ሸዋ Times

ሸዋ Times ሽዋ በኢትዮጵያ ገጸ ምድር መሃል ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ሥፍራ ነው!

09/12/2024

ሱሌይማን አብደላ ተላልፎ ተሰጠ!

05/12/2024

የጥበበኞቹ ልጆች ነን!

ህዳር 25 ቀን 1560 ዓ.ም!ከ 457 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የዓፄ ልብነ ድንግል ሚስት የነበሩት እቴጌ ሰብለ ወንጌል አመድ በር በምትባል ሥፍራ ያረፉበት ዕለት ነበር።የእቴጌ ሰብለ...
05/12/2024

ህዳር 25 ቀን 1560 ዓ.ም!

ከ 457 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የዓፄ ልብነ ድንግል ሚስት የነበሩት እቴጌ ሰብለ ወንጌል አመድ በር በምትባል ሥፍራ ያረፉበት ዕለት ነበር።

የእቴጌ ሰብለወንጌል የአጤ ልብነድንግል ባለቤት የነበሩትና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ከያዙ እንስቶች መካከል ተጠቃሽ የሆኑት እቴጌ ሰብለወንጌል ያረፉት ከዛሬ 457 ዓመታት በፊት (ኅዳር 25 ቀን 1560 ዓ.ም) ነበር፡፡

በመጋቢት ወር 1521 ዓ.ም ሽምብራ ኩሬ ላይ በተደረገው ጦርነት አጤ ልብነድንግል ድል ከሆኑ በኋላ ንጉሡ በዐምሐራና በትግራይ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ የግራኝ አህመድን ጦር ለመከላከል ሞከሩ፡፡

ይሁን እንጂ ለአንድ ጀንበር እንኳ ጥይት ድምፅ ተለይቶት የማያውቀው የሰሜናዊው/ደጋማው የክርስቲያን ግዛተ-አፄ (The Christian Highland Kingdom) ጦር በቱርኮች የጦር መሳሪያ እርዳታ የፈረጠመውን የግራኛ አህመድን ጦር መቋቋም ሳይችል ቀረ፡፡

መልካም ቀን ደጉ ባለሀገር!
29/11/2024

መልካም ቀን ደጉ ባለሀገር!

ህዳር 19 ቀን 1967 ዓ.ም!ከዛሬ 50 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ብርጋዴር ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ሁለተኛው የደርግ ሊቀ-መንበር እና የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡበት ዕለት ነበር።...
28/11/2024

ህዳር 19 ቀን 1967 ዓ.ም!

ከዛሬ 50 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ብርጋዴር ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ሁለተኛው የደርግ ሊቀ-መንበር እና የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡበት ዕለት ነበር።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈሪ በንቲ የመጀመሪያው የደርጉ ፕሬዝዳት ሌ/ጀነራል አማን ሚካኤል ከተገደሉ በኃላ ተመርጠው ወደ ስልጣን የመጡት ህዳር 19 ቀን 1967 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን እሳቸውም እስከ ተገደሉበት ዕለት ማለትም ጥር 26 ቀን 1969 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን ሁለት አመት ከሁለት ወር ከሠባት ቀናት መርተዋታል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አራተኛ ፓትርያርክ የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው ። በሰዓሊና ቀራጺ ቡዝዬ ካሰሽ በስሜን አሜሪካን የተሰራው ...
28/11/2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አራተኛ ፓትርያርክ የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው ።

በሰዓሊና ቀራጺ ቡዝዬ ካሰሽ በስሜን አሜሪካን የተሰራው መታሰቢያ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል አቡነ መርቆርዮስ አጽማቸው ባረፈበት ስፍራ እንዲቆም ይደረጋል።

ሰዓሊና ቀራጺ ቡዝዬ ካሰች በሀገራችን ታዋቂ የሆኑ የመታሰቢያ በርካታ ሐውልቶችን እና ፓርትሬቶችን በመስራት ይታወቃል ።

ህዳር 18 ቀን 1934 ዓ.ም!ከ 83 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ወራሪው የፋሺስት ኢጣልያን ጦር የመጨረሻውን ይዞታ ጎንደርን ለማስለቀቅ አባቶቻችን አርበኞች ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር በከተማ...
27/11/2024

ህዳር 18 ቀን 1934 ዓ.ም!

ከ 83 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ወራሪው የፋሺስት ኢጣልያን ጦር የመጨረሻውን ይዞታ ጎንደርን ለማስለቀቅ አባቶቻችን አርበኞች ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር በከተማዋ ዙሪያ ውጊያ ተደርጎ ጄኔራል ናሲ ከነሠራዊቱ እጁን ሰጥቶ የአገራችን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በፋሲለደስ ግንብ ላይ የተውለበለበት ዕለት ነበር።

"ቅዱስ ሚካኤል ምስክሬ ነው!"ኅዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም (ከዛሬ 3 ዓመታት በፊት)!ሳላይሽ፣ ሸዋ፣ ዐማራ፣ ኢትዮጵያ!አባት እሸቴ ሞገስልጅ ይታገስ እሸቴ ሞገስ
26/11/2024

"ቅዱስ ሚካኤል ምስክሬ ነው!"

ኅዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም (ከዛሬ 3 ዓመታት በፊት)!
ሳላይሽ፣ ሸዋ፣ ዐማራ፣ ኢትዮጵያ!

አባት እሸቴ ሞገስ
ልጅ ይታገስ እሸቴ ሞገስ

ህዳር 17 ቀን 1879 ዓ.ም!ከ138 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን አዲስ አበባ ከተማ በዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ በፍልውሃ ፣ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ አጥር አሳጠረውበት በነበረው ሥፍራ አካባ...
26/11/2024

ህዳር 17 ቀን 1879 ዓ.ም!

ከ138 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን አዲስ አበባ ከተማ በዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ በፍልውሃ ፣ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ አጥር አሳጠረውበት በነበረው ሥፍራ አካባቢ እቴጌ ጣይቱ ፍልውሃ ወደ በሚፈልቅበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት ተመልክተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተው ስለማረከቻቸው ቦታውን "አዲስ አበባ" ብለው የሠየሟት ዕለት ነበር።

ህዳር ሲታጠን!በሽታው ከኅዳር 7 እስከ 20 በቆየበት ጊዜ 40,000 የሚያህሉ ሰዎች እንደሞቱ ይነገራል!ብዙዎቹ የሚያውቁት የኅዳር በሽታ (የኅዳር መቅሰፍት) በሚባለው ስሙ ነው።በእርግጥ በሽ...
21/11/2024

ህዳር ሲታጠን!

በሽታው ከኅዳር 7 እስከ 20 በቆየበት ጊዜ 40,000 የሚያህሉ ሰዎች እንደሞቱ ይነገራል!

ብዙዎቹ የሚያውቁት የኅዳር በሽታ (የኅዳር መቅሰፍት) በሚባለው ስሙ ነው።በእርግጥ በሽታው ከውጪ ሀገራት በአየር(ንፋስ) ምክንያት በ1911 ዓ/ም ሀገራችን የገባ ሲሆን ሳይንሳዊ ስሙ "ግሪፕ" ሲባል ኢትዮጵያውያን ደግሞ ኢንፍሎኤንዛ መቅሰፍት ይሉት ነበር። በ3ቀንና በ4ቀን የሚገድል በሽታ ነበር፡፡ በጊዜውም በአዲስ አበባ ብቻ 9000 ሰዎችን ገድሏል።

የሚገርመው የበሽታው አስከፊነት ስለጨመረ በበሽታው የሞተውን ሰው የሚቀብር ሰው አይገኝም ነበር። ሬሳውን ቤተክርስቲያን ሄዶ ለመቅበር አቅም ያጣ ቤተሰብ ደግሞ እዛው ግቢው ውስጥ ይቀብሩ ነበር አንድ ቤተሰብ ሙሉ የሚያስታምማቸው በማጣት ቤተሰቡ በሙሉ ያልቅ ነበር።

አንድ ሰው የሞተበትን ዘመዱን ለመቅበር ጉድጎድ ቆፍሮ ሬሳውን ለማምጣት ቤቱ ሄዶ ሲመጣ በቆፈረው ጉድጎድ ሌላ ሰው ተቀብሮበት ያገኛል አንዳንዶች ደግሞ የሚቀብሩበት ጉድጎድ ጥልቅ ስላልነበር ሬሳውን አውሬ ይተናኮለው ነበር።

በኅዳር 12 ቀን ደግሞ ከበፊቱ ቀናት የሚበልጥ ሰዎች ሞተዋል። በአጠቃላይ በሽታው ከኅዳር 7 እስከ 20 በቆየበት ጊዜ 40,000 የሚያህሉ ሰዎች እንደሞቱ ይነገራል።

በዚህ በሽታ ብዙ ሹማምንትና የዘመኑ ታላላቅ ሰዎች ሞተዋል በበሽታው አልሞቱም እንጂ አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኰንን (ኃይለ ሥላሴ)፣ እቴጌ መነን ፣ ንግሥት ዘውዲቱ ተይዘው እንደነበር ይነገራል።

21/11/2024

በንፁሃን ደም መቀለድ ዋጋ ያስከፍላል! ማንም ያድርገው ማን ይህን ሰው የሆነ ሁሉ ይቃወማል።

በመርካቶ ቃጠሎ ተከስቷልበመርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ ድንች በረንዳ ዛሬ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 የእሳት አደጋ ተከስቷል።
17/11/2024

በመርካቶ ቃጠሎ ተከስቷል

በመርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ ድንች በረንዳ ዛሬ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 የእሳት አደጋ ተከስቷል።

የት ነው ያለው ግን ይኼ ሰውዬ?
17/11/2024

የት ነው ያለው ግን ይኼ ሰውዬ?

ህዳር 4 ቀን 1924 ዓ.ም!ከዛሬ 93 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ዙሪያ ትልቅ ተሳትፎ ያደረጉት ስመጥሩ የፖለቲካው ሰው ራስ ናደው (አባ ወሎ) ህይወታቸው ያለፈበት...
14/11/2024

ህዳር 4 ቀን 1924 ዓ.ም!

ከዛሬ 93 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ዙሪያ ትልቅ ተሳትፎ ያደረጉት ስመጥሩ የፖለቲካው ሰው ራስ ናደው (አባ ወሎ) ህይወታቸው ያለፈበት ዕለት ነበር

ራስ ናደው አባ ወሎ በፈረስ ስማቸው “አባ መብረቅ” በዳግማዊ ምንሊክ ዘመነ መንግሥት እና በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በተለይም በውጭ ጉዳይ ዙሪያ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸው ስመጥር የፖለቲካ ሰው ነበሩ።

ራስ ናደው ትውልዳቸው በሰሜን ሸዋ ታዋቂ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆነው ከአዲስጌ ቤተሰብ ነው። ራስ ናደው አባ ወሎ በውጪ ጉዳይ በነበራቸው ከፍተኛ ተሳትፎ ባሻገር ለረዥም ጊዜ የኢሉባቦር ግዛት (ገዢ) በመሆን አስተዳድረዋል።

በውጪ ጉዳይ ዙሪያ በነበራቸው ተሳትፎ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን ከ 1ኛው የዓለም ጦርነት ብኋላ በአሸናፊነት የወጡትን የተባበሩት ኃይል እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ወደ አውሮፓና አሜሪካ የሂደውን የኢትዮጵያ ልዑክ መርተዋል።

በዚህ ጉዞ በራስ ናደው የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ዩናይትድ ኪንግደምን እና አሜሪካን የጎበኘ ሲሆን እግረ መንገዱንም የኢትዮጵያን ልዑላዊነትና በዓለም አቀፍ ፖለቲካው ያላትን ቦታ ለዓለም አስረድቷል። ኢትዮጵያ ወደ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ለመግባት ጥረት በምታደርግበት ወቅት ራስ ናደው የኢትዮጵያ ወኪል ሆነው አገልግለዋል።

ለዚሁ ጉዳይ ወደ ጄኔቫ የሄደውን ቡድን የመሩም ሲሆን ቡድኑ ከራስ ናደው በተጨማሪ ብላቴን ጌታ ኃሩይ ወልደሥላሴና ፋሲካን በመልዕክተኝነት የያዘ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ራስ ተፈሪ መኮንን (በኋላ አፄ ኃይለላሴ) ወደ አውሮፓ ባደረጉት ጉብኝት አጅበው ከሄዱት ሰዎች መካከል ራስ ናደው አባ ወሎ አንዱ ነበሩ።

ዶክተር አበራ ሞላ ማናቸው?ዶ/ር አበራ ሞላ (መጋቢት 24 ቀን 1940 ዓ.ም) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ መናገሻ አውራጃ፣ ሰንዳፋ ከተማ የተወለዱ ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በግዕዝ ፊደል እንዲጽ...
13/11/2024

ዶክተር አበራ ሞላ ማናቸው?

ዶ/ር አበራ ሞላ (መጋቢት 24 ቀን 1940 ዓ.ም) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ መናገሻ አውራጃ፣ ሰንዳፋ ከተማ የተወለዱ ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በግዕዝ ፊደል እንዲጽፉ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ናቸው።

ዶክተር አበራ ሞላ የታወቁባቸው ዋናዎቹ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው። የመድንን ማነስ በማስወገድ ከዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ታዋቂ ምሁር፣ የግዕዝ ፊደልንና ሥነ ጽሑፍ በኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ውስጥ ባለውም መጠቀም እንዲቻል ያደረጉ ሰባት የዩናይትድ እስቴትስና ኢትዮጵያ ፓተንቶች ብቻቸውን ያሏቸው የግኝት ሊቅና የአክሱም ሐውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጣልያንን በማስገደድ ወሳኙን ርምጃ የወሰዱ አርበኛ ናቸው።

ዶክተሩ የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ቀለሞችና የግዕዝ ኣሥር ቤት ኣኃዛዊ ቍጥሮች ፈጣሪም ናቸው። የግዕዝ ፊደል ሳይቆራረጥ፣ ሳይቀነስና ሳይበላለጥ ዩኒኮድ እንዲገባ የሰጡና ለመብቱ የተሟገቱለት አሸናፊ ናቸው።

ጥቅምት 30 ቀን 1848 ዓ.ም!ከዛሬ 169 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የሸዋ ንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ እና የወይዘሮ በለጥሻቸው ወልዴ ልጅ የሆኑት ንጉስ ኃይለመለኮት ሳህለ ሥላሴ በድን...
09/11/2024

ጥቅምት 30 ቀን 1848 ዓ.ም!

ከዛሬ 169 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የሸዋ ንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ እና የወይዘሮ በለጥሻቸው ወልዴ ልጅ የሆኑት ንጉስ ኃይለመለኮት ሳህለ ሥላሴ በድንገተኛ ኅመም ምክንያት አርፈው በደብረ በግዕ የተቀበሩበት ዕለት ነበር።

የሸዋው ንጉሥ ኃይለመለኮት በሰውነታቸው ግዝፈትና ጥንካሬ እንዲሁም በልባቸው ቀናነት በሸዋ ዘንድ የታወቁና የተወደዱ ንጉሥ ነበሩ። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የኢትዮጵያ ታሪክ በሚለው መጽሐፋቸው እንደሚነግሩን ንጉሥ ኃይለመለኮት ከጥንካሬያቸው የተነሳ ኢላማ ተኩስ በሚተኩሱ ጊዜ መሳሪያውን አጠንክረው በመያዛቸው ምክንያት ጥይቱ ሲወጣ ጠምንጃቸው ለሁለት ተሰብሮ እጃቸው ላይ ቀርቶ ያውቃል።

ንጉሥ ኃይለመለኮት ከአባታቸው ሞት በመቀጠል ወደንግሥናው ዙፋን ከወጡ በኋላ ሸዋን ለ 8 ዓመታት አስተዳድረዋል። በስልጣን ላይ ሳሉም ተቀናቃኝ ሊሆኑባቸው የሚችሉትን ወገኖቻቸውን በእስር ዞር እንዲያረጓቸው ከጓናቸው ያሉ ሰዎች ሲመክሯቸው "ተዉ ይሄን አላደርገውም እግዚአብሔር የወደደውን ነው የሚያስገዛው" የሚሉ ቀና እንደነበሩ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ በመጽሐፋቸው ይጠቅሳሉ።

በመጨረሻም አጼ ቴዎድሮስ በሀገሪቱ በየቦታው ያለውን የተከፋፈለ አገዛዝ ወደ አንድ በማምጣት በማእከላዊ መንግሥት ስር የምትተዳር አንዲት ሀገር ለመመስረት አስበው ከየመሳፍንቱ ጋር በሚዋጉ ጊዜ ወደ ሸዋም ሊመጡ ነው የሚል ወሬ ተሰምቶ ንገሥ ኃይለመለኮትም ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ሆኖም ግን ገና ቀደም ብሎ ንጉሡ ኃይለመለኮት በጣም ታመው ነበርና እርሳቸው በጦርነቱ ሳይካፈሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩት ንጉሥ ኃይለመለኮት ሳህለሥላሴ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ አባት ናቸው።

ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደሚሆኑ ' ፎክስ ኒውስ ' ጠቁሟል።ትራምፕ፣ ካማላን ሃሪስን በማሸነፍ ቀጣዩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ይሆናሉ ሲል አሳውቋል።አሁን ባለው ውጤት...
06/11/2024

ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደሚሆኑ ' ፎክስ ኒውስ ' ጠቁሟል።

ትራምፕ፣ ካማላን ሃሪስን በማሸነፍ ቀጣዩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ይሆናሉ ሲል አሳውቋል።

አሁን ባለው ውጤት የቀድሞ ፕሬዜዳንት ትራምፕ ዳግም ሀገሪቱን የመምራት እድል ይሰጣቸዋል።

ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም!ከ 94 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ልዑል አልጋ ወራሹ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ ጭነው ቀዳማዊ ኃ...
02/11/2024

ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም!

ከ 94 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ልዑል አልጋ ወራሹ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ ጭነው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተባሉበት ዕለት ነበር።

ንግስተ ነገስት ዘውዲቱ መጋቢት 22 ቀን 1922 እንዳረፉ ፤ ስልጣኑን የተረከቡት ተፈሪ ከሰባት ወር በኋላ ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም ነበር የስርዓተ-ንግስ በዓላቸው በደማቅ ሁኔታ የተከናወነው፡፡

እነዚያ 7 ወራት በኢትዮጵያ ምድር ታይቶ የማይታወቅ የበዓል ማሸብረቂያ ዝግጅት የተካሄደባቸው ናቸው ፥ ንጉሠ ነገሥቱና እቴጌዋ የሚጓዙበት ሠረገላ ከጀርመን አገር መጣ ፥ ልብሱ ሁሉ በወርቅና በሐር የተሽቆጠቆጠ ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ክርንክስ ቤቶች እንዲወገዱ ተደረገ ፥ መንገዱ አስፋልት ሆነ፡፡

Address

Adama

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሸዋ Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category