AnwarTv

AnwarTv አንዋር ቲቪ በእስልምና ላይ የሚያተኩር የኢንተርኔት ቲቪ ነው
(1)

*******ቀብሩ ላይ መገኘት የማንችል ፋቲሃ ቀርተን ሰዋብ እናድርስ!********ኢናሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡንበታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣቶችን ሰብስቦ ቁርአን በማስቀራት የሚታወቀው ወንድማ...
24/05/2024

*******ቀብሩ ላይ መገኘት የማንችል ፋቲሃ ቀርተን ሰዋብ እናድርስ!********

ኢናሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

በታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣቶችን ሰብስቦ ቁርአን በማስቀራት የሚታወቀው ወንድማችን ዑመር አብዱል ጀሊል (ዑመር ሀፊዝ) ወደ አኼራ ሄዷል።

ዑመር ሀፊዝ በከተማችን የቁርአን ሀፊዞች በጣት በሚቆጠሩበት ጊዜያት ቁርአን የሀፈዘ እና ያሰተማረ፣ መድህ አልረሱልን ሥራዬ ብሎ በመያዝ አሽረፈል ኸልቅን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ለማወደስ ቀን ከለሊት ሳይደክመው የሚዘክር ለብዙ ወጣቶች ነብዩን ሶዐወ እንዲወዱ ያነፀ፣ መውሊድ በብዙ ቤቶች እንዲጀመር ሰበብ የሆነ፣ ሞላ ማሩ ወወክማ አጠገብ የሚገኘው ሰላም መድረሳ (መስጂድ) ውስጥ ለአስርት አመታት ተራዊህና ተሀጁድን በሙሉ ሰላሳ ጁዝእ ቁርአን በሂፍዝ ያሰገደ፣ አላህን ወዳጅ ነብዩን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አወዳሽ ወንድማችን ነበር።

ቀብሩን የጀነት ጨፌ፣ ጉርብትናውን ዘክሮ አወድሶ ከማይጠግባቸው ሰይዳችን ጋር እንዲሆን አላህን እንለምናለን።

ሥርአተ ቀብሩ ዛሬ ጁመዐ ኮልፌ ኢማም ሀሰን መስጂድ ከተሰገደ በኋላ የሚፈፀም ይሆናል።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AnwarTv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share