አዳሽ Adash

  • Home
  • አዳሽ Adash

አዳሽ Adash ይህ ገፅ የቀድሞ የአቢሲንያ ባንክ ክርስቲያን ሠራተኞች ህብረት ገጽ ሲሆን ቀድሞ እናደርግ እንደነበር ህብረት የምናደርግበት ነው፡፡

29/07/2022
12/09/2020

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ እንኳን አደረሳችሁ! ይህ 2013 ዓ.ም አዲስ አመት

የአመቱ የመጀመሪያ ወር የመጀመሪያ ቀን
☀️ከምድር ውሃ የደረቀበት፣ ኖህም
የመርከቢቱን ክዳን ያነሳበት እለት እንደሆነ እንዲህ የመለቀቅና ወደ ሰፊ ጀማሬ የመውጣት ይሁንልን
☀️የመገናኛው ድንኳን የተተከለበት እንደሆነ እንዲህ ከእግዚአብሔር ጋር የመገናኘት ሕይወታችን በአዲስ መንገድ የሚታደስበት ይሁንልን;
☀️በእዝራ ዘመን እንግዶችን ያገቡት ሰዎች
ተመርምረው የጨረሱበት እና ለመፍታት እጃቸውን የሰጡበት ቀን እንደሆነ እንዲህ ከእግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት ከወጣንበት የምንፋታበት፤ በሕይወታችን ካለ እንግዳና ባዕድ ልምምድ የምንፋታበት፣ እንደ እግዚአብሔር ሥርዓትና ሕግ ካልሆነ የህይወት ውሳኔ የምንፋታበት ቀን ይሁንልን;
☀️በንጉሱ በሕዝቅያስ ዘመን ካህናቱ ይቀደሱ
ዘንድ የጀመሩበት እንደሆነ እንዲህ ለእግዚአብሔር እንደገና የመቀደስ፣ የመለየት፣ ለጽድቅ የመቆም ቀንና ዓመት ይሁንልን;
☀️ሕዝቄኤል ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ እና
መቅደሱን አንጻ የተባለበት እንደሆነ እንዲህ መቅደሱ የሆንን እኛ ዛሬም ትኩስ በሆነው የክርስቶስ ደም ዳግም የምንነፃበት አዲስ ዓመት ይሁንልን።

አዲሱ አመት ብርሃኑ ሙሉ ቀን እስኪሆን እየጨመረ የሚሄድ ለሃገር ለ ቤ/ክ እንዲሁም ለቤተሰባችን የሚሄድ የብርሃን ዓመት ነው።

01/08/2020

ቀኖቻችን እንዴት እየተጠቀምንባቸው ነው?
ጊዜአችንን ለማን እየሰጠን ለማን እየከለከልን ነው?
ሁሉም ሰው እኩል 24 ሰዓት የተሰጠው ሲሆን ሁሉም ግን በተለያየ ሁኔታ ይጠቀምበታል፡፡ እርስዎስ ቀኖትን እንዴት እየተጠቀሙ ነው፡፡ ቀኑ ይዞ በመጣው ወይም ወደ ቀኑ ይዘውት በገቡት ሀሳብ እየኖሩ ነው፡፡ ሁልጊዜ አንርሳ ጊዜአችንን ለመልካም ነገር
ስንሰጥ ለክፍ ነገር ከልክለናል፣ ለጌታ ስንሰጥ ለዲያቢሎስ ከልክለናል፣ ለሥራ ሥንሠጥ ለሥራ ፈትነት ከልክለናል፣ ለሀሜት ስንሰጥ ለመልክም ንግግር ከልክለናል... ጊዜዎትን ለማን እየሰጡ ነው? ከእንግዲህ ጊዜዎን አስበውና አመዛዝነው ይስጡ ቀን እንዳመጣቦ አይዋሉ!
አዳሽ ቁ. 44

27/06/2020

“ለአዋላጅነት ታጭተን በአጨንጋፊነት አንገለጥ”

እንደ ሕዝብ ወንጌልን በኢትዮጵያ ምድር ቀድሞ በመቀበል እና ወንጌልን ለተቀሩት ኢትዮጵያዊያን ለማድረስ ትልቅ ሚና ከተወጡትና የአንበሳዉን ድርሻ የሚወስዱት በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልል ይኖሩ የነበሩት የቀደሙ የእምነት አባቶቻችን ናቸዉ፡፡

እንዚህ አባቶቻችን ወንጌል ለሀገራችን ሕዝቦች ሁሉ ለማድረስ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡
ክልላቸዉን ብቻ አይደለም መንደራቸዉንም ብቻ አይደለም ቤተሰባቸዉን ልጆቻቸዉን ትተዉ ዋጋ ከፍለዋል፡፡

በአየር፤በባቡር፤በመኪና ተሳፈረዉ አሊያም በከብቶች ወገብ ላይ ተፈናጠዉ አልነበረም ይልቁንም እግሮቻቸዉ በመንገድ ብዛትና በእሾ እስከ "ሚቦዳደስ" ድረስ ተጉዘዉ ወንጌል ላልደረሳቸዉ ወንጌል አድረሰዋል፡፡

በተለይም በደቡብ እና በኦሮሚያ ይኖሩ የነበሩ የቀድሞ አባቶቻችን በነገድ፤ በጎሳ፤ በክልል በጎጥ አጥር ሳይታጠሩ በስጋ ለማይዛመዷቸዉ፤በጎሳ ለማይገናኟቸዉ፤ በክልላቸዉ ለማይኖሩ የተቀሩ ኢትዮጵያዊያን በፍፁም ፍቅር ወንጌልን አድረሰዋል፡፡

ስለ ኢትዮጵያ መፃኢ-ዕድል(ስለ ሰላሟ፤ስለ እድገቷ፤ስለ አንድነቷ ስለ ጉብኝቷ) ብዙ ፀልየዋል፤ማልደዋል፤አልቅሰዋል፡፡

ዳሩ ግን ፀሎቱ ፅንስ ሆኖ አድጎ ለመወለድ ምጡ በተፋፋመበት በአሁኑ ወቅት ለአዋለጅነት የታዩት የቀድሞ አባቶች ልጆችና የልጅ ልጆች በአዋላጅነት ስፈራቸዉ ላይ እየታዩ አይደሉም፡፡

ዘሬ፤ዘርማንዘሬ፤ ነገዴና ጎሳዮ፤ክልል ክልሌ በሚል አዲስ ሙዝቃ ልባቸዉ ተይዟል፡፡

ለአዋላጅነት የታዩት ትዉልዶች በአጨንጋፊነት ጎራ ለመሰለፍ ዳር ዳር እያሉ ነዉ፡፡

በእየሱስ ክርስቶስ ከዘር፤ከቋንቋ፤ከነገድ ተዋጅተዉ ሳሉ ተመለስዉ "የዘር" ገብያ ላይ ዘርን ፍለጋ ተሰማርተዋል፡፡

ስጋና ምኞቱን ከእየሱስ ጋር በመስቀል ላይ የሰቀሉት መልሰዉ ቀመስቀል ላይ ሊያወርዱት በብዙ ይደክማሉ፡፡

ጊዜዉ ገና ቀን ነዉ ክፉ ሀሳብ በግላጭ ይታያል ለማየት ለወደደ ሁሉ፡፡ እንመለስ!!!

ለአዋለጅነት ታጭተን በአጨንጋፊነት አንገለጥ!!! ወደን እና መርጠን የገደልነዉን “ስጋዊነትን” ምድራዊነትን “መልሰን ከሞት አንቀስቅሰዉ!!!

እስጢፋኖስ ስሜ
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

እርሱ ለእኛ የመረጠው መንገድ ትክክል ነው! ክርስቲያኖች በሕይወታቸው በምድረበዳ (በደረቅ) መንገዶች ሲያልፉ ይበሳጫሉ፣ይጨነቃሉ፣ ያዝናሉ፣ ያጉረመርማሉ፣ መጽሀፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑንም ለማስረዳ...
14/06/2020

እርሱ ለእኛ የመረጠው መንገድ ትክክል ነው!

ክርስቲያኖች በሕይወታቸው በምድረበዳ (በደረቅ) መንገዶች ሲያልፉ ይበሳጫሉ፣ይጨነቃሉ፣ ያዝናሉ፣ ያጉረመርማሉ፣ መጽሀፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑንም ለማስረዳት ይዳዳሉ ፣ አብዛኞቹም ከመንገድ ይወጣሉ፡፡ እግዚአብሔር ግን እኛን ሁልጊዜ የሚያሳልፈን በምንፈልገው ሳይሆን በሚፈልገው መንገድ ነው፡፡ ‹‹ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም›› ዘፀ.13-7

ከወሰነልን (ከፈቀደው) መንገድ ውጪ ከሆንን ከእርሱ ሕይወት ጎድለን እንጎዳለን፡፡ ኢሳያስ በመልእክቱ እግዚአብሔር ከመንገዱ ውጪ እንደማያገኘን በግልጥ ያስረዳናል ‹‹በመንገዶችህ የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ፡›› ኢሳ.64-5

እግዚአብሔር ማርና ወተት መደ ምታፈሰው ከተማ ህዝቡን ሲያገባ ምድረበዳ የማይታሰብ ቢመስልም የይሁዳ ምድረበዳ ግን በዚያ ነበረ፡፡ እኛም ክርስቲያን ስንሆን ምድረ በዳ ፈጽሞ የማናይ ከመሰለን ተሳስተናል መጥመቁ ዮሐንስ ከይሁዳ ምድረ በዳ መምጣቱን፣ ኢየሱስም በመንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረበዳ መወሰዱን፣ ሐዋርያትም በህይወት ምድረበዳ ማለፋቸውን በማሰብ በምድረበዳ (ደረቅ በሆነ) ሕይወት ስናልፍ ጌታን በትእግስት በመጠበቅ ዳዊት በኤዶምያስ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ
እንደዘመረው ልንዘምር ይገባናል ያም ያጽናናናል፡፡

‹‹አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ። ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ። እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ።
በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ›› መዝ.63፤1-4
አዳሽ 38
https://t.me/Adashpage/144

"ዛሬን እየኖርክ ነው? ወይስ ነገን ለመኖር ተስፋ እያደረግህ?             ዛሬን መኖር ሁልጊዜን መኖር ነው!!!ዛሬህን በሰይጣን አታሰርቅ ቀኑን ሁሉ ለጌታ ዋጅተህ ኑርበት፡፡"     ...
09/06/2020

"ዛሬን እየኖርክ ነው? ወይስ ነገን ለመኖር ተስፋ እያደረግህ?

ዛሬን መኖር ሁልጊዜን መኖር ነው!!!

ዛሬህን በሰይጣን አታሰርቅ ቀኑን ሁሉ ለጌታ ዋጅተህ ኑርበት፡፡"

አዳሽ ቁ.39

https://t.me/Adashpage/147

ይህ በጆን ፓይፐር የተጻፈው "ኮሮናቫይረስና ክርስቶስ" የሚለው  መፅሀፍ ወቅታዊና እጅግ አስፈላጊ መፅሀፍ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ሊኖረን ስለሚገባ አመለካከትና ለወደፊቱ ማድረግ ስለሚገባን ዝግጅ...
27/05/2020

ይህ በጆን ፓይፐር የተጻፈው "ኮሮናቫይረስና ክርስቶስ" የሚለው መፅሀፍ ወቅታዊና እጅግ አስፈላጊ መፅሀፍ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ሊኖረን ስለሚገባ አመለካከትና ለወደፊቱ ማድረግ ስለሚገባን ዝግጅት የሚናገር፤ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት እና በዚህ ወረርሽኝ ውስጥ ምን እየሰራ እደሆነ የሚያሳይ ጥሩ መፅሀፉ ነው፡፡ አንብቤ ተጠቅሜበታለሁ ! እናንብብ ለሌሎችም እናጋራው

https://drive.google.com/open?id=1lekuB5BCPLamST5TQ6waO_H2ogOpd-eA&fbclid=IwAR1miLZnbLN3JR9AKu2zLl7FLqeQ8EmQ701YOehZ8NWkf0dxROVuGLJnKhw

19/05/2020

የመቃብር ወግ

በፓ/ር ልዑል ኃይሉ

ሰው እንደ እንስሳ አካላዊ ፍላጎት ብቻ ያለው ፍጡር አይደለም፤ ‘ከበላሁ፥ ከጠጣሁ፥ ወሲባዊ ርካታ አግኝቼ ዘሬን ከተካሁ ይበቃኛል’ ይል ዘንድ ፍጥረቱ አይፈቅድለትም። እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በምሳሌው አድርጎ ሠርቶታል፤ የክብርና የምስጋና ዘውድም ጭኖለታል። ስለዚህም ‘ወግ ማዕረግ ማየት’ ከመሻቶቹ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በየትኛውም ባህልና ቋንቋ ወግና ማዕረግ ይሉት ነገር አይጠፋም። ማኅበረሰባችን አባባሉን አዘውትሮ ሲጠቀምበት መስማት ለማናችንም አዲስ ነገር አይደለም። ወግና ማዕረግ በብዙ ዘርፎች ይታያል። ለምሳሌ የጋብቻ ወግ፥ ልጅ የመውለድ ወግ፥ የምርቃት ወግ፥ የሹመት ሽልማት ወግ … ዝርዝሩ ብዙ ነው። እኔ ግን ለዛሬው ስለ አንድ የወግ ዓይነት ላወራችሁ ወድጃለሁ - የመቃብር ወግ!

መቼም ‘ዞሮ ዞሮ ከቤት፥ ኖሮ ኖሮ ከመሬት’ የሚቀር የለም። ይሁንና የሰው ልጅ ወግ ከመጨረሻ ትንፋሹ ጋር አይቋረጥም፤ በሞቱም ክብሩ ይቀጥላል - “በሞቱ አከበሩት” ተብሎ እንደተጻፈ፤ 2ዜና 32፡33 ብዙጊዜ እንደታዘብነው ከአንዳንዱ ሰርግ የአንዳንዱ ቀብር ያስቀናል - በሞቱ የሚሰጠውን ክብር ስናይ! ከይሁዳ ነገሥታት መካከል “ታላቅ የሆነ የመቃብር ወግ አደረጉለት” (2ዜና 16፡14) የተባለለት ያለውን ያህል “ሕዝቡ … ለእርሱ የመቃብር ወግ አላደረገም” (2ዜና 21፡19) የተባለበትም አለ። ከዚህ የከፋ ደግሞ “አህያ እንደሚቀበር ይቀበራል” የተባለበትም አለ፤ ኤር. 22፡19 ደግሜ ልናገርና የሰው ፍላጎት እስከ ሞቱ ድረስ ብቻ አይደለም።

ኢዮብ በእግዚአብሔር በረከት ሙላት ላይ ሆኖ ባርኮቱን ሲቆጥር ስለ ፍጻሜውም አብሮ ይናገር ነበር - እንዲህ እያለ፦ “በልጆቼ መካከል እሞታለሁ…” ኢዮብ 29፡18 ቁዘማ ባጨፈገገው ፊት የሚነገር ሮሮ አይደለም ይሄ፤ ይልቁን በተስፋ በፈካ ገጽታ የሚነገር ቃል ነው። በሞት አልጋው (deathbed) ዙሪያ አደራውን የሚፈጽሙ የወገቡ ፍሬዎች ተኮልኩለው ማየት በጎልማሳነቱ ጊዜ በማዕዱ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ያሉ ልጆቹን ከማየት ጋር ተመሳሳይ የደስታ ስሜት የሚሰጥ ነው፤ መዝ. 128፡3 ደስ እያለው ወደ አምላኩ እቅፍ ይሄዳልና። ለዚህ ነበር ይህ ክብር የሆነላቸው እንደ ዳዊት ያሉ ቅዱሳን ሞታቸውን “የምድር ሁሉ መንገድ” በሚል ቀለል ያለ አባባል የሚገልጹት፤ 1ነገ. 2፡2

በመጽሐፍ ቅዱሳችን አሟሟትን በጊዜና በሁኔታ እያነጻጸሩ የሚናገሩ በርካታ ምንባባት ይገኛሉ። ለምሳሌ በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት ለሄደው ንጉሥ ኢዮስያስ በመልካሙ ጊዜ ወደ እርሱ እንደሚሰበስበው የተስፋ ቃል ሲሰጠው (2ነገ. 22፡20) በእርሱ ዘመን ለነበሩ ልበ ደንዳና ሕዝብ ግን የሚከተለው አስፈሪ ቃል ተነግሯል፦ “ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፥ ሰዎችም አያለቅሱላቸውም… የእዝን እንጀራ አይቆርሱላቸውም፤ ስለ አባታቸውና ስለ እናታቸውም የመጽናናት ጽዋ አያጠጧቸውም።” ኤር. 16፡6-7

እስኪ አሁን ደግሞ ፊታችንን ወደዚህች ሰዓት እንመልስ፤ ኮሮና ይሉት ወረርሽኝ ዓለምን መያዣ መጨበጫ አሳጥቶ እያመሳት እንዳለ ይታወቃል። ይህ ቸነፈር (pandemic) የሁሉን ገመና እንደመግለጡ ምድርን ያላሳጣት ነገር የለም ማለት ይቻላል። ለዚህ ነው ኮሮና የጤና ችግር ብቻ አይደለም የምንለው። (ከቀውሶቹ አንዱ ስለሆነው ማኅበራዊ ቀውስ በቀጣይ እጽፋለሁ፤ ያው የእኔ ዓላማ ግንዛቤን በማሳደግ የድርሻችንን እንድንወጣ ለጸሎትም ለድርጊትም ማንቃት ነውና)

ይህን ጽሑፍ እስከምጽፍባት እስካሁኗ ቅጽበት ድረስ ብቻ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተውሳኩ የተያዙ ሲሆን ከሶስት መቶ ሺህ ሰዎች በላይ ደግሞ ሞተዋል። እዚህ ላይ አስደንጋጩ ነገር የሞቱ ቁጥር ማሻቀብ ብቻ አይደለም፤ እላይ እንዳልሁት የሞትና የመቃብር ወግ እንኳ ብርቅ ሆኗል። በሚድያ እንደምንከታተለው በበለጸጉት አገራት ሟቾች የሚወዷቸውን የቤተሰቦቻቸውን አባላት የመሰናበት እድል የላቸውም። ቤተሰብም ሬሳውን የመቅበር አጋጣሚ የለውም። እንደ ሁቱና ቱትሲው ፍጅት ሰለባዎች ስምና መለያ የሌላቸው ጅምላ አስከሬኖች በገፍ ይቀበራሉ። እግዚኦ ያስብላል! ኢዮብ እንዳለው በልጆች መካከል መሞት ታላቅ እድልና ክብር መሆኑ አሁን ለሁሉም ግልጽ ሆኗል።

ወደ እኛም ሁኔታ ስንመጣ ወረርሽኙን ተከትሎ በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በዚህ ቫይረስ የሚሞቱ ሰዎችን የሚቀብረው መንግሥት ነው። ምናልባት ከቤተሰብ መካከል በቀብሩ ላይ ለመገኘት የሚፈቀድላቸው ይኖሩ ይሆናል፤ ነገር ግን የእድሩ ጥሩምባ ነፊ እድርተኛውን በጅምላ ይጠራ ዘንድ አይችልም። የእዝን ሥርዓቱም ቢሆን በፍጹም እንደ ወትሮው አይሆንም። በልቅሶ ድንኳን ውስጥ እግዚአብሔር ያጥናችሁ ሊል የሚከማች አስተዛዛኝ አይኖርም - ድንኳንስ ሲኖር አይደል?! ‘ማዘጋጃ ነው የሚቀብርህ’ የምትለዋ አባባል ከማስፈራሪያነት ወደ እውነታነት ተለወጠች ማለት ነው። ስለዚህም በዚህ ቫይረስ የሚሞት ሰው ዘመዶች ሐዘናቸው ድርብርብ ነው ማለት ነው። የልቅሶ ወግ እንደ ሰርግ ይናፍቀናል ብለን አስበን እናውቅ ይሆን? ወይ ጊዜ!

ደግሞም በሌላ መንገድ ነገሩን ካየነው የእግዚአብሔር በረከት ብለን ቆጥረናቸው የማናውቅ ብዙ የእርሱ ስጦታዎች ምን ያህል ውድ መሆናቸውን የምናስተውለው ስናጣቸው መሆኑ ይገባናል። ማነው ለመሆኑ በሚወደው ሰው ለቅሶና ቀብር ላይ የእግዚአብሔር ቸርነት ታስቦት ያመሰገነ? ‘እዬዬም ሲደላ ነው’ እንዲሉ በብዙ አጽናኞች ተከበን ያለቀስንባቸው ሐዘኖች የድሎት ጊዜያት ነበሩ ለካስ? አብርሃም ሊንከን እንዳለው እግር የሌለው ሰው እስክናይ ድረስ ጫማ የለኝም ብለን ማልቀሳችን ምን ያህል እንደማናስተውል ነው የሚያሳየው።

ለመሆኑ የመቃብር ወግ መጣጥፍ ሊቀርብበት የሚገባ ቁም ነገር ነውን የምትሉ ትኖሩ ይሆናል። የመቃብር ወግ የዕድር በረከት አይደለም፤ ደግሞም ማኅበራዊ ተጽዕኖ ያመጣብን ምድራዊና ተራ ጉዳይም አይደለም። እንደ አማኞች ሙታናችንን ስንቀብር መኸርን ተስፋ አድርጎ እንደሚዘራ ገበሬ የእምነት ሥራ እየሠራን እንደሆነ ገብቶን ነው የምናደርገው - የትንሣኤ ተስፋ ያለን ሕዝብ ነንና! በዚያ ቀውጢ የስደት ጊዜ እንኳ ሰማዕቱን እስጢፋኖስን የቀበሩት በጸሎት የተጉ ሰዎች ነበሩ፤ የሐዋ. 8፡2 ለምን ያ ዘገባ በቃሉ መስፈር አስፈለገው? ምክንያቱም የቀብር እንድምታ (implication) ብዙ ስለሆነ ነው። ስለዚህም በዚህ ወረርሽኝ ሰበብ ለጋራ አምልኮ መሰብሰብ አለመቻላችን ብቻ ሳይሆን ይህንንም ወግ ማጣታችን ተሰምቶን ወደ እግዚአብሔር እንጩህ። ከመቃብር ወጉም ባሻገር የለቅሶ አጋጣሚ ለስብከተ ወንጌል እጅግ ተመራጭ መሆኑን ታውቁ ይሆን? በቀብርና የለቅሶ ድንኳን ውስጥ መስበክ ከበልግ ዝናብ በኋላ እንደመዝራት እጅግ አመቺ ነው።

ስለዚህም እናንተ እግዚአብሔርን በጸሎት የምታሳስቡ ጉበኞች (ማላጆች) ሆይ፥ እግዚአብሔር ለምድራችን ዘንበል እስኪል ድረስ አትረፉ፤ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡት። በቀላሉ የምናያቸው ጉዳዮች (for granted የምንወስዳቸው) የእግዚአብሔር ባለ ዕዳዎች የሚያደርጉን የበረከቱ ቋቶች እንደሆኑ እንረዳ። ዓይኖቻችን በሰፊው ይከፈቱና ተቆጥረው የማያልቁትን የእግዚአብሔርን ድንቆች ይመልከቱ፤ “እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምን ነበር፤ ነገሬንም ወደ እርሱ አቀርብ ነበር። የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቆጠረውን ተአምራት ያደርጋል።” ተብሎ እንደተጻፈ፤ ኢዮብ 5፡8-9 ጸጋ ይብዛላችሁ!

15/05/2020

በዘሬ አይግባ ያልኩት እርሱ ነው ነፍሴን ያዳነው።

15/05/2020

በዘሬ አይግባ ያልኩት እርሱ ነው ነፍሴን ያዳነው

15/05/2020

በዘሬ አይግባ ያልኩት እርሱ ነው ነፍሴን ያዳነው። በወ/ም ፍሰሃ ደሳለኝ

11/05/2020

የጓዳችን ነገር - በፓ/ር ልዑል

በብዙኃን መገናኛዎች ነጋ ጠባ በተደጋጋሚ የሚሰጡ ማሳሰቢያዎች ሰው እንዴት ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንደሚከላከል ግንዛቤ የሚሰጡ ናቸው። ይሁንና ከዚህ ተስፋፊ ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዘው የመጡ ወይም ቢያንስ የተባባሱ በርካታ የጎንዮሽ ችግሮች አሉ። ከእነዚህ ችግሮች መካከል በጣም በስፋት ብዙዎችን እየወረሰ ያለው ከጭንቀት ጋር የተያያዘው የድባቴ (depression) ሕመም ነው። ለዚህ ችግር ግን ሚዲያዎች የሚገባውን ትኩረት ሲሰጡ አንመለከትም። ምክንያቱም ጉዳዩን የጤና ችግር ብቻ አድርጎ የመውሰድ አዝማሚያ ስላለ ነው። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ተደርጎ ከታወጀበት ጊዜ አንሥቶ በርካታ አገራት ከተሞችን የመዝጋትና እንቅስቃሴዎችን የመገደብ እርምጃዎችን ወስደዋል። ይህም ብዙዎች ተለማምደውት ወደማያውቁት የሕይወት ዘይቤ አስገብቷቸዋል - ያውም ወደው ሳይሆን የግዳቸውን። ይህ አዲሱ የሕይወት ዘይቤ ከቤት ሳይወጡ መዋልና ብዙ ጊዜ አብረው ከማያሳልፉት ቤተሰባቸው ጋር መክረም ነው። አንዳንዶች ይህን አጋጣሚ ኮሮና ይዞት የመጣው እድል ብለው ሲገልጹት ሌሎች በርካታ ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ያልተናነሰ አበሳ አድርገው ወስደውታል።

በተለይም ለትዳር ተጣማሪዎች ይህ ወቅት ትልቁ የፈተና ጊዜ መሆኑ እየታየ ነው። ፈተና ክፉም ደግም ያልሆነ ገለልተኛ ቃል ነው። ምክንያቱም ያለፉት ሲደሰቱበት የሚወድቁ ደግሞ ያማርሩታልና። በዚህ በሠለጠነው የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰው ተገዶ ያለፈቃዱ የሚመሠርተው ትዳር ብዙም የለም። አብዛኛዎቹ ተጋቢዎች ወደውና ፈቅደው ነው ራሳቸውን በትዳር የሚያስተሳስሩት። ጋብቻው በባህላዊውም ይሁን በዘመናዊው ሕግ ይፈጸም፥ አልያም በእምነት ተቋማት ወግ ይከናወን ያንን ቀን ሁለቱ ጥንዶች የጋራ ደስታችን ቀን ብለው ማወጃቸው እውነት ነው። አሳዛኙ ነገር ግን ያቺ የመጀመሪያ ሰሞን ደስታ በአብዛኛው ዘላቂ አትሆንም። በደስታው ፈንታ ሐዘን፥ በመዋደዱ ፈንታ መጠላላት፥ በመተሳሰቡ ፈንታ መወነጃጀል… መተካቱ የብዙ ትዳሮች መራር እውነታ ነው። በብዙ አገሮች በተደረጉ ጥናቶች በጋብቻ ላይ ለሚገኙ ጥንዶች ሁለተኛ የማግባት እድል ቢሰጥ ከሦስት አራተኛው (75%) በላይ የሚሆኑት ጥንዶች አሁን የትዳር አጋራቸው የሆነችውን/የሆነውን መልሰው የማያገቡ ናቸው። ያ ማለት አብረው እየኖሩ ያሉት ግድ ሆኖባቸው ነው ማለት ነው።

ታዲያ በተሟጠጠ ፍቅር አብረው የሚኖሩ ጥንዶች እርስ በርስ ያላቸውን መገፋፋት የሚያስጠብቁበት ሁነኛ መንገድ ራስን በሥራ፥ በመዝናኛና በተለያዩ ማኅበራዊ ትስስሮች (social engagement) መጥመድ ነው። በቀን ውስጥ አብረው የሚያሳልፉባት ጊዜ በተቻለ መጠን እንድትቀጥን ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ። ብዙ ጊዜም ይህ ጥረት የጋራ ስለሆነ የመሳካት እድሉ ሰፊ ነው።

አሁን ግን አስገዳጅ ሁኔታ መጥቶ የድብብቆሽ ጨዋታውን አፈረሰው። እናም እስር ቤት አንድ ክፍል እንደደረሳቸው ባላንጦች ሊቀይሩት የማይችሉት ዕጣ ወደቀባቸው። አንድ አፈንጋጭ አመለካከት ያለው ደራሲ በአንድ ወቅት ትዳርን ሲተረጉመው፦ ‘ሁለት ሰዎች የጋራ ሥቃይ የሚቀበሉበት ተቋም ነው’ ሲለው የእርሱ ቢጤ የሆነ ሌላ ጸሐፊ ደግሞ ‘ትዳር ማለት የመጨረሻ ፌርማታው ጋር እንደደረሰ ባቡር፥ ውስጥ ያሉት ሊወጡ፥ ውጭ ያሉት ደግሞ ሊገቡ የሚታገሉበት ማጎሪያ ነው’ ብሏል። አንዳንዶችም በቀልድ አስመስለው ይህንን የሚያጎሉ አባባሎችን ሲፈበርኩ ይታያል። የሆነ ሰው እንዳገባ ሲነገራቸው ‘ይበለው ክፉ ሰው ነበር’ የሚሉትን ሰምተናል። ሚስት ባሏን ‘ለመሆኑ እኔን እንድታገባ የጠቆመህ ማነው?’ ስትለው ‘አላስታውስም፥ ጠላቶቼ ብዙ ናቸው’ እንዳላት ይነግሩናል። ባል የጋብቻቸውን ሰርተፊኬት ለረጅም ሰዓት ሲመለከት ያየች ሚስት ‘የሰርጋችን ትዝታ ይዞህ ነው?’ ስትለው ‘አይ፥ ሰርተፊኬቱ ላይ ኤክስፓየር ዴት እንዳለ እየፈለግሁ ነው’ ያለውንም ሰምተናል። ሰሞኑን እንኳ አንድ ወዳጃችን ሰዎች ሲያወሩ ሰማሁ ያለውን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፎት አይቻለሁ፦ ጓደኛሞች ሲያወሩ አንዱ ሌላውን ‘እገሌ እኮ ታድሎ’ ይለዋል፤ ‘ምነው ምን አገኘ?’ ሲለው ‘ሚስቱ ለበዓል ክፍለ አገር ሄዳ መንገድ ተዘጋለታ!’ ብሎ መለሰ።

ከላይ የተመለከትናቸው ጉዳዮች ለጊዜው የሚያስፈግጉ ቀልዶች ሊመስሉን ይችላሉ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ከምንም በላይ የከበረውና ታላቅም ተልእኮ የተሸከመው ጋብቻ የተሰኘው ቅዱስ ተቋም በሰዎች ዓመፀኝነት ምክንያት ምን ያህል መስመሩን እንደሳተ ያሳየናል። ገና በመጀመሪያው ጋብቻም አዳም በደስታና በምስጋና የተቀበላትንና ከራሱ መውጣቷን ተቀብሎ ከእርሷ ጋር ያለውን አስደናቂውን ጥምረት ዘመን በማይሽረው ቃል የተናገረላትን ሴት ከኃጢአት ውድቀት በኋላ ፈጥኖ እንደከሰሳትና ሳይፈልግ የተጣበቀችበት በሚያስመስል አገላለጽ እንዳራቃት እናያለን። ዛሬም በዓለም ሁሉ ላይ የምናየው የተጋቢዎች ውጥረት የዚሁ ተቀጥላ ነው።

አሁን በምድራችን ላይ በተከሰተው ወረርሽኝ ምክንያት የሕክምና ባለሞያዎች እጥረት እንደተፈጠረ ይታወቃል። በአገራችንም ቢሆን በጡረታ የተገለሉና ገና በትምህርት ላይ ያሉ የሕክምና ባለሞያዎች ጭምር በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት እንዲሰባሰቡ እየተደረገ ነው። በባዕድ ወረራ ጊዜ እንደሚደረገው ‘የእናት አገር ጥሪ’ በተሰኘ ተማጽኖ ነው እየተጠሩ ያሉት። ከተከሰተው ድንገተኛ ወረርሽኝ አንጻር ይሄ የሚጠበቅና ምንም የማይገርም ነው። የዚህ ቫይረስ ችግር እልባት ካገኘ በኋላ ደግሞ በሌላ አንድ ዘርፍ ከፍተኛ የባለሞያ እጥረት እንደሚፈጠር ተተንብዮአል፤ ይኸውም በሕግ ዙሪያ ነው። ለምን ቢሉ በርካታ የፍቺ ጥያቄዎች ፍርድ ቤቶችን ያጨናንቃሉ ተብሎ ይጠበቃልና። ይህ ተራ ግምት ሳይሆን ዳታዎችን በመሰብሰብ በማኅበራዊ ሳይንስ ምሁራን የተደረገ ጥናት ነው። አብዛኞቹ ኬዞች በሥነ ልብናዊ ምክሮች የማይፈቱ እንደሆኑ ጭምር ነው የሚነገረው።

ለመሆኑ ይሄን ለምንድነው የምንነጋገረው? ምንስ እናድርግ? ደጋግሜ እንደማስረዳው እነዚህን ጽሑፎች የምጽፈው አንድም ለግንዛቤ ሲሆን (እውቀት ኃይል ነውና) ሁለትም የጸሎታችን ርዕስ እንድናደርገው ነው። በምንም ምክንያት ይምጡ ከማናቸውም ክፉ ነገሮች ጀርባ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ዲያብሎስ አድፍጦ እንደሚሠራ እናውቃለን። መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ ለእርሱ እድል መስጠት የተገባ አይደለም። ስለዚህም ልንቀድመው ግድ ይለናል።

የትዳር ግንኙነታቸው በውጥረት ውስጥ ያለ ጥንዶች ሊያደርጓቸው የተገቡ ጥቂት ነጥቦችን ከዚህ ቀጥዬ ላቀርብ እሞክራለሁ። ከሁሉ የሚቀድመው ነገር ለየትኛውም በእኛ እጅ ለተበላሸ ነገር እንደምናደርገው ክርስቲያናዊ ወግ በነገሩ ላይ ንስሐ መግባት ነው። እግዚአብሔር ጤነኛ ልጅ ሰጥቷት ተኝታበት እንደገደለችው ጋለሞታ እኛም አሁን ጤናውን ያጣውን ትዳራችንን ጌታ ሲሰጠን ከነሙሉ ክብሩ፥ መብቱና ግዴታዎቹ ጋር ነበር። ያበላሸነው እኛው ነንና በእግዚአብሔር ፊት በንስሐ እንውደቅ። ይህ የመጀመሪያ እርምጃ ነው።

ሲቀጥል ደግሞ የታመመን የሚያድን፥ የሞተ ነገርን በሕይወት የሚያኖር አምላክ እንዳለ እንረዳ። ጋብቻ ኪዳን ነው። ኪዳን ደግሞ የሚመሠረት ብቻ ሳይሆን ሲበላሽም የሚታደስ እንደሆነ እንወቅ። እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ኪዳን በተደጋጋሚ ሲያድስ እናያለን። እድሳቱ ያሻው የቃል ኪዳኑ ሰጪ እግዚአብሔር በድሎ ሳይሆን የቃል ኪዳኑ ተቀባይ ሕዝቡ ከመስመሩ ወጥቶ ነው። በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የኪዳን እድሳት የተደረገባቸው በርካታ ምንባባት እናገኛለን። ለምሳሌ በኢያሱ ዘመን፥ በሕዝቅያስ ዘመን፥ በኢዮስያስ ዘመን ወዘተ… የተደረጉትን የኪዳን እድሳቶች መመልከት እንችላለን። በእነዚህ ጊዜያት ሕዝቡ በእንባ ንስሐ ሲገባና ከፊት ይልቅ በጋለ ፍቅር ወደ አምላኩ ሲመለስ እናያለን። የልባችንን ጥንካሬ በንስሐ መስበር ከቻልን ጋብቻም በተመሳሳይ መልኩ ሊታደስ ይችላል።

ሌላው ማወቅ ያለብን ፍቅር ማለት እንከል አልባውን ሰው እንድናደናንቅበት የተሰጠን ቅኔ ሳይሆን በተቃራኒው ብዙ ችግር ያለበትን ሰው እንድንሸፍንበት የተሰጠን ሸማ መሆኑ ነው፤ ምሳ. 10፡12፤ 1ጴጥ. 4፡8፤ ያዕ. 5፡20 ስለዚህም ነው ፍቅር በእውቀት ማደግ የሚኖርበት፤ ፊል. 1፡9 በተዋወቅን ቁጥር ጉድለቶቻችንን እንተያያለን፤ ያኔም የተሰጠንን የጉድለት መሸፈኛ (ፍቅር) ይበልጥ እንጠቀምበታለን። ካለ ጨለማ ከዋክብት አይደምቁም፤ ያለ ኃጢአት ጸጋ አይገለጥም፤ እንከን በሌለበትም ፍቅር ቦታ የለውም። ስለሆነም እልፍ አእላፍ ጉድለት ያለባትን ሚስታችንን እልፍ ጊዜ እልፍ በሆነ ፍቅር እናቅናት። ያኔ እልፍ ጊዜ እልፍ የሆነው የራሳችን ገመና በምላሹ በፍቅር ይሸፈንልናል። ቤታችንም ከጭቅጭቅ ወጥቶ የዕረፍት ቤት ይሆናል። የተዳበሉን አጋንንት ይወጡና የሸሹት መላእክት ተመልሰው ይገባሉ።

ይህንን ለእኛ ብቻ አልልም፤ “ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ” እንደተባልነው (ምሳ. 24፡11) ወደ ፍቺ የሚሄዱትንም ትዳሮች እንታደግ። ቤተሰብ ሲበተን አገር ይቃወሳል። ጣሪያው ይዘብጣል፥ ትውልድ ላይ ቤቱ ይፈርሳል። እግዚአብሔር ፍቺ ይጠላል፤ ሚልክ. 2፡16 እግዚአብሔርን የምንወድ እርሱ የሚጠላው ነገር እንዳይከሰት እንጋደል። ስለሆነም በዚህ ርዕስ ላይ ለሁሉ እንጸልይ።

ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የቴሌግራም ቻናላችንን መከተል ትችላላችሁhttps://t.me/Adashpage
09/05/2020

ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የቴሌግራም ቻናላችንን መከተል ትችላላችሁ

https://t.me/Adashpage

ይህ ገፅ የቀድሞ የአቢሲንያ ባንክ ክርስቲያን ሠራተኞች ህብረት ብሮድካስት ቻናል ሲሆን ቀድሞ እናደርግ እንደነበር ህብረት የምናደርግበት ነው፡፡ ዓላማችን ትውልዱን ለተፈጠረበት ለተ....

ብሔራዊ ንስሐ ለብሔራዊ ኃጢአት
09/05/2020

ብሔራዊ ንስሐ ለብሔራዊ ኃጢአት

09/05/2020

ይህ ገጽ የቀድሞ የአዳሽ እትሞችንና ወቅታዊ የሆኑ መልዕክቶችን የምናስተላልፍበት ገፅ ነው፡፡

እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡

09/05/2020
09/05/2020
09/05/2020

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዳሽ Adash posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አዳሽ Adash:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share