የባም/ወ/ንግ/ኢን/መ/ት/ጽ/ቤት Ba/W/T/E/R/T/offic

  • Home
  • የባም/ወ/ንግ/ኢን/መ/ት/ጽ/ቤት Ba/W/T/E/R/T/offic

የባም/ወ/ንግ/ኢን/መ/ት/ጽ/ቤት Ba/W/T/E/R/T/offic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የባም/ወ/ንግ/ኢን/መ/ት/ጽ/ቤት Ba/W/T/E/R/T/offic, Digital creator, .

የባም/ወ/ንግ/ኢ/መ/ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም መሀመድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 445ኛ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ*...
16/06/2024

የባም/ወ/ንግ/ኢ/መ/ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም መሀመድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 445ኛ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ
***********
አቶ አደም መሀመድ በዓሉን አስመልክቶ እንዳሉት መላው የሙስሊም ማህበረሰብ የተራበን በማብላት፣ የተቸገረን በመርዳት የአረፋ በዓል ልዩ መገለጫው መሆኑን በመግለጽ ለመላው የሙስሊም ማህበርሰብ በሙሉ በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የአንድነት የመተሳሰብ በአል እንዲሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ሰኔ 8/2016ዓ.ም

በዛሬው ቀን ማለትም በቀን 28/9/16 ዓ .ም የባም/ወ/ንግ/ኢ/መ/ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም መሀመድ ከጽ/ቤቱ ማናጅመንት ጋር ስለ ወቅታዊ የንግድ ኢንዱስት መንገድ እና ትራንስፖርት  ስራ...
05/06/2024

በዛሬው ቀን ማለትም በቀን 28/9/16 ዓ .ም የባም/ወ/ንግ/ኢ/መ/ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም መሀመድ ከጽ/ቤቱ ማናጅመንት ጋር ስለ ወቅታዊ የንግድ ኢንዱስት መንገድ እና ትራንስፖርት ስራ በጥልቀት ከተወያዬ ብኋላ ስራዎችን በዕቅድ እና በተሰጠው ልኬት መሰርት ተሰርቶ ሪፖርት መገምገም እንዳለበት በአትኩሮት የተቀመጡ ሲሆን ከማናጅመንት አባላቱ ጋር ስለ ቀጣይ ስራዎች በስፋት ተወያይተው ዋና ዋና ነጥቦች ላይ መግባባት ለይ በመድርስ ስብሰባው በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል

በዛሬው ቀን ማለትም በቀን 23/09/16 ዓ .ም የባም/ወ/ንግ/ኢ/መ/ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም መሀመድ ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር ስለ ወቅታዊ የንግድ ኢንዱስት መንገድ እና ትራንስፖርት  ስ...
31/05/2024

በዛሬው ቀን ማለትም በቀን 23/09/16 ዓ .ም የባም/ወ/ንግ/ኢ/መ/ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም መሀመድ ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር ስለ ወቅታዊ የንግድ ኢንዱስት መንገድ እና ትራንስፖርት ስራ ከባለሞያዎች ጋር በጥልቀት ከተወያየ ብኋላ ለቀጣይ እስከታች ማለትም እስከ ቀበሌዎች በመድርስ መሰራት ያለባቸው የስራ አቅጣጫዎችን በትኩርት አስቀምጠዋል ።

የባምባሲ ወርዳ ንግድ ኢንዱስትሪ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በዛሬው ቀን ማለትም በቀን07/09/2016ዓ.ም የወርዳችን የነዳጅ ችርቻሮ ባለቤቶች ጋር ስለ ወቅታዊ የነዳጅ ዋጋ ስለ ነዳጅ...
15/05/2024

የባምባሲ ወርዳ ንግድ ኢንዱስትሪ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በዛሬው ቀን ማለትም በቀን07/09/2016ዓ.ም የወርዳችን የነዳጅ ችርቻሮ ባለቤቶች ጋር ስለ ወቅታዊ የነዳጅ ዋጋ ስለ ነዳጅ ደንብ እና አዋጅ በተጨማሪም በዘርፉ ስላለው የአሰራር ማነቆ እና መፊትሄዎቻቸው የጽ/ቤታችን ሀላፊ እና የወርዳ ወንጀል መከላከል ባሉበት ሰፊ ውይይት ከተደርገ ብኋላ ጽ/ቤቱ ለቀጣይ የትኩርት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥበጥሩ ሁኔታ ስብሰባው ተጠናቋል ።

የባምባሲ ወርዳ ንግድ ኢንዱስትሪ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በዛሬው ቀን ማለትም በቀን06/09/2016ዓ.ም በጽ/ቤቱ በተሰጠው የስራ ስምሪት መሰርት በነባር ቀሽማንዶ እና በቀሽማንዶ ቁ...
14/05/2024

የባምባሲ ወርዳ ንግድ ኢንዱስትሪ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በዛሬው ቀን ማለትም በቀን06/09/2016ዓ.ም በጽ/ቤቱ በተሰጠው የስራ ስምሪት መሰርት በነባር ቀሽማንዶ እና በቀሽማንዶ ቁ.2 ቀበሌዎች በመዘዋወር በእህል መጋዘኖች በሱቆች እና በነዳጅ ችርቻሮ ቤቶች የክትትል እና የቁጥጥር ስራ የሰራ ሲሆን ቁጥጥር እና የክትትል ስራው የእህል መጋዘኖችን እስከማሸግ የደርሰ ነበር የተሰራው ሰራ ጥሩ የነበር ቢሆንም ተጠናክሮ በተቀሩት ቀበሌዎች እንደሚቀጥል ጽ/ቤቱ ገልጽዋል

13/05/2024
የባምባሲ ወርዳ ንግድ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት  በዛሬዉ ቀን ማለትም 02/08/16 ዓ.ም አዲስ ከመጡት የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ አደም መሀመድ እና ወደ ገንዘብና ኢኮኖሚ ከተዘዋወሩት አቶ...
10/05/2024

የባምባሲ ወርዳ ንግድ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በዛሬዉ ቀን ማለትም 02/08/16 ዓ.ም አዲስ ከመጡት የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ አደም መሀመድ እና ወደ ገንዘብና ኢኮኖሚ ከተዘዋወሩት አቶ ሴርልሀቲም አብዱርህማን ጋረ እና ከጽ/ቤቱ ባለሞያዎቸ ጋር ስለቀጣይ ስራዎች ከተወያዬ ብኋላ ርክክብ አርገዋል

በባምባሲ ወረዳ የስልጣን ሽግሽግ ተደርጓልበዚህም መሠረት የባምባሲ ወረዳ ንግድ ትራንስፖርትና ገጠር መንገድ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሰርለሃቲም አብዱሮህማን የባምባሲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖ...
09/05/2024

በባምባሲ ወረዳ የስልጣን ሽግሽግ ተደርጓል

በዚህም መሠረት የባምባሲ ወረዳ ንግድ ትራንስፖርትና ገጠር መንገድ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሰርለሃቲም አብዱሮህማን
የባምባሲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ፣

የባምባሲ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት ንግድ ትራንስፖርትና ገጠር መንገድ ጽ/ቤት
ኃላፊ አቶ አደም መሀመድ

እና በአሶሳ ዞን የብሔረሰብ ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት የነበሩት አቶ ሀይደር አብዱልባጂ የባምባሲ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ሊግ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

መልካም የስራ ዘመን

"ሰላም የሁሉም መሰረት ስለሆነ ሰላማችንን መጠበቅ አለብን" ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)**********************ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወለጋ የ...
08/05/2024

"ሰላም የሁሉም መሰረት ስለሆነ ሰላማችንን መጠበቅ አለብን" ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወለጋ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ባደረጉት ንግግር ሰላም የሁሉም መሰረት ስለሆነ ሰላማችንን መጠበቅ አለብን ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ በከፈለው መስዋዕትነት በራሱ ቋንቋ የመጠቀም፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር እና ባህሉን የማሳደግ ነጻነት ማግኘቱን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዛሬ ይህን ድል አጽንተን ለቀጣይ ድል መነሳት እንጂ የተመለሱትን ጥያቄዎች እንደ አዲስ ማንሳት አይገባም ብለዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በነፍጥ የሚመለስ ጥያቄ ባለመኖሩ ጥያቄዎቻችን ሊመለሱ የሚችሉት በውይይት እና በመደማመጥ ብቻ መሆን አለበት ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ የመደማመጥ እና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ወርቃማ ባህል እያለው አሁን እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት ምክያንት ያልተገባ መስዋዕትነት እየከፈለና ልማቱም እየተጓተተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተለይ ወለጋ ላይ ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የሰላም አጦት ምክንያት ለሁሉም የሚተርፍ ሀብት ያለው አካባቢ ሳይለማ መቆየቱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በቀጣይ ይህን የሚያካክስ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

እየተጓዝን ያለነው ፈጣሪያችንን እና ህዝባችንን አስቀድመን ስለሆን ከብልፅግና ጉዟችን የሚገታን የለም ሲሉም ነው የገለፁት፡፡

ብልፅግናን ለማፋጠን እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ማዳበር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ኢትዮጵያን የሚመጥናት ብልፅግና ላይ ለማድረስ የሀሳብ ልዩነቶችን በንግግር በመፍታት በወንደማማችነት መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መነሳት አለብን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢቢሲ

በባምባሲ ወረዳና ከተማ አስተዳደር  ህዝብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የባለድርሻ አካለት ምክክር አደረጉ*******************(ባምባሲ፣ሚያዚያ 29/2016) የቤኒሻንጉል ጉ...
07/05/2024

በባምባሲ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ህዝብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የባለድርሻ አካለት ምክክር አደረጉ
*******************
(ባምባሲ፣ሚያዚያ 29/2016) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በንግዱ ዘርፍ ላይ ህዝብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠትና የኑሮ ውድነት ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋቋመው ግብር ኃይል ከወረዳውና ከተማ አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካለት ጋር ምክክር አደርገዋል።

በምክክሩ ወቅትም ከተወያዮች ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ነገሮች የተነሱ ሲሆን በየቦታው የሚታዩ ኬላዎች ህዝብ ማንገላታትና ከመጠን ያለፈ ክፍያ መጠየቅ ፣ ህገ ወጥ ደላሎች ፣ የገቢ አሰባሰብ አሰራር ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና የትራፊክ ክትትል ፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ፣ የስግብግብ ነጋዴዎች ችግር ፣ የማህበራት ገበያን ያለማረጋጋት ፣ የአዲስ አበባ- አሶሳ መንገድ ዝግ መሆንና ያለ አግባብ ክፍያ መጠየቅ የመሳሰሉት ጉዳዮች በህዝብና መንግስት መካከል ያሉ መልካም ግንኙነቶችን እያሻከሩ ያሉ ተግባራቶች በመሆናቸው ሊቀረፉ ይገባል ተብሏል።

ምክክሩን የመሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡስማን አህመድና የንግድና ቢሮ ኃላፊ አቶ አስር ኢብራሂም ሲሆኑ በንግድ ዘርፍ የሚስተዋሉ የህግ ማስከበር ሥርዓቱ ማጠናከር አለበት ብለዋል።

በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡስማን አህመድ እንዳሉት የተቀመጡ ህገ ወጥ ኬላዎች እንደ ሀገር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ጊዜ ሳይሰጥበት መፍትሄ መገኝት እንደለበትም አሳስበዋል።

አቶ ኡስማን አክለውም በእያንዳንዱ ዘርፍ የሚደረጉ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች መላላት በህዝብ ኑሮ ላይ ጨና የሚፈጥር በመሆኑ በየዘርፉ ያሉ አሰራሮች ህግን ተከትሎ ሥርዓት ማስያዝ እንደለበትም ተናግረዋል ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አስር ኢብራሂም እንዳሉት አመራች ከሽማችጋር የማገናኘቱ ሁኔታ ትኩረት ባለመሰጠቱ ለህገ ወጥ ደላሎች በር የከፈተና የኑሮ ውድነቱን እያባባሰ ያለ ተግባራት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለው ከዚህ በፊት የነበሩ የገበያ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የተሰሩ ሥራዎች በግብርና ምርቶች ላይ ቅናሽ በማሳየቱ ተጠናክሮ ማስቀጠል እንደለበት ገልጸዋል።

አቶ አስር አክለውም በንግድ ዘርፉ ህዝብ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለማስጣትና የኑሮ ውድነት ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም ገበያን ለመረጋጋት አምራቾች ከሸማቹ በቀጥታ የሚገናኙበት የገበያ ትስስር መፍጠር እና ህገ ወጥ ደላሎች ከንግድ ሥርዓቱ ማስወጣት መፍትሔ ነው ብለው በተለይም የእሁድ ገበያ ማጠናከር እንደለበት ገልጸው በግብርና ምርቶችን በስፋት በመስራት አምርቶ ወደ ገበያ እንዲያቀርቡ ትኩረት ተሰጥተው መሰራት እንዳለበትም ገልጸዋል ።

በንግድ ዘርፍ የገቢ አሰባሰብ ስራን ሥርዓት ማስያዝ ፣ የሌማት ቱርፋት ስራዎች ላይ ትኩረት ተደረጎ መሠራት እንደለበት የተሰመረበት ሲሆን በትራስፖርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከል የፀጥታ ዘርፉን ማጠናከር እንደለበት እና በየቦታ የተቀመጡ ኬላዎች መነሳትና የክትትል ቀጥጥር ሥራው ማጠናከር እንደለበት ተገልጿል ።

በተለይም በአብራሞ ወረዳ ላይ ያለው ኬላ የመንግስትን ስትራቴጂ ከማስፈጸም ይልቅ በግለሰቦች ቁጥጥር ለመዋሉ በርካታ ማሳያዎች ስላሉ መነሳት ይኖርበታል ተብሏል።

በውይይቱ ላይ የባምባሲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ራሃማ አብዱረሂም፣የባምባሲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የተለያዩ  ቦታዎች ላይ የአመራር  ሽግሽግ አደረገ*************(አሶሳ፣ ሚያዝያ29/2016ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የተለያዩ  ቦታዎ...
07/05/2024

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የተለያዩ ቦታዎች ላይ የአመራር ሽግሽግ አደረገ
*************

(አሶሳ፣ ሚያዝያ29/2016ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የተለያዩ ቦታዎች ላይ የአመራር ሽግሽግ ተደርጓል።

በዚህም መሠረት፦

1. አቶ አትንኩት ሽቱ - የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ
2. አቶ ደበሊ በልጋፎ - የመተከል ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
3. አቶ መላኩ አልገመር - የፓዌ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምክትል ዲን
4. አቶ ለሜሳ ዋወያ _ የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ም ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

#ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የባም/ወ/ንግ/ኢን/መ/ት/ጽ/ቤት Ba/W/T/E/R/T/offic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share