Nan Promotion

Nan Promotion Social Media Promotion & News based on Ethiopia Nyala

01/01/2025
-ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ ማንቹሪያን ደርቢ ጨዋታዉን ድል አድርጓል።-አማድ በዉድድር ዘመኑ ሁለተኛዉን የሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።-የፔፕ ጋርዲዮላዉ ማንቸስተር ሲቲ ካለፉት 11 ጨዋታዎች በ አን...
15/12/2024

-ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ ማንቹሪያን ደርቢ ጨዋታዉን ድል አድርጓል።
-አማድ በዉድድር ዘመኑ ሁለተኛዉን የሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።
-የፔፕ ጋርዲዮላዉ ማንቸስተር ሲቲ ካለፉት 11 ጨዋታዎች በ አንዱ ብቻ ነዉ ማሸነፍ የቻሉት።
-በጨዋታዉ ሜሰን ማዉንት በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ወጥቷል።
-በዛሬዉ ጨዋታ የማንቸስተር ዩናይትድ ጀግና የነበረዉ አማድ ከጨዋታዉ በኋላ "ፈጣሪ ይመስገን አሁን በቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ነዉ ትኩረታችን" ሲል ተናግሯል።

🙏🙏🙏የዓመቱ ምርጥ ባል * ኩላሊቱን * ለግሶ * አገባት ሀብታሙ ይባላል ለሩሀማ ለ4ዓመታት በኩላሊት ህመም ስትሰቃይ በነፃ  በራይድ ወደ ህክምና ቦታዋ ስያመላልስ ቆይቶበመጨረሻም አንድ ኩላሊ...
09/12/2024

🙏🙏🙏

የዓመቱ ምርጥ ባል

* ኩላሊቱን
* ለግሶ
* አገባት

ሀብታሙ ይባላል ለሩሀማ ለ4ዓመታት በኩላሊት ህመም ስትሰቃይ በነፃ በራይድ ወደ ህክምና ቦታዋ ስያመላልስ ቆይቶ

በመጨረሻም አንድ ኩላሊቱን ለግሷት

ይህው ባልም ሆኖ አገባት::

እንዲህ አይነትም ሰው አለ ለካ 🥰

ጥንዶች ፈጣሪ በልጆች ይባርካችሁ

❤️❤️❤️🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

04/12/2024

ሁላችንም ነውራችን ግንባራችን ላይ ቢፃፍ ሰው ፊት የማያስቆም ሚሊየን ሀጥያት አለን።
ፈጣሪ ነውራችንን ደብቆልን ስለሰው አናቡካ!

ነብስ ይማር 😢የተወዳጁ አርቲሥት ሠለሞን ቦጋለ አባት  ስርአተ ቀብር በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ። የአርቲስቱ ወዳጅ ጓደኞች እና መላ ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ተፈጸመ::ለአርቲስት ሰለሞን እ...
26/11/2024

ነብስ ይማር 😢

የተወዳጁ አርቲሥት ሠለሞን ቦጋለ አባት ስርአተ ቀብር በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ። የአርቲስቱ ወዳጅ ጓደኞች እና መላ ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ተፈጸመ::
ለአርቲስት ሰለሞን እና ቤተሰቦቹ መፅናናት እመኛለሁ 🙏

ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚመጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪ አየር ላይ ህይወቱ አለፈባሳለፍነው አርብ November 15 ቀን 2024 ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣  በበ...
19/11/2024

ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚመጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪ አየር ላይ ህይወቱ አለፈ

ባሳለፍነው አርብ November 15 ቀን 2024 ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣ በበረራ ቁጥር ET 500 ፣ በAirbus A350 አውሮፕላን ተሳፋሮ የሚመጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ መንገደኛ አየር ላይ እንዳለ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ህይወቱ አለፈ።

እድሜው ከ45 እስከ 50 ዓመት የሚገመተው ይህ ተሳፋሪ ከእህቱ አጠገብ አብሮ ቁጭ ብሎ በመብረር ላይ እያለ ፣ አውሮፕላኑ ነዳጅ ሞልቶ እና የበረራ ሰራተኞችን ቀፍሮ ከሮም፣ ጣልያን ተነስቶ ወደ አሜሪካ ጉዞ ከጀመረ ከአንድ ሰዓት በኋላ እህቱ ለበረራ አስተናጋጆች ወንድሟ የመተንፈስ ችግር እንዳጋጠመው ትነግራቸዋለች፣ የበረራ አስተናጋጆቹም የህክምና ባለሞያዎች ካላችሁ ለእርዳታ እንፈልጋችኋለን ብለዉ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ፣ በበረራው ዉስጥ የነበሩ ወደ 5 የሚጠጉ የህክምና ባለሞያዎች ወደ ግለሰቡ መጥተው ህይወቱን ለማትረፍ ተረባርበው የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ቢሰጡትም ግለሰቡ አየር ላይ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን በበረራ ላይ የነበሩ ተሳፋሪዎች ለመዝናኛ ሚዲያ አስታውቀዋል ።

መዝናኛ መጽሔት ዋሽንግተን ዲሲ

***
የአቶ ወንደሰን መኮንን

(ኃይለማርያም)

1977 -2024

የሽኝትና የቀብር ሥነ ስርአት ፕሮግራም

ረቡዕ Nov 20 2024 የሽኝት ፕሮግራም ከ 3:00 pm እስከ 7:pm

21453 Epicerie Plaza Sterling VA20164

በማግስቱ ሐሙስ Nov 21 2024

ፀሎተ ፍትሀት በደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ካቴድራል ከ 4:00 am ጀምሮ

1001 Ruritan Circle, Sterling, VA 20164

የቀብር ሥነስርአት በ 12:00 pm በፌርፋክስ ሚሞሪያል ፓርክ ይፈፀማል

9900 Braddock Rd Fairfax VA 22032

መስትዬ የኔ ደርባባ ቆንጂዬ እግዚአብሔር  ልጆችሽን  ለቁም ነገር ያብቃልሽ የኔ ዉድ
13/11/2024

መስትዬ የኔ ደርባባ ቆንጂዬ እግዚአብሔር ልጆችሽን ለቁም ነገር ያብቃልሽ የኔ ዉድ

ከአርቲስት ገነት ንጋቱ እና ከረ/ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ጀዋሬ የትዳር ህይወት ምን ትማራላችሁ?
11/11/2024

ከአርቲስት ገነት ንጋቱ እና ከረ/ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ጀዋሬ የትዳር ህይወት ምን ትማራላችሁ?

Beautiful Ethiopian Actress Kalkidan Tibebu
10/11/2024

Beautiful Ethiopian Actress Kalkidan Tibebu

Lake BasakaBenuna Village
10/11/2024

Lake Basaka
Benuna Village

እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሼር አድርጉት እባካችሁ ተባበሩ 🙏🙏🙏ቪዛ ያለበት 3 ፖስፖርት ጠፍቷል 🇺🇸 ወደ አሜሪካ ዛሬ በረራ ነበራቸው ግን ካልተገኘ መቅረታቸው ነው1. የአባት ስም :- እሸ...
09/11/2024

እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሼር አድርጉት እባካችሁ ተባበሩ 🙏🙏🙏

ቪዛ ያለበት 3 ፖስፖርት ጠፍቷል

🇺🇸 ወደ አሜሪካ ዛሬ በረራ ነበራቸው ግን ካልተገኘ መቅረታቸው ነው

1. የአባት ስም :- እሸቱ ኢሳያስ
2. የሚስት ስም :- ሜሮን ናጆ
3. የልጅ ስም :- ንፅሀፍቅር እሸቱ

ዛሬ ቅዳሜ ማታ ከቦሌ-ወደ አሜርካ ለሚኖራቸው በረራ ከዎላይታ ሶዶ ወደ አድስ አበባ የተጓዙ ቤተሰብ
ዶክሜንታቸውን በአአ ታክሲ ውስጥ ረስተው ስለወረዱ

በምትችሉት መንገድ ሁሉ እንድትረዱና መልካምነታችሁን እንድታሳዪን በምታመልኩት ስም ተጠይቃችሗል።

ከቤተሰብ የደረሰ መልዕክት:: ሼር አድርጉ🙏

ስልክ_ቁጥር 0935497085
0945306045 የወረታ ከፋይ ነን

እባካችሁ ዛሬ በረራ ነበራቸው ግን ካልተገኘ
መቅረታቸው ነው::

የሚገርሙኝ ዘመን ተሻጋሪ ቃላት - ከእመጓ መፅሐፍ________________________________- በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)    (ገፅ 162-163)በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተ...
07/11/2024

የሚገርሙኝ ዘመን ተሻጋሪ ቃላት - ከእመጓ መፅሐፍ
________________________________

- በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)
(ገፅ 162-163)

በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተዉታላችሁ፡፡ ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፤ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፤ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፤ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ፡፡ ምኞታችሁ ልክ የለውም፤ አምሮታችሁ ብዙ ነው፡፡

የአማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፡፡ ተዉ የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፤ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፤ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ፡፡ …

ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ፤ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም፡፡ ሁሉ አላችሁ፤ ግን ባዷችሁን ናችሁ፡፡ ሃይማኖት እንጅ እምነት የላችሁም! …

መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ መጀመሪያውን ብቻ ሞጭልፈህ ትተኸኝ ትሄዳለህ፡፡ ጥበብን ‹‹ሀ ግዕዝ›› ብዬ ላስተምርህ ብሞክር፣ መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ በመሰልቸት ‹‹ሆ ሳብዕ›› ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ፡፡

የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተልከፈከፈ የተማሪ ኮፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል፡፡

ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፣ ሰርታችሁ ሀብት ስታፈሩ፣ ከላይ የሆናችሁበትን ሃገር ለቃችሁ፣ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ፡፡ ትቀጥላላችሁ፣ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ፡፡ ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ፡፡ በጽኑ ታማችኋል!

ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ፡፡ ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፤ እናም ወደ ኋላ ስለታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል፡፡

ስለሆነም ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ። የአሸናፊነትንና የተሸናፊነትን ትርጉም በአንድ ላይ የያዙ ሃውልቶች ታቆማላችሁ፡፡ ለግልጽነትና ለነጻነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ ዕርቃን ወደ መሆን ወረዳችሁ፡፡

ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ፡፡ በዚህ ዓለም ጥድፊያ ታማችኋል፡፡ ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፤ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፤ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ አገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ፡፡

በቁማችሁ የናቃችሁትን የሀገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ፡፡ ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ፡፡

ግብዝነታችሁ መጠን የለውም፡፡ ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፤ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቂያ ታስባላችሁ፡፡ ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖሩም፡፡ ዘመናችሁም በምልልስና በመዋተት ያልቃል፡፡

ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም፡፡

ፈጣሪ የልጆቿን ልቦና ወደ ተቀደሰው ሥፍራ ይመልስ!

ኢትዮጵያችንን አብዝቶ ይባርክ!

ለደራሲው ከከበረ ምስጋና ጋር፣

መልካም ጊዜ!
via:Facebook

Address

40A Street, AL DAGHAYA/113
Dubai
999041

Telephone

+971585186765

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nan Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share