Gofa Through My Camera

Gofa Through My Camera 📸የጎፋ መልኮች የሚዳሰስበት ገጽ ነው 📸
█▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
┊┊┊▕▔╲▂▂▂╱▔▏
Me

ሜታ ኩባንያ ፌስቡክ መተግበሪያው የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ  ታህሳሥ 2/2017 (ኤፌ ኤም ሲ) የፌስቡክ እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ ኩባንያ የፌስቡክ መተግበሪያው የቴክኒክ ችግር ...
11/12/2024

ሜታ ኩባንያ ፌስቡክ መተግበሪያው የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ


ታህሳሥ 2/2017 (ኤፌ ኤም ሲ) የፌስቡክ እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ ኩባንያ የፌስቡክ መተግበሪያው የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው በራሱ ገፅ ላይ ለተጠቃሚዎቹ ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚዎች ችግር እንዳጋጠማቸው በተለያየ ሁኔታ ሲገልፁ ተስተውሏል።

ያጋጠመውን ችግር በአፋጣኝ ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፆ ለተፈጠረው ችግር ተጠቃሚዎቹን ይቅርታም ጠይቋል።

08/12/2024

ከካሜራው በስተጀርባ ያለው የከሜራ ማኖች ልፋት😪😪
Dubusha Tv #ምስጋናዬ ካለሁበት ይድረስህ🙏

✈️✈️ ፋይሌት ሆኗልፋይሌት ዳንኤል ድንቁ እንኳን ደስ አለክ💪
08/12/2024

✈️✈️ ፋይሌት ሆኗል
ፋይሌት ዳንኤል ድንቁ እንኳን ደስ አለክ💪

በቀለማት ሕብር የደመቀው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አከባበር በአርባ ምንጭ
08/12/2024

በቀለማት ሕብር የደመቀው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አከባበር በአርባ ምንጭ

የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች አርባምንጭ ከተማ ገቡየኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨም...
07/12/2024

የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች አርባምንጭ ከተማ ገቡ

የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ወደ አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ በእንግዳ ተቀባይነት የሚታወቀው የጋሞ ህዝብ በነቂስ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለመታደም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንዲሁም በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ አርባምንጭ ከተማ እየገቡ ይገኛል

በሁሉም የእንግዶች መግቢያ አቅጣጫ ደማቅና ባህላዊ አቀባበል እያደረገ የሚገኘው የጋሞ ህዝብ ዛሬም የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ሲገቡ በነቂስ በመውጣት ደማቅ አቀባበል አድርጓል።

ቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ሺህ ዶላር መመንዘር ጀመረ*****************************ቢትኮይን የተሰኘው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ (ክሪፕቶ ከረንሲ) በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ...
05/12/2024

ቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ሺህ ዶላር መመንዘር ጀመረ
*****************************

ቢትኮይን የተሰኘው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ (ክሪፕቶ ከረንሲ) በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

በዚህም የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ100 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም በዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ ታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

የቢትኮይን ዋጋ እንዲህ ሊጨምር የቻለው ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክሪፕቶ ከረንሲን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን እንደሚቀበሉ በማሳወቃቸው መሆኑ ተገልጿል።

ትራምፕ የቀድሞን የአሜሪካ የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽነር ፖል አትኪንስ የሃገሪቱ የስቶክ ገበያ የሆነውን ዎል ስትሪት እንዲመሩ ማጨታቸው ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ የቢትኮይን ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ሚስተር አትኪንስ አሁን ካሉት የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽን ኃላፊ ጋሪ ጌንስለር የበለጠ የክሪፕቶ ከረንሲ ደጋፊ ስለመሆናቸውም ነው የተገለፀው።

ዶናልድ ትራምፕ ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ክሪፕቶከረንሲን የተቹ ቢሆንም አሁን ግን አሜሪካን የምድራችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ ሲሉ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ እየናረ መምጣቱ ተጠቁሟል።

በተለይም ባለፈው ወር ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ የቢትኮይን ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳይ መቆየቱ ነው የተገለፀው።

አንዳንድ ትልልቅ ኩባንያዎችና ተቋማት ቢትኮይንን እንደ ገንዘብ መቀበል መጀመራቸውም ለተፈላጊነቱ ማደግ ሌላ ምክንያት ነው ተብሏል።

የዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ 100 ሺህ ዶላር መግባቱን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ያሉ የቢትኮይን ተጠቃሚዎች እና ደንበኞች ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

የጋሞ ዞን አስተዳደር  ወንድም ለሆነው የጎፋ ዞን ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ  የተገዛ መኪና አስስረከበ።አርባምንጭ ፣ህዳር 25/2017 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን ፦  የደቡብ ኢትዮጵ...
04/12/2024

የጋሞ ዞን አስተዳደር ወንድም ለሆነው የጎፋ ዞን ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገዛ መኪና አስስረከበ።

አርባምንጭ ፣ህዳር 25/2017 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን ፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኘበት የጋሞ ዞን አስተዳደር ወንድም ለሆነው የጎፋ ዞን በ17 ሚሊየን 250 ሺህ ብር ወጪ የተገዛ መኪና አስስረክቧል።

በርክብክቡ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ የጋሞና ጎፋ ህዝብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ከመሆኑም ባሻገር የተዋለደ እና የተጋመደ ህዝብ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዝህ ቀደም ሁለቱ ዞኖች አብረው በነበሩበት ወቅት የጎፋ ዞን እራሱን አስችሉ ዞን ሁኖ ስደራጅ የሀብት ክፍፍል መደረጉን የሚያስታውሱት ዋና አስተዳዳሪው በወቅቱ ለዞኑ መኪና ለመግዛት መታቀዱን እና በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን ተናግረዋል።

አክለውም በደም የተሳሰሩ ሁለቱ ዞኖችን በቁስ እንደማይገደቡና የዞኑ አስተዳደር ከክልሉ አመራሮች ጋር በመቀናጀት ሲመክርበት መቆየቱን እና በዛሬው ዕለት መኪናውን እርክብክብ በማድረጋቸው የተሰማቸው ደስታ ገልፀዋል።

የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ በበኩላቸው የዞኑ ህዝቦች ለዘመናት በሀሳብም ሆነ በአካል ተሳስረው የኖሩ ህዝቦች እንደመሆናቸው ዞኑ እራሱን አስችሎ ሲወጣ ደማቅ ሽኝት ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

አንድ ህዝብ ሆነው በሁለት መዋቅር እንደሚገኝ እና ለመኪናው ግዢ በጋሞ ዞን ደረጃ እስካሁን ሲያስቡበት እና ሲጨነቁበት መቆየታቸውን ገልፀው ለጎፋ ዞን ህዝብ ክብር ላበረከቱት መኪና አመስግነው በቀጣይም እየተረዳዱ እየተጋገዙ ለተሻለ ውጤት እንደሚተጉ ተናግረዋል ።

በርክብክቡ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የዞኑ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክልልና የዞን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተውበታል።

አንበሳ በአንድ አርሶአደር ላይ ጉዳት አድርሰዋል ።===================================በጎፋ ዞን በደንባ ጎፋ ወረዳ በጫና ገርፋ ቀበሌ ላይ ከማዜ ብሔራዊ ፓርክ ተነስተው ...
04/12/2024

አንበሳ በአንድ አርሶአደር ላይ ጉዳት አድርሰዋል ።
===================================
በጎፋ ዞን በደንባ ጎፋ ወረዳ በጫና ገርፋ ቀበሌ ላይ ከማዜ ብሔራዊ ፓርክ ተነስተው ወደ ኦሞ ወንዝ በረሃ አቋርጠው እያለፈ ያለ አንበሳ ፣በአንድ አርሶአደር አካል ላይ ጉዳት አድርሰዋል ። አሁን ባለው ሁኔታ የተጎዳው ግለሰብ በላይማ ፃላ ጤና ጣቢያው ላይ ህክምና ላይ ይገኛል።

በጎፋ ዞን የመንግስት ሠራተኞች  #የደመወዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ ላይ ያተኮረ መድረክ እየተካሄደ ነውሣውላ፤ ኅዳር 25/2017 በጎፋ ዞን የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ አፈ...
04/12/2024

በጎፋ ዞን የመንግስት ሠራተኞች #የደመወዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ ላይ ያተኮረ መድረክ እየተካሄደ ነው

ሣውላ፤ ኅዳር 25/2017 በጎፋ ዞን የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ ላይ ያተኮረ የኦሬንተሽን መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ውድነት ማካካሻ የደመወዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 77/2017 ለዞን፣ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

የክልሉ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤቱ በመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ አፈፃፀም መመሪያ ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ፤ ካለፈው የጥቅምት ወር ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪው ተግባራዊ እንዲደረግ ባስተላለፈው ውሳኔን ተከትሎ የሚደረግ መድረክ መሆኑን ተገልጿል።

በመድረኩ የሁሉም መምሪያና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የሰው ሃብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

ኢቢሲ የወላይታ ሶዶ ስቱዲዮ እያስመረቀ ይገኛልEBC: Ethiopian Broadcasting Corporation
03/12/2024

ኢቢሲ የወላይታ ሶዶ ስቱዲዮ እያስመረቀ ይገኛል

EBC: Ethiopian Broadcasting Corporation

24/11/2024
የ40 ዓመታትን  ቂም በቀል የሻረው የጎፋዎች የእርቅ ማዕድ  የ"ባራንቼ ዎጋ" ስርዓት በጎፋ ዞን ለ40 ዓመታት በቂም በቀል የሚፈላለጉ ጎሳዎች በፍቅር ተገናኝተዋል ፡፡ለ40 ዓመታት በቂም በ...
22/11/2024

የ40 ዓመታትን ቂም በቀል የሻረው የጎፋዎች የእርቅ ማዕድ የ"ባራንቼ ዎጋ" ስርዓት

በጎፋ ዞን ለ40 ዓመታት በቂም በቀል የሚፈላለጉ ጎሳዎች በፍቅር ተገናኝተዋል ፡፡

ለ40 ዓመታት በቂም በቀል የሚፈላለጉ ጎሳዎች በባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት በፍቅር ተገናኝተዋል።

ከፍትህ ስርዓቱ ጎን ለጎን ባህላዊ የእርቅ ስርዓት እየተበራከተ የመጣውን የወንጀል ድርጊቶችን ከመቀነስና ከመከላከል አኳያ ፋይዳው የጎላ ነው።

በጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ጸሐይ ወረዳ "ሼለካዎና" ጎሳ እና "ካላታ" ጎሳ አባላት መካከል በድንገተኛ የሰው ግድያ ምክንያት በቂም በቀል ለ40 ዓመታት እርስ በእርሳቸው ለመጠፋፋትና ለበቀል ሲፈላለጉና ሲጠባበቁ የነበሩ ቤተሰቦች በጎሳ መሪዎች በባህላዊ ዕርቅ ስነ-ስርዓት ቤተሰብ ሆነዋል።

በሁለቱ ጎሳዎች ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በአከባቢው ባህላዊ የእርቅ ዘዴ በሆነው "ባራንቼ ዎጋ" ስርዓት ተፈቷል።

በሁለቱ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ከ40 ዓመታት በላይ በማህበራዊ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና ከማሳደሩ ባሻገር በአካባቢው የሰላምና ፀጥታ ስጋት ሆኖ ቆይቷል።

የዑባ ንጉስ (ካዎ) ማዳን ጨምሮ ባቦዎች ፣ ከተለያዩ ጎሳዎች የተወጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የባህል መሪዎች ጥላቻን በፍቅር፣ ቂምን በይቅርታ፣ ግጭትን በውይይት፣ ጭካኔን በደግነት እንዲለወጥ በእርቁ ወቅት ሚናቸው የላቀ ነበር።

በዑባ የላ ቀበሌ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል የተፈጸመውን እርቅ ተከትሎ ከሶስት ወር በኋላ በየላ ሻቦ ቀበሌ የተበዳይ ቤተሰቦች ሰርግ ደግሰው የበዳይ ቤተሰቦችን ጠርተዋል።

በርካታ የበዳይ ቤተሰቦች 20 ኪሎ ሜትር አቋርጠው ስጦታ ይዘው ለበዳይ ቤተሰቦች ብቻ አቀባበል ተብሎ በተዘጋጀው ሰርግ ተገናኝተዋል።

በደስታ ተቃቅፈዋል መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ማዕድ ተጋርተዋል። በጋብቻ ምክንያት ከአከባቢው የተለዩ ዘመዳሞች ተገናኝተዋል። አሁን የሁለቱ ጎሳ አባላት ሰላማቸው ተረጋግጦ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ተመልሰዋል።

የሁለቱ ጎሳዎች አባላት በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት በጋብቻ፣ በለቅሶ፣ በሕዝባዊ የውይይት መድረኮች እንደማይሳተፉና በማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ አሉታዊ ጫና እንዳሳደረባቸው ያነሳሉ።

የበዳይ ቤተሰብ አባላት የሆኑት አቶ አካሉ አንቦ እና ወ/ሮ አለሚቱ ጫልጋ እንደተናገሩት፤ ላለፉት 40 ዓመታት የበቀል እርምጃ ይወሰድብናል በማለት ከህጻንነታችን ጀምሮ በሰፈራችን፣ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታና የተለያዩ ማህበራዊ ሁነቶች በሚከናወኑ ቦታዎች በስጋትና በጥርጣሬ ኖረዋል።

አሁን ለተፈጠረው ሰላምና ፍቅር የባህል መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የተበዳይ ቤተሰቦች ምስጋና ይገባቸዋል።

ሰው ከሰው ጋር ከታረቀ ፈጣሪም ከሰው ልጆች ጋር ይታረቃልና ፈጣሪያችን በሰጠን ዕድሜ መልካም መልካሙን በመስራት በይቅርታና በፍቅር የተሞላ ስብዕና ተላብሰን ለሌሎች ምሳሌ መሆን ይገባናል።

የተጣላ በመታረቅ የሰላምና እርቅ መንገድንም በመምረጥ በመካከላችን ወንድማማችነትን ለመፍጠር ይቅር ተባብለናል የሚሉት የተበዳይ ቤተሰብ አባላት የሆኑት አቶ ኢትዮጵያ ቶጶ እና አቶ ሳሙኤል ቶይሳ ናቸው።

ለሰላም የተዘረጋውን እጅ በደስታ መቀበል ትርፋማ ያደርጋል ነው ያሉት።

በይቅርታ እና በፍቅር እንጂ በጥላቻ እና በቂም በተሞላ ስብዕና ምንጊዜም ሰላማዊ ህይወት ሊኖረን አይችልም ሲሉ ገልጸዋል።

በአካባቢው የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለመፍታትና ቤተሰባዊ ግንኙነትን ለመፍጠር ባህላዊ የግጭት አፈታት መንገዶችን መጠቀም ይገባል።

በአከባቢው የባህል መሪ ከሆኑትና በማስታረቁ ተግባር ከተሳተፉት መካከል ባቦ ዱዳ ኩኛከ ኩማ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትን በመጠቀም ቂምና በቀልን በመተዉ በአብሮነት መንፈስ ወደ ነበረበት ሠላምና ከእርስ በእርስ መፈላለግና ከጥርጣሬ ወጥተው ሰላማዊ ህይወት እንዲመሩ በማሰብ ዕርቁን ማስፈጸማቸውን ያወሳሉ።

ባህላዊ የግጭት አፈታት መንገዶችን በመጠቀም በአካባቢው የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለመፍታትና ቤተሰባዊ ግንኙነትን ለመፍጠር በዞኑ በትኩረት እየተሰራ ነወ።

የጎፋ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ድንበሩ ደርቤ በበኩላቸው፤ በዞኑ ሰላምና አብሮነትን ለማስቀጠል ህብረተሰቡ የቆየውን ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ችግሮችን እንዲፈታ በዛላና ዑባ ደብረጸሐይ ወረዳዎች በተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል።

ጥላቻ መለያየትን፣ ግጭትን እና መከራን ሊፈጥር ይችላል፣ ይቅርታ ግን ቂምን ትተን ወደ ፊት እንድንራመድ ያስችለናል ባይ ናቸው። ለዚህ ደግሞ "የጎፋ ባራንቸ ወጋ" አበርክቶ የላቀ ስለመሆኑ ያነሳሉ።

የአካባቢ ሰላምና ጸጥታ ለመጠበቅና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የቀደምት አባቶች ሀብት የሆነው ባህላዊ የእርቅ ስነ-ስርዓት ተጠናክሮ ይቀጥል መልዕክታችን ነው።

አዘጋጅ፡ አይናለም ሰለሞን - ከሳውላ ጣቢያችን

 #ዶ/ር አቤነዘር መካከለኛ ክሊኒክ የዉስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና በተለያዩ ስፔሻሊስት እና በተለያዩ የህክምና ስፔሻሊስት ሐኪሞች እንዲሁም እጅግ ዘመናዊ በሆኑ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በ...
18/11/2024

#ዶ/ር አቤነዘር መካከለኛ ክሊኒክ

የዉስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና በተለያዩ ስፔሻሊስት እና በተለያዩ የህክምና ስፔሻሊስት ሐኪሞች እንዲሁም እጅግ ዘመናዊ በሆኑ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በመታገዝ የህክምና አገልግሎት እንሰጣለን።

👉 የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች

‣ ጠቅላላ የውስጥ ደዌ ህክምና

‣ የልብ ህክምና በዘመናዊ መሳሪያ ( Echo cardiography)

► የስኳርና የደም ግፊት ህከምናና ከትትል

‣ የኩላሊትና የጉበት ህክምናና ክትትል

► የጨጓራ ህከምናና ክትትል

‣ መለስተኛና ድንገተኛ ቀዶ ጥገና

‣ የወንድ ልጅ ግርዛት

‣ የኪንታሮትና ሌሎች ህክምናና ክትትል

‣የእንቅርት ህክምናና ክትትል

‣ የጡት ህክምናና ክትትል

‣ ጠቅላላ የህፃናት ህክምና

‣ የህፃናት የዕድግት ከትትል

‣ የማህፀን ህከምናና ጽንስ ክትትል
👉 አድራሻችን ከከፍተኛ ፍርድ ቤት አለፍ ብሎ ከኪሩቤል ሆቴል 10 ሜትር ወረድ ብሎ ዋናዉ መንገድ ላይ ያገኙናል ።መ

Address

Kanye

Telephone

+251926014623

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofa Through My Camera posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gofa Through My Camera:

Videos

Share