Aliyu Amba Communication affairs office

  • Home
  • Aliyu Amba Communication affairs office

Aliyu Amba Communication affairs office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aliyu Amba Communication affairs office, News & Media Website, .

08/05/2024
16/10/2022

06/02/2015

የአንኮበር ወረዳ ኢንዱስትሪ ና ኢንቨስትመንት ፅ/ቤት ኢንቨስት ካደረጉ ባለሀብቶች እንዲሁም ከታሳቢ ባለሀብቶች ጋር በአልዩ አንባ ከተማ ቀበሌ የምክክር መድረክ አካሄደ ።

የአንኮበር ወረዳ ኢንዱስትሪ ና ኢንቨስትመንት ፅ/ቤት በአልዩ አንባ ከተማ ቀበሌ ከሚገኙ ባለሀብቶች እንዲሁም ከአጋር አካላቶች ጋር ማለትም ከአልዩ አንባ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት እና ከከተማው ቀበሌ አስተዳደር ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል ። የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፅ/ቤቱ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሪት አበበች ደምሴ ሲሆኑ መድረኩ በዳቦ ቆረሳ ተከፍቷል ።
በአጠቃላይ በመድረኩ ስለአልዩ አንባ ከተማ ገፅታ ገለፃ፡ በወረዳው ስላሉት የኢንቨስትመንት አማራጮች ፡ለኢንቨስትመንት ያሉ ምቹ ሁኔታዎች ፡
የኢንቨስትመንት ፍቃድ ለማዉጣት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡
ኢንቨስት ሲያደርጉ የሚያገኟቸውን ማበረታቻዎች፡- የገቢ ግብር ነፃ ማበረታቻ እና የግምሩክ ቀረጥ ነፃ ማበረታቻ እንዲሁም ማበረታቻ የሚያገኙ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ዋና ዋናዎቹ ተጠቅሰው ግንዛቤዉ የተሰጠ ሲሆን የከተማ መሬት ለባለሀብቱ እንዴት መተላለፍ (ማግኘት ) እንዳለባቸው የአልዩ አንባ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሸዋዬ ከተማ ገለፃ አድርገዋል።
በመጨረሻም ከባለሀብቶች ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶ ተጠናቋል ።

14/10/2022

የአንኮበር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት የወረዳውን የ2015 በጀት ዓመት የበጀት ድልድል ይፋ አድርጓል፡፡

የወረዳው ገንዘብ ኢኮኖሚ ጽ/ቤት በበጀት ሰሚ፤ በአስተዳደር ምክር ቤትና በወረዳው ምክር ቤት አጸድቆ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ በዚህም መሠረት ለ2015 በጀት ዓመት የተመደበው ጠቅላላ የበጀት ጣሪያ 202 ሚሊዮን 402 ሽህ 320 ብር ሲሆን፤ከክልል መንግሥት የሚላክ ድጎማ 133 ሚሊዮን 975 ሽህ 936 ብር፤ በወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት የሚሰበሰብ የሚሰበሰብ 60 ሚሊዮን 977 ሽህ 752 ብር፤ ከውስጥ ገቢ 7 ሚሊዮን 309 ሽህ 821 ብር፤ ከውጭ እርዳታ 139 ሽህ 411 ብር መሆኑን ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህም ውስጥ ለደመወዝ 162 ሚሊዮን 173 ሽህ 215 ብር፤ ለስራ ማስኬጃ 33 ሚሊዮን 689 ሽህ 694 ብር፤ ከ6 ጤና ጣቢያዎች የውስጥ ገቢ 7 ሚሊዮን 309 ሽህ 821 የሚሸፈን በአጠቃላይ ለካፒታል በጀት 6 ሚሊዮን 539 ሽህ 411፤ 139 ሽህ 411 ብር በውጭ እርዳታ የሚሸፈን ሲሆን፤ ከክልሉ መንግሥት ድጎማ ውስጥ 2 ሚሊዮን ብር ለአልዩ አምባና ጎረቤላ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤቶች ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር ይደርሳል፡፡

የወረዳው ድህነት ቅነሳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የደመወዝና የስራ ማስኬጃ ድምር የሚከተለውን ይመስላል፡፡ ግብርና ጽ/ቤት 10 ሚሊዮን 801 ሽህ 261 ብር፣ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት 1 ሚሊዮን 283 ሽህ156፣ ትምህርት ጽ/ቤት 80 ሚሊዮን 261 ሽህ 982፣ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት 3 ሚሊዮን 282 ሽህ 742፣ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት 7 ሚሊዮን 950 ሽህ 772 ብር እንዲሁም ከነዚህ ውጭ ያሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ደግሞ 83 ሚሊዮን 202 ሽህ 307 ሲሆን አጠቃላይ 188 ሚሊዮን 553 ሽህ 88 ብር ነው፡፡

የወረዳው የ2015 ዓ/ም በጀት ዓመት የሴክተር መስሪያ ቤቶች የካፒታል በጀት ድልድልን በተመለከተም፤ የአንኮበር ወረዳ ውሃ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለላይ ጎረቤላና ጨፋ ቀበሌ ባዮ ጋዝ ግንባታ 1 ሚሊዮን 300 ሽህ ብር፣ መንገድና ትራንፖርት ጽ/ቤት ከዘጎ እስከ ሐር አምባ ከተማ ላለው የመንገድ ጥገና 1 ሚሊዮን፣ አዲስ ለተቋቋመው የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ጽ/ቤት በወረዳው ደረፎ ቀበሌ አጋምበረት ጎጥ ለሚሰራው የመስኖ ካናል 1 ሚሊዮን፣ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግንባታና የኤሌክትሪክ ወርክ ሾፕ ግንባታ 1 ሚሊዮን 500 ሽህ፣ ትምህርት ጽ/ቤት ለሐር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የላብራቶሪ ክፍል ግንባታ 1 ሚሊዮን 300 ሽህ፤ እንዲሁም ለጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለዋሻ ቀበሌ ጤና ኬላ መጸዳጃ ቤት ግንባታ ለዋሽ ፕሮጀክት መቀናጆ የተያዘ በጀት 439 ሽህ 411 ብር ሲሆን አጠቃላይ 6 ሚሊዮን 539 ሽህ 411 ብር መሆኑን ከአንኮበር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

20/09/2022
9.1.15
19/09/2022

9.1.15

18/09/2022

ጥራታቸውን የጠበቁ ብረቶች አቅርበንላችኋል
የሀገር ውስጥ የአርማታ ብረት በግሬድ 75 ዋጋ ዝርዝር
•8mm=488
•10mm=762
•12mm=1096
•14mm=1495
•16mm=1955
•20mm=3050
የቱርክ ብረት ዋጋ
8mm=510
10mm=800
12mm=1140
14mm=1555
16mm=2030
20mm=3170
call us 0911232662
0923249212

16/09/2022

የሲሚንቶ ስርጭትና ዝውውርን ለመወሰን የወጣ የሕዝብ ማስታወቂያ‼️

1. ማንኛውም የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት ለተፈቀደላቸው አካላት ብቻ የሲሚንቶ ሽያጭ መፈፀም አለበት፤

2. በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት በፌደራልም ወይም በክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ በመወሰድ ለየክልልና ከተሞች እንዲያቀርቡ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ ማናቸዉም ሰው የሲሚንቶ ምርት ለግብይት ያዞ መገኘት አይችልም፤

3. ለአንድ ጊዜ ለግል ወይም ለቤተሰብ ፍጆታ የተፈቀደ ከፍተኛው የሲሚንቶ ምርት መጠን 15 ኩንታል ነው፤

4. በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲሚንቶ እንዲያከፋፍሉ የተፈቀደላቸው አካላት ወይም በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተፈቀደላቸው ተቋራጮች የገዙትን የሲሚንቶ ምርት ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለሽያጭ ማቅረብ፣ ለመሸጥ መሞከር ወይም ከተፈቀደለት መስመር ውጪ በማንኛውም ማጓጓዣ ጭኖ መገኘት፣ ማጓጓዝ፣ በንግድ መደብር ወይም በማናቸውም ቦታ አከማችቶ መገኘት የተከለከለ ነው፤

5. ማንኛውም ሰው ከዚህ በላይ የተገለጸውን የሕዝብ ማስታወቂያ ተላልፎ ከተገኘ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 43 እና አግባብ ባላቸው ሌሎች ህጎች መሠረት በአስተዳደራዊ እና በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል፤

6. ይህ የህዝብ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሌላ የህዝብ ማስታወቂያ እስከሚሻር ድረስ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
©የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

14/09/2022
13/09/2022

ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር-ቤት የተላለፈ ማሻሻያ መልዕክት።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔ አስተላልፏል።

1ኛ. በከተማ አስተዳደሩ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ጠዋት ከ11ሰአት በፊት መውጣት ማታ ከ1:00 ሰዓት በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ክልክል ነው።
2ኛ. በከተማው የሚገኙ ሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንዲሁም ከለሊቱ 11 ሰአት በፊት እንቅስቃሴ ሲያደርግ የተገኘ ማንኛውም ተሽከርካሪ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።

3ኛ. በከተማው የሚገኙ መጠጥ ቤቶች ምግብ ቤቶች ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 4:00 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።

4ኛ. በከተማው በሚገኙ የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

5ኛ. ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ሀይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው ይዞ የተገኘ ይወረሳል።
6ኛ. ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የሚደረጉ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

7ኛ. የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታና ወሬን ማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ ሽብር መንዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
8ኛ. አዳር የሚሰሩ በከተማችን ያሉ ፍብሪካዎችና ድርጂቶች ድርጁቱ በሚሰጣቸው ህጋዊ መረጃ ና በፀጥታ መዋቅሩ የተረጋገጠ የይለፍ ከያዘ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡
9ኛ. መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀት አካባቢውን ቀንና ሌሊት ከሰርጎ ገቦች በንቃት መጠበቅ አለበት።
10ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ፀጉረ ልውጥ ሲያጋጥም በፍጥንት ለህግ አካል ጥቆማ በመስጠት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረግ ከማህበረሰቡ ይጠበቃል።
11ኛ. የከተማው ባለሆቴሎች እና አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ግለሰብ በድርጅታችሁ ሲያጋጥማችሁ ለህግ አካላት ጥቆማ እንድትሰጡ።

12ኛ. በከተማ አስተዳደሩ ያላችሁ የቤት አከራይዎች የምታከራዩትን ግለሰብ ማንነትት መታወቂያ በመጠየቅ ለይታችሁ እንድታከራዩ የተከራዩንም መረጃ በፎርም በመሙላት ለከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ እንድታሳውቁ መልዕክት አስተላልፏል።
13ኛ. ማንኛውም ሰው የመከላከያ የልዩ ሀይል ወዘተ የደንብ ልብስ ለብሶ መገኘት በህግ ያስቀጣል ።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን የውሳኔ ሀሳቦች የሚጥስ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድበትም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር

መስከረም 3/1/2015 ዓ.ም

11/09/2022

የአንኮበር ወረዳ የአልዩ አምባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
መጪው አዲስ ዓመት የሀገራችን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲረጋገጥ አበክረን የምንሰራበት ዓመት ይሆናል፡፡
እንኳን ለ2015 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ ፡አደረሰን፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን በቋንቋ ፣ በሀይማኖት ፣በፖለቲካ አስተሳሰብ ያለን ልዮነት ሳይገድበን የኢትዮጵያን ጠላቶች በተደጋጋሚ አሳፍረን የመለስን እና የሀገራችንን አንድነት ጠብቀን ያቆየን ህዝብ ነን። ዛሬም ለሰላም አማራጭ ጆሮ ያልሰጠው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ ህዝባችን ላይ ጦርነት አውጆ እየፈፀመ ይገኛል፡፡
ምንም እንኳን መንግስት ችግሩን በውይይት ለመፍታት ፅኑ አቋሞ ቢኖረውም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጣው ባንዳ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን እና ጥምር ሀይሉ በተለመደው ጀግንነቱ ጦርነቱ እየተቀለበሰ ይገኛል፡፡ ህዝባችንም በተለያየ አግባብ ደጀንነቱን እያረጋገጠና ጎን ለጎን የልማትና የመልካም አስተዳዳር ስራዎችን ሳይንጠባጠቡ እንዲቀጥሉ እየሰራ ይገኛል።

🍧🏆🍧መልካም በዓል !!!💚💞💖
አ/አ/ ከ/መ/ማ/ቤት
መስከረም 01/01/5015

እንኳን ለ2015 ዓ/ም በሠላም አደረሳችሁ !!
10/09/2022

እንኳን ለ2015 ዓ/ም በሠላም አደረሳችሁ !!

09/09/2022
09/09/2022

ከሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ መካሻ አለማየሁ የተላለፈ የዘመን መለወጫ 🌿
☀የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት☀

ለመላው የሀገራችን ፣ የክልላችን እንዲሁም የዞናችን ህዝብ ፤

እንኳን ለ2015 የዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በቅድሚያ አዲሱ አመት የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተባበር እና የአንድነት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።

ያለፈው 2014 ዓመት እንደሀገርም ሆነ እንደ ክልል እንደ ዞናችንም ቢሆን በርካታ ተስፋዎች እና ፈተናዎች ያስተናገድንበት አመት ነበር ፣

ከመልካም አፈፃፀሞቻችን መሳ ለመሳ በርካታ ፈተናዎች የተጋፈጥንበት ዓመት ቢሆንም ፈተናዎችን በድል ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በላይ በተሻለ ሀገራዊ አንድነት መንፈስ ተንቀሳቅሰናል ፤ ፈታኞቻችንንና ፈተናውን ሁሉ ድል እያደረግን ከተደገሱልን ውስብስብ የጠላት እቅዶች ድል አድርገን እየወጣን ነው።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፤ የአማራን ህዝብ ለማዋረድና አንገት ለማስደፋት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሀይልና ግብረ- አበሮቹ ጋር አንገት ለአንገት የተናነቅንበት ፤ ህዝባችን ከጫፍ እስከ ጫፍ ለህልውና ትግሉ ግንባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን መስዋትነት በመክፈል ሀገሩን ብሎም ማንነቱን ለማስጠበቅ በጀግንነት የተንቀሳቀሰበትና የተዋደቀበት ዓመት እንዲሁም ጠላት ከጣርማበር ጫፍ ደርሶ በተባበረ ክንድ ልኩን አሳይተንና አሳፍረን የመለስንበት ነበር።

በዚህ ፀረ ኢትዮጵያ ሃይል የተከፈተብንን የሽብር ጥቃት ለመመከትና ለማክሸፍ የዞናችን ፣ የክልላችንና የኢትዪጵያ ህዝብ ላሳየው አንድነትና በፊት ተሰላፊ ሆኖ ጠላትን በአጥንትና ደማቸው ዋጋ ትግል ላደረገው በየደረጃው ለሚገኘው ወገናችን ሁሉ ከፍተኛ ምስጋናየን አቀርባለሁ።

የዘንድሮውን አዲስ አመት የምንቀበለውም ለሶስተኛ ጊዜ አሸባሪው ወረራ በፈፀመብን ሰአት ፣ ለሁለተኛ ጊዜ የህልውና ትግል በምናደርግበት ውስጥ ሆነን አሸባሪውን ወራሪ ሀይል በአማራ ክልል በወረራ በገባባቸው በሁሉም አካባቢወች መቀበሪያው እንዲሆን እየታገልን፣ የደጀንነት ስራችንን ለጥምር ጦራችን እያደረግን በአንፃሩ ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችንን እየደገፍንና እያሰብን ጥረት እያደረግን የምንቀበለው አዲስ ዓመት ነው።

የጀመርነው ፀረ ትህነግ ትግል የሚያበቃው ይህ ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ አማራ የሆነው አሸ*ባሪ ለአገራችን ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ላይ ስናደርሰው ብቻ መሆኑን አዉቀን ለተጨማሪ እና ዘላቂ መፍትሔ ለሚያመጣው ትግል ራሳችንን ይበልጥ ማዘጋጀት አንድነታችንን ማጠናከር አለብን።

ስለሆነም የ2015 አዲስ ዓመትን ስንቀበል እንደተለመደው ሁሉ ሙሉ ቀልባችንና ስሜታችን የመንደራችንና የቀያችን የጎጇችን ድባብ እንደ ሸዋ ባሕል እንደ ኢትዮጵያውያን ወግ "በአል በአል" እንዳይሸት አሸባሪው ቡድን በከፈተብን ግልጽ ወረራ እና ጭፍጨፋ የልብ ስብራታችንን በድጋሚ ያስተናገድንበት ቢሆንም ኢትዮጵያዊና አማራዊ አንድነታችንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በማጠናከር ፈተናዎችን በድል ተሻግረን ጠላቶቻችንን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተን እብሪታቸውን ከልክ አስገብተን ለተጨማሪ ትግል በመዘጋጀት የወ*ያኔ አሸባሪነት ፋይሉ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲዘጋ አድርገን የምንተባበርበት መሆን አለበት ።

በዚህ አጋጣሚ በዚህ ታሪካዊ ተጋድሎ አገራችንን ከብተና ህዝባችን ከውርደት ላዳናችሁ የምን ጊዜም ጀግኖች የቁርጥቀን ልጆቻችን፣ ከብረት የጠነከረው ደጀኑ ህዝባችን እና ለነበልባሉ የጥምር ጦራችን ያለኝን ልባዊ አክብሮትና ምስጋና በእኔና በዞናችን ህዝብ ስም ለመግለፅ እወዳለሁ።

በዓሉንም ስናከብር ውድ የህይወትና የደም ዋጋ እየከፈለ ያለውን ወገን በደጀንነት በመደገፍ ፣ ቤተሰቦቻቸውንም በመጠየቅ፣ የተፈናቀሉትን በመርዳት ፣ በዓሉንም አብረናቸው በማክበር እንዲሆን እጠይቃለሁ።

አዲሱ አመት ፈተናዎቻችን ሁሉ በድል ተሻግረን የኢትዮጵያን ብልጽግና የምናይበት እንደሚሆን እምነቴ የፀና ነው።
በተለይ በ2015 ዓመት የሸዋ ህዝብ በሁሉም ዘርፍ ከፍ እንዲል አንድነታችን ጠንክሮ እንዲወጣ በምናደርገው ጥረት የሁላችሁም ድጋፍ አስፈላጊ ነው እና፤
ድጋፋችሁ አይለየን ስንል በትህትና በዞን አስተዳደሩ ስም እንጠይቃለን!
መልካም አዲስ አመት🙏🏽

"ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!"

መካሻ አለማየሁ
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ሰሸዞአ

03/09/2022
02/09/2022

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aliyu Amba Communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share