axemed.com

axemed.com happy mowulid

24/04/2022

እብደቱ ሲጨምር ክኒኑን መጨመር ግድ ይላል!
✦✦
የጀበሉ የአስተሳሰብ ጥግኮ.... የሚደንቅ ነው። እነሆ ዛሬም እንዲህ ሲል አስቧል።

"የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግር ዑለማው ነው ወይስ ተርታው ህዝብ ነው? ብዬ ስል የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ችግር ዑለሞች ናቸው።"

አለ ተራራው ብራንድ በሆነው አስተሳሰቡ።

ደሞኮ ከዚህ አስተሳሰብ ውጭ ሌላ ጠብቄ ከፍቼ መስማቴ።አጃኢብ ነው።ፍርድህን ነው ተራራው።ድሮስ ቢሆን ينبغي ማለት አቅቶት የንበጊ ያለ ሽፍታ አንደበት ከዚህ ሌላ እንዴት ሊናገር ይችላል? እንዲህ ያለው ጭንቅላትኮ እንዴት ነገርና ሴራ ሸርቦ በበሬ ወለደ ዜና ህዝብ ማበጣበጥና በጨዋታው አትራፊ መሆንን እንጂ ሌላን ሊያስብ አይችልም።ምክንያቱም ከጥንቱ ሲሰራ የሸር ቋት ይሆን ዘንድ ተፈርዷልና።

አንድ ገራሚ ሻዒር ያንተ አምሳያ አጋጥሞት ምን አለ መሰለህ
ما ضر شمس الضحى في الأفق ساطعة
ألا يرى نورها من ليس ذا بصر

"ረፋድ ላይ ወለል ብላ የወጣችውን ጀንበር አይን የሌለው ሰው አላየኋትም [ብሎ ቡራከረዩ ቢል]የርሱ አላየሁም ማለት ጀንበሯን፣ ብርሃኗን ከቶ [ሊያጠፋው] አይቻለውም።"
አለ።

መቼም "የንበጊ" የሚል ብራንድ አንደበት ሺዕር የማንበብ አቅም ስለማይኖረው ብዬ ነው በትርጉም ያቀርብኩልህ።

የሰወዬው ችግር እንዳንተ አይኑ ላይ እንጂ ጀንበሯ ላይ አልነበረም።
ስለሆነም ስለዑለሞቻችን ለማወቅ ሺ አመት መማር ይኖርብሃል።በቀላል ተፊሲር አይገባህም ለማለት ነው።
✦✦✦
ባትሰማም ስማ ተራራው።

የኢትዮጵያ ዑለሞች ማለት
አንተና መሰሎችህ መጥተው ያለ አቅማቸው ከመወጣጠራቸው በፊት ያለ አንዳች ክፍያና ጥቅማጥቅም ለዲናቸው ኖረው በዲናቸው ያለፉ፣ ተከታዮቻቸውም በዚሁ የቀጠሉ የዲን ብርሃኖች ናቸው፣አዎን ህዝበ ሙስሊሙን በፍቅር አንድ አድርገው የመሩ ዘመን የማይረሳቸው ታላላቆች ማለት ዑለሞቻችን ናቸው።በነርሱ ጊዜ አንዋር መስጅድን ጨምሮ ሌሎች መስጅዶች እንደ አሁኑ ለአንድ ሶላት ሁለት ኢማም አይለይባቸውም ነበር።እናንተ መጣችሁና በገንዘብ ሃይል የሙስሊሙን አንድነት ከፋፈላችሁት።

እርግጥ ነው አንተና መሰሎችህ በአጠቃላይ የውሃብያ አስተሳሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ መስፋፋት ከጀመረ ወዲህ ለኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አንድነት ካንሰር ሆናችኋል።ሳዑዲ ሰራሹን የውሃቢዝም አስተምህሮ በገንዘብ ሃይል በመላ ኢትዮጵያ ማሰራጨት ከጀመራችሁ ወዲህ አዎን ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ተበጥብጠዋል።

ከአጼው የደረሰባቸው ግፍ አልበቃ ብሎ በእንቅርት ላይ እንዲሉ እናንተም ለዲን እንጠቅማለን በሚል የዳቦ ስም በርካታ አሳፋሪ ተግባር ፈጽማችኋል።ከዚህ በኩል ካየነው አዎ ዑለሞቻችን ለናንተ የጥቅም ጋጋት ፊት ስላልሰጡና መስመራቸውን ጠብቀው ስለኖሩ እንደ ችግር ቆጥራችኋቸዋል።ለዚያም ነው ቀድመህ 9ኙ ኮሚቴ ላይ የክልልና የቦርድ ብለህ የመረጥካቸው ባንተ ሳንባ የሚተነፍሱ አሳዛኝ ሰዎችህ በኩል ያሰብከው አጀንዳ መና ሲቀር ጊዜ ሰብስበህ "የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ችግር ዑለሞች ናቸው።"በማለት ያቀረሸኸው።ገና ብዙ ትላለህ።

ዑለሞች ስትል አህሉሱና ዑለሞችን እንደፈለግክበት ለመረዳት ነብይ መሆን አይጠበቅብንም።ምክንያቱም ከዚህ ቀደም ጠምጣሚ ካድሬ ብለህ ያሾፍከው ዶክተር ጀይላንን አስበህ ሳይሆን ሙፍቲንና መሰሎቻቸውን አልመህ ነው።ይሄ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ችግር ዑለሞች ናቸው ከሚለው ቃልህ በፊት"ማክበሩ ምናምኑ እንዳለ ሆኖ ...." ያልካት አማርኛ "አድኖ መግደል" በሚል ዘይቤ ለመሻይኾቻችን ያለህን የንቀት ጥግ ለማሳየት ተጠቀመህባታልና እናመሰግናለን።ኢንሻአሏህ የንቀትህን ዋጋ ደግሞ ጀሊሉ ሳይከፍልህ አይቀርም።ዑለሞቻችን ግን ሻዒሩ እንዳለው የአንተና መሰል ሞገደኛ ሰዎችህ ጋጋታ አበደን ከክብራቸው ማማ ሊያወርዳቸው አይችልም።እናማ ስንደመድመው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የችግር ቋት ትናንትም እናንተ ነበራችሁ ዛሬም አንተና መሰሎችህ ናቸው።

ደጋግሜ አስረግጬ የምነግርህ ነገር ቢኖር መቼም ቢሆን እስልምናችን በዘራፊዎች ሊመራ እንደማይችል ነው።ታላላቅ መሻይኾቻችን የመሰረቱት መጅሊሳችን በታላላቅ የዲኑ ልሂቃኖች የበላይነት እንጂ መመረጥን በምርጫ ኮሮጆ በሚለኩ የዋህ ፖለቲከኞች አይደለም።ይሄን ደግሞ ኢንሻአሏህ በቅርቡ እውን ሆኖ ታየዋለህ።

ሺዕሩን ደገምኩልህ

ما ضر شمس الضحى في الأفق ساطعة
ألا يرى نورها من ليس ذا بصر
ደግመህ ከተረጎምከው አደንቅሃለሁ።
✦✦✦
አህመዲን ጀበል የተባረረውን ቦርድና የክልል መጅሊስ አመራር ተብዬዎችን ሰብስቦ እንዲህ የሚንጨረጨረው ማን ስለሆነ ነው? ብላችሁ ጠይቁ።መልሱን ታገኙታላችሁ።
ማን መረጠው? ውሃብያዎች መርጠውት ይሆናል።ከአህሉሱና ግን ማንም አልመረጠውም።ዘጠኙ ኮሚቴ አለ? የለም ፈርሷል።17ቱ ኮሚቴ ሙስሊሙን ይወክላል? አይወክልም።ዓሊም ነው? ፈጽሞ አይደለም።
✦✦✦
አዎን እንዲህ ደጋግማችሁ ስትጠይቁ ሰውዬው ምንም እንዳልሆነና እስር ያገነነው ተራ ጃሂል መሆኑን ትገነዘባላችሁ።

ይቀጥላል...

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when axemed.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share