Breaking News In Ethiopia " ሰበር ዜና "

Breaking News In Ethiopia "  ሰበር ዜና " Human Rights, Freedom Of Expression & Rule Of Low ln Ethiopia. Big No For War, Enough With ETHNIC FEDERALISM! Ready To Deal ANY Difference's.......

የአዲስ አበባ ፖሊስ የደኅንነት ስጋት ትፈጥራላችኹ በሚል ጠርጥሬያቸዋለኹ ያላቸውን ነዋሪዎች በዘፈቀደ ካሠረ በኋላ በነፍስ ወከፍ 2 ሺሕ ብር እየተቀበለ እንደሚለቅ ታስረው ከተፈቱ ሰዎች ሰምተ...
05/02/2025

የአዲስ አበባ ፖሊስ የደኅንነት ስጋት ትፈጥራላችኹ በሚል ጠርጥሬያቸዋለኹ ያላቸውን ነዋሪዎች በዘፈቀደ ካሠረ በኋላ በነፍስ ወከፍ 2 ሺሕ ብር እየተቀበለ እንደሚለቅ ታስረው ከተፈቱ ሰዎች ሰምተናል። ባለፈው ቅዳሜ ገርጂ አካባቢ ከታሠሩ 50 ወጣቶች መካከል፣ ስድስቱ በነፍስ ወከፍ 2 ሺሕ ብር ከፍለው መለቀቃቸውንም ነግረዉናል። ገንዘቡን መክፈል አንችልም ያሉ ወጣቶች፣ ለአራት ቀናት ከታሠሩ በኋላ ፖሊስ ጣቢያውን የሚጎበኙ ዓቃቢያነ ሕግ እንደሚመጡ ሲታወቅ እንደተለቀቁ ተናግረዋል። ገንዘቡ የሚከፈለው በደረሰኝ ሳይኾን፣ ለተረኛ ፖሊሶች በጉቦ መልክ የሚከፈል ነው ተብሏል።

02/02/2025

ጎበዝ ፍቅር ሲዝምን ያሰረ መንግስት፣ ሰመረ ባሪያውን ቢያስር አይግረማችሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ የፈለከውን ባለስልጣን መዘርጠጥ ትችላለህ፣ ነገር ግን “ታላቁን ንጉስ አብይ አህመድን “ ከነካህ ወይም የምትነካ ከመሰለ ፣ በደቂቃ ውስጥ ዘብጥያ ትወርዳለህ። ይህ ያልተፃፈ ህግ የብልፅግና ደጋፊም ሆንክ አልሆንክ ሁሉም ላይ ተግባራዊ ይደረጋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈቀደው ብቸኛ የመናገር መብት አብይ አህመድን “ አታቱርክ” ወይም “ሃሳብ አፍላቂው መሪ “ እያሉ ማወደስ ብቻ ነው። በተለይ ዲያስፖራ ሆነህ ይህን ማድረክ ከቻልክ፣ የፈለከው ሁሉ ይደረግልሃል። ለራስህ ክብር መስጠትና ማፈግፈግ ስትጀምር ግን ወዲያውኑ ቀይ ካርድ ትከናንበህ ትባረራለህ። ዲያስፖራ ካልሆንክ ደግሞ እንደ ገጣሚ ምስራቅ ተፈራ ሸብ ትደረጋለህ።

ንጉሱ ውዳሴን እንጅ ትችትን የሚሸከሙበት ጫንቃ የላቸውም።

የተለየ ነገር አለባበሱ ነው። ከከበቡት ካዳሚዎቹ ለየት ብሎ መልበስን ስታየል አድርጎታል። ጥሩ መሪ መሆን ቢያቅተው የተለየ ለብሶ በመታየት ትኩረት ለመሳብ የሚያደርገው ትጋት ያስደምማል። ፕሮ...
02/02/2025

የተለየ ነገር አለባበሱ ነው። ከከበቡት ካዳሚዎቹ ለየት ብሎ መልበስን ስታየል አድርጎታል። ጥሩ መሪ መሆን ቢያቅተው የተለየ ለብሶ በመታየት ትኩረት ለመሳብ የሚያደርገው ትጋት ያስደምማል። ፕሮቶኮል አለመጠበቅ ከሌላው የተለየ ብቃት እንዲጎናጸፍ ያደረገው ይመስለዋል። ስለሚናገረው ነገር አይጨነቅም። ለራሱም ድምጹ አስጠልቶታል። የቃላት ጋጋታ፥ ኳኳታ፥ አርቲ ቡርቲ፥ የገዛ ንግግሩ ሰልችቶታል። ከፊቱ የተደረደሩት ግዑዛን ፈርዶባቸው፥ የቡዴና ነገር ሆኖባቸው የእጃቸው ግድግዳ እስኪላጥ ያጨበጭቡለታል። የሚለው ለራሱም አልጣመውም። እንደቢንቢ የሚጮሁ ቃላትን ሲያነበንብ ከአደራሹ ማዕዘናት ጋር እየተላተመ መልሶ ለራሱ ይሰማዋል። ከአምስት አመት በፊት ከተናገረው ምን ይለያል? ከካቻምናው? ከአምናው? አንድ ዓይነት። የቃላት ክምር። የቅጥፈት ቁልል። የውሸት ጋራ። የክህደት ጥግ። ፊቱ ቅጭም ሲል የገዛ ንግግሩ እንዳስጠላው ያስታውቅበታል። ጥንቆላ፥ ቅዠት፥ ባዶ ተስፋ፥ እጅ እጅ ይላል! ቋቅ!

31/01/2025

ሁሉም ቤት አንድ አስቸጋሪ ልጅ አለ። እናቱ ግን የምትወደው። ሴትም ወንድም።

ይህ ልጅ አስቸጋሪ ነው። ቤት ይበጠብጣል፣ ጎረቤት ይረብሻል፣ ከሰው ተጣልቶ ሁሌ ሰሞታ ይመጣበታል። አስቸጋሪ ባህሪ አለው።

ከፍ እያለ ሲሄድ ይጠጣል፣ ይሰክራል፣ ያመሻል፣ በአጥር ዘልሎ ይገባል። ብቻ አስቸጋሪ ነው። ቤተሰቡ የእርግማን መዓት ሲያወርዱበት እናቱ ግን ትወደዋለች። የጠቀመችው እየመሰላት የሚፈልገውን ተደብቃ ትሰጠዋለች። በባህሪው መክንያት በቤተሰቡ በመሰደቡና በመጠላቱ የተጎዳባት ይመስላታል። የብልግናና የማስቸገር ደረጃቸው ይለያይ እንጂ በየቤቱ እንዲህ ያለ ቢያንስ አንድ ልጅ አለ። እናቱ ግን የምትወደው።

እነዚህ እናቶች ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ላለው ምዕመን ይህንን ባህሪ ያወረሱት ይመስለኛል። እስኪ ዝም ብለህ እዚህ ሰፈር ሲሳደቡ እና የእርግማን መዓት ሲያወርዱ የሚውሉ ሰዎችን ተመልከታቸው። ምን ያክል ተከታይ እንዳላቸው ታዝበሃል። ቲክቶክማ የባሰ የባልቴት መንደር ነው።

ጌታው ''ኮሜንት'' ላይ ስም እንዳትጠራብኝ። ከመሃይም ጋር እንዳትጣላ፣ መንጋው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል'' የሚል ፅሁፍ አንብቤያለሁ። በማህበራዊ ሚዲያው ስንቱ መለኛ ሃሳብ በዚህ ምክንያት አፈር እንደበላ፣ ስንቱ ጀግና እንደተሰበረ እና ለሀገር የሚጠቅም ሰው ቅስሙ ተሰብሮ እንደተቀመጠ ቤት ይቁጠረው። የስድብ ቋቶቹ ግን በብዙው ዘንድ እየተወደዱ አሉ።

በተረት ላጠቃልልህ። ''ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ'' እንዲባል የማህበራዊ ሚዲያው ስልተቀመር (algorithm) አንተነትህን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የምትከተላቸው ሰዎችና የምታያቸው ኮንተንቶች የአንተ መለያ ናቸው።

የማህበራዊ ሚዲያው algorithm አንተን አጥንቶ እነደጨረሰህ ከልብህ ጣፍና ቀላል ምሳሌ ልስጥህ። ጠዋት ከእንቅልፍህ ተነስተህ ፌስ ቡክ ከፈትክ እንበል። የመጀመሪያ ገፅ ላይ የሚመጣልህን ነገር ተመልከት። ስድድብ ነው? ከሆነ ከነዚያ ባለጌዎች ጋር እየዋልክ ነው። የቴክኖሎጂ ጉዳይ ነው? ከሆነ ረጅሙን ጊዜህን ቴክኖሎጂ ላይ እያዋልክ ነው። ማህበራዊ ጉዳይ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ፋሽን.... ወዘተ ነው። ያ አንተ ነህ!!

እና ምን ልልህ መሰለህ ጌታው?
ልልህ የፈለኩት ገብቶሃል። ግን ባለጌንና መሃይምን አትከተል ለማለት ነው።

በመጨረሻም የማህበራዊ ሚዲያ algorithm በስድብ ከተካኑና ሰው ሲያኝኩ ከሚውሉ ሰዎች ጠብቆ ሃሳብ ካላቸው ሰዎች ሰፈር ያውልህ ብየ እመርቅሃለሁ።
ስላም ዋል!!

ኢህአዴግ የስልጣን ዘመኑ መገባደጃ ጊዜ ሲጨንቀው አዲሱ ገብረእግዚአብሔርን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሞ ነበር።  ኢህአዴግንኮ ክፉኛ የጠላነው በትውልዱ አስተሳሰብ ልክ አልራ...
31/01/2025

ኢህአዴግ የስልጣን ዘመኑ መገባደጃ ጊዜ ሲጨንቀው አዲሱ ገብረእግዚአብሔርን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ ሾሞ ነበር።

ኢህአዴግንኮ ክፉኛ የጠላነው በትውልዱ አስተሳሰብ ልክ አልራመድ ብሎ በሁሉም ነገር ኋላቀር መንግስት ሆኖብን ነው። በተለይ ሰብዓዊ መብት ረገጣ ላይ። እና ብልፅግና ከዚያ ከኋላቀር መንግስት በአቅም ማነስ ስሙ የሚነሳን ሰው ለሹመት የሚበደረው ምን ያክል ሰው ቢያጣ ነው? መቼም ተቋም ለማፍረስ ነው ብሎ ከማሰብ ሰው አጥቶ ነው ብሎ ማሰብ የተሻለ ነው።

በነገራችን ላይ በቅርቡ ተቋሙ ውስጥ ያሉ ፕሮፌሽናል ሰዎች ለቀቁ የሚሉ ዜናዎችን መሰማታችን የማይቀር ነው።

ቦንጋ ላይ የቦንጋ ህዝብ ብርሃኑን ትቶ አሸብርን ከመረጠ ኢማጅን ብሬ ምን አይነት ሰው እንደሆነ🤣

እና ምን ለማለት መሰለህ ጌታው?
ምንም አልልህም። ግን በሰብዓዊ መብት ጉዳይ እንደ ዶ/ር ዳንኤል በደልክን የሚናገርልህን ተቋም የቀብሩ አፋፍ ላይ ነውና ተሰናበተው እያልኩህ ነው።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ውስጥ ይፈጽመዋል ያለውን "የጅምላ" እና "የዘፈቀደ" እስር ለማስቆም ዓለማቀፍ ግፊት እንዲደረግ ጥሪ አድርጓል። በክልሉ ውስጥ አኹ...
29/01/2025

አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ውስጥ ይፈጽመዋል ያለውን "የጅምላ" እና "የዘፈቀደ" እስር ለማስቆም ዓለማቀፍ ግፊት እንዲደረግ ጥሪ አድርጓል። በክልሉ ውስጥ አኹንም የዘፈቀደ እስር ቀጥሏል ያለው ድርጅቱ፣ መንግሥት በዘፈቀደ ያሠራቸውን ዜጎች በሙሉ እንዲለቅ ወይም በይፋ ክስ እንዲመሠርት ጠይቋል። ድርጅቱ፣ የኢትዮጵያ ዓለማቀፍ አጋሮች እንዲሁም አሕጉራዊና ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በዘፈቀደ የታሠሩ ዜጎች እንዲፈቱ ተጽዕኗቸውን ተጠቅመው ግፊት እንዲያደረጉም ጥሪ አድርጓል።

በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ታጣቂዎች አንድ አንጃ የኾነው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት፣ ባለፈው ሳምንት አማራ ክልል ውስጥ ከዲፕሎማቶች ጋራ ተገናኝቶ መወያየቱን እስክንድር ለቪኦኤ የምሥ...
29/01/2025

በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ታጣቂዎች አንድ አንጃ የኾነው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት፣ ባለፈው ሳምንት አማራ ክልል ውስጥ ከዲፕሎማቶች ጋራ ተገናኝቶ መወያየቱን እስክንድር ለቪኦኤ የምሥራቅ አፍሪካ ክፍል ተናግረዋል። የቡድኑ ተወካዮች የተነጋገሩት፣ ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከኢጋድ፣ ከአውሮፓ ኅብረትና በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኢምባሲ ተወካዮች ጋር እንደኾነ እስክንድር መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በቴክኒካል ቡድኖች ደረጃ የተካሄደው ንግግር ያተኮረው በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ቡድኑ ያለውን አቋም ለመግለጽ እንደነበር የገለጡት እስክንድር፣ ከመንግሥት ጋር ድርድር የማድረግ ጉዳይ ግን እንዳልተነሳ ተናግረዋል ተብሏል።

የቻይናው ዲፕሲክ የሳይበር ጥቃት ደረሰበትበተለቀቀ በቀናት ውስጥ በዓለም ላይ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው የቻይናው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አጋዥ መተግበሪያ (DeepSeek) የሳይበር ጥቃት እ...
29/01/2025

የቻይናው ዲፕሲክ የሳይበር ጥቃት ደረሰበት

በተለቀቀ በቀናት ውስጥ በዓለም ላይ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው የቻይናው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አጋዥ መተግበሪያ (DeepSeek) የሳይበር ጥቃት እንደደረሰበት ተዘግቧል፡፡

ዲፕሲክ የአሜሪካውን ቻትጂፒት (ChatGPT) የሚፎካከር እና ተፈላጊነቱም እያደገ መሆኑ በተዘገበ በቀናት ውስጥ ነው ከፍተኛ የተባለ የሳይበር ጥቃት የደረሰበት፡፡

ይህን ተከትሎም ዲፕሲክ በጊዜያዊነት አዳዲስ ተጠቃሚዎችን መቀበል ከማቆሙ በስተቀር ሌሎች ተጠቃሚዎች መጠቀማቸውን እንደማያስተጏጉል አስታውቋል፡፡

በአሜሪካ አፕ ስቶር እና ጎግል ስቶር ላይ በነጻ ከሚገኙ መተግበሪያዎች ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘ ሆኗል፡፡

ይህን ተፈላጊነቱን ተከትሎም ሀገራት መተግበሪያውን መጠቀም አለመጠቀም ላይ የተለያዩ ምክረሃሳቦችን እየሰጡ ነው፡፡

በዚህ ወቅት ዲፕሲክ የደረሰበት የሳይበር ጥቃት ከማን እንደሆነ በግልፅ ባይታወቅም ከተፎካካሪዎቹ ሊሆን እንደሚችል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡

28/01/2025

አሁንም እናገራለሁ። ለመቶ ሺህ ብር ብላችሁ ራሳችሁንና የንግድ ሃሳባችሁን አደባባይ ላይ አታውጡ። ሃሳብ ያለው ሰው ጥቂት ጥረት ከታከለበት መቼም ቢሆን ይሳካለታል። ከጊዜ ጋር ጥድፊያ ትርፉ መጋጋጥ ነው። ልትሰሩ ያሰባችሁትን ማሰብ የማይችል ሰው ገበያው ላይ እንዳይበዛ ተጠንቀቁ። መቶ ሺህ ብር ይዞ ሃሳብ ያጣ ጅ ብ የናንተን ስራ የራሱ ለማድረግ አሰፍስፎ እንደሚጠብቅ ተረዱ።

ማንም ቢወስደው የማያሳስብ የቢዝነስ ሃሳብ ያላችሁ ሰዎች መቶ ሺህ ብር ለናንተ ብዙ ስለሆነ እንደፈለጋችሁ ሁኑ። ብሩን ይዛችሁ ዞር ስለምትሉ ይመቻችሁ።

በሚሊየን የሚሻጥ የቢዝነስ ሃሳብ ይዛችሁ መቶ ሺህ ብር ያጣችሁ ሰዎች ሃሳባችሁን አታባክኑ። በርግጥ ጥቂቶች በመቶ ሺህ ብር እርሾነት የሆነ መስመር የያዙ ሊመስላችሁ ይችላል። ጥያቄው ግን እውነት እነዚህ ሰዎች መቶ ሺ ብር አጥተው ነበር እስከዛሬ መስመር ያልያዙት የሚለው ነው። አይመስለኝም። ብዙ መቶ ሺህ ብሮችን ያባከኑበት እድላቸውን የሚረግሙ የኪሳራ ተማሪዎች ናቸው።

ያ ሸላሚ ነኝ ብሎ በሶሻል ሚዲያው ያገነናችሁትም ሰው ቢሆን እንደናንተው ገንዘብ ፈላጊ ነው። ልዩነቱ እሱ እናንተን ተጠቅሞ ገንዘብ ያገኛል፣ እናንተ እኛን ተጠቅማችሁ የገንዘብ ድርጎ ለማግኘት ትፍጨረጨራላችሁ።

ይቅናችሁ 👍

27/01/2025

ቱርኮች “ምታው ብዬ ብልከው ገደለው” የሚል ተረት አላቸው። አይ ኤም ኤፍ እንኳን ፣አብይን ህዝቡን በኑሮ ውድነት ምታው እንጂ፣ ግደለው ብዬ አላኩትም አለ አሉ።

አቡጡ ፀረ ህዝብ ነው። ህዝብን ( የትግራይ ይሁን የአማራ፣ የኦሮሞ ይሁን የወላይታ) እወክላለሁ የሚል ሁሉ ከአብይ ጋር ተነጋግሬ፣ ተደራድሬ መሥራት እችላለሁ ብሎ ያሰበ ቀን፣ ወከልኩት የሚለው ህዝብ ላይ ሞት ፈርዷል።

ፀረ-ህዝብን አትደራደረውም!!

መነኸሪያ ሬዲዮ ይቅርታ ጠየቀ፣ ፕሮግራሙ ታግዷል።ቲክቶከር ሮማን በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በተባባሪ አዘጋጆች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች መካከል አንዱ በሆነው  የብርሐን መንገድ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ...
25/01/2025

መነኸሪያ ሬዲዮ ይቅርታ ጠየቀ፣ ፕሮግራሙ ታግዷል።

ቲክቶከር ሮማን በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በተባባሪ አዘጋጆች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች መካከል አንዱ በሆነው የብርሐን መንገድ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ መቅረቧ ይታውቃል፡፡

የቀረበችው “ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ማዋል” በሚል ከዚህ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፈችውን የተዛቡ አመለካከቶችን በተመለከተ ይቅርታ ለመጠየቅ እና ከስህተቷ ሌሎች ትምህርት እንዲወስዱ ነው፡፡

በመሆኑም በርካታ አድማጮቻችን በግለሰቧ መቅረብ መከፋታቸውን ነግረውናል፡፡ ለተፈጠረው ጉዳይ ጣቢያችን ይቅርታ እየጠየቀ ላልተወሰነ ጊዜ በተባበሪ አዘጋጆች የሚቀረበው የብርሐን መንገድ የተሰኘ ፕሮግራም የታገደ መሆኑን እናሳወቃለን፡፡

በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት ወቅት የፕሮግራሙ አዘጋጆች በቀጥታ ስልክ መስመር የገባ አድማጭን ያቋረጡበት መንገድ ከሙያ ስነምግባር ያፈነገጠ በመሆኑ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

25/01/2025

ከቻልክ ወርቅ ሁን፣ ካልቻልክ ዶላር። በፍፁም ግን ብር እንዳትሆን!!

ምን መሰለህ ጌታው!?
ብር ሀገር ውስጥ ነው የሚሰራው። ሚሊሻ በለው። የኢትዮጵያን ድንበር አልፈህ ስትወጣ 100 ብር እና 5 ብር እኩል ወረቀት ናቸው። ተራ ባለ አራት መዓዘን ወረቀቶች። ለየኔ ቢጤ ልስጠው ብትል ራሱ ''ቂጥክን ጥረግበት'' ነው የሚልህ። አስተሳሰብህም በዚህ ልክ መቃኘት አለበት። እንደ ብር ሰፈር ለሰፈር የምታስብ ከሆነ ወጣ ስትል ቀፎ ነህ። ማንም የማይፈልግህ ሰው ትሆናለህ። ሰፈርህ ከመፎከር ውጪ ዋጋ አይኖርህም። ሰሚም የለህም።

"ዶላር ሁን" ስልህ ደግሞ በዓለም ላይ ከሌሎች የተለየ ዋጋ ይኑርህ እያልኩህ ነው። ወረቀቱ ላይ ቁጥር ቢሆንም የተፃፈው ቅሉ የተፃፈው ቁጥር ግን ዋጋ አለው። የትም ሀገር ይገዛል፣ ይለውጣል። አንተም ስታስብ ድንበር ተሻጋሪ ሁን። ድንበር ተሻግረህ ከማን ጋር መወዳደር፣ ከማን ጋር መተባበር፣ ከማን ጋር መነገድ ወዘተ እንዳለብህ ለይ። የዶላር ችግሩ ግን ባለቤቱ በፈለገው ጊዜ ሊያትመውና ሊያረክሰው መቻሉ ነው። ቢሆንም ግን ዋጋህ አለማቀፋዊ ነው። ውሃና እሳት ሲያገኘው ግን ድራሹ እንደሚጠፋ አትርሳ።

''ወርቅ ሁን'' ስልህስ? በቃ ወርቅ ነዋ!! በቁጥር ሳይሆን በሚዛን የሚለካ፣ በእሳት የተፈተነ። የትም ዋጋው ውድ የሆነ!!

ወ...ር....ቅ...

ይህ ተስፋ የቆረጠ አውሬ በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን እጅግ ዘግናኝ ግፍ አንብቡ። ይህ የኢትዮጵያ ወታደር አይደለም፥ የባዕድ አገር ወታደር ቢመጣም ንፁሃንን እንደነዚህ አውሬዎች የሚገድል...
24/01/2025

ይህ ተስፋ የቆረጠ አውሬ በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን እጅግ ዘግናኝ ግፍ አንብቡ። ይህ የኢትዮጵያ ወታደር አይደለም፥ የባዕድ አገር ወታደር ቢመጣም ንፁሃንን እንደነዚህ አውሬዎች የሚገድል አይመስለኝም።

ፋኖ ይህን አውሬ ሰራዊት ለመበታተንና ኢትዮጵያ ከእንግዲህ እንዲህ አይነት ወታደር እንዳይኖራት ለማድረግ፣ ከየትኛውም ሃይል ጋር ታክቲካል ትብብር ፈጥሮና በፍጥነት አንድ ሆኖ መዋጋት አለበት።

“ እናቱ መሞት ብቻ ነው የቀራት። ሐዘኑ በጣም አማሯታል። 'የት አባቴ ልድረስ?' እያለች ነው። አንድ ፍሬ ወንድ ልጅ ያለው እሱ ብቻ ነበር። ሥራም የሚያግዘኝ እሱ ብቻ ነው። አንድ ልጄን አጣሁ። ከዚህ በኋላ ምን አለኝ? ብቻዬን ነው የቀረሁ። አጋዤን እንደዚህ አድርገውት ሄዱ" ሲሉ የቤተሰባቸውን ሐዘን ገልፀዋል።”

አንድ ወታደር መግደል ደከመኝ ስላለ ሊሞገስ ይገባል? ወታደራዊ አመራሩ እስካሁን ገድሎ ገድሎ ሁኔታው እንደማያስክሄደው ሲያውቅ ጠ/ሚኒስቴሩ ነው ያዘዘኝ ብሎ እጁን ታጥቦ ጀግና ሊባል ነው? አ...
24/01/2025

አንድ ወታደር መግደል ደከመኝ ስላለ ሊሞገስ ይገባል? ወታደራዊ አመራሩ እስካሁን ገድሎ ገድሎ ሁኔታው እንደማያስክሄደው ሲያውቅ ጠ/ሚኒስቴሩ ነው ያዘዘኝ ብሎ እጁን ታጥቦ ጀግና ሊባል ነው? አሁንም ከመንጋነት አልተማርንም?

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ባለፋት 5ዓመታት በሁሉም ክልሎች ለተገደሉት በሚሊዬኖች ለሚቆጠሩ ንፁሃን ሃላፊነት መውሰድ ተጠያቂነት ማስፈን የግድ የግድ ነው። ሀገር ያፈረሰው አንዱ እና ዋነኛው መንስዔ ሁሉንም ጥፋቶች ለእከሌ ሰጥተው እጅ መታጠቡ እና በመንጋም እውቅናም መሰጠቱ ነው።
~ ያኔ ገዳይ እና አስገዳይ እጁን በሌላው ላይ ታጥቦ ጀግና ይሆናል። ጀግና ሆኖም ለሌላ ግድያ ዙር መንበሩን ያደላድላል። ትናንት የኦሮሞ ልጆችን ይገድል የነበረው: "ግደል ተብዬ ነው: ተላላኪ ነበርኩ" ብሎ እጁን ታጥቦ ጀግኖ.... መግደሉን የቀጠለው ነው። ትናንት የአማራ ልጆችን ይገድል የነበረው: "ግደል ተብዬ ነው: ተላላኪ ነበርኩ" ብሎ እጁን ታጥቦ ጀግና ተብሎ...መግደል የቀጠለው ነው።

~ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ከቀጠለች: የምትቀጥለው ፍትህ ሲሰፍን ብቻ ነው። ተመሳሳይ አዙሪት የሚሰራ ከመሰለህ ተሳስተሃል። ተጠያቂነትን የማያሰፍን አካሄድ አንድ እርምጃ ወደፊት አያራምድም።

♦ እኛም ሃገር ተግባራዊ ቢደረግ 👌ትራምፕ በፊርማቸው እንዲቀር ካገዱት ወይም ካቋረጡት የፌደራል ፕሮግራም አንዱ DEI( Diversity, Equity, and Inclusion) ነዉ ይሄ ማለት ...
23/01/2025

♦ እኛም ሃገር ተግባራዊ ቢደረግ 👌

ትራምፕ በፊርማቸው እንዲቀር ካገዱት ወይም ካቋረጡት የፌደራል ፕሮግራም አንዱ DEI( Diversity, Equity, and Inclusion) ነዉ ይሄ ማለት በእኛ አገር "አካታችነት ወይም የብሄር ተዋፅኦ"በሚል ሰዎች የሆነ ብሄር አባል ወይም ቋንቋ ተናጋሪ ስለሆኑ ብቻ ችሎታና እዉቀት ሳይኖራቸዉ የሚሾሙበት ኋላ ቀር እሳቤ ነዉ።

እኔም በግል ይሄ አይነት አስተሳሰብ እኛ አገር ዉስጥ ሊቀር ይገባል ብቻ ሳይሆን በህግ ተከልክሎ ማየት የምፈልገዉ ጉዳይ ነዉ ። ሰዎች በችሎታቸዉና በእዉቀታቸዉ ብቻ ሊመዘኑ ይገባል እንጂ አካታችነት በሚል ብሄራቸዉ ወይም የተገኙበት ማህበረሰብ መሥፈርት ዉስጥ ሊገባ አይገባም ባይ ነኝ።

ይኼ አይነቱ አሰራር ወደ እኛ አገር መጥቶ ቢተገበር በመንደርና በወንዜ ልጅ ብሎም በብሄርና በቋንቋ ተቧድኖ ተገልጋይን ሲያማርር እና ያልተገባ ጥቅም ለማገኘት ሰራ የሚያጓትተዉን ከመንግስት መዋቅር ጠርጎ በማስወጣት የተገልጋይን እርካታ መጨመር በሎም የአገርን ሀብትና ንብረት ከብክነት መታደግ ይቻላል ።

ሆኖም ግን ፤ ......
" አይደለም ሠራተኛው ፤ የመንግስት አወቃቀሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ነው " 🤔🤔

22/01/2025

የሀገሪቷ ዕዳ 68. 9 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተረጋግጧል።

በዚህ መሰረት ለእያንዳንዱ ዜጋ 5, 300 Us Dollar (ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ) ዕዳ ይደርሰዋል ማለት
ነዉ።

6, 89 ,00, 00 ,00 ,000 $ ÷ 130 Million = ??

እሺ እነ No More ምን አሰባችሁ ታዲያ 😉??

ስለ ገዱ አንዳርጋቸው ተጨማሪ *************************ከትራምፕ በዓለ ሲመት ጋር ተያይዞ፣ ገዱ አንዳርጋቸው የተገኙበት ብዙ ጉባኤያት ላይ ነበር፡፡ Latino Inaugural ...
21/01/2025

ስለ ገዱ አንዳርጋቸው ተጨማሪ
*************************
ከትራምፕ በዓለ ሲመት ጋር ተያይዞ፣ ገዱ አንዳርጋቸው የተገኙበት ብዙ ጉባኤያት ላይ ነበር፡፡ Latino Inaugural Ball እና Black Caucus Freedom Ball እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

Latino Inaugural Ball ላይ የተገኙት አብዛኞቹ የላቲን የትራምፕ ድጋፍ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ለአሜሪካ አይመቹም የተባሉት የላቲን ሀገራት የወደፊት መሪዎችም እንደሚሆኑም የሚጠበቁ ሰዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ ቬንዝዌላን መውሰድ ይቻላል፡፡አንዱ ንግግር ያደረጉት ሰው የወደፊቱ የቬንዝዌላ መሪ እንደሚሆኑ እምነት የተጣለባቸው ናቸው፡፡ፎቶአቸውን ከስር አያይዤዋለሁ፡፡ ገዱስ ለምን ተጋበዙ? ከዚህ ምን እንዲማሩ ነው? እንደኔ መልክቱ ግልጽ ነው!

የገዱ አንዳርጋቸው ብዙም ያልተነገረለት ግን የተገኙበት የትራምፕ ሲመት አካል የሆነው ሌላው ጉባኤ የጥቁር አሜሪካውያን ሪፐብሊካን ጉባኤ ላይ ነው፡፡ Black Caucus Freedom Ball እዚህ ላይ ደግሞ ገዱን ከበርካታ ጥቁር የአሜሪካ ሪፐብሊካን የወደፊት ባለስልጣናት ጋር ትውውቅ እንዲያደርጉ የተፈለገ ይመስላል፡፡

በነገራችን ላይ ፣ ትራምፕ ስቴት ዴፓርትመንት የሚሰሩትን ዲፕሎማቶች በሙሉ በሚባል ሁኔታ ከትናት ሰኞ ጀምሮ ስራ እንዲያቆሙ አዘዋል፡፡ ስቴት ዴፓርትመንት ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ተበትኖ፣ በምትካቸውም አዳዲስ ሰዎች እየተሶሙ ነው፡፡ ( መረጃውን ኮሜንት ላይ ያገኙታል) ከተሿሚዎቹ ውስጥም እነዚህ ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች እንደሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ ስማቸው በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ገዱ ለምን ይሄን ሁሉ ጉባኤ እና ሲመት እንዲካፈሉ ተፈለገ? እውነት ባጋጣሚ? ያለምንም ዓላማ ያንን ሁሉ ሴኪውሪቲ ክሊራንስ አልፈው ?

ገዱ አንዳርጋቸው ፣ ገራገር ቢመስሉም ፣ በአንጻሩ አደገኛ የሴራ ሰው እንደሆኑም ይነገራል፡፡ አማራ ክልል ውስጥ ያለውን የብልጽግና መዋቅር የሰሩት እሳቸው ከመሆናቸው አኳያ ፣ ያንን መዋቅርም ለማፍረስ ከሳቸው የተሻለ ሰው የለም የሚል እሳቤ እንዳለ ይገመታል፡፡ ገዱ፣ ከልማት ጣብያ ሰራተኛ ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ የተዘረጋውን መዋቅር በጃቸው እንደሆነ ይነገራል፡፡

በፌደራል በኩልም፣ ሚኒስትር ከመሆናቸው አኳያ በርካታ ሚስጥሮችን የሚያውቁና እዛም ውስጥ እስካሁን ሴል እንዳላቸው ፣ በሴራ ፖለቲካም ህወሀትን ለማውረድ ከ ኦህዴድ ጋር ተጣምረው ሲሰሩ የዘረጉት አደገኛ መዋቅር እንዳላቸው በሰፊው ይታማሉ፡፡የሰለላ ድርጅቱም ባያውቃቸው ነበር ሚገርመው፡፡ ሰውየው ገራገር ቢመስሉም፣ ከባድ እና ውስብስብ ሰው እንደሆኑ የሚያውቋቸውና አብረዋቸው የሰሩ ሰዎች ይናገራሉ፡፡

ስገምት፣ አሜሪካም ይሄ መረጃው ያላት ይመስላል፡፡ ያለ ምክንያት ገዱን ብቅ እንዲሉ አላደረገችም ብዬ በገመት ለውነት የራቅሁ አይመስለኝም፡፡

እንደ ብዙ ገማቾች ከሆነ፣ ገዱን groom እያረጓቸው እንደሆነ ይታሰባል፡፡

በነገራችን ላይ ፣ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ከተካሄደ በኋላ ፣ የትራምፕ ስብሰባ ሴኩሪቲው እጅግ ጠንካራ ነው፡፡ የተሳታፊዎች ስም አስቀድሞ ተልኮ፣ የጀርባ ጥንት ተደርጎ ፣ የደህንነት መስሪያ ቤቱ የፈቀደላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው የሚሳተፉት ፣ የተሳተፉትም፡፡ እና ገዱም ባጋጣሚ እዚህ ሁሉ ስብሰባ ላይ የሴኩሪቲ ክሊራንስ አግኝተው ተሳተፉ ማለት የማይታመን ነገር ነው፡፡ አሜሪካ ምንግዜም አሸናፊውን ኃይል ቀድማ ለይታ ነው የሆነ ነገር ምትጀምረው፡፡ ሳስበው something is brewing ያላንዳች የፖለቲካ ትርፍ ገዱን እዚህ ሁሉ እንዲገኙ ተደረጉ ማለት ለኔ ቀልድ ነው፡፡

ፎቶዎች፤ የቬኒዝዌላ ይወደፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብለው እምነት የተጣለባቸው ሰው ንግግር ሲያደርጉ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ ገዱ ላቲኖ ኢናጉሬሽን ቦል ላይ የተነሱት ፎቶ ነው፡፡ ሌላው የጥሪ ካርዳቸው ነው፡፡

19/01/2025

♦እጅግ ልብ ይሰብራል💔💔

ይህ የሆነው በሀገራችን ነው። በወላጆቹ ፊት ልጅ በጥይት ተመቶ ሲ*ገደል 😭😭

በወላጆቹ ፊት የፊጥኝ አስረው አስቀምጠው በጭካኔ መግደላቸው አልበቃ ብሎ ፣ ቪዲዮን ቀርጸው ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉም እንዲያየው አድርገዋል ። ይህ ደግሞ ማን ምን ያመጣል "የምን ታመጣላችሁ" አደገኛ እብሪት መሆኑ ነው ።

በእርግጥ ለባለፉት 6 እና 7 ዓመታት እንደ ሃገር ከባድ ቀውስ ውስጥ ገብተናል ፤ በቪዲዮ እና በፎቶ ተቀርጾ ያየናቸው ዘግናኝ ጉዳያዎች እንዳሉ ሆኖ ፣ በአደባባይ በይፋ ያልታዩ እና ያልተነገረላቸው የሰው ልጅ የስቃይ ሞት ቁጥሩ ቀላል አይደለም ። መንግስታዊ ሽብር አይነት እና መጠኑ እየጨመረ ነው የመጣው።

Adresse

Schweinfurt
97424

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Breaking News In Ethiopia " ሰበር ዜና " erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an Breaking News In Ethiopia " ሰበር ዜና " senden:

Videos

Teilen