Ethio insider news

  • Home
  • Ethio insider news

Ethio insider news its is the medium of broadcasting different news events and other information via internet in the field of broadcast

18/12/2022

አክሱምና አድዋ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ
**********************

ለረጅም ጊዜ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የቆዩት አክሱም፣ አድዋና ውቅሮ ማሪያም ከተሞች በዛሬ ዕለት ዳግም አገልግሎቱን አግኝተዋል።

እነዚህ ከተሞች ዳግም ተጠቃሚ የሆኑት ከሽረ-አድዋ የተዘረጋውን የ66 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር እንዲሁም የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመር የጥገና ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተከሰተው ጦርነት በኤሌክትሪክ ማሰራጫ መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት ከስር ከስር መልሶ በመጠገን የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች ዳግም ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላም ከአማራና አፋር ክልሎች በተጨማሪ በትግራይ ክልል የቴክኒክ ባለሙያዎችን በማሰማራትና አስፈላጊ ግብዓቶችን በሟሟላት አገልግሎት የተቋረጠባቸው አካባቢዎችን ዳግም ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።

አሁንም በሶስቱም ክልሎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያላገኙ አካባቢዎችን ዳግም ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መልዕክት አስታውቋል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

18/12/2022

እየሰፋ የመጣው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እንቅስቃሴ እና የፈጠረው ስጋት
---------------------------------------------------------------------------------
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቀውስ በኦሮሚያ ክልል በተባባሰው ፖለቲካዊ እና ብሔር ተኮር ውጥረት ሳቢያ እጅጉን ተባብሷል።
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከዚህ ቀደም ሊደርስባቸው ወዳልቻላቸው ከተሞች እየቀረበ ጥቃት እየፈጸመ ነው። አዳዲስ ምልምሎችን አሰልጥነው የምርቃት ሥነ ሥርዓት በከተሞቹ ያካሂዳሉ።
ቀውሱን ለመግታት ከቡድኑ ጋር ንግግር የማድረግ ሐሳብን ገሸሽ ያደረገው መንግሥት፣ ምላሽ እየሰጠ ያለው ወታደሮች በማሠማራት እና የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት በማካሄድ ነው።
ነገሩን የበለጠ ያባባሰው ደግሞ የአማራ ሚሊሻዎች ወደ ኦሮሚያ እየገቡ ከታጣቂዎቹ ጋር እየተዋጊ ነው መባሉ ነው።
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ራሱን እንደ ኦሮሞ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ ሲገልጽ፣ ከተቃዋሚዎች ጋር ትስስር ባላቸው መገናኛ ብዙኃን ዕውቅና ተሰጥቶታል። ከዓመታት በፊት ግን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ የተገለለ ነበር።
መንግሥት ያዋቀረው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እንደሚለው በኦሮሚያ ባለፉት አምስት ወራት “በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዘግናኝ ሁኔታ ተገድለዋል።”
የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ በኅዳር ወር የተፈናቀሉ ሰዎች ከ700 ሺህ ሲበልጡ፣ በታኅሣሥ መባቻ ተጨማሪ 220 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ለመፈናቀል መገደዳቸውን ገልጿል።
በግጭቱ ታሳታፊ የሆኑት ሁሉም ቡድኖች የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን አያምኑም።
ሙሉውን ለማንበብ፦https://bbc.in/3HHAhsz

06/11/2022

ተወዳጁ ድምጻዊ የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
*************************

ድምጻዊ አሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየ ሲሆን ዛሬ ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ባለውለታ ከሆኑት አንጋፋ ከያኒያን መካከል ዓሊ ቢራ በቀዳሚነት ከሚቀመጡት ይመደባል። በበርካታ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጭምር በተጫወታቸው ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው አርቲስት ዓሊ ቢራ በተለይ በአፋን ኦሮሞ በተጫወታቸው በርካታ ሙዚቃዎቹ ዘመን ተሻጋሪ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን በመቻሉ የቋንቋው ምልክት እስከመሆን ደርሷል ይሉታል በርካቶች።

በግንቦት 1940 ዓ.ም በድሬዳዋ የተወለደው አርቲስት ዓሊ ቢራ፣ በህጻንነቱ የተለያዩ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሙዚቃዎችን እያደመጠ ማደጉን እና ለትምህርት ቤት ጓደኞቹ እና ለቤተሰቦቹ በማንጎራጎር የሙዚቃ ህይወቱን መጀመሩን በተለያያ ጊዜ ከሰጣቸው ቃለ ምልልሶች መረዳት ይቻላል።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በድሬዳዋ ከተማ ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በአዲስ አበባ ካቴድራል ትምህርት ቤት ተከታትሏል። አሜሪካ ሀገር በሚገኘው የሳንታ ሞኒካ ኮሌጅም የሙዚቃ ትምህርቱን ተምሯል።

አርቲስት ዓሊ ቢራ በ1954 ዓ.ም የኦሮሞን ሙዚቃ ለማስተዋወቅ ዓላማ ያደረገ የባህላዊ ሙዚቃ ቡድን “አፍረን ቀሎ”ን በመቀላቀል ነበር የሙዚቃ ስራውን የጀመረው። በቡድኑ ውስጥ ሌላ ዓሊ የተባለ ልጅ በመኖሩ ሁለቱን ለመለየት መጀመሪያ ከሚያዜመው "ቢራ ዳ ባሬ" ዘፈን ተወስዶ "ዓሊ ቢራ" የሚለው ሰም ተሰጠው። ዓሊ ስለ አፍረንቀሎ የሙዚቃ ባንድ ወቅት ሲናገር “ እኔ ከመስራቾቹ አንዱ ነኝ እንጂ መስራች አይደለሁም፤በእድሜ ከነሱ አነስ እላለሁ።

አፍረንቀሎን ከመሰረቱት ውስጥ ዓሊ ሸቦ የሚባል እሱም ከሃረማያ ዩኒቨርሰቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጥቶታል። እኔ ከነሱ ጋር ተቀላቅዬ አፍረንቀሎን መሰረትኩ” ብሏል።

አርቲስት ዓሊ ቢራ በክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ ተቀጥሮ ለሦስት ዓመታት ሰርቷል፤ እንዲሁም ‘አይቤክስ’ ባንድን በመቀላቀል ለስምንት ዓመታት የሙዚቃ ስራዎቹን በዲ አፍሪክ ሲያቀርብ ቆይቷል። ስለ ፍቅር፣ አካባቢ እና ፖለቲካ በጥቅሉ ከ267 በላይ ሙዚቃዎችን ተጫውቷል። ዓሊ ጊታር፣ ፒያኖ፣ ኡድ እና ሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎችን ይጫወታል። ከአርባ በላይ ሀገራት (በሁሉም አህጉራት) እጅግ በርካታ በሆኑ መድረኮች የሙዚቃ ስራዎችን ተጫውቷል።

ዓሊ ቢራ “Birra Children’s Education Fund” የተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ከባለቤቱ ጋር አቋቁመው ለሕፃናት ትምህርት ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አርቲስት ዓሊ ከኦሮምኛ በተጨማሪ፣ በሶማሊኛ፣ በአፋርኛ፡ በሐረሪ፣ በአማርኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች በርካታ ዘፈኖችን መጫወት ችሏል።አንድ ሰሞን ስለ ራሱ የተናገረው አርቲስት ዓሊ ቢራ "ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" ብሏል።

የ75 ዓመቱ አርቲስት ዓሊ ቢራ ለኢትዮጵያ ህዝቦች አብሮነትና ማህበራዊ ትስስር ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አበርክቷል።በሙዚቃዎቹ ዘመን ተሻጋሪ መልዕክቶችን በማስተላለፍ መልካም ትውልድ እንዲቀረጽ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።የተለያዩ ፈተናዎችን ተሻግሮ በከፍተኛ ጽናትና ብቃት ለረጅም ዓመታት በኪነ ጥበቡ ውስጥ ያሳለፈ መሆኑ ደግሞ አሁን ላለው ትውልድ ታላቅ ተምሳሌት ያደርገዋል።

አርቲስቱ በተስረቅራቂ ድምፁ ዘመን ተሸጋሪ ጥዑም ሙዚቃን ከመጫወት በተጨማሪ የግጥምና ዜማ ደራሲም ነው። አርቲስት ዓሊ ቢራ ባለፉት 50 ዓመታት በኦሮሞ የሙዚቃ ስራዎች ውስጥ እንቁ ሆኖ ቆይቷል።

ለቋንቋው የሙዚቃ እድገትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

በኪነጥበቡ ዘርፍ ላበረከተው አስተዋፅኦ የክብር ዶክተሬት ማዕረግ የተሰጠው አርቲስት ዓሊ ቢራ፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ተቋማት የተለያዩ እውቅናዎችን እና ሽልማቶችን አግኝቷል።

• በአጠቃላይ ከሃምሳ በላይ ታላላቅ ሽልማቶች ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ተቋማት ወስዷል።
• ከድሬዳዋ እና ከጅማ ዩኒቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬት ተበርክቶለታል።
• በድሬደዋ ከተማ ፓርክ እንዲሁም በአዳማ መንገድ በስሙ ተስይሟል።
• የኦሮሚያ ክልል በሙዚቃው ዘርፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ ልዩ የኒሻን ሽልማት አበርክቶለታል።
• የመጀመሪያው የኢሬቻ የሰላም ሽልማት ተሸላሚም ነው።
• የመጀመሪያው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የኪነጥበብ ሽልማት የህይወት ዘመን ተሸላሚም ሆኗል።
• የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ከፍተኛ ሽልማት
• በካናዳ ቶሮንቶ የአፍሪካን የምንግዜም አንጋፋ ሙዚቀኛ ሽልማት እና
• የኦዳ አዋርድ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ነው።

02/11/2022
02/11/2022

Expression of Gratitude on the Conclusion of Peace Talks

The agreement signed today in South Africa is monumental in moving Ethiopia forward on the path of the reforms we embarked upon four and half years ago. Our commitment to peace remains steadfast. And our commitment to collaborating for the implementation of the agreement is equally strong.

On behalf of the people and Government of Ethiopia, I would like to express my gratitude to the African Union Commission and the AU High Representative for the Horn of Africa His Excellency former President Olusegun Obasanjo, together with esteemed members of the high representative’s team; His Excellency former President Uhuru Kenyatta and Her Excellency Dr. Phumuzile Mlalmbo, former Deputy President of the Republic of South Africa. I would also like to thank His Excellency Mr. Moussa Faki Mahamat, Chairperson of the African Union Commission for spearheading the AU’s principled position of ‘African Solutions to African Problems’.

To my dear brother His Excellency Cyril Ramaphosa, President of the Republic of South Africa, Ethiopia is grateful to you and the sisterly nation of South Africa for hosting these talks to their successful conclusion.

I would like to express appreciation to friends of Ethiopia that have taken an active role in supporting the conclusion of this agreement. We count on your continued support in reconstructing conflict affected areas in the Northern part of the country and an enhanced partnership with Ethiopia in our countrywide development endeavors.

Last but not least, to the brave members of the Ethiopian National Defense Forces and the courageous people of this nation that stood a testing period, I humbly share deepest gratitude.

May God Bless Ethiopia and her Children!
November 2, 2022

01/11/2022
31/10/2022
27/07/2022
27/07/2022
24/07/2022
18/07/2022

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ቅንጅት በመፍጠር በሀገራቱ ድንበር መካከል የታጠቁ ሃይሎች እንዳይንቀሳቀሱ እንደምትከላከል አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ቅንጅት በመፍጠር በሀገራቱ ድንበር መካከል የትኛውም የታጠቁ ሃይሎች እንዳይንቀሳቀሱ እንደምትከላከል የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሱዳን መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል ነቢል አብደላ በሰጡት መግለጫ፥በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል በድንበር አካባቢ ለተፈጠሩ ችግሮች አፋጣኝ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በሀገራቱ አመራሮች መካከል ውይይት መጀመሩን አስታውሰዋል፡፡

በተጀመረው የውይይት ማዕቀፍ ውስጥም ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ቅንጅት በመፍጠር በሀገራቱ ድንበር መካከል የትኛውም የታጠቁ ሃይሎች እንዳይንቀሳቀሱ እንደምትከላከል የሀገሪቱ የጸጥታው እና የመከላከያ ምክር ቤት የቴክኒክ ኮሚቴ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ተዘግቶ የነበረው ሱዳንን በመተማ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛት የገላባት ድንበር እንደገና እንዲከፈት መወሰኑን ነው የገለጹት፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

17/07/2022
16/07/2022

በትግራይ ክልል በሚሊየን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እህል ማቅረብ በመቻሉ ሊያጋጥም የነበረ የረሃብ አደጋ መቀልበሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በሚሊየን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እህል ማቅረብ በመቻሉ ሊያጋጥም ይችል የነበረን የረሃብ አደጋ መቀልበሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለፀ።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቢሮው የሰሜን ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አድሪያን ቫን ደር ክናፕ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ እንደተናገሩት፥ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማሳለጥ ግጭት ለማቆም በመወሰኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሚሊየን ለሚቆጠሩ ዜጎች የምግብ እህል ማድረስ ችሏል።

የግጭት ማቆም ውሳኔውን ተከትሎ በመቶ የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎች ምግብ በመጫን በክልል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማድረስ ችለዋል።

ከግጭት የማቆም ውሳኔው በኋላ ያለማቋረጥ የምግብ አቅርቦት እየተካሄደ መሆኑን በማንሳትም እስካሁን 4 ሺህ ተሽከርካሪዎች እህል ወደ ትግራይ ክልል ማስገባታቸውን ገልፀዋል።

በዚህም ምክንያት ለ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ምግብ ማቅረብ ተችሏል።

ሆኖም ግጭቱ በጎዳቸው የአማራ እና አፋር አካባቢዎች መድረስ ይጠበቅብናል ያሉት ሀላፊው፥ ይህን ለማድረግ የግጭት ማቆም ውሳኔው ተግባራዊነት መቀጠል ይገባዋል፤ ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍም ያስፈልገናል ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

12/07/2022

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ስለምን ተሳካላት?
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኬንያው ኔሽን ጋዜጣ ዛሬ ይዞት በወጣው ጽሁፍ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ስለምን ተሳካላት? በሚል ርዕስ ሰፋ ያለ ሀተታ አስነብቧል።

ጽሁፉ ሲጀምር ባለፉት ሁለት አመታት የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን አሳሳች ዘገባዎች ስሟ ሲብጠለጠል የቆየችው ኢትዮጵያ በሌላ በኩል ደግሞ በተለይም በግብርናው መስክ ጠንክራ በመስራቷ አንጸባራቂ ውጤት ማስመዝገቧን ገልጿል።

ኢትዮጵያ በ10 አመቱ የልማት እቅዷ ጥራቱን የጠበቀ አስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ግብ መጣሏን የጠቀሰው ጽሁፉ፤ ለዚህ ግብ ስኬት ደግሞ ቁልፍ አድርጋ የወሰደችው እንደ ግብርና ያሉ የኢኮኖሚ አማራጮችን መሆኑን ያብራራል።

በግብርናው መስክ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብም መከከለኛ እና ሰፋፊ የመስኖ እርሻም ትልቅ ትኩረት እንደተሰጣቸውና በተለይም እንደ ስንዴ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት ስራዎች በስፋት መጀመራቸውን ጽሁፉ ያትታል።

ቀደም ባሉት አመታት የአገሪቷ የግብርና ፓሊሲ በመኸር እና በበልግ ወቅት እርሻ ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን የጠቀሰው ይህ ጽሁፍ፤ ባለፉት ሶስት አመታት ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግስት ስንዴን በበጋ ወራት መስኖ በክላስተር ማምረት እንደሚቻል በማመን ሶስተኛ የእርሻ ወቅትን አስተዋውቋል ይላል ኔሽን በሀተታው።

የአገሪቷ ምቹ የተፈጥሮ ስጦታ፣ የተሻሻለ ምርጥ ዘር፣ መስኖ እና ሜካናይዜሽን ታክሎበት ከፍተኛ ምርት ማግኘት ማስቻሉን ይጠቅሳል የኔሽን ዘገባ።

በዚህም ባለፈው የበጀት አመት ከ405 ሺህ ሄክታር መሬት 16 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ወይንም አንድ ነጥብ 72 ቢሊዮን ኪሎ ስንዴ በመስኖ ማምረተ ተችሏልም ሲል ስኬቱን አትቷል።

በሁለተኛው ዙርም ከ208 ሺህ ሄክታር መሬት ኢትዮጵያ ስምንት ነጥብ 35 ሚሊዮን ኩንታል ወይንም 835 ሚሊዮን ኪሎ ስንዴ በመስኖ ማምረት እንደቻለች ያብራራል።

ይህ ድል መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትልቅ ትኩረት፤ በተለይም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቁርጠኝነት የታየበት ያልተስተጓጎለ ክትትል ውጤት ነው ይላል ኔሽን በዘገባው።

መንግስት በመጪው በጀት አመት ስንዴን ከውጭ ማስገባት ማቆም ብቻ ሳይሆን ወደ ውጭ ገበያም ለመላክ ማቀዱን ያብራራው ይህ ጽሁፍ፤ የስንዴ ልማቱንም ወደ አንድ ሚሊዮን ሄክታር ከፍ ለማድረግ ውጥን እንዳለውም ጠቅሷል።

የአገር ውስጥ የምግብ አምራች ፋብሪካዎችም የሚፈልጉትን እንደ ዱረም ያሉ ልዩ ልዩ አይነት የስንዴ ምርቶችን ለማቅረብ ዓላማው መሆኑን የአገሪቷ የግብርና ሚኒስቴርን በመጥቀስ ጽሁፉ ያብራራል።

ኢትዮጵያ ከራሷ ጠንካራ ተሞክሮ ልምድ በመቅሰም፤ በከፍተኛ አመራሮቿ ጠንካራ ክትትል፤ በዕምቅ ሀብቷ ታግዛ ያቀደችውንም እንደምታሳካ የአስካሁኑ አፈጻጸሞ እማኝ መሆን ይችላል ሲል በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም የተጻፈው ይህ ሀተታ መልዕክቱን ይቋጫል።

10/07/2022
28/06/2022
27/06/2022

ከህወሓት ጋር ሊደረግ የታሰበው የሰላም ሂደት ካልተሳካ አስፈላጊውን መልስ የሚሰጥ የጸጥታ ኃይል ይዘጋጃል::

የሰሜኑ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ አቅጣጫ ማስቀመጡን ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ

የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ እና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አቅጣጫ ማስቀመጡን የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ።

የሰላም ሂደቱ መርሆ ሕጋዊነትን እና ሕገ መንግስታዊነትን የጠበቀ እንዲሁም የሀገርን መሠረታዊ ጥቅም የሚያስከብር ሊሆን እንደሚገባው አጽንኦት መሰጠቱም ተገልጿል።

የሰላም ሂደቱ በአንድ ወገን ብቻ ውጤታማ ስለማይሆን ሂደቱ ካልተሳካ አስፈላጊውን መልስ የሚሰጥ የጸጥታ ኃይል እንዲዘጋጅም አቅጣጫ መቀመጡን ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናግረዋል።

27/06/2022
27/06/2022

ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ
********************
(ኢ.ፕ.ድ)

በቅርቡ የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ)፣ የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅንቄ (ጉህዴን) እና የኦነግ-ሸኔ አሸባሪዎች ተደራጅተውና ተቀናጅተው በጋምቤላ ክልል በጋምቤላ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በጊምቢና ደምቢ ዶሎ ከተማ ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ አድርገው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት በወሰዱት እርምጃ የሽብር ቡድኖቹ በከፍተኛ ደረጃ እየተደመሰሱና ተፈጥሮ የነበረውም ችግር ተወግዶ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ተደርጓል።

ይሁን እንጂ የሽብር ቡድኖቹ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊንቢ ከተማ አካባቢ የሚገኝ ቶሌ ቀበሌ ላይ ሰላማዊ በሆኑና ምንም በማያውቁ ንፁሃን ህፃናትና ሲቪሊያን ላይ ጉዳት ማድረሳቸውና በርካቶችንም መግደላቸው ይታወሳል።

ወያኔ ሀገር የማፍረስ እኩይ ዓላማውን በጦርነት ማሳካት ስላልቻለ በየቦታው ባደራጃቸውና ባስታጠቃቸው ተላላኪ ቡድኖች አማካኝነት የጅምላ ግዲያ በተልዕኮ እየፈፀመና እያስፈፀመ ይገኛል።የዚህ ድርጊት ዋና ዓላማም ህዝብ በመንግስት ላይ ተስፋ ቆርጦ እንዲነሳና ሰላም እንዲደፈርስ ለማድረግ ነው።

የሽብር ኃይሎችን በሁሉም አካባቢ የመቆጣጠር እና ህግ ማስከበር ስራ እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት አንድ መሆንና አሸባሪዎችን በጋራ መፋለም ሲገባን በተለያየ ውዥንብርና ከፋፋይ ሂደት ውስጥ መግባት በፍፁም አይኖርብንም።

በተለይ በአሸባሪው ህዋሓት ጁንታ ቡድን ፋይናንስ የተደረጉ ሚዲያዎችን በመጠቀምና እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማደናቀፍ ተማሪዎችን በብሄርና በሀይማኖት በመከፋፈል ግጭት እንዲፈጠር ለማነሳሳት ሌት ተቀን አሸባሪዎች እየሰሩ መሆናቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ ደርሶበታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠላትን ሴራና አካሄድ ጠንቅቀን ካልተረዳንና እነርሱ በከፈቱልን ቦይና ወጥመድ ውስጥ የምንገባ ከሆነ ለውስጥና ለውጭ ጠላቶቻችንን እኩይ ሴራ በራችንን እንደከፈትን ይቆጠራል።

እነዚህ በዶላር የተገዙ ሚዲያዎች ከዚህ ቀደም በጎንደር ችግር ከመፈፀሙ አስቀድመው ህዝቡን በሀይማኖት ለመከፋፈል አጀንዳ ቀርፀው ሰላም ለማደፍረስና ግጭት ለማቀጣጠል ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

የተፈጠረውን ግጭት በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች እንዲዳረስና የእምነቱን ተከታዮች ወደ ለየለት ሁከትና ብጥብጥ ለማስገባት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ሆኖም የጥፋት ተልዕኳቸው በህዝባችን የመቻቻል ባህል፣ አርቆ አስተዋይነት፣ ትዕግስት እና በፀጥታ ኃይሎቻችን ከፍተኛ ርብርብ መክሸፉ ይታወቃል።

‘’ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንዲሉ’’ እነዚህ ሚዲያዎች ሰሞኑን እንደለመዱት ግጭት ለመቀስቀስ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ያነጣጠረ ግጭት ለማስነሳት «በአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ እና የሌሎች ብሄር ተማሪዎችን ለማጥቃት የተደራጀ የደህንነት ቡድን ወደ አማራ ክልል ተልኳል» የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ከራሱ በፊት ለህዝብና ለሀገር ህይወቱን እየሰዋ የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚጠብቅ ኃይል መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ የተፈጠረውን ክስተት ምክንያት በማድረግ በሽብርተኞች ላይ የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ እንዳይቀጥል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎችና ማህበረሰብ የተከሰተውን ችግር ምክንያት በማድረግ ሆን ብለው ግጭት ለማነሳሳት እየተንቀሳቀሱ ያሉ የአሸባሪው ህዋሓት ጁንታ ቡድን ተላላኪዎችና ቅጥረኞች መኖራቸውን ተገንዝባችሁ ከነዚህ አሸባሪዎች ራሳችሁን በመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያሳስባል።

ሆኖም ይሄንን ማሳሰቢያ ተላልፈው ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ አካላትን የማይታገስና ጥብቅ ህጋዊ እርምጃም ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ያስታውቃል።

ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

26/06/2022

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል ወደኢትዮጵያ የገባውን የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎችን ለማሶጣት አካባቢው ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት ገብቷል። የአካባቢው ኗሪዎች እንደሚሉት ከሆነ መከላከያ ስራዊቱ ወደ ቦታ የደረሰ ሲሆን ታጣቂዎቹ እስካሁን ድረስ የዝርፊያ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ብለዋል።

የመከላከያ ስራዊቱ ዛሬ ሲገባ የዋለ ቢሆንም ከታጣቃዎቹ ጋር ግን የተኩስ ልውውጥ አለመክፈቱን ነው ከአካባቢው ኗረመዎች የደረሰን መረጃ የሚያመለክተው።
ታጣቂዎቹ በኢትዮጵያ መሬት ውስጥ 150 ኪሜ ዘልቀው የገቡ ሲሆን ከአመት በፊት ጀምረው ለከብት ግጥሽ ፈልጋ በሚል
ነው ወደዚህ ቦታ መስፋፋት የጀመሩት።

ሱሌማን አብደላ

የ  #ጃዋር መሐመድ እይታhttps://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1135245270741122&id=191235888475403&sfnsn=mo
25/06/2022

የ #ጃዋር መሐመድ እይታ
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1135245270741122&id=191235888475403&sfnsn=mo

ዜና የጃዋር ማስጠንቀቂያ! ‹‹የማውቀውን ልንገራችሁ ኦሮሚያ ትፈራርሳለች›› admin June 25, 2022 1 min read 0SHARESShareTweet Continue Reading Previous: “ሞት በቃ” እንዲሁም “አማራ እየሞተ የምትበለጽግ ኢትዮጵ...

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio insider news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio insider news:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share