የደሴ ሱመያዎች ወቅታዊ መረጃዎችን የማስታወቂያ መረብ

  • Home
  • የደሴ ሱመያዎች ወቅታዊ መረጃዎችን የማስታወቂያ መረብ

የደሴ  ሱመያዎች ወቅታዊ  መረጃዎችን የማስታወቂያ  መረብ በድናችን ላይ የተጣለብንን የመብት እረገጣ እንቃዎማለን"!!
ድ?

የሸሂድ ወንድውሞች ቀብር አሏህ በጀነቱ ይሞሽርልን።
10/06/2023

የሸሂድ ወንድውሞች ቀብር አሏህ በጀነቱ ይሞሽርልን።

10/06/2023

ፊቶቻችሁን መመልከት በራሱ ሃሴት ይሰጣል። ይህ ዑማ በእናንተ ቀና ብሏል። መስእዋትነታችሁ አይዘነጋም።
በዘመን የማይደበዝዝ ገድል ፈፅማችዃል።

አዎ ህያዋን ናችሁ አምላካችን ነፍሶቻችሁን በመላእክት መካከል የኩራት ካባን አለበሳት፣ ሰማይ ቤት በእናንተ ነፍስ መዓዛ የደመቀ ሆነ፣ አዎ መልካም ነፍስ ከፍታ እንጅ ዝቅታ አያውቃትም!!

የዚህ ዘመን ጀግኖች♥♥♥♥♥♥
ሁሌም በልባችን ውስጥ ትኖራላችሁ!!!!

#ሕያዋንነፍሶች
#ሰጋጁንገደሉት
#የአንዋርመስጂድጭፍጨፋ
#ሸገርሲቲ
#የመስጂድፈረሳ

«የፈረሱት መስጅዶች በተሻለ ቁጥርና በተሻለ ጥራት ይገነባሉ። በንጹሐን ወንድሞች ላይ ቃታ የሳቡ ወንጀለኛ የጸጥታ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ እንሠራለን።»Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡ...
08/06/2023

«የፈረሱት መስጅዶች በተሻለ ቁጥርና በተሻለ ጥራት ይገነባሉ። በንጹሐን ወንድሞች ላይ ቃታ የሳቡ ወንጀለኛ የጸጥታ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ እንሠራለን።»

Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.

ሸር አድርጉ እና እስኪ ይመልከቱ ኩዌት " ጃህራ" በምትባል ከተማ በኢትዮጵያው ንጉስነጃሺ ስም የተሰየመ ጎዳና ነው ። አክሱም መስጊድ ይከላከላል   በነጃሺ ስም እንኳን መንገድ ሊሰየም ነጃሺ...
28/08/2018

ሸር አድርጉ እና እስኪ ይመልከቱ
ኩዌት " ጃህራ" በምትባል ከተማ በኢትዮጵያው ንጉስ
ነጃሺ ስም የተሰየመ ጎዳና ነው ። አክሱም መስጊድ ይከላከላል በነጃሺ ስም እንኳን መንገድ ሊሰየም ነጃሺ የሚባል መሪ የለም ብለው ይክዳሉ ከአጂብ በላይ ጉድ በል ያገር ሰው

ታላቅ የመሻይኾች አቀባበል በአዲስ አበባታላቁ አሊማችን ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዛህረዲንና ሸይኽ እንድሪስ አሊ ደጋን ወደ ሀገር የሚገቡት ነሀሴ 22/2010 ማክሰኞ ከጥዋቱ 4:00 ሰአት በመሆኑ...
27/08/2018

ታላቅ የመሻይኾች አቀባበል በአዲስ አበባ

ታላቁ አሊማችን ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዛህረዲንና ሸይኽ እንድሪስ አሊ ደጋን ወደ ሀገር የሚገቡት ነሀሴ 22/2010 ማክሰኞ ከጥዋቱ 4:00 ሰአት በመሆኑ በሸህ ሆጀሌ መስጂድ ኮሚቴዎቹ በተገኙበት ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የሚቀበላቸው ይሆናል

.     人   ( ___)   ┃口┃  --------------------------  ┃口┃ እንኳን ለ1439ኛው   ┃口┃ የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ _አደረሠን ኩሉ አም ወአን...
20/08/2018

. 人 ( ___) ┃口┃ -------------------------- ┃口┃ እንኳን ለ1439ኛው ┃口┃ የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ _አደረሠን ኩሉ አም ወአንቱም ቢል ኸይር በአሉ የሠላም የብልፅግና የፍቅር ያድርግልን_
◦•●◉✿ ✿◉●•◦
•════•••🍃🌺🍃•••════•🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎈🎈🍃🎊🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌷🌷🌷🍃🌱🍃🎊🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

ጊዜን ገለባባጭ የሆንክ ጌታዬ ሆይ ምስጋና ይገባህ ከማለት ውጪ ምን ማለት ይቻላል?በዚሁ አጋጣሚ የለውጡ ቀንዲል የሆንከው ወንድማችን ኡስታዝ አቡበክር እንኳን ለ1439ኛው የኢድ አል አድሃ-አ...
20/08/2018

ጊዜን ገለባባጭ የሆንክ ጌታዬ ሆይ ምስጋና ይገባህ ከማለት ውጪ ምን ማለት ይቻላል?

በዚሁ አጋጣሚ የለውጡ ቀንዲል የሆንከው ወንድማችን ኡስታዝ አቡበክር እንኳን ለ1439ኛው የኢድ አል አድሃ-አረፋ በዓል በሰላም አደረሰህ

ታላቅ የምስራች በስደት ላይ ያሉ ሁለቱ አሊሞች በቅርብ ወደ ሀገር ሊገቡ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋልታላቁ ዓሊም ሸይኸ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲን እና ታላቁ የደጋኑ ዓሊም ሸይኸ ኢድሪስ አሊ ሙሀመድ ...
13/08/2018

ታላቅ የምስራች በስደት ላይ ያሉ ሁለቱ አሊሞች በቅርብ ወደ ሀገር ሊገቡ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል
ታላቁ ዓሊም ሸይኸ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲን እና
ታላቁ የደጋኑ ዓሊም ሸይኸ ኢድሪስ አሊ ሙሀመድ ደጋን
ኦገስት 27-8-2018 ወይም ነሀሴ 21-2010 እለተ ሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ።
እንሻአሏህ

🇪🇹የዙል_ሒጃ 10 ቀናት🇪🇹ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናት የፊታችን እሁድ ወይንም ሰኞ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል!!ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል "ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበ...
09/08/2018

🇪🇹የዙል_ሒጃ 10 ቀናት🇪🇹
ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናት የፊታችን እሁድ ወይንም ሰኞ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል!!

ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል "ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበለጠ መልካም ስራ ከመቼውም በላይ አሏህ ዘንድ ውድ የሚሆንበት ቀን የለም" አላህ ዘንድ ውድ የሆኑ 10 ቀናትን አምስት ወቅት ሰላቶችን በወቅታቸው፣ ከፊትና ከኋላ የሚሰገዱ ሱናዎችን ከመጠበቅ ጋር፣ ወንዶች በጀማዓ በመስገድ ቁርዓን በመቅራት፣ ዚክር፣ ዱዓ እንዲሁም ተክቢራ በማብዛት የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና የታመሙን በመጠየቅ

ከዙልሂጃ 1 ጀምሮ እስከ 9ኛው ቀን በመጾምና የጾሙ ሰዎችንም በማስፈጠር ወዘተ አሏህ የሚወዳቸው መልካም ስራዎችን በመስራት እናሳልፋቸው::

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ

እጅግ አሳዛኝ መረጃበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከየት እንደመጡ ያልታወቁ ሰወች በአንድ መድረሳ እና የሃይማኖት ት/ቤት ድንገት ዘዉ ብለዉ ገብተዉ በትምህርት ላይ የነበሩ ህፃናትን በስለ...
09/08/2018

እጅግ አሳዛኝ መረጃ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከየት እንደመጡ ያልታወቁ ሰወች በአንድ መድረሳ እና የሃይማኖት ት/ቤት ድንገት ዘዉ ብለዉ ገብተዉ በትምህርት ላይ የነበሩ ህፃናትን በስለት ነገር በዱላ እና በድንጋይ ጨፍጭፈዉ ዘግናኝ ጉዳት አደረሱ፡፧ጉዳቱ የሞቱ ህፃናት እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ራሳቸዉን የሳቱ እጅግ ብዙ ህፃናት እንዳሉ ከቦታዉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚህ ዘግናኝ ድርጊት የተሳተፉ ወንጀለኞችን የኮምቦልቻ ከተማ እና የደሴ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ሐላፊወች አስተዳደር እና ፀጥታ አካላትም እጅ በሰፊዉ ያለበት መሆኑ ተደርሶበታል፡፡

እነዚህ ፀጉረ ልዉጥ ወንጀለኞች እንዲያመልጡ በመተባበር መላዉ የኮቻ ህዝብን በመናቅ ተገዥ ባንዳ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ዉለዉ ለህግ እንዲቀርቡ ህብረተሰቡ በቁጣ እየጠየቀ ነዉ፡፡
© TolosaIbsa

ዜና ከደሴ ☞በደሴ ከተማ ዳውዶ መስጅድ መድረሳ ውስጥ ከተለያየ ቦታ መጥተው የአህባሽን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 56ቱ ወጣቶች በፀጥታ አካላትና በህዝበ ሙስሊሙ ትብብር ከደሴ ከተማ እንዲወጡ ተ...
08/08/2018

ዜና ከደሴ

☞በደሴ ከተማ ዳውዶ መስጅድ መድረሳ ውስጥ ከተለያየ ቦታ መጥተው የአህባሽን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 56ቱ ወጣቶች በፀጥታ አካላትና በህዝበ ሙስሊሙ ትብብር ከደሴ ከተማ እንዲወጡ ተደረገ፤ በኮምቦልቻ ጣቢያም ታስ

 #ሀገራችን ወሎ ታዋቂ ዝነኛ አሊሞች ያሉበት የሆን እንድለኛየማያምን ካለ ተሪክ አገላብጡከኛ ከወሎ ነው አሊሞች የወጡበህይወት ያሉትኝ እስኪ ይናገሩእነሱን ያፈራ ብሩክ ነው አፈሩኢልምን ለማስ...
07/08/2018

#ሀገራችን ወሎ ታዋቂ ዝነኛ
አሊሞች ያሉበት የሆን እንድለኛ
የማያምን ካለ ተሪክ አገላብጡ
ከኛ ከወሎ ነው አሊሞች የወጡ
በህይወት ያሉትኝ እስኪ ይናገሩ
እነሱን ያፈራ ብሩክ ነው አፈሩ
ኢልምን ለማስተማር ከሀገር ተሰደው
ግዜያቸውን ሰጥተው እንደ ተለመደው
ኢልምን የቀሰሙ ኢልምን ያስተማሩ
ብዙ አሊሞች አሉን ታሪክን የሰሩ
በኢስላም ታሪክ ላይ አሻራ የጣሉ
ከፊሎች ሞተዋል ከፊሎችም አሉ
አላህ ይማራቸው ይዘንላቸውም
መቸም ቢሆን እኛ አንረሳቸውም
በህይዎት ያሉትን አላህ እድሜ ሰጥቶ
ይጥቀመን ኢልማቸው እንደ ሻማ በርቶ💓
ዘረኛ የሚል አይጠፋምኮ😀

07/08/2018

ነገ ማለትም ረቡዕ ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ላይ በደሴ በታላቁ አረብ ገንዳ መስጂድ ስብሰባ አለ!

As Wr Wb.....~~~~~~~~ለደሴ ከተማ ሙስሊሞች፦★★★★★☞ነገ ሮብ ነሀሴ 01/2010 ከተዋቱ 3:00 በአረብ ገንዳ መስጅድ የአረብ ገንዳ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ስለጠራ ሁሉም የከተ...
07/08/2018

As Wr Wb.....
~~~~~~~~
ለደሴ ከተማ ሙስሊሞች፦
★★★★★
☞ነገ ሮብ ነሀሴ 01/2010 ከተዋቱ 3:00 በአረብ ገንዳ መስጅድ የአረብ ገንዳ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ስለጠራ ሁሉም የከተማው ሙስሊም እንድገኝ በአላህ ስም እንጠይቃለን!!
……………
Share,Share,Share

ዓሊሞች የነብያቶች ወራሾች ናቸውክብር ለዓሊሞች!
06/08/2018

ዓሊሞች የነብያቶች ወራሾች ናቸው

ክብር ለዓሊሞች!

በእሁዱ አቀባበል ፕሮግራም ላይ ታላላቅ ኡለሞች እንደሚገኙ ታወቀ!...ዶክተር ጄይላንተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመርሸይኽ ሙሐመድ ሃሚዲንሸይኽ ሃሚድ ሙሳበርካታ ኡስታዞች ዱዓቶች ወጣቶች የሀገር ሽማግ...
02/08/2018

በእሁዱ አቀባበል ፕሮግራም ላይ ታላላቅ ኡለሞች እንደሚገኙ ታወቀ!...
ዶክተር ጄይላን
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር
ሸይኽ ሙሐመድ ሃሚዲን
ሸይኽ ሃሚድ ሙሳ
በርካታ ኡስታዞች ዱዓቶች ወጣቶች የሀገር ሽማግሌዎች በቡድን በመሆን ይገኛሉ!..
እርሶም እንዳይቀሩ እሁድ ጠዋት ኤርፖርት
Share....Share...Share

እንኳን ደስ አላችሁ!!በሂጃባችሁ ምክንያት ከስራ ገበታችሁ ለተፈናቀላችሁ ሙተነቂብ እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!......ሙተነቂብ በመሆናቸው ከስራ ገበታቸው የተፈናቀሉት እህቶቻችን ወደ ስ...
01/08/2018

እንኳን ደስ አላችሁ!!
በሂጃባችሁ ምክንያት ከስራ ገበታችሁ ለተፈናቀላችሁ ሙተነቂብ እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!......
ሙተነቂብ በመሆናቸው ከስራ ገበታቸው የተፈናቀሉት እህቶቻችን ወደ ስራቸው በክብር እንዲመለሱ ተወሰነ!.....
ላለፉት አመታት በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን መንግስት አክራሪነትን እዋጋለው በሚል ዘመቻ ሽፋን ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎቻቸውን እንዲጥሱና የሃይማኖት ነፃነታቸው ተገፎ እምነታቸውን የሚያዛቸውን ትዕዛዛት እንዳይፈፅሙ ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ከሌሎች የሃገራችንን ዞኖች በተለየ የስልጤ ዞን ሙሉ በሙሉ ሙስሊም እንደመሆኑ መጠን በቀድሞ በፌደራል ጉዳዬች ሚኒስትር በኩል ከፍተኛ ጫና ይደረግብት የነበረ ዞን ነው፡፡
የዞኑ አመራሮች ሁሉም ሙስሊሞች ቢሆኑም ወይ ስልጣናቸውን አልያ ደግሞ እምነታቸውን እንዲመርጡ ሲገደዱ ነበር፡፡ በስልጤ ዞን በፀረ አክራሪነት ዘመቻ ስም ከተደረጉ ፀረ ህገ መንግስት ተግባራት መካከል ሙስሊም ሴት እህቶች ኒቃብ እንዳይለብሱ የሚከለክል ተግባር ነበር፡፡
ተወላጆቹ ሙሉ በሙሉ ሙስሊም በሆኑባት የስልጤ ዞን ከበላይ የመንግስት አካል በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት አክራሪነትን እንዲዋጉ አልያ ከስልጣናቸው እንደሚነሱ ተዝቶባቸው ቆይቷል፡፡
ይደረግባቸው ከነበሩት ጫናዎች መካከል በዞኑ ኒቃብ የሚለብሱ ሙስሊም ሴቶች በአክራሪነት የተፈረጁ በመሆናቸው ኒቃባቸውን እንዲያወልቁ ማስገደድ እንዲሁም የዞኑ የመንግስት አመራሮችም የገዛ የትዳር አጋራቸውንም ቢሆን ኒቃቧን በማሶለቅ በዞኑ ኒቃብ የማሶለቅ ዘመቻውን በተግባር እንዲያሳዩ ሲገደዱ ነበር፡፡
በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ኒቃብ የሚለብሱ ሴቶች ኒቃባቸውን እንዲያወልቁ አልያ ደግሞ ከስራቸው እንዲሰናበቱ ተወሰነ፡፡ በዚህም በርካታ ሙተነቂብ እህቶች ከመንግስት መስሪያ ቤት እና ከትምህርት ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡
ለሚሰሩበት የመንግስት መስሪያ ቤት ለቦታው የሚመጥን እውቀት፣ችሎታ እና ብቃት ቢኖራቸውም ሃይማኖታቸው ያዘዛቸውን ኒቃብ በመልበሳቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርገው ቆይተዋል፡፡ኒቃብ በመልበሳቸው ብቻ ከስራ ተባረው የሚያስተዳድሩ ቤተሰባቸው የኑሮ ጫና እንዲከብዳቸው ተደርጓል፡፡

ኒቃባችንን ለዱኒያዊ ህይወት ስንል አናወልቅም በሚል በፅናት ከስራ መሰናበቱን ምርጫቸው ያደረጉ ቆራጥ እህቶቻችን መጀመሪያውኑ ከስራ ሲሰናበቱ ተወኩላቸው በአላህ ነበርና ዛሬ ላይ ቀን እንዲለወጥ አላህ አድርጎላቸዋል፡፡
የስልጤ ዞን ካቢኔ በኒቃብ ምክንያት ከስራ ገበታቸው እንዲባረሩ የተደረጉት እህቶች በሙሉ ወደ ቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ፣እስከዛሬ ድረስ ከስራ ታግደው በቆዩባቸው ጊዜያቶች በሙሉ ደሞዛቸው ታስቦ እንዲከፈላቸው በመወሰን ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ወስኗል፡፡
ለጊዜያዊ ጭቆና በሚል የእምነታቸውን መመሪያ አንጥስም በሚል ለታገሱት እህቶቻችን አላህ(ሱ.ወ) ትዕግስታቸውን አይቶ በክብር ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ጊዜውን ቀይሮላቸዋል፡፡
በእርግጥም ከችግር ቡኋላ ምቾት አለ፡፡ ትላንት ተበዳይ ነበሩ፡፡ ዛሬ ደግሞ ይቅርታ ተጠይቀው ወደ ክብር ቦታቸው እንዲመለሱ ሆኗል፡፡
በእምነትህ ፅኑ በመሆንህ ዛሬ ላይ የተጎዳህ ቢመስልህም አላህ ዘንድ የተከበርክ በመሆንህ ጊዜውን አላህ እንደሚለውጥልህ እርግጠኛ መሆን እንደሚገባህ ከነዚህ እህቶችም መማር ይገባናል፡፡
።።
☞ Abu Dawd Osman ☜
እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ
አልሃምዱሊላህ

30/07/2018

በሚኒሶታ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ እምነት፣ዘር እና ቀለም ሳይለያየን ለውድ ሃገራችን በአንድነት መስራት እንደሚጠበቅብን ጠ/ሚኒስትሩ ዶ/ር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ ጥሪያቸውን አቅርበዋል

ሃሩን ቲዩብ - ሰበር ዜናታላቁ አሊማችን ሸኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ የፊታችን እሁድ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ታወቀ። ሸኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ በሀገር ቤት በነበሩበት ጊዜ ዲኑን በማስተማርና...
30/07/2018

ሃሩን ቲዩብ - ሰበር ዜና

ታላቁ አሊማችን ሸኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ የፊታችን እሁድ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ታወቀ። ሸኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ በሀገር ቤት በነበሩበት ጊዜ ዲኑን በማስተማርና ወጣቶችን በማጠናከር በርካታ ስራዎችን ይሰሩ የነበሩ ናቸው። በ1987 በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ በተነሳው ግርግር ምክንያት ኡለሞች ሲታሰሩ ሸህ ሰኢድ አህመድ በወቅቱ በነበሩበት ሳኡዲ አረቢያ በስደት ቀርተው እዚያው ሲኖሩ ቆይተዋል።

ታላቁ አሊም ሸህ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ በስደት ባሉበት አገር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ዲኑን በማስተማር ሲተጉ ቆይተዋል። እነሆ የፊታችን እሁድ ጠዋት ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ተነግሯል። ኢትዮጵያ በሚገቡበት ጊዜም በታላላቅ ኡለማዎች፣ ኡስታዞች፣ የመንግስት ባለስልጣናትና በህዝቡ አቀባበል ይደረግላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሸኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋን በሚኖሩበት ሳኡዲ አረቢያ አሸኛኘት ለማድረግና በሀገር ቤት ለመቀበል ኮሚቴ ተዋቅሮ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ሃሩን ቲዩብ ከዚሁ ጋር የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያቀርብ ይሆናል።

ሰበር ዜና※※※※※በሸህ ኑሩ ግድያ በሀሰት ተዎንጅሎ ታስሮ የነበረው ዎንድማችን ሙሀመድ ዩሱፍ ዛሬ 23/11/10 ተፈትዋል!"
30/07/2018

ሰበር ዜና
※※※※※
በሸህ ኑሩ ግድያ በሀሰት ተዎንጅሎ ታስሮ የነበረው ዎንድማችን ሙሀመድ ዩሱፍ ዛሬ 23/11/10 ተፈትዋል!"

ደሴ ሸዋበር መስጅድ ለህዝበ ሙስሊሙ ከተመለሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ጁምአ ሰላት እንደ ቀድሞው በሰጋጆች ተጥለቅልቆ ማየት ምንኛ ደስ ይላል! መስጅዱ ሞልቶ ዲቪዥን የሚባለው ቦታ ድረስ ተ...
27/07/2018

ደሴ ሸዋበር መስጅድ ለህዝበ ሙስሊሙ ከተመለሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ጁምአ ሰላት እንደ ቀድሞው በሰጋጆች ተጥለቅልቆ ማየት ምንኛ ደስ ይላል! መስጅዱ ሞልቶ ዲቪዥን የሚባለው ቦታ ድረስ ተሰግዷል። አልሀምዱ ሊላህ

የደሴ ሸዋበር መስጅድ ቢላሎችአስደሳች ዜና የተከበራችሁ የደሴ ከተማ ሙስሊም መሀበረሰብ እንኮን ደስአላችሁ እንኮን ደስ አለንለሰባት አመታት በአህባሹ መጅሊስ ቁጥጥር ስር የነበረዉ ታላቁ የደሴ...
24/07/2018

የደሴ ሸዋበር መስጅድ ቢላሎች
አስደሳች ዜና
የተከበራችሁ የደሴ ከተማ ሙስሊም መሀበረሰብ እንኮን ደስአላችሁ እንኮን ደስ አለን
ለሰባት አመታት በአህባሹ መጅሊስ ቁጥጥር ስር የነበረዉ ታላቁ የደሴ ሸዋበር መስጂድ በዛሬዉ እለት ለህዝበ ሙስሊሙ ተመልሶል ፡፡ ትናንትና ማለት ሰኞ ከመግሪብ ሰላት በሆነዉ ነገር የአሸባሪዎች ስራ ብናዝንም ፡፡ በዛሬዉ እለት ማለትም ማክሰኞ በነበረዉ የሙስሊሙ አንድነት ፣ ሰላም በእጅጉኑ ተደስተናል ፡፡ ስንናፍቀዉ የነበረዉን ታላቁ ሸዋበር መስጅዳችን ተረክበናል እንዲሁም የምንሳሳላቸዉን ታላቁ ኢማማችን ፣ ኻጢባችንን ፣ አባታችንን ፣ መካሪያችን ኡስታዝ ሸኽ ያእቁት አብዱል መጅድን ወደነበሩበት ኢማምነት መልሰን መተናል ፡፡
አላሁ አክበር ፡ አላሁ አክበር ፡ አላሁ አክበር
ኢንሸአላህ በጠዋቱ ስብሰባ ላይ የተመለመሉ የመስጅዱ የኮሚቴ አባላት ምርጫ ፡፡ ዛሬ ማክሰኞ ከአሱር በሆላ ኡስታዞች ፣ ኡለሞች ፣ መሻኢሆች መርጠዉ እንደሚሳዉቁ ቀነ ቀጠሮ ይዘዋል ፡፡
ዝርዝር መረጃዉን ኢንሻአላህ ማታ ጠብቁን ፡፡

24/07/2018

ደስታ አለን ከደሴ…
------//------
በደሴ ከተማ በቅርቡ ከህዝቡ የተነጠቀው የአረሺድ መስጁድ ወደ ህዝቡ ተመልሶ ለ6 አመት የቆመው ግንባታው ተጀምሮ እየተፏፏመ ነው… ባሳለፍነው ረመዷን ለመስጊድ ግንባታ ለመዋጮ ሴቶች እህቶች ከወርቅ የተሰራ የጆሮ የጣትና የአንገት ሀብላቸውን እያወለቁ የሰጡበት… አንድ ሌትር የ10 ብር አግማስ የታሸገ ውሀ እስከ 10,000 ብር በጨረታ የተሸጠበት ህዝቡ በእልህ በቁጭት ወደፊት… ያለበት አጋጣሚ እያጣጣምን ሁለተኛው ድል ከወደ ሸዋበር መስጂድ ተገኝቷል። የሸዋበር መስጊድ ወደ ህዝቡ ተመልሷል። አልሀምዱሊላህ!!!
ወቲልከል አያሙ ኑዳዊሉሀ በይነናስ… !

የደሴው ጀመዓ~ ~ ~ ~ ~ ~(ቸለካላካሉ)፧(ተፃፈ oct 9/2014 አላህ የሞቱትን ለጀነት ያለንውን ለእውነት ይሰብስበን)፧ትውልዴም እድገቴም ወሎ ላይ ነው ደሴ፣እያየች አድጋለች ደጋጎቹን ...
24/07/2018

የደሴው ጀመዓ
~ ~ ~ ~ ~ ~
(ቸለካላካሉ)

(ተፃፈ oct 9/2014 አላህ የሞቱትን ለጀነት ያለንውን ለእውነት ይሰብስበን)

ትውልዴም እድገቴም ወሎ ላይ ነው ደሴ፣
እያየች አድጋለች ደጋጎቹን ነፍሴ፣
ዛሬ እስኪ ላውሳቸው ትናገር ምላሴ፣
አባባ ሸህ አደም ፀሃዩ ጨረቃው የኢልሙ ባህር፣
የጅህልና ጥላት የደግነት ቁንጮ ድንቅ መምህር፣
አስተዋይ አሳቢ አንቱ የሁሉ አባት፣
ከቶ አልደረሰም ወይ ባንድ የምንሰግድበት፣
አባባ- ወላሂ ናፈቀኝ ቁርዓን ተፍሲሩ፣
አይደርስም ወይ መግሪብ እንድትጀምሩ፣
ኧረ ባህረዲን አዛኑን አሰማ፣
ሰንብቷል ጀማውን ልቤ ከተጠማ፣
አንት የቢላል ወራሽ የደሴ ልጅ አንዱ፣
ወጥተህ የሄድክበት ይከፈት መንገዱ፣
አቡበከር አህመድ የኢስላም ጠበቃ የሙስሊሙ ወኪል፣
ከየት አገኛለሁ ዲኔን በማስተማር ካንተ እሚሆን እኩል፣
እኔ ብቻ ሳልሆን ኸልቁ ናፍቋልና፣
ዛሬ ነገ ሳትል ፈጥነህ ድረስና፣
ከአላህ በተቸረህ የማስተማር ለዛ፣
ነፍሴን መላ በላት ሳትረግፍ እንደጤዛ፣
ኧረ የትነው ቦታው ሸሆቼ ያሉበት፣
ያቁት አብዱልመጂድ የኢልሙ ባለቤት፣
ረሃብ ጥሙ ነግሶ በሰራ አከላቴ፣
ልምዴን ካሳጣሁኝ አልቀረም መሞቴ፣
ሸህ ሀሰን ሀሚዲን የፉርቃኑ ካስማ፣
ምናለ ባገኝሁ ሳይውጠኝ ጨለማ፣
አብደላ ይማም ሆይ ያባባ ደረሳ፣
ጣፋጩ ሙዳራህ እንደምን ይረሳ፣
ጁምዓ አረብ ገንዳ እጠብቅሀለሁ፣
ኹጥባ እንድትተረጉም አደራ ብያለሁ፣
አሉ እልፍ አዕላፎች ገና ያልተወሱ፣
በልቤ ዙፋን ላይ በዲን የነገሱ፣
እንጃልኝ ኧረኔስ ናፍቆቴ በረታ ሆዴ ተላወሰ፣
ኃላ እንዳይቆጫችሁ እንባዬ በርክቶ አይኔ ከፈሰሰ፣
እና ወዳጆቼ ከልብ ሁናችሁ አድርጉልኝ ዱዓ፣
ፈጥኖ እንዲሰበሰብ ልክ እንደ በፊቱ የደሴው ጀመዓ።

ዛሬ  የዝሁር ሰላት በደሴ ሸዋበር መሰጅድ በኢማማችን በሸህ ያቁት መሪነት ተሰገደ አልሀምዱሊላህ።
24/07/2018

ዛሬ የዝሁር ሰላት በደሴ ሸዋበር መሰጅድ በኢማማችን በሸህ ያቁት መሪነት ተሰገደ አልሀምዱሊላህ።

ሸህ ያቁት አብዱል መጅድ ሚንበር ላይ ሲዎጡ ኡማው ተላቀሰ፦=================ለአመታት ከተባረሩበት በሸዋበር መስጅድ ሚንበር ተጋብዘው ብቅ ሲሉ መስጅዱ በእምባ ራሰ፣ሁሉም ሳያስበው እ...
24/07/2018

ሸህ ያቁት አብዱል መጅድ ሚንበር ላይ ሲዎጡ ኡማው ተላቀሰ፦
=================
ለአመታት ከተባረሩበት በሸዋበር መስጅድ ሚንበር ተጋብዘው ብቅ ሲሉ መስጅዱ በእምባ ራሰ፣ሁሉም ሳያስበው እምባው የአይኖቹን ግድብ ብርግዶት ፈሰሰ።
እዛ የነበሩት የደቡብ ዎሎ ዞን እና የደሴ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች አብረው በሀዘን ድባብ ውስጥ ሰመጡ።
ሸህ ያቁት በአማረ አንዴበታቼው አባታዊ ምክራቼውን አንቆረቆሩብን።ህዝቡ እልክ መሳይ ሲቃ ተናነቀው።
~~~~`
የመጡት የመንግስት ባለስልጣኖች በሰላማዊነታችን አመሰገኑ፣ የተፈጠረውን ረብሻ እና ችግር ፈጣሪዎቹን አዎገዙ፣ሁሉንም እርምጃ እንዴሚዎስዱ ቃል ገቡ።
☞በመጨረሻም ዝሁር ሰግዴን ለሸዋበር መስጅድ ጊዜያዊ ኮሚቴ መርጠን እየተቃቀፍን ተላቅሰን ለአስር ሰላት ተቀጣጥረን ተለያየን!!!
~~~~~~~
የሸዋበርን ጊዜዊ ኮሚቴ መርጠናል።
~~~~~~~~~~~~~~
1,አልዪ
2,ቡሽራ ሀሰን
3,ሸህ አህመድ ኢብራሂም (ተመቶ ሆስፒታል የተኛ)
4,ሁሴን አራጋው፣
5,መድ ከበደ፣
6,ጀማል አራጌ፣
7,ሸህ ሁሴን
……………
☞ማሳሰቢያ ለአስር ሶላት ሁላችንም እንዳንቀር ፣መረጃውን ለሁሉም እናድርስ!!!

ሰበር ዜና ደሴየደሴውን ግጭት አደራጅቶና አቀነባብሮ ያስፈፀመው ኮመንደር ደረጀ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ገለፁ።  #ሼር.ሰሞኑን የአአህባሽ ወጣቶችን በመሰብሰብ በሚስጢር ከከምቦልቻም ጭምር በማ...
23/07/2018

ሰበር ዜና ደሴ

የደሴውን ግጭት አደራጅቶና አቀነባብሮ ያስፈፀመው ኮመንደር ደረጀ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ገለፁ። #ሼር.
ሰሞኑን የአአህባሽ ወጣቶችን በመሰብሰብ በሚስጢር ከከምቦልቻም ጭምር በማስመጣት "ውሃብያዎች ስጅዳችሁን ሊቀሟችሁ ስለሆነ አዘናግታችሁ እርምጃ ውሰዱባቸው።» የሚል ትእዛዝ እንደሰጣቸውና ቢታሰሩም የሚፈቱበት መንገድ ለማመቻቸት ቃል እንደገባላቸው ውስጥ አዋቂዎች ገልፀዋል።
በዚህ መሰረት ጋጀራ መጥረቢያና ሌሎች ስለታም መሳሪያዎችን በመያዝ ተሰብስበው መስጅድ ውስጥ ቂርዓት የአሚቀሩ ሰዎችን በቀጥታ በመጨፍጨፍ ጉዳት አድርሰዋል።
በዚህ መሰረት ሆስፒታል እየተረዱ የሚገኙ በአሁኑ ሰዓት
1,ሸህ አህመድ ኢብራሂም(ከፍተኛ ጉዳት)
2,ዘይኑ ሙሀመድ
3,ሸህ ዩሱፍ ሙሀመድ (በጣም የተጎዳ)
4,መ/ድ መኪ(ከፍተኛ)
5,አህመዴልሀድ(ከፍተኛ ጉዳት)
6,ኑሩ ሲሆኑ አሁን ላይ አድማ በታኝ በመምጣቱ ጉዳዩ ተረጋግቷል። ኮማንደር ደረጀ እንዳይሰወር ጥብቅ ክትትል እንዲደረግበት ህዝበ ሙስሊሙ አሳስቧል።

አዳዲስ ፈጣን መረጃ በመላው አለም የሚከናወኑ ቪዲዮች ለማገኘት የያሲኔ ወዳጅ Youtube ጠቅ በማድረግ ፈጥነው ሰብስክራይብ ይበሉ መረጃ በ24 ሰአት..
Share..Subscribe..Share..Subscribe
👉 http://psce.pw/8WWCR

23/07/2018

የደሴ ሙስሊሞች ከጥንት እስከ እዚች ሰአት ድረስ ለእምነታቸው ብዙ መስዋዕትን እየከፈሉ ይገኛሉ። ፈተና አድሳቸው አይደለም ሁሌም መስዋዕት ከፋይ ናቸው። ዛሬ መግርብ ሰአት ላይ ሆን ተብሎ ታቅዶበት በተዘጋጀው ሴራ ወንድሞቻችን ቆስለዋል ተጎድተዋል። በአስቸኳይ ለተደረገው መረጋጋት እናመሰግናለን። ሆኖም ግንይህ በቂ አይደለምና ክትትሉ ጥብቅ ምርመራ ይፈልጋል። ውድ ወንድሞቸ በዚች ሰአት አብሬያችሁ መሆንን ተመኘሁ!! 😓

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደሴ ሱመያዎች ወቅታዊ መረጃዎችን የማስታወቂያ መረብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share