Hager press

Hager press ታላቅ ነበርን ታላቅም እንሆናለን!

★በቲውተር ገፃቸው ጄነራሉ አምባሳደር እንዲህ አሉ..."ወያኔ አደገኛ ቁማርተኛ ነው! የቁማር ህግ መብላት ወይም መበላት ነው! የወያኔ ፖለቲካ ጨዋታ ህግ የቁማር ህግ ነው! ቁማርተኛ አገር አ...
06/09/2022

★በቲውተር ገፃቸው ጄነራሉ አምባሳደር እንዲህ አሉ...
"ወያኔ አደገኛ ቁማርተኛ ነው! የቁማር ህግ መብላት ወይም መበላት ነው! የወያኔ ፖለቲካ ጨዋታ ህግ የቁማር ህግ ነው! ቁማርተኛ አገር አጥፊ እንጂ አልሚ አይሆንም! የቁማር ህግ ደግሞ ለፖለቲካ አይሆንም! ወያኔም አገግሞ ዳግም አገር አያምስም!" አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ

በላይነሽ አመዴ...🇪🇹👌ንስሩ አየር ሃይላችን ከደቂቃዎች በፊት  #በዋጃ መውጫ አካባቢ በሰው አልባ አውሮፕላን/ድሮን(በበላይነሽ አመዴ) አማካኝነት በወሰደው ኢላማውንና ታርጌቱን የጠበቀ አስደ...
03/09/2022

በላይነሽ አመዴ...🇪🇹👌

ንስሩ አየር ሃይላችን ከደቂቃዎች በፊት #በዋጃ መውጫ አካባቢ በሰው አልባ አውሮፕላን/ድሮን(በበላይነሽ አመዴ) አማካኝነት በወሰደው ኢላማውንና ታርጌቱን የጠበቀ አስደናቂ ኦፕሬሽን የጁንታው ታንኮችና በርካታ ጀሌዎቹን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ አመድነት የቀየራቸው ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም #በቆቦ አካባቢ የሚገኘውን የሽብር ቡድኑን የትጥቅና ስንቅ ማዕከል እንዲሁም ዘርፎ ያከማቸውን ሀብትንም ዶግ አመድ በማድረግ ወደ ትንቢያነት ቀይሮታል።

የወንበዴዎችና የባንዳዎች ስብስብ የሆነው ሽብርተኛው ትህነግ ወያኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ግብዓተ-መሬቱ የሚፈፀምበት ሰዓቱ ተዳርሷልና ሁላችንም ለጀግኖቻችን ያለንን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥል፤ ደጀንነታችንንም በተግባር እናሳይ።

🇪🇹 ኢትዮጵያችን ታሸንፋለች 🇪🇹

31/08/2022

መሰናበቻ መሰናበቻ
አሁን የቀረን ጌታቸው ብቻ !

☆ኢትዮጽያ ያከሸፈችው የካይሮ መቀሌን ሴራ ውስጥ ለውስጥ ግብፅን እያስጨነቃት ነው..!!!አሸባሪው ቡድን ተማምኖበት ጦርነት የከፈተበት የጦር መሳሪያና የኮሚኒኬሽን መሳሪያዎችን ጭኖ በቅርቡ መ...
31/08/2022

☆ኢትዮጽያ ያከሸፈችው የካይሮ መቀሌን ሴራ ውስጥ ለውስጥ ግብፅን እያስጨነቃት ነው..!!!

አሸባሪው ቡድን ተማምኖበት ጦርነት የከፈተበት የጦር መሳሪያና የኮሚኒኬሽን መሳሪያዎችን ጭኖ በቅርቡ መቀሌ ሊያርፍ በጀግናው አየር ሃይላችን የተመታው ሞንቶኖቭ አውሮፕላን ከፓይለቱ ጀምሮ ሙሉ ኦፕሬሽን በግብፅ መንግስት ማካሄዱ ሙሉ መረጃ ሀገራችን እጅ መግባቱ የግብፅ ፖለቲከኞች የመንግስታቸውን የጥንቃቄ ጉድለትን የሚያሳይ እንዲሁም የኢትዮጵያን ጥንካሬ አጉልቶ እንዲታይ ያደረገ ከዛም በላይ የግብፅ መንግስት በአፍሪካ ሀገራት በአይን ቁራኛ እንድትታይ የሚያደርጋት የወረደ ኦፕሬሽን ነው በማለት የአልሲሲን አስተዳደር ላይ ተቃውሞ እያቀረቡ በመሆኑ የአልሲሲ አስተዳደር ለከፍተኛ ጭንቀት ለፖለቲካዊ ኪሳራ መዳረጉ መወቅ ተችልዋል።
አህመድ

🇪🇹🇪🇹 ኢትዮጵያ ማሸነፏን ትቀጥላለች 🇪🇹🇪🇹

 (ይሄ ሠውዬ) By- Eyob Mihreteab Yohannes የነፈዘ፣ የደነዘዘ፣ የማይቀየር፣ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ የጭቆና እሳቤ ሊላቀቅ የማይችል፣ ሙስና Specialist የሆነ፣ በኔትዎርክና...
22/04/2022



(ይሄ ሠውዬ)
By- Eyob Mihreteab Yohannes

የነፈዘ፣ የደነዘዘ፣ የማይቀየር፣ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ የጭቆና እሳቤ ሊላቀቅ የማይችል፣ ሙስና Specialist የሆነ፣ በኔትዎርክና በዝምድና የተቆላለፈ ድንዙዝ አራት ሚልዮን ካድሬ እጁ ላይ አለ።

አያባርራቸው መከራ። አያሻሽላቸው መከራ።

(ይሄ መሪ)

እልፍ ሚልዮኖችን ያፈናቀለ፣ በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር የበላ፣ ግማሽ ሚልዮን ሕዝብን የቀሠፈ፣ የአለም ሃያላን አገራት እጃቸውን ያስገቡበት፣ አሁንም ያላለቀ፤ ተገድዶ፣ እጁን ተጎትቶ የገባበት ቀፋፊ ጦርነት እጁ ላይ አለ።

(ይሄ ሠው)

አባይ ግድብ የተባለ የተረገመ ፋይል ግብፅን የሚያህል እጀ ረጅም ጠምዛዥ አገር አስነስቶበት፣ ከአረቡም ከሱዳኑም ከአሜሪካውም ስታጣላውና፣ በገፍ ሕገ-ወጥ መሳሪያ ስትልክበት፣ ሸማቂዎችን ስታሠለጥንበት ትውላለች።

(ይሄ ሠውዬ)

ያላሰበው ኮሮና መጣበት። ያልጠበቀው ድርቅ ተከሰተበት። ያልገመተው የአንበጣ መንጋ ገበሬውን እርዳታ ጠባቂ አደረገበት። ከጁንታ ተዋጋህ ብለው AGOAን ዘጉበት። ነጮቹ እርዳታና ብድር ቀነሱበት።

(ይሄ መሪ)

በሕዝብና ቤት ቆጠራ የማይስማማ ሕዝብ። በክልል ድንበር ወሰን የማይስማማ ሕዝብ። በሕገ-መንግስቱ የማይስማማ ሕዝብ። በሃገረ ኢትዮጵያ ግንባታ የማይግባባ ሕዝብ። በብሔር ተቧድኖ የሚበላላ ሕዝብ። በሃይማኖት ፅንፈኝነት ሊፋጅ ከቋፍ የደረሰ መቶ ሚልዮን ድሃ እና ሥርዓት አልበኛ ሕዝብ እጁ ላይ አለ።

(ጠቅላዩ)

በአራት አመት የአገር አስተዳዳሪነት ዘመኑ ያጋጠመው ምስቅልቅልና መከራ ከአሜሪካው Great Depression የከፋ፣ ከአውሮፓው Economic Recession የባሰ፣ ከሁለቱ የአለም ጦርነቶች ጋራ የሚተካከል Burden ነው።

(እመነኝ)

አብይ አህመድ ከሙዝ ብሉ፣ ከቆስጣ ትከሉ፣ ከአነቃቂ Motivation፣ ከህንፃ እድሳት፣ ከማእድ እንጋራ በላይ የሆነ እጅግ #አደገኛ፣ ቆማሪ፣ ደፋር፣ ተጋፋጭ፣ ጠንካራ፣ ብልህ፣ የተዘጋጀ፣ የWorld Orderን ጠንቅቆ የተረዳና በCrises የማይነቀነቅ ጠንካራ መሪ ነው።

ህወሃትን መንግሎ ጥሎ፣ ጦርነቱን አቸንፎ፣ ግብፅን መክቶ፣ ምእራባውያንን ተጋፍጦ ከሱ ተቃራኒነት ወደሱ ደጋፊነት መጠምዘዝ የቻለ ሰውዬ - በተነፃፃሪ ጢኒጥዬ Challenge ለሚባለው ለኑሮ ውድነት እና ለInstability ይቸነፋል ብለህ እንዳታስብ። . . . የጊዜ ጉዳይ ነው።

(አብይ አህመድ አሊ)

እያቃጠለህ፣ እያበሸቀህ፣ እያበሳጨህ፣ እያጨለለህ የምትደግፈው፤ ጨክነህ የማትጨክንበት፣ ውድቀቱን ሳይሆን ስኬቱን የምትመኝለት መሪ ነው። ያንተው ገመና፣ ያንተው ኩራት ነው። ላም እሳት ወለደች ነገር ነው።
. . እንደዛ ነው።

★ሩሲያ በህልውናዋ ላይ አደጋ ከተደቀነ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም እንደምትችል ገለጸች!የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ፕሬዝደንት ፑቲ...
23/03/2022

★ሩሲያ በህልውናዋ ላይ አደጋ ከተደቀነ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም እንደምትችል ገለጸች!

የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ፕሬዝደንት ፑቲን የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ መጠቀምን ከግምት ሊያገቡ ይችላሉ ወይ? ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ነው ይህንን የተናገሩት።

"ሕዝብ እና የአገር ውስጥ ደኅንነትን የማረጋገጥ መርኅ አለን፤ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ በምን አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ የሚለውን መረዳት ይቻላል። በአገራችን ላይ ከፍተኛ የህልውና የደኅንነት ስጋት ካለ፤ የኒክሊየር ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል" ብለዋል።

የአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ፤ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት "አደገኛ ነው" ብለዋል። የፔንታጎን ቃል አቀባይ ይህ ኃላፊነት ካለበት የኒክሊየር ጦር መሳሪያ ባለቤት የሚጠበቅ አይደለም ብለዋል።

ቃል አቀባዩ የአሜሪካ መንግሥት የሞስኮን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንደሚከታተልም ገልጸዋል።

የቀድሞ የአሜሪካ መከላከያ ኃላፊ ሊዮን ፓኔታ በተመሳሳይ የክሬምሊን ቃል አቀባይ አስተያየትን አጥብቀው ተችተዋል። የቀድሞ የአሜሪካ ከፍተኛ የመከላከያ ባለሥልጣን እንዳሉት "ሩሲያ በዚህ ጦርነት አነስተኛ መጠን የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ለመጠቀም ምክንያት ስትፈልግ ማየት ከአደገኛነቱ ውጪ ሌላ አይታየኝም።"

ሊዮን ፓኔታ ሩሲያ እውነተኛ ያልሆነ ከፍተኛ ስጋት ተደቅኖብኛል ካለች የኒውክሊየር ጦር መሳሪያን ጥቅም ላይ ልታውል ትችላለች ሲሉ ለሲኤንኤን ተናግረዋል። "ይህ ሊፈጠር እንደሚችል አላውቅም። [ይህ የሚሆን ከሆነ] ፑቲን አሜሪካ ምን አይነት ምላሽ ልትሰጥ እንደምትችል እና እራሱን ማትረፍ ስለማቻሉ ማሰብ አለበት" ብለዋል።

የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት መጽሃፍ አጠበች አሉ ¡ይህ መንግሥት ህዝቡን ለጨለማው አገዛዝ አሳልፎ ሊሰጠው ነው::ዲጂታል መታወቅያን ማንም መስማማት የለበትም! ህዝብ ሆይ ንቃ!!
13/03/2022

የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት መጽሃፍ አጠበች አሉ ¡
ይህ መንግሥት ህዝቡን ለጨለማው አገዛዝ አሳልፎ ሊሰጠው ነው::
ዲጂታል መታወቅያን ማንም መስማማት የለበትም! ህዝብ ሆይ ንቃ!!

ትንሽ ስለ ፑቲን በዘመዴ"…ይኸውልህ ወዳጄ ቪላድሚር ፑቲን ማለት አባቱ በጦርነት የቆሰለ ወታደር፣ እናቱ የፋብሪካ ወዛደር፣ የቀን ሠራተኛ የነበረች እልም ያለ የደሀ ደሀ ቤተሰብ ልጅ የነበረ ...
25/02/2022

ትንሽ ስለ ፑቲን በዘመዴ

"…ይኸውልህ ወዳጄ ቪላድሚር ፑቲን ማለት አባቱ በጦርነት የቆሰለ ወታደር፣ እናቱ የፋብሪካ ወዛደር፣ የቀን ሠራተኛ የነበረች እልም ያለ የደሀ ደሀ ቤተሰብ ልጅ የነበረ ሩሲያዊ ነው። ቤተሰቦቹ ስለዘር፣ ስለ ጎጥ፣ ስለ መንደር ሳይሆን ስለ አባት ሃገር ሩሲያ ታላቅነት እያስቀፀሉ ያሳደጉት በድህነትና በስቃይ ሕይወት ውስጥም ያደገ፤ ሁል ጊዜ ፊቱ ኮስታራና አስፈሪ ሰው እንደመሰለ ያደገ ሩሲያዊ ነው።

"…ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በጦርነት የደከመችው የታላቋ ሶቬየት ኅብረት ጎልማሳ ወታደር፣ ከጦር ዕዙ የእርፍት ጥቂት ቀናትን ወስዶ ከራሽያ ከተሞች አንዷ ወደሆነችው እና የትዳር አጋሩ የሆነችው ማሪዮ ኢቫኖቫ ወዳለችበት ፒተርበርግ ከተማ ተጓዘ። ይህን ጊዜ በከተማው መግቢያ በር ላይ እጅግ ብዙ አስክሬን የያዙ ትላልቅ መኪናዎች ወደ ጅምላ መቃብር ስፍራ በዝግታ እያዘገሙ ሲጓዙ ተመለከተ።

"…ድንገት ከሬሳዎቹ መሐል ወደ ዘመቻ ከመሄዱ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ለሚስቱ ማሪያ ኢቫኖቫ የገዛውን አይነት ጫማ ከአንዲት ሴት አስክሬን እግር ላይ ተመለከተ። "ሚስቴ ትሁን?" በሚል ስጋት እና ፍርሃት ጫማውን ወደተመለከተው አስክሬን ተጠጋ። እንደፈራውም አልቀረም። ሚስቱን ከሬሳ ክምሮች መሃል አገኘ። ይህን ጊዜ ሚስቱን በጅምላ ላለመቅበር ፍቃድ ጠይቆ ሲወስዳት አልፎ አልፎ ትክ ትክ የሚል ትንፋሽ እንዳላት አስተዋለ።

"…ሚስቱን በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም ወስዶ ያለቀ ትንፋሽ ላይ ህይወት ቀጠለ። ይህ ኩነት ከተፈጸመ ከሁለት ዓመት በኃላ በ1952 ዓ.ም ይህቺ ሴት ወንድ ልጅ ተገላገለች። ስሙንም ፑቲን አለችው። ሙሉ ስሙም ቭላድሚር ቭላድሚሮቪች ፑቲን ይባላል። አሁን የታላቋ ራሽያ ሀገረ ገዢም የሆነ። የዓለማችን ቁጥር አንድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተብሎም ስሙ በደማቅ ቀለም የተጻፈ ሰውም ሆነ።

"…አሁን ሩሲያን ከዓለማችን ዋነኛ የነዳጅ አምራች ሃገሮች ተርታ አሰልፎ፣ 70% የሚሆነው የሩስያ ሕዝብም ባለ መካከለኛ ገቢ አድርጎ፣ የሩስያ ሕዝብን የነፍስ ወከፍ ገቢም ከ28 ሺህ ዶላር በላይ አድርሶ እየመራ ያለ ቆፍጣና ነፍጠኛ መሪ ነው። አሁን የሃገሪቷ ዋና ከተማ ሞስኮ የዓለማችን ቁጥር አንድ የሆኑ ብዙ ቢልየነሮች መገኛ ሆና እንድትገኝ አድርጓታል። አሁን ሩሲያ የዓለማችን ቁጥር አንድ የኒዩክለር ክምችት ያላት ሀገር እንድትሆንም አድርጓታል። በአውሮፓም አንደኛ እና በዓለም ሁለተኛ መሆን የቻለ የሃገር መከላከያንም ገንብቷል። ፑቲን ከዛሬ 30 ዓመታት በፊት በምዕራባውያን ሰራ የፈረሰችውን የሶቭዬት ኅብረትን መልሶ የመገንባት ዕቅዱን እውን ለማድረግ ጉዞውን እያገባደደ ያለ ይመስላል ነው የሚባለው።

"…በመጨረሻም ዩክሬን እንደ ደረጄና ኃብቴ፣ እንደ ፍልፍሉ፣ እንደ ተስፋዬ ካሳ፣ እንደ ክበበው ገዳ ያለ ኮሜዲያን መርጣ ስትቀልድ መሬው ፑቲን ነፍጠኛው እጅ ላይ ጣላት። የሶሪያው ፕሬዘዳንት በሽር አላአሳድ እንዳሉት "ፑቲን ታሪክን የማረም" ሥራ ላይ ናቸውም ተብሏል። ነፍጥ፣ ከልብ እና ከሃይማኖት ጋር ሲኖርህ ታሸንፋለህ።

"…እኔም የኢትዮጵያዬን ፑቲን እየጠበቅኩት ነው። የሆነ ቀን፣ ከሆነ ስፍረ ድንገት ይመጣል። እየጠበቅኩት ነው።

💚💛🧡
18/01/2022

💚💛🧡

💚💛❤
17/01/2022

💚💛❤

ይህችን የማንነታችን ዓርማ ጀግኖች የተሠውላት ሰንደቃላማችን ትላንት በባንዳነትና በሌብነት የተደራጀ ጎጠኛ አይቀይራትም!!   የሰይጣን ዓርማህን ከፈለክ ግንባርህ ለይ ለጥፈው!!
17/01/2022

ይህችን የማንነታችን ዓርማ ጀግኖች የተሠውላት ሰንደቃላማችን ትላንት በባንዳነትና በሌብነት የተደራጀ ጎጠኛ አይቀይራትም!!
የሰይጣን ዓርማህን ከፈለክ ግንባርህ ለይ ለጥፈው!!

11/12/2021

ሰበር ዜና
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ዋናውን የወልድያ መቀሌ ጎዳና ቆርጦታል
*****************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመሩት የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በአሸባሪው ወራሪ ላይ በሰነዘሩት ክንደ ብርቱ ማጥቃት፣ በምሥራቅ ግንባር ስትራቴጂያዊ የሆኑትንና ወራሪው በፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆኑን የሚያሳዩትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቀሌ ዋናውን አውራ ጎዳና በመቁረጥ ጠላት መውጫ አጥቶ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ግንባር የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከተሞችና ተራሮች በመቆጣጠር ጥምር ጦሩ ወደ ሐራ ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል፡፡
በውጫሌ ግንባር ደግሞ የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየገሠገሠ ነው፡፡
በእነዚህ ግንባሮች በተደረገው ኦፐሬሽን በአሸባሪው የጠላት ኃይል ላይ በተሠነዘረበት ማጥቃት ጠላት ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል፡፡
የወገን የመካናይዝድ ኃይልና ንሥሮቹ የአየር ኃይሉ በጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን የጠላት ኃይል ምንም ዓይነት ተሸከርካሪ እና ከባድ መሣሪያዎችን ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ስላደረጉት፣ ጠላት በየአቅጣጫው ጥሎ ለመፈርጥጥ ተገድዷል፡፡


ነጻነታችንን የምናረጋግጠው በተባበረ ክንዳችን ነው!
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

💚💛❤
09/12/2021

💚💛❤

ለሃገር የሚከፈል መስዋትነት !"ኢትዬጵያዬ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ"
07/12/2021

ለሃገር የሚከፈል መስዋትነት !
"ኢትዬጵያዬ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ"

★ይህ በፎቶ የምታዩት ሃውልት የዘንዶውን መንፈስ ለማስመለክ ወያኔ በምእራባዊያን እገዛ በኢትዬጵያ ለይ በሚስጥር የሠራው ነው:: ቦታው አትላስ መብራቱ ጋር አውሮፓ ህብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ...
02/12/2021

★ይህ በፎቶ የምታዩት ሃውልት የዘንዶውን መንፈስ ለማስመለክ ወያኔ በምእራባዊያን እገዛ በኢትዬጵያ ለይ በሚስጥር የሠራው ነው:: ቦታው አትላስ መብራቱ ጋር አውሮፓ ህብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት
ይሄ ነገር እንዴት ነው?
ዓብይ ይልማ

ቃል በተግባር !
02/12/2021

ቃል በተግባር !

ሰበር_መረጃታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ቁጥጥር ስር ዋለችየጋሸናን ግንባር ምሽጎች ሰብረው የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት...
01/12/2021

ሰበር_መረጃ
ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ቁጥጥር ስር ዋለች

የጋሸናን ግንባር ምሽጎች ሰብረው የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጠሩ።

በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙባትን የላሊበላ ከተማንና ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያውን ለመቆጣጠር የተቻለው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በየግንባሩ የተጀመረው ማጥቃት ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ ነው።

ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ ነው።

ራሳቸውን በጠላት እንዳላስደፈሩት የግዳንና የራያ ወረዳዎች ሁሉ ቀሪዎቹ በወረራ ሥር የሚገኙ የዋግ ሕምራ፣ የሰሜንና የደቡብ ወሎ ሕዝብ፣ ከጀግኖቹ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ጠላትን እንዲደመስስና ነጻነቱን እንዲያስከብር መንግሥት ጥሪ ማቅረቡን መሆኑን ከመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

★በኢትዮጵያ የአሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲዎች ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠየቁኅዳር 22/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የአሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲዎች...
01/12/2021

★በኢትዮጵያ የአሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲዎች ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠየቁ

ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የአሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲዎች ማብራሪያ እንዲሰጡት ጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ በአገሪቱ ጉዳይ ኤምባሲዎቹ እየተከተሉት ያለውን ያልተገባ አካሄድ በተመለከተ ነው ማብራሪያ የጠየቀው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል በኤምባሲዎቹ በኩል እየወጡ ያሉት የተሳሳቱ መግለጫዎች አግባብነት እንደሌላቸው አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ በኤምባሲዎቹም ሆነ በአሜሪካ አስተዳደር ከሚያደርጉት የሽብር መንዛት ተግባር እንዲቆጠቡ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

የአፍሪካዊያን ጉዳይ በአፍሪካዊያን እንዲፈታ ለእኛው ተውልን ሲል ገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ለአገራቱ አምባሳደሮችና ኤምባሲዎች ደብዳቤ ጽፏል።

 #ዘመቻ  _ለኅብረ_ብሔራዊ_አንድነትበጋሸና ግንባር የወገን ጥምር ሃይል ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል።  በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የወገን ጦር በሁሉም ግንባሮች ወደ ከፍተኛ ማጥ...
01/12/2021

#ዘመቻ _ለኅብረ_ብሔራዊ_አንድነት

በጋሸና ግንባር የወገን ጥምር ሃይል ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የወገን ጦር በሁሉም ግንባሮች ወደ ከፍተኛ ማጥቃት በመግባት ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ነው

ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ በጋሸና ግንባር የአርቢትን፣ የአቀትን እና የጋሻና ከተሞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡

አፍሪካዊቷ አገር ኒጀር    ን በሰልፍ ተቀላቀለች።ከምስራቃዊ የአፍሪካ ክፍል ኢትዮጵያ እና ኤርትራ፤ ከምዕራባዊው ክፍል ደግሞ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር ለምዕራባዊያን የእጅ አዙር ቀኝ ግ...
30/11/2021

አፍሪካዊቷ አገር ኒጀር ን
በሰልፍ ተቀላቀለች።

ከምስራቃዊ የአፍሪካ ክፍል ኢትዮጵያ እና ኤርትራ፤ ከምዕራባዊው ክፍል ደግሞ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር ለምዕራባዊያን የእጅ አዙር ቀኝ ግዛት “በቃ” በማለት ድምጻቸውን እያሰሙ ይገኛል።

የቀድሞ ቀኝ ገዢያቸው ፈረንሳይ በውስጥ ጉዳያቸው የምታደርገውን የእጅ አዙር ቀኝ አገዛዝና ኢኮኖሚያዊ ብዝበዛ በመቃወም እስካሁን 3 የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዜጎች ለተቃውሞ ወደጎዳናዎች ወጥተዋል።

ከሰሞኑ የፈረንሳይ ጦር ቀጠናውን ሙለ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ለመጠየቅ አደባባይ የወጡት ቡርኪናቤዎች እና ኒጀራዊያን ዛሬም ድረስ የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ። በተመሳሳይ ባለፉት ጥቂት ወራቶች በተደጋጋሚ የባማኮ ጎዳናዎችን በተቃውሞ ያጨናነቁት ማሊያዊያንም ቢሆኑ ዛሬም ድረስ “ምዕራባዊያን ጠላቶቻችን ናቸው” እያሉ ይገኛል።

የማሊ ሰልፈኞች በተለይ መንስታቸው ከምዕራባዊያን ጋር ያለውን ወዳጅነት ሰርዞ በሩሲያ እንዲተካ ጠንከር ያለ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛል። ከማሊ ባሻገር በኒጀር እና ቡርኪና ፋሶም በርካታ ዜጎች የአፍሪካ እውነተኛ ወዳጆች ሩስያ እና ቻይና ናቸው፤ ምዕራባዊያን ሰልችተውናል እያሉ ይገኛል።

ይሄ በምዕራብ አፍሪካ እያቆጠቆጠ የሚገኘው ፀረ-የእጅ አዙር ቀኝ አገዛዝ ተቃውሞ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጠንካራ ህዝባዊ ማዕበል እየተስፋፋ ከመጣው የኢትዮጵያውያኑ የ “No More” ንቅናቄ ጋር ተዳምሮ መላው አፍሪካን እንዳያጥለቀልቅ ምዕራባዊያኑን ከወዲሁ ሀሳብ ላይ የጣለም እየመሰለ መጥቷል።

ሱሊማን አብደላ

26/11/2021

*ይሄ ግለሰብ የአልጄዚራ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው ውሸቱን ነው። መሃል አዲስ አበባ በግንባታ ላይ ያለን ህንፃ እያሳየ በጦርነት እንደወደመ ይናገራል። ውጪ ሀገር ተቀምጠው የሚዋሹት አንሶን ይሄ ጭራሽ ዓይናችን ስር ተቀምጦ የሚገነባ ህንፃን እያሳየ በጦርነት የወደመ ነው ብሎ ያላግጥብናል። የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፖሊስ ይሄን ሰውዬ ይዞ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ አለበት። ዲፕሎማቶቻቸው እና ሚዲያዎቻቸው የሚሰሩት ፕሮፓጋንዳ ሳያንሰን የማንም ኮተታም ህንፃ ላይ ቆሞ ያላግጥብናል እንዴ? የግለሰቡ ተግባር ተራ ውሸት ነው ብሎ ማለፍ ስህተት ነው። ምክንያቱም ዛሬ ላይ እንዲህ እያላገጠ የቀባጠረው ነገ CNN እና BBC ላይ በምንጭነት ሲጠቀስ ታገኙታላችሁ። ከዚህ ቀደም Telegraph የሚባለው ሚዲያ የኢትዮጵያ ጦር የኬሚካል ጦር መሣሪያ ተጠቅሟል ብሎ የዋሸውን ነጭ ውሸት BBC መዘገቡ ይታወሳል። እነዚህ ሰዎች የሚናገሩት ውሸት እንጂ ለእውነትነቱ ሆነ ተዓማኒነቱ ደንታ የላቸውም። ስለዚህ በዚህ ሰውዬ ላይ ተገቢ የሆነ እርምጃ አለመውሰድ የሃሰት ፕሮፓጋንዳን ከማበረታታት ተለይቶ አይታይም።

ኢትዮጵያ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶችን አባረረች። ዲፕሎማቶቹ በአዲስ አበባ አየርላንድ ኤምባሲ ይሰሩ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያን በሳምንት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መወሰኗን ኢትዮጵያ አስታውቃለች...
24/11/2021

ኢትዮጵያ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶችን አባረረች።

ዲፕሎማቶቹ በአዲስ አበባ አየርላንድ ኤምባሲ ይሰሩ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያን በሳምንት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መወሰኗን ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በኢትዮጵያ ይሰሩ የነበሩ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶች በሳምንት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

23/11/2021

"ለሃገሬ በሁሉም ነገር አለውላት" አርቲስት አቡሽ ዘለቀ

መኖራችን ሃገር ስትኖር ነው!
23/11/2021

መኖራችን ሃገር ስትኖር ነው!

“ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን!ውድ የሀገሬ ልጆች፣የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ኢትዮጵያ በልጆቿ ጀግንነትና መሥዋዕትነት ክብሯንና ነጻነቷን አስጠብቃ ...
22/11/2021

“ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን!

ውድ የሀገሬ ልጆች፣
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጀግንነትና መሥዋዕትነት ክብሯንና ነጻነቷን አስጠብቃ የኖረች ሀገር ናት። ይሄን ወዳጅም ጠላትም ያውቀዋል። ድንበሯን ሊደፍሩ የሞከሩ አይበገሬ ክንዷን አይተዋል። ሊያስገብሯት የቋመጡ አቀርቅረው ተመልሰዋል። ክህደት ለፈጸሙባት ተገቢውን ትምህርት መስጠት፣ ከጀርባ የወጓትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣትን ታውቃለች። ለሺህ ዘመናት የተጎናጸፈችው ነጻነትና ሉዓላዊ ክብር በችሮታ የተገኘ አይደለም። ያለ ዋጋ ነጻነትን አጽንቶ መጠበቅ አይቻልምና፤ ኢትዮጵያ የሚለው የነጻነት ስም የደም ዋጋ ተከፍሎበታል፣ ብርቱ ጀግኖች ሞተውለታል።

በታሪክ የምናውቃቸው አባቶቻቸው በአስተዳደርና በርእዮተ ዓለም ይለያያሉ፤ ለመብት፣ ለፍትሕና ለእኩልነት በነበራቸው አመለካከት ይለያያሉ። ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት፣ ነጻነትና ሉዓላዊነት ባላቸው ቦታ ግን ልዩነት አልነበራቸውም። በቋንቋ፣ በብሔርና በጎሳ ብዝኃነት ቢኖራቸውም የአልደፈርም-ባይ ቆራጥነታቸው አንድ ያደርጋቸዋል። የግል ፍላጎታቸው የቱንም ያህል የተራራቀ ቢሆን፣ የጋራ ጠላት ሲመጣ ኢትዮጵያዊነት ከግላዊነታቸው በላይ ይቀመጣል።

ድሮም ሆነ ዛሬ የእያንዳንዳችን ፍላጎት፣ የሁላችንም ሕይወት ከኢትዮጵያ በታች ነው። እኛ ኖረን ኢትዮጵያ ከምትሞት እኛ ሞተን ኢትዮጵያ እንድትኖር እንፈልጋለን። የሁላችንም የሆነች፣ ነጻነትና ፍትሕ የሰፈነባት፣ በገናናነቷና በነጻነቷ በዓለም አደባባይ የምትጠራ ሀገር እንድትኖረን ምኞታችን ነው። ለኢትዮጵያ ትልቅ በመመኘት፤ ሀገራችን አንገቷ ቀና እንዲል በመፈለግ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ዐቅማችን የፈቀደውን ሁሉ አድርገናል። ፖለቲካችን ከመገዳደል ወደ መተጋገል እንዲቀየር ታግለናል። ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በሰው ሀገር የሚንከራተቱት ሁሉ እንዲገቡ ለማድረግ ሞክረናል። ካለፈው በጎውን ወስደን ጥፋቱን በይቅርታ ለማረም ተንቀሳቅሰናል። “በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር” ብለን አዲስ ምዕራፍ ከፍተናል። የመለያየትና የጥላቻን ግንብ አፍርሰን የመደመርና ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ድልድይን ልንገነባ ቃል የገባነውን ወደ ተግባር ለመተርጎም ዐቅማችን የፈቀደውን አድርገናል።

ኢኮኖሚው እንዲያገግምና መዋቅራዊ ለውጥ እንዲያመጣ፤ የዳኝነት ሥርዓታችን እንዲሻሻል፣ የሰብአዊ መብት አያያዛችን እንዲስተካከል፤ የውጭ ግንኙነት መርሐችን ጎረቤት ተኮር እንዲሆን ታግለናል። በዚህ መካከል እንደ ሰው በርትተናል። እንደ ሰውም ደክመናል። እንደሰው አልምተናል፣ እንደ ሰውም አጥፍተናል። በኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ በኢትዮጵያ ክብርና በኢትዮጵያ ታላቅነት ግን ለአፍታም አዘንብለን አናውቅም።

ኢትዮጵያ የምታጓጓ ሀገር ናት። ከትናንትናዋ ይልቅ ነገዋ ታላቅ ነው። መከራ ማለፍ ነባር ችሎታዋ ነው። ይሄንን የገጠመንን መከራም እናልፈዋለን። ኢትዮጵያ ማሸነፏ አይቀርም። አሁን ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጨረሻውን ፍልሚያ የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን። ጠላቶቻችን በውጭና በውስጥ ተቀናጅተው ዘምተውብናል። በአንድ በኩል ታሪካዊ ጠላቶቻችን በራሷ ፈቃድና በራሷ መንገድ ብቻ የምታድግ ኢትዮጵያ ላለማየት የጥፋት በትር ሰንዝረዋል። ኢትዮጵያ አፍሪካዊ በሆነ መንገድ ከተነሣች፣ ተነሥታም ካሸነፈች፣ ከዚህ በኋላ ለማንም የማትመለስ ትሆናለች። ይሄን አፍሪካዊ መንገድ ለማደናቀፍ ሁሉንም ዓይነት የክፋት መሣሪያዎች አሰልፈዋል። የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን የእነርሱን ብርታት በኢትዮጵያ ድካም ላይ ለመገንባት ተነሥተዋል። የኢትዮጵያ ፍላጎት ይዞ ማለፍ እንጂ ጥሎ ማለፍ አልነበረም፤ ለዚህ ነው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን በዋናነት ጎረቤት ተኮር እንዲሆን ያደረግነው፤ ይህ ትግል የመላ ጥቁር ሕዝቦች ትግል ነው። ኢትዮጵያ አንበርክኮ ጥቁር ሕዝብን ለማሳፈርና አዲሱን የቅኝ ግዛት ቀንበር ለመጫን የሚደረግ ሤራ ነው።
ጥቁር ሕዝቦች የራሳችን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ክብር እንዳይኖረን ሆን ተብሎ የሚደረግ አንገት የማስደፋት ትግል ነው። ይህ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተ ዘመቻ፣ ኢትዮጵያን በማንበርከክ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነትና የአሸናፊነት አርአያ እንዳያገኙ የተከፈተ ዘመቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ለጥቁር ሕዝብ ክብርና ልዕልና ስትሉ፣ በፓን አፍሪካ መንፈስ፣ ሁላችሁም ጥቁር ሕዝቦች፣ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ አቀርብላችኋለሁ።

በመጨረሻም ይህ ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ነው። ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው የሚደረግ ትግል ነው። ልጆቻችን ክብርና ነጻነትን ለብሰው፣ በዓለም አደባባይ በኩራት ቀና ብለው እንዲሄዱ የሚደረግ ትግል ነው። በዓለም ላይ በክብር የምንጠራበት ስም እንዲኖረን የሚደረግ ትግል ነው። መኖር ወይም አለመኖራችንን የሚወስን ትግል ነው። ያለ ጥርጥር ግን እናሸንፋለን። ኢትዮጵያን ጠርቶ መሸነፍ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው።

ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ፡፡ የእኛ መዝመት የሚፈጥረውን ክፍተት ከግንባር የቀሩት በሙሉ ዐቅማቸው ሸፍነው ይሠራሉ፡፡ በግንባር ያልተሰለፉ የክልልና የፌደራል አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሙሉ ዐቅማቸው ይከውናሉ።

ጎልማሶች በዘዴና በብልሃት አካባቢያቸውን እየጠበቁ፣ አረጋውያን እናትና አባቶች በጸሎት እየተጉ፣ ሁሉም ሰው ተባብሮ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋግጣል። ከዚህ በኋላ በሩቁ ተቀምጠን ተቺና አራሚ የምንሆንበት ጊዜ አይደለም። መደረግ ያለበትን እኛው ራሳችን እናድርገው። ለኢትዮጵያ ከእኛ በላይ ከየትም አይመጣም። ኢትዮጵያ የሚለው ስም የአሸናፊዎች ስም ነው፤ የነጻነት ምልክት ነው። አልጠራጠርም፣ የእኔ ትውልድ ለአሸናፊ ስሙና ለነጻነት ምልክቱ የሚጠበቅበትን ዋጋ ከፍሎ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በክብር መዝገብ ላይ በወርቅ ብዕር ያትማል።

አመሰግናለሁ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትሩር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ኅዳር 13፣ 2014 ዓ.ም

15/11/2021

ከመሳይ መኮንን

ከህወሀት እጅ የተነጠቁ አከባቢዎች የተወሰኑት ስማቸው እየተነሳ ነው። በትልልቅ ከተሞች የመልቀምና የመጠራረግ ስራዎች ስለሚቀሩ ስማቸውን ይፋ ከማድረግ መቆጠቡ ይመረጣል። ከደሴና ኮምቦልቻ በተጨማሪ ቁልፍ የሆኑ ከተሞች አሁን ያላቸው ወቅታዊ ሁኔታ መጪውን ጊዜ የሚያመላክት በመሆኑ ስራው አልቆ በይፋ እስኪነገረን በትዕግስት መጠበቁ የተሻለ ነው። በተረፈ ፊንጨፍቱ፣ ከለላ፣ ዳባ፣ ብሌኔ፣ ቀርሰሌና አቀስታ የተሰኙ የወሎ አከባቢዎች ሙሉ በሙሉ ከህወሀት ወራሪ ሃይል ጸድተዋል።

በዋግምህራ አከባቢም ከአራት ወረዳዎች በላይ ከህወሀት ጀሌዎች ተነጥቀዋል። በቆቦ ዙሪያ የተወሰኑ ቦታዎች በአማራ ፋኖዎች ቁጥጥር ስር መግባታቸውን እየሰማን ነው። ከማጀቴም እንዲሁ ህወሀት ከጀግኖች ምት የተራረፈ ጥቂት ሃይሉን ይዞ በመፈርጠጡ አከባቢው በኢትዮጵያውያን እጅ ገብቷል። ለአንዳንድ ወታደራዊ ጉዳዮች ጥንቃቄ በሚል እንዲገለጹ አልተፈለገም እንጂ በሰሜን ወሎ የተወሰኑ ስትራቴጂክ አከባቢዎችም ነጻ መውጣታቸውን ለማወቅ ችዬአለሁ።

በሌላ በኩል የህወሀት የሚሌ ህልም የመጨረሻውን ምዕራፍ የተጠጋ ይመስላል። በትላንትናው ዕለት ከየቦታው የተራረፉ ታጣቂዎቹን ሰብስቦ ዕድሉን ሞክሮ በከፍተኛ ኪሳራ ጥቂት ሃይሎቹን ይዞ ወደ ባቲ ተመልሷል። ላለፉት ሁለት ሳምንታት ገደማ ሚሌ ለመድረስ መከራውን ሲበላ የከረመው የህወሀት ሃይል መከራውን በትግራይ ወጣቶችና አዛውንቶች ዕልቂት አጭዶ፣ በከፍተኛ ሰብዓዊና የመሳሪያ ኪሳራ ሂሳቡን አወራርዶ የመቀሌ መሽሎኪያ ኮሪደር እያፈላለገ ነው። የአፋር ክልል የጸጥታ ቢሮ ከፍተኛ አመራር ዛሬ እንዳጫወቱኝ ከሆነ የትላንቱ ውጊያ ለህወሀት የመጨረሻው የሚሌ ሙከራው ነው።

ቅዳሜ ዕለት ሰብሮ ለመግባት ግዙፍ ሃይል አሰልፎ ቢመጣም በብርቱዎቹ የአፋር ሃይሎችና በመከላከያ ሰራዊት መልሶ የማጥቃት እርምጃ አፈር ከድሜ ግጧል። ሃላፊው ጨምረው እንደሚሉት ህወሀት ከዚህ በኋላ የሚያደርገው ጥቃት የሚሌን በር ለመስበር ሳይሆን ከበባውን ሰንጥቆ ወደ መቀሌ ለማምለጥ ነው። ሚሌን ይዘናል የሚለው ሰበር ዜና እንደ ጠዋት ጤዛ ከተነነ በኋላ የህወሀት መንደር በሀዘን ግርዶሽ ማቅ ለብሷል። ደብረጺዮን ቴሌቪዥን መስኮት ላይ ብቅ ብሎ "ድሮውንም ለድርድር ልባችን ክፍት ነው፣ ጦርነት ምርጫችን አልነበረም" የሚል ልመናና እብሪት የተቀላቀበት መግለጫ ሰጥቷል። እንደሚሰማው ሽሬን፣ አድዋንና አክሱምን ጨምሮ በትልልቅ የትግራይ ከተሞች መሳሪያ ያነገበ አንድ ሰው አይታይም። ወጣት የሚባል ለመድሃኒት ቢፈለግ አይገኝም። ሁሉም ታጣቂ ከመቀሌ ተሰባስቧል። መቀሌ ታፍናለች።

ህወሀት ከእንግዲህ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የሚልከው ሰው የለም። የትግራይን ህዝብ ለጦርነት ማግዶ ጨርሷል። ሰሞኑን የተማረኩ ህጻናት እንደሚናገሩት በመንደራቸው የሚያውቋቸው ጓደኞቻቸው በሙሉ አልቀዋል። ትግራይ በህወሀት የእብደት ጦርነት የነገውን ትውልድ ጭምር ለሞት ገብራ ጨርሳለች። ሁኔታዎች በፍጥነት እየተቀየሩ ነው። ህወሀቶች በእብደትና ድንቁርና የገቡበት ጦርነት መልሶ ራሳቸውን ሊበላቸው መሆኑን አሁን ላይ ተረድተውታል። የአሜሪካን ድጋፍ ከመጨረሻው ፌርማታ ሊያደርሳቸው ስላልቻለ ማጣፊያው አጥሮአቸው ግራ ተጋብተው እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑ እየተነገረ ነው። ምናልባት ከመሀላቸው ለሽንፈቱ የጦስ ዶሮ ተፈልጎ ሊወገድ የሚችልበት ሁኔታ ይጠበቃል። የዲያስፖራው የህወሀት አጋፋሪ በእነእስታሊንና ረሺድ አብዲ ከበሮ ድለቃ እየጨፈረ መዝለቅ እንደማይቻል ከዘገየም ቢሆን ተረድቶት የሚይዝ የሚጨብጥ አጥቷል። "ትግራይ ጄኖሳይድ" እያለ በየጎዳናው እንዳይንከባለል፣ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት ማስኩን አስወልቆታል። ግራ የገባ ነገር?!

የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ቴዎድሮስ ከጄኔቫ ማንቋረር ጀምሯል። እንደጊንጥ ጭንቅላቱን ቀብሮ ከቆየ በኋላ የህወሀት ነፍስ ሲቃ ሲይዛት ከተደበቀበት ሽለፈት አንገቱን ብቅ አድርጎ "ትግራይ ጉሮሮዋ ተያዘ" እያለ እያላዘነ ነው። በእርግጥም ከህወሀት ሰፈር የጣር ድምጽ ጎልቶ ይሰማል። ግስላው የአማራ ልዩ ሃይል፣ አንበሳው ፋኖ፣ ክንደ ብርቱው መከላከያ ሰራዊት፣ እሳተ መለኮቱ የአፋር ኢትዮጵያዊ፣ ከዚህም ከዚያም የተሰባሰበው የዘመኑ የኢትዮጵያ አርበኛ በሚቀጥሉት ቀናትና ሳምንታት ለከሀዲው ባንዳ ሶላቶ የህወሀት ቅጥረኛ ቡድንና ለምዕራባውያን ትምህርት ሊሰጡ ከተዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊትም ለሀገሩ ህልውና ህይወቱን ሊሰጥ ከያለበት ተጠራርቶ ወደግንባር ሊዘምት መሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊነት እንደጥንቱ ዘንድሮም ያሸንፋል።

እንበርታ!!

12/11/2021

ከጋሻው መርሻ
ከአቅሙ በላይ ተንጠራርቶ የተንሰራፋው ወራሪ ኃይል ከአፋር እስከ ደቡብ ወሎ፣ ከደቡብ ወሎ በዋግኸምራ ጠለምት ድረስ እየተቀጠቀጠ ይገኛል። ይህ ቡድን ያለ የሌለ አቅሙን ሁሉ አሟጦ በመጠቀም ደሴን ከውስጥም ከውጭም ጥሶ በመግባት ይዞታውን አስፍቶ ነበር። ይሁን እንጅ እንቁራሪት እንደ ዝሆን እጮሃለሁ ብላ እንደተተረተረችው ሁሉ ወራሪው ቡድንም በሁሉም አቅጣጫ እንደጉድ እየረገፈ ይገኛል። የደሴ እና ኮምቦልቻ መያዝ በትግሉ ላይ እጥፋት አምጥቷል። ሚሊዮኖች እንደ ተርብ እንዲተሙ አድርጓል። ቁጭት እና እልህ በህዝባችን ውስጥ እንዲጋባ አድርጓል። ደሴ እና ኮምቦልቻ ትግሉን አቀጣጣይ ጋዝ ሆነዋል። ይህን ቡድን ከአሁን በኋላ ሌላ ወረራ መፈፀም የማይችልበት ደረጃ ላይ እናደርሰዋለን። በህዝባችን ከተማመንን ዳገቱ ሜዳ ይሆናል...

08/11/2021

ሸዋ መዳኛ ነው!

የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ ብዙው ታሪክ ሸዋ ጎልቶ ይነሳል። ሸዋ ከአክሱም ነገስታት ጀምረን ብናየው ወርቃማ አገራዊ ታሪክ አለው። ነገስታቶች ሲከፉ እና ሲገፉ ወደ ሸዋ ይሰደዳሉ። ያኔ ሆደ ሰፊው ሸዋ ተቀብሎ ከጠላት ታድጎ፣ ሃሳቡን መርምሮ ተከፍቶም ከሆነ በሃሳብ አርቀው፣ ተገፍቶም ከሆነ ጦር ሰብቀው ወደ ሥራው ይመልሳሉ። የመሪነት ጥበቡ እምብዛም ከሆነ ሃሳቡን መርምረው አርፎ እንዲቀመጥ ግን ምንም እንዳይጎለው እየተንከባከኩ እስከ እለት ሞቱ ያስቀምጡታል። ሸዋ በመሪነት ዘመኑም ወርቃማ ታሪክ አለው። ሸዋ ራሱ ኢትዮጵያ ነው።

ሸዋ ኢትዮጵያ ልትፈርስ ጫፍ ስደርስ ይታደጋታል። እንግሊዞች በለስ ቢቀናቸው አጤ ቴዎድሮስን ማርከው፣ ካልሆነም ገለው ኢትዮጵያን እንዳልሆነች ሊያደርጉ ነበር። ነገር ግን እምየ ምኒልክ ከአጤ ዮሐንስ ተረክበው የአጤ ቴዎድሮስን ራዕይ አስቀጠሉ። በእምየ ምኒልክም ጣሊያን መጥታ ባሪያ ልታደርግ ስትቋምጥ ሸዋ መክሮ ዘክሮ ኢትዮጵያውያንን አስተባብረው ድባቅ መተው ለጥቁር ልጆች የድል ትንሳኤን አብስረዋል። በጃኖሆይ ዘመንም የሸዋ አርበኞች አምስት ዓመት የጦር ጥበብን እና ጀግንነትን አስመስክረዋል። ሸዋ በዲፕሎማቱ የተዋጣለት ነበር። ዛሬም ባንዳ ቢፈነጭ፣ ኢትዮጵያ ልትፈርስ ብትመስልም ዞሮ ዞሮ መዳኛዋ ሸዋ ነውና ትድናለች። ስለዚህ:-

አገሬን እወዳለሁ፣
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣

እናም መሰል ወግ ከማውራት ወጣ በልና እኔስ ለአገሬ ምን ሰራሁ? አገሬ በምን ቁመና ላይ ናት ያለችው? አገሬን እንዴት ከአጥፊዎች ልታደግ? ከእኔ ምን ይጠበቃል ብለህ ራስህን ጠይቅ። ምንም ሳሰራ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የምትል ከሆነ መለኮታዊ ኃይል እንዲቀይራት ትጠብቃለህ ማለት ነው። መለኮታዊ ኃይል የሚሰራውም አንተ ባለህ መክሊት ልክ ሰርተህና ታምነህ ስትገኝ ነው። ስንፍናን እግዚአብሔርም አይወድም። ስለዚህ በምን መርዳት እንደምትችሉ ለመጠቆም ያህል:-

* ገንዘብ ያለው በገንዘቡ
* መኪኖች ያሉት ለሰራዊት እና ለሎጅስቲክ ማንቀሳቀሻ በመስጠት
* ጉልበት ያለው በጉልበቱ ሄዶ የሚታዘዘው ላይ ቢሳተፍ፣ የቆሰለ ቢያነሳ፣ ለሰራዊት ትጥቅና ስንቅ ይዞ ቢንቀሳቀስ

* ለሰራዊት ደጀን ቢሆን

* ሃሳብ ያለው በሃሳብ ለምሳሌ የጦር ስልት ያለው፣ የአደረጃጀት ስልት ሌላም ሌላም ሙያዊ እውቀት ያለው

* ከአካባቢ፣ ከወዳጅ ዘመድ ስንቅ በማሰባሰብ ግንባር በመላክ እና መሰል ተግባር ላይ በመሳተፍ ዘማች ሆኖ አገርን ማደን ይቻላል። ስለዚህ ኳስ እንደሚከታተል ዳር ቆሞ አገሬ እወዳለሁ፣ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ማለት ከንቱነት ነው። ወቅቱ ስለማይፈቅድ መጠነኛ ስብሰባ ነበረችና ትናንት የሸዋ ተወላጆች ባለሃብቶች ትንሽም ቢሆኑ ተሰባስበው ሎጅስቲክ ላይ ሲመካከሩ እና ያላቸውን ሲያወጡ አንድ አርበኛ አባት የተናገሩት ውስጤ ቀርቷል። ነገ አጋራችሓለሁ

እናም ወገኖቼ ኢትዮጵያን ትወዳላችሁ አይደል? ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ትፈልጋላችሁ አይደል? ስለዚህ ፆታ፣ ዘር፣ ቀለም እና ሃይማኖት ሳትለዩ ትኩረት ለሸዋ ስጡ፤ ድጋፍ አድርጉ።

ሔቨን ዮሐንስ

08/11/2021

★ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢትዬጵያ ለይ ስለሚደርሰው ጫና የሰጡት ማብራሪያ!
"ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ አትበተንም ጠላቶቿን አሸንፋ የአፍሪካ ፈርጥና ምሳሌ ትሆናለች"

★የምእራባውያን ጫና እየከረረ ሄዷል። ዛሬ አብዛኛው የኢትዮጵያ ዩቱብ ዜና አቅራቢዎች የኔታ ቱዩብን ጨምሮ እንዲታደጉ ተደርጓል። መንግስት የራሱን እርምጃ ሊወስድ ይገባል ።
07/11/2021

★የምእራባውያን ጫና እየከረረ ሄዷል። ዛሬ አብዛኛው የኢትዮጵያ ዩቱብ ዜና አቅራቢዎች የኔታ ቱዩብን ጨምሮ እንዲታደጉ ተደርጓል። መንግስት የራሱን እርምጃ ሊወስድ ይገባል ።

☆በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የወጣው ያለው  ህዝብ የውጭ  መገናኛ ብዙሃን እየነዙት ያለውን የሀሰት መረጃ የሚቃወም መፈክር ይዞ ወጥቷል
07/11/2021

☆በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የወጣው ያለው ህዝብ የውጭ መገናኛ ብዙሃን እየነዙት ያለውን የሀሰት መረጃ የሚቃወም መፈክር ይዞ ወጥቷል

★የሱዳን ወታደራዊ አመራር ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን በቁጥጥር ስር አደረገ!የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሀገሪቱ ወታደራዊ አመራር የቁም እስረኛ እንዲሆኑ መደረጋቸውን መ...
25/10/2021

★የሱዳን ወታደራዊ አመራር ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን በቁጥጥር ስር አደረገ!

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሀገሪቱ ወታደራዊ አመራር የቁም እስረኛ እንዲሆኑ መደረጋቸውን መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።በጀነራል አልቡርሀን የሚመራሙ ወታደራዊ አመራሩ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ ባለሰልጣናትንም በቁጥጥር ሰር አውሏል።ሰሞኑን በሱዳን ወታደራዊ አመራሩን የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።

☆በማይጠብሪ የሸባሪው ማሰልጠኛ እና የሰውኃይል ማደራጃ ላይ አየር ኃይል እርምጃ ወሰደየኢፌዴሪ አየር ኃይል በአሸባሪው ህወሓት የወታደር ማሰልጠኛዎች፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች፣ የነዳጅ ማክማቻዎች...
24/10/2021

☆በማይጠብሪ የሸባሪው ማሰልጠኛ እና የሰውኃይል ማደራጃ ላይ አየር ኃይል እርምጃ ወሰደ

የኢፌዴሪ አየር ኃይል በአሸባሪው ህወሓት የወታደር ማሰልጠኛዎች፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች፣ የነዳጅ ማክማቻዎች እና ሌሎችም ለሽብር ስራው የሚጠቀምባቸው የተመረጡ አካባቢዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል።

ባገኘነው መረጃ ዛሬም በምዕራብ ግንባር ማይጠብሪ ላይ የሚገኘውን የአሸባሪው ማሰልጠኛና የሰው ኃይል ማደራጃ ጣቢያ ላይ አየር ኃይላችን እርምጃ ወስዷል።

ባለፉት ቀናት አየር ኃይሉ ንጹሃን ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የተመረጡ የአሸባሪው ህውሓት የሚጠቀምባቸው ዒላማዎች ላይ የተሳካ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ይታወቃል።

ምስል፡ ከማህበራዊ ሚዲያ

☆የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደ ትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ የሚያደርጋቸውን በረራዎች በሙሉ ዛሬ ማገዱን አስታወቀ።ድርጅቱ በረራዎቹን ያገደው 11 መንገደኞችን ያሳፈረ ዛሬ ከአዲስ አበባ የተ...
23/10/2021

☆የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደ ትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ የሚያደርጋቸውን በረራዎች በሙሉ ዛሬ ማገዱን አስታወቀ።ድርጅቱ በረራዎቹን ያገደው 11 መንገደኞችን ያሳፈረ ዛሬ ከአዲስ አበባ የተነሳ አንድ አውሮፕላኑ መቀሌ እንዳያርፍ ከተከለከለ በኋላ መሆኑን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሽቴፋን ዱጃሪክ አስታውቀዋል። ዱጃሪክ እንዳሉት ይኽው የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ የአየር አገልግሎቶች በምህጻሩ ዩ ኤን ኤች ኤ ኤስ በረራ ከፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ፈቃድ ያገኘ ቢሆንም በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ተቆጣጣሪዎች መቀሌ እንዳያርፍ ትዕዛዝ ተስጥቶታል። አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ተመልሶ በሰላም ማረፉን የተናገሩት ዱጃሪክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች የሆነውን በጥንቃቄ እያጠኑ መሆኑንም ገልጸዋል።

22/10/2021

☆የኢትዮጵያ አየር ሀይል በመቀሌ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት የአየር ድብደባ በማድረጉ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ነገር ግን የጁንታውን የሀይል አቅም በማዳከሙ የትህነግ ሀይሎችን አበሳጭቷል።

21/10/2021
☆የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዛሬ ጥቅምት 10 ረፋድ ላይ በመቐለ ከተማ በተመረጡ ኢላማዎች በተሳካ መልኩ መቷል። የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዛሬ ኢላማ አድርጎ የመታው የህወሓት የጦር መሳርያ መጋዝኖ...
21/10/2021

☆የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዛሬ ጥቅምት 10 ረፋድ ላይ በመቐለ ከተማ በተመረጡ ኢላማዎች በተሳካ መልኩ መቷል። የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዛሬ ኢላማ አድርጎ የመታው የህወሓት የጦር መሳርያ መጋዝኖች ናቸው።

በመቐለ ከተማ ውስጥ በርከት ያሉ ጦር ማከማቻዎች፣ ዲፖዎች እና የወታደራዊ ማሰልጠኛዎች እንዳሉ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከሁለት ቀን በፊትም በመቐለ የነበረ የህወሓት መገናኛ ዘዴዎች በተሳካ መንገድ መምታቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አየር ሃይል ታርጌት የተደረጉ ቦታዎች ሲመታ ጥንቃቄ በተሞላው ነው። ፀረ ድሮን አስገብተናል መቐለ አየር ማለፍ አትችልም ብሎ ፕሮፖጋንዳ ሲሰራ የነበረው ህወሓት : የኢትዮጵያ አየር ሃይል ምንም ነገር እንደማያግደው በተግባር አሳይቷል።

በመቐለ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የመሳሪያ ማከማቻ ተመታበመቐለ ከተማ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የጦር መሳሪያ ማከማቻ፣ መስሪያ እና የከባድ ...
20/10/2021

በመቐለ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የመሳሪያ ማከማቻ ተመታ

በመቐለ ከተማ የሚገኘው መስፍን ኢንዱስትሪያል የአሸባሪው ህወሓት የጦር መሳሪያ ማከማቻ፣ መስሪያ እና የከባድ መሳሪያዎች መጠገኛ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ነግረውናል። እንደምንጮቻችን ገለጻ አሸባሪው ቡድን በመቐለ ከተማ የሚገኘውን የመስፍን ኢንዱስትሪያልን ሙሉ በሙሉ የመሳሪያ ማከማቻ እና ማምረቻ እንዲሁም የከባድ መሳሪያዎች የጥገና ማዕከል አድርጎ እየተጠቀመበት ነው።

የኢፌዲሪ አየር ኃይል በመቐለ ከተማ የሚገኙና አሸባሪ ቡድኑ ለሽብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን ስፍራዎች፣ እና መሳሪያዎች ላይ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። መከላከያ ሰራዊቱ በአየር ኃይሉ አማካኝነት በመቐለ ከተማ የሚገኙ የግንኙነት መሳሪያዎችን እና ታወሮችን የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምባቸው መቆየቱን በማረጋገጥ እርምጃ የወሰደ ሲሆን ዛሬም የአስቸኳይ ጊዜ ማጣሪያ ባወጣው መረጃ የሽብር ቡድኑ ለመሳሪያ ማከማቻነት እና ለጥፋት ስራው የሚጠቀምባቸው አካባቢዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አረጋግጧል።

ምስል፡ ከድረገጽ

☆ዲፕሎማቶች የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ከምንግዜም በላይ መሥራት አለባቸውአዲስ አበባ፣ጥቅምት 9፤2014 (ኤፍ ቢሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲፕሎማቶች፣ ለሠራተኞቹና ለተጠሪ ተቋማት...
19/10/2021

☆ዲፕሎማቶች የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ከምንግዜም በላይ መሥራት አለባቸው

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 9፤2014 (ኤፍ ቢሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲፕሎማቶች፣ ለሠራተኞቹና ለተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በሁለት ዙር ያካሄደው ሥልጠና መጠናቀቁን አስመልክቶ የመዝጊያ መርኃ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እያካሄደ ነው።

በመርኃ ግብሩ ላይ የታደሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደተናገሩት፤ ሠልጣኞቹ በቆይታቸው ተልዕኳቸውን በብቃት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ክህሎት ጨብጠዋል።

ሰልጣኞቹ በቀጣይ ወደ ዲፕሎማሲው ሥራ ሲገቡ የአገራቸውን ገጽታ በመገንባትና የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም በላቀ ደረጃ ማስከበር እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

በተለይም አሁን በአገሪቱ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአገሪቱን እውነታ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሠልጣኞቹ በአስተሳሰብ ለውጥ፣ በተቋሙ የለውጥና የአደረጃጀት ሥራ፣ በዲጂታል ዲፕሎማሲና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና መውሰዳቸው ይታወሳል።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hager press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hager press:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share