Debrebirhan Press

Debrebirhan Press ሰለ እውነትና ፍትህ ይታገላል
(1)

ተንኮልና ምቀኝነትን መጸየፍ አለብን !!"..የምንኖርባት ጊዜ ከዘላለማዊ ህይወት ላይ ተቀንሳ በቅንፍ ውስጥ የተቀመጠች በጣም ትንሽ ጊዜ ናት.." በዚች ጊዜ ውስጥ በህይወታችን ስንኖር መረዳዳ...
25/03/2024

ተንኮልና ምቀኝነትን መጸየፍ አለብን !!

"..የምንኖርባት ጊዜ ከዘላለማዊ ህይወት ላይ ተቀንሳ በቅንፍ ውስጥ የተቀመጠች በጣም ትንሽ ጊዜ ናት.." በዚች ጊዜ ውስጥ በህይወታችን ስንኖር መረዳዳትን ፤ መተባበርንና መቀራረብን መልመድ አለብን።

ተንኮልና ምቀኝነትን መጸየፍ አለብን።

በየመጠለያው ቤታቸው ፈርሶ በሀዘን እና ረሃብ ለሚሰቃዩ ዜጎች፣ በክፉዎች እየተሳደደች ለምትገኝ ቅድስት ቤተክርስቲያን፣ በሰላም እጦት ምክንያት መውጣት መግባት ለቸገራቸው ወገኖች፣በጦርነት ምክ...
12/09/2023

በየመጠለያው ቤታቸው ፈርሶ በሀዘን እና ረሃብ ለሚሰቃዩ ዜጎች፣ በክፉዎች እየተሳደደች ለምትገኝ ቅድስት ቤተክርስቲያን፣ በሰላም እጦት ምክንያት መውጣት መግባት ለቸገራቸው ወገኖች፣በጦርነት ምክንያት ቤተሰባቸው ለተበተነ፣በማንነታቸው በየቦታው ለሚገደሉ እና ለሚፈናቀሉ ኢትዮጲያውያን ሁሉ አዲሱ አመት የእረፍት ፣ የሰላም እና የነፃነት ያርግላቸው። ሀገራችንን ሰላም ያርግልን።
#መልካምአዲስዓመት

‹‹ እንደ ምኒልክ  አይነት ሩህሩህ የለም›› ታየ ቦጋለ፡፡  ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነት መሥማት ልቡ የወደደ ሁሉ ይከተላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ ይወዳቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ...
07/09/2023

‹‹ እንደ ምኒልክ አይነት ሩህሩህ የለም›› ታየ ቦጋለ፡፡

ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነት መሥማት ልቡ የወደደ ሁሉ ይከተላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ ይወዳቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ጠላቱ የሆነ ደግሞ አምርሮ ይጠላቸዋል፡፡

ባገኙት አጋጣሚ በደረሱበት ሁሉ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነት ይናገራሉ፡፡ ይመሰክራሉ፡፡ የኢትዮጵያዊያንን ታሪክ በእውነት ሚዛን ይመዝናሉ፡፡ ወገንተኝነታቸው ለእውነት ነው የታሪክ መምሕሩና የመራራ እውነት ደራሲው ታዬ ቦጋለ፡፡

ከዘመናት በፊት በዘመነችው፣ ከቀደሙት በፊት በቀደመችው ፣ የታሪክ ሀብታም በሆነችው ኢትዮጵያ ይመካሉ፡፡

ምኒልክና እውነተኛ ፌደራሊዝም ስርዓትን በተመለከተ ከአብመድ ጋርቀ ቆይታ አድርገዋል፡፡

ምኒልክ ሶስት አይነት የዘመቻ ምዕራፍ ነበሯቸው ነው ያሉት፡፡ የመጀመሪያው የሸዋ ንጉሥ በነበሩበት ወቅት የሸዋ አማራና የሸዋ ኦሮሞ የጦር አበጋዞቻቸውን ይዘው በሰላማዊ መንገድ ግዛቶቻቸውን አስፍተው ነበር፡፡ በእነዚህ ሰላማዊ ዘመቻዎቻቸው ጅማን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን ይዘዋል፡፡

በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ ገዥ የመደቡት የአካባቢውን ተወላጆች ነው፡፡ ትክክለኛ የሆነውን ፌደራሊዝም የጀመሩና አሁን ላይ የብሔር ፌደራሊዝም የሚባለውን እሳቸው እስከ ታች ድረስ በተግባር ያሳዩ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ዜጎች በቋንቋቸው እንዲተዳደሩ ያደርጉ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

ሁለተኛው ዘመቻቸው ደግሞ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከሆኑበት ጊዜ እስከ አድዋ ጦርነት ባለው ጊዜ ነበር፡፡ በዘመቻቸው አብዛኛውን ቦታ የያዙት በሰላማዊ መንገድ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ሶስተኛው የዘመቻ ምዕራፍ ደግሞ ከአድዋ ድል በኋላ እንደነበር አንስተዋል፡፡ የምኒልክ ዘመቻ አንድም ኢትዮጵያዊያንን በጋብቻ የማስተሳሰር፤ ሌላኛው በየአካባቢው ራሱን እንዲያስተዳድር የማድረግ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ትህነግ የሚመካበትና አሁን ላይ ያለው ፌደራሊዝም ግን የይስሙላህ መሆኑን ነው ያመላከቱት፡፡ እንደፈለገ የሚያሽከረክርበት ፌደራሊዝም ነው ያሉት የታሪክ ምሁሩ የምኒልክ ፌደራሊዝም እውነተኛ፣ በጣም ዘመናዊ፣ በዚያ ዘመን ውስጥ ሊታሰብ የማይችል የፌደራሊዝም ስርዓት ነበር ብለዋል፡፡

ምኒልክ አፍሪካን ወራሪዎች እየገቡባት እንደሆነ ያውቁ ስለ ነበር ከወገኖቻቸው ጋር ከመጋጨት ይልቅ በዙሪያቸው ጠላት እንዳለ በመናገር በፍቅር ለመኖር ጥረት ያደርጉ እንደነበርም ነው የተናገሩት፡፡

ያለፉት ሶስት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ ታሪክ ችግሩ በፈጠራ የተመሰረተና የኦነግን፣ የወያኔንና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉትን ሰዎች ዓላማ የያዘ መሆኑን ነው የታሪክ ምሁሩ ያስረዱት፡፡
‹‹እንደ ምኒልክ አይነት ሩህሩህ የለም›› ሲሉም ስለ ምኒልክ የሚወራው የሀሰት ትርክት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ከሰው መሀል አልቆ ሲያስገዛህ በሰው መጨከን አይገባም፣ ለሰው ሲያዝኑ እግዚአብሔር እድሜ ይሰጣል፣ የሚሉት ምኒልክ የባርያ ንግድ የሚባለውን ተግባርና አስተሳሰብ አጥብቀው ይቃወሙ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

ምኒልክ አይደለም ለወዳጅ ለካዳቸውና ሊገድላቸው ለተዘጋጄ ጭምር ይቅርታ የሚያደርጉ ሰው እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡ ትልቅ ቁም ነገራቸውና ትልቅ ራዕያቸው ከዘመን የቀደመ መሆኑንም ነግረውኛል፡፡ ምኒልክ ሕዝቤ በባዶ እግሩ እየሄደ እኔ በጫማ አልሄድም ብለው የወርቅ ጫማቸውን አውልቀው በባዶ እግራቸው የሚሄዱ መሪ እንደነበሩም ምሁሩ አስታውሰዋል፡፡

ምኒልክ የስልጣኔ አውራና ጠቢብ ናቸው ያሉት አቶ ታዬ ቦጋለ ስለ እሳቸው የሚወራው በሙሉ ለፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ካልሆነ በስተቀር እንደዚያ አይነት ሥነ ልቦና ያላቸው አይነት ሰው አልነበሩም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በአንድነታቸው እንዲቀጥሉ የማያግባቡ ትርክቶች ሲኖሩ በማቆምና የሌላው ዓለም ተሞክሮ ምን ይመስላል የሚለውን ማዬት ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በትምህርት ዓለማ መሄድና ሁሉንም ሰው በእኩል ማዬት ተገቢ እንደሆነም ጠቅሰዋል። ወደሰፈር ከመውረድ በአንድነታችን ላይ መስራት እንደሚገባንም ነው ያሳሰቡት፡፡

የሰው ልጅ ለእንስሳት መብት በሚቆምበት ዘመን ያልተፈለገ ነገር ውስጥ መግባት እንደማይገባም አሳስበዋል፡፡ ውይይት፣ አዳዲስ ስርዓተ ትምህርት መቅረፅ፣ ቀናነትን፣ ሰውነትን መያዝ፣ በእምነት መራመድ፣ በዘመናት ውስጥ የነበረንን መስተጋብር ማንሳት ይገባልም ብለዋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን ታላላቅ የታሪክ አዋቂዎችን በማቅረብ ሰውን ከብዥታ ማውጣት እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ዓለም የምትጠፋው ከመጥፎዎች እኩይ ድርጊት ይልቅ በመልካሞች ዝመታ ነው›› እንዲሉ መልካሞች ዝም እንዳይሉ ማድረግ ይገባልም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ተነካች በተባለበት ሁሉ አብሮ በሚወድቀው በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ እንያት፤ እኛ የአንድ እናት ልጆች ነን፤ ሰው በሞራል፣ በሃይማኖትና በሰውነት መኖር መቻል አለበትም ብለዋል፡፡

ሰው ሰው መሆኑን ቢያውቅና ለምን ዓላማ እንደተፈጠረ ቢገነዘብ፣ እመነት ቢኖረውና በእመነቱ ህግጋት ቢሄድ፣ በኢትዮጵያዊነት ሥነ ምግባርና ሞራል ታንፆ ቢያድርግና የሚያደረግው ድርጊት ውጤቱ ምንድን ነው የእኔን ማሕበረሰብ ይጠቅማል ወይ የሚለውን ቢረዳ መልካም እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ አንድ ላይ መታገል እንደሚገባም መክረዋል፡፡ ወደዚህ ምድር ፈልጎ የመጣ የለም፤ ወደዚህ ምደር ሌላውን ጠልቶ ሌላውን ፈልጎ የመጣ ሰው ባለመኖሩ ሰውነቱን ልናከብረው እንጂ ልንጠላው አይገባም ነው ያሉት የታሪክ ምሁሩና የመራራ እውነት ደራሲው ታየ ቦጋለ፡፡

በታርቆ ክንዴ

መንገደኛ የተሰኘ የአገር አቋራጭ የአውቶብስ ትኬት መቁረጫ ሲስተም ይፋ ሆኗል።ሲስተሙ የአውቶብስ ቲኬት ለመቁረጥ የሚባክነውን ጊዜ ያስቀራል ተብሏል። ከታች የተያያዘውን ሊንክ ከጎግል ስቶር በ...
06/09/2023

መንገደኛ የተሰኘ የአገር አቋራጭ የአውቶብስ ትኬት መቁረጫ ሲስተም ይፋ ሆኗል።

ሲስተሙ የአውቶብስ ቲኬት ለመቁረጥ የሚባክነውን ጊዜ ያስቀራል ተብሏል።
ከታች የተያያዘውን ሊንክ ከጎግል ስቶር በማውረድ በሞባይልዎ እና በኮምፒውተርዎ መጠቀም ይችላሉ።
ጊዜ እና እንግልት ይቀንስልዎታል።

Mengedegna - Ethiopia bus ticket booking system in English, Amharic and Oromifa.

Mengedegna is an online bus booking application that helps internet users to reserve and purchase bus tickets across Ethiopia using their phones or computers through the bus reservation system. It is multilingual (English, Amharic and Afaan Oromoo) and works with most bust operators in Ethiopia. The app was developed by Walia Technologies PLC with the goal of establishing a safe and simple bus reservation system. The app's main purpose is to help users reserve and purchase bus tickets utilizing an online system with just a few clicks of your phone that eliminating the need to queue at a counter to buy a bus ticket. Customers can also use this simple app to check the availability and types of buses, as well as the departure time online. The application is integrated with TeleBirr and PayPal for quick payment, and it also allows customers to cancel and reschedule their reservations at any time. With our dedicated customer service, the application is available at all times, 24 hours a day.

Our mission is to transform Ethiopia's bus transportation system from an offline to a digitized and modern system, as well as to establish a user-friendly, easy-to-use system for the state's transportation sector. This application will provide hassle-free bus ticketing transporation system and play a huge role in digitizing Ethiopia’s Bus ticketing system.

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.waliatech.mengedegna

"..የምንኖርባት ጊዜ ከዘላለማዊ ህይወት ላይ ተቀንሳ በቅንፍ ውስጥ የተቀመጠች በጣም ትንሽ ጊዜ ናት.." በዚች ጊዜ ውስጥ በህይወታችን ስንኖር መረዳዳትን ፤ መተባበርንና መቀራረብን መልመድ ...
04/09/2023

"..የምንኖርባት ጊዜ ከዘላለማዊ ህይወት ላይ ተቀንሳ በቅንፍ ውስጥ የተቀመጠች በጣም ትንሽ ጊዜ ናት.." በዚች ጊዜ ውስጥ በህይወታችን ስንኖር መረዳዳትን ፤ መተባበርንና መቀራረብን መልመድ አለብን።

❤️የኢትዮጵያ የታሪክ ኣርማ ሸዋ ደብረ ብርሃን❤️✍ሸዋ ደብረ ብርሃን ንጉሡና ፈላስፈው አጼ ዘርዐ ያእቆብ የመሰረታት ከተማ ናት✍ሸዋ ደብረ ብርሃን በአሰራሩ ግሩም የሆነው የደብረ ብርሃን ስላ...
04/09/2023

❤️የኢትዮጵያ የታሪክ ኣርማ ሸዋ ደብረ ብርሃን❤️

✍ሸዋ ደብረ ብርሃን ንጉሡና ፈላስፈው አጼ ዘርዐ ያእቆብ የመሰረታት ከተማ ናት

✍ሸዋ ደብረ ብርሃን በአሰራሩ ግሩም የሆነው የደብረ ብርሃን ስላሤ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝበት የታሪክ ምድርነው

✍ሸዋ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ወደኢትዮጵያ እንዲመጣ መንፈሳዊ ስራ የሰሩት የአጼ ዳዊት ምድር ነው
✍ሸዋ መስቀለ ክርስቶስን ወደኢትዮጵያ አምጥቶ በበግሸን መስቀለኛ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ያደረገ እና በርካታ የሃይማኖት የፍልስፍና የምርምር የታሪክ መጻሕፍትን የጻፈና ከሀድያንን ድል የነሳው የኢትዮጵያው ንጉሥ የአጼ ዘርዐ ያእቆብ የልደት ቦታ ነው
✍ሸዋ ቡልጋ በጸሎቱ ክንፍ ያወጣው ጻድቅ የአቡነ ተክለሃይማኖት መገኛ ምድር ነው
✍ሸዋ ቡልጋ በጸሎቷ በምናኔ ህይወቷ ልዩ የሆነችሁ እና ክንፍ ያወጣችሁ የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የትውልድ ቦታ ነው
✍ሸዋ ተአምረኛው መዘዞ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝበት ቦታ ነው
✍ሸዋ ድንቅ ድንቅ ተአምራት የሚከናወኑበት ጠገሮ እጨጌ ዮሐንስ ገዳም የሚገኝበት ቅዱስ ምድር ነው
✍ሸዋ የኢትዮጵያውያን የሕመም ችገር የሚፈታበት የታመሙት ሁሉ ተጠምቀው የሚድኑበት ሸንኮራ ዮሐንስ የሚገኝበት ቅዱስ ቦታ ነው
✍ሸዋ ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበት ሳማ ሰንበት ያለበት የተቀደሰ ስፍራ ነው
✍ሸዋ የፈላስፈው ባለ ቅኔ ሊቁ ኢያሱ መገናኛ ነው
✍ሸዋ የጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነው ነጩ ጣሊያንን ደባቅ መቶ የአፍሪካን ነጻነት የኢትዮጵያን ድል ያቀዳጀው ዳግማዊ ሚኒሊክ ምድር ነው
✍ሸዋ ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መነሻ የሆነ ባቡር መብራት መኪና ስልክ ወዘተርፈ ወደኢትዮጵያ ያመጠው የሚኒሊክ የትውልድ ቦታ ነው
✍ሸዋ ተአምር በማድረጓ በፈዋሽ ጸበሏ የምትታወቀው ጻድቃኔ ማርያም ገዳም የምትገኝበት ምድር ነው
✍ሸዋ የየኔታ ቤተ የአቋቋም ምስክር የነበረበት ኤልሻማ መድኃኔዓለም መገኛ ነው
✍ሸዋ የታላቁና ተአምር አድራጊው ዘብር ገብርኤል የሚገኝበት የተአምራት ቦታ ነው
✍ሸዋ ስዕለት ሰሚዋ ኩኬለሽ ማርያም ያለችበት ቦታ ነው
✍ሸዋ የቅዱሳን አጽም የማይፈርስበት የመልከ ጼዴቅ ገዳም የሚገኝበት ቅዱስ ምድር ነው
✍ሸዋ ቅዱስ ኡራኤል ደሙን የረጨበት ጽዋ የሚገኝበት እመጓ ኡራኤል ያለበት ድንቅ ምድር ነው
✍ሸዋ በዲንጋይ ላይ ዘንባባ የታተመባት ልዩና አስደናቂ የሆነችሁ ጅሩ ኣርሴማ ያለችበት ቅዱስ ምድር ነው
✍ሸዋ ልዩ ልዩ ገዳማትና አድባራት የድንጋይ ፍልፍል ቤተ መቅደሶችና የዋሻ ገዳማት የሚገኙበት አስገራሚ ቦታ ነው
✍ሸዋ ምንጃር ኤራቡርቲ 44 ታቦታት በአንድ ላይ የሚወርዱበት በታቦታት የተቀደሰ ምድር ነው
✍ሸዋ የተጉለቴ ዜማ መፍለቂያ ምድር ነው
✍ሸዋ የህይወት ምግብ የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማሳተም የትውልዱን ዓይነ ልቡና ያበሩ ተስፋ ገብረ ስላሤ የተወለዱበት ምድር ነው
✍ሸዋ የበርካታ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንት መፍለቂያ ምድር ነው
✍ሸዋ የታላቁ የደጉ አባት የብጹእ አቡነ ኤፍሬም የትውልድ ቦታ ነው
✍ሸዋ በሀገረ መንግስት ግንባታ
በኪነ ህንጻ
በገዳማት ኣድባራት ምስረታ
በስነ ጽሑፍ ስራዎች
ለኢትዮጵያ የታሪክ ሰንደቅ ነው
✍በዘመናችንም የስነ ጽሁፎ ሰዎች
ሀገር ወዳድ ሰዎች የጥበብ ሰዎች የአቋም ሰዎች የሚገኙበት ምድር ነው
ብቻ ሸዋ ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ የታሪክ ሰንደቅ ነው
የኢትዮጵያ ኣርማ ሸዋ ደብረ ብርሃን ነው

© መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

8  ስምንት ጠቃሚ ወርቃማ ሕጎች ለልጆች እንሆ1- ለልጅህ የሚጠይቀውን ሁሉ ከመስጠት ተቆጠብ።  የሚፈልገውን ሁሉ የማግኘት መብት እንዳለው አምኖ ያድጋልና።  2-ልጃችሁ የስድብ ቃላትን ሲናገ...
01/09/2023

8 ስምንት ጠቃሚ ወርቃማ ሕጎች ለልጆች እንሆ

1- ለልጅህ የሚጠይቀውን ሁሉ ከመስጠት ተቆጠብ። የሚፈልገውን ሁሉ የማግኘት መብት እንዳለው አምኖ ያድጋልና።

2-ልጃችሁ የስድብ ቃላትን ሲናገር ከመሳቅ ተቆጠቡ። ክብር ማጣት/ክብር አለመስጠት መዝናኛ እንደሆነ እያሰበ ያድጋል።

3- በመጥፎ ባህሪው ሳይነቀፍ ሊያሳየው ለሚችለው መጥፎ ባህሪ ቸልተኛ መሆንን ያስወግዱ። በህብረተሰብ ውስጥ ምንም አይነት ህግጋት እንደሌለ በማሰብ ያድጋል።

4- ልጅዎ የሚያበላሽቦትን ማንኛውንም ነገር ከማንሳት ይቆጠቡ። ለኃላፊነቱ ሌሎች ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው በማመን ያድጋል።

5- ማንኛውንም ፕሮግራም በቲቪ እንዲመለከት አትፍቀድ። በልጅነት እና በአዋቂነት መካከል ምንም ልዩነት እንደሌለ በማሰብ ያድጋል።

6- ለልጅዎ የጠየቀውን ገንዘብ ሁሉ ከመስጠት ይቆጠቡ። ገንዘብ ማግኘት ቀላል እንደሆነ በማሰብ ያድጋል እናም ለመስረቅ ወደ ኋላ አይልም።

7- ጎረቤቶቹን፣ መምህራኑን እና ፖሊሶችን ሲበድል ሁል ጊዜ እራስዎን ከጎኑ ከማድረግ ይቆጠቡ። የሚሠራው ሁሉ ትክክል ነው፣ የተሳሳቱት ሌሎች ናቸው ብሎ በማሰብ ያድጋልና።

8- ወደ ጸሎት ቤት ስትሄድ ብቻውን እቤት ውስጥ እንዳትተወው አለበለዚያ እግዚአብሔር እንደሌለ እያሰበ ያድጋል።

አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሣሥ 6 ቀን 1978 ዓ.ም የወጣአፄ ምኒልክን አንድ እንግሊዛዊ " ከጥቁርና ከነጭ ማን ይበልጣል ?" ሲል ይጠይቃቸዋል:: ምኒልክም " አስበህ እንደጠየቅከኝ አስቤ መልስ...
30/08/2023

አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሣሥ 6 ቀን 1978 ዓ.ም የወጣ

አፄ ምኒልክን አንድ እንግሊዛዊ " ከጥቁርና ከነጭ ማን ይበልጣል ?" ሲል ይጠይቃቸዋል:: ምኒልክም " አስበህ እንደጠየቅከኝ አስቤ መልስ እሰጥሃለው " ብለው በቀጠሮ ይለያያሉ፡፡ ከዛም ሊቃውንቶቻቸውን ሰብስበው ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ እንዲሰጡ ይጋብዟቸዋል፡፡ ለጊዜው ምንም መልስ አልተገኘም፡፡ በኃላ አለቃ ድንቄ የተባሉ ብልህና አዋቂ ሰው " አይቸገሩ ጃንሆይ ! መልሱን እኔ እሰጥዎታለሁ " አሏቸው፡፡ ምኒልክም በፅሞና ይጠብቋቸው ጀመር፡፡
አለቃ ድንቄም " ፈረንጁ ከጥቁርና ከነጭ ማን ይበልጣል አይደል ያለው ? ፍላጎቱ ይገባናል፡፡ እርስዎም በፈንታዎ " ከአይንህ ነጩ ነው ጥቁሩ የሚያይልህ ? " ብለው ይጠይቁት መልሱን ከዛ ያገኘዋል " አሏቸው፡፡ እውነትም ምኒልክ ለፈረንጁ ይህን ሲሉት በነገሩ ተደንቆ ዝም አለ፡፡

ምንጭ ፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሣሥ 6 ቀን 1978 ዓ.ም
_________________________
መልካም ቀን❤❤❤❤❤

“የሚፈርስ መዋቅርም ሆነ፥ የሚፈታ ትጥቅ የለንም" ብለዋል!” -የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን' አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለውበደቡብና ምዕራብ ትግራይ የነበሩ የአስተዳደር መዋቅሮች ይፈርሳ...
25/08/2023

“የሚፈርስ መዋቅርም ሆነ፥ የሚፈታ ትጥቅ የለንም" ብለዋል!” -የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን' አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው

በደቡብና ምዕራብ ትግራይ የነበሩ የአስተዳደር መዋቅሮች ይፈርሳሉ መባሉን ተከትሎ 'የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን' አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው የሚኒስቴሩ መልእክትን ለአንድ ክልል ወይም ለተወለዱበት አካባቢ ያጋደለ ብለውታል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ትላንት የአሸንዳ በዓልን አስመልክተው በይፋዊ የማሕበራዊ መገናኛ ገፃቸው ባሰራጩት መልእክት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ« በኃይል የተወሰዱ» ያሏቸውን አወዛጋቢ ግዛቶች "በሕገመንግስቱ መሰረት የሚመለሱበት ሁኔታ ለመፍጠር" እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

በመከላከያ ሚኒስቴሩ ዶክተር አብርሃም በላይ የትናንት መልእክት ዙርያ ለዶቼቬለ ምላሽ የሰጡት 'የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን' አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው የሚኒስቴሩ መልእክትን ለአንድ ክልል ወይም ለተወለዱበት አካባቢ ያጋደለ ብለውታል። አቶ አሸተ አክለውም "የሚፈርስ መዋቅርም ሆነ፥ የሚፈታ ትጥቅ የለንም" ብለዋል።

አማረ አባተ ቸኮል

"ተገፋሁ ተበደልኩ ብዬ ሀገሬን አልክድም።"አትሌት ጥላሁንእንኳን ደህና መጣህ!  የአትሌት ጥላሁን ኃይሌ የዉድድር ታሪክና  ውጤቶች 👏👌🏾 የሚከተሉት ናቸዉ። 📌በ 5000 ሜ ምርጥ ከሚባሉ ውጤ...
25/08/2023

"ተገፋሁ ተበደልኩ ብዬ ሀገሬን አልክድም።"አትሌት ጥላሁን

እንኳን ደህና መጣህ!

የአትሌት ጥላሁን ኃይሌ የዉድድር ታሪክና ውጤቶች 👏👌🏾 የሚከተሉት ናቸዉ።

📌በ 5000 ሜ ምርጥ ከሚባሉ ውጤቶቹ የሚከተሉት ናቸው::

👉🏾ዳይመንድ ሊግ (ኦስሎ, ኖርዌይ,Jun 2022) ወርቅ 🥇

👉🏾ዳይመንድ ሊግ (ሮም ጣልያን , Jun 2019) ወርቅ 🥇

👉🏾ግንቦት 2019 በብሔራዊ ውድድር (National Championship ) ወርቅ 🥇

👉🏾መስከረም 2019 አለም ሻምፒዮና ( World Championships) 4 ተኛ

👉🏾ሐምሌ 2018 ከ20 አመት በታች ወጣቶች (UG20 Championship) 5 ተኛ

N.B : ቀናቶቹ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነው::

Source : World Athletics

ስለ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል ምን ያህል ያውቃሉ ?የሻዳይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአማራ ክልል የሚከበር በዓል ነው።በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆ...
22/08/2023

ስለ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል ምን ያህል ያውቃሉ ?

የሻዳይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአማራ ክልል የሚከበር በዓል ነው።

በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆቦ አካባቢ ሶለል እና በላስታ እና በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አሸንድዬ በሚል የሚከበረ የልጅ አገረዶች ጨዋታ በዓል ነው።

በዓላቱ አማራ ክልል ባለብዙ ዘርፍ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብት ባለቤት መሆኑን ፣ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ባሕላዊ ትውፊቶች ያሉት፣ ሕዝቦች በመተሳሰብ በመፈቃቀር እና በአንድነት የሚኖሩበት መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።

የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል በዓል የአዲስ አመት መምጣቱን ተከትሎ የሚከበር ብስራት ነው።

ልጃገረዶች ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ውጣ ውረዶችን አልፈው ብሩህ ዘመን እየመጣ መሆኑን የሚያበስሩበት፣ እጮኛ የሚያጩበት፣ ከአቻዎቻቸው ጋር የሚጨፍሩበት እና የሚጫወቱበት ባሕላዊ ጨዋታ ነው።

በተጨማሪ እናቶች እና ህጻናት ያለ ልዩነት ሚሳተፉበትም ነው።

በዓላቱ በህዝባዊ አንድነት የሚያከብሩ፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር እና አብሮ የመኖር እሴትን ለትውልድ ማስተላለፊያ ጠንካራ ገመድ ናቸው።

ለውጭ ሀገራት ብርቅ በመሆኑም የገቢ ምንጭም ነው።

እነዚህ በዓላት በተለይም ባለፉት አመታት በአማራ ክልል በነበረው ጦርነት እና አለመረጋጋት እንዲሁም በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 ምክንያት በሚፈለገው ልክ በተሟላ ሁኔታ አልተከበሩም።

ዘንድሮም በዓሉ በተቃረበበት ወቅት በክልሉ ሰላም ደፍርሶ ፣ ንፁሃን ተገድለው፣ በርካቶች ተጎድተው አጠቃላይ ቀውስ በመፈጠሩ እንዲሁም ክልሉ ባአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመውደቁ ድባቡ እንደከዚህ ቀደሙ የደመቀ አይደለም።

በነዚህ በዓላት በተለይ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት በርካታ ቱርስቶች ወደ ክልሉ ይጎርፉ የነበረ ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት እንቅስቃሴ ሁሉ ተዳክሞ ነበር ፤ ከወራት በፊት በተገኘው አንፃራዊ ሰላም የቱሪስት እንቅስቃሴ ትንሽ የመነቃቃት ነገር ቢፈጠርም ዳግም በፀጥታ ችግር እና ጦርነት ወደ ክልሉ የሚደረግ የቱሪስት እንቅስቃሴ እጅግ ተዳክሟል።

ፎቶ ፦ ፋይል

"አጼ ምኒልክ ኦሮሞ የሚባል ስም አልወድድም እገላቸዋለሁ፣ ወላይታን አልወድድም እፈጃቸዋለሁ፣ አደሬን አልወድድም ብለው አንድን ሕዝብ መርጠው ጠላቴ ነው ብለው አያውቁም፣ አስበውም አያውቁም። ...
21/08/2023

"አጼ ምኒልክ ኦሮሞ የሚባል ስም አልወድድም እገላቸዋለሁ፣ ወላይታን አልወድድም እፈጃቸዋለሁ፣ አደሬን አልወድድም ብለው አንድን ሕዝብ መርጠው ጠላቴ ነው ብለው አያውቁም፣ አስበውም አያውቁም።

አገር እንዲሠለጥን ነው፣ ሕዝብ ሁሉ እንዲሠለጥን ነው የተቻላቸውን ሁሉ ያደረጉት። ለአንድ ሕዝብ የተለየ ጥላቻ ኖሯቸው ይኽንን ሕዝብ እንውጋው ብለው ይነጋገራሉ ብዬ መገመት እንኳን አልችልም፡፡ እሳቸው ለአገራቸው ሥልጣኔ ነው የለፉት ማንንም አይጠሉም ነበር ። ይኽን ሁሉ የሚያደርጉት ሌሎች ናቸው፡፡"

የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በአንድ ወቅት የተናገሩት

ኮለኔል መንግስቱ ሀይለማርያም በአንድ ወቅት በኬኒያ በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፖሊሶች እና ከባለስልጣናቱ ተደጋጋሚ ትንኮሳ ሲገጥማቸው ኬኒያ ድረስ በማቅናት "እኔን ጠልተው እንጂ ሀገራቸ...
19/08/2023

ኮለኔል መንግስቱ ሀይለማርያም በአንድ ወቅት በኬኒያ በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፖሊሶች እና ከባለስልጣናቱ ተደጋጋሚ ትንኮሳ ሲገጥማቸው ኬኒያ ድረስ በማቅናት "እኔን ጠልተው እንጂ ሀገራቸውን ጠልተው አይደለም እዚህ ያሉት! ሀገር አላቸው!" በማለት ማስጠንቀቅያ ሰጥቶ መመለሱ ይነገራል።.

ሁሌም የሚገርመኝ ነገር ነው።

በዓለ ደብረ ታቦር ሀዋሳ Beneberu
19/08/2023

በዓለ ደብረ ታቦር ሀዋሳ

Beneberu

Dirección

Madrid

Página web

Notificaciones

Sé el primero en enterarse y déjanos enviarle un correo electrónico cuando Debrebirhan Press publique noticias y promociones. Su dirección de correo electrónico no se utilizará para ningún otro fin, y puede darse de baja en cualquier momento.

Contato La Empresa

Enviar un mensaje a Debrebirhan Press:

Compartir


Otros Medio de comunicación/noticias en Madrid

Mostrar Todas