Tana Times

Tana Times Zehabesha.com

Zehabesha is an extensive Ethiopian news source. We provide balanced news, perspective

Ethiopian News: Trusted, In-Depth Analysis | The Habesha  -
12/05/2025

Ethiopian News: Trusted, In-Depth Analysis | The Habesha -

The Habesha Ethiopian News Stay updated with the latest Ethiopian news and in-depth analysis on top stories from The Habesha. Get all the important updates in one place.

07/12/2024

Alyou Tebeje is the founder and manager of Zehabesha.com, an Ethiopian news website that has gained prominence for its commitment to independent journalism and in-depth reporting. The site is particularly known for its scholarly approach, offering analytical content on political, social, and economic matters concerning Ethiopia and the Horn of Africa.

While Zehabesha.com covers a wide array of topics, including Ethiopian politics, cultural affairs, human rights, and regional news, it is most recognized for providing a platform for critical and independent perspectives in an often polarized media landscape. Under Alyou Tebeje’s leadership, Zehabesha.com has worked to distinguish itself by focusing on thorough investigative journalism and offering an alternative to mainstream narratives.

The website is especially popular among Ethiopians in the diaspora, who rely on it for news and analysis that is not always readily available through state-controlled or commercial media outlets. It is also known for providing a space where diverse opinions on Ethiopia’s complex political situation can be expressed.

Would you like more detailed information on Alyou Tebeje's background or the types of content Zehabesha.com publishes?

"ምንም እንኳን ትግራይ ፌዴሬሽኑ ውስጥ ሆና ነፃ ሀገር ለመሆን ሂደት ላይ ብትሆንም አሁን ላይ እኔ በሱ ዙሪያ ለመናገር አልፈልግም።ቤተክርስቲያናችን ግን ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሙሉ በሙሉ ተገንጥላ...
28/10/2024

"ምንም እንኳን ትግራይ ፌዴሬሽኑ ውስጥ ሆና ነፃ ሀገር ለመሆን ሂደት ላይ ብትሆንም አሁን ላይ እኔ በሱ ዙሪያ ለመናገር አልፈልግም።ቤተክርስቲያናችን ግን ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሙሉ በሙሉ ተገንጥላለች።ያ ማለት መንበረ ሳላማ በቃ ልክ እንደ ግብፅ ወይም ልክ እንደ ኤርትራ ወይም ልክ እንደ ኢትዮጵያ ወይም ልክ እንደ ሶሪያ ራሷን ችላ የቆመች "ሃገር" ሆናለች ማለት ነው። ይህ ለትግራይ ትልቅ ብስራት ነው።"
- ሰረቀ ብርሃን

ይህ የህወሃት ካድሬ ፣ ጳጳስ ነኝ ባይ፣ እንዲህ አይነት አስተያየት ሲሰጥ ሳይ አዘንኩ፡፡ ቆይ ትግራይ እንዴት ብላ ነው ከኢትዮጵያ የምትገነጠለው ? እንዴት ሰዎቹ ማገናዘብ ይሳናቸዋል ? ምን አይነት ድንቁርና ነው ?

ትግራይ ማለት እኮ ኢትዮጵያ ማለት ነው ? ትግራይ እኮ የኢትዮጵያ እምብርት ማለት ነው፡፡ ያ ኩሩ፣ ታላቅ፣ እነ ጀግናው አጤ ዮሐንስን፣ እነ ጀግናው አሉላ አባ ነጋ ያፈራ ማህበረሰብ እንደዚህ አይነት አሜከላ ሰዎችን ማፍራቱ በጣም ያሳቅዝናል፡፡የትግራይ ህዝብ ትልቁ ጥያቄ በሕይወት መኖር ነው፡፡ በሰላም መኖር ነው፡፡ እንደ ሰረቀ ያሉ እብዶች የሚናገሩት የትግራይን ህዝብ በጭራሽ አይወክልም፡፡

ህወሃት ስትባል በአጠቃላይ የተረገመች ድርጅት ናት፡፡ ለትግራይ ህዝብ በሽታና ነቀርሳ የሆነች፡፡ የትግራይን ህዝብ አሁን ላለበት ስቃይና መከራ የዳረገችው ይችው የተረገመንችዋ ሕወሃት ናት፡፡ "ማሸነፍ የማትችሉትን ጦርነት አትጀምሩ፣ ጦርነት አያዋጣችሁም" ብለን ስንጮህ፣ ስናስጠነቅቅ፣ በጥጋብና በእብሬት ተሞልተው፣ አንዴ አይደለም ሁለቴ፣ ሶስቴ ጦርነት ከፍተው ነው፣ ለመቶ ሺሆች እልቂት ምክንያት የሆኑት፡፡

ያ አልበቃ ብሏቸው፣ እርቅ፣ ሰላም፣ መግባባት እንዲመጣ ከመስራት፣ የትግራይ ማሀብረሰብ ከአጎራባች ወንድሞቹ ጋር እንደገና እንዲተሳሰር ከማድረስ፣ ህወሃታዊ ሰዎችም፣ አሁን ዘረኛና አጋንንታዊ መንፈስ አለቀቃቸውም፡፡ አሁንም ከትግራይ ሪፑብሊክ ቅዠትአልወጡም፡፡

በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ውስጥ 4 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ነው ያለው፡፡ 1.5 ሚሊዮን ተጋሩ የሚኖሩት ከትግራይ ውጭ በተቀረው የኢትዮጵያ ግዛት ነው፡፡ ነጻ ትግራይ ሲሉ የ1.5 ሚሊዮን ተጋሩ ጉዳይን አስበውታለን ? አንድ በሉ፡፡

ትግራይ በአሁኑ ጊዜ በፌዴራል መንግስት ድጎማ፣ በውጭ እርዳታ ነው እየተዳደረች ያለችው፡፡ ከ4 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ 2.6 ሚሊዮኑ የምግብ ድጋፍ እየተደረገለት ነው የሚኖረው፡፡ 1.5 ሚሊዮኑ ተፈናቃይ ነው በትግራይ ያለው፡፡ በመጠለያ ካምፖች የሚኖር፡፡ የትግራይ መገንጠል እነዚህ ችግሮች ያቃልላልን ? ሁለት በሉ፡፡

በትግራይ መብራት፣ የስልክ፣ የኔትዎርክ፣ የባንክ ወዘተ አገልግሎቶች ከመሃል አገር ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ከፍተኛ የዉሃ ችግር አለ፡፡ የፌዴራል ፕሮጀክቶች ታስበው ነበር፣ በተለይም የመቀሌን የውሃ ችግር ለማቃለል፡፡ እንገነጠላለን ሲሉ ውሃው፣ መብራቱ፣ ኔትዎርኩን አሁን ከመዓከላዊ መንግስት የሚመጡ አገልግሎቶችን ከየት እናገኛለን ብለው ነው የሚያስቡት ? ሶስት በሉ፡፡

ትግራይ በሰሜን ከኤርትራ፣ በምእራብ ከአማራ አማራ ከነ ወልቃይት፣ በደቡብ ምእራብ ከአማራ ክልል ጠለምት፣ በደቡብ ከአማራ ክልል ዋገመራና ሰሜን ወሎ፣ በምስራቅ ደግሞ ከአፋር ክልል የምትዋሰን ናት፡፡ ተገንጥለናል ሲሉ፣ ኤርትራዉያን፣ አማራው ጠላታችን ሆኖ ይቀጥላል ማለታችው ነው፡ ታዲያ ከውጭ አለም ጋር በየት በኩል ሊገናኙ ነው ? ምን አልባት ሆይ ሆይ የሚሏቸው አገራት ካሉ ማለቴ ነው ? አራት በሉ፡፡

አሁን ያሉት ህወሃቶች እርስ በርሳቸው እየተባሉ ነው፡፡ ጌታቸው ረዳ ከዓላማጣ፣ ጻድቃን ገብረ ተንሳኤ ከማይጨው ስለሆነ፣ አድዋ አካባቢ ያሉ ከትግራይ መስተዳደር ሃላፊነታቸው ሊያነሷቸው ደፍ ደፍ እያሉ ነው፤፡ በአውራጃ ሳይቀር እርስ በርስ እየተባሉ ነው፡፡ ትግራይ ነጻ ከወጣች፣ አድዋዎች የበላይ ሆነው የሚዘዉሩትን አገር እንደርታዎች፣ ወይንም ተንቤኖች አሜን ብለው ይቀበሉታልን ? ይህም እንኳን የተረጋጋች የትግራይ ሪፑብሊክም ሊያመጣ፣ እንደው እርስ በርስ በትግራይ የበለጠ ደም መፋሰስ እንዲኖር የሚያደረግ አይደለምን ? ህዝቡም የበለጠ እንዲሰደድና ከ4 ሚሊዮን ወደ 3፣ 2 ሚሊዮን ቁጥሩ እንዲወርድ አያደረግምን ? በህዝብ ብዛት ትግራይን ከሲዳማ ክልል በታች በህዝብ ብዛት የመሆን እድሏ ከፍ ያለ አይደለምን ? አምስት በሉ፡፡

እነዚህ እንድ እሰረቀ ያሉ እብዶች የሚናገሩት፣ እያደረጉት ያለው ነገር፣ የትግራይን ህዝብ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ክፉኛ የሚጎዳ ነው፡፡ የተጋሩ መሬቱ መላው ኢትዮጵያ ነው፡፡ የትግራይ ወገኖች በትግራይ ታስረው መቀጠም የለባቸውም፡፡ ሌላውም የኢትዮጵያ ክፍል አገራቸው ፣ በዚያ ሄደው መስራት፣ መኖር፣ መነገድ፣ ሃብት ማፍራት፣ መውጣት፣ መግባት፣ መማር፣ ማስተማር፣ መመረጥና መምረጥ መቻል አለባቸው፡፡ ከአማራና ከኤርትራ ወገኖች ጋር መነጋገር፣ ይቀር መባባል፣ ላሉ ችግሮች ሁሉን አሸናፊ የሆነ መፍተሄ ማምጣት፣ አንድ መሆን ነው ለትግራይ የሚበጀው፡፡

እመኑኝ ይሄን ነጻ ትግራይ የሚሉት ነገር የትግራይ ህዝብ መከራ የሚያባዛ ብቻ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ መቅሰፍትን የሚያመጣ ነው፡፡

Address

OR

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tana Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tana Times:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share