SELAM TV ሰላም ቲቪ

SELAM TV ሰላም ቲቪ ሰላም ባለበት እውነት አለ

Sleepover in Mazdalfa ♥️No palaces, no luxury buildings, no families and no expensive shedsA night where the rich and th...
15/06/2024

Sleepover in Mazdalfa ♥️
No palaces, no luxury buildings, no families and no expensive sheds
A night where the rich and the poor are equal
We plough the earth and cover ourselves is a mercy from Allah, Glory be to His servants
And your arm is rotting
A sleep is incomparable to anyone who wants to be considered
Very tired, she sleeps a deep sleep.
As if on the Day of Judgment, you find yourself among the dead, white bodies shaking the whole body for the greatness of the situation
Everything in His wisdom, Glory be to Allah, she wakes up from sleep with joy, collecting stones and preparing to walk and stretch the journey after the morning prayer directly to the feelings of Mona

O Allah, grant us Hajj to your Holy House for many years and a long time
And every longing, O Lord of the worlds 🤍🕋

ከአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ ቤት የተሰጠ መግለጫ ። ሀገራችን ኢትዮጲያ ብዝሐ ሐይማኖት እና ብዝሐ ብሔሮች በአንድ ላይ ተሰባስበው የሚኖሩባት የጋራ ቤታችን መሆኗ ሁላችንም የሚ...
09/05/2024

ከአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ ቤት የተሰጠ መግለጫ ።

ሀገራችን ኢትዮጲያ ብዝሐ ሐይማኖት እና ብዝሐ ብሔሮች በአንድ ላይ ተሰባስበው የሚኖሩባት የጋራ ቤታችን መሆኗ ሁላችንም የሚያኮራ እና በባለቤትነት ስሜት የምንኖረው ፀጋችን ነው ። በሀገር ግንባታ ሂደት የተለያዩ ብሄሮችና እምነቶች በመደጋገፍ የጋራ ጠላት በገጠማቸዉ ጊዜ አብረዉ በመቆም በጋራ ደማቸዉን አፍስሰዋል፤ አጥንታቸዉን ከስክሰዉ የተለያዩ እምነቶች በሰላምና በችግር ጊዜ አብረዉ በመቆም ለሀገር መጽናት ዉድ ዋጋ ከፍለዉ የጋራ የሆነችን ሀገራችንን አስረክበዉናል፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስለሞችም የዚህ ታሪክ ወራሽ በመሆናችን አባቶቻችን በከፈሉት ዋጋና ባስረከቡን ሀገር ልጆቻቸዉ ኩራት
ይሰማናል ።

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ክልላችን ያለበትን ሁኔታ በመረዳት አባባሽ ሁኔታዎችን እና መንገዶችን በመተዉ ለክልላችን ሠላምና መረጋጋት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ። ከፍተኛ ምክር ቤቱ የአማራ ክልል ሙስሊሞችን ሁለንተናዊ ውክልና ወስዶ እንደሚንቀሳቀስ አንድ ተቋም የክልሉን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድን በመምርጥ ለክልሉ ሰላምና ልማት የተሻለውን መንገድ መርጦ ሠላምን እና መረጋጋትን ለመፍጠር አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ላይ ያለ ተቋም ነው።

በተለያዩ ቡድኖች አማካኝነት በሚነሳ ግጭት ህዝባችንን የከፋ ዋጋ እያስከፈለዉ እንደሆነ ብንረዳም በልዩ ሁኔታ በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ፣ መፈናቀል፣ ዘረፋ፣ መታገትና መገደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነዉ፡፡

የክልሉ መጅሊስ የምእምኑን ስቃይና እንግልት ግድያ ፣ የመስጅዶች እና ሃሪማዎች መቃጠልና መነጠቅ፣ የምዕምኑን መፈናቀል በየጊዜው እየተከታተለና እየመዘገበ ማስረጃ እያደራጀ ለሚመለከተዉ አካል መረጃ እየሰጠ የመጣ ቢሆንም ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ይመጣሉ በሚል እምነት ፣ በሆደ ሰፊነት በመታገስ ፣ የሀገርን ህልውና ትልቁ ግብና የክልላችን ልማት አማራጭ የሌለው ጉዳይ በማድረግ ለሚፈጠሩት ችግሮች ሁሉ በቅርበት ካሉ ከሚመለከታቸዉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመነጋገርና በመወያየት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በማሳሰብ እዚህ ደርሷል ።

በተለይም “ሙስሊሞች በዴሞግራፊ እና በፖለቲካ ሚና አናሳ ናቸው” ተብለው በታሰቡባቸው ቦታዎች ሙስሊሞችን በጅምላ ማፈናቀል፣ መግደል፣ ማሳደድ፣ ሃብትና ንብረታቸውን መንጠቅና ማውደሙ እየተባባሰ መጥቷል። ሙስሊም በዝ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ደግሞ በእጅ አዙር የብሄር ግጭት መነሻ የሚመስል ሁለንተናዊ ቀውስን በመፍጠር በተለየ መልኩ መስጅዶችን፣ ሃሪማዎችንና የሃይማኖት መሪዎችን ትኩረት ያደረገ ጥቃት ይፈጸማል።

በተለያዩ አካባቢዎች በአንዳንድ “ የሀይማኖት አስተማሪዎች “ ሀላፊነት የጎደለዉ ስብከት እየተሰበከ አብሮ የሚኖርን ህዝብ አሳዛኝ በሆነ መልኩ እምነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲፈፀም ሞክኒያት ሆኗል ።

ምንም እንኳን ከላይ የገለፅናቸዉ ለሀይማኖታችን ቀናኢ ነን ብለዉ የሚያስቡ አንዳንድ ግጭት አምጪ እና አባባሽ ግለሰቦች መሰል እኩይ ተግባር ቢፈጽሙም ሰፊዉ የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ወገናችን ዛሬም ቢሆን ለሙስሊም ወገኖቹ አለኝታ በመሆን በአብሮነት እንደሚኖር የታወቀ ሀቅ ነዉ ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ባሉ የሃይማኖት አባቶች፣ በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ ቅስቀሳዎች በሙስሊሞች ላይ ጥቃት የሚያነሳሳ እጅግ አደገኛ ቅስቀሳ ፣ ፕሮፓጋንዳና ስብከት በማናለብኝት ሲደረጉ ቆይተዋል ። ይህም የክልሉን ሙስሊሞች በተናጠልም ፣ በቡድንም ፣ እንደ ማህበረሰብም ለከፍተኛ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ሲጋለጡ እያስተስተዋልን ነው ።

የክልሉ ሙስሊሞች ለዘመናት ትውልዶቻቸውን ካስቀጠሉባቸው ይዞታዎቻቸውና ርስቶቻቸው ፣ ታሪክና ማንነታቸውን ካበቀሉበት የትውልድ ቀያቸውና ክልላቸዉ በየጊዜው በሚነሱ አሻጥሮች ፣ ቀጥተኛ የማፈናቀል ጥቃቶች እንዲሰደዱ ሲደረግ ሀገራቸውን ጥለው የት እንዲሄዱ እንደተፈለገ ግራ ያጋባል ።

በደቡብ ጎንደር ዉሻ ጥርስ ሀሪማ ፣ በማእከላዊ ጎንደር ፉርቃና ደልዳሊት ሀሪማዎች ፣ አምባአገር ሀሪማ ፣ እንዲሁም መስጅዶች ላይ ጥቃት የደረሰ ሲሆን ሰባሀ ሀሪማ በ 2012 ቤተ-ከርስቲያን ተሰርቶበታል ። በተጨማሪም በአዊ ዞን በዚገም ወረዳ መስጅዶች ተቃጥለዋል ። በተጠቀሱት አካባቢዎች በሚገኙ ሙስሊሞች ላይም ከዚህ በፊት ይደረግ ከነበረዉ እገታና ዘረፋ በጊዜዉ ማስቆም ባለመቻሉ ሁኔታዉ አድጎ ቀያቸዉን ለቀዉ እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን እያየን እየሰማን ነዉ ። በኦሮሚያ ልዩ ዞን የተፈጠረዉን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተልን ሲሆን በሌሎች ሀሪማዎች ላይ ተመሳሳይ ስጋቶች እንዳሉ እንዲታወቅ እንፈልጋለን ።

በተጨማሪም በአንበሳሜ ( ደራ ) ወረዳ ወፍ አርግፍ ቀበሌ ከ800 አመት በላይ እድሜ ያለዉ ጥንታዊ መስጅድና የሙስሊሞች መካነ-መቃብርን በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በቅርስነት የተመዘገበዉን ቦታ በማፍረስ የአካባቢዉን ሙስሊም በማፈናቀል ቦታዉን ቤተ-ክርስቲያን የሰሩበት መሆኑን ስንሰማ በሀሪቱ ያሉ አማኞች እንዲያዉቁትና መንግስትም ሆነ ቤተ-ክርስቲያኗ በዚህ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ እልባት እንዲሰጡ ለመጠየቅ እንወዳለን ።

ይህ ሁሉ ጥቃት ሲፈጸም በርካታ ሃይሎች እጀቸው እንዳለበት እንረዳለን ። የህዝባችን ደህናነትና የሰላም ዋስትና በማረጋገጥ በኩል መንግሥት እየወሰደዉ ያለዉ እርምጃ የሚበረታታ ቢሆንም ነገሮችን በሰላም ለመፍታት በሚያደርገዉ ሆደ ሰፊነትና ታጋሽነት እድሉን ለተጨማሪ ጥፋት የሚጠቀሙ የተወሰኑ ሀይሎቾ የመንግስትን መዋቅር እና ማህበረሰቡ በአመኔታ የሰጣቸዉን ስልጣን ለአጥፊዉ ቡድን አላማ እስከመጠቀም የደረሱበት ሁኔታ እንዳለ ተስተዉሏል ። በዚህም መንግስት ታችኛዉን መዋቅር መፈተሽ እንዳለበት ለማስታወስ እንወዳለን ።

በመሆኑም የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይህ ነገር እየተባባሰ ከዚህም በላይ በሀገርም ሆነ በምእምኑ ላይ ከፍተኛ የህይወት ፣ የቁስና የስነ-ልቦና ጉዳት ከማድረሱ በፊት በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን ። ይህንን ዘረፋ፤ ስቃይ ፣ እንግልት፤ እገታ ፣ መገደልና መፈናቀል በጽኑ እናወግዛለን ፡፡

ከዚህም በላይ ይህን እኩይ ተግባር ለማስቆም መንግስት፣ ሰላማዊዉ የክልሉ ህዝባችን፣ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ወገናዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ይህ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ግፍና ግድያ ለዘመናት አብሮና ህብረት ፈጥሮ የኖረዉን ህዝባችንን አብሮነት ለማናጋት የታሰበ ስለሆነ በጋራ እንድንታገለዉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በክልላችን የሚገኙ መሳጅዶች የጁመዓ መልእክቶቻችሁን በዚሁ ችግርና መከራ ውስጥ ስላሉት ወገኖቻችን በማድረግ፤ ለደረሰብንና እየደረሰብን ለሚገኘው መከራም ሰደቃ በየመስጅዱ አቅመ-ደካሞችን በማገዝ እንዲሆን በተጨማሪም በግፍ ለተገደሉ ደረሳዎችና ምእመናን ሰላተል ጋኢብ እንዲሰገድላቸው እንደ አካባቢያችን ተጨባጭ ይፈፀም ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን ።

በዚህ መከራና እንግልት መሀል ለሞቱ ምእምኖቻችን አሏህ ጀነትን እንወፍቃቸዉ እየጠየቅን ለቤተሰቦቻቸዉ ሶብርን ( መፅናናትን ) እንመኛለን ።

ረመዳን አንዴት እንቀበል
02/03/2024

ረመዳን አንዴት እንቀበል

የፓርላማ አባል እና የግብርና ሚንስትር ደኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ ባደረሱበቸው ጫና መስጂድ እንዳይሰሩ መደረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ..ሀሩን ሚዲያ፥ ታህሳስ 11/2016....
22/12/2023

የፓርላማ አባል እና የግብርና ሚንስትር ደኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ ባደረሱበቸው ጫና መስጂድ እንዳይሰሩ መደረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ..
ሀሩን ሚዲያ፥ ታህሳስ 11/2016..
የፓርላማ አባል እና የግብርና ሚንስትር ደኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ ባደረሱበቸው ጫና መስጂድ እንዳይሰሩ መደረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።
የቀድሞው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝዳንት የነበሩትና የቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን አመራር የነበሩት ፕሮፌሰር ኢያሱ አካባቢያቸው ላይ መስጅድ መሰራቱን ባለመፈለጋቸው ምክንያት የአካባቢው ሰው ህጋዊ ካርታ ያለውን መስጅድ መስራት እንዳልቻለ ተገልጿል።..
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አግራዉ በሚል ስያሜ የሚታወቀው መስጂድ በትላንትናው እለት ጊዚያዊ የመስጂድ አጥር ግንባታ ለማድረግ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት የወረዳው አመራሮች ከከንባ ጽ/ቤት ተደውሎልናል በሚል ግንባታው እንዲቆም አድርገዋል ።..
ያለ ህግ አግባብ እንዲታገድ ስለተደረገበት ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ሲጠይቁ "የአከባቢው ማህበረሰብ ቦታው ላይ መስጂድ እንዳይገነባ ፒትሽን ፈርሞ ስላስገባ ነው ካርታውን አምክነን ሌላ ተለዋጭ ቦታ እንሰጣችኃለን" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።..
ያለምንም የህግ አግባብ የመስጂዱ ግንባታ በመታገዱ ማህበረሰቡ በጊዚያዊነት የመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ድንኳን በመወጠር ሰላቱን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።..
© ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j

14/12/2023

በ ደቡብ አፍሪካ የሚገኝው የ ነጃሺ ትረስት ሲያስተምራቸው የቆዩትን ተማሪዎች ምርቃት

23/06/2023

መላው የዘምዘም ቤተሰብ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ ያላችሁ!!!
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

ዘምዘም ባንክ በመዲናችን የፋይናንስ ተቋማት ማእከል ተብሎ በሚጠራው ቦታ የባንኩን ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ለመገንባት የሚውል ቦታ ተረከበ።
ዘምዘም ባንክ ዛሬ በሻራተን አዲስ ሆቴል የሚድያ ሰዎች፣ የባንኩ ሸሪአና ቦርድ አባላት፣ የባንኩ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ባንኩ እስካሁን ስላስመዘገባቸው ስኬቶች እንዲሁም ወቅታዊ ደረጃው ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል። በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ባንኩ የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ መገንቢያ የሚውል መሬት በመዲናዋ የፋይናንስ ማእከል ስፋቱ 4,135.66ካ/ሜ የሆነ ባታ ከአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እንደተፈቀደለት እና የሊዝ ስምምነት እንደፈፀመ አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም ባንካችን የህዝብን ፍላጎት መሰረት አድርጎ የተመሰረተ ባንክ እንደመሆኑ፣ ባንኩ ለሚያስገነባው ህንጻ Design Concept (የንድፍ ጽንሰ ሃሳብ) ህዝባዊ ተሳትፎ ባደረገ መልኩ እንዲሆን ሁኔታዎችን ያመቻቸ ሲሆን፣ ማንኛውም ግለሰብ ወይንም ድርጅት ዘምዘምን በጋራ እንገንባ ተብሎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የባንኩ ቴሌግራም ቻናል ላይ ወይንም ባንኩ በሚገልጻቸው ሌሎች አማራጮች ሃሳቡን መግለጽ የሚችል መሆኑንም አሳውቀዋል።
በመጨረሻም ባንካችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላቀረብነው የቦታ ጥያቄ በበቂ ትኩረት አፋጣኝ ምላሽ በመስጠቱ በባንኩ ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እንገልጻለን።

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ ያላችሁ!!!

ዘምዘምን በጋራ እንገንባ ….
ዘምዘም የማይነጥፍ የእድገት ምንጭ

ሹሐዳዖች ሰማዕታቶች የቀብር ስነስርዓታቸው በኮልፌ የሙስሊሞች መካነ መቃብር በርካታ ወንድሞቻቸው በተገኙበት እየተካሔደ ነው ።  አላህ (ሱወ ) ይቀበላቸው።
03/06/2023

ሹሐዳዖች ሰማዕታቶች የቀብር ስነስርዓታቸው በኮልፌ የሙስሊሞች መካነ መቃብር በርካታ ወንድሞቻቸው በተገኙበት እየተካሔደ ነው ።
አላህ (ሱወ ) ይቀበላቸው።

በአንዋር መስጂድ የነበሩ በቁጥር እጅግ በርካታ ሰዎች በሰላም እንዲወጡ ተደርጓል!!!የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ እና የበላይ አመራሮች ...
02/06/2023

በአንዋር መስጂድ የነበሩ በቁጥር እጅግ በርካታ ሰዎች በሰላም እንዲወጡ ተደርጓል!!!

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ እና የበላይ አመራሮች በአንዋር መስጂድ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የማረጋጋት ስራ በመስራት አንድ ሸሂድ (መስዋእት) የሆነ ሙስሊም እና ጉዳት የደረሰባቸውም ወደ ሆስፒታል እንዲሆዱ አድርገዋል።

የጁመዓ ሰላት ለመስገድ በአንዋር መስጂድ የተገኙና በተፈጠረው ችግር ምክንያት በመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ታግተው የቆዩ ምእመናን ወደየቤታቸው በሰላም ከሸኙ በኃለሰ አንድም ሰው እንዳልቀረ ካረጋገጡ በኃላ አመራሮቹ የመስጂዱን ቅጥር ጊቢ ለቀው መጥተዋል።

ም/ቤታችን ለሞቱት ጀነት እንዲወፍቃቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ለተጎዱትም ቶሎ ማገገምን ይቸር ዘንድ አላህን እንጠይቃለን።

በቀጣይም ህዝበ ሙስሊሙ እየተፈፀሙበት ያለውን አላግባብ የመብት ጥሰቶች በተገቢው መልኩ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ጉበኤ ውሳኔ መሰረት የተቋቋመውን ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴን እና ም/ቤታችን የሚሰጠውን አቅጣጫ እንደ መሪ ተቋም በማክበር ተግባራዊ እንዲያደርግ እንጠይቃለን!!!

አዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

ሰበር ዜናበታላቁ አንዋር መስጅድ በዛሬው እለት የተካሔደ ተቃውሞ ባይኖርሞ የመንግስት የጸጥታ ሀይል ግን ወደ ህዝቡ ቀጥታ መሳርያ እየተኮሰ እንደሆነ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ለሀሩን ሚዲያ ገልጸ...
02/06/2023

ሰበር ዜና

በታላቁ አንዋር መስጅድ በዛሬው እለት የተካሔደ ተቃውሞ ባይኖርሞ የመንግስት የጸጥታ ሀይል ግን ወደ ህዝቡ ቀጥታ መሳርያ እየተኮሰ እንደሆነ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ለሀሩን ሚዲያ ገልጸዋል። እስካሁን ቁጥራቸው በቅጡ ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ ሰዎችም መጎዳታቸውን አብረው ገልጸውልናል። ጥቃቱ ወደ ሴቶች መስጅድም የዘለቀ ሲሆን ሴት ምዕመናኖች ላይም የጸጥታ አካሉ የጥይት እሩምታ መክፈቱን ለማወቅ ችለናል። ዝርዝሩን እየተከታተልን ሲሆን መረጃዎችን ወደናንተ የምናድርስ ይሆናል።

© ሀሩን ሚዲያ

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሸገር ከተማ እየተፈፀመ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ በጋራ በመሆን አውግዘዋል::
01/06/2023

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሸገር ከተማ እየተፈፀመ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ በጋራ በመሆን አውግዘዋል::

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሸገር ከተማ እየተፈፀመ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ በጋራ በመሆን አውግዘዋል::በቀጣይም ይህን የመብት ጥሰት ለማስቆም በሚደረገው ሂደት ሁ.....

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሸገር ከተማ እየተፈፀመ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ በጋራ በመሆን አውግዘዋል::
01/06/2023

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሸገር ከተማ እየተፈፀመ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ በጋራ በመሆን አውግዘዋል::

ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተላለፈ መልእክትግንቦት 24, 2015 የከተማችን ህዝበ ሙስሊም የነገን ጁመዐ በሰላም እንዲያሳልፍ የተላለፈ ጥሪ ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ...
01/06/2023

ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተላለፈ መልእክት

ግንቦት 24, 2015

የከተማችን ህዝበ ሙስሊም የነገን ጁመዐ በሰላም እንዲያሳልፍ የተላለፈ ጥሪ

ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደም ሀይማኖታዊ መብቱን ለማስከበር ብሎም በሀገር ደረጃ ለተደረገው የስርአት ለውጥ ፈር ቀዳጅ በመሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀድሞ የነበረውን አምባገነን ስርአት ለመለወጥ ፊት-አውራሪ በመሆን ታግሏል።

የስረአት ለውጥ ከተስተዋለ ወዲህ በተለይ በጠቅላይ ሚነስትራችን በክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ የሚመራው የሀገራችን መንግስት ለህዝበ ሙስሊሙ ቀድሞ የነበሩ የሀይማኖት መብት ረገጣዎች እንዲቀንሱ ፣ ህዝባችን ከመንግስት ጋር የነበረው ግንኙነት እንዲሻሻል ፣ ማህበረሰባችን ለሌሎች መጠቀሚያ እንዳይሆን በማድረግ መንግስታዊ ሀላፊነቱን በመወጣት በመሪ ድርጅቱ ስር እንዲጠለል አስተዋፆ አበርክቷል።

መንግስትም ህዝበ ሙስሊሙ ሲጠይቃቸው ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል ተቋሙን በአዋጅ የማቋቋም መብት፣ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ፣የእምነት ተቋማት ቦታዎችን በህጋዊ መልኩ የማግኘት መብት በማመቻቸት ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎችን አበርክቷል።

ከላይ በጥቂቱ የተጠቀሱ ፋይዳዎች ለምን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደ ዜጋ ተከበረለት ፣ ለምን ተጠቃሚ ሆነ የሚሉ በእምነቱ ላይ የውስጥ ጥላቻ ያነገቡ፣የግል ፍላጎት ያላቸው፣ድብቅ የፖለቲካ አስተሳሰባቸውን ለማሳካት እንዲሁም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተጠቃሚነቱ ከጎላ ፣ሰላሙን ከተጎናፀፈ ማየትን የማይችሉ መስማትን የማይወድ ፣አካላት ሌት ተቀን በመስራት ማህበረሰባችንን ከመንግስት ለመነጠል እየሰሩ ይገኛሉ ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ (ሲቲ) የመስጅድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ማህበረሰባችን ያቀረበውን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎች ማለትም የመስጅድ ፈረሳው ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ፣የፈረሱትም መስጅዶች ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንዲመለስ መሪ ድርጅታችን መጅሊስ ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት በተለያዩ ደረጃዎች ከሚገኙ የመንግስት አካላት ጋር እያደረገ ይገኛል።

በመሆኑም መንግስትም የፍትህን መጓደል የጥያቄውን አሳሳቢነት፣በሸገር ሲቲ አስተዳደር በውይይት ላይ ያልተመሰረተን አካሄድን ከግንዛቤ በማስገባት ለተከሰተው የመብት ጥሰት ፍትህ የማስፈን ሚናውን በአፋጣኝ እንደሚወጣ ተስፋ እናደርጋለን።

በመጨረሻም ህዝባችን ኮሚቴው የደረሰበትን እስኪያሳውቀን ድረስ ውጤቱን በትእግስትና በዱአ እንዲጠባበቅ ጥሪያችንን እያቀረብን

የነገ የጁመአ ሰላት የከተማችን ሙስሊሞች በሁሉም መስጅዶች በሰላም ሰግዶ ወደ ቤቱ በሰላም እንዲመለስ መልእክታችንን እያስተላለፍን ፣
በከተማችን የሚገኙ ኢማሞች በሰላምና በትእግስት ዙሪያ የጁመአ ኹጥባ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

መንግስትም ጉዳዩን በፍጥነት እልባት እንዲሰጥ እና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከእስር እንዲለቅ አጥብቀን እንጠይቃለን።

01/06/2023

የሰላም ቲቪን አዲሱን የፌስቡክ ገፅ ላይክ ይበሉ

የተለያዩ ኢስላማዊ እና ሀገራዊ ፕሮግራሞችን ሲያደርሰን የነበረው ሰላም ቲቪ የፌስቡክ ገፅ በጠላፊዎች በመሰረቁ አዲሱን ገፃችንን ላይ በማድረግ ፣ፔጃችንን ለሌሎችም በማስተዋወቅ ዳግም ፕሮግራሞቻችን እና መረጃዎቻችን ለብዙሃን እንዲዳረስ ሼር በማድረግ ይተባበሩን ።

የፌስቡክ ፣ የዩቲውብ እና የቴሌግራም ቻናላችን በመቀላቀል ተደራሽ እንዲሆን የበኩላችን እንወጣ

https://www.facebook.com/selaamtv2

https://www.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RA

https://t.me/ media
https://t.me/selaam2015

ሰላም ባለበት እውነት አለ

31/05/2023

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሸገር ከተማ እየተፈፀመ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ በጋራ በመሆን አውግዘዋል::

በቀጣይም ይህን የመብት ጥሰት ለማስቆም በሚደረገው ሂደት ሁሉ የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል::

በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የኦሮሚያ ክልል መንግስት በመስጂዶች ላይ እየፈፀመ ያለውን የማፍረስ ዘመቻ እና ሙስሊሙን የመናቅ ተግባር በከፍተኛ ደረጃ እያወገዙት ይገኛሉ::

06/12/2022

የሰላም ቲቪን አዲሱን የፌስቡክ ገፅ ላይክ ይበሉ

የተለያዩ ኢስላማዊ እና ሀገራዊ ፕሮግራሞችን ሲያደርሰን የነበረው ሰላም ቲቪ የፌስቡክ ገፅ በጠላፊዎች በመሰረቁ አዲሱን ገፃችንን ላይ በማድረግ ፣ፔጃችንን ለሌሎችም በማስተዋወቅ ዳግም ፕሮግራሞቻችን እና መረጃዎቻችን ለብዙሃን እንዲዳረስ ሼር በማድረግ ይተባበሩን ።

የፌስቡክ ገፃቸውን፣ የዩቲውብ እና የቴሌግራም ቻናላቸውን በመቀላቀል በርቱ እንበላቸው

https://www.facebook.com/selaamtv2

https://www.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RA

https://t.me/ media
https://t.me/selaam2015

ሰላም ባለበት እውነት አለ

09/07/2022

Address

Johannesburg

Telephone

+27645355686

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SELAM TV ሰላም ቲቪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to SELAM TV ሰላም ቲቪ:

Videos

Share

Category