Dessie Tossa Radio ጦሳ ሬዲዮ ደሴ

  • Home
  • Dessie Tossa Radio ጦሳ ሬዲዮ ደሴ

Dessie Tossa Radio ጦሳ ሬዲዮ ደሴ ደሴ ወሎ ኢትዮጵያ

20/05/2024

የግሼኗ ማርያም እና የገታው ሀጂ ቡሽራ ሀገር
Good morning wollo!

ሰሞኑን ከደረሱን ምዕክቶች በከፊል1)ሳሚ= "የምስራቅ አማራዋ መዲና"ደሴ= "እኔን,,, ነው"? 2) እጂግ በጣም ብዙ ተጠቃሚ ያለውንና መሀል ከተማ ላይ የሚገኘውን የአረብ ገንዳ - ፎቶ አዲስ...
18/05/2024

ሰሞኑን ከደረሱን ምዕክቶች በከፊል

1)ሳሚ= "የምስራቅ አማራዋ መዲና"
ደሴ= "እኔን,,, ነው"?

2) እጂግ በጣም ብዙ ተጠቃሚ ያለውንና መሀል ከተማ ላይ የሚገኘውን የአረብ ገንዳ - ፎቶ አዲስ መንገድ፣ እንዲሁም ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት የሸርፍ ተራ መንገድ ሳይሰራ እና ብዙም አገልግሎት የማይሰጠው የመድሃኒያለም መንገድ ለግንባታ ቅድሚያ የተሰጠበት መስፈርቱ ምን ይሆን? አ3ስኪ ጠይቁልን ሲሉ አንድ አድማጭ በውስጥ ጥያቄ ልከውልናል። እስኪ የሚያውቅ ያስረዳቸው።

3) ታሪካዊው የኦሎምፒክ ሞቴልና፣ ባለ 5 ፎቁ የኔትወርክ ካፌ ህንፃ በአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ሲፈርሱ፣ የእግረኛ መንገድ ዘግቶ፣ የመነሃሪያን ሰዎች አደጋ ላይ ጥሎ በላሜራ ተጣጥፎ ደረቁ ድልድይ ላይ የተሰራውን የፅዋ ማህበርተኞቹን ቤት እስከአሁን ቅቤ እየቀባ ያስቀመጠው ማን ነው?

15/05/2024

ስለደሴ ይመለከተኛል!
!
በከተማችን ሰለሚከናወኑ
ማንኛውም ጉዳዮች መረጃ እንቀበላለን በሜሴጅ አሳውቁን።

የፋኖ አውርቶ አደሮች አለማቸውን ይቀጫሉ፣ በአማራ ልጆች ደም እጃቸውን ታጥበው የሚቆርሱት እንጀራ ግን እንዴት ነው ከጉሮሯቸው የሚወርድላቸው? ኧረ እነሱም እናት አላቸው! እንዳናንተ መደላቀቁ...
12/05/2024

የፋኖ አውርቶ አደሮች አለማቸውን ይቀጫሉ፣
በአማራ ልጆች ደም እጃቸውን ታጥበው የሚቆርሱት እንጀራ ግን እንዴት ነው ከጉሮሯቸው የሚወርድላቸው?
ኧረ እነሱም እናት አላቸው! እንዳናንተ መደላቀቁ ይቅርባቸውና በደማቸው አትነግዱ!

ሸር! ሸር! ሸር! እንኳን ደስ ያላችሁ!!! ይህ ደሴ እና ኮምቦልቻን በ7 ኪሎ ሜትር ብቻ ለማገናኘት የሚያስችለውን የ2 ኪሎ ሜትር የዋሻ (tunnel) ዲዛይን ስራ ለማፅድቅ እና ስራውን ለማ...
12/05/2024

ሸር! ሸር! ሸር!
እንኳን ደስ ያላችሁ!!!

ይህ ደሴ እና ኮምቦልቻን በ7 ኪሎ ሜትር ብቻ ለማገናኘት የሚያስችለውን የ2 ኪሎ ሜትር የዋሻ (tunnel) ዲዛይን ስራ ለማፅድቅ እና ስራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን የመጨረሻ ፊርማ ሊፈረም በክልሉ ፕሬዝዳንት ዴስክ ላይ እንደደረሰ ታውቋል። በጣም ደስ ይላል!!

ይህ ለሁለቱ ከተሞች ብሎም ለአካባቢውና ለሀገራችን ልማት እጅግ አስፈላጊ የሆነ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም ክልሉ ሳያጸድቃቸው መና ሆነው እንደቀሩት ትልልቅ የፕሮጀክት ሀሳቦች እና ዲዛይኖች ሁሉ ይህ ወሳኝ ፕሮጀክትም መክኖ እንዳይቀር ሁላችንም በንቃት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እንስራ!

ሸር! ሸር!
እንደሚታወቀው "ያፒ መርከዚ" የተባለው በባቡር ሃዲድ ግንባታ ላይ እየሰራ የሚገኝ የቱርክ መንገድ ስራ ድርጅት ያስገባቸውን ትልልቅ ማሽነሪዎች ተጠቅሞ ይህ ፕሮጀክት ሊፈጅ ከሚችለው አንድ አስረኛ ወጭ ብቻ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ዲዛይን መስራቱን እና ፋይናንሻል ስቴትመንት ማቅረቡ ይታወቃል።
ይህ ማለት ባህርዳር ላይ የተሰራውን ድልድይ አንድ አራተኛ በሆነ ወጭ ብቻ እንደ ማለት ነው።

ሀሳብ እየሰጠን ሸር እያደረግን ክልሉ ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲወስንና እቅዱ ወደ ትግበራ እንዲገባ እናግዝ!

ሸር!

የባህር ዳር ሰው ጉድጓድ ቆፍሮ፣ ጠጠር ለቅሞ ከገበጣ መጫወት የዘለለ ስፓርት በማይውቅበት ጊዜ እነዚህ ጥበበኛ የደሴ ልጆች ሆጤ ሜዳ ነኝ ወይስ ኦልድትራውፎርድ ያለሁት እስክትል ድረስ እግር ...
11/05/2024

የባህር ዳር ሰው ጉድጓድ ቆፍሮ፣ ጠጠር ለቅሞ ከገበጣ መጫወት የዘለለ ስፓርት በማይውቅበት ጊዜ እነዚህ ጥበበኛ የደሴ ልጆች ሆጤ ሜዳ ነኝ ወይስ ኦልድትራውፎርድ ያለሁት እስክትል ድረስ እግር ኳስን ይራቀቁበት ነበር። ዛሬስ ማን? ለምን? ብለህ በትጠይቅ ግልፅ ነው። የጎጃሙ የምስለኔ መንግስት ከገበሬ ዘር እስከ ስፓርት በጀት ከመንደሩ እንዳይወጣ ባልተፃፈ ህግ እየተመራ ትናንትም በወያኔ ጉያ ሆኖ፣ ዛሬ ደግሞ ቀን ወጣልኝ ብሎ የወሎዎን፣ መዲና የሸግየዎቹን አገር፣ የጥበበኞቹን አንባ ደሴ ከተማን አፈር ለማልበስ እየማሰነ ነው። ወሎ ለፍቅሩም፣ለጥበቡም፣ ለጀግንነቱም ከማንም በላይ መሆኑን ማን ይንገራቸው።
የወሎ ጥያቄ የልማትና የእኩል ተጠቃሚነት እንጂ እንደዛ መንደር ሰዎች የጎጥ አይደለም! ሲጀመር ወሎየነት እና ጎጠኝነት ዘይትና ውሃ ማለት ነውና
ያያኔው ኮከብ ዮናታን በትረ የከተበውን ተመለከቱ!

ዮናታን በትረ እንደ ከተበዉ

💠መጣጥፌ በአማራ ብሔርተኝነት ስም ዘመኑን ባለዋጀ ሾቪኒስቲክ አስተሳሰብ የተገለጡትን 15ኛው ክፍለዘመን ላይ የተቸከሉትን ጠርዝ_ረገጥ ዚዮኒስቲክ  ልሂቃን እንጂ በጅምላ ክርስትያን ወይስ ሙስ...
08/05/2024

💠መጣጥፌ በአማራ ብሔርተኝነት ስም ዘመኑን ባለዋጀ ሾቪኒስቲክ አስተሳሰብ የተገለጡትን 15ኛው ክፍለዘመን ላይ የተቸከሉትን ጠርዝ_ረገጥ ዚዮኒስቲክ ልሂቃን እንጂ በጅምላ ክርስትያን ወይስ ሙስሊም ማህበረሰብን አይመለከትም። እንዲሁ ወሎን በወሎነት የሚያፀኑ ብዙሃን የሆኑትን ተራማጅ አስተዋይ የአማራ ብሔርተኞችንም አይመለከትም።
💠ከታች ጁሃር አንድ ወቅት የፖሰተው ነበር። ከታች እንደምናየው ጎጃም ከሚለው ጀምሮ በጎጃም የተለያዩ ስያሜዎች ከኦሮምኛ ቋንቋ ይመዘዛሉ። በጎንደርም በለሳን የመሰሉ ብዙ ከኦሮሚፋ የሚመዘዙ ስያሜዎች እንዳሉ ይታወቃል። ሆኖም እነኚህ በchauvinistic, Stalinistic & Zionistic አስተሳሰብ በአማራ ብሔርተኝነት ስም የተገለጡ ልሒቃን ስለነኚህ ስሞች ትንፍሽ ሲሉ አይሰማም።
ታዲያ ስለወሎ ብቻ ስለምን ብለን እንጠይቅና ፍርዱን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንተወዋለን። ያልተበከለ ህሊና እውነትን ይፈርዳልና። ወሎን ለይተው ቤተአማራ እያሉ ሲያፏጩ ሁሌ የምንሰማው ነገር ነው። ወሎን ለይተው ለምን? የወሎዬ ማህበረሰባዊ ስሪት ለኢትዮጵያ examplary ተደርጎ ይወሰዳል። ታዲያ ሾቪኒስቲክ ዚዮኒስቲክ ልሒቃኑ ስለምን ጠሉት? ከወሎ ጀምሮ የተለያዩ ከባቢያዊ ስያሜዎቹን እንቀይራለን ሲሉ በተደጋጋሚ ይሰማሉ። ይህን ሲሉ ህዝቡን አማክረው በህዝቡ ይሁንታ ሳይሆን በኃይል ነው። እነርሱ እንደሚሉት ከወሎ ጀምሮ ኦሮምኛ ነው ይሉና የኦሮሞን ህዝብ በወራሪነት ይፈርጃሉ። እንደሚሉት በወራሪ የተሰጡ ስያሜዎች በመቀየር የ15ኛው ክፍለዘመን ስያሜዎች ወደሚሏቸው ይተኩ ባዮች ናቸው። ጥንታዊ ስያሜዎች ብለው በውሸት የፈጠሯቸው እንዳሉም ታዝቤያለሁ። ለምሳሌ ወረባቦ ቤተጊዮርጊስ ነበር ይላሉ። የቀጣጠፉት ውሸት እንጂ ባቦዎች ጥንትም ባቦዎች ነበሩ።
ትውፊት ባህላዊ ማንነት ማጥፋት (cultural genocide) የቅኝገዢነት መንፈስ እንደሆነ ልብ ይሏል። ዚዮኒስቲክ አተያያቸውን justify ለማድረግም ኦሮሞስ ናዝሬትን አዳማ አሰበ ተፈሪን ጭሮ ደዘን ቢሾፍቶ ሲል ቀይሮ የለም ይላሉ? አጂብ ነው!!
💠 ከ15ኛው ክፍለዘመን በፊት ከበሽሎ ወንዝ መለስ ቤተዐምሐራ ተብሎ ይጠራ እንደነበር ይነገራል። በዘመኑ ህዝቡ ቁጥር አነስተኛ ሆኖ የህዝቡ ሃይማኖት constituent በተለይ አማራ ሳይንት አንድ ሃይማኖት ተከታይ የነበረ ነው። የኋላዋን መላ ወሎን የሚያካትትም አልነበረም። ቤተዐምሐራ ሲባልም በደም ሴማዊነትን እንጂ ኩሽን የሚያካትት አልነበረም። ዛሬ አማራ ተብሎ ከሚታወቀው ጋርም ግንኙነትም የለውም።
በወሎ ኦሮሞዎች ስላሉ ኦሮሞዎችን ከመጥላት ነው እንዳይባል በጎጃምም አማርኛ ጆሯቸውን ቢቆርጧቸው የማይችሉ ኦሮሞዎች አሉ።
💠ታዲያ የወሎን ስም መቀየር በቀጣዩ ዓለም ፅድቅ ያስገኛል ተብለው ነውን?
💠እንዲያ እንዳንል ሾቪኒስቲክ ልሒቃኑ ሃይማኖትን ለፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ ካዋሉት እንጂ መንፈሳዊነት ያላቸው አይደሉም። ለነገሩ አነሳሁት እንጂ ፅድቅም ሆነ ኩነኔ የወሎን ከባቢያዊ ስያሜዎች ከመቀየር ጋር ይያያዛል የሚል አስተምህሮ በመፅሐፍ ቅዱስም እንደሌለ የምናውቀው ነው።
💠ታዲያ የወሎን ለይተው ስለምን ጠሉት? በአማራ ብሔርተኝነት ስም የተገለጡት ቆሞቀር ተቸካይ ዚዮኒስቲክ ልሒቃን በልባቸው የቋጠሩት ፅንፍ የረገጠ ክፋት ሌላ ነው። ወሎ ሙስሊም እና ክርስትያኑ በብዛት ተሰባጥሮ የሚኖርበት ቀጠና ነው። ወሎ ሲባል አፈሩም ዛፍ ቅጠሉም ህዝቡም ወሎዬ ለማለት ነው። የእነርሱ ጥላቻ ሙስሊሙ ከሌላው አከባቢ በተለዬ ብዛት አለው ከሚል አተያይ የመነጨ ነው። ወሎ ፍፁም Secular የሆነ ስያሜ ሲሆን በሌላ በኩል ቤተአማራ secular አይደለም። በተለይ የዚዮኒስቶች ቤተአማራነት አረዳድ በታሪክ ከምናውቀው የተለዬ ነው። ቃሉ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ከበሽሎ ወንዝ መለስ በአንድ ሃይማኖት ተከታዮች ጥቅም ላይ ሲውል የነበረ ስያሜ ነው።
ዛሬ ላይ በአማራ ብሔርተኝነት ስም የተገለጡት ሾቪኒስቲክ ተቸካይ ኋላቀር ልሒቃን ግን ቃሉን የሚያውሉት ለመላ ወሎ ነው። ከሚሴን ምድረገኝ ነበር ይላሉ። የሚገርመው ከሰገሌ በኋላ ወሎ ከተማ አከባቢዎች እየተጋዙ የሠፈሩ ሠፋሪ ውላጆች በታሪክ በ1543 አከባቢ ጀምሮ የወሎ ኦሮሞ ተብለው በታሪክ ምሁራን የሚታወቁትን እናባራለን ሲሉ ዛቻ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሙከራዎችም የሚመስሉም ስንታዘብ ኖረናል። አጂብ ነው ነው ነገሩ!! ነባሮቹን የሠፋሪ ውላጆች ሊያባሩ ማለት ነው። በነገሬ ላይ የሠፋሪ ውላጆች ስል አገላለፄ Native ወሎ ክርስትያኖችንና ሙስሊሞችን እንደማይመለከት ለማመላከት ነው። ከሰገሌ ጦርነት በኋላ በአስገባሪነት በወሎ በየትኞቹ ከተሞች አከባቢዎች እንደሠፈሩ ተለይተው ስለሚታወቁ ነባሮቹን ለማፈናቀል ሲነሱ የወሎን ማህበረሰብ ዕረፍት እየነሱ ያሉት የሠፋሪ ውላጆች ተለይተው ራሳቸው ይጠረጋሉ።
እነኚህ ተቸካይ አድሃሪያን የሆኑ ልሒቃን ቡድን ቤተአማራ ሲለን የወሎን መሬት መሆኑ ደግሞ ይአጂባል። ጥንት ሴሜቲክ ቤተዐምሐራዎቹ ከአርጎባው ከኦሮሞው ከትግሬው ወዘተረፈ ጋር ተጋብተው ፣ ባህላቸውን አውርሰውም ተወራርሰውም ተጋምደውም ተዋህደውም በመደጋገፍ በአብሮነት መሠረት ላይ የታነፀ ወሎዬነት ሲሉ የሰየሙት ማህበረሰባዊ ስሪት አንፀው አውርሰው ካለፉ ዘመናት ተቆጥረዋል።
💠ከፋነን ጋር በተያያዘ አንድ ያስገረመኝን ነገር ላንሳ!! በግሌ ማናቸውንም ውጊያ ጦርነት አልደግፍም። የልሒቃን ቅራኔዎች በውይይት ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በመደራደር በመነጋገርና በሠጥቶ መቀበል ፖለቲካዊ ድያሎግ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ በፅኑ አምናለሁ። ጦርነት በህዝብ ላይ መከራ ነውና። በዚያም በዚህም የሚረግፉት ወገኖች ናቸው። ማንኛውም ጦርነት የሚያደርሰው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አገርንም ህዝብንም ለመከራ ስለሚዳርግ ግጭቶችና ቅራኔዎች የህዝብን ጥቅም ባማከለ በሠላማዊ መንገድ መፈታቱ ይበጃል ባይ ነኝ። ከጦርነት ጋር በተያያዘ ከላይ ያስቀመጥኩት የበኩሌ አተያይ እንደተጠበቀ ሆኖ በወሎ አከባቢዎች በኮሎኔል ፋንታሁን መሪነት በፋነንነት የሚንቀሳቀሱ [rebels] እንዳሉ በሜዲያ እየታዘብን ነው። በኮሎኔሉ ሥር ያሉት ፋነኖች ሙስሊምም ክርስትያንም ቅልቅል ናቸው። የወሎ ዕዝ ነን ሲሉ ያወጡትን መግለጫም በሜዲያ እንዳነበብኩም አስታውሳለሁ። ታዲያ በአማራ ብሔርተኝነት ስም የተገለጡት በሾቪኒስቲክ አስተሳሰብ ላይ የተቸከሉት ልሒቃን ለጎጃሞቹ ለጎንደሮቹ ደጋግመው በአሜሪካ የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ሲያዘጋጁ በኮሎኔል ፈንታው ሙሃባ ሥር ላሉት ግን አንድም ጊዜ አልሰማንም። ምክንያታቸው ደግሞ ከወትሮ መሠሪ ባህሪያቸው አንፃር ወሎ የሚለውን መሠረት ስለያዙ እና ከፋነኖቹ መካከል ሙስሊሞችም ስላሉበት እንደሆነ መገመቱ ምክንያታዊ ይሆናል። እንዲሁ ከትግራይ ጋር ጦርነት ሲጀመር ገና ከውጥኑ በዳውንቴው ገዱ ተጠምዝዘው ወሎዬነትን በመካድ የሩቅ ምስራቅ ወይም ምስራቅ ምናምን ነን ሲሉ ለሰየሙት ፋነኖች ሲያዋጡ እንደነበር በሜዲያ ማንበቤን አስታውሳለሁ። ተቸካይ ኋላቀር ልሒቃኑ ለሁለት ቡድን በተከፈሉ ወሎዬዎች መካከል እንኳን እንደት ልዩነት እንደሚፈጥሩ ልብ ማለት ይቻላል።
ስለሾቪኒሶቲክ ዚዮኒስቲክ ልሒቃኑ የሴራ እና የክፋት ትብታብ ቢወራ አያልቅም_ ይበቃል።
ስለሴራቸው ትብታብ የህሊና ፍርዱን ለአንባቢዎች ትቻለሁ።

Hara Hari

በ4.5ሚሊየን ብር ጀሜ ላይ ጤና ጣቢያ ግንባታ ተጀመረደሴ:ሚያዚያ24/2016(ደሴ ኮሚኒኬሽን)የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሺመልስ ጌታቸው እና የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ...
03/05/2024

በ4.5ሚሊየን ብር ጀሜ ላይ ጤና ጣቢያ ግንባታ ተጀመረ

ደሴ:ሚያዚያ24/2016(ደሴ ኮሚኒኬሽን)
የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሺመልስ ጌታቸው እና የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሰይድ የሱፍ በተገኙበት ጀሜ ላይ በ4.5 ሚሊየን ብር የሚገነባውን ባለ አንድ ብሎክ ጤና ጣቢያ ግንባታ አስጀምረዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ጤና ጣቢያዎች ለጀሜ አካባቢ ማህበረሰብ ተጀራሽ አይደለም ነበር ያሉት የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሰይድ የሱፍ አካባቢው ለዘመናት ይጠይቁት የነበረ እና በአካባቢው የጤና ጣቢያ አለመኖር ችግርን የሚፈታ ከተማ አስተዳደሩ ችግራቸውን አይቶ ምላሽ የሠጠበት ፕሮጀክት ነው።

በዚህ አመት 1ብሎክ ግንባታ በ4ወር ውስጥ አጠናቆ እንዲያስረክብ ከኮንትራክተሩ ጋር ውለታ ፈፅመን ወደስራ ገብተናል ያሉት አቶ ሰይድ የሱፍ በሚቀጥለው አመት ሙሉው ግንባታ ይገነባል ብለዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ ግንባታው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ በባልተቤትነት በመያዝ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የጀሜ ጤና ጣቢያ ግንባታ የሚሠራው ሠለሞን ደምሴ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ በ4.5ሚሊየን ብር ባለአንድ ብሎክ ህንፃውን ገንብቶ ለማስረከብ ውለታ ቢወስድም በ2ወር ውስጥ ግንባታውን አጠናቆ እደሚያስረከብ ገልጸዋል።

የአካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ እብራሂም ለበርካታ አመት ስንጠይቅ የነበረው ጤና ጣቢያ ይገንባልን ጥያቄ በመመለሡ ተደስተናል ጤና ጣቢያ በቅርበት ባለመኖሩ ከ3በላይ ፊርማታዎችን ተጉዘን ነበር ህክምና የምናገኘው አሁን ላይከተማ አስተዳደሩ ምላሸ ሰጥቶ አካባቢያችን ላይ በመገንባቱ የእናቶችና ህፃናት ሞትን ይቀርፋል፣ ከእንግልት ያድነናልና ህብረተሠቡ ለግንባታው የተለያዩ ድጋፎችን ከጉልት እስከ ገንዘብ ድረስ ድጋፍ ለማድረግና የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ብለዋል።

ክልሉ ለአመታት በጀት እያጠፈ፣ ያልተሰራ ስራ ሪፓርት እያስደረገ፣ ምስለኔዎችን እየሾመ የወሎዎን መዲና ከልማት እርምጃዋ ቀፍድዶ ቢይዛትም አሁን ብቅ ያሉት የከተማዋ አመራሮች ማህበረሰቡን አስ...
22/04/2024

ክልሉ ለአመታት በጀት እያጠፈ፣ ያልተሰራ ስራ ሪፓርት እያስደረገ፣ ምስለኔዎችን እየሾመ የወሎዎን መዲና ከልማት እርምጃዋ ቀፍድዶ ቢይዛትም አሁን ብቅ ያሉት የከተማዋ አመራሮች ማህበረሰቡን አስተባብሮ እየሰራው ያለው ስራ ይበል የሚያሰኝ ነው።
ወትሮም ቢሆን የደሴ ማህበረሰብ በግብር ከፋይነትም ሆነ ለሀገሩ በተጠራበት በመሰለፍ ዙሪያ ቀዳሚ ቢሆንም የክልሉ በጀት የሚፈሰው ግን ወዲያ—ወዲያውን ሆኖ እእዚህ ደረስን!

05/02/2023
ደሴ ዛሬ
05/02/2023

ደሴ ዛሬ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie Tossa Radio ጦሳ ሬዲዮ ደሴ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share