Osama Bladin

Osama Bladin Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Osama Bladin, Digital creator, .

18/06/2024
18/06/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክልላዊ የኢንቨስትመንት ፎረም በነገው እለት በወላይታ ሶዶ ከተማ ይካሄዳል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክልላዊ የኢንቨስትመንት ፎረም በነገው እለት በወላይታ ሶዶ ከተማ እንደሚካሄድ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ኦንጋዮ ኦዳ ገለፁ።

የቢሮ ሃላፊው በመግለጫቸው የኢንቨስትመንት ፎረሙ በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እያለሙ የሚገኙ ባለሀብቶችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች እንደሚገኙ፣ በመድረኩ የክልሉ የኢንቨስትመንት እምቅ አቅምና አመችነት ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚደረግም አብራርተዋል።

የኢንቨስትመንት ፎረሙ አልሚ ባለሀብቶችን እና አገልግሎት ሰጭ የመንግስት ተቋማትን በቀጥታ በማገናኘት በዘርፉ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን ይለዋወጣሉ የሚስተዋሉ ችግሮችንም በጋራ መክረው ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።

17/06/2024

ተረጂነትን ወደ ታሪክነት
===
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከልመና እና ተረጂነት በመላቀቅ በምግብ ዋስትና እራሷን ለመቻል በምታደርገዉ ጥረት ውስጥ እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶች እጅግ ተስፋ ሰጪ ናቸዉ ።

ሀገራችን በስንድ ምርታማን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ እራሷን በመቻል እዉቅናን ያገኘችበትን ስኬት አስመዝግባለች።
ጠንክረን በመስራት ምርታማነታችንን በማሳደግ ታሪካችንን እናድሳለን።


FDRE Government Communication Service-በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

15/06/2024

እንኳን ለ1445ኛዉ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለ1445ኛዉ ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል-አድኃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ሕዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን አቅመ ደካሞችን በመደገፍና በማሰብ እንዲያከብር ጠይቀዋል።

በዓሉ አላህ የነብዩ ኢብራሂምን ፍቅርና እምነት ፍጹምነትን ለማስተማር ልጃቸውን ለመስዋዕትነት እንዲያቀርቡ ያዘዘበት፤ እርሳቸውም ለፈጣሪ የነበራቸው እምነትና ፍቅር ጥግ በሚያሳይ ፍጹምነት የሚወዱት ልጃቸውን እስማኤልን ወደ መሰዊያው ያቀረቡበት መታሰቢያ በዓል ነው።

ፈጣሪም በልጃቸው ምትክ ለመስዋዕትነት የበግ ሙክት የተካላቸው መሆኑ የሚታወስበት በዓል መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ዕለቱ የዕርድ ወይም የኡዱህያ ቀን ተብሎ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር መሆኑ ይታወቃል።

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና ያለውን በማካፈል መሆን እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

እንደዚሁም ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር አንድነቱንና ወንድማማችነቱን በሚያጠናክር መልክ በዓሉን ማሳለፍ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በመካሄድ ላይ በሚገኘው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ህዝበ ሙስሊሙ ንቁ ተሳትፎና ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

በዓሉ የሠላም፥ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

15/06/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ የኢድ አል አድሃ (ዐረፋ) በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት

ወላይታ ሶዶ፣ ሰኔ 08/2016 (ወዞመኮጉመምሪያ)

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1445ኛዉ የኢድ አል አድሃ (ዐረፋ) በዓል በሰላምና ጤና አደረሳችሁ !

የዒድ አል-አድሃ ዐረፋ በዓል በሙስሊሙ ህብረተሰብ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠዉ በተለይም ነቢዩ ኢብራሒም ለፈጣሪያቸው ያላቸውን መታዘዝ ያሳዩበት የመታዘዝ እና የመስዋዕትነት በዓል ነው።

በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ሥራ ከገባ 10 ወራቶችን ብቻ ያስቆጠረዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብዝሃ ኃይማኖት፣ ባህል፣ ታሪክና የአብሮነት እሴቶች ጎልተዉ የሚታዩበት የሁሉም ሕዝቦች የጋራ ቤት ነዉ፡፡

ሀገራችን የጀመረችዉ የዕድገትና ብልፅግና ጉዞ በሁሉም ዘርፎች አመርቂ ዉጤቶችን እያስመዘገበ መጓዙን ቀጥሏል። ክብረ-ነክ ከሆነዉ የድህነትና የተረጂነት ታሪክ ለመላቀቅ የጀመርናቸው ዘርፈ-ብዙ የልማት ተግባራት ሀገራችንን ከተስፋ ወደ የሚጨበጥ ብርሃን በማሸጋገር ላይ ይገኛሉ።

የዐረፋን በዓል ስናከብር ከመቼዉም ጊዜ በላይ ክልላዊ አንድነታችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል። አንድነቱን ያጸና፣ ብዝሃነቱን ያስከበረ ሕዝብ የትኛውንም ፈተና ድል በመንሳት አንግቦ የተነሳዉን የሰላም፣ የልማትና የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ከግብ ማድረሱ አይቀርም።

ሀገራችንንና ክልላችንን የሰላም፣ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በምናደርገው ጉዞ መላው ሕዝባችን እንደተለመደው ሁሉ ከጎናችን በመሰለፍ የሰላሙ ዘብ፣ የልማቱ ፋና ወጊ እንዲሆን በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመረዳዳትና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እየገለፅኩ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን የመጠየቅና ማዕድ የማጋራት የተለመደ ተግባሩን በማጠናከር እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡

ዒድ ሙባረክ !!

አቶ አለማየሁ ባዉዲ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

15/06/2024

የወላይታ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ለ1ሺህ 445 ኛውን የኢድ አል አድሃ/አረፋ በዓል በማስመልከት ለወላይታና ለመላው የሀገራችን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

የወላይታና መላው የሀገራችን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው የኢድ አል አድሃ /አረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ/ አደረሰን።

የኢድ አል አድሃ /አረፋ በዓል ነቢዩ ኢብራሂም በአላህ ትእዛዝ ልጃቸውን ለመሥዋዕትነት ያዘጋጁበትን፤ ጽናታቸው ተፈትኖ ያሸነፉበት የፅናትና የአሸናፊነት ተምሳሌት ነው።

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና ያለውን በማካፈል መሆን ይኖርበታል። እንደዚሁም ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር አንድነቱንና ወንድማማችነቱን በሚያጠናክር መልክ በዓሉን ማሳለፍ ይገባል፡፡

አሁን ያለንበት ወቅት ከምን ጊዜውም በላይ ትብብርና መደጋገፍ የሚጠይቅ በመሆኑ በዓሉን በምናከብርበት ወቅትም ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በመሆን ማክበር ይኖርብናል።

እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ ሀይማኖት ሀገር በመሆኗ ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር ነባሩን የአብሮነት ዕሴቶቻችንን በሚያጎላና አንድነቱንና ወንድማማችነቱን በሚያጠናክር መልክ በዓሉን እንደምናሳልፍ ይጠበቃል።

በመካሄድ ላይ በሚገኘው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ህዝበ ሙስሊሙን ጨምሮ የሌሎች ዕምነት ተከታዮችም ንቁ ተሳትፎና ድጋፍ የሚሻ ይሆናል።

በዞናችን በመኸር እርሻ ዝግጅት ፣ በአረንጓዴ አሻራ ፣ በመንገድና በውሃ መሠረተ ልማቶች ዝርጋታ ፣ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችና በሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ዘርፎች ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን ጥረቶቹ ፍሬያማ እንዲሆኑ የሰላማችንን ዘላቂነት በማረጋገጥ ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ከፀጥታ መዋቅሮቻችን ጋር በላቀ ቅንጅታዊ ተሳትፎ አጠናክረን በመቀጠል ለተሻለ ውጤት እንድንተጋ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

በዓሉ የጤና ፣ የሰላምና የደስታ በዓል እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን ለመግለፅ እፈልጋለሁ።

በድጋሚ ለኢድ አል አድሃ /አረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ/ አደረሰን።
አመሰግናለሁ።

አቶ ሳሙኤል ፎላ
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ሰኔ 08/1016ዓ.ም

15/06/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛዉ የኢድ አል-አድኃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!፦ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ዘውዱ ሳሙኤል ለ1445ኛዉ የዒድ አል-አድኃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የኢድ አል አድሀ(የአረፋ) በዓል ህዝበ ሙስሊሙ በድምቀት ከሚያከብራቸው በዓላት መካከል አንዱ ነው። በዓሉ በምዕመናን ዘንድ ትልቅ ትርጉም ያለው ሲሆን የአንድነት እና የአብሮነት እሴቶቻችን በጉልህ የሚንጸባረቁበት በዓል ነው።

አገራችን የበርካታ ኃይማኖቶችና ባሕሎች ባለቤት ናት፡፡ እነዚህ ኃይማኖታዊና ባሕላዊ እሴቶቻችን የእኛነታችን መገለጫ፤ የአብሮነታችን ማሳያዎች ናቸው።

የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓለም መቻቻል፣ መከባበር፣ መረዳዳት፣ ተካፍሎ የመብላትና በማህበራዊ ህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ልዩነቶችን በጋራ የመፍታት እሴት ጎልቶ የሚታይበት ታላቅ በዓል ነው።

እንደ ሀገር ብሎም እንደዞናችን በሁሉም ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን አጠናክረን ለማስቀጠል እና ከተረጂነት እና ከድህነት ለመውጣት በእጃችን ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ በመጠቀም እና እርስ በእርስ መተሳሰብና መደጋገፍ ይኖርብናል።

ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን እየተከልን የጀመርነውን ሁሉአቀፍ የብልፅግና ጉዞ እንድናስቀጥል ብሎም የሕዝባችንን ችግር ደረጃ በደረጃ እየለየን እንድንፈታ ከምንጊዜውም በላይ ወቅቱ የሚጠይቅ ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም በተሰማራበት መስክ ተግተን እንሥራ የሚለው ዋነኛ መልዕክቴ ነው፡፡

የብሔር፣ የሀይማኖት፣ የከፋፋይ ትርክትንና የፖለቲካ ጽንፈኝነትን በመቃወም አንዳችን ለአንዳችን ዋልታ እና ማገር፤ ድርና ማግ መሆን ያስፈልጋል። አሁን ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገን ፍቅር እና አንድነት ብቻ ነው፡፡

ፓርቲያችን ብልፅግና ሰላምን ለማረጋገጥ፣ ከድህነት ለመውጣት፣ ኢኮኖሚያችንን ለማሳደግ፣ ሕዝባችንን ለማበልጸግ ትግል ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ተጋጭተን ሳይሆን ተነጋግረን፤ ተሻምተን ሳይሆን ተካፍለን፤ ተገፋፍተን ሳይሆን ተጋግዘን፤ ለሀገራችን ብሎም ለህዝባችን ከሠራን ያለምንም ጥርጥር የምንመኘውን ብልፅግናን እውን እናደርጋለን።

ሕዝበ ሙስሊሙም በዓሉን ሲያከብር ኃይማኖታዊ ህግጋቱ በሚያዘው መሰረት ለሰላም ዘብ በመቆም፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፣ የታረዙትን በማልበስና በመደጋገፍ የበኩላችሁን ሚና በመጫወት አርአያነታችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ አደራ እላለሁ።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445 ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም፣የጤና የመተሳሰብ እና የአንድነት በዓል እንዲሆን በራሴና በዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም እመኛለሁ።

መልካም በዓል!

ዘውዱ ሳሙኤል
የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Osama Bladin posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share