EthioCyber Group

EthioCyber Group Let's stand Up for Ethiopia!

09/10/2024

በነገራችን ላይ ሚስቶቻቸውን ማስደሰት የማይችሉ ሰዎች አይደለም በወንድሞቻቸው ደስታ በልጆቻቸው ደስታ ይበሳጫሉ።
ለዛ ነው የጀግናውን ወንድማቸውን ድል ለሚስታቸው ውሽማ ለመሸለም የሚሽቀዳደሙት። አይ መረገም!😉😉😉😉😉

ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ መክፈል ሊጀምር መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ይህንን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መሰል ነገር መጥቷል፡፡ ይህም ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴ...
07/07/2024

ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ መክፈል ሊጀምር መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ይህንን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መሰል ነገር መጥቷል፡፡ ይህም ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት እንድችሉ ያደርጋል። One invite = 15 Telegram star ✅ እናንተም ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሊንካችሁን በመላክ ተጠቃሚ ሁኑ፡፡ ይህንን እንደ ኤርድሮፕ ሊስት የሚደረግ ሳይሆን ወደ Actual ወይም ትክክለኛ ገንዘብ የሚቀየር ነው፡፡ ለመጀመር https://t.me/major/start?startapp=1907735916

👑Help me to become best of the best in and get some Stars!
15⭐️ invite bonus for you
50⭐️ if you are Premium Major

08/03/2024

Gebrshet_-_Bitew_-_Abawukaw_-_Fano_-_ገብርሸት_-_ቢተው_-_አባውቃው_-_ፋኖ_-_New_Ethiopian_Music_2024_Official_Video

21/05/2023
21/05/2023

እኛ ኦርቶዶክስአውያን ከቤተክርስቲያን ቀኖና ውጭ የሚደረግን ሹመት አጥብቀን እንቃዎማለን!

መረጃ!በምዕራብ አርሲ እና በምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት እየተደረገ ያለው ማሳደድና እሥር እንደቀጠለ ነው።ሕገ ወጡ ቡድን ካሳለፍነው እሑድ ጀምሮ የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ...
07/03/2023

መረጃ!

በምዕራብ አርሲ እና በምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት እየተደረገ ያለው ማሳደድና እሥር እንደቀጠለ ነው።

ሕገ ወጡ ቡድን ካሳለፍነው እሑድ ጀምሮ የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን መውረሩና አገልግሎት እንዲጀመር አገልጋዮቹን እያስገደዱ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

ከዚያም ባለፈ የደብሩ አስተዳዳሪ የነበሩት አባ ተስፋ ጊዮርጊስ የተባሉት ግለሰብ ለምን ከሕገ ወጡ ቡድን ጋር ይሠራሉ ብለው የጠየቋቸውን 8 ወጣቶችን አሳስረዋል።

ከዚያ በተጨማሪ ከሥር በፎቶ ላይ የሚታዩት ግለሰቦች ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍና ወጣቶችን በማሳሰር ላይ ይገኛሉ። በመጀመሪያው ፎቶ ላይ የሚታየው ግለሰብ አቶ አቢቲ ይባላል።

ይህ ግለሰብ የዛሬ ወር ጥር 27/2015 ዓ.ም በሻሸመኔ በነበረው ጭፍጨፋ ላይ ሕገ ወጦቹን ደግፎ ሲመራ ሲያስተባብር የነበረ የማኅበረ ቅዱሳንን አባላትና የሰንበት ት/ቤቱን አገልጋዮችን በግቢው ውስጥ እየጠቆመ ሲያስጨፈጭፍ የነበረ: ከጭፍጨፋው ማግስት እሑድ ጥር 28/2015 ዓ.ም ሕገ ወጦቹ በቅዱስ ሚካኤል ተገኝተው ፎቶ ሲነሱ በነበረበት ወቅት ፎቶ ሲያነሳና በመኪናው እያጀበ ሲመራ የነበረ ግለሰብ ነው።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ባሰባሰበው መረጃ መሠረት ይህ ግለሰብ የ"አባ ገብረ እግዚአብሔር ታደለ" (የሕገ ወጡ ጳጳስ) የፋይናንስ ጉዳዮች አስፈጻሚ ከመሆኑም ባለፈ ቅድስት ቤተክርስቲያን አንክድም ያሉ ታማኝ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ዲያቆናትን "ገብታቹ የምናዛችሁን ብትፈፅሙ ይሻላችኋል አለበለዚያ በፓሊስ ማንቁርታቹ ተይዞ ትገቧታለችሁ" በማለት እስከ ማስፈራራት ደርሷል።

ይህንን ነውረኛ ተግባሩን የሚቃወሙ ምእመናንን በማሳፈስ እና በማሳሰር ላይ ይገኛል።

ሁለተኛው የደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ አሳዬ ይባላሉ።

እኚህ ግለሰብ ከአባ ተስፋ ጊዮርጊስ ጋር በመመሳጠር የሕገ ወጡን አካል ጉዳይ እያስጸሙ ይገኛሉ። ከውጪ በመሆን ወጣቶችን እየጠቆሙ በማሳሰር፣ እንዲሁም የወንጀላቸው ተባባሪ አንሆንም የሚሉ ካህናትን ለፖሊስ በመጠቆም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

በተያያዘ ዜና በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጭሮ ከተማ በምዕራብ ሐረርጌ በጭሮ ከተማ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን እያሳደዱ ማሰሩ እንደቀጠለ መሆኑን ሀገረ ስብከቱ ገልጿል።

በትናንትናው ዕለት የካቲት 27/2015 ዓ.ም አቶ ሄርሞን ከበደ የተባሉ ኦርቶዶክሳዊ እንደታሰሩና ሌሎች ወጣቶችም እየታደኑ እንደሆነ ተገልጿል።
Tewahedo_Media_Center



የምእራብ አርሲ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና በሆነው ደብረ ስብሃት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ተመድቤአለሁ የሚል ግለሰብ መምጣቱ ተገለጸ፡፡በሕገ ወጥነት ...
06/03/2023

የምእራብ አርሲ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና በሆነው ደብረ ስብሃት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ተመድቤአለሁ የሚል ግለሰብ መምጣቱ ተገለጸ፡፡
በሕገ ወጥነት ከተሾሙት “ኤጲስ ቆጶሳት” መካከል አባ ቻፒ ከተባለው ግለሰብ የተመደብኩ የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ነኝ የሚል ግለሰብ በሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ባለስልጣኖችና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቤተ ክርስቲያኑ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
ግለሰቡ በደብረ ሰብሃት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ነባር አገልጋዮች አገልግሎት እንዲሰጡ የማይመጡ ከሆነ እኛ እንመድባለን ማለታቸውንና የደብሩ አለቃ አባ ተስፋ ጊዮርጊስም ተቀብለው መመሪያውን እያስፈጸሙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ነገር ግን ብፁዓን አባቶች የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጋር በተወያዩት መሠረት ቀጣይ ሳምንት የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአበው ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ታቅዶ እንደነበረ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። መረጃው የማኅበረ ቅዱሳን ነው።

የ4ኛውን ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሥልጠና ምደባከየካቲት 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመደባችሁ፣ ስለቀጣይ ሰልጣኞችና ሌሎችን መረጃዎች ከታች ባለው ቴሌግራም እየገ...
20/02/2023

የ4ኛውን ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሥልጠና ምደባ
ከየካቲት 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመደባችሁ፣ ስለቀጣይ ሰልጣኞችና ሌሎችን መረጃዎች ከታች ባለው ቴሌግራም እየገባችሁ ማየት ትችላላችሁ ተብላችኋል።
https://t.me/+51OjE34GoUY5NzQ0

አዲስ አበባ ውስጥ ደላሎች መኪኖች ሲያሻሽጡ የሴት መኪና ነች የሚሏት ነገር አለ ። ያው ሴቶች ጠንቃቃ ስለሆኑ ፡ በደንብ የተያዘ መኪና ነው ለማለት ነው ። እና ይህችም ሄሊኮፕተር የሴት ሄሊ...
17/02/2023

አዲስ አበባ ውስጥ ደላሎች መኪኖች ሲያሻሽጡ የሴት መኪና ነች የሚሏት ነገር አለ ። ያው ሴቶች ጠንቃቃ ስለሆኑ ፡ በደንብ የተያዘ መኪና ነው ለማለት ነው ። እና ይህችም ሄሊኮፕተር የሴት ሄሊኮፕተር በሏት ፡ አዲስ አትሁን እንጂ ይዞታዋ እንደምታዩት ነው ። ሞዴሏ AgustaWestland AW109 ሲሆን ዋጋዋ ደግሞ 350 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ነው ።
በሌላ አነጋገር ፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር ዛሬ ገዛኋቸው ካላቸው የቻይና አውቶብሶች ዋጋ እኩል ነው ። ከላይ ካለችው ሄሊኮፕተር ስር ያሉት ሁለቱ ደግሞ Enstrom F-28 ይባላሉ ሁለቱም ሞዴላቸው ተመሳሳይ ነው .. እና የነሱ ዋጋ ደግሞ ገዥ ከሆናችሁ እስከ 340 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ድረስ ይሸጡላችኋል ፡ ጊዜው የቴክኖሎጂ ነውና ሞዴላቸውን ፅፋችሁ ጉግል ብታደርጉት እነዚህንና መሰል ሄሊኮፕተሮችን የአዲስ አበባ መስተዳድር ከቻይና አንዱን አውቶብስ ገዛሁበት ባለው ዋጋ ሄሊኮፕተር ትገዛላችሁ ። ምክንያቱም 350 ሺህ ዶላር ማለት በጣም ብዙ እና ከአውቶቡስ አልፎ ሄሊኮፕተር ሁሉ ሊገዛ የሚችል ገንዘብ ስለሆነ ነው ።
ከቻይና የተገዙት አውቶቡሶች ዋጋ ከመጋነኑ የተነሳ ፡ ለአንድ አውቶቡስ ወጣ የተባለው ሶስት አውቶቡስ የሚገዛ ገንዘብ ነው ። 350 ሺህ ዶላር የቻይና አውቶቡስ ዋጋ ሳይሆን የሄሊኮፕተር ዋጋ ነው ። እና ሰሚ ባይኖርም ፡ የሀገር ሀብት ፡ የምስኪን ህዝብ ላብ ነውና ለምን እንላለን ።
via Wasihun

14/02/2023

እስረኞች የሚፈቱት እስራቱም የሚቆመው ለታሰሩለት ዓላማ በአንድነት ስንታገል ብቻ ነው!
*********************************************************************
እስረኞች የሚፈቱት እስራቱም የሚቆመው ለታሰሩለት ዓላማ ሁላችንም ስንሰራ የታሰሩበት ዓላማ ሲፈታ ብቻ ነው። ከዛ ውጭ እከሌ ታሰረ እከሌ ተፈታ የሚለው ዋናውን ጉዳይ ያስረሳናል እንጅ እስረኞችን አያስፈታምም የቤተክርስቲያናችን ቀዳሚ አጀንዳ እሄ አይደለም። እንኳ እስር እስከ ሞት ድረስ እንታገላለን ስንል የነበረው ለቤተክርስቲያን አንድነት ለአባቶቻችን ክብር ለአምላክ ፍቅር ነው። ወንድሞቼ እናስተውል ስለ እስረኞች ሳይሆን ስለ ቤተክርስቲያ መደፈር እንጩህ? ተዋህዶን ለማጥፋት ስለተነሱበት መንገድና እነማን ለማጥፋት እንደተነሱ እየጠቀስን ስሁት ስራቸውን እናጋልጥ። በአንድነት ተዋህዶ ሀይማኖቴን አትንኩ፣ከቤተክርስቲያን ላይ እጃችሁን አንሱ የተፈጠረውን ችግር አባቶቻችን መፍታት ይችላሉ፣ መንግስት ህግን ብቻ ያስከብር ከቤተክርስቲያን ላይ እጁን ያንሳ፣ ህገወጦችን ያስቁም፣ አባቶቻችንን ማዋከብ ያቁም ልንል ይገባል። እንደዛ ብለን ስንጮህ ምን አልባት በጩኸታችን ልክ የታሳሪዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። እሄን የሚያደርጉት አንድም ከዋናው አጀንዳችን ወጥተን እከሌን ፍቱት እከሌ ተፈታ እከሊትን ሊያስሯት ነው በሚል አጀንዳ እንድንጠመድ አንድም ድምጽን ለማፈን ነው። ነገር ግን ሁላችንም አንድ መሆናችንን አንድ ምህረት አብ ሲታሰር 1000 ምህረታቦች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ሲገነዘብ ዋናውን ጉዳይም እስረኞችንም ይፈታሉ። እመኑኝ የኦርቶዶክስ ልጆችና ወዳጆች እሄ ነው እኛንም ሀይማኖቻችንንም ነጻ የሚያዎጣው።





የአባቶች በረከታቸው ይድረስብን!
14/02/2023

የአባቶች በረከታቸው ይድረስብን!




13/02/2023

አንድ ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትርያርክ

13/02/2023

አጀንየን አላቅም።
መንግስት በኦርቶዶክስ ላይ የሚያደርገውን አስነዋሪ ጣልቃ ገብነትና አድልዎ ለመቆም ይገባል። በምእመኖቿ ላይ የሚያደርሰውን መዋከብና እስር ሊያቆም ይገባል።




የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሁሉም ዘርፍ ሁሉንም አይነት ሚዲያ ያስፈልጋታል። ሀይማኖታዊውን አስተምህሮ ብቻ የሚያስተምር፣ በኢኮኖሚው አለም ቤተክርስቲያኗን መሰረት አድርጎ የሚተነትን...
13/02/2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሁሉም ዘርፍ ሁሉንም አይነት ሚዲያ ያስፈልጋታል። ሀይማኖታዊውን አስተምህሮ ብቻ የሚያስተምር፣ በኢኮኖሚው አለም ቤተክርስቲያኗን መሰረት አድርጎ የሚተነትን፣ በፖለቲካው፣ ከምንም በላይ ግን በሳይቨሩ አለም። በዚህ ዘመን በደንብ መሰራት ያለበት ሳይቨሩ ላይ ነው። በተለይ አባቶቻችን ስለ ልጆቻቸው ቤተክርስቲያን ስለ ምእመኗ ብቻ እንዳያስቡ መምህራን ሀይማኖታዊ አስተምሮዋቸውን ብቻ እንዳያስተምሩ እንቅፋት የሚሆንባቸው የሳይቨሩ አለም ጦርነት ነው። አባቶቻችንንና ቤተክርስቲያንን ከሳይቨር ጦርነት ለመጠበቅ ጠንካራ የሳይቨር ግሩፕ ማቋቋም ግድ የሚልበት ጊዜ አሁን ነው። ቤተክርስቲያንንና የቤተክርስቲያኒቱን አባቶች እነሱ ባላሰቡበት መንገድና ምን አልባትም በሚቀነባበሩ የሀሰት መረጃዎች ሰለባ እንዳይሆኑ እንዴት መጠበቅ አለብን? ሁሉም ሊያስብበት የሚገባ በተለይም የቤተክርስቲያን ነገር ያሳስበኛል የሚል ኦርቶዶክስ በደንብ ሊያጤነው የሚገባ ጉዳይ ነው።




ደብል ካስት ተዘጋጅቷል¡ የተወገዘው የግለሰቦች ስብስብ ደግሞ ሌላ የአትርሱኝ ዜና ማውጣቱን ሰማን። በትላንትናው ዕለት በሕገ ወጥ ሲመተ ጵጵስናው ላይ ከተሳተፉ ግለሰቦች መሐል የይቅርታ ጥያቄ...
13/02/2023

ደብል ካስት ተዘጋጅቷል¡
የተወገዘው የግለሰቦች ስብስብ ደግሞ ሌላ የአትርሱኝ ዜና ማውጣቱን ሰማን።
በትላንትናው ዕለት በሕገ ወጥ ሲመተ ጵጵስናው ላይ ከተሳተፉ ግለሰቦች መሐል የይቅርታ ጥያቄ ያቀረቡ አንድ ሰው ዜና ከተዘገበ እና ሌሎቹም ይቅርታ ለመጠየቅ ቢፈልጉ እንኳን በር ተቆልፎባቸው እንደተቸገሩ መሰማቱን ብጹዕ አቡነ አብርሐም ከተገለጹ በኋላ የውጉዛኑ ብድኑ፤ የተዋንያን አባላት ሊመናመኑብኝ ነው የሚል ስጋት ውስጥ መውደቁን መታዘብ ይቻላል።
በዚህም መሰረት ትላንት ማምሻውን ባወጡት መረጃ ተጨማሪ "ኤጲስ ቆጶሳትን" ከተለያዩ ቦታዎች አውጣጥተው ለመሾም ያዘጋጇቸውን ግለሰቦች ስልጠና በመስጠት ላይ እንዳሉ ገልጸዋል።
እንግዲህ እነዚህ የሚጎሉ ተዋንያንን ለመሙላት ቅድመ ዝግጅት መኾኑ ነው።
ይቅርታ ጠይቀው ለሚመለሱት ኹሉ በርህራሔ መቀበላችን ክርስቲያናዊ ግዴታችን መኾኑ እንደተጠበቀ ኾኖ፤ ያው ተውኔቱ በደብል ካስት ጭምር የታገዘ ነው ብለን ከመሳቅ እና በድፍረታቸው ከመሳቀቅ በቀር ምን እንላለን?

Tutorial Time! part 1*********************How to Block Liar's and unfair page?ውሸታምና ሚዛናዊ ያልሆኑ የፌስቡክ ገጾችን እንዴት ማ...
13/02/2023

Tutorial Time! part 1
*********************
How to Block Liar's and unfair page?
ውሸታምና ሚዛናዊ ያልሆኑ የፌስቡክ ገጾችን እንዴት ማስወገድ ይቻላን?
Via: ECG(EthioCyber Group)

በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ለሁለትዮሽ ውይይት ሩሲያ/ሞስኮ መግባቱ ተገለፀ !!!የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም (ኢትዮ ሳበር ግሩፕ/ኢሳግ...
13/02/2023

በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ለሁለትዮሽ ውይይት ሩሲያ/ሞስኮ መግባቱ ተገለፀ !!!

የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም (ኢትዮ ሳበር ግሩፕ/ኢሳግ)

በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ከብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር ለመወያየት እና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም መልዕክትን ለማድረስና በሁለትዮሽ የአብያተክርስቲያናቱ ቀጣይ ግንኙነት ላይ ውይይት ለማድረግ ሞስኮ መግባቱ ነው የተገለፀው።

የልዑካን ቡድኑ አባላት የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጊዜያዊ እና ቋሚ ፕሮጀክቶች መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

12/02/2023

እኔ ግን ሲሞቅ የምሞቅ መቀዛቀዝ የምቀዘቅዝ አጀንዳየን በስንዴና በማይጠቅም ማደናገሪያ የምቀይር አይደለሁም። ምክንያቱም የቅዱሳን አባቶቼ ልጅ ነኝ።
መንግስት ለአባቶቻችን የገባውን ቃል ይፈፅም። ኦርቶዶክስአውያንን ማዋከብ ያቁም የሰራቸውን ይፍታ ከቤተክርስቲያን ላይ እጁን ያንሳ።




መንግስት ቃሉን ይጠብቅ መንግስታዊ ሀላፊነቱን ይወጣ። የታሰሩትን ይፍታ ምእመናንና አባቶችን ማዋከቡን ያቁም።
12/02/2023

መንግስት ቃሉን ይጠብቅ መንግስታዊ ሀላፊነቱን ይወጣ። የታሰሩትን ይፍታ ምእመናንና አባቶችን ማዋከቡን ያቁም።



"ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፦የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለኹና ከእኔ ጋራ ደስ ይበላችኹ ይላቸዋል።" ሉቃስ 15:6
12/02/2023

"ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፦የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለኹና ከእኔ ጋራ ደስ ይበላችኹ ይላቸዋል።" ሉቃስ 15:6

ሰበር ዜና+++++++++++++++++++++++++++++++++++++በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት አባ  ንዋየሥላሴ አክሊሉ...
12/02/2023

ሰበር ዜና
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት አባ ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሢኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በይቅርታ ደብዳቤያቸውምሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሁኑን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው እለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።

EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

11/02/2023

መንግስት የጀመረውን ማን አለብኝነትና ጭፍን አካሄድ ዞር ብሎ ቢያይ መልካም ነው።

_and_Convince



Dirección

Buenos Aires
Salta
1876

Página web

Notificaciones

Sé el primero en enterarse y déjanos enviarle un correo electrónico cuando EthioCyber Group publique noticias y promociones. Su dirección de correo electrónico no se utilizará para ningún otro fin, y puede darse de baja en cualquier momento.

Compartir


Otros Canal de televisión en Salta

Mostrar Todas