Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ ሀገራዊ፣ አካባቢያዊ እና የጉራጌን ህዝብ ባህል ቋንቋ ኢኮኖሚ ፣ ፖለቲካ ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ሁለንተናዊ ጉዳዮች የምንጦምርበት ገጽ ነው።
(1)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻዉ ጣሰው፣ ከስልጤ ብሔረሰብ የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮች ጋር ተወያዩበዉይይት መድረኩ ቀደም ሲል በስልጤ ዞን አሊቾ ዉሪሮ ወ...
21/01/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻዉ ጣሰው፣ ከስልጤ ብሔረሰብ የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮች ጋር ተወያዩ

በዉይይት መድረኩ ቀደም ሲል በስልጤ ዞን አሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ዉስጥ ተከስቶ የነበረዉን አለመግባባት በብሔረሰቡ ባህላዊ እሴትና የእርቅ ስርዓት መሠረት በባህል ሽማግሌዎች አማከይነት እርቅ በመፈጸም እልባት ማግኘቱ ተገልጿል ።

በአካባቢዉ ተፈጥሮ የነበረዉን ጊዜያዊ አለመግባባት በመፍታት የአብሮነት መንፈሱ ወደቀድሞዉ መልካም ሁኔታ እንዲሸጋገር የባህል ሽማግሌዎቹ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻዉ ጣሰዉ ምስጋና አቅርበዋል ።

የየአካባቢዉ የባህል ሽማግሌዎች የየአካባቢዉን ባህላዊ እሴቶችና የግጭት መፍቻ ሥርዓቶችን መሠረት አድርገዉ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችንና አለመግባባቶችን መፍታት እንደሚጠበቅባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንደ ዘገበው::

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

 ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ወንድማችን ሙሰማ ዘይኑ ረዲ ይባላል.. የትውልድ ስፍራው   ሲሆን.. ይኖርበት ከነበረው ከዚሁ ቀበሌ 2012 ዓ.ም መባቻ አካባቢ ድንገት ከቤት እንደወጣ አልተመለ...
20/01/2025



ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ወንድማችን ሙሰማ ዘይኑ ረዲ ይባላል.. የትውልድ ስፍራው ሲሆን.. ይኖርበት ከነበረው ከዚሁ ቀበሌ 2012 ዓ.ም መባቻ አካባቢ ድንገት ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም.. ቤተሰቦቹ ይህንን ወጣት ልጃቸውን ለማግኘት ከጠፋበት ወቅት ጀምሮ ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ሊያገኙት አልተቻለም.. ወንድማችን የአዕምሮ ህመም ታማሚ ሲሆን ያለበትን አድራሻ የሚያውቅ ከታች በተጠቀሱት የስልክ ቁጥሮች በመደወል እንዲያሳውቀን እና የአፋልጉን መረጃውን በሚዲያ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትብብር ያድርግልን ሲሉ ቤተሰቦቹ ይማፀናሉ‼

ስልክ
0932302936
0973547746
0937610801

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከከምባታ ዞን ከተዉጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በዞኑ ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ውይይት አካሂደዋል፡፡የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል...
17/01/2025

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር ) ከከምባታ ዞን ከተዉጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በዞኑ ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻዉ ጣሰዉ ከከምባታ ዞን ከተዉጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በዞኑ ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ በዛሬዉ ዕለት በጽህፈት ቤታቸው ዉይይት አካሂደዋል።

በውይይት መድረኩ የሀገር ሽማግሌዎቹ የአካባቢዉን ልማትና መልካም አስተዳደር ከመንግሥት ጎን በመሆን ለማጠናከር ያላቸዉን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

መድረኩ ልማትንና መልካም አስተዳደርን በሕዝብ ጠንካራ ተሳትፎ እዉን ለማድረግ ለተጀመረዉ እንቅስቃሴ አጋዥና ስኬታማ መሆኑ ተጠቁሟል።

ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ!

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ምርጫ ቦርድ የተሻሻለው የምርጫ ረቂቅ ህግ አዳዲስ ድንጋጌዎችን አካቷልየኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሻሻለው የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ረቂቅ ህግ አዘጋጅቷል። አዲሱ ረቂቅ ም...
17/01/2025

ምርጫ ቦርድ የተሻሻለው የምርጫ ረቂቅ ህግ አዳዲስ ድንጋጌዎችን አካቷል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሻሻለው የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ረቂቅ ህግ አዘጋጅቷል። አዲሱ ረቂቅ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ህግን የሚጥስ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት እንደ ጥሰቱ ክብደት እስከ አምስት አመት ድረስ ህጋዊ መብቱን ከመሻሩ በፊት ከስራ ማገድ እንዳለበት የሚያስገድድ ድንጋጌ አስቀምጧል።

የተሻሻለው ረቂቅ ህግ ከታገዱ በ30 ቀናት ውስጥ ለፌዴራል ፍርድ ቤት ይግባኝ የማለት መብት ይሰጣል - ይህ አሁን ባለው ህግ ውስጥ ያልተካተተ ድንጋጌ። በተጨማሪም ረቂቅ ሕጉ በምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን በሚመርጡበት ጊዜ 20% የጾታ ኮታ እንዲያሟሉ ይጠይቃል።

Via EL

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ባለፈው ቅርብ ጊዜእንኳንስ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ክልል ካልሆንክ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ሳይቀር በኮታ ነው የምትከፋፈለው ብለን ነበር። ለማስረጃነት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተወሰደውን ከስር...
15/01/2025

ባለፈው ቅርብ ጊዜ

እንኳንስ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ክልል ካልሆንክ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ሳይቀር በኮታ ነው የምትከፋፈለው ብለን ነበር።

ለማስረጃነት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተወሰደውን ከስር ያለው ምስል ይመልከቱ። "ብለን ነበር!" ብለን ግን አንሰላችም፤ በየጊዜው በሚፈጠሩ ቁምነገሮች ሙግታችንን በማስረጃ አስደግፈን እናቀርባለን።

"ክልል ዘመን አመጣሽ ፋሽን ነው" ያለው ማን ነበር?። የማክሰሚያ ፕሮጀክቱ ያለ ጥርጥር phaseout ያደርጋል።

የታሪክ ሽምያ እና ቅሚያ እያደረገ ባለ ማህበረሰብ መካከል እየኖሩ ሀገራዊ ድርሻን በመጠየቅ ጊዜያዊና ቋሚ ጥቅሞችን ከማስከበር ለአፍታም መዘናጋት አያስፈልግም።

#ኬር #ወገሬት

Via አብዱረዛቅ ነስሩ

በመጨረሻም....አንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አህመድ "እንዴት ይረሳል እንደ ዘበትያደረግነው ሁሉ በልጅነት "በተሰኘው ተወዳጅ ዜማ መድረኩን ተሰናበተ። አድናቂዎቹ ሁሉ አይናቸው እንባ እንዳቀረረ ...
12/01/2025

በመጨረሻም....

አንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አህመድ
"እንዴት ይረሳል እንደ ዘበት
ያደረግነው ሁሉ በልጅነት "በተሰኘው ተወዳጅ ዜማ መድረኩን ተሰናበተ።

አድናቂዎቹ ሁሉ አይናቸው እንባ እንዳቀረረ አብረውት በማዜም ተሰናብተውታል፣
እውነትም እንዴት ይረሳል እንደዘበት?

የፕሮግራሙ አዘጋጆች ጆርካ ኤቨንትና ዳኒዴቪስ ከመድረክ ውበቱ ጀምሮ እስከ መስተንግዶ ድረስ የተዋጣ ዝግጅት አሳይተዋል።

ለዚያውም ይህንን የመሰለ ልዩ ፕሮግራም ስፖንሰር በማድረግ ራሱን ከዚህ ታሪካዊ ክስተት ጋር ለማስተሳሰር የከጀለ ድርጅት በሌለበት ሁኔታ። (ከሳምንት በፊት በተካሄደው የቲክ ቶክ አዋርድ ላይ ብዙ ስፖንሰሮች እንደነበሩ ልብ ይሏል )

የመድረኩ አጋፋሪ ነፃነት ወርቅነህ እንደ ቤተሰብ ጨዋታው ጥያቄ የመጠየቅ ልማዱ ቢጎትተውም ጥሩ አስተናብሯል።

በኮንሰርቱ ፖስተር ላይ አንድም ሴት ድምጻዊት ያለመኖርን የተመልካች ጥያቄ የተረዱት የፕሮግራሙ አዘጋጆች አንዲት ወጣት ድምፃዊን የማህሙድ ዘፈንን እንድትጫወት አድርገዋል፣ ግን እንስት ድምጻውያኖቻችን ለምን ከዚህ መድረክ ጠፉ?
በኮንሰርቱ ላይ ስማቸውና ምስላቸው ከተገለፁት አርቲስቶች ሌላ ለማሕሙድ ክብር ሲሉ በአዳራሹ የተገኙት አርቲስቶች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። (ሀይልዬ ታደሰ፣ታደለ ሮባና ታደለ ገመቹ፣ ልጅ ሚካኤል፣ሄኖክ አበበ፣ለምለም ሀይለሚካኤል፣እሱባለው ይታየው፣ማሚላ ሉቃስ፣ናቲ ማን፣ጆሲ፣ካሙዙ፣)በቃ?

ከ60 ዓመት በላይ ላዜመ አንጋፋ አርቲስት የመድረክ ስንብት ላይ አብረውት ባያንጎራጉሩ ለክብሩ ሲሉ በስፍራው መገኘት የነበረባቸው የሙያ አጋሮቹ እነዚህ ብቻ መሆን ነበረባቸው? በእርግጠኝነት ግን አንድ ነገር መናገር ይቻላል።

አያድርገውና ማሕመድ ነገ ቀኑ ደርሶ ከዚህ ዓለም ሲለይ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ አርቲስቶች ሙሉ ጥቁር ልብስና ጥቁር መነፅር ( ፋሽኑ ያላለፈበት) አድርገው በቲቪ ካሜራ እይታ ውስጥ ለመግባት ሲጋፉ ይታያሉ።

ዛሬ ማሕሙድን በክብር ለመሸኘት ያልተገኘ አርቲስት ነገ ማህሙድ እድሜ ላይ ሲደርስ አንጋፋ ብሎ በክብር የሚሸኘው ተተኪ ያገኝ ይሆን?
አበው ሲተርቱ " ከትንሽ ወይም ከትልቅ መወለድ ሙያ አይደለም፣ራስን ለታላቅ ክብር ማብቃት እንጂ"ይላሉ።
ለማንኛውም ማሕሙድ የጎደለበት ነገር የለም።

ሆኖም " እንዴት ይረሳል እንደ ዘበት" በሚለው ተወዳጅ ዜማው መድረኩን ተሰናብቷል።
አንዳንድ ጊዜ ግን የአርቱ ዓለም ሰዎች አስመሳይነትና ቡድንተኝነት ያቅለሸልሻል።

Hailu

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ጥር 4 በአዲስ አበባ ከተማ!ለሐዋሪያት ሆስፒታል!ዕሁድ ጥር 04/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ብሔራዊ ቲያትር አጠገብ በሚገኘው ራስ ሆቴል አዳራሽ  ለሐዋሪያት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክ...
09/01/2025

ጥር 4 በአዲስ አበባ ከተማ!
ለሐዋሪያት ሆስፒታል!

ዕሁድ ጥር 04/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ብሔራዊ ቲያትር አጠገብ በሚገኘው ራስ ሆቴል አዳራሽ ለሐዋሪያት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና መሳሪያዎች ለማሟላት ተወላጆችና ወዳጆችን ያሳተፈ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይደረጋል። ፕሮግራሙ በወረዳው አስተዳደር የሚመራ ሲሆን ከጠዋቱ 3:30 የሚጀምር ይሆናል።

በቦታው በመገኘት ድጋፋችንን እናሳይ! በአካል መገኘት የማንችል ደግሞ የወረዳው አስተዳደር በሚያስተዳድራቸው የሂሳብ ቁጥሮች የአቅማችንን ድጋፍ እናድርግ!

СВЕ:- 1000650277523
NIB:- 7000054845068

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

Ethiopis TV program/ኢትዮጲስ የገና በዓል ከአላዛር ጋር/የልጆች መማሪያ አፕልኬሽን ሰርቷል። ...https://youtube.com/watch?v=7fz9noAoAvs&feature=sha...
09/01/2025

Ethiopis TV program/ኢትዮጲስ የገና በዓል ከአላዛር ጋር/የልጆች መማሪያ አፕልኬሽን ሰርቷል። ...
https://youtube.com/watch?v=7fz9noAoAvs&feature=shared

ኢትዮጲስ የህጻናት ፕሮግራም ዘወትር እሮብ እና ቅዳሜ በኢ.ቢ.ኤስ ቲቪ፡፡👇 ለአዳዲስ እና ተጨማሪ ቪዲዮች እና ፕሮግራሞችን ለማግኘት*SUBSCRIBE US ON YOUTUBE -https://www.youtube.com/ethiopistvprogram*LIKE ...

ቤንዚን በሊትር ከ 100 ብር በላይ እንዲሸጥ ተወሰነከዛሬ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን  የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ ተደረገየሚኒስትሮች ም/ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም...
07/01/2025

ቤንዚን በሊትር ከ 100 ብር በላይ እንዲሸጥ ተወሰነ

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ

የሚኒስትሮች ም/ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ የአፈጻጸም ውሳኔ መሠረት፤ ከዛሬ ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለዉ እንዲሸጥ በመንግስት መወሰኑ አሳዉቋል።
በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ የችርቻሮ የመሽጫ ዋጋ

ቤንዚን በ101.47 ብር/ሊትር

ናፍጣ በ98.98 ብር/ሊትር

ኬሮሲን በ98.98 ብር/ሊትር

የአውሮፕላን ነዳጅ በ109.56 ብር/ሊትር

የከባድ ጥቁር ናፍጣ በ105.97 ብር/ሊትር

የቀላል ጥቁር ናፍጣ በ108.30 ብር/ሊትር በመሆን ከዛሬ ታህሳስ 29/2017 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እንዲሸጥ ተወስኗል።

በአዲስአበባ በተለይም ከሰሞኑ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ሲስተዋሉ ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። አንዳንድ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችም ተደበቁ የሚሉ ዜናዎች ሲሰራጩ ነበር።

ምንጭ ዳጉ_ጆርናል

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ለመላው የዘቢዳር ሚዲያ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2017 የገና በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
06/01/2025

ለመላው የዘቢዳር ሚዲያ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2017 የገና በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ፖለቲከኛ፣ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ እና የአዋሽ ባንክ የቦርድ አመራር የነበሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ ቡልቻ በ1997 በተደረገው ምርጫ  ተወዳድረው የፓርላማ አ...
06/01/2025

ፖለቲከኛ፣ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ እና የአዋሽ ባንክ የቦርድ አመራር የነበሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ቡልቻ በ1997 በተደረገው ምርጫ ተወዳድረው የፓርላማ አባል በነበሩበት ፓርላማ አቋማቸውን የሚያንፀባርቁ ሃሳቦችን በማንሳት ሲሞግቱ እናውቃቸዋለን።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ የወዳጅና ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ትመኛለች!

በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 8 የመሬት የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር ክልል አዋሽ ሸለቆ ተመዘገበ  ታህሳስ 26/2017 ፡-ከሌሊቱ 9 ሰዓት ከ 52 ላይ በሬክተር ስኬል እስካሁን ከታዩት ከፍተኛ የ...
04/01/2025

በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 8 የመሬት የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር ክልል አዋሽ ሸለቆ ተመዘገበ

ታህሳስ 26/2017 ፡-ከሌሊቱ 9 ሰዓት ከ 52 ላይ በሬክተር ስኬል እስካሁን ከታዩት ከፍተኛ የተባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር ክልል አዋሽ ሸለቆ ከአቦምሳ በ34 ማይል ርቀት ላይ ተመዝግቧል።

በሬክተር ስኬል እስካሁን ከታዩት ከፍተኛ የተባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር ክልል አዋሽ ሸለቆ 5 ነጥብ 8 የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ታኅሳስ 25 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ከ52 ላይ በተንቀሳቃሽ ሥልክ መተግበሪያዎች ባገኘነው መረጃ መሰረት አብዛኛውን ጊዜ ከባለሙያዎች የሚገኘው መረጃ መተግበሪያዎቹ ከሚሰጡት ከፍ ይላል።

ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎችም ከሌሎች ጊዚያት በተለየ ሁኔታ ተሰምቷል።

ዘገባው የጋዜታ + ነው

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

እንደ ፊውዳልም እንደ ባሪያ አሳዳሪም የሚያደርገው የግብር ስርኣታችን=========================ተከታዩን ጽሑፍ በውስጥ መስመር ያደረሱን የገፃችን ተከታይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ...
03/01/2025

እንደ ፊውዳልም እንደ ባሪያ አሳዳሪም የሚያደርገው የግብር ስርኣታችን
=========================

ተከታዩን ጽሑፍ በውስጥ መስመር ያደረሱን የገፃችን ተከታይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ሙሉቀን ደምሴ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ናቸው። እርሶም ጽሁፉን በትዕግስት ያንብቡና ሃሳብ አስተያየትዎን ያካፍሉ። መልካም ንባብ!!

የባሪያ አሳዳሪ ስርአት (slavery system) በጉልበት ግንኙነት (labor relations) ላይ የተመሰረተ ማህበረሰባዊ ግንኙነትን ፈጠረ። ጌታው በባሪያው ጉልበት፣ ምርትና ህይወት ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረው በማድረግ ጥቂቶች በብዙሃን ጫንቃ ላይ እንዲመቻቹ አደረገ። ባሪያው ለጌታው እንደ ሸቀጥ የሚታይ የማምረቻ መሳሪያ ሆነ። ሲያሻው እያሳረሰው፣ ሲያሻው እያሳጨደው፣ ሲያሻው እያስፈለጠው፣ ጉልበቱ ሲደክም አለያም ጥሩ ገንዘብ ያወጣል ባለው ሰአት እንደ ሸቀጥ ገበያ አውጥቶ ሲሸጠወ ኖረ።

የፊውዳል ስርአት በመሬት ባለቤትነትና አጠቃቀም ላይ የተመሰረተ የባላባትና ጪሰኛ ግንኙነት (feudalism)ን ፈጠረ። ገበሬው ገባር የሚባል ስም ተሰጥቶት መሳሪያ አንግቶ ለመጣ መልከኛ ሁሉ ሲገብር ሲሰፍር ኖረ። የውግያና ጦርነቱ ሁሉ ዓላማ ብዙ ጪሰኛን በተፅዕኖ ስር ማድረግ ነበር። ጪሰኛው ለባላባቱ ሸቀጥና የሸቀጡ ምንጭ ነበር።

በባሪያ አሳዳሪ ዘመን የባሪያ ፍንገላ (ጉልበቱን መጠቀም እና እንደ ሸቀጥ መሸጥን ይጨምራል) በፊውዳል ስርአት ዘመን ደግሞ ጭሰኛ ማስገበር የጉልበትና የሀገብት ምንጭ ሆኑ። እንግዲህ ባሪያ በጉልበቱ፣ ጭሰኛም በምርቱ ግብር እንዲከፍል ይገደድ ነበር። ባሪያ አሳዳሪውም ሆነ ፊውዳሉ ይህን የሚያደርጉት ያው "ለሀገር ጥቅም፣ ሀገር ለመገንባት፣ ሀገርን ከጥቃት ለመከላከል፣… ወዘተ" ለሚባሉ የተለመዱ መንግስታዊ ምክንያቶች ነበር። ሁለቱም እራሳቸውን የቻሉ ስርዓቶች እንደመሆናቸው ስርዓቱ ፋይናንስ የሚደረግበት አሰራር ዘረጉ። አስገባሪውና ገባሪው መካከል የነበረው ግንኙነት በመብትና በጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ከላይ ወደ ታች የሚወርድ ነበር። የላይኛው መጫን የታችኛው መሸከም፣ የላይኛው መደንገግ የታችኛው መገዛት፣ የላይኛው ማስከፈል የታችኛው መክፈል፣ የላይኛው ማዘዝ የታችኛው መታዘዝ የስርዓቶቹ አይነተኛ መገለጫ ነበር።

ይህንን ጉዳይ ያነሳሁት መንግስት በግብር ስም በህዝቡ ላይ እየጣለው ያለው ተደራራቢ ና ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ጉዳይ ላይ አንድአንድ ነገር ለማንሳት ነው። በነገራችን ላይ በሀገራችን ግብር ከነ ስሙ ከገባር ስርአት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። የዘመናዊት ኢትዮጵያ የግብር ስርዓት አስተዳደርም የዚያ ቅሪት የተጣባው ይመስላል። ዘመናትና መንግስታት በሐገራችን ቢፈራረቁም የአስገባሪ‐ገባሪ ግንኙነት በጉልሁ የተቀየረ አይመስለኝም። መንግስት ባሪያ አሳዳሪ/ባላባት ህዝቡም ባሪያ/ጪሰኛ የመሰለ ግንኙነት እስከ አሁን እንደቀጠለ ነው። መሬት የተባለ ሁሉ የመንግስት ነው። የ1967 አዋጅ ገበሬውን ከተበታተነ በዝባዥ ባላባት ጭሰኝነት አወጣው ቢባልም የተደራጀ መንግስት ጭሰኛ አድርጎት አለፈ። Land to the tiller የተባለበት ትግል መሬትን የመንግስት፣ ህዝቡንም የአንድ አምባገነን መንግስት ጭሰኛ አድርጎት አረፈው።

ከሰሞኑ በጉራጌ ዞን አካባቢ የሚገኙ አርሶአደሮች ከፍተኛ የመሬት መጠቀሚያ ግምት ተጥሎባቸው በከፍተኛ ቅሬታ ውስጥ ገብተዋል። በአመት መቶና ሁለት መቶ ብር ሲከፍሉ የነበሩ አርሶ አደሮች (አብዛኛዎቹ እንኳን ሊገብሩ ከመንግስት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው ) ዘንድሮ በሺዎች እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል። አርሶአደሩ በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርጓል። ደግሞ አስተያየት እና አቤቱታ የሌለው ጭነት ነው። በርካቶችም የተጠየቁትን ግብር እራሳቸው መክፈል ስላልቻሉ ከተማ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን መጠየቅ ጀምረዋል። ተበድሮና ለምኖ ግብር መክፈል በእውነቱ በፊውዳል ዘመን ቢሆን እንጂ የሚታሰብ አይመስልም!

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየቱን ያጋራኝ አንድ ወዳጄ "ቤተሰቦቼ ደውለው ከፍተኛ ግብር ጣሉብን፣ ክፈልልን ሲሉኝ ግብር ካፈራችሁት ምርት ላይ የሚከፈል ነው እንጂ ከሌላ ሰው ኪስ የሚከፈል አይደለም። ካለ ንብረት ላይ ሽጣችሁ ክፈሉ፣ ካቅማችሁ በላይ ከሆነ በዛ ብላችሁ ተከራከሩ፣ አልቀንስም ካሉ እና እናንተም መክፈል ካልቻላችሁ ራሳቸው የፈለጉትን ይውሰዱ አልኳቸው።" ሲል ሁኔታውን ገልፆታል።

የግብር ጭነቱ ያላጎበጠው ግብር ከፋይ ያለ አይመስልም። ከምንም በላይ ደግሞ ግብር ከፋዩን እንደ ጭሰኛና ባሪያ የሚመለከት የግብር አስተዳደር ስርአት ነው ያለው። ሲቪል ሰርቫንቱ በመደበኛነት ከሚቆረጥበት ግብር በተጨማሪ ለተለያዩ ጊዜያዊ መዋጮዎች ያለ ፈቃዱ ከደሞዙ ይቀነስበታል። አባል ላለሆነበት ብልፅግና ፓርቲ ሳይቀር ያለ ፈቃዱ ይቆረጥበታል።

ነጋዴውን ከመነሻው እንደ ሌባ የሚያይ ስርአት ነው ያለው። የገቢዎችና ነጋዴው ግንኙነት የሌባና ፖሊስ አይነት ነው። የነጋዴው ሰነድ የሚመረመረው እንደ ወንጀለኛ ዶሴ ነው። አጭበርባሪዎች አሉ ቢባል እንኳን እንዴት ሁሉንም እንደ ሌባ ማየት ይቻላል? ገቢ ልትገብር ሄደህ 3 እና 4 ቀናት መሰለፍ!

አንዳንድ ቦታ ላይ መንግስት ለነጋዴው የግብር እቅድ ያወጣለታል። ሰሞኑ አንድ አስመጪ የሆነ ወዳጄ ከፍተኛ ቀረጥ ተጠይቆ አቤቱታ ለማቅረብ ወደሚመለከተው የጉምሩክ ቅርንጨፍ ኃላፊ ጋር ይገባል። ኃላፊውም ቅሬታውን ካደመጠ በኋላ ጣቱን ግድግዳ ላይ የተለጠፈውን የቅርንጨፍ ፅ/ቤቱ አመታዊ የገቢ እቅድ ላይ እያመላከተው "ካንተም ሆነ ከሌሎች በዚህ መጠን ካልተሰበሰበ እቅዳችንን ማሳካት አንችልም። ይህንን እቅድ ማሳካት ደግሞ ግዴታችን ነው" ብሎ እንደመለሰው አጫወተኝ።

የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ልክ እንደ ድሮ ጦር አበጋዞች ሆነዋል። ጠዋት አንዱ አስገብሮህ ሲወጣ ሌላው ከሰአት ይመጣል። አስገባሪው ብዙ ነው። መሬት አስተዳደር፣ ጉምሩክ፣ ገቢዎች፣ ባንክ፣ መብራት ኃይል፣ ውሃ ልማት፣ ቀበሌ፣ ኮሚቴ፣…። ከሰሞኑ በአንዱ ጓደኛዬ የደረሰው ለዚህ ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል። ከቀጠና የመጣን ነን ያሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሰዎች መጥተው እቃ የገዛህበት ደረሰኝ፣ የቆረጥከው ደረሰኝ፣… በብዙ ጥያቄዎች አዋክበውት ተመለሱ። እነሱ ሲወጡ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ጥያቄ ይዘው የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች መጡ። ቀጥሎ ደግሞ ፖሊሶች መጋዘን ውስጥ መሳሪያ አለ የሚል ጥቆማ ደርሶን ነው ብለው መጡ። ፖሊሶች መሳሪያ ሲያጡ ንግድና ኢንዱስትሪ እና ገቢዎች የጠየቋቸውን ጥያቄዎች ጠየቁ። ይሄ የናንተ ስራ አይደለም ቢላቸው ምን እንደሚከተለው ያውቃል። ሁሉንም እንደ ጠባያቸውና እንደ ፍላጎታቸው አስተናግዶ መለሰ። በአንድ ቀን ሶስት ባላባቶች ማስተናገድ ቀላል አይደለን። ባላባት ቤትህ ከገባ መቼስ በባዶ እጅ አትመልሰውም። ሰውዬው ይነግድ ወይስ ጌቶቹን ያስተናግድ!

በአንዳንድ አካባቢዎች ጠዋት ለመንግስት ግብር ከፍለህ ከሰአት አንዱ ሽፍታ መጥቶ ከብትህን ይነዳል፣ ከፈለገ እራስህን አግቶ ያለህን አጥቦ ይቀበልሃል። ለመንግስት የከፈልከው ግብር ለህይወትህና ንብረትህ ዋስትና ማረጋገጥ አይችልም። ለብዙ ጦር አበጋዞች ትከፍላለህ። በነገራችን ላይ በጥንት ኢትዮጵያ ታሪክ ጠዋት ለአንዱ የጦር አበጋዝ የገበረ ገበሬ ከሰአት ለሌላው የጦር አበጋዝ የገበረበት አጋጣሚ እንዳለ ማንበቤ ትዝ ይለኛል።

በፐብሊክ ፋይናንስ ዘርፍ ግብር የሚጣልበትና የሚተዳደርበት የራሱ አላማዎችና መሰረቶች አሉት። ከነዚህ አንዱ Simplicity የሚሉት ነው። የግብር ስርአቱ የከፋዩና ተገዢነትና የግብር ሰብሳቢው አፈፃፀም በቀላሉ የሚያስተናግድና ከውስብስብነትና ተደራራቢነት የፀዳ እንዲሁም ተገማች መሆን አለበት። የግብር መጠን በእርግጠኝነት የሚታወቅበት አሰራር መኖር አለበት። ይህ ማለት አንድ አስመጪ ከውጭ እቃ ከመጫኑ በፊት ለመንግስት ምን ያህል እንደሚከፍል በእርግጠኝነት ማወቅ አለበት ማለት ነው። ወይም አንድ ነጋዴ አመታዊ ግብሩን ከራሱ የሂሳብ መዝገብ ተነስቶ ለእርግጠኝነት በቀረበ ሁኔታ ማወቅ አለበት ማለት ነው። ግብር በየትኛውም የስራ መስክ እን cost የሚታይ በመሆኑ እንደ ማናቸውም ወጪዎች ለእርግጠኝነት በቀረበ ደረጃ ተገማች መሆን አለበት። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን እቃህ ጉምሩክ ደርሶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አትችልም። በኛ ሀገር ሁኔታ ያስተናገደህ ሰው፣ ምን ያህል አቋራጭ መንገድ ታውቃለህ፣ መንግስት ካንተ ስንት ይጠብቃል፣ ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች ይወስኑታል።

ሌላው የEfficiency መለኪያ ነው። በግብር የሚጎብጥና ግብር ሳይከፍል የሚኖር መኖር የለበትም ማለት ነው። ግብር ሰዎች ስራን እንዲሸሹ፣ ግብርን ለመሰወር እንዲገደዱ፣ ወይም በህገ ወጥ ስራ እንዲሰማሩ ያሚያደርግ መሆን የለበትን ይላል። እዚህ ሀገር ግብር ከፋይ ነጋዴ መሆን ማለት በራስህ ላይ የማይቀር እዳ እንደማስቀመጥ የሚታይ ነው። መንግስት በአመታዊ ሪፖርት የተቀበለህ የሂሳብ መዝገብ በኦዲት ጊዜ ይጥለዋል። ከአመታት በኋላ ቅጣትና ወለድ ተጨምሮበት ያለ ጥፋትህ ከአቅምህ በላይ እንድትከፍል ትደረጋለህ። መጀመሪያ ለምን ተቀበልከኝ ብለህ መጠየቅ አትችልም። ነጋዴዎች ያለ ደረሰኝ ለምንድነው የምትሸጡት ብለህ ብትጠይቃቸው የሚሰጡህ መልስ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። መንግስት ነጋዴውን እንደ ሌባ ስለሚያየው “ሌባው ነጋዴ” ያመጣውን ሂሳብ በቀላሉ አይቀበለውም። ይህን ያህል ሂሳብ ያመጣው ይህን ያህሉን ደብቆ መሆን አለበት ብሎ ጭፍን እዳ ይጥልበታል። ግብር ከፋይነትህ ክብርና ሙገሳ አያመጣልህም። ስለዚህ አንደኛውኑ ተደብቆ በህገ ወጥ መንገድ በመስራት እራሱን ከወደፊት እዳ ለማዳን ይሞክራል። መንግስት ህጋዊ መዝገብ ይዞ በመጣው ላይ የሚያሳየው ቅጣት ሌሎች ወደ ግብር መረቡ በገዛ ፈቃዳቸው እንዲመጡ ሳይሆን እንዲደበቁ የሚያደርግ ነው። የታክስ መጠን ሰዎች የስራ ምርጫ የሚወስን መሆን የለበትም ይላል።

ሌላው የግብር መርህ fairness ነው። በተመሳሳይ ደረጃ ያሉ ሰዎች ተመሳሳይ ግብር መክፈል አለባቸው ይላል። ሙስናና የዝምድና አሰራር የታክስ ፍትሃዊነት ጠንቅ ናቸው።

እንግዲህ ከላይ እንዳየነው የግብር አላማ ልማት ማረጋገጥ፣ የዋጋ መረጋጋት መፍጠር፣ የስራ ዕድል መፍጠርና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል መፍጠር የመሳሰሉትን ያካትታል። እነዚህ ዓላማዎች ማሳካት ግብር መጨመር ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቹ ግብር መቀነስን የሚጠይቁ ናቸው። መንግስት ግብርን እንደ ገቢ መሰብሰቢያ ብቻ እያየ በዜጎቹ ላይ የግብር መዓት ሲቆልል በአንፃሩ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ የስራ ዕድል የመፍጠር አቅም እያቀጨጨ ይሄዳል። መንግስት በሰበሰበው ገንዘብ ስለሚፈጥረው የስራ ዕድል ብቻ እያየ ቢሆንም በአንፃሩ ተደራራቢ እና ከፍተኛ ግብር የግሉ ሴክተር የስራ ዕድል ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ መገንዘብ ያሻል። የዋጋ መረጋጋትን ለመቆጣጠር እንደ ኢኮኖሚው የእድገት ግለት ግብር መጨመርና መቀነስ ሊጠይቅ ይችላል።

መንግስት ግብር መሰብሰብ እንዳለበት አከራካሪ አይደለም። ግብር የሚሰበስበው ግን የልማትና የሀብት ክፍፍል ግቦችን ለማሳካት አንዳንዴም ኢኮኖሚው በጤናማነት እንዲሄድ እንደ ማስተካከያ መሳሪያነት ለመጠቀም መሆን አለበት። መንግስት ግብር ስለሰበሰበ ልማት አያመጣም። እንዲያውም በተቃራኒው የግብር መቀነስ ቁጠባና ኢንቨስትመንት በመጨመር የኢኮኖሚውን እድገት የሚያፋጥንበት ዕድል ሰፊ ነው። ገንዘቡ በግብር ከፋዩ እጅ የተሻለ ሃገራዊ ልማት የሚያመጣበት ዕድልም አለ። መንግስት ቀጥተኛ ግብር በመቀነሱ ምክንያት ኢኮኖሚው መነቃቃት ሲያሳይ ቀጥተኛ ባልሆኑ መንገዶች የተሻለ ገቢ መሰብሰብ ይችላል። በተለይ ሌባና ሙሰኛ መንግስት ሲኖር በመንግስት እጅ የሚገባ ገንዘብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል። ሙስናና ሌብነት ባይኖር እራሱ ግዙፍ መንግስት በአብዛኛው የግል ሴክተር ጠንቅ ነው። መንግስት ስላበጠ አገር ታድጋለች ማለት አይደለም። crowd out effect ይሉታል የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች። ኢኮኖሚውን የሚዘውር ግዙፍ መንግስት ባለበት ሐገር ጠንካራ የግል ዘርፍ ሊፈጠር አይችልም። በአንድ ቤት ሁለት አባወራ አይኖርም አይነት ነገር ነው። በኢኮኖሚ ውስጥ በሰፊው እጁን የሰደደ መንግስት እራሱ "ስግብግብ ነጋዴ" ይሆንና መንግስታዊ ባህሪውን ያጣል።

ህዝቡን አስጨንቆ ከስራ ውጭ የሚያደርግ የግብር ስርአት በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳርፈው ጠባሳ በቀላሉ የሚሽር አይሆንም። ግብር ዜጎች በአቅማቸው ልክ ሐገራቸውንና ህዝባቸውን የሚደጉሙበት፣ ከመንግስት አኳያም ከገቢ መሰብሰቢያነት ባሻገር የኢኮኖሚውን ጤናማ ጉዞ ማሳለጫ መሆኑ ቀርቶ ዜጎችን ማስጨነቂያ መሳሪያ ከሆነ የዜጎችና መንግስት ግንኙነት የባሪያና ጌታ ወይም የባላባትና ጭሰኛ ከመሆን አይላቀቅም።

ሌላው የግብር መርህ fairness ነው። በተመሳሳይ ደረጃ ያሉ ሰዎች ተመሳሳይ ግብር መክፈል አለባቸው ይላል። ሙስናና የዝምድና አሰራር የታክስ ፍትሃዊነት ጠንቅ ናቸው።

እንግዲህ ከላይ እንዳየነው የግብር አላማ ልማት ማረጋገጥ፣ የዋጋ መረጋጋት መፍጠር፣ የስራ ዕድል መፍጠርና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል መፍጠር የመሳሰሉትን ያካትታል። እነዚህ ዓላማዎች ማሳካት ግብር መጨመር ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቹ ግብር መቀነስን የሚጠይቁ ናቸው። መንግስት ግብርን እንደ ገቢ መሰብሰቢያ ብቻ እያየ በዜጎቹ ላይ የግብር መዓት ሲቆልል በአንፃሩ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ የስራ ዕድል የመፍጠር አቅም እያቀጨጨ ይሄዳል። መንግስት በሰበሰበው ገንዘብ ስለሚፈጥረው የስራ ዕድል ብቻ እያየ ቢሆንም በአንፃሩ ተደራራቢ እና ከፍተኛ ግብር የግሉ ሴክተር የስራ ዕድል ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ መገንዘብ ያሻል። የዋጋ መረጋጋትን ለመቆጣጠር እንደ ኢኮኖሚው የእድገት ግለት ግብር መጨመርና መቀነስ ሊጠይቅ ይችላል።

መንግስት ግብር መሰብሰብ እንዳለበት አከራካሪ አይደለም። ግብር የሚሰበስበው ግን የልማትና የሀብት ክፍፍል ግቦችን ለማሳካት አንዳንዴም ኢኮኖሚው በጤናማነት እንዲሄድ እንደ ማስተካከያ መሳሪያነት ለመጠቀም መሆን አለበት። መንግስት ግብር ስለሰበሰበ ልማት አያመጣም። እንዲያውም በተቃራኒው የግብር መቀነስ ቁጠባና ኢንቨስትመንት በመጨመር የኢኮኖሚውን እድገት የሚያፋጥንበት ዕድል ሰፊ ነው። ገንዘቡ በግብር ከፋዩ እጅ የተሻለ ሃገራዊ ልማት የሚያመጣበት ዕድልም አለ። መንግስት ቀጥተኛ ግብር በመቀነሱ ምክንያት ኢኮኖሚው መነቃቃት ሲያሳይ ቀጥተኛ ባልሆኑ መንገዶች የተሻለ ገቢ መሰብሰብ ይችላል። በተለይ ሌባና ሙሰኛ መንግስት ሲኖር በመንግስት እጅ የሚገባ ገንዘብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል። ሙስናና ሌብነት ባይኖር እራሱ ግዙፍ መንግስት በአብዛኛው የግል ሴክተር ጠንቅ ነው። መንግስት ስላበጠ አገር ታድጋለች ማለት አይደለም። crowd out effect ይሉታል የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች። ኢኮኖሚውን የሚዘውር ግዙፍ መንግስት ባለበት ሐገር ጠንካራ የግል ዘርፍ ሊፈጠር አይችልም። በአንድ ቤት ሁለት አባወራ አይኖርም አይነት ነገር ነው። በኢኮኖሚ ውስጥ በሰፊው እጁን የሰደደ መንግስት እራሱ "ስግብግብ ነጋዴ" ይሆንና መንግስታዊ ባህሪውን ያጣል።

ህዝቡን አስጨንቆ ከስራ ውጭ የሚያደርግ የግብር ስርአት በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳርፈው ጠባሳ በቀላሉ የሚሽር አይሆንም። ግብር ዜጎች በአቅማቸው ልክ ሐገራቸውንና ህዝባቸውን የሚደጉሙበት፣ ከመንግስት አኳያም ከገቢ መሰብሰቢያነት ባሻገር የኢኮኖሚውን ጤናማ ጉዞ ማሳለጫ መሆኑ ቀርቶ ዜጎችን ማስጨነቂያ መሳሪያ ከሆነ የዜጎችና መንግስት ግንኙነት የባሪያና ጌታ ወይም የባላባትና ጭሰኛ ከመሆን አይላቀቅም።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

02/01/2025

ባለፉት 60 ዓመታት የጉራጌን ማህበራዊ ስሪቶቻችን ከአነጹት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ዋነኛው ማህሙድ አህመድ ነው፡፡ ማህሙድ በማህበራዊው ዘርፍ ሀገራዊ ውክልናችን ያጸናንበት፣ መጠርያችን እና ክብራችን ሆኖ በጽናት ቆይቷል፡፡

ከአማርኛ የሙዚቃ ስራዎቹ አንጻር የጉራግኛ ሙዚቃዎቹ እጅግ ጥቂት ይሁኑ እንጂ ስራዎቹ ለዘመናዊ የጉራግኛ ሙዚቃዎች መሰረት የጣሉ ናቸው፡፡

የጉራግኛ ሙዚቃዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቃ በአለም መድረክ እንዲታወቁ ከነበራቸው የጎላ አስተዋፅኦ ባሻገር መጪውም ጊዜ በዕሱ ከፍታ ልክ የሚመጡ የብሔረሰቡ ድምጻውያን ጥሩ የማዕዘን ድንጋይ ያኖረ ጉምቱ ሰው ነው፡፡

ጋሽ ማህሙድ የመጨረሻ መድረኩ ጥር 3 2017ዓ.ም በሚልንየም አዳራሽ ያቀርባል። የመጨረሻውም አልበም በቅርቡ ይደመጣል። ግለ ታሪኩን ያተተበት መጽሐፍ ሆነ ሌሎች ዝክረ ማህሙድ ዝግጅቶች በተከታታይ ይቀርባሉ።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

የመጥፋት አደጋ  የተጋረጠበት ጀᎈረ  የጎርደና ᎀጨ
02/01/2025

የመጥፋት አደጋ የተጋረጠበት ጀᎈረ የጎርደና ᎀጨ

የገጠር ኮሪደር እና ጀᎈረ ኮሪደር || የመጥፋት አደጋ የተጋረጠበት የጎርደና ᎀጨሓሪ ዲጂታል፡- በተለያዩ የሚድያና ሚዲያ ነክ ዘርፎች ማለትም ሓሪ ፖድካትን ጨምሮ በዲጂታል ሚዲያ የሚራጩ ...

በመርካቶና አንዳንድ አካባቢዎች የደረሠኝ ቁጥጥሩ ውጤት አምጥቶልኛል አለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ፡፡መርካቶን ጨምሮ በሥምንት ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ዋና ዋና የግብይት ሥፍራ...
02/01/2025

በመርካቶና አንዳንድ አካባቢዎች የደረሠኝ ቁጥጥሩ ውጤት አምጥቶልኛል አለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ፡፡

መርካቶን ጨምሮ በሥምንት ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ዋና ዋና የግብይት ሥፍራዎች ደረሠኝ በመቁረጥ እና ተያያዥ ጉዳይ ላይ እየተከናወነ ያለው ቁጥጥር ውጤት አምጥቷል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከተማዋ ማግኘት ያለባትን ገቢ በአግባቡ እንድታገኝ ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓትን ማስፈን ትኩረት ተሰጥቶት የቁጥጥር እና ክትትል ሥራ በትጋት እየተከናወነ መሆኑን የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት አየለ አስታውቀዋል፡፡

ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ ከሚቻልባቸው ስልቶች ግብይትን በደረሠኝ ማስደገፍ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው÷ ደረሠኝ የመቁረጥ ግዴታ በሕግ የተደነገገባቸው ነጋዴዎች ይህን መተግበር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ይህን በማይተገብሩ ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው፤ ለአብነትም 1 ሺህ 445 መርካቶ የሚገኙ ነጋዴዎች ከደረሠኝ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ከማስጠንቀቂያ እስከ 100 ሺህ ብር ተቀጥተዋል ሲሉ ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

በሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ምክንያት ከንግድ እራሳቸውን አግልለው የነበሩ መመለሳቸው፣ ደረሠኝ የሚቆርጡ ነጋዴዎች ቁጥር መጨመሩ፣ የገቢ አሳሰብ እና ሕግ የማስከበር አቅም እያደገ መሆኑ የደረሠኝ ቁጥጥሩ ተጨባጭ ውጤት ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡

አሁንም ቢሆን ደረሠኝ መቁረጥ የሚጠበቅባቸው ያለመቁረጥ፣ ሐሰተኛ ደረሠኞችን መጠቀም፣ ደረሠኝ ሲቆርጡ ከግብይት በታች ገንዘብ መጻፍ፣ ዕቃ የማሸሽ፣ ከሕግ ለማምለጥ በሚል በድብብቆሽ ግብይት የመፈጸም ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይህን ታሳቢ በማድረግ ችግሩ በሚታይባቸው የተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በሌሊት ጭምር የቁጥጥር እና ክትትል ሥራ በጥብቅ እየተሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በ FMC እንደዘገበው።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ፣  የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ :- ታህሣሥ 23/2017የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግ...
01/01/2025

በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ፣ የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ

:- ታህሣሥ 23/2017

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው።

ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል።

Via Ethiopia law

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

Address

Bole Road, Wereda 17
Addis Ababa

Telephone

+251977961254

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ:

Videos

Share