Serkalem Abate

  • Home
  • Serkalem Abate

Serkalem Abate Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Serkalem Abate, Digital creator, .

12/06/2024
11/06/2024

አባት እናቶቻችን በደምና በአጥንታቸው ያስረከቡንን ሉዓላዊት አገር ላብአችንን ጠብ አድርገን በመስራት ከተሟላ ክብሯ ጋር ለመጪው ትውልድ እናሸጋግራለን !

ኢትዮጵያ የዘመኑን የአርበኝነት አዋጅ ካወጀች ሰነባብታለች ፤ ይህ አዋጅ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ የተባበረ ክንድ የሚጠይቅ በድህነት ላይ የሚደረግ ብርቱ ትግል ነው፡፡

የእኛ ትውልድ የአርበኝነት ድል ኢትዮጵያን ለረጅም ዘመን ዋጋ እያስከፈለ የመጣውን ድህነትን ከስሩ ለመንቀል ቀን እና ሌት በመስራት የምንጎናፀፈው ሁለንተናዊ ብልፅግና መሆኑን ፓርቲያችን መዳረሻችንን ባሳወቀበት አቋሙ ግልፅ አድርጓል።

ዋና ትግላችን ከድህነት ጋር በመሆኑ አንዳንድ አካላት ግስጋሴአችንን ለማደናቀፍ በየጊዜው ለሚያደርጉት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት በሚል እግራችንን ከልማታችን የምንነቅል አለመሆናችን የሚረዳ ይረዳዋል። እነዚህን ጦርነት ጎሳሚ ግለሰቦችና ቡድኖች እንደወትሮው ሁሉ በአንድ እጃችን እየተከላከልን በሌለኛው እጃችን ደግሞ በድህነት ላይ የከፈትነውን ዋናውን ጦርነት እናጠናክራለን።

ፓርቲያችንም ደጋግሞ እንደገፀው የምንበለፅገው ላብአችንን ጠብ አድርገን በመስራት እንጅ በሌላ አይደለም።

ተመፅዋችነት ጊዜያዊ ችግሮችን ለማለፍ ሊያግዝ ይችል ይሆናል እንጅ ከችግር አያወጣንም።

ችግሮችን በኢትዮጵያዊያን ነበር አሴቶች እርስ በእርስ ተረዳድተን እና ተደጋግፈን ማለፍ እየቻልን የሌላ አካልን እርዳታ ጠባቂ ከሆነን ከእያንዳንዱ እርዳታ ጀርባ የሚኖሩ ቅድመ ሁኔታዎች የጭቃ ውስጥ እሾህ የሚሆኑበት አጋጣሚ መኖሩንም ልብ ማለት ያሻል።

ሰርቶ የመለወጥ እሳቤ በተረጅነት አስተሳሰብ ከታጠረ የሌላን ሰው እጅ ጠባቂ በማድረግ ከድህነት ጋር ያላምዳል ፤ ድህነት ደግሞ ያዋርዳል።

እራሱንና አገሩን መለወጥ የሚችል አምራች የሰው ሀይል ፣ የሰጡትን የሚያበቅል ለም መሬት፣ የተመጣጠነ ምቹ የአየር ፀባይ ፣ ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ ሌሎች አገሮችንም የሚያረሰርሱ ወንዞች ፣ የከበሩ ማዕድናት ፣ የገዘፉ የጀግንነት ታሪኮች ይዘን በምንም መመዘኛ ከእኛ የተሻለ የመበልፀግ አቅም በሌላቸው አገሮች ተቀድመን የዓለም ጭራ መሆናችን በእኛ ትውልድ ከቁጭት የተሻገር ተግባራዊ ምላሽ ሊሰጠው ግድ ይላል።

እጆቻችን እርዳታ ለመስጠት ሳይሆን ለመቀበል የምንዘረጋው ያሉንን ፀጋዎች ተረድተን ባለመስራታችን መሆኑን በመረዳት ፓርቲያችን አገራችን ያሏትን አቅሞች በመጠቀም መለወጥ ትችላለች የሚል ቁርጠኛ አቋም አንግቦ 7/ 24 የመስራት ባህልን እየገነባ የኋላቀርነት ጨለማን እየገፈፈ የዕድገት ብርሃን ለኩሷል።

እንደ አገር በስንዴ ምርት በከተማችን ደግሞ በሌማት ትሩፋት እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶች በራሳችን አቅም ከመበልፀግ የሚያስቀረን የድህነት ወጥመድ አለመኖሩን የሚያሳዩን ብቻም ሳይሆኑ በቀጣይ ለምናስመዘግባቸው ስኬቶችም ማስፈንጠሪያ ድሎቻችን ናቸው።

የሌማት ትሩፋትን ለአብነት ጠቀስን እንጅ ከተማችን አዲስ አበባ በሁሉም መስክ የኢትዮጵያውያን ቤት ፣ የአፍሪካውያን መዲና ፣ የዓለም የስበት ማዕከል መሆኗን በሚመጥናት የዕደገት ግስጋሴ ውስጥ መግባቷ ለማንም የሚታይ ፣ የሚዳሰስ እንዲሁም የሚጨበጥ ነው።

በርቀት አይተናቸው የምንቀናባቸውን ታላላቅ የዓለም ከተሞች ገፅታ እየተላበሰች የምትገኘው ከተማችን አዲስ አበባ ቀንም ማታም እየተሰራች እየፈካች ትገኛለች።

እንደ አገር ሲንከባለሉ የመጡ ውስብስብ ችግሮች ቢኖሩብንም ተቀራርበን እየተመካከርን መፍትሄ እያፈለቅን በጋራ ከመስራት ውጭ የሚበጀን የለም።

ፓርቲያችን አገራችን ችግሮችን የመፍታት የቆየ እሴት እንዳላት በማመን የውስጥ ችግራችን እራሳችን እንደምንፈታው እርግጠኛ የሆነውን ያህል ድህነትን ድል በማድረግ በራሳችን አቅም ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ማረጋገጥ እንደምንችልም ከምንም በላያ በህዝባችን ይተማመናል።

አባቶቻችን ያወረሱንን የጀግንነት ክብር ከፍ አድርገን የምናስቀጥለው በእርዳታ ተረጅ የሆነ እንጂ የተለወጠ አገር እንደሌለ አምነን በመስራትና በመስራት የድህነት ታሪካችንን ስንፍቅ ብቻ ነው።

የተረጅነትን አስተሳሰብ በአምራችነት ፀጋ እየለወጥን ቀደምት አባት እናቶቻችን በደምና በአጥንታቸው ያስረከቡንን ሉዓላዊት አገር ላብአችንን ጠብ አድርገን በመስራት ከተሟላ ክብሯ ጋር ለመጪው ትውልድ እናሸጋግራለን !

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ ቤት

04/06/2024

ሀገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና!

ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት በአብሮነትና በህብረት የፈጸሟቸው ታላላቅ የጋራ ገድሎች አሏቸው። የጋራ ታሪክና ዕሴት የሆኑ የሺ ዘመናት ኩነቶች ህያው ምስክር በመሆን ትስስርና መስተጋብሮችን አመላካች ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን የጋራ ባህልና ዕሴት ያላቸው ህብረብሔራዊነት ያፀናቸው ህዝቦች ናቸው። ሆኖም በጋራ ያሳካናቸው ታሪኮች እንደተጠበቁ ሆነው በጋራ የመመካከርና የዕርቅ ባህላችን ችግር የሚታይበት አካታችነትና የወል ዕውነትነት የጎደላቸው ናቸው። በተለይም የምክክርና የድርድር ባህላችን ብዙ ርቀት ያልተሄደበት ነው።

ምክክርና ድርድር ለኢትዮጵያዊያን ብዙ ርቀት ያልተሄደበት ግን ድርብ ድልን ማስመዝገብ የሚችል የሰላም መንገድ ነው። አሁን ላይ የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ዘመንን የዋጀ ዘመን ተሻጋሪ መፍትሄን በመስጠት ሰላምንና ብልጽግናን ለማስረጽ አስቻይ ሁኔታን ይፈጥራል።

በጋራ ያሳካናቸው የጋራ ድሎች አሉን፤ ድሎች አስጠብቆ የሚያጸና ሁሉን አቀፍና አካታች ሁለንተናዊ ብልጽግናን የምናረጋግጥበት የድርድርና የምክክር መድረኮቻችንን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል። ድሎቻችንን ለማፅናት መምከር ወሳኝ ነው።

በምክክርና በድርድር በመደመር ዕሳቤ ዘመንን የዋጀ ለትውልድ ተሻጋሪ ሀገርን መገንባት የዚህ ትውልድ አደራና ሀላፊነት ነው። ምክክር ለጋራ ሰላምና ብልጽግና አማራጭ የሌለው አማራጭ ነው። ተደምረን በመመካከር ህብረብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀና ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ሀገርን ለመጭው ትውልድ እናበስራለን!

04/06/2024

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ በመጠቀም የምግብ ዋስትናችንን እናረጋግጥ !

ኢትዮጵያ ለብዙ አመታት የተረጂነት አስተሳሰብ ፈተና ሆኖባት ቆይታለች በተለይም ያሉንን የመሬት፣ የሰው ሀይል፣ የማእድንና የውሃ ሀብቶቻችን በአግባቡ ባለመጠቀማችን ምክንያት ለረጅም አመታት ከተረጂነት ለመላቀቅ አልተቻለም፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ያሉንን እምቅ ሀብቶቻችን በአግባቡ በመጠቀም ተረጂነት አንገት የሚያስደፋ፣ የሚያዋርድ ብሎም የሀገር ሉአላዊነትን የሚያስደፍር ተግባር በመሆኑ በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር ለመዋጋት እና የስራ ባህልን ለመቀየር ፓርቲያችን ትኩረት ሰቶ እየሰራ ይገኛል።

በቀጣይ እነዚህ ሀብቶቻችን በአግባቡ ከተጠቀምን በአጭር ጊዜ መለወጥ እንደሚቻልና ለዚህም ወጣቱ ያለው ሚና ከፍተኛ ስለሆነ የስራ ባህሉን በማሻሻል ፓርቲያችን በተለያዩ ጊዜያት በሚያመቻቸዉ የስራ እድል ተጠቃሚ በመሆን በተገኙ አጋጣሚዎች እድልን ወደ ድል መቀየር ይገባል፡፡

የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናችን ለማረጋገጥ በግብርና ዘርፉ በትኩረት መስራት ግድ ይለናል፤ የአደጋ ጊዜ ስጋት ለመቋቋም እና ምላሽ ለመስጠት የሚሆኑ ስራዎቻችን ይበልጥ ለማጠናከር የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ የአብሮነት እሴታችን ይበልጥ ማዳበርና ፀጋዎቻችንን በመለየት ወደ ተግባር መግባት ይጠበቅብናል ፡፡

በሌማት ትሩፋት ተግባራቶቻችን ያሳየነው ውጤት የይቻላል አስተሳሰብ በተጨባጭ ያሳየ እንደመሆኑ በቀጣይም በታቀዱ የልማት ስራዎቻችን ላይ አጠናክረን በማስቀጠል የተረጂነት አስተሳሰብ በመቅረፍ የብልጽግና ጉዞ ማረጋገጥ ይገባል ፡፡

02/06/2024

የፅንፈኝነት አስተሳሰብን በማረም ህብረብሔራዊ አንድነትን እናፀናለን!

ጽንፈኝነት የነጠላ ትርክት ላይ ብቻ በመንጠልጠል በየእኔ ብቻ አመለካከት የታጠረ ህብረብሔራዊነትንና የወል ዕውነቶችን የማይቀበል አፍራሽ አስተሳሰብ ነው።፣ የእኔ ብቻ ትክክል ነኝ የሚልና ከእዛ ውጭ ያሉ ዕይታዎች ሁሉ እውነት አይደሉም ብሎ የሚያስብ የነጠላ ትርክት ዕሳቤ ነው ጽንፈኝነት።

ፓርቲያችን ብልጽግና የነጠላ ትርክቶችን በማረም አካታችና ሁሉን ዓቀፍ የሆ የፖለቲካ ስርዓትን መነሻ አድርጎ ኢትዮጵያን በህብረብሔራዊ አንድነት ለማጽናት እየሰራ ይገኛል። ጽንፈኝነትን በመከላከል ብሔራዊ ገዥ ትርክትን በማስረጽ ለትውልድ የምትመችና የበለፀገችዋን ኢትዮጵያ ለማየት የሁላችንንም ጥረት የሚጠይቅ ነው።

ብልጽግና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ዕውንነት አብቦ የብሔር የሕዝቦች መስተጋብራዊ አንድነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የጋራ ብልፅግናን ማስፈን እንዲቻል ሁሉም ዜጋ በመደመር ዕሳቤ የወል ዕውነቶችን ማጽናትና ማስቀጠል ይገባል። ችግሮቻችን ሁሉ በወንድማማችነትና እህትማማችነት በጋራ በመፍታት ከዋልታረገጥ አስተሳሰብ በመላቀቅ የጋራ የሆነች የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ።

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

22/05/2024

በልጆቿ ትጋት የደመቀች ከተማ :- አዲስ አበባ

ብልጽግና በትልቁ የሚያስብ ፤ ያሰበውን በጥራትና በጊዜ የሚፈጽም ፤ ዛሬ ላይ ነገን ጭምር የሚገነባ ፤ ተሻጋሪ ሀሳብ ያለው የትውልድ ፓርቲ ነው። በዚህም የትጋትና የልህቀት ዕሳቤ እንችላለን ብለን ብቻ ሳይሆን ችለንንና ሰርተን አጠናቀን ሪቫኖችን በመቁረጥ ለትውልድ የሚተርፍ አሻራን ማስቀመጥ ችለናል።

አዲስ አበባ በህብረብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ሰላሟን ያጸናች፣ የመደመር ዕሳቤን አንግበው ቀን ከለሊት ለብልጽግናዋ በሚተጉ ልጆቿ አንደስሟ እየደመቀች ያለች አፍሪካዊት የተሞክሮ ማዕከል እየሆነች የምትገኝ ውብ ከተማ በመሆን ላይ ነች።

የፓርቲያችን ዓላማ ሁለንተናዊ ብልፅግናን በሚያረጋግጥ አካታች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ሁለንተናዊ ተምሳሌት መሆን ነው። አድስ አበባ የዜጎችን ማህበራዊ መስተጋብር የሚያስተሳስርና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት
የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን በላቀ ትጋት በማከናወን ቃልን በተግባር የሚያስመሰክር ዘላቂ የሆነን ሁለንተናዊ የብልጽግና ተምሳሌትነትን የሚያበስር የኮሪደር ልማት ስራ በፍጥነትና ጥራት እየተሰራ ይገኛል።

ብልጽግና ባስቀመጠው ግልጽ ራዕይ መሰረት የከተማዋን ታሪክና ስም የሚመጥን ከፍታ ላይ በማድረስ የአፍሪካ መዲናነቷን የሚያፀና የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ፣ የዲፕሎማሲ ስበት ማዕከል ለማድረግ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችና ሰውተኮር ልማቶች ተከናውነዋል።

አሁን በፍጥነትና በጥራት በነዋሪዎቿም ትብብር በመሰራት ላይ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ከተማችን አዲስ አበባ የሚመጥናትም የሚገባትም ብልፅግና መሆኑን ያስመሰከረና አጠቃላይ ገፅታን በመቀር ለነዋሪዎቿ ምቹና ፅዱ የሚያደርጋት ይሆናል።



22/05/2024

አዲስ አበባ በትጉህ ዕጆች እየለማች፣ በታታሪ ነዋሪዎቿ ሰላሟን በማፅናት ለትውልድ በሚሻገር ምንዳ ሀገራዊ የመደመር ውጤትና አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ትሆናለች!!

ትጋት ፣ ቁርጠኝነት ፣ ህብረትና ፣ ትውልድ ተሻጋሪነት የፓርቲያችን የመደመር እና የብልፅግናችን የስኬት ጉዞ መገለጫዎች ናቸው። ብልጽግና የትውልድ ፓርቲ በመሆኑ በመደመር መርህ በትውልድ ቅብብሎሽ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ያፀናል። በዚህም በከተማችን እየተተገበሩ የሚገኙ የልማት ስራዎች ዛሬን ከነገ ጋር የሚያስተሳስሩና የትውልድን አሻራ ለዘመናት የሚያሸጋግሩ ጥራትና ፍጥነትን ያማከሉ ናቸው።

ነገን ታሳቢ ያደረጉ የከተማዋ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች፣ ጽዱና ውብ የሆኑ የትራፊክ ፍሰትን የሚያሳልጡ አደባባዮቿ ፣ ታላላቅ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ፣ የሳይንስናቴክኖሎጂ የምርምር ተቋማት ፣ የታሪክና ባህል ሙዚየሞች ፣ መናፈሻዎች ፣ በመሪዎቿ ድንቅ ዕሳቤና ትጋት እየተተገበሩ የሚገኙት የጫካ ፕሮጀክትና የኮሪደር ልማት እውነትም ቃልን በተግባር የሚያፀና የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የመሆን ግስጋሴያችንን የሚያረጋግጡ የፓርቲያችን የአስተሳሰብና የተግባር ውጤት ማሳያ ናቸው።

በመደመር የትጋት ዕጆች እያበበችና እየደመቀች የመትገኘዋ አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ህይወት በሚያሻሻል መልኩ ስሟንና ታሪኳን በሚገልጽ ከፍታ ተዋዳዳሪና የትኩረት ማዕከል መሆን ችላለች።

በዚህም የነበረውን የስራ ባህል በመለወጥ 7/24 የነቃችና በስራ ላይ ያለች ከተማ በማድረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብሮችን በማሳለጥ ተደጋጋሚ የሆኑ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናንና ሽልማቶችን ወስዳለች።

በአጠቃላይ በህብረ ብሔራዊነት የፍቅርና የሰላም ከተማ የሆነችዋ ከተማችን የአፍሪካ መዲና እና የዓለም ዲፕሎማቲክ የስበት ማዕከል መሆኗን የሚያጎሉ ስራዎች ላይ ነች። አዲስ አበባ በልጆቿ ደምቃ፣ በትጉህ ዕጆች እየለማች፣ በታታሪ ነዋሪዎቿ ሰላሟን በማፅናት ለትውልድ የሚሻገር ምንዳን በማስቀመጥ የወል እውነት የሆኑ ልማቶቿን አሳልጣ ሀገራዊ የመደመር ውጤትና አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት ትሆናለች።



13/05/2024

ትውልድን ማነፅ ሀገርን በማይናወጥ መሰረት ላይ መገንባት ነው!

ሀገር የትውልድ ቅብብሎሽ ውጤት ነች። ትውልድ ከተጣመመ ሀገር አትቃናም፤ ትውልድ ከወደቀ ሀገር አትበለጽግም፤ ያለትውልድ የላቀ ዕሳቤ ሀገራዊ ብልጽግናን ማሳካት አይቻልም። ከዚህ አንፃር ብልጽግና ፓርቲ ሀገራዊ ሁለንተናዊ ለውጥን ማሳካት የሚቻለው ትውልድ ላይ ሲሰራ መሆኑን በማመን ዘርፈብዙ ትውልድን የሚያንፁ ስራዎችን በመስራት ላይ ነው።

ብልጽግና ፓርቲ መነሻው ሰው ተኮር ዕሳቤ ሲሆን በመደመር ዕሳቤ ትውልድን በማነፅ ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞን ዕውን ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ሀገር የምትቀጥለው በትውልድ ቅብብሎሽ በመሆኑ ትውልድን በማነጽ ሀገራዊ ብልጽግናን ማጽናትና ማሻገር ይቻላል፤ ይጠበቃልም።

የኢትዮጵያ የአፍሪካ እና የዓለም ሁለንተናዊ ብልፅግና ተምሳሌትነት የሚረጋገጠው ትውልድን ራዕይ ሰንቆ በተሻለ አስተሳሰብና ዕውቀት በመገንባት ሀገር ተረካቢነትን ማስቀጠል ሲቻል ነው። በመሆኑም አዲስ አበባ የሁለንተናዊ ብልጽግና ተምሳሌት ትሆን ዘንድ ለትውልድ ምቹና ተስማሚ በማድረግ ህጻናት በጥሩ ስነ-ምግባር፣ በዕውቀትና ክህሎት ተቀርጸው የሚያድጉባት በማድረግ ነው። ለዚህም የእናቶችና ህጻናትን ማዕከላትን በመገንባት የተመጣጠነ ምግብ ፣ የትምህርት ፣ የጤና እና የስነ ልቦና ግንባታ እንዲያገኙ ተደርጓል።

ብልጽግና ፓርቲ ትውልድን መገንባት ሀገርን መገንባት መሆኑን በፅኑ ያምናል። ይህ ከፅንስ ጀምሮ የሚደረገው የትውልድ ግንባታ ሂደት ትውልድን በተስተካከለ የጤናና ስነ-ምግባር ሁኔታን በመፍጠር ብቁና ሀገር ተረካቢ ዜጋን ለማፍራት ያስችላል። ትውልድን መገንባት ነገን በጽኑ መሰረት ላይ ማነጽ ነው፤ ዛሬ አብዝተን የዘራነው መልካም ዘር ነገ መልካም ፍሬዎችን እንድናጭድ የሚያስችል ለሀገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው ነው፡፡

ፓርቲያችን ትናንትን ከዛሬ በማስተሳሰር የነገዋን ኢትዮጵያ ተስፋና ብልጽግና ራዕዩ አድርጎ ይሰራል፤ ዛሬን መስራት ለነገ ምንዳ ነው። ለትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ፕሮጀክቶችን መስራት የፓርቲያችን መገለጫ ነው። በዚህም መነሻነት የፓርቲያችን ማህበራዊ ፕሮግራም መሰረት የጤናና ትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ በመስራት ለህጻናት ምቹና ተስማሚ ማቆያዎች፣ የመጫዎቻ ቦታዎችና ተቋማትን በመገንባት ጥቅም ላይ ውለዋል።




Prosperity Party Yeka Branch - ብልጽግና

09/05/2024

ትምህርት ቤቶች ትውልድ የሚገነባባቸው የልህቀት ማዕከል ናቸው!

ለተተኪው ትውልድ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን እውን እናደርጋለን በሚል ዕሳቤ በየካ ክ/ከተማ በሚገኙ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ፕሮጀክቶችን በ90 ቀናት ዕቅዶች መፈጸም ላይ ይገኛል

በዚህም በደጃዝማች ወንድይራድ ቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለመተግበር የህፃናት መጫወቻ፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመሰብሰብ አዳራሽን ጨምሮ ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ እየተካሄደ በመሆኑ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በየጊዜው በአካል በመገኘት ድጋፍና ክትትል እያደረጉ ይገኛል።

ትምህርት ቤቶች በትውልድ ግንባታ ምትክ የለሽ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ ፓርቲያችን ብልጽግና የትምህርት ተቋማት ልማት ላይ ባለው ቁርጠኛ አቋም ያለዉ በመሆኑ ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን ስኬት ትውልዱን መቅረፅን አጠናክሮ ይቀጥላል። በዚህም የየካ ክ/ ከተማ አስተዳደር ህዝቡን በማወያየትና ጥያቄዎችን ተቀብሎ ፈጥኖ ወደ ስራ በመግባት የመማሪያ ክፍሎችና የመምህራን ቢሮዎች፣ የህፃናት ማቆያ፣ የመፀዳጃና ተጨመሪ የማንበቢያ ላይብረሪዎችን ያካቱቱ ህንፃዎችን ገንብቶና አዘምኖ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ማስቀጠል ችሏል።

የትምህርት ዘርፍ ላይ ከተሰሩ በርካታ ስኬቶች መካከል የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚነትና ሽፋንን ማሳደግ በመቻሉ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና ተሳትፎ ከማሳደጉም በላይ ከተማችን አድስአበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ሽልማት ተችሮታል። የብዝሃ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ስርአተ ዝርዝር በማስተግበርና የመማሪያ ቁሳቁሶችና ግብዓቶችን በማሰራጨት ጥራትን መሰረት ያደረገ ትምህርት ተደራሽ ተደርጓል።

የእድገት መሰረትና የድህነት መዉጫ ቁልፍ ትምህርት ነዉ ብሎ የሚያምነው ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሃገር የትምህርት ዘርፉን ከገባበት ስብራት ለማዉጣት በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እና የፈተናን ኩረጃ ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጨምሮ ት/ቤቶች የንድፈሀሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር በተለይም በተቀናጀ የከተማ ግብርናና የፅዳትና ውበት ትግበራ የሀገር ዕድገት ተምሳሌት ይሆኑ ዘንድ አመርቂ ስራዎችን መፈፀም ተችሏል።

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

30/04/2024

ከምንም ነገር በላይ ለሰው ልጅ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ ሰላም ዋነኛ ነገር ነው፡፡ ከሰላም ውጭ ቤተሰብም ይሁን ሀገር ሊረጋጋ አይችልም ስለዚህ ሰላም ለግለሰብም፣ ለቤተሰብም፣ ለማህበረሰብ በአንድ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች ፍላጎታቸውንና አላማቸው ለማሳካት የሰላም ያህል ዋጋ ያለው ነገር የለም፡፡

የወረዳችንን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ለረጅም አመታት ህብረተሰቡ ይገለገልበት የነበረው ፖሊስ ጣቢያ ከአከባቢው እሩቅ በመሆኑ ህብረተሰቡን ለተጨማሪ እንግልት ሲዳረግ በመቆየቱ ምክንያት የወረዳችን አስተዳደር ይህን ችግር ተገንዝቦ G+2 የፖሊስ ጣቢያ ግንባታ እያደረገ ይገኛል።

የፖሊስ ጣቢያው ግንባታ የወረዳው ባለሀብቶች እና ወጣቶች በበጎ ፈቃደኝነት አቅማቸው በፈቀደ መልኩ በጉልበትም፣ በገንዘብም፣ በማቴሪያልም አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እያደረጉልን ይገኛል ይህ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል እንላለን፡፡ ፖሊስ ጣቢያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ተወላጅና ባለሀብት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ወረዳ 02 ፓርቲ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን

30/04/2024

"በህብር ወደ ብልጽግና"

የብልፅግና ፓርቲ ዋና አላማ ህብረ ብሄራዊነቱን የጠበቀ እና የጋራ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያለው ማህበረሰብ መገንባት ነው።

ስለ ህብረ ብሄራዊነት ስናወራ ሁሉንም ብሔረሰቦችን፣ ኃይማኖቶችን ወይም ማንነቶችን ያካተተ ነገር ግን የትኛውንም ብሔር የማያገለል ማለታችን ነው።

የብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሄራዊነት በአሳታፊነት፣ ብዙሃነት እና አቃፊነት መገለጽ አለበት ብሎ ያምናል።

ህብረ ብሄራዊ አንድነት ብዘኃነትን እንደ ልዩ ሥጦታ ይመለከተዋል። ህብረ ብሄራዊ አንድነት የእርስ በርስ መተሳሰራችን መገለጫ እና የጠንካራ አንድነታችን ምልክት ነው። ህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያሳየው እጣ ፈንታችን በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ መቆም፣ መረባረብ እና ለጋራ አላማ መቆም እና መደጋገፍ እንዳለብን ነው።

ህብረ ብሄራዊ አንድነት የጋራ የማንነታችን መገለጫ፣ የአንድነታችን እና የጠንካራ ትስስራችን ምልክት ነው። የህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያሳየው እጣ ፈንታችን በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን ተገንዝበን በጋራ መቆም፣ መረባረብ እና ለጋራ አላማ መቆም እና መደጋገፍ እንዳለብን ነው።

ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ብዙ ሆነን አንድ አንድ ሆነን ብዙ በመሆን ለጋራ ዓላማና ተልዕኮ የተሰባሰብንበት አንድነት ነው።

በብዝሃነታችን ውስጥ እየበራን፣ በአንድነታችን ጠንክረን መገስገስ የውበታችንና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው።

ፍትህ ከተረጋገጠ ሰብአዊ ክብር ከሰፈነ ብልፅግና ከመጣ እንደ ሀገር ቀጣይነታችን ይለመልማል። ነገር ግን የጋራ ህብረ ብሄራዊነት እነዚህ ምሰሶዎች ከተሳኩ ብቻ ሳይሆን ለዓላማው መሳካት የበኩላችንን ሚና እንድንጫወት ስለሚያስችሉን "በጋራ ወደ ብልፅግና እንሄዳለን" በሚለው መመሪያ መሰረት ፓርቲያችን ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።

30/04/2024

የሁለንተናዊ ብልጽግና ተምሳሌትነት በየካ ክ/ከተማ የት/ቤቶች ማስፋፊያና ማዘመን ተግባር በዕምርታዊ ለውጥ ላይ ይገኛል!

በየካ ክ/ከተማ ሁለንተናዊ ብልጽግና ተምሳሌትነትን የሚያበስርና የትምህርት ተዳራሽነተን ለማስፋት የማስፋፊያና ማዘመን ተግባር ተከናውኗል። በክ/ከተማው ት/ቤቶችን በማስፋፋትና በማዘመን እውነተኛ የልህቀት ማዕከልና የትውልድ ግንባታ ተምሳሌት ይሆኑ ዘንድ ሰፊ ስራዎችን በማከናውን የጎላ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ለተተኪው ትውልድ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን እውን እናደርጋለን በሚል ዕሳቤ በየካ ክ/ከተማ በሚገኙ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ የማስፋፊያና የማዘመን ስራን መፈጸም ተችሏል።

ከነዚህም መካከል በወረዳ11 የሚገኝ የደጃዝማች ወንድራድ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተጠቃሽ ነው። ትምህርት ቤቶች በትውልድ ግንባታ ምትክ የለሽ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ ፓርቲያችን ብልጽግና የትምህርት ተቋማት ልማት ላይ ባለው ቁርጠኛ አቋም ያለዉ በመሆኑ ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን ስኬት ትውልዱን መቅረፅን አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም ክ/ከተማው በትምህርት ቤቶች የተማሪ መምህር ጥምርታን በማሻሻል ምቹ የመማር ማስተማር ሁኔታ እንዲፈጠር በትጋት እየሰራ ይገኛል።

የየካ ክ/ ከተማ የመማሪያ ክፍሎችና የመምህራን ቢሮዎች፣ የህፃናት ማቆያ፣ የመፀዳጃና ተጨማሪ የማንበቢያ ላይብረሪዎችን ያካቱቱ ህንፃዎችን ገንብቶና አዘምኖ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን ማስቀጠል ተችሏል። የመማሪያ ክፍሎችና የመምህራን ቢሮዎች፣ የህፃናት ማቆያ፣ የመፀዳጃና ተጨማሪ የማንበቢያ ላይብረሪዎችን ያካቱቱ ህንፃዎችን ገንብቶና አዘምኖ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን በውጤታማነት ተተግበሯል።

ትምህርት ቤቶች በትውልድ ግንባታ ምትክ የለሽ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ ፓርቲያችን ብልጽግና የትምህርት ተቋማት ልማት ላይ ባለው ቁርጠኛ አቋም ያለዉ በመሆኑ ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን ስኬት ትውልዱን መቅረፅን አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም ክ/ከተማው በትምህርት ቤቶች የተማሪ መምህር ጥምርታን በማሻሻል ምቹ የመማር ማስተማር ሁኔታ እንዲፈጠር በትጋት እየሰራ ይገኛል።

የእድገት መሰረትና የድህነት መዉጫ ቁልፍ ትምህርት ነዉ ብሎ የሚያምነው ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር የትምህርት ዘርፉን ከገባበት ስብራት ለማዉጣት በየካ ክ/ከተማ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ የየካን ከፍታ የሚያበስሩና የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሳደግ፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እና የብልጽግና ተምሳሌትነትን የሚረጋግጡ አመርቂ ስራዎችን መፈፀም ተችሏል።

የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትንማዕከል ያደረገው የፓርቲያችን ማህበራዊ ፕሮግራም መሰረት ትምህርት ቤት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ትውልድ ላይ የሚደርግ መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም የትምርትን ጥራትና ተደራሽነት የሚያረጋግጡ አመርቂ ስራዎች ተመዝግበዋል።

የትምህርት ቤቶች ደረጃ መሻሻል የትምህርት ጥራት ላይ አወንታዊ ሚና የሚኖረው ሲሆን አድስአበባን የሁለንተናዊ ብልጽግና ተምሳሌት የሚደረገውን ዕምርታ የሚያጎላ ነው። ክ/ከተማው ትምህርት ቤቶችን የማደስና ሌሎች ተግባራትን እያከናውነ ሲሆን የመማሪያ ክፍሎችን በመጨመር የተማሪ መምህር ጥምርታውን በማሻሻል ጥራትንና ተደራሽነትን የሚያጎለብት ይሆናል።

በአጠቃላይ የእድገት መሰረትና የድህነት መዉጫ ቁልፍ ትምህርት ነዉ ብሎ የሚያምነው ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር የትምህርት ዘርፉን ከገባበት ስብራት ለማዉጣት በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡ የየካን ከፍታ የሚያበስሩና የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እና የብልጽግና ተምሳሌትነትን የሚረጋግጡ አመርቂ ስራዎችን መፈፀም ተችሏል።

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Serkalem Abate posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share