20/12/2024
1. ‹‹መከራ ሠውን ይሠራዋል፤ ቁሳዊ ብልፅግና ግን አስፈሪ ጭራቅ ያደርገዋል፡፡››
2. ‹‹ከሁሉ መጀመሪያ ሠው ሁን!
የሠብዓዊነትን ቀንበር ለመሸከም አትፍራ፡፡››
3. ‹‹መሞት ምንም አይደል፡፡ አለመኖር ግን አስከፊ ነው፡፡››
4. ‹‹ብልህ ሠዎች ከሕይወት መከራ መፅናኛቸውን የሚፈልጉት ከመፅሐፍ ነው፡፡››
5. ‹‹ጊዜው ከደረሠ ሃሳብ በላይ ሃይለኛ የለም፡፡››
6. ‹‹ሌላ ሠው ማፍቀር የፈጣሪን ሌላኛውን ፊቱን ማየት ነው፡፡››
7. ‹‹የሃብታሞች ገነት የተሠራው ከደሃዎች ሲዖል ነው፡፡››
8. ‹‹የማያለቅሱ ማየት አይችሉም፡፡››
9. ‹‹ምንም ዓይነት ጦር ወይም መሣሪያ ጊዜው የደረሠ ሃሳብን ሊያስቆመው አይችልም፡፡››
10. ‹‹ሠዎች ጥንካሬ አላጠራቸውም፡፡
ያጠራቸው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ብቻ ነው፡፡››
11. ‹‹ሕሊና ማለት በሠው ውስጥ የፈጣሪ መኖር ነው፡፡››
12. ‹‹ልማድ ወይም ሱስ ስህተቶችን መንከባከቢያ ስፍራ ነው፡፡››