Kiyas official

Follow me
03/05/2024

Follow me

27/04/2024
🛑  የአውስትራሊያው ታዋቂ የአሦሪያ ጳጳስ የግድያ ሙከራ፣ መ*ና*ፍ*ቁ ንስጥሮስ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች (እንደወረደ)(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)ሀ/ መነሻ   | የሰኞ የብዙዎች መነጋገሪያ ርዕ...
16/04/2024

🛑 የአውስትራሊያው ታዋቂ የአሦሪያ ጳጳስ የግድያ ሙከራ፣ መ*ና*ፍ*ቁ ንስጥሮስ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች (እንደወረደ)

(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)

ሀ/ መነሻ
| የሰኞ የብዙዎች መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ የነበረው በአውስትራሊያ የሚገኙ የአሲሪያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ላይ በቤተ መቅደሳቸው እንዳሉ የተፈጸመባቸው የመግደል ሙከራ ነው። ጳጳሱ በቀጥታ ሥርጭት በሚተላለፈውና በመላው ዓለም ያሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾቻቸው በሚከታተሉት ዝግጅት ላይ ነው በስለት የመግደል ሙከራ የተደረገባቸው። አንድ በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሰው ጳጳሱን በስለት ደጋግሞ ሲወጋቸው በቪዲዮው ይታያል። ከእርሳቸውም በተጨማሪ በቤተ መቅደሱ የነበሩ ሌሎች ሰዎች አደጋ ደርሶባቸዋል::

እኒህጳጳስ በፌብርዋሪ ወር 2024ም ተመሳሳይ በስለት የመግደል መኩራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል፡፡ በፊብሩዋሪ ወንጀሉን የፈጸመው የ 15 ዓመት ወጣት እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።

ዛሬ የተፈጸመባቸው የመግደል ሙከራ በጣም አሳዝኖኛል፣ አስደንግጦኛልም:: በርግጥ ወንጀሉን የፈጸመው ሰው ማንነት ግልጽ ባይሆንልኝም ከሊበራሉ ዓለም እስከ አክራሪ ጽንፈኞች ድረስ ጥቃት ሊያደርሱባቸው የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ መገመት ይቻላል። በትምህርታቸው ጠንካራነት ምክንያት።

በቅርቡ እንኳን እሥራኤል በጋዛ ፍልስጥኤማውያን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት የተቃወሙበትን ንግግር ተመልክተናል። ይህንን ጽሑፍ እስከጻፍኩበት ሰዓት ድረስ የአውስትራሊያ ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸመውን ሰው ማንነት እና ወንጀሉን ለመፈጸም የገፋፋውን ምክንያት አልገለጸም።

ለሁሉም ግን እንኳን እግዚአብሔር አተረፋቸው፡፡ አሁንም ቶሎ አገግመው ወደር ወደሚወዱት አገልግሎት እንዲመለሱ ምኞቴ ነው።
++++

ለ/ ጳጳሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል (Bishop Mar Mari Emmanuel) ማን ናቸው?
----------
ማር ማሪ ኢማኑኤል በአውስትራሊያ የሚገኘው የ"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን (Christ The Good Shepherd Church) በተባለ ሥፍራ ያገለግላሉ። በ2009 (እ.አ.አ) ቅስናን፣ በ2011 ደግሞ ጵጵስና መቀበላቸውን ታሪካቸው ያሳያል።

ጳጳሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል በስብከቶቻቸው የሚያነሧቸው ጉዳዮች በብዙ ሰው ዓይን ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸው ይመስላል። በዘመነ ኮሺድ በመላው ዓለም የተጣለውን ከቤት ያለመውጣት እግድ በጽኑዕ በመቃወማቸው ይታወቃሉ። ከዚያም ቀጥሎ በአሜሪካ እና በሩሲያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸው ሐሳቦች በተለይም በሊበራሉ ዓለም "አክራሪ" አሰኝቷል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን "የተመረጡት በሕቡዕ ቡድኖች ይሁንታ ነው" ማለታቸው እንዲሁም "ግ*ብ*ረ ሰ*ዶ*ማ*ዊነት"ን በጽኑዕ መቃወማቸው ጠላት ያፈራባቸው ይመስላል።

ታዋቂነታቸው ከእንግሊዝኛ ተናጋሪው አልፎ ወደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድም ደርሷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ጳጳሱ ያወቅኹት ስለ ቤተ ክርስቲያኒን ጠንካራ ትችት ያቀረቡበትን እና ቤተ ክርስቲያን "ንስሐ ግቢ" የሚል መንፈስ ያለው አጭር ቪዲዮ አይቼ ነው። "እንዴ!!! ቤተ ክርስቲያን ኃጢአት የማይስማማት የክርስቶስ አካሉ መሆኗን የደፈጠጠ የምዕራቡ ዓለም ፕሮ*ቴስ*ታን*ቲዝም ትምህርት የሚናገር ጳጳስ ከየት ተገኘ?" ብዬ ተገርሜ ነበር። የግብጽ/ቅብጥ ጳጳስ መስለውኝም ነበር። ኋላ ነው የአሦር ኦርቶዶክስ ጳጳስ መሆናቸውን የተረዳኹት። ብዙ ኦርቶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ስብከቶቻቸውን ሼር ሲያደርጉ "የተዋሕዶ ጳጳስ መስለዋቸው ይሆን?" እል ነበር።
+++++

ሐ/ ስለ ምሥራቅ አሦሪያ ቤተ ክርስቲያን በመጠኑ
-----

16/04/2024

#ኦርቶዶክሳዊ

16/04/2024

#ኦርቶዶክሳዊ

Adresse

Elz

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Kiyas official erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an Kiyas official senden:

Videos

Teilen

Kategorie