Ethiopian cities - የኢትዮጵያ ከተሞች

  • Home
  • Ethiopian cities - የኢትዮጵያ ከተሞች

Ethiopian cities - የኢትዮጵያ ከተሞች Everything about Ethiopian cities.
(1)

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ምስለልዩነት (ሎጎ) ላይ አስተያየት መስጠት ከተቻለ ለመሞከር!1) የመደብ ቀለሙ ከአዲስ አበባ ጋር ይቀራረባል የራሷን ልዩነት የሚያሳይ ቀለም ቢኖራት፣2) የዓጽም ሓ...
23/04/2024

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ምስለልዩነት (ሎጎ) ላይ አስተያየት መስጠት ከተቻለ ለመሞከር!

1) የመደብ ቀለሙ ከአዲስ አበባ ጋር ይቀራረባል የራሷን ልዩነት የሚያሳይ ቀለም ቢኖራት፣

2) የዓጽም ሓውልቱ ከከተማዋ ታሪክ ጋር ያለው ግንኙነት ምንያክል ተቀራራቢነት አለው? ከተማዋ ከአጽም ጋር የተያያዘ ታሪክ ያላት አይመስለኝም።

3) የከተማዋ መሪቃል (tag line) ቢኖርና ቢካተትበት (የስምጥ ሸለቆ.... ልዩነቷን አያሳይም)

4) አዳማ የኢንዱስትሪውና የምስራቅ ኢትዮጵያ መውጫ በመሆኗ ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ያለባት ደማቅ ከተማ ነች። ስለዚህ ሎጎዋ ይህንኑ ቢያሳይ

5) አዳማ የተለያዩ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትን አቅፋ የያዘች ከተማ ነች። ይህ ቢካተት ጥሩ ይሆን ነበር።

6) ነጥብ ስጠው ብትሉኝ 15/100 እሰጠዋለሁ።

7) አዳማ ለሪብራንዲንግ ባለሙያዎችን መጥራት አለባት።

የአዲስ አበባ ጋሪዎች፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ  እስከ እስክ 1950ዎቹ ድረስ የፈረስ ጋሪ መደበኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ነበር፡፡ የመጀመርያው ምስል ሁለቱ ጋሪዎች በዮሀንስ መንገድ ላይ ...
07/03/2024

የአዲስ አበባ ጋሪዎች፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ እስከ እስክ 1950ዎቹ ድረስ የፈረስ ጋሪ መደበኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ነበር፡፡ የመጀመርያው ምስል ሁለቱ ጋሪዎች በዮሀንስ መንገድ ላይ ወደ አስፋልት መንገዱ ሲገቡ ይታያሉ፡፡ በሩቁ የሚታየው የመከላከያ ሚኒስቴር ህንጻ ነው፡፡

ሁለተኛው ምስል የመጀመርያው የአፍሪካ አንድነት ጉባኤ በደረሰ ወቅት የከተማይቱን አጠቃላይ መልክ ለመለወጥ በተደረገው ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ያረጁና የታመሙ የጋሪ ፈረሶች ከስራ እንዲወጡ፣ በየወቅቱ እንዲመረመሩ፣ አዲስ ታርጋ እንዲያወጡ ወዘተ የሚጠይቅ የማዘጋጃ ህግን የሚጠቅስ በ ህዳር 1955 ዓም የወጣ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ምስል ነው፡፡

ለመሆኑ ጋሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ መካከል እንዲወጡ የተወሰነው መቼ ነው?

የመጀመሪያው የምስል ምንጭ፡፡ ቲሞቲ ፔን ጆንሰን ነው፡፡

በቴሌግራም ተከታተሉን
Follow us on telegram
https://t.me/ethiopianarchitectureandurbanism

ከዚህ ገጽ ይዘት ሲወስዱ እባክዎን ምንጭ ይጥቀሱ፡፡

ይህ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝ ሆቴል ነው ሆቴሉ ጥቅም አልባ ሲሆን በአጠገቡ እንኳ መንገድ ሲሰራ እንዲፈርስ አልተደረገም ምክንያቱም እድሜ ጠገብ እና ታሪካዊ በመሆኑስላረጀ አይፈርስም !!❤️...
28/02/2024

ይህ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝ ሆቴል ነው


ሆቴሉ ጥቅም አልባ ሲሆን በአጠገቡ እንኳ መንገድ ሲሰራ እንዲፈርስ አልተደረገም ምክንያቱም እድሜ ጠገብ እና ታሪካዊ በመሆኑ

ስላረጀ አይፈርስም !!❤️🙌🏼 By Zemelak Endrias

በ1666 ዓ.ም ለንደን ከተማ አንድ ዳቦ ቤት ውስጥ የተፈጠረው የእሳት አደጋ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ ከተማዋን ዶግ አመድ አድርጓታል። ከተማዋን ወደነበረችበት ለመመለስ ከሃምሳ ዓመታት...
22/02/2024

በ1666 ዓ.ም ለንደን ከተማ አንድ ዳቦ ቤት ውስጥ የተፈጠረው የእሳት አደጋ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ ከተማዋን ዶግ አመድ አድርጓታል። ከተማዋን ወደነበረችበት ለመመለስ ከሃምሳ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ የግንባታ ሥራ ተከናውኗል።

https://youtu.be/br5BRj-nIlg?si=tHhSQGH2NON4VtKd

London's history is marked by devastating fires that have scarred its landscape and collective memory. From the Great Fire of 1666, which altered the city's ...

፱ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አሳላፊዋ ወላይታ ሶዶ ፈካ ደመቅ እያለች ነው፡፡ ለኔ ቁም ነገሬ ፎረሙ ሳይሆን የወላይታ ሶዶ የታሪክ ቤተ - ግምጃነቷ ነው፡፡• እሷ ማለት አብዮተኛው ገርማሜ ...
19/02/2024

፱ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አሳላፊዋ ወላይታ ሶዶ ፈካ ደመቅ እያለች ነው፡፡ ለኔ ቁም ነገሬ ፎረሙ ሳይሆን የወላይታ ሶዶ የታሪክ ቤተ - ግምጃነቷ ነው፡፡

• እሷ ማለት አብዮተኛው ገርማሜ ነዋይ፣ የወላይታ አውራጃ ገዢ ሆኖ በቆየባቸው ጊዜያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ የታወጀባት መሆኗ፤

• አሁንም በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል ሕዝብ የማስፈር ዕቅድ የተካሄደባት ከተማ መሆኗ (ባይሳካም)፤

• የንጉሥ ጦና ቤተሰዎችን ጨምሮ ባላባቶችና ባለርስቶች፣ ጢሰኛው ላይ የነበራቸው ፈላጭ ቆራጭነት ሥርነቀል ለውጥ ለማምጣት የተሞከረባት ከተማ መሆኗ፤

• የልማት ዐርበኛው ደጃዝማች ወልደ ሰማያት ገብረወልድ ባስተዳደሯት ዘመን ደግሞ በከተማ ደረጃ የሕዝብና ቤተ ቆጠራ የተካሄደባት የመጀመሪያዋ ከተማ መሆኗ፤

• በደቡብ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቋቋመባት ከተማ መሆኗ፤

• ወላይታ ሶዶ አባ መላኩ ወ/ገብርኤል (፫ኛው የኢ/ተ/ቤተክርስቲያን ፓትረያርክ) ያስገኘች ከተማ መሆኗ፤

• በኢትዮጵያ ከተሞች የልማት ዐቅድና ትሩፋት ቀድማ የተነቃቃች ከተማ መሆኗ በልዩነት ያስመዘግባታል፡፡

ካሊፎርኒያዎች Sales Force Park ይሉታል።
13/02/2024

ካሊፎርኒያዎች Sales Force Park ይሉታል።

የግዙፉ አድዋ ሙዚየም ኪነ ህንጻ በዋና አርክቴክቱ እስክንድር ውበቱ አንደበትበአዲስ አበባ እምብርት ፒያሳ፤ የሚኒሊክ ሀውልት እና የአራዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚያዋስኑት ግዙፍ ...
11/02/2024

የግዙፉ አድዋ ሙዚየም ኪነ ህንጻ በዋና አርክቴክቱ እስክንድር ውበቱ አንደበት

በአዲስ አበባ እምብርት ፒያሳ፤ የሚኒሊክ ሀውልት እና የአራዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚያዋስኑት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። በቅርቡ ከታደሰው እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ማዘጋጃ ቤት ጋር ደግሞ በድልድይ ተገናኝቷል።

እስከ ዛሬ ድረስ የራሱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሳይኖረው የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትም ቋሚ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚያገኘው በዚህ ፕሮጀክት ነው። እየተጠናቀቀ ያለው ይህ ፕሮጀክት ሁለት ሺህ ሰዎችን የሚይዝ የከተማ አዳራሽም በውስጡ ይዟል።

ከሁሉም በላይ ግን የአድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት ግዙፍነት የሚነሳው ሊዘክረው ካሰበው ታሪካዊ ሁነት ነው። ይህ ግዙፍ መንግሥታዊ ፕሮጀክት፤ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በተለየ የኢትዮጵያን ነጻነት ያስጠበቀው እና በተለያዩ አገራት የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴን ያነሳሳው የአድዋ ድል መታሰቢያ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ካስገነባቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች ውስጥ የሚጠቀሰው የአድዋ ሙዚየም፤ ግንባታው የተጀመረው ሐምሌ 2011 ዓ.ም. ነበር። ህንጻው የማጠናቀቂያ ሥራዎች በላፉት ጥቂት ሳምንታት የተከናወኑ ሲሆን፣ ዛሬ እሁድ የካቲት 3/2016 ዓ.ም. እንደሚመረቅ ይጠበቃል።

የፒያሳ አዲስ ምልክት ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የዚህ ሙዚየም ዋና አርክቴክት እስክንድር ውበቱ ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአርክቴክቸር እና የከተማ ፕላን ምሩቁ እስክንድር፤ ህንጻዎችን ሲነድፍ 28 ዓመት ገደማ አሳልፏል። ከሥራዎቹ መካከል አዲስ አበባ ሰንጋ ተራ አካባቢ የሚገኘው ባለ 37 ወለሉን የሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት “ሕብር ታወር” ተጠቃሽ ነው።

ከእስከ ዛሬ ሥራዎቹ መካከል ትልቁ ደግሞ ፒያሳ ላይ የተዘረጋው የአድዋ ሙዚየም ነው።

እንደ እስክንድር አገላለጽ ይህ ፕሮጀክት፤ እንደ ሌሎች ሥራዎች የደንበኛን ፍላጎት በህንጻ ንድፍ የመተርጎም ሥራ ብቻ አይደለም። “ከ1.5 ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የሚቀመጥ ነገር ህንጻ ብቻ አይደለም” የሚለው እስክንድር፤ በትምህርት፣ በሙያ እና በንባብ ያሰባሰበውን የ“ኧርባን ዲዛይን” ጽንሰ ሀሳብ በትልቅ ደረጃ ሙከራ (experiment) ያደረገበት መሆኑን ይገልጻል።

▪ አርክቴክት እስክንድር እና የአድዋ ሙዚየም መገጣጠም

የአድዋ ሙዚየምን የሚገነባው ተቋራጭ “ቻይና ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል” ከእስክንድር ጋር ሲሠራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እስክንድር የነደፈውን የሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻን የገነባው ይህ ኩባንያ ነበር።

በ2011 ዓ.ም. የአድዋ ሙዚየምን ለመገንባት ጨረታ የወጣው ከቤተ መንግሥት ፓርኪንግ እና ከአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ፕሮጀክቶች ጋር በአንድ ላይ እንደነበር እስክንድር ያስታውሳል። እነዚህን ፕሮጀክቶች ለመገንባት የሚጫረቱ ተቋራጮች የህንጻውን ንድፍ የሚሠራ የአርክቴክት ድርጅት አብረው ማቅረብ ነበረባቸው።

በዚህ ጨረታ ላይ የሚወዳደረው ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል ለኢትዮጵያዊው የአርክቴክቸር ድርጅት “እስክንድር አርክቴክትስ” የእንጣመር ጥያቄ አቀረበ።

“እነዚህን ፕሮጀክቶች ሲጫረቱ ከፕሮጀክቶቹ ውስጥ ‘የትኛው ውስጥ መሳተፍ ትፈልጋለህ?’ ተብሎ ነው [ጥያቄው] የመጣው። ከነበሩት ውስጥ ይበልጥ ሊፈትነኝ የሚችል እና ሀሳቡም በጣም ቅንጭብ ሆኖ የቀረበ ስለሆነ፤ ብዙ ዲዛይን የማድረግ ዕድል ስለሚኖረኝ አድዋን መርጬ ከቻይና ጂያንግሱ ግሩፕ ጋር ተጣማሪ ሆነን እዚህ ውስጥ ገባን” ይላል ሥራው የመጣበትን አጋጣሚ ሲያስታውስ።

ፕሮጀክቱን ያስጀመረው በቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የሚመራው የከተማዋ አስተዳደር የሚገነባውን ህንጻ በተመለከተ ያስቀመጣቸው የመነሻ ሀሳቦች ነበሩ። ህንጻው የሚኒሊክ ሀውልት ከሚገኝበት መንገድ እኩል ሆኖ እንዲጀምር እና እጅጉን ከፍታ ያለው እንዳይሆን ማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ መነሻዎች ውስጥ አንዱ ነው።

በሙዚየሙ ህንጻ ላይ የሰንሰለታማ ተራራ እና የነጋሪት ሀሳቦችን እንዲጸባረቁ ማድረግም የከተማ አስተዳደሩ መስፈርቶች ነበሩ። እነዚህ ሀሳቦች እንዴት ይካተቱ የሚለው ደግሞ የህንጻ ነዳፊው እስክንድር ፈጠራ ነው።

“የራሴን ሀሳቦች እንድጨምር ነጻነት ነበረኝ” የሚለው አርክቴክቱ፤ “ሁልጊዜ የሚጠየቀውን ኢትዮጵያዊ ኪነ ህንጻ” ለመሥራት ሙከራ ማድረጉን ይናገራል።

▪ ከሚኒሊክ ሀውልት ጋር ፀሐይ የሚጋራው የምድር ቤት ነጋሪት

በ3.3 ሄክታር ላይ ያረፈው የአድዋ ሙዚየም ቁመቱን ከፍ ያደረገ አንድ ወጥ ህንጻ አይደለም። በተለያዩ መንገዶች የተሳሰሩ እና የአጠቃላይ ህንጻው አካል የሆኑ የተለያዩ ስብስቦችን (ሰብ ሴቶችን) የያዘ ነው።

ወደ አድዋ ሙዚየም የሚያስገቡት አራት ዋነኛ መግቢያዎች፤ የሚያደርሱት የተለያየ ገጽታ እና አገልግሎት ወዳላቸው የህንጻው ክፍሎች ነው። መግቢያዎቹ ስያሜያቸው የደቡብ ጀግኖች፣ የሰሜን ጀግኖች፣ የምሥራቅ ጀግኖች እና የምዕራብ ጀግኖች የሚል ነው።

እስክንድር፤ “ታሪክ እንደሚያሳየው ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ [ጦርነቱ ላይ] ተሳትፎ ተደርጓል ነው። ስለዚህ ሁሉም በአቅጣጫ ተወክለዋል። የበሮቹ ስያሜ ሲሰጥ ስሜቱም፣ ተመሳሌትነቱም እርሱ ነው” ይላል ከስያሜው ጀርባ ያለውን ምክንያት ሲያስረዳ።

ከአድዋ ጦርነት ጋር የተያያዙ ቅርሶች የሚቀመጡበት ሙዚየም የሚገኘው በሚኒሊክ ሀውልት በኩል ባለው የሰሜን ጀግኖች መግቢያ ነው። ይህ መግቢያ ሀውልቱ ከሚገኝበት መንገድ እኩል (flat) ሆኖ የሚጀምር ሲሆን ለአድዋ ድል በዓል ማክበሪያ የሚውል ሰፊ ፕላዛን ይዟል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ የአድዋ ድል በዓል በዚህ ስፍራ ላይ እንደሚከበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በአድዋ ድል በዓል ማክበሪያው ስፍራ መሀል ላይ በአንድ ጎኑ ከፍ ያለ ባለመስታወት ክብ ቅርጽ ተቀምጧል። ከመስታወቱ ስር የሚገኘው፤ ምድር ቤት (basement) ውስጥ የተሠራው ባለ ሁለት ወለል ሙዚየም ነው።

መስታወቱ፤ አስፓልቱን ተሻግሮ ባለው የሚኒሊክን ሀውልት ላይ የምታርፈውን ፀሐይ ወደ ታች አውርዶ ምድር ቤት በሚገኘው ሙዚየሙ ውስጥ ተፈጥሯዊ ብርሃን ይፈነጥቃል። በክብ መስታወት (circular skylight) በኩል 20 ሜትር ቁልቁል የሚወረወረው የፀሐይ ብርሃን ማረፊያው ደግሞ በሙዚየሙ መሀል፣ ከመስታወቱ ትይዩ የተቀመጠ ነጋሪት ነው።

እስክንድር የነጋሪቱን አቀማመጥ ሲገልጽ፤ “የሙዚየሙ መጀመሪያም፣ ማጠንጠኛም ነው” ይላል።

“ጦርነት ሲገባ፣ አዋጅ ሲነገር፣ ክተት ሲታወጅ የሚጎሰመው ነጋሪት ነው። ነጋሪቱ መሃል ላይ ሆኖ የሙዚየሙ የትኩረት ማዕከል (focal point) ነው፤ መነሻም ነው። ሙዚየም ውስጥ ስትገባ ጉብኝትህን ከአንድ ነገር ትጀምራለህ” ሲል ያብራራል።

“ሙዚየሙ ራሱ ሙሉ በሙሉ ከመሬት በታች ነው ያለውና ቀጥታ የሚመጣልህ ብርሃን ነው” የሚለው አርክቴክቱ፤ “ብርሃንን ቀርጾ ማስገባት እና በብርሃን መጫወትን” ሙከራ ያደረገበት የህንጻው ክፍል መሆኑን ያስረዳል።

እስንክድር፤ በህንጻው ንድፍ ላይ ደጋግሞ ያንጸባረቀው ሌላኛው ሀሳብ የአድዋ ጦርነት የተካሄደበትን ምድረ ገጽ የሚወክለው ሰንሰለታማ ተራራ ነው። የህንጻው የውስጥ እና የውጭ ጎኖች፣ የደረጃ መደገፊያዎች ላይ በተቀመጡት ወጣ ገባ እያሉ አግድም በሚሄዱ መስመሮች እንዲሁም በደረጃ ፋንታ በተቀመጡት ተዳፋቶች (ramp) ላይ መንጸባረቁን እስክንድር ይናገራል።

ተራራ “በአርክቴክቸራል ቋንቋ” ከተገለጸባቸው የህንጻው ክፍሎች ውስጥ አንዱ በማዘጋጃ ቤት በኩል የሚገኘው መግቢያ ነው። በዚህ መግቢያ ላይ ከደረጃ ባሻገር የተቀመጠው ዚግ ዛግ የሚሄድ ተዳፋት (ramp) ከርቀት ሲታይ የተራራ ይመስላል።

በዚህ መግቢያ ወደ የሚዘልቁ ጎብኚዎች ደረጃውን እንደጨረሱ የሚያገኙት እቴጌ ጣይቱ በመቀለው ውጊያ የውሃ ምንጮችን በመያዝ የጣልያን ጦር እጅ እንዲሰጥ ለተጠቀሙት ስልት መታሰቢያነት የዋለ የውሃ ፋውንቴን ነው።

ተራራማ እና ድንጋያማ አካባቢን በአድዋ ሙዚየም ላይ የማንጸባረቅ ሀሳብ፤ የህንጻው ቀለም ላይም ታይቷል። በተለይ በህንጻው የውጭ ክፍል ላይ ጎልቶ የሚታየው ቀለም “ሸክላ መሳይ” ነው።

ከህንጻው ትልቅነት አንጻር የተለያዩ ቀለማትን መጠቀም ይቻል እንደነበር የሚናገረው እስክንድር፤ ይበልጥ “ተፈጥሯዊ ነው” ብሎ ያሰበውን ይህንን ቀለም በብቸኝነት መጠቀሙን ይገልጻል። “ተራሮቹን የበለጠ የመግለጽ አቅም ያለው ቀለም ነው። ለህንጻውም የራሱ መገለጫ ሰጥቶታል” ይላል።

▪ ድንጉዛ በፒያሳ

እስክንድር፤ አንድ ህንጻ ሲሠራ ለአካባቢው እና ለነዋሪዎች የሚያስተላልፈው “ጥበብ” ሊኖረው ይገባል የሚል እምነት አለው።

በአድዋ ሙዚየም ላይ “ሞክሬዋለሁ” የሚለው ዋነኛው ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ምልክቶች እና መገለጫዎችን በህንጻ ዲዛይን ውስጥ የማካተት ሀሳብን ነው።

“ሌሎች አገራት ላይ ብዙ ፓተርኖች ላይ ኤክስፐርመንት ያደርጋሉ። እኛ አሁን ማየት ያለብን ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ ነው። እነዚህን ነገሮች መሞከር እፈልግ ነበር” ሲል የህንጻን ገጽታ ከአገርኛ አውድ ጋር (local context) ጋር የማስተሳሰር ሙከራው በዚህ ፕሮጀክት መጀመሩን ያስረዳል።

በኢትዮጵያ ባህል ውስጥ “ያልታዩ ጥበቦች” መኖራቸውን የሚያነሳው እስክንድር፤ “ዘመናዊ ነገር እንሥራ ማለት አይደለም። በብዙ መልኩ እኛን የሚመስል ነገር [ወደ ማስቀመጥ] ነው መሄድ ያለብን” ይላል።

በአድዋ ሙዚየም ላይ ያካተተው አንዱ አገርኛ ምልክት በደቡባዊ ኢትዮጵያ በጋሞ እና በወላይታ አካባቢዎች የሚለበሰው “ድንጉዛ” ነው። በደማቅ ቀይ፣ ቢጫ እና ጥቁር ቀለሞች ዐይን የሚገባው ድንጉዛ፤ በጥለቱ ላይ የሚቀመጡት ወጣ ገባ ያሉ መስመሮችም መለያዎቹ ናቸው።

ይህን የድንጉዛ ጥለት የመስመር አካሄድ ከ100 ሜትር በላይ በሚሄድ የህንጻው ክፍል ላይ ተንጸባርቋል። በህንጻው የውጪ ክፍል ላይ የሚገኙት የጦር እና ጋሻ ምልክቶች የተቀረጹት በድንጉዛ የመስመር አካሄድ በተቀመጡ ቅርጾች ላይ ነው።

ከአክሱም ሀውልት እና ከላሊበላ ኪነ ህንጻ የተወሰዱ ምልክቶችም በህንጻው የደረጃ ድጋፎች እና የኮሪደር ስፍራዎች ላይ ማንጸባረቁንም አርክቴክቱ ይናገራል።

▪ የድሮዋ ፒያሳ መልክ በአዲሱ የአራዳ ምልክት ላይ

የንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት፤ አዲስ አበባ አሉኝ የምትላቸው ኪነ ህንጻዊ ውበትን የተጎናጸፉ ህንጻዎች የተገነቡበት ነው። ብሔራዊ ቲያትር፣ ማዘጋጃ ቤት እና የንግድ ባንክ የቀድሞ ዋና መሥሪያ ቤት ከእነዚህ ህንጻዎች መካከል ናቸው።

እነዚህን ህንጻዎች የተነደፉት እንደ ፈረንሳዊው ሄንሪ ሾሜት እና ጣልያናዊው አርትሮ ሜዜዲሚ ባሉ የውጭ አርክቴክቶች ነው። እስክንድር፤ “የአካባቢውን ሁኔታ አጥንተው አካባቢያዊ አውዱን (local context) ለማምጣት የሚሞክሩ አርክቴክቶች ነበሩ” ሲል ያሞካሻቸዋል።

የእነዚህ ህንጻዎች አንድ መገለጫ ከፊታቸው አጭር ሆነው ለእግረኛ መረማመጃ ስፍራ መፍጠራቸው ነው። “የአራት ኪሎ መደዳው እና ዞሮ ወደ ፒያሳ ሲመጣ [ህንጻዎች] በደረጃዎች እተገናኙ አርኬድ (ታዛ) አላቸው። እግረኛ በምቾት፣ በጥላ እንዲሄድ ነው” የሚለው አርክቴክቱ፤ የፒያሳ ህንጻዎች ከመንገዱ ጋር “በጣም የተናበቡ” መሆናቸውን ያነሳል።

“ከፒያሳ የምወስደውን የበፊት (traditional) ፕላኒንግ ልበለው። አሁን ዘመናዊ ፕላኒንግ ደግሞ አለ። እኔ ወደዚያ [ወደበፊቱ] ነው መመለስ የምፈልገው። ያ ጥሩ ፕላኒንግ ነው” የሚለው አርክቴክቱ በአድዋ ሙዚየም ላይ እግረኛ የሚራመድባቸው ታዛዎችን መፍጠሩን ያስረዳል።

በሙዚየሙ ህንጻ ውስጥ የሚገኙት መደብሮች ደጃፋቸው እንደ ፒያሳው መብራት ኃይል ህንጻ እግረኛን የሚያስተናግዱ ናቸው።

ከአራዳ ህንጻ ጋር አዋሳኝ በሆነው አቅጣጫ የሚገኘው የአድዋ ሙዚየም ደግሞ ሌላኛው የፒያሳ ገጽታ ምሳሌ አድርጎ የተነደፈ ነው። በሙዚየሙ ሁለት ብሎኮች መካከል ረጅም ደረጃ የተዘረጋበት ይህ የደቡብ ጀግኖች መግቢያ፤ ከፒያሳው 70 ደረጃ ጋር ተመሳሳይነት አለው።

▪ የአድዋ ሙዚየም ሀውልቶች እና የሚነሱ አስተያቶች

የአድዋ ሙዚየም የህንፃ ንድፍ ሲሠራ ከጦርነቱ ጋር የተያያዙ 40 ገደማ ቅርጾች እንደተካተቱበት እስክንድር ይናገራል። ከእነዚህ የሚቆሙ እና በግድግዳ ላይ የሚለጠፉ ቅርጾች ውስጥ ግማሾቹ መሠራታቸውን የሚገልጸው አርክቴክቱ፤ “የተወሰኑት ወደፊት ይሰራሉ” ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅሷል።

በአሁኑ ጊዜ ተቀርጸው ከቆሙት ሀውልቶች መካከል የአጼ ሚኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ እንዲሁም 12 የጦርነቱ አዝማቾች ይገኙበታል። የአጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ሀውልት የውሃ ፋውንቴን በሚገኝበት ፕላዛ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠዋል። የጦር አዝማቾች ሀውልት ደግሞ በከተማ አዳራሽ የውጨኛ ክፍል ላይ በሚገኙት አምዶች ላይ ተቀምጠዋል።

እንደ እስክንድር ገለጻ የሀውልቶቹን አቀማመጥ በተመለከተ መጀመሪያ የሠራው ንድፍ ላይ ተጨማሪ ሀሳቦች ተካትተዋል። በንድፉ ላይ የ12ቱ የጦር አዛዦች ሀውልቶች በአንድ እልፍኝ ላይ እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር። የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት ደግሞ በመቀለው ጦርነት ንግሥቲት ላመጡት የጦርነት ስልት መታሰቢያ በተሠራው የውሃ ፋውንቴን መሃል ላይ እንዲሰፍር ተነድፎ ነበር።

የእነዚህ ሀውልቶች ፎቶግራፍ በሶሻል ሚዲያ ገጾች ላይ ከተሰራጨ በኋላ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ተደምጠዋል። በቅሬታ መልክ ከተነሱት አስተያየቶች ውስጥ የሀውልቶቹን የቁመት መጠን እና ገጽታ እንዲሁም የተሰሩበት ቁስን የተመለከቱ ይገኙበታል። የሠዓሊያን እና የቀራፂያን ማኅበር በሙዚየሙ ቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች ላይ “አልተሳተፍኩም” ማለቱም ሌላኛው አስተያየት ነበር።

የሀውልት እና ሌሎች የቅርፅ ሥራዎች የሚከናወኑት ከ20 እስከ 25 አባላት ባሉት የቀራፂያን ቡድን መሆኑን የሚናገረው እስክንድር፤ “በፎቶግራፍ የተደገፉ የታሪክ መጽሐፍትን ይዘው፤ ጊዜው በቂ እንኳን ባይሆን [የሀውልቶቹን] ገጽታ ከዚያ ላይ እያጠኑ ሠርተዋል። ይህንን አይቻለሁ” ይላል።

ይሁንና የቅርጽ ሥራዎቹ ቀድመው ተጀምረው ለጥናት ሰፊ ጊዜ መሰጠት እንደነበር ይገልጻል።

አርክቴክቱ እንደሚያስረዳው በአድዋ ሙዚየም ውስጥ ከሚቀመጡት የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች መካከል “ወሳኝ” የሆኑት ከነሐስ እንዲሠሩ በህንጻው ንድፍ ላይ ሰፍሯል። ይሁንና በአሁኑ ሰዓት ለሀውልቶቹ ግንባታ ጥቅም ላይ የዋለው ቁስ ሌላ መሆኑን አመልክቷል።

“እኛ ስናስቀምጥ ወሳኝ ሥራዎች በነሐስ እንዲሠሩ ተቀምጧል። የተያዘላቸው የሥራ ዝርዝር እንደዚያ ነው። በዚህኛው ግን አሁን ለማስመረቂያ ስለማይደርሱ፤ በመቀጠል የነሐስ ሀውልቶች እንደሚሠሩ ነው የማውቀው” ሲል በህንጻው ንድፍ ላይ በተቀመጠው መሠረት ሀውልቶቹ በድጋሚ ይሠራሉ የሚል እምነቱን ገልጿል።

ሀውልቶቹ አሁን የተሠሩበት ቁስም ቢሆን ግን ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ቅርፆችን ለመሥራት ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን አስረድቷል።

ከቅርፅ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱትን አስተያየቶች እንደሚጋራ የሚናገረው እስክንድር፤ “የአርት ሥራን መልሶ አሻሽሎ መሥራት፣ መለወጥ ይቻላል” ይላል። በአሁኑ ሰዓት ያልተሠሩት የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች ሲከናወኑ “ከዚህ ልምድ ተወስዶ የሚቀጥለውን ሂደት በማሳተፍ፣ ጊዜ በመስጠት እና በጥናት ይበልጥ ቢኬድበት” የሚል ምክረ ሀሳቡን አስቀምጧል።

የሀውልቶቹን ሥራ ጨምሮ ከዋና ንድፍ ላይ ለውጥ የተደረገባቸው ነገሮች ቢኖሩም “90 በመቶ በሚባል ደረጃ” ያስቀመጠው አርክቴክቸር ወደ ተግባር መተርጎሙን እስክንድር ይናገራል። የአድዋ ሙዚየም ግንባታ “በአስቸጋሪ” ሁኔታ ውስጥ የተከናወነ መሆኑን በመጥቀስም ጥሩ ሥራ መሠራቱን ያስረዳል።

ከሙዚየሙ ግንባታ ጋር የሜካኒካል፣ የኤሌክትሪካል እና የኦዲዮ ቪዥዋል ሥራዎችም “በጣም በከፍተኛ ሁኔታ” መከናወናቸውን በመግለጽ፣ በግንባታው ሂደት ጥቅም ላይ የዋሉት እቃዎችም ደረጃውን የጠበቁ እንደሆኑ አክሏል።

እስክንድር፤ “ለአድዋ በሚመጥን መልኩ ያለንን ሁሉ ሰጥተን ሠርተነዋል። ለብዙ ጊዜ ሌሎች ሥራዎችን ሳንሠራ ሁልጊዜ እዚህ ጋር ነን። ማንኛውም እንደዚህ [ዓይነት] ኪነ ህንጻ ሲሠራ ፍጹም ሊሆን አይችልም፤ ብዙ ትችቶች እንደሚመጡ አውቃለሁ። ግን ባለን አቅም ሁሉ የምንችለውን ጥረት አድርገን [ሠርተነዋል]” ይላል።

እስክንድር ወደ ሦስት አስርት ዓመታት እየተጠጋ ባለው የሥራ ልምዱ ውስጥ ትልቁ ስለሆነው ፕሮጀክት ሲያነሳ፤ “በውጭም ዓለም ሙዚየምን የሚሠራ አርክቴክት ‘ዕድለኛ ነው’ ይባላል። በክፍለ ዘመን [አንዴ] የሚመጣ ዕድል ሊሆን ይችላል። እጅግ በጣም ዕድለኛ ነኝ” ሲል ስሜቱን ለቢቢሲ አጋርቷል።

ምንጭ: ቢቢሲ አማርኛ

አዲስ አበባ ታማኝ አፍሪካዊት።Addis Ababa Faithfully African
11/02/2024

አዲስ አበባ ታማኝ አፍሪካዊት።
Addis Ababa Faithfully African

የአዲስ አበባ አፍሪካዊ ማዕከላዊነት ይለምለም።  Ababa
11/02/2024

የአዲስ አበባ አፍሪካዊ ማዕከላዊነት ይለምለም።

Ababa

ቦስተን አሜሪካ
10/02/2024

ቦስተን አሜሪካ

04/02/2024

Carlton Tavern reopens six years after planning ruling that campaigners hope will prevent developers demolishing other sites

01/02/2024

ዱባይ በዝናብ ስር

ከመጠን በላይ አትደግሱ!የውቅሮ ምክር ቤት+==============:+የውቅሮ ከተማ ምክር ቤት ከመጠን በላይ ድግስ ደጋሾችን ለመቅጣት የሚያስችል ህግ አፀደቀ‼️የውቅሮ ከተማ ም/ቤት የ4ኛ ዓመ...
30/01/2024

ከመጠን በላይ አትደግሱ!
የውቅሮ ምክር ቤት
+==============:+
የውቅሮ ከተማ ምክር ቤት ከመጠን በላይ ድግስ ደጋሾችን ለመቅጣት የሚያስችል ህግ አፀደቀ‼️
የውቅሮ ከተማ ም/ቤት የ4ኛ ዓመት 37ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ይህንኑ ህግ ማፅደቁን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቨዥን ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምክርቤቱ በመደበኛ ጉባኤው የፀጥታ ጉዳዮች፣ ስራ አጥነት፣ ድርቅና የንፁሕ መጠጥ ዉሀ እጥረት የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል። በተጨማሪም በከተማዋ ድግስ በሚል ሰበብ ከፍተኛ የሆነ ብክነት እየተስተዋለ ነው የተባለ ሲሆን እነዚህን ችግሮችን ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራ የውቅሮ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉ ማሩ ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ህዝብ ከፍተኛ በሆነ ችግር ውስጥ እያለና በድርቅ ወቅት ከመጠን ያለፈ ድግስ የሚደግሱ ሰዎችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ሲሉ የውቅሮ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፈትለወርቅ አበበ ገልፀዋል።
ነገር ግን ቅጣቱ ምንድን ነው ስለሚለው ጉዳይ የተገለፀ ነገር የለም።

የሒሮሺማ ከተማ የ75 ዓመታት ጉዞ።ከአቶሚክ ቦምብ አመድ ተነስታ አለምዓቀፍ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ከተማ ነች።
29/01/2024

የሒሮሺማ ከተማ የ75 ዓመታት ጉዞ።
ከአቶሚክ ቦምብ አመድ ተነስታ አለምዓቀፍ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ከተማ ነች።

23/01/2024
"ከተማ የሕንጻ ጫካ አይደለም። የሰዎች ማያ ቦታ ነው።" ዴስሞስ ሞሪስ everyone
21/01/2024

"ከተማ የሕንጻ ጫካ አይደለም። የሰዎች ማያ ቦታ ነው።" ዴስሞስ ሞሪስ
everyone

ክረምትና በጋ በአሜሪካ ከተሞች! New York
20/01/2024

ክረምትና በጋ በአሜሪካ ከተሞች! New York

https://vm.tiktok.com/ZM64hn2M8/
20/01/2024

https://vm.tiktok.com/ZM64hn2M8/

873 likes, 22 comments. “1923 አዲስ አበባ የምንገድ ላይ ቅኝት ክላሲካል ሀይሉ መርጊያ classical music by Hailu Mergea”

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian cities - የኢትዮጵያ ከተሞች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share