ባለውለታዎቹ የላዳ ታክሲዎች
ረዥም ዕድሜ ያስቆጠሩ የላዳ ታክሲዎች እርጅና ቢያጠቃቸውም አሁንም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ጋራዥ መመላለሱና የመለዋወጫ ዕቃ አለመገኘቱ ሥራዎቻቸው ቢፈትናቸውም አሁንም የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት አገልግሎት ከሚሰጡት አሽከርካሪ ጋር ቆይታ ያደረገው ባልደረባችን ስዩም ጌቱ ያጠናቀረው የቪድዮ ዘገባ እንድትመለከቱት በአክብሮት እንጋብዛለን። ስለላዳ ታክሲዎች ያላችሁ ገጠመኝ በአስተያየት መስጫው ጻፉልን።
በሎስ አንጀለስ የእሳት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 10 ደረሰ
የሆሊዉድ ኮረብታዎች በእሳት ጋይተዋል
ቃጠሎዉ በአብዛኛዉ ሞጃዎቹ አልያም ቅንጡዎቹ ላይ ጉዳት ማድረሱ እየተነገረ ነዉ።
በሎስ አንጀለስ በተከሰተው ሰደድ እሳት ሳቢያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 10 መድረሱ ተገለፀ። በሎስ አንጀለስ አካባቢ ከ10,000 በላይ ህንፃዎች፣ አብዛኞቹ ቤቶች፣ በእሳት ቃጠሎዉ መዉደማቸዉን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። በፓስፊክ ፓሊሳደስ ተራራማ አካባቢ ከ5,300 የሚበልጡ ሕንጻዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ አልያም ወድመዋል። በሎስ አንጀለስ ለቀናቶች በዘለቀዉ ሰደድ እሳት በከተማዋ ታሪክ እጅግ አውዳሚ እና የከፋ መሆኑን ባለስልጣናት በሚሰጡት መግለጫ እየገለፁ ነዉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሎስ አንጀለስ የተከሰተዉን ሰደድ እሳት ለመዋጋት ምክር ቤቱን እርዳታ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። በከተማዋ የሚገኘዉ የሆሊዉድ ታዋቂ የፊልም ማዕከል አንዳንድ ክፍሎች በሰደድ እሳቱ ስጋት ዉስጥ ወድቀዋል። በእሳቱ ቤታቸዉን ለቀዉ ለመዉጣት ከተገደዱት በአስር ሽዎች ከሚቆጠሩት ነዋሪዎች መካከል፤ የአሜሪካ ታዋቂ ሙዚቀኞች የፊልም አክተሮች እንዲሁም የአገሪቱ ታዋቂ ቱጃሮች ይገኙበታል። ቃጠሎዉ በአብዛኛዉ ሞጃዎቹ አልያም ቅንጡዎቹ ላይ ጉዳት ማድረሱ እየተነገረ ነዉ።
የቪዛ ገደብ ማንሳት ለአፍሪቃ አንድነት ይጥቅማል?
ጋና አፍሪቃዉያን በሙሉ ያለ ቪዛ ሐገሯ እንዲገቡ ፈቅዳለች።ይሕ ማለት አፍሪቃን አንድ የማድረጉ ሕልም ዕዉን የመሆኑ ምልክት ይሆን?ግን ብዙ ገንዘብ የሚጠይቀዉ የጉዞ፣ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ወጪስ?
(ቪዲዮዉን ይመልከቱ)
ትራምፕ ሥልጣን ሳይዙ አሜሪካ ለመግባት የሚደረግ ጥድፊያ
በመቶ የሚቆጠሩ የማዕከላዊና የደቡብ አሜሪካ ስደተኞች ሜክሲኮ ዉስጥ እንዲንቀሳቀሱ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል።ፍቃዱ፣ ስደተኞቹ ዩናይትድ ስቴትስ ለመድረስ የሚገጥማቸዉን ችግር ለማቃለል ይረዳቸዋል።ፈቃዱን ያገኙት ከ1000 የሚበልጡ ስደተኞች ከጓቲማላ ሜክሲኮ ከገቡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነዉ።ስደተኞቹ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ከመረከባቸዉ በፊት አሜሪካ ለመግባት ተስፋ አድርገዋል።በመጪዉ ጥር 20 ቀን 2025 ሥልጣን የሚይዙት ትራምፕ በርካታ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማጋዝ ቃል ገብተዋል።
የቪዶዮ ዘገባዉን ይመልከቱ
የገና ገበያ በአዲስ አበባ እንዴት ዋለ?
የገና ገበያ በአዲስ አበባ እንዴት ዋለ?
በአዲስ አበባ ገበያዎች መጠጦች፣ በግ እና በሬ የሚሸጡ ነጋዴዎች በገና ዋዜማ የበዓል ገበያ መቀዛቀዙን ይናገራሉ። የክርስትና እምነት ተከታዮች የገና በዓልን ለማክበር ሲዘጋጁ በዋና ከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች በሚገኙ ገበያዎች ሽንኩርት፣ ቅቤ፣ ማር፣ ጠጅ፣ በግ፣ ፍየል እና የቀንድ ከብቶች በስፋት ለሽያጭ ቀርበዋል።
በሾላ እና በአባዶ ገበያዎች በተለምዶ “የፈረንጅ” የሚባሉ ዶሮዎች ከ400 እስከ 500 ብር እንደሚሸጡ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ታዝቧል። “የሀበሻ” የሚባሉ የዶሮ ዝርያዎች በአንጻሩ ከ900 እስከ 1,500 ብር ድረስ ይሸጣሉ። ቅቤ እና አይብን የመሳሰሉ የወተት ውጤቶችም ውስን የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል።
አንድ የቀንድ ከብቶች “ውድም አይደለም፤ ርካሽም አይደለም። መካከለኛ ነው” ሲሉ የገበያውን ሁኔታ ተናግረዋል። ዛሬ ሰኞ ገዥ “በደንብ አልገባም” የሚሉት ነጋዴ ባለፉት አርብ እና ቅዳሜ ቀናት ገበያው የተሻለ እንደነበር አስረድተዋል። ነጋዴው እንደሚሉት የበሬ ዋጋ ከ55 ሺሕ እስከ 250 ሺሕ ብር ደርሷል።
በግ እና ፍየል የሚሸጡ ነጋዴ ስለገበያው ይዞታ ሲያስረዱ “ትንሽ ሰው አቅም ያጣ ይመስላል” ብለዋል። ነጋዴው እንደሚሉት ፍየል ከ8,000 እስከ 30,000 ብር ይሸጣል። በግ ከ7,000 እስከ 20,000 ብር ይሸጣል።
የቪዲዮ ዘገባ፦ ሰለሞን ሙጬ
የታህሳስ 28 ቀን 2017 የቀxwታ ሥርጭት
የገና በዓል ገበያ በባሕር ዳር
የገና በዓል ገበያ በባሕር ዳር
የገና የበዓል ገበያ በባሕር ዳር ደምቆ ነው የዋለው። በዋናው የሰባት አሚት ገበያ የእርድ እንሣት በብዛት የገባ ቢሆንም ገዥዎች ዋጋው ከአለፈው ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል። ሻጮች በበኩላቸው እንሣቱን ለመመገብ የሚወጣው ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ መጠነኛ የዋጋ ጨማሪ መደረጉን ነው እንደምክንያት የሚያነሱት።
ቪዲዮ፦ ዓለምነው መኮንን
የአካል ጉዳተኞችን መብት በሥዕል ማስተማር
የአካል ጉዳተኞችን አመራር ማሳደግ እና የመብቶቻቸውን መከበር ያለመ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ተዘጋጀ። በዐውደ ርዕዩ በተለያዩ የሙያ መስክ የተሰማሩ 60 አካል ጉዳተኛ ሰዎች አካል ጉዳተኝነትን እና ችግሮቹን የተመለከቱ ሐሳቦቻቸውን ለሠዓልዎች ተናግረው ሐሳቦቹ ወደ ሥዕል ተለውጠው ቀርበዋል።
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና በዓለም ጋለሪ ትብብር የተዘጋጀው ይህ ዐውደ ርዕይ ስለ አካል ጉዳተኞች መብቶች ግንዛቤን ማሳደግ እና የአካል ጉዳተኞች መብቶችን ለማስከበር እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ለሌላው ማስተማር የሚል ዓላማ ያለው ነው።
ቪዲዮ ዘገባ ፤ ሰለሞን ሙጬ ፤ አዲስ አበባ
በሰሜናዊ ማላዊ የሚገኝ ማኅበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸው ፈታኝ ሁኔታዎችና አደጋዎችን ወደ መልካም አጋጣሚነት እየቀየሩት ነው። ባለጠጎች ገበሬዎች ሙዝን በመማምረት ከሙዝ የሚሰራ ወይን በመጣል ለትርፍ እያዋሉት ይገኛሉ።ሙዞችን በስኳር፣ እርሾ፣ ሎሚ፣በዘቢብም ተጨምሮበት በማብላት በዓይነቱ ልዩ የሆነ የሙዝ ጠጅ ይጥላሉ። የአልኮል መጠኑ ደግሞ 13 በመቶ ነው ።
ኢትዮጵያ ከ50 በላይ የቅመማ ቅመም አይነቶችን ለማምረት የሚያስችል የእርሻ ሥነ ምህዳር እንዳላት ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡ በአውሮፕያኑ 2022 ዓ.ም በተደረገ ጥናት በአገሪቱ ከ386 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የቅመማ ቅመም ምርት ይውላል ፡፡ ከ 600 ሺህ በላይ አርሶአደሮችም ኑሯቸውን በዚሁ ዘርፍ ላይ የመሠረቱ ናቸው ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ የዝንጅብል ምርት ከማሳ እየተሰበሰበ ይገኛል ፡፡ በአካባቢው ከታህሳስ እስከ ጥር ያሉት ወራቶች የደረሰ የዝንጅብል ምርት የሚለቀምበት ወቅት ነው ፡፡ በወረዳው አጆራ ቀበሌ የዝንጅብል አምራች የሆኑት ኢንዲሪያስ ላሞሬ እና ዳዊት ደጀኔ ምርቱ በስፋት ከተተከለ ጥሩ ውጤት ይገኝበታል ይላሉ ፡፡
ይሁንእንጂ በአካባቢው የምርት አቅርቦቱን ለመጨመር የሚያስፈልጉ የእርሻ ማዳበሪያና የፀረ ነፍሳት ኬሚካል አቅርቦት እንደሌለ አምራቾቹ ይገልጻሉ ፡፡ ይህ በመንግሥት በኩል ሥለማይገኝ አቅርቦቱን በውድ ዋጋ ከነጋዴ እጅ ለመግዛት ተገደናል ፡፡ ይህም ጭማሪ ያለው ምርት እንዳናመርት እያደረገን ይገኛል “ ብለዋል ፡፡
ቪዲዮ ዘገባ ፤ ሸዋንግዛው ወጋየሁ (DW) ሐዋሳ
ኢትዮጵያ ከ50 በላይ የቅመማ ቅመም አይነቶችን ለማምረት የሚያስችል የእርሻ ሥነ ምህዳር እንዳላት ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡ በአውሮፕያኑ 2022 ዓ.ም በተደረገ ጥናት በአገሪቱ ከ386 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የቅመማ ቅመም ምርት ይውላል ፡፡ ከ 600 ሺህ በላይ አርሶአደሮችም ኑሯቸውን በዚሁ ዘርፍ ላይ የመሠረቱ ናቸው ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ የዝንጅብል ምርት ከማሳ እየተሰበሰበ ይገኛል ፡፡ በአካባቢው ከታህሳስ እስከ ጥር ያሉት ወራቶች የደረሰ የዝንጅብል ምርት የሚለቀምበት ወቅት ነው ፡፡ በወረዳው አጆራ ቀበሌ የዝንጅብል አምራች የሆኑት ኢንዲሪያስ ላሞሬ እና ዳዊት ደጀኔ ምርቱ በስፋት ከተተከለ ጥሩ ውጤት ይገኝበታል ይላሉ ፡፡
ይሁንእንጂ በአካባቢው የምርት አቅርቦቱን ለመጨመር የሚያስፈልጉ የእርሻ ማዳበሪያና የፀረ ነፍሳት ኬሚካል አቅርቦት እንደሌለ አምራቾቹ ይገልጻሉ ፡፡ ይህ በመንግሥት በኩል ሥለማይገኝ አቅርቦቱን በውድ ዋጋ ከነጋዴ እጅ ለመግዛት ተገደናል ፡፡ ይህም ጭማሪ ያለው ምርት እንዳናመርት እያደረገን ይገኛል “ ብለዋል ፡፡
ቪዲዮ ዘገባ ፤ ሸዋንግዛው ወጋየሁ (DW) ሐዋሳ
ከዶቼ ቬለ የታኅሣሥ 21 ቀን 2017 ዓ.ም. የቀጥታ ስርጭት