት ከተለመደው አገልግሎት ወጣ ያሉና ከአቅም በላይ የሆኑ ሥራዎችን በአገር መከላከያ ሠራዊት በመታገዝ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡
በአገር ደረጃ የሠራዊት እጥረት ስላለ በየዓመቱ ዩኒቨርሲቲው አሥር ሺሕ ሠራዊት እያሠለጠነ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡ በአማራ ክልል የሚገኘው የደብረ ማርቆስ ፖሊስ ማሠልጠኛ በ2015 ዓ.ም በደረሰበት ጥቃትና ወድመት መዘጋቱንና ምንም ዓይነት ሥልጠና እያከናወነ አለመሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
ሰፋ ያለ የኦዲት ክፍተት የተገኘበት ዩኒቨርሲቲው በሰጠው ምላሽ፣ ወቅታዊ ግዳጅን ለመስጠት በሚያስችለው ቁመና ላይ ተገኝቶ ለግዳጅ ዝግጁ ለመሆን በሚሠራበት ወቅት ክፍተት መፈጠሩን አስታውቋል፡፡

በሀገሪቱ የተባባሰው የኑሮ ውድነት ዜጎችን ለምሬት እና የስደት አማራጭን እያጎለበተ መሆኑን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አስታወቁ፡፡ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግ...
20/12/2024

በሀገሪቱ የተባባሰው የኑሮ ውድነት ዜጎችን ለምሬት እና የስደት አማራጭን እያጎለበተ መሆኑን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አስታወቁ፡፡
በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫቸው "የኑሮ ውዶነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫን እያጎላው መጥቷል" ብለዋል፡፡
የጋራ መግለጫውን የሰጡት መድረክ፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ ኅብር ኢትዮጵያ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና ኢሕአፓ ናቸው፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በሚመለከት ለናሁ ቴሌቭዥን በላከው መግለጫው “መንግሥት ጦርነትን እንደ መግዣ ሥልቱ ከመጠቀም ወደ መንግሥታዊ ኃላፊነት በመመለስ፤ አገርና ህዝብን በጋራ ከጥፋት መታደግ ጊዜ የማይሰጠው አገራዊ ጥሪ ነው” ብሏል።
በተጨማሪም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከሱ ገዢውን የብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር በእጅጉ ኮንኗል። የብልፅግና መንግስት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ "የአገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ከዕለት-ወደ ዕለት ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዙ ነው" ብሏል።
ይህም ለሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ እየዳረገን ነው ሲልም ወቅሷል። አክሎም “የኑሮ ውድነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል” ሲልም ገልጿል።
ኮከሱ " ማኅበራዊ ህይወታችን በሥራ አጥነት፣ መፈናቀል፣ የማኅበራዊ ተቋማት መዳከምና የአገልግሎት መቋረጥ ወይም መቀንጨር፣ የሠራተኞች ብሶት መገለጫቸው ከሆነ ውሎ አድሯል" ብሏል።
አገሪቱ ከገባችበትና ካለችበት ፖለቲካዊና ማህበረዊ ምስቅልቅል እንድትወጣ ሃቀኛ፣ ሁሉን-አቀፍ፣ አሳታፊ፣ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ ለማውረድ ተዓማኒ ውይይት እንዲደረግም ጥሪ አቅርቧል።

የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ መልሶ ለማጤን ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።አንድ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣ...
20/12/2024

የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ መልሶ ለማጤን ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።
አንድ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ለአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ “የሶማሊያ መንግሥት ለልዑኩ ኅይል ከሚያዋጡት ሀገራት ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ወታደሮችን አግኝቶ ደልድሏል” ሲሉ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ አንዳቸው የሌላውን ሉዐላዊነት፣ እንዲሁም የግዛት አንድነት እንደሚያከብሩ አንካራ፣ ቱርክ ላይ ባለፈው ሳምንት ስምምነት መፈጸማቸውን ገልጸዋል።
ስምምነቱ በመፈጸሙም ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአዲሱ ልዑክ ውስጥ የመካተታቸውን ጉዳይ "እንደገና እንደምታጤን” ባለስልጣኑ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የፈጸመችውንና የባሕር በርን የተመለከተውን የመግባቢያ ስምምነት የማትሰርዝ ከሆነ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሶማሊያ ስትጠይቅ መቆየቷ ይታወሳል።
ሶማሊያ ይህን ብትልም ኢትዮጵያ ግን በሶማሊያ የሚገኙት ወታደሮቿ አል ሻባብን መዋጋት እንደሚቀጥሉ አስታውቃ ነበር።
የኢትዮጵያ ትኩረት አል ሻባብ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በቅርቡ አስታውቀው ነበር።
በአንካራው ስምምነት ፕሬዜዳንቱ፤ በአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሀገራቸው (ሶማሊያ) ለከፈሉት መስዋዕትነት በይፋ እውቅና ሰጥተዋል።
ሁለቱ ሀገራት በአንካራ ላይ የደረሱትን ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት ልዑክ ውስጥ ሊካተቱ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

በድሬድዋ ከተማ የስማርት ሲቲ እና ስማርት ቪሌጅ ግንባታን ለማከናወን የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡ በዛሬው ዕለት በሮዜታ ኮንስትራክሽንና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር አማካኝት ይፋ የሆኑት ፕሮጀ...
19/12/2024

በድሬድዋ ከተማ የስማርት ሲቲ እና ስማርት ቪሌጅ ግንባታን ለማከናወን የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

በዛሬው ዕለት በሮዜታ ኮንስትራክሽንና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር አማካኝት ይፋ የሆኑት ፕሮጀክቶች ስማርት ሲቲ እና ስማርት ቪሌጅ የተባሉ ሁለት ዋና ዋና ፕሮጄክቶች መሆናቸው ተገልቷል፡፡ የመጀመሪያው የስማርት ቪሌጅ ፕሮጄክት የሮዜታ ጄነራል ትሬድንግ ፒ ኤል ሲ ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው እና የድሬድዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁዋር በጋራ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡ ፕሮጄክቱ በሶስት ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚገነቡ፤ የመገበያያ ማዕከል ህንጻ ያካተተ ከ250 በላይ አፓርታማዎች የሙከራ ግንባታ እንደሚካሄድ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው ለናሁ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው ፕሮጄክት የሶስት ሺ ቤቶች ግንባታ ሲሆን፤ ይህ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በሚያቀርበው ቦታ ላይ ቤቶች ተሰርተው በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡበት ነው ተብሏል፡፡ የቤቶቹ ግንባታ ለየት የሚያደርገው ግንባታው በቴክኖሎጅ የታገዘ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የሚያልቁ መሆናቸው ነው ሲሉ አቶ ቴዎድሮስ ከጣቢያችን ናሁ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ባለአስር ወለል ህንጻዎችን ከሶስት እስከ አራት ወራ ባሉት ጊዚያት ውስጥ በፍጥነትና በጥራት ለማጠናቀቅ ታሳቢ አድርጎ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጄክቱ የድሬደዋ ከተማ የውጭ ኢንቨስትመንት ማዕከል እየሆነች ስትመጣ በአንጻሩ የቤት እጥረት በማጋጠሙ፤ ያን ችግር ለመቅረፍ ያለመ እንደሆነ የሮዜታ ጄነራል ትሬድንግ ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ቴዎድሮስ አስረድተዋል፡፡

በሮዜታ ኮንስትራክሽን አማካኝነት የሚገነቡት ቤቶች በውጭ ስታንዳርድ የሚገነቡ መሆናቸው ወደከተማዋ ለሚመጡት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥሩ አብራርተዋል፡፡

ፕሮጄክቱ ከዳር እንድደርስ አስተዋጽዖ ላደረገው የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እና የከተማዋ ከንቲባ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ቴዎድሮስ፤ ባለ ግዙፍ ታሪኳን ድሬድዋን የተሻለች እና ለኑሮ ተስማሚ እናድርግ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

“ናሁ ቴሌቭዥን አለተዘጋም፤ የሳታላይት ቅያሪ ነው ያደረግነው”  - ስራ አስኪያጁበተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ከአውድ ውጪ የተተረጎሙ መረጃዎች እንደተሰራጩበት ናሁ ቴሌቭዥን አስታወቀ፡፡በ...
18/12/2024

“ናሁ ቴሌቭዥን አለተዘጋም፤ የሳታላይት ቅያሪ ነው ያደረግነው” - ስራ አስኪያጁ
በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ከአውድ ውጪ የተተረጎሙ መረጃዎች እንደተሰራጩበት ናሁ ቴሌቭዥን አስታወቀ፡፡
በማህበራዊ የትስስር ገፆች፤ ናሁ ቴሌቭዥን እንደተዘጋ በማስመሰል የተሰራጨው መረጃ “የተሳሳተ ነው” ያለው ተቋሙ፤ የሳታላይት ቅያሪ ማድረጉን እወቁልኝ ብሏል፡፡
የኢትዮ ሳት ስርጭቱን ማቋረጡን ያስታወቁት የተቋሙ ስራ አስኪያጅ፤ በቀጣይ ስርጭቱን በዲ.ኤስ.ቲቪ እና በተለመዱ የማህበራዊ ትስስር ገፆች አማራጭነት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
ናሁ ቴሌቭዥን ከአስር አመት በላይ የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያ ይዘት ያላቸው ወቅታዊ እና አዳዲስ ሃገራዊ እና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን እንዲሁም የመዝናኛ ፕሮግራሞችን ያላማቋረጥ ወደ ተመልካቾች ሲያደርስ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በእነዚህ ጊዚያትም በሃገሪቷ ጎልተው ከወጡ እና ተቀባይነት እንዲሁም ተወዳጅ መሆን ከቻሉት ጥቂት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ውስጥ አንዱ መሆን ችሏል፡፡
ነገር ግን ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች አማካኝነት "ናሁ ቴሌቭዥን ተዘግቷል" የሚሉ ወሬዎች ሲንሸራሸሩ ሰንብተዋል፡፡
በመሆኑም ናሁ ቴሌቭዥን እንዳልተዘጋ እና በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ከአውድ ውጪ የተተረጎሙ መረጃዎች እንደተሰራጩበት የናሁ ቴሌቭዥን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አስታውቀዋል፡፡
ናሁ ቴሌቭዥን ከዚህ ቀደም በሶስት የሳተላይት አማራጮች ማለትም በኢትዮ ሳት፣ በዲ.ኤስ.ቲቪ እና በካናል ፕላስ ወደ ተመልካቾች ሲደርስ መቆየቱን የናሁ ቴሌቭዥን ስራ አስኪያጅ አቶ ኢዶሳ ቀጀላ ገልፀዋል፡፡
ነገር ግን ናሁ ቴሌቭዥን ለተወሰኑ ጊዚያት ከሶስስቱም የሳተላይት አማራጮች ወርዶ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በዲ.ኤስ.ቲቪ፣ በዩ.ቱ.ዩብ ቻናል እና በተለመዱ የማህበራዊ ትስስር ገፆች አማካኝነት ተደራሽ ሆኖ መቀጠሉን አቶ ኢዶሳ ቀጀላ በሰጡን ማብራሪያ አስታውቀዋል፡፡
"አንድ ተቋም ወይንም የቴሌቭዥን ጣቢያ ተዘጋ የሚባለው ሰራተኛ በትኖ መስሪያ ቤት ዘግቶ ሙሉ በሙሉ ከገበያ ውጭ ሲሆን እና ስራ ሲያቆም ነው" ያሉት አቶ ኢዶሳ፤ ናሁ ቴሌቭዥን ግን አሁንም በሳተላይት እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ወቅታዊ እና አዳዲስ ዜናዎች እና ፕሮግራሞችን ለተመልካቾች እያረሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ናሁ ቴሌቭዥን እንደተዘጋ ተደርጎ እና በሃገሪቱ በሶስት ወራት ውስጥ ተዘግተዋል ከተባሉ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ውስጥ አንዱ ተደርጎ በተለያዩ ማህራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን መረጃ እንደተመለከቱ የገለፁት አቶ ኢዶሳ ቀጀላ መረጃዎቹ ከአውድ ውጭ የተተረጎሙ እና ፍፁም ሃሰተኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ማንኛውም የቴሌቭዥን ጣቢያ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ከሳተላይት ሊወርድ እንደሚችል እና ናሁ ቴሌቭዥንም ከዚህ ቀደም ከሶስት ጊዜ በላይ አጋጥሞት ነበር ነገር ግን ናሁ ቴሌቭዥን አንድም ቀን ተዘግቶ አያውቅም ብለዋል፡፡
በዚህም በችኮላ እና የተጣራ መረጃ ሳይኖራቸው ተቋማችን ሚዛናዊ የሆነ መረጃ ሳይኖራቸው እና ናሁ ቴሌቭዥን እንደተዘጋ አድርገው መረጃውን ያሰራጩ አካላትን እንደ አስፈላጊነቱ ተጠያቂ እንደሚያደርጉ አቶ ኢዶሳ ተናግረዋል፡፡
"ናሁ ቴሌቭዥንም ከሳተላይት የወረደበት ምክንያት ምንድን ነው?" ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄም አሁን ላይ ሃገሪቷ የገጠማት ኢኮኖሚያ ቀውስ ዋነኛ ምክንያት ስለመሆኑ በምላሽሻው ጠቅሰዋል፡፡
ቴሌቭዥን ጣቢያው የግል እና ለትርፍ የተቋቋመ በመሆኑ ቀጥተኛ ገቢው የፋይናንስ ተቋት ቢሆንም አሁን ላይ ባለው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ከዶላር ዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የሳተላይት ክፍያ በእጥፍ መጨመሩም ዋነኛ ምክንያች መሆናቸውን አክለዋል፡፡
ምንም እንኳ ናሁ ቴሌቭዥን የበጀት እጥረት ቢያጋጥሙትም የሰራተኞችን ደሞዝ በአግባቡ ለመክፈል እና ወደፊት ከሰራተኞቹ ጋር ወደፊት ለመቀጠል እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በመሆኑም ባለፉት ጊዚያት ናሁ ቴሌቭዥንን በሳተላይት አማራጮች ያላገኙን ተመልካቾችን ይቅርታ የጠየቁት አቶ ኢዶሳ በአሁኑ ወቅት በዲ.ኤ.ስ ቲቪ ቻናል 481 እና በሁሉም የማህራዊ ሚዲያ አውታሮች እና ቴሌቭዥንን ፕሮግራች ማግኘት እንደሚችሉ እና በቅርቡ በአዲስ አቀራረብ እና ይዘት ወደ እንደሚመለስ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በትግራይ የክልሉ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች የሚሳተፉበት የማዕድን ምዝበራ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ገለፁ። የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ ባ...
17/12/2024

በትግራይ የክልሉ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች የሚሳተፉበት የማዕድን ምዝበራ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ገለፁ።
የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ ባይቶና እና ዓረና በጋራ በሰጡት መግለጫ የህወሓት አመራሮች ማእድናት በመዝረፍ እንዲሁም አዳዲስ ታጣቂዎች በመመልመል እና በማስታጠቅ ላይ ናቸው ብለዋል።
በትግራይ ክልል በተቃዋሚነት ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች መካከል የሆኑት የትግራይ ነፃነት ፖርቲ፣ የታላቅዋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና እና ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ባለፈው ሳምንት በትግራይ አራት ዞኖች በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች ልዑካን በማሰማራት የክልሉ ወቅታዊ ፖለቲካዊ እና አጠቃላይ ሁኔታ መዳሰሳቸውን በመግለፅ ስለግኝታቸው ለመገናኛ ብዙሕን መግለጫ ሰጥተዋል።
ፖርቲዎቹ እንዳስታወቁት፣ በትግራይ በተለይም ሰሜን ምዕራብ እና ማእከላይ ዞኖች ከፍተኛ የወርቅ መአድን ምዝበራ በክልሉ ፖለቲካዊና የሰራዊት አመራሮች እየተፈፀመ ነው ያሉ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ህወሓት አዳዲስ ታጣቂዎች በመመልመል እና ነባር ያላቸው ተዋጊዎች ለጦርነት እንዲዘጋጁ ቅስቀሳ ላይ ነው ሲሉ ከሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ የውጭ ሀገር ዜጎች በቀጥታ የሚሳተፉበት የወርቅ ማዕድን ምዝበራ በስፋት እየቀጠለ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ “ወርቅ የማውጣት ስራው አደገኛ ኬሚካሎች በመጠቀም ጭምር የሚከወን በመሆኑ በተፈጥሮ ሀብት እና ሰው ላይ አደጋ እየፈጠረ ነው” ያሉት ሶስቱ ፓርቲዎች፥ “በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ እየተከወነ ነው” ያሉት የወርቅ ማውጣት ስራ በዘላቂነት ክልሉን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ገልፀውታል።

በአንዳንድ ሚዲያዎች የገቢዎች ቢሮ ዝቅተኛ የደመወዝ ጣርያ ማስቀመጡን በሚመለከት የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ቢሮው አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ፣ ሰሞኑን ባን...
17/12/2024

በአንዳንድ ሚዲያዎች የገቢዎች ቢሮ ዝቅተኛ የደመወዝ ጣርያ ማስቀመጡን በሚመለከት የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ቢሮው አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ፣ ሰሞኑን ባንዳንድ የግል ተቋማት የደመወዝ ግብርን ለማስተካከል የወሰነው ውሳኔ በሆቴሎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች የሚሠሩ ሠራተኞችን ዝቅተኛ ደሞዝ ከመወሰን ጋር ግንኙነት የለውም በማለት ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል።
ውሳኔው፣ የታክስ ስወራን ለመከላከል በጥናት ከተለዩ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ የደሞዝ ክፍያዎች መካከል ዝቅተኛውን በመውሰድ የደሞዝ ግብር በወጥነት እንዲሰበሰብ ለማድረግ ያለመ መኾኑን ቢሮው አስታውቋል።
64 በመቶዎቹ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች “ምንም ዓይነት የደሞዝ ግብር እንደማይከፍሉ ወይም ከገበያ ዋጋው በመቀነስ እንደሚከፍሉ በጥናት ለይቻለኹ” ያለው ቢሮው፤ 44 ከመቶ ኃ/የተ/ግ/ድርጅቶች ደሞ አንድም ሠራተኛ የለንም በማለት የደመወዝ ግብር እንደማይከፍሉ አረጋግጫለኹ ብሏል።
ስለሆነም ባካሄደው የገበያ ዋጋ ጥናት መነሻነት ምንም የማይከፍሉትን እንዲከፍሉ የማድረግ፣ ዝቅተኛ የደሞዝ ግብር ያሳወቁ ደግሞ እንዲያሻሽሉ መደረጉን አስረድቷል።
በመሆኑም ቢሮው የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ ታክስ የመሰወር ድርጊት የፈፀሙ ግብር ከፋዮችን በመለየት በዘላቂነት ለመቅረፍ በጥናቱ ከለያቸው ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ የደሞዝ ክፍያዎች ዝቅተኛውን በመውሰድ የደሞዝ ግብር ወጥነት ባለው መልኩ እንዲሰበሰብ ወስኗል ብሏል።
ቢሮው፣ የተወሰኑ የግል ድርጅቶች የሚከፍሉትን የደመወዝ ግብር ለመወሰን ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሏቸውን የደመወዝ ተመንና ሊኖራቸው የሚገባውን አማካይ የሠራተኛ ብዛት መወሰኑ ይታወሳል።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የህግ ታራመዎችን ለሚቀጥሉት 5 ቀናት መጎብኘት እንደማይቻል ተገለፀ፡፡ይህም የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እሥረኞች ከዛሬ ታህሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ...
17/12/2024

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የህግ ታራመዎችን ለሚቀጥሉት 5 ቀናት መጎብኘት እንደማይቻል ተገለፀ፡፡
ይህም የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እሥረኞች ከዛሬ ታህሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሌላ እሥር ቤት ስለሚዘዋወሩ መሆኑን የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
እስረኞቹን ገላን አካባቢ ወደ ተሰራው ማረሚያ ቤት የማዛወሩ ሥራ እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም እስኪጠናቀቅ ድረስ ቤተሰብ እስረኞቹን መጠየቅ እንደማይችልም አስታውቋል።
በመሆኑም በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደ ተገነባው ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የማዘዋወር ስራ ይሰራል፡፡
የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እስረኞቹ የሚዛወሩበትን ምክንያት እና የቤተብ ጥየቃ የሚመለስበትንም ቀን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ከመጪው ሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛው አገልግሎት እንደሚቀጥል እና ቤተሰብ እስረኞቹን መጠየቅ እንደሚችልም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እገዳ ተጣለበት፡፡ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሜ እገዳ እንደተጣለባቸው ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ፡፡ከታህ...
13/12/2024

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እገዳ ተጣለበት፡፡

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሜ እገዳ እንደተጣለባቸው ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ፡፡
ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤው አሳውቋል፡፡
ከጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውንና በትግበራ ወቅት ክፍተት የታየበት “የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ” በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡
በዚህም ማሻሻያው ተጠናቆ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከሚላክ ድረስ በሁሉም ተቋማት የፕሮፌሰርነት ዕድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን ሚኒስቴሩ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለተቋማቱ በጻፈው ደብዳቤ ገልጾ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ “አንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክልከላውን በመጣስ፣ መመሪያውን ባልተከተለ፣ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ሪፎርሞች ጋር በሚጣረስ መልኩ የፕሮፌሰርነት ዕድገት መስጠት መቀጠላቸውን ለመረዳት ችለናል” ሲል በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለተቋማቱ የተላከ ደብዳቤ ላይ ተገልጧል።
ከታህሳስ 1 ቀን ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው የገለፀው ትምህርት ሚኒስቴር፤ የተቋማቱ ከፍተኛ አመራር አካላት እና የሥራ አመራር ቦርድ የተሻሻለው መመሪያ ተጠናቅቆ እስኪደርሳችሁ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡
Via wazema radio

በአከባቢው በተደጋጋሚ የሚካሄዱ ውጊያዎች ያማረሯቸው የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች በአከባው ሰላም እንዲሰፍን ጠየቁ፡፡የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መልእክት በአከ...
13/12/2024

በአከባቢው በተደጋጋሚ የሚካሄዱ ውጊያዎች ያማረሯቸው የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች በአከባው ሰላም እንዲሰፍን ጠየቁ፡፡
የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መልእክት በአከባቢው የቀጠለው ግጭት እልባት እንዲሰጠው በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።
የዓለም ቅርስ የሆነው የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መገኛ የሆነችው የላሊበላ ከተማ ሕዝብ የካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ዋንኛ ዓላማው ሰላምን ማስፈን ስለመሆኑም ተመላክቷል።
የኑሮ መሠረቱ እና ኅልውናው በቅርሱ ላይ የተመሠረተው የላሊበላ ሕዝብ “ቀደም ሲል በሰሜኑ ጦርነት አሁን ደግሞ ባለው ሰላም ማጣት ለረሃብ እና ለችግር እየተዳረግን ነው” በሚል “ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም እንፈልጋለን፣ ማንም ማንንም አይግደል መገዳደል ይቁም” ሲል በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል።
መጪውን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እና የቅዱስ ላሊበላን ልደት በአንድ ጊዜ የምታከብረው ላሊበላ ይህ ወቅት በሀገር ውስጥና በውጭ ቱሪስቶች የምትጎበኝበት ነዋሪውም የዕለት ጉርሱን የዓመት ልብሱን የሚሸምትበት ገቢ የሚያገኝበት መሆኑ ይታወቃል።
ነገር ግን በክልሉ ባለው ግጭት ምክንያት ችግር ላይ በመውደቁና ተስፋው የሆነውን ይህንን በዓል ለማክበር ወጥቶ ሠርቶ ለመግባት ሰላም እንዲረጋገጥለት እንደሚፈልግ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቋል።
ሰልፈኞቹ ግጭቶችና አለመግባባቶች በጦርነት ሳይኾን በውይይትና በንግግር እንዲፈቱ መጠየቃቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ላሊበላ ከተማ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ተደጋጋሚ ግጭቶች የተካሄዱባት አከባቢ ናት።
በተለይ በአከበቢው በተደጋጋሚ በተካሄዱ ጦርነቶች፤ ተፋላሚዎች በሚተኩሷቸው ከባድ መሳሪያዎች ሳቢያ፣ በጥንታዊዎቹ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከባድ ስጋት እንደተደቀነ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲገልጹ መቆየታቸው አይዘነጋም።

Address

Rosetta Bldg. 2nd Floor # 14/2010
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nahoo Television posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share