Black Kingdom

  • Home
  • Black Kingdom

Black Kingdom Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Black Kingdom, Digital creator, .

07/12/2024
07/12/2024

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
***********

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

06/12/2024
06/12/2024
06/12/2024

ጉባኤው በጫካ የቀሩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በጫካ የቀሩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡ ጥሪ አቀረበ።

በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም ስምምነት በመፈጸማቸው የሰራዊቱ አባላት ወደ ካምፕ መግባት መጀመራቸው ይታወቃል።

የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም አማራጭን በመቀበሉ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል።

በጫካ የቀሩ የሰራዊቱ አባላትም ፈጥነው ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡም ጥሪውን አስተላልፏል።

ሰላም እንዲሰፍን የሃይማኖት አባቶች ጸሎት እና ምህላን ሲያደርጉ እንደነበር ያስታወሰው መግለጫው፤ በቀጣይነትም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጉባኤው የሰላም ግንባታ ላይ አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል።

06/12/2024
06/12/2024

አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ እስከ ጥር እንድቆይ የተደረገበት ምክንያት ውዝፉን ወደ ሌላ ስራ ለማዞር እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታል !!!!!!

በአሶሳ ዞን የአቡራሞ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ6(ስድስት) ወራት አፈፃፀም የአመራር ምዘና አፈፃፀም ሪፖርት፣የወረዳው የጄርባ አጥንት ለሆኑ ውስን አመ...
06/12/2024

በአሶሳ ዞን የአቡራሞ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ6(ስድስት) ወራት አፈፃፀም የአመራር ምዘና አፈፃፀም ሪፖርት፣

የወረዳው የጄርባ አጥንት ለሆኑ ውስን አመራሮች የተሰጠ ምዘና ግን እስቲ መመልከት ይቻላል ።

ይህ ማለት አቡራሞ ላይ ጠንካራ አመራርን ለማዳከም አካላቸው ጭፍን አመለካከት እንደሆነ ያመላክታል !!!!!!

06/12/2024
05/12/2024

የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር አካላት እና የፀጥታ ኃይሎች ሕጻናት እና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ በርካቶችን የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ በሚል በግዳጅ እንደያዙ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ አደረገ።
ከመከላከያ ሚኒስቴር የምልመላ መስፈርት ውጪ በግዳጅ የተያዙ ሕጻናትን እና ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ ጭምር እንዲከፍሉ እነዚሁ ባለሥልጣናት ማስገደዳቸውን ኢሰመኮ ባደረገው ምርመራ እንደደረሰበት ሐሙስ፣ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።
ኢሰመኮ ክትትል እንዳደረገባቸው ከጠቀሳቸው ስፍራዎች አንዷ በሆነችው ሻሸመኔ ዕድሜያቸው ከ18 በታች መሆናቸውን የተናገሩ ታዳጊዎች “ወታደራዊ ሥልጠና ትገባላችሁ” በሚል ማቆያ አዳራሾች መግባታቸውን አረጋግጧል።
በሻሸመኔ ከተማ ሃሌሉ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ማቆያ አዳራሽ ከነበሩ 32 ሰዎች መካከል 14 ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 አንደኛው ደግሞ 11 ዓመት መሆኑን ኢሰመኮ ባናገራቸው ወቅት መግለጻቸው ተጠቅሷል።
ከትምህርት ቤት ሲወጡ ከነዩኒፎርማቸው እዚሁ ማቆያ አዳራሽ እንዲገቡ የተደረጉ ሁለት የ15 ዓመት የ5ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁለት ሳምንት እንዳስቆጠሩ ገልጸዋል።
https://bbc.in/3VsbI95

05/12/2024
05/12/2024

📢 ከአማራ ኤፍ ኤም ደብረ ብርሃን 91.4 ጋር ይሥሩ 📻

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ይበልጥ ወደ አሉበት እየቀረበ ይገኛል!

በሬድዮ ዘርፍ የአማራ ኤፍ ኤም ደብረ ብርሃን 91.4 ሬድዮ ጣቢያ በየቀኑ በሚያሰራጨዉ የ 6 ሰዓታት ስርጭት ከበርካታ አድማጮች ጋር አብሮ ይገኛል፡፡

ከደብረ ብርሃን እና ሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች በተጨማሪ፦

👉 በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን የተለያዩ ወረዳዎች፣ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፣ ድሬዳዋና እና ምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ አካባቢዎች ጣቢያችን በጥራት ይደመጣል፡፡

ሬድዮ ጣቢያችን በየእለቱ ፦
በምዕራፍ አንድ ጠዋት ከ3 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት እና
በምዕራፍ ሁለት ከ8 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የተለያዩ አስተማሪና አዝናኝ ዝግጅቶችን ወደ አድማጮች እያደረሰ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ የቴሌቪዥን እና የማኅበራዊ ገፅ የዘገባ ሥራዎችን ጣቢያችን እየሠራም ይገኛል፡፡

በብዙ አካባቢዎችና በበርካታ አድማጮች በሚደመጠዉ ጣቢያችን ምርትና አገልግሎትዎን እንዲያስተዋዉቁ እንጋብዝዎታለን፡፡

ይደዉሉልን !
📞 011 6 81 1875
📞 011 6 81 2583

የአማራ ሚደዲያ ኮርፖሬሽን
📻 አማራ ኤፍ ኤም ደብረ ብርሃን 91.4 ሬድዮ ጣቢያ !

05/12/2024

በስሜን ወሎ ዞን በድሮን ጥቃት የ83 ዓመት እናት ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ “ ብልባላ” በተባለች መንደር ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በተፈፀመ የድሮን ጥቃት አንዲት የ83 ዓመት እናታቸው እንደተገደሉባችው የሟች ልጅ ተናገሩ። ሌሎች የዓይን እማኞች እንዳሉት ጥቃቱ በግል መኖሪያ ቤት ላይ የተፈፀመ ነው፣ ሌሎች ሁለት የጤና ባለሙያዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት የድሮን ጥቃቶች በተለያዩ አካባቢዎች በንፁሐን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ እንደሆነ የሰባዊ መብት ድርጅቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ገልፀዋል፣ በጥቃቱ ሠዎች ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም ብዙዎች ናቸው። ኅዳር 24/2017 ዓም ሌሊት 5፡30 አካባቢ በክልሉ ሰሜን ዞን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ብልብላ በተባለች መንደር በሰው አልባ አውሮፕላን መኖሪያ ቤታቸው ላይ በተፈፀመ ጥቃት የ83 ዓመት እናታቸው እማሆይ ደስታ ካክራው መገደላቸውን የሟች ልጅ እንደሆኑ የገለፁልን ቀሲስ ይትባረክ አድማሱ ነግረውናል።

ሌሎች 2 በግቢው ተከራይተው በሚኖሩ የጤና ባለሙያዎች ላይም የአካል ጉዳት ደርሷል ብለዋል፣ መጀመሪያ ላይ ድምፅ እየተመላለስ ሰላይ ላይ የሰማ እንደነበር የነገሩን ቀሲስ ይትባረክ፣ ሁኔታውን ለማወቅ ከቤታቸው ወጥተው በር ላይ ሲመለከቱ እጅግ የሚያስፈራ ድምፅና ፍንዳታ ግቢያቸውን ማናወጡን ተናግረዋል፣ በግቢያቸው ከነበሩ ክፍሎች መካክል 3 እንዳልነበር ሆነው ሲፈርሱ በጥቃቱ ከተመቱ ክፍሎች በአንዱ የነበሩት እናታቸው ሰጋቸው ተበጣጠሶ ህይወታቸው አልፏል ብለዋል።

ቀብራቸወንኳ በወና ባህል መስረት ፍትኃት ሳይደረግ መቀበራቸውን በእጅጉ ለስነልቦና ችግር መጋለጣቸውን አመልክተዋል፣ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተጨማሪ ጥቃት ይደርሳል ከሚል ሰጋት ህብረተሰቡ ተሰብስቦ ሥርዓቱን ማከናወን ባለመቻሉ መሆኑን ገልፀዋል።
በመኖሪያ ቤቱ አካባቢም ሆነ በግቢው ውስጥ ታጣቂዎች እንዳልነበሩ የገለፁልን ቀሲስ ይትባረክ፣ ግቢው ከዚህ በፊት የመኝታ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር ጠቅሰው ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ ግን ገበያው የተቀዛቀዘ በመሆኑ ከቤተሰብ የተረፉ ክፍሎችን ለመንግሥት ሠራተኞች ሲያከራዩ እንደነበር ተናግረዋል።

ጥቃቱ ከተፈፀመበት በቅርብ የነበሩ አንድ እናት አስተያየት ሰጪ በፍንዳታው ድንጋጤ ለደቂቃዎች ራሳቸውን ስተው እንደነብር ገልጠዋል። በፍንዳታው መጠነኛ ጉዳት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ መድረሱን አመልክተው፣ “እማሆይ ደስታ ካክራው” የተባሉ መነኩሴ በጥቃቱ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። ጥቃቱ በትክክል የድሮን ጥቃት ነው ያሉን ሌላ የዓይን እማኝ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶ ስለነበርና ድምፁን ስለምናውቅ፣ ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ስለመሆኑ ጥርጥር እንደሌላቸው ጠቅሰው በዚህ ጥቃት ሌሎች በግቢው ተከራይተው የነበሩ ሁለት የጤና ባለሙያዎች ቆስለዋል ብለዋል። አስተያየት ሰጪዎቹ የድሮን ጥቃቱ ታጣቂዎች በአካባቢው በሌሉበት ግለሰብ ቤት ላይ የተፈፀመ እንደሆነ ነው የገለፁት።

ስለደረሰው ጥቃት ተጨማሪ አስተያየት ለማካትተ ለላስታወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ለዓለም ብርሐኔ ብንደውልም ሆነ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ብንጠይቅም ምላሽ አልሰጡም። የኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቨሪ የተባለን ተቋም ጠቅሶ ዶይቼቬሌ ሰሞኑን እንደዘገበው፣ ክሚያዝያ 2015 እስከ ሕዳር 2017 ባሉ ጊዜዎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች 54 የአየርና የድሮን ጥቃቶች ተፈፅመዋል፣450 ያክል ሠዎች ደግሞ ተገድለዋል። የአማራ ማሕበር በሰሜን አሜሪካ ደግሞ ከጥቅምት 5/2016 እስከ ሕዳር 14/2017 ዓ ም ባለው ጊዜ 125 የአየርና የድሮን ጥቃቶች መፈፀማቸውን፣ 754 ሠላማዊ ሠዎች መገደላቸውንና 223 ሠዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው መመዝገቡን ዶይቼ ቬሌ በቅርቡ ዘግቧል።

05/12/2024

'Qalbiin na tuqamte' - Obbo Taayyee
Obbo Taayyeen yeroo hedduu hidhaa seenaniiru.
Yeroo tokko hidhaa waggaa sadii booda barumsatti deebi’anii xumuran.
Haa ta'u malee, eebbaaf guyyoonni afur yoo hafan ammas irra deebiin qabaman.
‘’Halkan sana akka malee qalbiin na tuqamte. Keessattuu waan maatii kiyyaa yaadee baay’een ofitti aare,'' jedhan.
↪️ https://bbc.in/3ZDcQt6

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Black Kingdom posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share