Kembata World Wide Media Network

Kembata World Wide Media Network KWWMN registered inSouth Africa non-profit-organization.withheadquartersin Johannesburg,South Africa
(13)

Kembata worldwide Media Network registered in South Africa based as an independent and non-organization with headquarters in Johannesburg, South Africa. The organization is made up mainly of ambassadors, doctors, other professions that help in achieving to serve the Ethiopian community in South Africa It is an institution that provides genuine information and access to those in need.

በአርባምንጭ የመስክ እና ከተማ ጉብኝት እንዲሁም የ #አረንጓዴዓሻራ መርሐ ግብር በምስል፡፡
06/07/2024

በአርባምንጭ የመስክ እና ከተማ ጉብኝት እንዲሁም የ #አረንጓዴዓሻራ መርሐ ግብር በምስል፡፡

አርባ ምንጭ በኢትዮጵያ ግዙፉን ሆስፒታል ነገ ታስመርቃለችሄሊኮፕተር የሚያሳርፈውና በዓመት ለሰባት ሚሊዮን ዜጎች የሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ኮምፕርሄ...
05/07/2024

አርባ ምንጭ በኢትዮጵያ ግዙፉን ሆስፒታል ነገ ታስመርቃለች

ሄሊኮፕተር የሚያሳርፈውና በዓመት ለሰባት ሚሊዮን ዜጎች የሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነገ ይመረቃል።

ሆስፒታሉ የሄሊኮፕተር አምቡላንስ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ ከህንጻው አናት ላይ ማረፊያ የተዘጋጀለት መሆኑን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ትምህርትና ሕክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ዳይሬክተር ብርሃኑ አንዳርጌ (ዶ/ር) ለኢፕድ አስታውቀዋል።

በ25 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈው ሆስፒታሉ ደረሳቸውን የጠበቁ 600 አልጋዎች እንዳሉት ዶክተር ብርሃኑ አስረድተዋል። ሙሉ ለሙሉ ወደስራ ሲገባ 100 ስፔሻሊስት ሐኪሞችና በአጠቃላይ ከሁለት ሺህ በላይ ሰራተኞች አገልግሎት ይሰጣሉ።

ዶክተር ብርሃኑ እንደገለጹት፤ ሆስፒታሉ የኦክሲጅን ከማምረት ባለፈ ኦክሲጂኑን በየክፍሉ የሚያዳርስ መስመር፣ ዲጂታል የኤክስሬይ ማሽኖች፣ ሲቲ ስካን፣ የኤም አር አይ፣ ዘመናዊ የአልትራሳውንድ ማሽኖች ተገጥመውለታል።

የተሻሻሉ የደም መመርመሪያ ማሽኖች፤ የተለያዩ ላብራቶሪዎችን ያጠቃለለው ሆስፒታሉ የጽኑ ህሙማን ክፍሎች፣ የድንገተኛ አገልግሎት ህክምና መስጫዎች፤ በተመላለሽና በተኝቶ ሕክምና የተለየያዩ የጤና አገልግሎቶች ይሰጥበታል ብለዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና በአጎራባች ክልሎች የሚገኙ ከሰባት ሚሊየን በላይ ዜጎች የውስጥ ደዌ፣ የቀዶ ጥገና፣ የሕፃናትና እናቶች፣ የማህፀንና ጽንስ፣ ከአንገት በላይ፣ የአጥንትና የሥነ-አዕምሮ እንዲሁም የተለያዩ ሕክምናዎች እንደሚያገኙበት አብራርተዋል።

በምርመራ ደረጃ ዘመኑ የደረሰባቸው ቴክኖሎጂዎችን የያዙ የምርመራ ማሽኖችን በሆስፒታሉ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

በምረቃው መርሃ ግብር የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የሆስፒታሉ ግንባታ በመጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል። #ኢፕድ

1 ሺህ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ(አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28/ 2016 ዓ.ም) በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።በዛሬው...
05/07/2024

1 ሺህ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

(አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28/ 2016 ዓ.ም) በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ ዜጎች ውስጥ 810 ወንዶች፣ 171 ሴቶች እና 19 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 48 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ56 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ለ8ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 430 ተማሪዎች አስመረቀበዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ለ8ኛ ጊዜ...
05/07/2024

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ለ8ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 430 ተማሪዎች አስመረቀ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ለ8ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 430 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል፣ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪና እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶክተር ዳዊት ለገሰ፥ "ተመራቂዎች ትምህርት ማጠናቀቅና መመረቅ የመጨረሻ ግብ አለመሆኑን በመገንዘብ በተማራችሁበት የሙያ መስክ ለሀገር ሠላም እና ዕድገት የድርሻችሁን ልትወጡ ይገባል" ብለዋል።

የዋቸሞ የኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ፥ ተመራቂዎቹ በሚሰማሩበት የሥራ መስክ መንግሥትንና ሕዝብን በታማኝነትና በቅንነት በማገልገል የዩኒቨርስቲውን ስም የሚያስጠሩ መልካም ተግባራትን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ በዚህ ዓመት 365 ተማሪዎችን በመደበኛ እና በተከታታይ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ፤ 65 ተማሪዎችን ደግሞ በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።

ካምፓሱ በ6 ኮሌጆች በ19 የትምህርት ክፍሎች በተከታታይ እና በመደበኛ ትምህርት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ 5,162 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።

ካምፓሱ እስካሁን 4309 ተማሪዎች ማስመረቁን ከከምባታ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የህዝብን ቅሬታ በመስማት የኢሚግሬሽን ስራ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እና ተቋማዊ ለውጦችን በማከናወን በጥቂት ወራት ውስጥ ብዙ ማሻሻያዎች እየተተገበሩ ይገኛሉ:: ለምሳሌ...
05/07/2024

የህዝብን ቅሬታ በመስማት የኢሚግሬሽን ስራ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እና ተቋማዊ ለውጦችን በማከናወን በጥቂት ወራት ውስጥ ብዙ ማሻሻያዎች እየተተገበሩ ይገኛሉ:: ለምሳሌ ያህል:-

- በቀን በኦንላይን 900 ፓስፖርት መስጠት የነበረውን አገልግሎት ወደ 1,700 ማድረስ ተችሏል፣
- ቀደም ብለው የተጠራቀሙ ጥያቄዎችን አስተናግዶ ለመጨረስ በተሰራ ስራ 1 ሚሊዬን ፓስፓርት ታትሞ ገብቶ እስከ 87% ተሰራጭቷል፣
- የተከማቹ ቅሬታዎች 100% ተፈትተዋል፣
- በኢትዮዽያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ 10,467 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል፣
- ሃሰተኛ ማስረጃ የያዙ 18,000 ሰዎች ቅጣት እንዲከፍሉ ተደርጓል፣
- በ188 ሀገሮች የቪዛ አገልግሎት በመክፈት ለ819,278 ተስተናጋጆች e-visa ጨምሮ የቪዛ አገልግሎት ተሰጥቷል
- ለ4,276,474 ግለሰቦች በአየርና በየብስ መዳረሻ ጣቢያዎች አገልግሎት ተሰጥቷል

በአሁኑ ወቅትም ተቋሙን የዘመነ እና አገልግሎቱን በጥራት የሚሰጥ ተቋም ለማድረግ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው::

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሰራርና የህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑ ተገለጸአዳማ ፤ ሰኔ 28/2016 በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሰራርና የህግ ማዕቀ...
05/07/2024

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሰራርና የህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑ ተገለጸ

አዳማ ፤ ሰኔ 28/2016 በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሰራርና የህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።

የድርጅቶቹ የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄዷል።

በዚሁ ጊዜ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ሙሐመድ አብዶ ድርጅቶቹ ውጤታማ መሆን እንዲችሉ የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየቱን ገልጸዋል።

በተለይም ምክር ቤቱ የልማት ድርጅቶቹ ውጤታማነት ላይ ማነቆ የሆኑ ህጎችና አሰራሮች እንዲሻሻሉ የአሰራርና የህግ ማሻሻያዎች ማድረጉን ተናግረዋል።

ይህም የሀብት አጠቃቀምና አገልግሎት አሰጣጡን፣ የፋይናንስና ሀብት አሰባሰብ እንዲሁም ገቢ የማመንጨት አቅማቸውን ማሻሻሉን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መስራት እንዲችሉ መደረጉን ፕሮፌሰር መሀመድ ተናግረዋል።

በቀጣይም ገቢ የማመንጨት አቅማቸውን ማሳደግ እና በፋይናንስ ጤናማነትና የሒሳብ ወቅታዊነትን ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሃይለሚካኤል በበኩላቸው፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ማገዝ እንዲችሉ በተሰራው ስራ ውጤት እየተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።

ድርጅቶቹ ከለውጡ በፊት በአሰራር፣ በአስተዳደርና በአመራር ሰጪነት ችግር ሲስተዋልባቸው እንደነበር ገልጸው፤ በድርጅቶቹ በፋይናንስ አሰራር ውጤታማነት፣ በመረጃ እና ሒሳብ አያያዝ ወቅታዊነት ላይ መሻሻሎች እየታየ ነው ብለዋል።

በተሰራው ሥራ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት፣ በኢትዩ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል።

በዚህም በመጠናቀቅ ላይ ባለው በጀት ዓመት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከ37 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን አቶ ሀብታሙ አንስተዋል።

የልማት ድርጅቶቹ ውጤታማነትና ተወዳዳሪነት እያደገ መምጣቱን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በዚህም ገቢያቸውና ትርፋቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

በፓሪስ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው ተለዩ  በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላ...
05/07/2024

በፓሪስ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው ተለዩ

በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው መለየታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በዚህም ፡-

800 ሜትር ሴቶች አትሌት ፅጌ ድጉማ፣አትሌት ሐብታም ዓለሙ፣አትሌት ወርቅነሽ መለሰ፣አትሌት ንግስት ጌታቸው (ተጠባባቂ)

1ሺህ 500 ሜትር በወንዶች አትሌት አብዲሳ ፈይሳ፣አትሌት ሳሙኤል ተፈራ፣አትሌት ኤርሚያስ ግርማ፣አትሌት ታደሰ ለሚ (ተጠባባቂ)

1ሺህ 500 ሜትር ሴቶች አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣አትሌት ብርቄ ሃየሎም፣አትሌት ድርቤ ወልተጂ፣አትሌት ሂሩት መሸሻ (ተጠባባቂ)

5ሺህ ሜትር ወንዶች አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት፣አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣አትሌት አዲሱ ይሁኔ፣አትሌት ሰሞን ባረጋ (ተጠባባቂ)

5ሺህ ሜትር ሴቶች አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣አትሌት መዲና ኢሳ፣አትሌት እጅጋየሁ ታዬ፣አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ (ተጠባባቂ)

10 ሺህ ሜትር ወንዶች አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣አትሌት ሰለሞን በረጋ፣አትሌት ቢኒያም መሀሪ (ተጠባባቂ)

10 ሺህ ሜትር ሴቶች አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣አትሌት ፎቴን ተስፋዬ፣አትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ፣አትሌት አይናዲስ መብራቱ (ተጠባባቂ)

3ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች አትሌት ለሜቻ ግርማ፣አትሌት ሳሙኤል ፍሬው፣አትሌት ጌትነት ዋለ፣አትሌት አብርሃም ስሜ (ተጠባባቂ)

3ሺህ ሜትር ሴቶች አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ፣ አትሌት ሎሚ ሙለታ

በማራቶን ሴቶች አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣አትሌት አማኔ በሪሶ፣አትሌት መገርቱ ዓለሙ፣አትሌት ጎይቶቶም ገ/ስላሴ (ተጠባባቂ)

በማራቶን ወንዶች አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣አትሌት ሲሳይ ለማ፣አትሌት ዴሬሳ ገለታ፣ አትሌት ታምራት ቶላ (ተጠባባቂ)

20 ኪሎ ሜትር ርምጃ በወንድ አትሌት ምስጋና ዋቁማ በመሆን ተለይተዋል፡፡

"ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች በጎነትን በማስረጽና አብሮነትን በማጠናከር የዜግነት ኃላፊነታቸውን ሊወጡና አሻራቸውን በተግባር ሊያኖሩ ይገባል" - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ...
05/07/2024

"ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች በጎነትን በማስረጽና አብሮነትን በማጠናከር የዜግነት ኃላፊነታቸውን ሊወጡና አሻራቸውን በተግባር ሊያኖሩ ይገባል"
- የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

(አርባምንጭ፣ ሰኔ 28/ 2016 ዓ.ም) የ2016 ዓ.ም የወጣቶች የክረምት ወራት ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መክፈቻ መርሀ-ግብር በደቡብ ኢትዮጵያ አርባምንጭ ከተማ ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለፁት፤ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለዉ እንደ ስሙ በበጎ ልቦና ከንፁህ ልብ፤ ከንፁህ ህሊና ከንጹህ ፍቅርና ፍጹም መልካምነት የመነጨ በነጻ የሚሰጥ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰዎች ውስጣቸው ከሚሰማቸው ሰብዓዊ አመለካከት በመነሳት ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማትና ለአካባቢ ደህንነት ነፃ ጊዚያቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና በጎ አመለካከታቸውን ተግባር ላይ የሚያውሉበት በምላሹም ከማህበረሰቡ ጠቃሚ ዕሴቶች፣ የህይወት ክህሎት፣ ልምድና ባህሎችን የሚቀስሙበትም ነው ብለዋል።

በዕለቱ ክብርት ሚኒስትር ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የ2016 ዓ.ም ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አርማና መለያ ባንዲራ አስረክበዋል።

ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በጎነትን በማስረጽና አብሮነትን በማጠናከር የዜግነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና አሻራቸውን በተግባር እንዲያኖሩም ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ወጣቶቹ ለበጎ ስራ በተንቀሳቀሱበት አካባቢ ሁሉ የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ አደራ ብለዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጎነትና አብሮነትን ለማጠናከር እንደሀገር ለሚደረገው ጥረት ስኬታማነት ሁሉ የበኩሉን እገዛና ድጋፍ እንደሚያደርግ ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገልፀዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሠ (ዶ/ር) በበኩላቸው በጎነት በኢትዮጵያውያን ህሊና ውስጥ ያለ ነገር ግን በአግባቡ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ትልቅ ሀብት መሆኑን ጠቅሰው ከለውጡ ማግስት ወዲህ ግን በጎፍቃድን በሰው ተኮር ስራዎች ላይ በማዋል ብዙ በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን መድረስ መቻሉን ጠቅሰዋል።

አክለውም በክልሉ ወጣቶቹ ያስጀመሩትን የበጎ ፈቃድ ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

የደም ልገሳ እና ሌሎች የበጎ ፈቃድ ተግባራት እንደሚከናወን ተጠቁሟል።

የወጣት አብርሃም አበራ  የቀብር ስነስርዓት በዛሬው እለት በትውልድ ሀገሩ ሀደሮ ከተማ ላይና በተመሳሳይ ሰዓት በደቡብ አፍሪካ እጅግ በጣም በርካታ የደርባንና አካባቢዋ ማህበረሰብም በመሰባሰብ...
05/07/2024

የወጣት አብርሃም አበራ የቀብር ስነስርዓት በዛሬው እለት በትውልድ ሀገሩ ሀደሮ ከተማ ላይና በተመሳሳይ ሰዓት በደቡብ አፍሪካ እጅግ በጣም በርካታ የደርባንና አካባቢዋ ማህበረሰብም በመሰባሰብ ለወጣት አብርሃም ያለውን ድንቅ ፍቅር አሳይቷል።

ነብስ ይማር😭

ተረጂነት የሀገርን  ክብር እና ሉአላዊነትን ዝቅ እንደሚያደርግ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ካጋጠመን ችግር ለመውጣት ጠንክሮ መስራት ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው። በማዕከላዊ ኢትዮጵ...
05/07/2024

ተረጂነት የሀገርን ክብር እና ሉአላዊነትን ዝቅ እንደሚያደርግ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ካጋጠመን ችግር ለመውጣት ጠንክሮ መስራት ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጸጋዎቻችንን በማልማት፣ በምግብ እራሳችንን ለመቻል እንተጋለን ተረጂነትን እንቀለብሳለን በሚል መሪ ሀሳብ የአመራር የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው

በምክክር መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት ከአንድ ወር በፊት ከክልሉ አመራር ጋር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እንዴት መሻገር አለብን በሚል ዝርዝር ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

በክልሉ የተደረገውን ውይይት በየደረጃው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ማስጨበጥ መቻሉን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ተረጂነት ክብርን እና ሉአላዊነትን ዝቅ እንደሚያደርግ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ተግባር መገባቱን አስረድተዋል።

ተረጂነት በተግባር እና በአስተሳሰብ ደረጃ መቀልበስ እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መድረስ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቁመዋል።

በመድረኩ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የክልሉ አመራር ተረጂነትን ለመቀልበስ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተዘጋጀ እቅድ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እያደረገ ነው።

#የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን

የኢትዮጵያና የብራዚልን የንግድ ሚዛን ለማሻሻል እንደሚሰራ ተገለፀኢትዮጵያ ወደ ብራዚል የምትልካቸውን ምርቶች መጠን በማሳደግ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ሚዛን ለማሻሻል በቅንጅት ...
05/07/2024

የኢትዮጵያና የብራዚልን የንግድ ሚዛን ለማሻሻል እንደሚሰራ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ወደ ብራዚል የምትልካቸውን ምርቶች መጠን በማሳደግ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ሚዛን ለማሻሻል በቅንጅት እንደሚሰራ የንግድና ቀጣናዊ ትስስትር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ከብራዚል ልኡካን ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትና የንግድ ልውውጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ብራዚል የብሪክስ አባል እንደመሆናቸው የንግድ ግንኙነታቸውንና ወዳጅነታቸውን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ወደ ብራዚል የሚላኩ ምርቶችን በማሳደግ እንዲሁም ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ባላት እምቅ ሀብት ብራዚላዊያን መጥተው መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነትን ይበልጥ ማጎልበት እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል።

በውይይቱ በቁም እንሰሳት ንግድ ዘርፍ ከብራዚል ልምድ ለመውሰድ፣ በግብርናው እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች በጋራ ለመስራት እና ግንኙነታቸውን ለማጎልበት በቀጣይነት ለመመምከርና ስምምነቶችን ለመፈራረም መግባባት ላይ መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እያሱ ኤልያስ (ፕ/ር) ከብራዚል የግብርናው ዘርፍ አመራሮች ጋር በዘርፉ በሁሉም መስኮች በተለይም በተፈጥሮ ሀብት ልማት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አሰናበቱየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን ...
05/07/2024

አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አሰናበቱ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) አሰናበቱ።

ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ.ም መሾማቸው ይታወሳል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) አሰናብተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የእሳት አደጋዉ እሳቱ 🔥 ጠፍቷል!ዛሬ ንጋት 11:49 ሰዓት ላይ በለሚኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 አበበች ጎበና ፊት ለፊት በንግድ ሱቆች ላይ ተነስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋ...
05/07/2024

የእሳት አደጋዉ

እሳቱ 🔥 ጠፍቷል!

ዛሬ ንጋት 11:49 ሰዓት ላይ በለሚኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 አበበች ጎበና ፊት ለፊት በንግድ ሱቆች ላይ ተነስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የእሳት አደጋዉ በንግድ ሱቁቹ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ ተገልጿል።

እሳቱ በአካባቢዉና በተለይም በንግድ ሱቆቹ አጠገብ ወደሚገኘዉ ነስር መስጂድ ላይ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል።

በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተመላክቷል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኦንላየን ሲኒማ ተመረቀበሀገራችን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማበልፀግ የሚታወቀው ኢግልላየን ቴክኖሎጂ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር "ቴሌ ቲቪ" የተሰኘ በኢትዮጵያ የመ...
05/07/2024

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኦንላየን ሲኒማ ተመረቀ

በሀገራችን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማበልፀግ የሚታወቀው ኢግልላየን ቴክኖሎጂ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር "ቴሌ ቲቪ" የተሰኘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኦንላይን ሲኒማ አስመርቋል።

ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የደንበኞችን ምቾት የሚጨመሩ፣ የኑሮ ዘይቤያቸውን የሚያዘምኑ እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚያስችሉ የተለያዩ የዲጂታል አሰራሮችን እውን በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት በመዝናኛው ዘርፍ የፊልም አፍቃሪያን በእጅ ስልካቸው፣ በታብሌት፣ በስማርት ቴሌቪዥን እንዲሁም ኮምፕዩተር አማካይነት የፈለጉትን ሀገርኛ ፊልም በቀላሉ በቴሌብር ክፍያ በመፈጸምና በመከራየት ማየት የሚችሉበትን አዲስ አሰራር አመቻችቷል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኙትን “6 ሰዓት ከሌሊቱ” እና “ትዝታ” የተሰኙ ሁለት የአማርኛ ፊልሞችን ክፍያቸውን በቴሌብር በመፈጸም ካሉበት ቦታ ሆነው መመልከት የሚችሉ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን በደስታ እንገልጻለን ብሏል ኢትዮ ቴሌኮም።

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ ተጀመረየመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ...
04/07/2024

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ ተጀመረ

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጀምሯል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ በልማት ትብብር፣ በጋራ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ ምክክሮች ይካሄዳሉ፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል፤ ለድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች የጋራ መፍትሄ በማስቀመጥ የሁለቱን ወንድማማች ሀገራት ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የድንበር እና የውጭ ዜጎች ጉዳይ ዳይሬክተር አምባሳደር አንቲፓስ ኒዮክ በበኩላቸው፣ መድረኩ የጋራ ጉዳዮችን ለመፍታት ጠቀሜታው የጎላ ስለመሆኑ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኀበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ ለህፃን ቸርነት ሄኖክ(በቅኖች አምላክ ምንም ማድረግ ባትችሉ ሼር ሳታደርጉ አትለፉ!)ከ29 ሳምንታት እርግዝና በሗላ የተወለዱት መንትዮቹ ለወላጆቻቸው ደስታ፡ እምነትና ...
04/07/2024

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ ለህፃን ቸርነት ሄኖክ
(በቅኖች አምላክ ምንም ማድረግ ባትችሉ ሼር ሳታደርጉ አትለፉ!)

ከ29 ሳምንታት እርግዝና በሗላ የተወለዱት መንትዮቹ ለወላጆቻቸው ደስታ፡ እምነትና ተስፋን ይዘው ነው የመጡት። ወላጆቻቸውም የፈጣሪን ቸርነትና ምህረት በማሰብ ቸርነትና ምህረት የሚል ስያሜ ሰጧቸው።ህጻናቱ ንቁና ደስተኛ ቢሆኑም ጨቅላው ቸርነት የስፓስቲክ ሴሬብራል ፓልሲ ህመም ተጠቂ መሆኑን ወላጆቹ ያወቁት ብዙም ሳይቆይ ነው። ይህ ህመም በህጻኑ ቸርነት ላይ የእድገት ውስንነት በማስከተል ፣የመቀመጥ፣የመራመድ እና የመንቀሳቀስ ችሎታው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሮበታል።

እናትና አባቱ እንደ ወላጅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለቸርነት የሚቻለውን የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ሲደክሙ ቆይተዋል።

ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዘርፉ የባለሙያ ውስንነትና እና የህክምና መገልያ መሳሪያ እጦት በውጭ አገር የሕክምና አማራጮችን እንዲያፈላልጉም አስገድዷቸዋል።

በዚህም መሰረት በታይላድ ባንኮክ የተሻለ ህክምና በመኖሩ በህጻኑ ቸርነት የጤና ሁኔታ ላይ ውጤት ለማግኘት ረዘም ያለ እና የተጠናከረ የሕክምና ዘዴዎችን በቶሎ እንዲጀምር ሃኪሞች መክረዋል፡፡

የሚያስፈልጉት የህክምና ዓይነቶች፡ ኦኩፔሽናል ቴራፒ ፣ የአካል/ፊሲዮቴራፒ ፣ የንግግር ሕክምና ፣ የሬድኮርድ ሰስፔንሽን፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፣ Snoezelen መልቲሴንሰር ቴራፒ ፣ መድኃኒቶች ፣ የአጥንት መሳርያዎች ፣ አጋዥ መሳሪያዎች፣ በሮቦቲክ የታገዘ የእግር ቴራፒ እና ሌሎች አማራጭ ሕክምናዎች የቸርነትን ልዩ ፍላጎቶችን፣ ውስንነቶችንና እና ተግዳሮቶች ለማሟላት የተዘጋጁ ናቸው።

ቸርነት በፍጥነት ሊሰጠው የሚገባውን እነዚህን ህክምናዎች ለማግኘት ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት የሚከፈለው የህክምና ወጪን፣ የመኖርያ እና የጉዞ ወጪዎችን ጨምሮ፣ $70,000 ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል። እርስዎ በቸርነት የሚያደረጉት የትኛውም ዓይነት አስተዋጽዖ በዚህ ደስተኛና ንቁ ህጻን የወደፊት ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል፣ ብሩህ የወደፊት ተስፋ እና እድልም ይሰጠዋል።

በመሆኑም በተከፈተው የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ በመሳተፍ፡ ሌሎችም እንዲሳተፉ በማጋራትና በማበረታታት ከቸርነት ጎን እንዲቆሙ በማክበር እንጠይቃለን።

https://gofund.me/de1cee92

Henok Girma Tibebu
1000388774887 (CBE)
100003003029 (Berhan Bank)

የቸርነት ጉዞ አካል ስለሆናችሁ እና ለምታበረክቱት ማንኛውም እርዳታ ከልብ እናመሰግናለን።

(ሼር ማድረግም በጎነት ነውና ምንም ማድረግ ባይችሉ ቢያንስ ለ10 ሰው ያጋሩ!)

የኢትዮ-ሶማሊያን ወቅታዊ አለመግባባት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለመስጠት በአንካራ ቀጣይ ውይይት ይካሄዳልሰኔ 27/2016 የኢትዮ-ሶማሊያን ወቅታዊ አለመግባባት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለመስጠት በመጪ...
04/07/2024

የኢትዮ-ሶማሊያን ወቅታዊ አለመግባባት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለመስጠት በአንካራ ቀጣይ ውይይት ይካሄዳል

ሰኔ 27/2016 የኢትዮ-ሶማሊያን ወቅታዊ አለመግባባት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለመስጠት በመጪው ነሐሴ በተርኪዬ አንካራ ቀጣይ ውይይት እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ፤ በሳምንቱ የተከናወኑ ዐበይት የዲፕሎማሲ ተግባራትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ በተርኪዬ አመቻችነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከሶማሊያ አቻቸው ጋር በሁለቱ ሀገሮች ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በአንካራ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

በውይይቱም የኢትዮ-ሶማሊያን ወቅታዊ አለመግባባት ዘላቂ የዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ መስጠት የሚያስችሉ ንግግሮችን አድርገዋል ብለዋል።

የኢትዮ-ሶማሊያን ወቅታዊ አለመግባባት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለመስጠት ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በተርኪዬ አንካራ ሁለተኛ ዙር ቀጣይ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ቃል-አቀባዩ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመዋጋት በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ዓለም አቀፍ ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን አንስተዋል።

ለጎረቤት ሀገራት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን በነፃ በመስጠት ለቀጣናዊ የአየር ንብረት ለውጥ ጥረትና የጋራ ልማት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

የ2016 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርም "የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ" በሚል መሪ ሃሳብ ከ7 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን የመትከል ሥራ ተጀምሯል ብለዋል።

በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ያስመዘገበችው ስኬት በዓለም ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት በግንባር ቀደምትነት መሰለፏን ያረጋገጠ መሆኑን ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በጅቡቲ በነበራቸው ጉብኝት ከሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት በማይናወጥ የዲፕሎማሲ ትብብር የቀጠለ የጋራ ዕጣ-ፈንታና የማይነጣጠሉ ሀገራት መሆናቸውን ያመላከተ መሆኑን ገልፀዋል።

በጉብኝቱም ስትራቴጂካዊ ትብብርን ማጠናከር፣ የሁለትዮሽ ትብብርን የሚያጎለብቱ የመሠረተ-ልማት ግንባታና ጥገና፣ የወደብ አገልግሎትን ማሳለጥ የሚያስችሉ ውይይቶች ተደርገዋል ብለዋል።

በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ አሸባሪ አልሸባብ የደቀነው ስጋት፣ በሱዳን የጸጥታ ሁኔታና ሌሎችም ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅሰዋል።

የኢትዮ-ቤጂንግ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄዱን፣ ሁለተኛ ምዕራፍ የሁለተኛው ትውልድ ዳያስፖራ አባላት አቀባበል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተለያዩ ሀገራት እና የተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸውንም አንስተዋል።

ጠንካራ ስነ ልቦና ችግሮችን መሻገሪያ ድልድይ ነው- ወጣት በለጠ ቡቱናሰኔ 27፣ 2016 በጠንካራ ስነ ልቦና አለመቻልን ወደ መቻል የቀየረው በለጠ ቡቱና የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ...
04/07/2024

ጠንካራ ስነ ልቦና ችግሮችን መሻገሪያ ድልድይ ነው- ወጣት በለጠ ቡቱና

ሰኔ 27፣ 2016 በጠንካራ ስነ ልቦና አለመቻልን ወደ መቻል የቀየረው በለጠ ቡቱና የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያለፉትን አምስት ዓመታት በማታው የትምህርት መርሐ ግብር በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ተማሪ በለጠ ቡቱና ጠንካራ ስነ ልቦና ካለ የማይታለፍ መንገድ የለም ብሏል።

ወጣት በለጠ ወላጅ እናትን በልጅነት ማጣትን ጨምሮ ህይወቱን በርካታ ፈተናዎችን ተጋፍጧል።

የአካል ጉዳት ያለበት ወጣት በለጠ አጋዥ አባትም የሌለው በመሆኑ የመኖር ተስፋውን ሊያደበዝዝ ቢችልም ለችግርና ለፈተና እጅ ባለመስጠት ጉዞውን ማስቀጠል ችሏል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ሲያመጣ በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ከተደረገለት በኋላ ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አቅንቷል።

ዩኒቨርሲቲውም ከ1 ዓመት የትሞህርት ቆይታ በኋላ ነፃ የትምህርት፣ የማደሪያና የምግብ አገልግሎቶችን አመቻችቶለታል።

ተማሪ በለጠ ቡቱና አካል ጉዳተኝነት ሳያግደው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው 4 ሺህ 800 ተማሪዎች ውስጥ አንዱ በመሆን በ3 ነጥብ 2 አጠቃላይ ውጤት የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።

ወጣቱ ተመራቂ ለዚህ ምዕራፍ ባደረሰው ብርቱ የስነ-ልቦና ዝግጅት ወደፊት ለሀገሩ የላቀ አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ ስለመሆኑም ነው የተናገረው።

በመቅደስ አስፋውና ታመነ አረጋ

ለኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጉ ስድስቱ  “መ” ዎች1) መወያየት- ችግሮችን ከግጭት ይልቅ በውይይት መፍታት 2) መትከል- ከችግኝ ባሻገር ለኢትዮጵያ የሚበጁ ተቋማትን በመትከል ሀገርን ማጽናት 3...
04/07/2024

ለኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጉ ስድስቱ “መ” ዎች

1) መወያየት- ችግሮችን ከግጭት ይልቅ በውይይት መፍታት

2) መትከል- ከችግኝ ባሻገር ለኢትዮጵያ የሚበጁ ተቋማትን በመትከል ሀገርን ማጽናት

3) መታደስ- እሳቤዎቻችንና አኗኗራችንን ወቅቱን በዋጀ መልኩ ማደስ

4) መሰብሰብ- ግብርን ጨምሮ ለህዝብ ጥቅም የሚውሉ ገቢዎችን መሰብሰብ

5) መነጠል- ከክፉ ሃሳብን፣ ከዘረኝነት እና ከሰፈርተኝነትን መነጠል

6) መዘጋጀት- አሁናዊ ሁኔታዎችን በሚዋጅ መልኩ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ማዘጋጀት ፤ ለዚህ ደግሞ እርስ በርስ ማገር በመሆን አገርን ማጠናከር፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)
በፓርላማ ከሰጡት ምላሸ

36ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል*********************6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ...
04/07/2024

36ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል
*********************

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደበኛ ስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አዳምጦ ረቂቅ በጀቱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በ36ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳልሰኔ 27/2016(ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ጀም...
04/07/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

ሰኔ 27/2016(ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 36ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አዳምጦ ረቂቅ በጀቱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም በፌዴራል መንግሥቱ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ።

በስብሰባው ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።

የስብሰባው ሙሉ ሂደትም በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የሚተላለፍ መሆኑን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ትላንት በአዳማ ከተማ በተነሳ ተቋውሞ የሰው ህይወት መጥፋቱ ተነገረ ሰኔ 26/2016 ዓም ማለትም በትላንትናው ዕለት በአዳማ ከተማ በነዋሪው እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በነበረ ግ...
04/07/2024

ትላንት በአዳማ ከተማ በተነሳ ተቋውሞ የሰው ህይወት መጥፋቱ ተነገረ

ሰኔ 26/2016 ዓም ማለትም በትላንትናው ዕለት በአዳማ ከተማ በነዋሪው እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በነበረ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

የግጭቱ መንስኤ መንግስት ህገ ወጥ ናቸው ብሎ መኖሪያ ቤቶቹን በዶዘር ማፍረስ ሲጀምር መሆኑን ተገልጿል። በዚህ እስካሁን የሰባት ሰዎች ህይወት እንዳለፈና ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች እንደተጎዱ በአፋን ኦሮሞ ከሚወጡ ዘገባዎች ፋስት መረጃ ተመልክቷል።
እንደዘገበው

የነቢይ መኮንን የጥበብ በረከቶች----አፈንዲ ሙተቂ----ዛሬ ዜና ህልፈቱ የተነገረው አንጋፋው ገጣሚ፣ ጋዜጠኛ እና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን በሕይወት ሳለ የሰራቸው የጽሑፍና የጥበብ በረቶች የት...
04/07/2024

የነቢይ መኮንን የጥበብ በረከቶች
----
አፈንዲ ሙተቂ
----
ዛሬ ዜና ህልፈቱ የተነገረው አንጋፋው ገጣሚ፣ ጋዜጠኛ እና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን በሕይወት ሳለ የሰራቸው የጽሑፍና የጥበብ በረቶች የትኞቹ ናቸው? ባዮግራፊው በትክክል ስላልተጻፈ ሁሉንም ማስፈር ይከብዳል። ቢሆንም የሚከተሉትን አስታውሳለሁ።
------
1. "ነገም ሌላ ቀን ነው"

በአሜሪካዊቷ ደራሲ ማርጋሬት ሚቸል የተጻፈውን "Gone with the Wind" የተሰኘ ታላቅ ድርሰት በአማርኛ ቋንቋ የተረጎመበት ድንቅ መጽሐፍ ነው። ይሁንና ነቢይ ያሳተመው የመጽሐፉን የመጀመሪያ ክፍል ብቻ ነው። ሁለተኛውን ክፍል ስለማሳተሙ መረጃው የለኝም። ነቢይ መጽሐፉን የተረጎመው ለአስር ዓመታት ያህል በማዕከላዊ እና በከርቸሌ በታሰረበት ዘመን በሲጃራ ፓኮዎችና በብጥስጣሽ ወረቀቶች ላይ እየጻፈ ነው።
------
2. "ናትናኤል ጠቢቡ"

ጀርመናዊው ጸሐፊ ተውኔት Gotthold Ephraim Lessing የጻፈውን "Nathan der Weise" የተሰኘ ቴአትር ወደ አማርኛ የተረጎመበት ርእስ ነው። ቴአትሩ በብዙ የዓለም ሀገሮች "Natahn the Wise" በሚለው የእንግሊዝኛ ስሙ ነው የሚታወቀው። በተውኔት ታሪክ በብዙ ቋንቋዎች ከተተረጎሙት ምርጥ ቴአትሮችም አንዱ ነው።

ነቢይ የተረጎመው ተውኔት በብሄራዊ ቴአትር ይታይ ነበር። ቴአትሩ በሙስሊሞች፣ በአይሁዶች እና በክርስቲያኖች መካከል የሀይማኖት መቻቻል እንዲኖር ነው የሚያስተምረው።
------
3. "ባለ ጉዳይ"

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተደጋግሞ የታየ Satirical ድራማ ነው። ድራማው በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሰፈነውን የጠነዛ ቢሮክራሲ እና የጉቦ አሰራር በአስቂኝ መንገድ የሚያሳይ ነው። የድራማው ዋና ገጸ-ባሕሪ "ቀናው ተበጀ" ይባላል። እርሱን ሆኖ የሰራው አክተር ደግሞ ፍቃዱ ተክለማሪያም ነው። በዚህም የተነሳ ፈቃዱ በድራማው ውስጥ የተጠራበት ስም "ቀናው ተበጀ" ቅጽል ስሙ ሆኖ ነበር።
-----
4. "ማለባበስ ይቅር"

HIV- AIDS የሀገር አደጋ በሆነበት ዘመን ነቢይ መኮንን "ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩትን ማግለል በሽታውን ያባብሳል። ስለዚህ ፍቅር እንስጣቸው። አናግልላቸው" የሚል መልእክት ያለው ግጥም ገጥሞ የዘመኑ ወጣት ዘፋኞች እንዲዘፍኑት አድርጎአል። የዘፈኑ መጠሪያ "ማለባበስ ይቅር" ሲሆን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ይታይ ነበር።

ታዲያ ባላወቅኩት ሁኔታ ብዙዎች ግጥሙን የጻፈው ነቢይ መኮንን መሆኑን ሳይገልጹ ስራውን ሙሉ በሙሉ በዜማ ደራሲው አርቲስት ሚካኤል በላይነህ ስም ያወሱታል። ይህ ስሕተት መታረም አለበት።
-----
5. ስውር ስፌት

ነቢያ የገጠማቸውን ግጥሞች ያሰባሰበበት ባለ ሁለት ክፍል መድብል ነው። በዚያ መድብል ከሰፈሩት ግጥሞች መካከል ይህኛው ግሩም ነው።

ይቺው ናት ኢትዮጵያ...
ይቺው ናት ዓለምህ፣
ብቻዋን የተኛች ከዓለም ተደብቃ!!
አኪሯ ቀዝቅዞ፣
"ያንቀላፋች ውቢት" ያንተው የክት እቃ...
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፣
አብረህ አንቀላፋ፣ ወይ አብረሃት ንቃ!!
(ነብይ መኮንን፡ “ስውር-ስፌት”)
-------
6. "የኛ ሰው በአሜሪካ"

ነቢይ መኮንን አሜሪካ በሄደበት ጊዜ በዚያ ስለሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን የጻፈው አስገራሚ፣ አስቂኝ እና አስተማሪ የጉዞ ማስታወሻ ነው። ማስታወሻው መጀመሪያ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በተከታታይ ከቀረበ በኋላ በ1997 ገደማ በአንድ መጽሐፍ ታትሞ ወጥቷል።
-------
7. "የዳቪንቺ ኮድ"

ነቢይ በ1999-2000 ዳን ብራውን የጻፈውንና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ የነበረውን "The Davinci Code" የተሰኘ መጽሐፍ ወደ አማርኛ ተርጉሞ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ በተከታታይ ያስነብብ ነበር። እኛም ትርጉሙን በአንድ መጽሐፍ እንዲያሳትም ነግረነዋል። ይሁንና መጽሐፉ የታተመ አይመስለኝም።
--------
8. "ነገር የገባት ሰጎን"

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በ1995 በፓሪስ ከተማ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ስታስገኝ በመላው ሕዝባችን ስሜት ላይ ከፍተኛ ደስታ ነው የፈጠረችው። ነቢይ መኮንንም ደስታው ፍንቅል ብሎ ወጥቶ ለጥሩነሽ ያለውን አድናቆት "ነገር የገባት ሰጎን" በሚል ግጥም ገልጾላታል። ግጥሙም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ወጥቶ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

ጥሩነሽ ከአምስት ዓመታት በኋላ በቤጂንግ ኦሊምፒክ ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ስታስገኝ ነቢይ ስሜቱን የገለጸበትን "ነገር የገባት ሰጎን- ቁጥር ሁለት" የሚል ርእስ ያለው ግጥም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ አስነብቦናል።
------
የነቢይን የስነ-ጽሑፍ እና የኪነ-ጥበብ ውሎች በጥቂቱ እንዲህ ቃኝቻለሁ። ከኔ የተሻለ መረጃ ያላችሁ ወዳጆቻችን የምታውቁትን ልትጨምሩበት ትችላላችሁ።

Dear Nebiy,
You were a gifted literary figure and an iconic scholar. We miss you so much. May your soul rest in peace.
-----
አፈንዲ ሙተቂ
ሰኔ 26/2016
በድሬ ዳዋ ከተማ ተጻፈ።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያለማንም ቀስቃሽ የሚሰራና በምትኩም ምላሽ የማይጠበቅበት መልካም ተግባር ነው - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርሰኔ 26/2016 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያለማንም ቀ...
04/07/2024

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያለማንም ቀስቃሽ የሚሰራና በምትኩም ምላሽ የማይጠበቅበት መልካም ተግባር ነው - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሰኔ 26/2016 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያለማንም ቀስቃሽ የሚሰራና በምትኩም ምላሽ የማይጠበቅበት የህሊና እርካታ የሚሰጥ መልካም ተግባር መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

በዘንድሮ የወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ለሚሳተፉ ወጣቶች ኦረንቴሽንና ስልጠና ተሰጥቷል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያለማንም ቀስቃሽ የሚሰራና በምትኩም ምላሽ የማይጠበቅበት የህሊና እርካታ የሚሰጥ መልካም ተግባር ነው።

በጎነትን ለማስረጽ፣ የአብሮነት እሴቶችን ለማጎልበት፣ ሰላምን ለማጽናት፣ ቀጣይነት ያለውና አስተማማኝ ልማትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባትና ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለመመለስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ መነሻነት የዘንድሮ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ሀሳብ ለ3ኛ ጊዜ በ14 የስምሪት መስኮች በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ለዚህ መልካም ዓላማ የተሰባሰቡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማበረታታት አፈጻጸሙን በተመለከተም የክትትልና ድጋፍ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ወጣቶቹ በሚኖራቸው የበጎ ተግባር ቆይታ ስነ-ምግባርን በመላበስ የአካባቢያቸውን ባህል እንዲያስተዋውቁና ከሌሎችም እንዲማሩ፣ እንዲሁም የአብሮነት እሴትን ማጎልበት፣ የሀገርና የትውልድ ግንባታን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የዜጎችን ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ማሳደግ የሚያስችሉ በጎ ስራዎችን በማከናወን ህዝብና ሀገራቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉና ዓላማው እንዲሳካ የድርሻቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል።

ዘንድሮ በሚካሄደው ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ተሳተፊ ወጣቶቹም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ኦረንቴሽንና ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የዲጂታል ግብይት ፕሮቶኮል ለዲጅታል የንግድ ዘርፍ ሰፊ እድል የሚፈጥር ነውሰኔ 26/2016( የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የዲጂታል ግብይት ፕሮቶኮል ለዲጅታል የን...
03/07/2024

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የዲጂታል ግብይት ፕሮቶኮል ለዲጅታል የንግድ ዘርፍ ሰፊ እድል የሚፈጥር ነው

ሰኔ 26/2016( የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የዲጂታል ግብይት ፕሮቶኮል ለዲጅታል የንግድ ዘርፍ ሰፊ እድል የሚፈጥር መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

በሚኒስቴሩ እና የኢትዮጵያ የአይ ሲቲ ማኅበር ትብብር የተዘጋጀው በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የዲጂታል ግብይትን ለማካተት በሚያስችለው ፕሮቶኮልና ኢ-ኮሜርስ ላይ ያተኮረ አውደ- ጥናት ተካሂዷል።

በአውደ-ጥናቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ(ዶ/ር)፤ የዓለም የግብይት ሂደት በፍጥነት ወደ ዲጂታል መቀየሩን ገልፀዋል።

በዚህ ረገድ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የዲጂታል ግብይት ፕሮቶኮልም ለአህጉራዊ የምጣኔ ኃብት እድገት ጥሩ መሠረት የሚያኖር ነው ብለዋል።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የዲጂታል ግብይት ፕሮቶኮል ለዲጅታል የንግድ ዘርፍ ሰፊ እድል የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የአይ ሲቲ ዘርፉን የላቀ ፋይዳና ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ሲሉ አረጋግጠዋል።

በሚኒስቴሩ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ስዩም መንገሻ፤ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን መሠረት በማድረግ በአይ ሲቲ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በግሉ ዘርፍ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በመመስረት አሠራሮች መዘርጋታቸውንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ የአይ ሲቲ ማኅበር ፕሬዝዳንት ይልቃል አባተ፤ አውደ-ጥናቱ በያዝነው ዓመት የካቲት ወር ላይ በጸደቀው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና የዲጂታል ግብይት ፕሮቶኮል አባሪዎች ላይ ለመምከር የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቶችን ሰጡጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላን እና አቶ ቀጀለ መርዳሳን ከኃላፊነት አነሱጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የባህልና ስፖርት ሚኒስ...
03/07/2024

ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቶችን ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላን እና አቶ ቀጀለ መርዳሳን ከኃላፊነት አነሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩን አቶ ቀጀላ መርዳሳን እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትሩን አቶ ገብረመስቀል ጫላን ከኃላፊነት አነሱ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱን ሚኒስትሮች ከዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ አንስተው በምትካቸው አዲስ ሚኒስትሮችን መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ አስታውቋል።

በዚህም መሠረት ከኃላፊነት በተነሱት አቶ ቀጀላ መርዳሳ ምትክ ወ/ሮ ሽዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ሆነው እያገለገሉ በነበሩት አቶ ገብረመስቀል ጫላ ምትክ ደግሞ አቶ ካሳሁን ጎፌን ሾመዋል። አቶ ካሳሁን ጎንፌ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ውስጥ በሚኒስትር ዴኤታነት እያገለገሉ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ሹመት አቶ ገብረመስቀል ጫላን በመተካት በሚኒስትርነት ተሹመዋል።

ከሚኒስትርነት የተነሱት አቶ ቀጀላ መርዳሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ግን የተሰጣቸው አዲስ ሹመት ይኑር አይኑር አልታወቀም።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስመረቀሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 381 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።ከተመራቂ ተማ...
03/07/2024

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስመረቀ

ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 381 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።

ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከልም 273ቱ ሴቶች ሲሆኑ 1 ሺ 108ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በ2ኛ ዲግሪ መርሐ-ግብር በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ህግ፣ ግብርና፣ ጤና እና ሌሎች የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን÷ ዘንድሮ በልዩ ሁኔታበጤና ስፔሻሊቲ ዘርፍ አምስት የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቶችን አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር በሽር አብዱላሂ÷ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ በኩል ዩኒቨርሲቲው ስኬታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ መናገራቸውን የሶማሊ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ጥናቶችና ምርምሮችን ላይ በስፋት እየሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ በክልሉ ተከስቶ የነበረውን ድርቅ ለመከላከል በተከናወኑ ስራዎች ላይ አስተዋፅዖ ማበርከቱን አስታውሰዋል።

ነፍስ ይማር በደቡብ አፍሪካ የረጅም አመት ነዋሪ የነበረው ወንድማችን ዳኒ ከዚህ አለም ተለይቶልለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን እንመኛለን
03/07/2024

ነፍስ ይማር
በደቡብ አፍሪካ የረጅም አመት ነዋሪ የነበረው ወንድማችን ዳኒ ከዚህ አለም ተለይቶል

ለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን እንመኛለን

ታዳጊ ቅዱስ የሺዋስ ወደ ሰሜን አሜሪካ 🇺🇸 በረረለትምህርታዊ ጉብኝት ቦይንግ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያን እንዲጎበኝ የተጋበዘው ተማሪ ቅዱስ ነፃ የበረራ ትኬት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በማ...
03/07/2024

ታዳጊ ቅዱስ የሺዋስ ወደ ሰሜን አሜሪካ 🇺🇸 በረረ

ለትምህርታዊ ጉብኝት ቦይንግ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያን እንዲጎበኝ የተጋበዘው ተማሪ ቅዱስ ነፃ የበረራ ትኬት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በማግኘት ለ2 ወራት ጉብኝት ትላንት ወደ አሜሪካ በርሯል።

ገና በለጋ ዕድሜው፣ የ5 ዓመት ህፃን እያለ በአቪዬሽን ፍቅር የወደቀው ታዳጊው ቅዱስ የሺዋስ በዋሽንግተን ሲያትል የቦይንግ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያን ጨምሮ፣ በሜሪላንድ የናሳ የጠፈር ምርምር ማዕከልን፣ በአላባማ ሃንትስቪል ሮኬት ሴንተርን እና የተለያዩ የኅዋ እና የአቪዬሽን ማዕከላትን የመጎብፕት መርሃግብር እንዳለው ታውቋል።

ከ13 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ በአቪዬሽን እና በአውሮፕላን ሳይንስ ዙሪያ ሦስት መጽሐፍትን ያሳተመው እና በራሱ የቴሌግራም ቻናል በርካታ አርቲክሎችን የጻፈው፣ ራሱን ኦንላይን በማስተማር አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ አረብኛና ስፓኒሽን ጨምሮ 7 ቋንቋዎችን የሚናገረው ታዳጊው ቅዱስ የሺዋስ ከሁለት ዓመታት በፊት በአርትስ ቴሌቪዥን እና አቢሲኒያ ፍላይት የጋራ ፕሮግራም በዕድሜ ትንሹ አውሮፕላን ያበረረ ታዳጊ አድርገውት እንደነበር አይዘነጋም።

የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ ቅዱስ በ16 አመቱ የብቻ በረራ (Solo flight) በማድረግ የአገሩን ስም በመልካም የማስጠራት ፍላጎቱን ከኢትዮጵያ ሲቪል-አቪዬሽ ባለሰልጣን ፈቃድ ጠይቆ መልስ በመጠባበቅ ላይ ሲሆን በረጅም ጊዜም የራሱን የአውሮፕላን ዲዛይን የሚሰራበት ኩባንያ ባለቤት የመሆን ራዕይ እንዳለው ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠች ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህሰኔ 26/2016 ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመ...
03/07/2024

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠች ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ሰኔ 26/2016 ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እያከናወነችና ተጨባጭ ውጤትም እያመጣች መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅድ ትግበራ መርሃ-ግብር በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ሚኒስትሮች፣ የፌዴራልና የክልል ተቋማት አመራሮችና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚህ ወቅት፤ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለተከታታይ ድርቅና የጎርፍ አደጋ መጋለጧን አንስተዋል።

በተለይም ታዳጊ ሀገራትን በእጅጉ እየጎዳ ያለውን ይህንን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ለመከላከል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር መሥራት ይገባል ብለዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን አንስተው፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተለይም በአረንጓዴ አሻራ ልማት የተከናወኑ ስኬታማ ሥራዎችን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እያከናወነችና ተጨባጭ ውጤትም እያመጣች መሆኑን ተናግረዋል።

በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መሠረት እስከ 2022 ዓ.ም የሚቆይ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የአየር ንብረት ለውጥ የምላሽ ዕቅድ ማዘጋጀቷንም ለአብነት አንስተዋል።

ለሚቀጥሉት 30 ዓመታትም የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የረዥም ጊዜ የአነስተኛ ካርቦን ልቀት የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ዕድገት ስትራቴጂ እንዳላትም ጠቅሰዋል።

በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አንዱ ምሰሶ ተደርጎ በመያዙ በዕቅድ እየተሰራበት መሆኑንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ልማት የጎረቤት ሀገራትን አብሮ የመልማትና የጋራ ተጠቃሚነትን መሠረት ባደረገ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሕዝብን በማስተባበር ከ32 ቢሊየን በላይ ችግኞችን በመትከል ዓለም አቀፍ ትጋቷን ማሳየቷን አስታውሰው፤ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር መሳካት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሏትን በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ ትገኛለች ብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃም የሚጠበቅባትን ኃላፊነት ለመወጣትም በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ሀገራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅዷን በማሻሻል ለተ.መ.ድ. የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፋዊ ስምምነት ከሁለት ዓመት በፊት ማስገባቷን አስታውሰዋል።

በተሻሻለው በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ትግበራ ዕቅድ፤ ኢትዮጵያ በ2022 ዓ.ም. የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን በ68 ነጥብ 8 በመቶ የመቀነስ ግብ ማስቀመጧን ገልፀዋል።

የትግበራ መርሃ-ግብሩ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሚናን በተቀናጀ መልኩ የመወጣት ቁርጠኝነትን የሚያሳይና የኢትዮጵያ ተምሳሌታዊ ጥረትን አጠናክሮ መቀጠል የሚያስችል ነው ብለዋል።

የመኸርና የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መርሃ-ግብር የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ጉልህ አስተዋጽዖ እያበረከተ እንደሚገኝም አንስተዋል።

በኢነርጂ ዘርፍም ኢትዮጵያ ለታዳሽ የኃይል አማራጭ ትኩረት በመስጠት ግልጽ ስትራቴጂክ ፖሊሲ ነድፋ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

Address

144 Pangani Heihght
Botswana
00100

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kembata World Wide Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kembata World Wide Media Network:

Videos

Share

Category

Kembata World Wide Media Network -KWWMN

KWWMN የልማት ቲቪ ኢትዮጵያ ሰፊ የከምባታ አለም አቀፍ መገናኛ አውታር Update ወርልድ ዋይድ ቴሌቪዥን ይዘን እንቀርባለን ዘር ቀለም ሳይለዩ አገራቸውን በታማኝነት እናገለግላለን። ከታች በሚገኘው አድሬስ መልስ የፈለጉትን መልዕክት ማስቀመጥ ይችላሉ እናመሰግናለን የእርስዎ ምክር እና አስተየት ነው እዚህ ያደረሠን Thanks for messaging us. I value your comments, recommendations, suggestions and questions. try to respond as soon as possible. please understand that for me. thank u! ከከምባታ የልማት ቲቪ የዝግጅት ክፍል. WWW.KWWMN.OCM

[email protected] & [email protected]


Other Botswana media companies

Show All

You may also like